Tuesday, September 25, 2012

የ«ተሐድሶዎች» አላማ ምንድን ነው?

ተሐድሶ የሚለው ስም አነጋጋሪ ከሆነ ሰንብቷል። በብዙዎች ዘንድም አሉታዊ ስም ሆኖ ይታያል።  ስሙን ለራሱ ያወጣ ወገን ባይኖርም፣ ስሙን ተቀባይ የሆነ ወገን ግን አልጠፋም። ተሐድሶ የሚል ስም የተለጠፈባቸው ወገኖች ቤተ ክርስቲያን ከእውነተኛው የክርስትና ትምህርት ወጥታ በስሕተት ትምህርት ውስጥ ትገኛለችና ስሕተቶቿን በማረምና የጣለችውን የከበረ እውነት በማንሣት ወደ ትክክለኛው መንገድ መመለስ አለባት የሚሉ ናቸው። እነርሱ እንዲህ የሚል አቋም ቢኖራቸውም፣ ተሐድሶ የሚለውን ስም ያወጡ ወገኖች ግን ከዚህ በተቃራኒው ነው የሚመለከቷቸው። ለሌላውም የሚያስተዋውቋቸው አፍራሽ ሀይል አድርገው ነው። በተደጋጋሚ የኦርቶዶክስን ቤተክርስቲያንን ለማፍረስና ፕሮቴስታንት ለማድረግ እየሠሩ ነው የሚል ክስ ሲያቀርቡ ነው የሚደመጠው። እውን የ«ተሐድሶዎች» አላማ ኦርቶዶክስን ወደ ትክክለኛው መንገድ መመለስ ነው ወይስ ወደፕሮቴስታንታዊ ማንነት መለወጥ?

በተሐድሶ ስም የሚነግዱ አንዳንዶች ባይጠፉም፣ በተቃዋሚዎቻቸው «ተሐድሶ» የሚል ስም የተሰጣቸው የቤተክርስቲያን ልጆች አላማ ግን፣ ተቃዋሚዎቻቸው እንደሚሉት ቤተክርስቲያኒቱን ማፈራረስና ወደሌላ ማንነት መለወጥ አይደለም። ቤተክርስቲያኒቱ ተሐድሶ በማድረግ ወደትክክለኛው መንገድ መመለስ አለባት የሚል ነው። ይህም በጽሑፎቻቸው ውስጥ በግልጽ ይታያል። በብዙዎቹ ተሐድሶኣዊ ጽሁፎች ውስጥ የተገለጠው ምንድን ነው? በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚቃረኑ የስህተት ትምህርቶች ከቃሉ ጋር እንዴት እንደሚቃረኑና እንዴት ወይም በምን መታረም እንዳለባቸው ማሳየት ነው። በተጨማሪም በኦርቶዶክስ አስተምህሮ ውስጥ የሚገኙ ትክክለኛ አስተምህሮዎችም በበጎ ጎን ይጠቀሳሉ። ይህም ለተቃዋሚዎቻቸው ባይዋጥላቸውም የእነርሱ አላማ ማደስ እንጂ ማፍረስ እንዳልሆነ ያመለክታል።

ከዚህ በፊት የተሐድሶ ጥያቄ እየተነሳ የነበረው «ተሐድሶ» የሚል ስም በተለጠፈባቸው ወገኖች በኩል ብቻ ነበር። አሁን አሁን ግን «ተሐድሶ»ን ይቃወሙ የነበሩ ወገኖችም ሁሉ ጥያቄውን እያነሱት ይገኛሉ። እነርሱ ለቤተክርስቲያን ተሐድሶ ካስፈለጋትም የሚያስፈልጋት ተሐድሶ የመዋቅር ወይም የአስተዳደር እንጂ የሃይማኖት ተሐድሶ አያስፈልጋትም የሚል አቋም ያራምዳሉ። በቅርቡ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከሰንደቅ ጋዜጣ ጋር ቃለመጠይቅ ያደረገው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ያስተጋባውም ይህንኑ ነው። እርሱ እንዳለው «… ይህች ቤተ ክርስቲያን በ21­ኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ ነው የምትገኘው። ስለሆነም 21ኛውን ክፍለ ዘመን የሚመጥን ሕግ፣ መመሪያና መዋቅር ሊኖራት ይገባል። ፓትረያርክ ለመሾም ከምትሮጥ ይልቅ በዚህ ላይ ጠበቅ ያለ አቋም ቢኖራት ነገሮች መልካም ይሆናሉ። እስኪ ይታይህ መንግሥት ለምን ያህል ጊዜ ነው መዋቅሩን ያሻሻለው? ቤተክርስቲያን ግን በፍጹም። አንዳንዶች የሃይማኖት ሪፎርም ጠያቂዎች ናቸው። አሁን ግን የሃይማኖት ሳይሆን መዋቅራዊ ሪፎርም ነው ነው የሚያስፈልገው።»

ከመጨረሻው አረፍተ ነገር እንነሳና ዳንኤል ሃይማኖታዊው ተሐድሶ መከናወን ያለበት አሁን አይደለም ወደፊት ነው የሚል ይመስላል። ዳንኤል ሁሌም ቢሆን ተሐድሶ የሚለውን ቃል መጠቀም አይፈልግም። ከዚህ ቀደም በማኅበረ ቅዱሳን ላይ በጻፈው ጽሑፍ ውስጥ ተሐድሶን “እንደ ገና መነሣት /ሬናይዛንስ/» ብሎ ነው የጠራው። ሰንደቅ ጋዜጣ ላይ ደግሞ «ሪፎርም» ነው ያለው። ዳንኤል ለምን ይሆን ከዚህ ስም የሚሸሸው? ግልጽ ነው። እርሱና ማኅበሩ «ተሐድሶ» የሚለውን ስም ለሌሎች ስለሰጡ እነርሱ ተጠቅመውበት ቢገኙ ጥያቄ ሊነሳባቸው ስለሚችል ነው። በተጨማሪም ታዲያ ሌሎቹስ ምን አጠፉ? እንዳይባሉም ነው። ስለዚህ «ተሐድሶ»ን በሌላ ስም እየሰየሙ መጠቀማቸውን ስራዬ ብለው ይዘዋል።

ምንም ይሁን ምን፣ የመዋቅርም ይሁን የሃይማኖት ቤተ ክርስቲያኒቱ ተሐድሶ እንደሚያስፈልጋት መታወቁ ዋና ነገር ነው። በዳንኤል አመለካከት ለቤተክርስቲያኗ የሚያስፈልጋት መዋቅራዊ ለውጥ ነው። እርግጥ መዋቅራዊ ለውጥ እንደሚያስፈልጋት ምንም ጥርጥር የለውም። መዋቅሯ ቢለወጥ ግን ምናልባት ዘመናዊት ቤተ ክርስቲያን ትሆናለች እንጂ፣ መንፈሳዊት ልትሆን አትችልም። ጊዜውን ያገናዘበና ከዘመኑ ጋር የሚያራምድ አሠራርን መከተል ለቤተክርስቲያን አስፈላጊ ቢሆንም፣ መንፈሳዊ ማንነቷ በእግዚአብሔር ቃል የሚመራ እስካልሆነ ድረስ ተሐድሶው ሰዎች የሚፈልጉት ብቻ እንጂ የእግዚአብሔር ሐሳብ ያለበት ነው ማለት አይቻልም። ስለዚህ ቤተክርስቲያን እየታደሰች መሄድ ያለባት በመንፈስ እንጂ በዘመናዊነት አይደለም።
ነገር ግን ቤተክርስቲያን ሃይማኖታዊ ተሐድሶ አያስፈልጋትም ወይ? ሃይማኖት የማይታደስ ነገር መሆኑ ይታወቃል። ይህ የሚሠራው ግን ሃይማኖቱ በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተመሠረተ ሲሆን ብቻ ነው። ሃይማኖት እየተባለ ስለተጠራ ብቻ ግን ተሐድሶ አያስፈልገውም አይባልም። በእግዚአብሐር ቃል ላይ የሰው ሐሳብ ተጨምሮበት ከተደበላለቀ፣ ከእውነት መንገድም ከወጣ ይህ ሃይማኖት ተሐድሶ ያስፈልገዋል። «የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም ዕውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን» ተብሎ እንደ ተጻፈ (2ቆሮ. 10፥5)። የእግዚአብሔርን እውነት የበረዘውና የከለሰው የሰው ሐሳብ መፍረስና የእግዚአብሔር እውነት መጽናት አለበት። «ተሐድሶ» የተባሉ ወገኖች ሐሳብና አላማ ይኸው ነው እንጂ ሌላ አይደለም።

ከእግዚአብሔር ለቅዱሳን አንድ ፈጽሞ የተሰጠችውንና (ይሁ. 3) ሰዎች በተለያየ ጊዜ የራሳቸውን ሐሳብ ጨምረው የበረዟትንና የከለሷትን ሃይማኖት ጥራት በእግዚአብሔር ቃል መሰረት ማደስና መጠበቅ ዋና ተልእኳቸው ነው። ይህ ተሐድሶ ካልተካሄደ በቀር፣ መዋቅራዊ ለውጥ ስለተደረገ ብቻ ቤተክርስቲያን ትስተካከላለች ብሎ ማሰብ የእግዚአብሔርን ሐሳብ መሳት ነው የሚሆነው።

በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ የቀናውን ሃይማኖት የበረዙና ቤተክርስቲያኗን ለመንፈሳዊ ኪሳራ የዳረጉ በርካታ ኑፋቄዎች አሉ። ስለሆነም የ«ተሐድሶዎች» አላማ በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተጨመሩ የስሕተት ትምህርቶች እንዲወገዱ፣ ሊጸኑ የሚገባቸው እንዲጸኑ፣ መሻሻል ያለባቸውም እንዲሻሻሉ እንጂ የእውነት ተቃዋሚዎች እንደሚያስወሩት ኦርቶዶክስን ለማፈራረስ የተነሱ ኃይሎች አይደሉም። እንዳንኤል «ተሐድሶ» ማለት እኛ የምንለው ብቻ ነው እንጂ «ተሐድሶዎች» የሚሉት አይደለም፤ ስሙም «እንደገና መነሳት ወይም ሪፎርም» እንጂ ተሐድሶ አይደለም ቢሉን ተቀባይነት የለውም። ይልቅስ ለቤተክርስቲያን የሚያስፈልጋት መንፈሳዊ ተሐድሶ እንጂ የመዋቅር ለውጥ ብቻ አይደለምና መጀመር ያለበት ከመንፈሳዊው ተሐድሶ ነው። የቤተክርስቲያናችን መንፈሳዊ ችግሮቿ ከተስተካከሉ ሌላው ቀና ነው። ስለዚህ ተሐድሶው ከመዋቅር ሳይሆን ከሃይማኖቱ ጉዳይ ይጀመር።

እዚህ ላይ ሃይማኖቱ ምንም እንከን የለበትም የሚል እንደሚበዛ አልጠራጠርም። ነገር ግን ሃይማኖታችን አስተምህሮአዊ ችግር እንዳለበት ማሳየት ቀላል ነው። የእመናተችን መግለጫ ጸሎተ ሃይማኖትና እርሱን የመሰሉ የሃይማኖት መግለጫዎች ናቸው። በዚህ ላይ የመሠረተው አስተምህሮም አምስቱ አእማደ ምስጢር ነው። ዛሬ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ እውነተኛ ትምህርት መስለው የተቀመጡትና አንዱን አማኝ ሌላውን መናፍቅ የሚያሰኙት ከዚህ ውጪ የሆኑት በየትኛውም የእምነት መግለጫ ውስጥ ያልተካተቱና ጊዜ ያመጣቸው የስሕተት ትምህርቶች ናቸው። አሁን የኦሪት ነገሮች በቤተክርስቲያናችን እንዲቀጥሉ የተወሰነው በየትኛው ጉባኤ ነው የትኛውስ የእምነት መግለጫ ነው የሚደግፋቸው። ባይሆን የገላውዴዎስ የእምንት መግለጫ ይቃወማቸዋል። ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚቃረን ሐሣብ ያላቸው አዋልድ መጻሕፍት በቤተክርስቲያን ውስጥ እንዲኖሩና የመጽሐፍ ቅዱስን ስፍራ እንዲቀመጡስ የተወሰነው መቼ ነው? ምነው ፍትሐ ነገሥቱ እንዲህ ያሉቱን የሐሰት መጻሕፍት እንደ እውነተኛ መጻሕፍት ወደቤተክርስቲያን ያገባ ቢኖር ይለይ ይል የለምን? መስቀል በደሙ ስለተቀደሰ ለፈጣሪ የሚቀርበው አምልኮትና ስግደት ይገባዋል የተባለውስ በየትኛው የእምነት መግለጫ ነው? ፍጡራን መልክ ተደርሶላቸው፣ ገድል ተጽፎላቸው እንዲመለኩስ የተደነገገው በየትኛው በየትኛው የእምነት መግለጫ ነው? በእውነት የቤተክርስቲያናችን ትክክለኛ እምነተ በጸሎተ ሃይማኖት እርሱን በመሰሉ የእምነት መግልጫዎች የተገለጠው ነው። በዚህ ላይ የተጨመሩና ከመጽሐፍ ቅዱስ ሐሣብ ጋር የሚቃረኑ ሁሉ  መታደስ አለባቸው። በጸሎተ ሃይማኖት ያልተካተቱና ሊካተቱ የሚገባቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐሳቦችም ስፍራ ሊሰጣቸው ይገባል። ከዚህ ውጪ ያሉትና እርሱን ተቃውመው የሚገኙት ሰው ሰራሽ ትምህርቶችና ልምምዶች ሁሉ ግን ሊወገዱ ይገባል። 

51 comments:

 1. go to hell with your tehadiso!!! this view doesnot hold water. who the hell are you to evaluate the church and judge on her beleif? what is your knowledge? how far are you from your father evils?
  no tehadiso in our belief!!!!

  ReplyDelete
 2. menafeqe asemesaye

  ReplyDelete
 3. yealeqochehene yemenafeqan werea kemetawera ezawe adarashachewe hedehe begeletse chefere!!!

  maneme yetewahedone emenete selemayechelat(yegehanem dejoche selemayecheluate) atelefa enedenanete seara bihonema dero ke 500 ametate befite matefate nebere!!!

  wedajea atelefa tehadeso protestant newe antem protestante nehe wedefit yemimetawe maebeale antenem terego yasewetahale .

  ateteratere nebiye ayedelehum gene protestant yalebachewe menefesu(yeseyetane mehonune libe bele yehea eyesus negne eyale behelemehe endihume be wenehe be adarashu yemimetabehe maletea newe) keshekasha silehone erasun yagaletalena newe!!!emenegne beneseha wede qedeme emenetehe temelese!!!!

  demo lenegerehe ma endehoneke enea aweqalehu!!!

  ReplyDelete
 4. WEY MENAFIKAN BENANTE BET TSIFACHIHU LIBACHIHU WULK BILOAL.

  ReplyDelete
 5. Aye Aba selamawoch, could you tell us how just this very idea,you wrote here, is diffrent from what anyother protestant follower claims? Did not they agree 100% with what you are talking about? Do not you think you are too late to foolish God's sheeps? The fact is, we not only know your objectives but also we know more and mor about our beloved Church teachings by now.We are working hard to get back all those you fooled. That all just proves you are not diffrent from any proper protestant. If you believe that is the right way, you are free to follow. But, God's word clearly tell you the fact that you will be punished as below:

  "Thus saith the Lord, Stand ye in the ways, and see, and ask for the old paths, where is the good way, and walk therein, and ye shall find rest for your souls. But they said, We will not walk therein." Jeremiah 6:16

  ReplyDelete
 6. ተሐድሶ የሚለውን ቃል በጽሑፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ያነበብኩት የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር መሻሻል ወይም ከወቅቱ የመንግሥት መመሪያ ጋር የቤተ ክርስቲያንን አመራር ለማስማማት የሚደረግ ለውጥ በሚል ትርጉምና መንፈስ ነው እንጅ እንዲህኛው ዘመን የቤተ ክርስቲያንን የአምልኮ ሥርዓት ለመቀየር ለሚታገሉ ወገኖች በመጥሪያነቱ አልነበረም ፡፡

  ስለዚህም ተሐድሶ የሚለውን ስም ፣ አስቀድመው የቤተ ክርስቲያን አስተዳደርን ለማሻሻል በሚል ፍቺ የተጠቀሙበት ስለሆነ ፣ እኒህ ኋላ መጥተው ፣ ትምህርቷና ሥርዓቷ ስላስቸገራቸው እንዲቀየር የሚሞግቱትን ጠበብት ፣ አሁንም ሌላ ተስማሚ መለያ ስም ቢሰጣቸው መልካም ነው እላለሁ ፡፡ ቀድሞውንም ሃይማኖት ልትታደስ አልተሰጠችንም ፤ ይህን መጠሪያ ደግሞ እነርሱም ሳይወዱትና ሳይፈቅዱት አላግባብ ስለተለጠፈባቸው በአስቸኳይ መስተካከል ይገባዋል ፡፡ አንተው ለምን አትሞክርም ማለታችሁ ስለማይቀር እንደ እኔ ከሆነ እስከ ዛሬ ከሚጽፉትና ከምናነበው ኘሮቴስታንታዊ /ሉተራዊ/ ኦርቶዶክስ ቢባሉ ፣ ዓላማቸውንና ትምህርታቸውን አጠቃሎ ስለሚገልጸው ተስማሚ ስማቸው ይመስለኛል ፡፡

  በተረፈ በቅርብ የሚታወቀውን ታሪካዊ ማስረጃው ስንመለከት ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከግብጾች የሞግዚት አስተዳደር ነጻ ስትወጣ ፣ አዲስ የአስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ ፣ የተደረገው የመዋቅር ለውጥና መሻሻል ተሐድሶ ይባላል ፡፡ እዚህ ላይ አሁንም ልብ ልንለው የሚገባ ቁም ነገር ሃይማኖት ከጥንት ጀምሮ አንድ ስለሆነች ፣ ፖለቲካን ተከትሎ የሚደረገው የመታደስ ለውጥ አልተመለከታትም ፡፡

  የንጉሡ አስተዳደር ፣ በአመጽ ሲወገድም ከደርግ ሥርዓት ጋር የሚስማማ አዲስ አስተዳደራዊ መዋቅር በማስፈለጉ ተሐድሶ ተደርጓል ፡፡ ነገር ግን በዚህም ቢሆን ሃይማኖት አልተለወጠችም ፡፡ ይህንንም እውነታ ለመመልከት በሦስተኛው ፓትርያርክ በዓለ ሢመት ስለተሐድሶ የተጻፈውን እንዲነበብ የመክፈቻ አድራሻው በቀጣይ ቀርቧል ፡፡

  http://ethiopianorthodox.org/amharic/archivee/historical/abunetekelehaimanotamharic.pdf

  ከገጽ 32 ጀምሮ ስለ ተሐድሶ ይመለከቷል ፡፡
  ስለዚህም ተሐድሶ ማለት የወቅቱን ፖለቲካ ተከትሎና አስማምቶ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደርን መቃኘት ማለት ነው ፡፡ ዲያቆን ዳንኤልም የጊዜውም ሥልጣኔ በፈጣን ሁኔታ እያደገ ስለመጣ ፣ ይህንኑ ተከትሎ መሻሻሉ የግድ ነውና ተሐድሶ ያስፈልጋታል ማለቱ የሚተቹት አባባል አይደለም ፡፡

  ReplyDelete
 7. Betam Yegermal eko...you put clearly their (Tehadiso) mission in our church. It shows totally to change the EOTC to protestant. if they said no need " Gedelat, sigidet lemskel..Awalid metsahifit...etc" "lotu sibehat" so where is the difference with protestant.

  These days you are highly revealing who you are without forced by anybody, this indicate that God is doing his job to get rid of your evil ideas within the church.

  Don't try one inch against our fathers and ancient religion you will never reach anywhere with your evil ideas. The laity knows now who you are, if you try then you will see....I know one true event somewhere in South Ethiopia, the whole laity in the city destroyed the protestant missionaries when they tried to preach at annuala Timiket venue. This is one of the simplest that happened. If you come in with reformation of the religion itself I will say, you are really in the wrong truck.

  Enquanm Bedenb Awekinachihu, lenegeru dirom Enawekachulen

  ReplyDelete
  Replies
  1. Yegermal eko...you put clearly their (Tehadiso) mission in our church. It shows totally to change the EOTC to protestant. if they said no need " Gedelat, sigidet lemskel..Awalid metsahifit...etc" "lotu sibehat" so where is the difference with protestant.

   These days you are highly revealing who you are without forced by anybody, this indicate that God is doing his job to get rid of your evil ideas within the church.

   Don't try one inch against our fathers and ancient religion you will never reach anywhere with your evil ideas. The laity knows now who you are, if you try then you will see....I know one true event somewhere in South Ethiopia, the whole laity in the city destroyed the protestant missionaries when they tried to preach at annuala Timiket venue. This is one of the simplest that happened. If you come in with reformation of the religion itself I will say, you are really in the wrong truck.

   Enquanm Bedenb Awekinachihu, lenegeru dirom Enawekachulen

   Delete
 8. በሃሳቡ ብስማማም፡ አሁን የሚያስፈልገው እውነተኛውን የኦርቶዶክስ ትምህርት መስጠት ነው የሚያስፈልገው። ስለማህበረ ቅዱሳን ማንነትና ሥራው በሚገባ የሚገለጠው እውነትን በማሳየት ብቻ እንጂ ስለነሱ ማውራት ከንግዲህ ቢያበቃ የሚሻል ይመስለኛል። ከንግዲህ የብሎጋችሁ ሰፊ ቦታ እውነትን ከሃሰት በማነፃፀርና ትክክለኛውን መጽሓፍ ቅዱሳዊውን ትምህርት በማስተማር የተሞላ ይሁን። ምክንያቱም ሰውን ነፃ የሚያወጣው ሃሰትን በማወቅ ሳይሆን እውነትን በማወቅ ነውና(ዮሃ.8፡32፣1ቆሮ.2፡1-5)። ለመሆኑ ትምህርተ ሃይማኖት እና የክርስትና ህይወት የሚለውን መጽሃፍ (ባልሳሳት በአባ አበራ የተጻፈውን)ተነጋግራችሁበት ታውቃላችሁ? ወገኖቼ ከንግዲህ በሚያንጸን ነገር እናተኩር። ህዝባችን እውነትን(ቃሉን) ተጠምቷል/ተርቧልና። እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ።
  በመድኃኒታችንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ወገናችሁ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. መቼ እውነት ተናግረው ያውቁና እንደዚህ ያለ ሀሰብ ታቀርባለህ። ማሕበረ ቅዱሳንን በተመለከተ የሚያወሩት ስለጠፋበቸው ወይም ማንነታቸው ስለተገለጠ ለማውራት ፋታ ቢያደርጉም ልጣስታውሳቸው ባትምክር እነርሱ እነደጥላ ነቅ እየፈለጉ መከተላቸው ልዩ ባህሪያቸው ነው። ወንድሜ ላንተም በዚያው መንገድ ለተጠመድህ ልቦና ይስጥህ ከማለት ውጭ ምን ይባላል።

   Delete
 9. heduna esilima wode tehadiso orthodox endimeles astemiru. egna bianis kiristian nen. kidimia lemisetewu kidima situ.
  hodamoch!

  ReplyDelete
 10. keep on dreaming EVER....

  ReplyDelete
 11. Tigermalachu Aba Selam Asemasaye

  ReplyDelete
 12. የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል ይባላል፡፡
  ፈረንጆች ቤተክርስቲይንን ድሮ ተቃውመው
  አሁን ምን ደረጃ ላይ እንደደረሱ እያየን ነው
  ቤተክርስቲይን ያላትን በጎ ነገር እንደ ሽንኩርት
  እየላጥን ባዶዋን ለማስቀረትና በመጨረሻም እምነት
  የለም ለማለት እትቸኩል
  ታያልህ አይቀረም በቅርብ ጊዜ እምነት የሚባል ይጠፋል
  ስለዚህ የዚህ ሰባኪ ባትሆን ጥሩ ነው፡፡
  ልብ ይስጥህ

  ReplyDelete
 13. weregna! seitan drom bihon yehaset abat new enantem kabatachihu ke diablos nachihuna ye abatachihun hasab tenagerachihu tadia Ye kiristosn ema keyet tametutalachihu. abatachihun eyesus kirstos stadergu yane ye ewnetegnawun ye geta eyesus timihirt tinageralachihu. lezih demo geta endiredachihu ensteliyalen.

  ReplyDelete
 14. ወሬኛ! ዲያቢሎስ ከመጀመሪያዉ ሀሰተኛ ነዉ የሃሰት አባትም ነዉ እናንተም ካአባታችሁ የወሰዳችሁትን ትናገራላችሁ፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስንማ ከየት ታመጡታላችሁ አይፈረድባችሁም እኮ፡፡ የእዉነተኛዉን ጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን ትምህርት ለማስተማርማ የእሱ ልጆች መሆን ያስፈልጋችሀኋል፡፡ እዉነተኛዉን ትምህርት ለማስተማርና የክርስቶስ ልጆች ለመሆን ትችሉ ዘንድ ጌታ አለማመናችሁን ይረዳ ዘንድ እንጸልይላችሁለን መቸም ጥፋታችሁን የሚወድ የለምና፡፡

  ReplyDelete
 15. yemayetawek yetekedene neger yelem berasachu seat manenetacehun geletacehwal.and teyake leteyekachu:
  1,keprotestant gar yalacehu leynet meden new?
  2,endemetelut tesaktolcehu hezbun betewesdut;MK befers enkwan hasetega aysedekemena terfachu menden new.yenefsacehu fesame ayasasebacehum?menfesawie sewes yewendemun gebena yenageral?abatocenes "yawaredal"?EBAKACEHU YERASEN NEFESEN KEMADAN YEMEBELT YELEMENA LENEFESACEHU ASEBU?PLESSSSSSSSSSSS

  ReplyDelete
 16. I think, the problem with the conservatives and the reformists is the intermingling of Culture (Tradition) and Dogma. Most of the people do not seem to know the difference between these two or they unconsciously intermingle them in their discourses. Whenever one gives speech in such matters one should always keep in mind that the culture of the church is created for the sake of dogma; it is never otherwise.

  In addition, because tradition (culture) is something which depends on people's understanding of the time as the consciousness of the people grows up it shall and should be reformed, corrected and perfected. There is no such a thing as perfect culture. No! The culture of any church is a result of the socio-economic and political dynamics of the time. So, as the world's economic, social and political systems are made by fallible human beings they are by default vulnerable to have failures and commit wrong doings. Yet, as the consciousness of the people grow and change through generational progress the society should always open its door for looking inside and criticize whatsoever there is to be criticized.

  Nationalist sentiment and unnecessary patriotism could be the biggest obstacles in such situation, particularly from those who don't see the difference between what shall be changed (tradition) and what cannot be (dogma). So the best way to realize the reform is to uncover and disclose the traditional things that are to be changed in a logical and humble way. Let the people see what is there to be changed to be reformed to be criticized and what to hold on. This needs thorough research and toil rather than writing a simple article. Learn from the other ancient churches, particularly from the Catholic church.

  The Catholic church reformed herself after summoning the amazing council, Vatican II, that took from 1963- 1965, and evaluated her 2000 years journey. When that amazing council was concluded after three years the church got all the blue print she needed to persevere through the storms of modernist and postmodernist society. Now she is trying to implement what she has got from that blessed council which literally reformed the church and made her to shatter her doors confinement that led the church to made herself recluse from the society and other Christian communities. Now, as I see it, she is growing in almost every aspect of Christian life despite anomalies among some of her clergy. She is trying to reclaim the secularized Europe to Christ once again. She is everywhere with all peoples of the world introducing the good news according to their culture.

  The Ethiopian Church should learn from this and revisit her 1600 history and evaluate what she has, what she has not and what she shall have to continue her mission to the next generation effectively. Make no mistake that, if she continues with the kind of unlearned clergy and severely disorganized state she won't be serving the coming highly secularized, sexualized and consumerized generation.

  If the Ethiopian Church continues to be like what she is today she will have the same fate like the Catholic church in Europe- loosing her flock to the cruel secularism. I wish this would never happen in this church.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Great analysis; I wish everyone in our church has your kind of outlook. Our church needs to reevaluate everything and if we're not willing to cope with change, then without a doubt our church will loose her flocks because of man made traditions. The core doctrine and dogma of the orthodox faith is completely biblical as our early church fathers taught us. But the problem is with the later writings. It completely contradicts the core doctrines of our orthodox faith and simply unbiblical.

   Delete
  2. My brother I give creidt for your analysis. But you can't compare apple and orange. Catholics are in the wrong was and they need more reform until the get back to the origin. Here is your problem.. There is only one and only one True church, the Oriental Ortdox Tewahedo Church does not need reform.
   To make short.. reform required for "church" that are defected form the truth... Ethiopian Orthodx Tewahedo Church will remain same as was following from the apostel..

   Delete
  3. To Anonymous @October 8, 2012 8:31 PM

   What makes you think that they are different from you? Have you ever try to examine their teachings? Have you ever tried to investigate the difference between the Churches? I wish if you could tell me. Calling oneself an orthodox doesn't make a person an Orthodox. Thanks to ecumenical efforts and the communication facility of 20th century now both sides have learned that there is no such a fundamental dogmatic difference between the churches. Today the difference between the Catholic church and the Orthodox churches is mostly administrative. Let me invite you to read the following documents from the following websites.

   www.vatican.va/.../rc_pc_christuni_doc_19730510_copti_en.

   http://www.vatican.va/archive/hist_councils/ii_vatican_council/documents/vat-ii_decree_19641121_unitatis-redintegratio_en.html

   I hope you will enjoy reading these documents.

   Delete
 17. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ምንም አይነት የሃይማኖት ተሃድሶ አያስፈልጋትም። ቅዱሳንን እንደየ ክብራቸው ማምስገንን እንጂ ማምለክ ብላ አንድም ቀን አስተምራ አታውቅም። ለመስቀልም አምልኮ እንዲደረግም አታስተምርም። እናንተ ግን ይችን ርትዕትና ንጽህት የሆንች ሃይማኖት እናድሳት ትላላችሁ። ይች ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ደም የተመሰረተች ናት። ቅዳሴዋ፣ መዝሙሯ፣ ገድላት፥ ሁለመናዋ የሚሰብከው ወንጌል ነዉ።
  "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እነርሱ ግን "አንሄድባትም" አሉ።" ኤርምያስ ፮፥፩፮
  ለእናንተም እግዚአብሔር አምላክ የቀደመችውንም መንገድ አሳይቶ በንስሃ ጎዳና ይምራችሁ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Tenagireh motehal. Bematawukew neger gebiteh kemezebarek zim bitil min alebet?

   Delete
 18. እግዚአብሔር ይባርካችሁ ወንድሞች።ማቅ ሥርዓተ ቅዳሴን በአሜሪካ አድሶታል!!!
  ለመሆኑ ተሐድሶ ስራ የሚሰራው ማነው ?
  መልሱ ማህበረ ቅዱሰን ነው። ለምን ብባል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስያን ሥርዓተ ቅዳሴውን በማደሱ ነው። ለምሳሌ በአሜሪካም ሆነ በሌሎች ውጪ ሀገር በሚገኑት የማቅ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በቅዳሴ ሰዓት የፓትርያርኩ ስም አይጠራም። የሀገረ ስብከቱም ሊቀ ጳጳስ ስም አይጠሩም። ይህ በራሱ ሥርዓተ ቅዳሴውን አድሰውታል ወይንም አሻሽሎታል ማለት ነው። ወገኖቼ የማቅ አባላት የሆኑት ካህናትም ሆኑ ዲያቆናት የሚገኙበት ቤተ ክርስቲያን የሀገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ ስም በቅዳሴ አገልግሎት አይጠሩም። አንዱ ካህን (ዲያቆን) ስጠራ ሌለው አይጠራም በአንድ መቅደስ ውስጥ ሁለት አይነት አገልግሎቶች ይካሄዳሉ በአንዳንድ ቦታው።በጣም ያሳዝናል። ማቅ በራሱ ሥርዓተ ቅዳሴውን አድሶታል።ሌሎችን ሰዎች ስም ግን በከንቱ ያጠፋል። ይህ ደግሞ እጅግ ትልቅ ስህተት ነው። በአሜሪካ አህጉም የሚደረገው ቅዳሴ በማቅ ቅጥረኞች ታድሶዋል።ገለልተኛ የተባሉትም የማቅ ቤተ ክርስቲያን ናቸው። ፓትርያርክ ስም ሆነ የሀገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ ስም በቅዳሴ ወቅት መጠራት ያዘዘው ሥርዓተ ቅዳሴ መጽሐፍ ነው። ታድያ የማቅ ካህናትና ዲያቆናት ተሀድሶን አማነው ተቀብለው እየሰሩበት አይደለምን? ። ይህ እውነተኛ ምስከርነት ነው። ህዝበ ሆይ በማቅ አትታለል ማቅ በአሜሪካ ምድር ቅዳሴው አድሶታል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. It's just acquisition. It shows you have never been on those churches... ??? what was the reason MK guys fight with you guys?

   Delete
  2. ከችኮላ የተነሳ የቃላት ድግግሞሽ በዝቶበታልና እባኮትን በድጋሚ ይጻፉ

   Delete
 19. Minew begilits protestant nen ("We are protestants") bitilu? Min asasebachihu?

  ReplyDelete
 20. Mk fake and criminal priest who have been with aids and stomach cancer his x girl that she got hiv transferd from him to her moved canada to hide her self. She is regularely zelebanose yibedat neber her name is Tedeye and an element of mk. Death to mk elements.

  ReplyDelete
  Replies
  1. "You" ,whom ever you are, should know how to comment on social media especially "religious" blogs like this one. How crap it is to dump such an explitive word in social media. Try to be ethical even if you don't care religious.

   Delete
  2. Diros keduruYe min Yitebekal? Nisiha giba...

   Delete
  3. Have you seen how aba selam is "balege" they post such a nonsense and crab comments. shame on you the bloger!

   Delete
 21. "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እነርሱ ግን። አንሄድባትም አሉ።" ትንቢተ ኤርምያስ ፮፥፩፮
  አባቶቻችን ያስተማሩንን የቀደመችዉን ሃይማኖት ልናድሳት አንችልም።እርሷ በክርስቶስ ደም የተመሰረተች ናትና። የገሃነም ደጆች ከቶ አይችሏትም።

  ReplyDelete
 22. እባካችሁ ለደቂቃ መልካም ነገር አስቡ፡፡ እንኳን ኦርቶዶክስ ነን የሚሉ ሰዎች ይህን ጽፈው ይቅርና ፕሮቴስታንቶች ቢጽፉት ፣ ስድብን ምን አመጣው? ሀሳባቸው ልክ መስሎ ካልታያችሁ በተገቢው መንገድ መጽሐፍትን አጣቅሳችሁ መልስ ስጡ ፣ ተማማሩ፡፡ ይሕን ትታችሁ ስድብ ስትጽፉ ፣ እውነተኛ የእናንተን ማንነት እየተናገራችሁ ነው፡፡

  ReplyDelete
 23. የተሐድሶዎች አላማ በእርግጥም ኦርቶዶክስን ወደ ትክክለኛው መንገድ መመለስ ሳይሆን ወደፕሮቴስታንታዊ ማንነት መለወጥ ነው ።

  ReplyDelete
 24. ቤተክርስትያን ሰዉን በመንፈስ ቅዱስ ታድሳለች እንጂ እርሷ አትታደስም።

  ReplyDelete
 25. ወሬማ ወሪያችሁን ንዙ ሌላማ ምን ትይዙ ሞኝ የለቱን ብልህ ያመቱን እንደሚባለው ተሓድሶና ማቅ
  ተብዮዎች አንድኛው ድል ሁለትኛው ብዕል(ሀብት)ለማግበስበስ(ለማግኘት)ካልሆነ በስተቀር የሀይማኖትና
  የእምነት ትርጉም ምሥጢርና ዘለቄታስ ይቅርና ንባቡን በሙሉ ዓይን የተመለክታችሁት አይመስልም እናም
  ሕዱሳን--ቅዱሳን ሳትታደሱና ሳትቀደሱ ታድሰናል ተቀድሰናል እናድሳለን እንቀድሳለን እያላችሁ ወሬ ከምትዘረዝሩ ራሳችሁን መርምሩ ለቤተ ክርስቲያን አድነት ተባበሩ አለዚያ ግን ሰዎችን አታደናቁሩ!

  ReplyDelete
 26. Egziabher and gize le kidusan fetsimo silesetat haimanot enigadelalen. Kidist Sinidu ORTHODOXAWIT TEWAHIDO HAIMANOTACHIN nek yelebatim. PROTESTANT endasahw bidenefa rasunina meselochun yizo wede tilku eskigeba new.

  Amlake kidusan libona yistachihu.

  ReplyDelete
 27. Mk fffffff...u ...

  ReplyDelete
 28. ሰላም አባ ሰላማዎች የክርስቶስ ሰላም ሁልጊዜ ከእናንተጋር እንዲሆን እየተመኘሁ ለማይገባው ደደብ ምንም ቢነገረው ስለማይሰማ፣
  ለሚሰማውና ለሚገባው ዘወትር ሳትሰለቹ የቃሉን እውነትና ትክክለኛ ክርስትናን መመስከር ይገባችሁል። ሊጠፋ የታዘዘ ከተማ ነጋሪት
  ቢጎሰም አይሰማ እንደተባለው ሆኖባቸው አንዳንድ ድፍን ቅሎች የሚሰጡትን አስተያየትና ቆሻሻ ስድቦችን ከምንም ሳትቆጥሩ ፀጋና
  ህይወት የምታገኙበትን እውነተኛ ምስክርነታችሁን እንድትቀጥሉ በእግዚአብሔር ስም እጠይቃችሁአለሁ። አንድ ቀን የብርሃናት ጌታ
  ብርሃኑን ሲያበራላቸው አይናቸው ተከፍቶ ይረዱታል። በሉ አባ ሰላማዎች ብዙ ብዙ ነገር መናገርና መፃፍ እየፈለግሁ ነገር ግን በዚች
  ጠባብ ቦታና ጊዜ አልችልም። በፊት በፊት በጣም እየተከታተልኩ የድጋፍ አስተያየቶችንም ቶሎ ቶሎ እፅፍ ነበር፣ አሁን አሁን ግን
  ከመፃፍ በጣምተቆጥቤ ነበር፣ ያም ሆነ ይህ ማለት የፈለግሁት አይዙአችሁ በርቱ በስውር የሚያይ አምላካችን በስውር ፀጋና በረከቱን
  እንዲሁም ምህረቱን በእናንተ ላይ ስላበዛ ደስ ይበላችሁ። ጠላት የሰይጣን ማህበር ማቅ እንደሆነ እንኩአን ለእኛ ለአምላካችንና ለጌታችን
  ለኢየሱስ ክርስቶስም ጠላት ነው። እናንተ ግን የቀደመውን ፍቅር ይዛችሁ ተመላለሱ።
  ትላለች እህታችሁ።

  ReplyDelete
 29. ወገኔ!

  የኦርቶዶክስን ቤተክርስቲያንን ማፍረስና ፕሮቴስታንት የማድረግ አላማ እንዳላቸው በሕይወቴ ያሳለፍኩትን (የተሳተፍኩትን)ከ17 አመት በላይ የወነ ተመክሮ፤ ማለትም ስልጠናን ጨምሮ ...አለኝ። ከእኔ በላይ ደግሞ ፈረንጅ ፕሮቴስታንት ሳይቀሩ መስክረዋል። http://www.youtube.com/watch?v=zu8BLzlQ82M

  ተሐድሶዎች(ፕሮቴስታንቶች) የፈለጉትን ይበሉ። ኦርቶዶክስያዊያን ግን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጌቶች ጌታ የነገስታት ንጉስ ነው!

  ReplyDelete
 30. የተሐድሶ እንቅስቃሴ በውስጥም በውጭም እንደት እንደጀመረና ዓለማውም ምን እንደሆነ ከጀርባው ከሚያሽከረክራ ኃይል ጭምር እናውቃለን፤ ለምን ማኅበረ ቅዱሳንን ጠምደው እንደያዙትም እንረዳለን፤ ለወደፊት በምን ዓይነት ስልት ሊንቀሳቀስ እንደሚችልም የተረዳን አንጠፋም፤ ምክንያታቸውም ምን እንደሆነ የፈታተሸን ሰዎች ሞልተናል፡፡ እውነት እንነጋገር ከተባለማ የተሐድሶን ዓላማና የመንቀሳቀሻ ስልቱን ማንና ለምን እንደነደፈው የተሐድሶ አንቀሳቃሾችም አያውቁትም ፤ እናውቃለን የሚሉትም መስሏቸው ነው፡፡ አንድ ነገር ልጠቁማችሁ የተሐድሶ ሰንሰለት ከስውድን ወንጌላዊት ቤ/ክ (1920ዎቹ አ.አ. ውስጥ ቤ/ክ ከፍተው ብዙ ወጣቶችን ፕሮቲስታን ለማድረግ ጥራለች፤ በአሁኑ ሰዓት ግን የስውድን ወንጌላዊት ቤ/ክ በምሥጢር የሠይጣን አምልኮን ታራምድ አንደነበር መረጃዎች ተገኝተዋል) እስከ ቤተ ክህነት የደረሰ ነው፡፡ ለማንኛውም ወደፊት የተሐድሶ እንቅስቃሴ ምንጭ፣ አካሔድ፣ ታሪካዊ ዳራ፣ ዓላማና ማንነት በመረጃ ነጥሮ ሲቀርብ ከውስጥ ያሉትም ቢሆኑ ራሳቸውን አርመው ያስተካክላሉ የሚል እምነት አለኝ፡፡ ለአሁኑ ቁርጠኛ እንቅስቃሴ እያካሄዱ ያሉት አባላቱ እንዳይደነግጡ ይቆየን!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ጉረኛ፤- እንኩአን ለዲንቢጥ ለዝሆንም አንደነግጥ- የፈለጋችሁትን ሥም ብትሰጡንና ብትፈራገጡ፣ ለሌላው ለማስጠላት ውሸቱን ሁሉ
   በክፉ ብትናገሩ፣ አምላካችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእያንዳንዳችንን ውስጥና ውጭ በድንብ ስለሚያውቅ ብዙ አትቸገሩ።
   ያመነውን አውቀናል የቆምንበትን አለት፤ ፅኑ ነው መሠረቱ የታመነ ነው ከጥንቱ። እሱ ያውቀናል ምን አስጨነቃችሁ። በሌላው
   የክርስትና ህይዎት ውስጥ ምን አገባችሁ። አንድ ሰው የፈለገውን የመሆን ነፃነት እኮ በእግዚአብሔር ዘንድም ተሰጥቶአል። ታዲያ
   እናንተ አንዴ ተሃድሶ ፣አንዴ ደግሞ መናፍቅ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ተቀንጥሶ፣ ተበጥሶ እያላችሁ ህዝበ ክርስቲያኑን ከእግዚአብሔር ቤት
   ለማሸሽና በሰዎች መካክል ክርስቲያናዊ ፍቅር እንዳይኖር ለማድረግ እንቅልፍ እስክ ማጣት ድረስ መጫር ምን ይሉታል ጌታችን
   እንኩአን እሳትና ውሀ ቀርቦልሃል፤ እጅህን ወደ ፈለግህበት ላክ አይደል ያለው ስለዚህ ሰዎች ያልበላቸውን ጀርባ በግድ ልከክላችሁ
   አትበሉ። እንኩአን ክርስቲያኖችን እስላሞችንም ቢሆን እንደእምነታቸው ማመን ይችላሉ እንጂ ፤ አንተ እንዲህ ነህ አንቺ እንዲያ ነሽ
   አንተ ልክ አይደለህም እኔ ልክ ነኝ በማለት ጉንጫችሁን ባታለፉ መልካም ነው። ምክር ለመስጠት ያህል ነው ። ካስተዋላችሁ እኛን
   ፍቅር የሚያሳጣን ፤ በማያገባን ነገር ውስጥ ስንገባ ነው። ማለትም በሰው የግል እምነትና ህይወት ወስጥ ስንገባ ነው። እስቲ ሌሎች
   አለሞችን ተመልከቱ በግል እምነትና በግል ህይወት ውስጥ ገብተው አይበጣበጡም። ለምን አናስተውልም የሰይጣንን ሥራ እኮ እየሰራንለት
   መሆኑን አንዘንጋ። በሌላ ጊዜ እስክንገናኝ ድረስ ደህና ሁን\ኝ።

   Delete
 31. Advicable message to all Eotc that working for change from traditional way to real biblical foundation, we need reform guys. It is time shermuta monk such like tebate and,zelebanose hurt followers , because no strong regulation to punishing them otherwise keeping them life of stupidity. So, the,master key point is reform or tehadesso from traditional to christological doctrine. The criminal monk is good example for us. They have two hut one spritual, the other is hypacrite. We need reform now.

  ReplyDelete
 32. we need change or reformation in our church. No body said anything regarding the church dogma but so many things against the traditional orders. you need to differentiation between dogma and kenona(orders). kenona, is changeable anytime, that why need to reform or tehadiso in our traditional church. no body obeying the old system of the church,including the church leaders. if you not obeying the kenona, why we do reforming ? Please do not cheat your self. be open mind for good thing to use and accept.

  ReplyDelete
 33. Ine yemilew.... yekedemew timihrt yemitilut/ weym lematat yemtasibut timihier ' sidbna wuchet nebere malet new manfesawinet..?
  / mechem yihenin inantew tawkutalachihu...

  ReplyDelete
 34. Behaiemanot abew kamenachehu lemesekelu ensegedalen yemilewenem mekebel alebachehu

  ReplyDelete
 35. Daniel Said....አንዳንዶች የሃይማኖት ሪፎርም ጠያቂዎች ናቸው። አሁን ግን የሃይማኖት ሳይሆን መዋቅራዊ ሪፎርም ነው ነው የሚያስፈልገው።
  You guys said...ከመጨረሻው አረፍተ ነገር እንነሳና ዳንኤል ሃይማኖታዊው ተሐድሶ መከናወን ያለበት አሁን አይደለም ወደፊት ነው የሚል ይመስላል
  As everybody see from the above, D/K Daniel never said relegious reform would needed for future !!! Please do not guess,lie and conclude what you wand to convey to others !!! Do not spoil names. Above all keep your former Religion always!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 36. እባካችሁ ንቁ አይናችሁን ተንኮል ጋርዶታል እቺን ቤተክርስቲያን ተከፍላ ካላየን አንተኛም ነው ግን ለምን እስቲ እራሳችሁን ጠይቁ ባላችሁበት እምነት እርካታ የላችሁማ ስሙ አንድ አባት ምን እንዳሉኝ ጴንጤ በሦስት ይከፊላል ግራጴ፣ ሆዳጴና አራጴ ግራየገባው፣ ሆዳምና አራዳ ጴንጤ እናንተ ግራጴ ናችሁ ግራ ገብችል ከቤተክርስቲያን እንዳትሆኑ ሴጣን እየተጠቀመባችሁ አለቅ ተብላችል ወደ ዛ እንዳትሄዱ የትኛው ጋር አይደል 245 ደርሶል የጴንጤ ቤተክርስቲያን እውነት የጌታ ወዳጅ ከሆናችሁ ጭራሽ በጌታ የማያምኑት ሙስሊሞች ጋር ለምን ሄዳችሁ ይህን ሥራ አትሰሩም ነገር ግን አላማችሁ ማፍረስ ስለሆነ ቤተክርስቲያን ስንዱ እመቤት ናት ያለቀላት በእግዜአብሔር ወንጌል የተገነባች በእምነት የተመሰረተች ባባቶች ደም የቆመች ነች ልፉ አመላክ አለላት ከእርሶ እየጨለፉ መመገብ እንጁ አንዲት ማድረግ አይቻልም ከላይ ጠባቂ አለላት ቤተክርስቲን ክርስቶስ የሞተላት ናት አንችላትም በሉት ለአባታችሁ ለሴጣን ኑ በንስሀ ተመለሱ ነተመለሱ ሁሉ ክፍት ነች እባካችሁ ስንት የተበላሸ የጴንጤ ቤት አለ አይደል ከራሳቸው መጽሔት የምናነብው በስላሴ እንን የማያምኑ እራሳቸውን በነቢይ ስም የሚጠሩና ሐዋርያት ነን የሚሉ አንዲት ተጋድሎ ሳያደርጉ እስቲ እነሱን አስተካክሉ ሂዱ ቤተክርቲያን ጥንቅቅ ያለች ነች እሲ ግራጴዎች በሉ እግዚአብሔር ልብ ይስጣችሁ፡፡

  ReplyDelete
 37. Thank you for your opinion,but we have possible and impossible things to accept now days there is great fighting between
  the sons of light and darkness not dogma and traditional
  orders

  ReplyDelete