Friday, September 7, 2012

ምሕላው ፎርማሊቲያዊ ወይስ ልባዊ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከጳጉሜን 1 - መስከረም 10/2005 የሚቆይ የሁለት ሱባኤ የምሕላ ጊዜ ማወጁን ሰምተናል፡፡ ምሕላው የታወጀው እግዚአብሔር በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ምትክ እርሱ ባወቀ ተተኪ ፓትርያርክ በመንበሩ እንዲያስቀምጥ ለመጠየቅ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ መግለጫው ቅዱስነታቸው በዘመናቸው በመንፈሳዊ በማኅበራዊና በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ሰፊ ሥራ የሠሩ አባት መሆናቸውን ጠቅሶ፣ በአገር ውስጥና በውጭ አገር በሚገኙ  አህጉረ ስብከት ያሉ አድባራት ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት ስለ ተተኪው ፓትርያርክ እንዲጸልዩ የሚያሳስብ ነው፡፡

ሲኖዶሱ ቤተክርስቲያን በዚህ ሁኔታ ውስጥ ስትገኝ የምሕላ ጊዜ ማወጁ የተለመደ ነው፡፡ ከሁሉ በፊት ቅድሚያ መሰጠት የነበረበትም ለዚህ ነበር፡፡ ይሁንና ሲኖዶሱ ሲመራ የነበረው ፍጹም መንፈሳዊነት በጎደለው አኳዃን በስጋና በደም ሀሳብ ነበር፡፡ ለጸሎት ቦታ የሌላቸው ብዙዎቹ የአሁኖቹ የሲኖዶስ አባላት የአቡነ ጳውሎስን ቀብር ለማበለሻሸት ከመሥራት አንስቶ በሚዲያ የሰጡትን መግለጫ እስከ መለወጥ የደረሰ የተዘበራረቀ ነገር ውስጥ ገብተው ተስተውለዋል፡፡ ከእድሜና ከጤና አኳያ በዐቃቤ መንበርነት ለመሥራት ብቁ ያልሆኑ አባት በመመደብና አጋዥ ያስፈልጋቸዋል በሚል በሽግግሩ ወቅት ያሻቸውን ለማድረግ እነአባ ሳሙኤልና መሰሎቻቸው ራሳቸውን መርጠውና ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመሆን እንዳሻቸው ለመሆን ተንቀሳቅሰዋል፡፡ አቡነ ሳሙኤል አቡነ ሉቃስ እና አቡነ ዝቅኤልየስራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎች ስለሆን የአዲስ አበባ አድባራትን አስተዳዳሪዎችን እና የጠቅላይ ቤተክህነት ሰራተኞችን ሰብሰብን ማናገር አለብን።የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ ያለሥራችሁ አትግቡ የሚል ተቃውሞ ገጥሟቸውም ነበር።  ሕግ እያለ ሌላ ሕግ እናውጣ እስከማለት የደረሰው የእነአባ ሳሙኤል ቡድን እርስ በርሱ መስማማት ሳይችል ሐሳቡ ሁሉ እየከሸፈና መያዣ መጨበጫ እየጠፋው ባለበት በዚህ ወቅት የምሕላ ጊዜ መታወጁ፣ ልብ ላለውና በትክክል ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ ለፈለገ ሰው ጊዜው አልረፈደም፡፡

ነገር ግን የምሕላው አላማ ምንድን ነው? እንዲህ ያለውን ምሕላ እግዚአብሔር ይሰማዋል ወይ? የሚሉት ጥያቄዎች መልስ ማግኘት አለባቸው፡፡ በቅድሚያ ምሕላ የሚደረገው የደንቡን ለማድረስ ማለትም ፓትርያርክ በሚሞትበት ወቅት ሌላ ፓትርያርክ እስኪሾም ምሕላ ይያዛል ስለተባለ የዚያን ፎርማሊቲ ለማሟላት ነው ወይስ በትክክለኛ ልብ እግዚአብሔር የራሱን ሰው ፓትርያርክ አድርጎ እንዲያስቀምጥ ወደ እርሱ ለመለመን? በልባችሁ የራሳችሁን ፓትርያርክ አስቀምጣችሁ ከሆነስ እኛን ምሕላ ያዙ የምትሉን?

ቤተክርስቲያኗ ያለችበት ሁኔታ ምሕላ የሚያስይዝ መሆኑ አይካድም ነገር ግን ምሕላ ለመያዝ ለምሕላ የተዘጋጀ ልብ ያስፈልጋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ በአባቶች ተከፋፍላ ባለችበት ሁኔታ በአገር ውስጥና በውጭ አገር ያሉት አባቶች ባልታረቁበት ሁኔታ ስለተተኪ ፓትርያርክ መጸለይ ምን ትርጉም አለው? ቃሉ፣ «እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ብታቀርብ፥ በዚያም ወንድምህ አንዳች በአንተ ላይ እንዳለው ብታስብ፥ በዚያ በመሠዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ፥ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ፥ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ። አብረኸው በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ ጋር ፈጥነህ ተስማማ፤ ባላጋራ ለዳኛ እንዳይሰጥህ ዳኛም ለሎሌው፥ ወደ ወህኒም ትጣላለህ፤ እውነት እልሃለሁ፥ የመጨረሻዋን ሳንቲም እስክትከፍል ድረስ ከቶ ከዚያ አትወጣም።» ነው የሚለው (ማቴ 5፥23-26)፡፡ በአገር ውስጥ ያሉት አባቶቻችን ግን በውጪ ከሚገኙት አባቶቻችን ጋር ሳይታረቁና የእርቁን ሂደት በሆነ ባልሆነው እያጓተቱ ምሕላ ያውጃሉ፡፡ በእውነት አባቶቻችንን በቃሉ ደፍረን እንዲህ እንላቸዋለን «አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም።» ገላ.6፥7፡፡

ምንም እንኳን በስጋና ደም ሐሳብ ስትመሩ ቆይታችሁ ወደ ምሕላ መመለሳችሁ መልካም ነገር ቢሆንም ምሕላው ልባዊና እግዚአብሔር የሚቀበለው እንዲሆን ለምሕላው ቢያንስ የሚከተለው ዝግጅት ያስፈልጋል፡፡ ይኸውም በውጪ ካሉት አባቶች ጋር መታረቅ ነው፡፡ ቢያንስ ይህ ጉዳይ ባልተስተካከሉበት ሁኔታ የሚደረግ ምሕላ ለፎርማሊቲ ያህል እንጂ እውነተኛ ምሕላ፣ ወደ እግዚአብሔርም የሚቀርብ ምሕላ ሊሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ ምሕላው የሠመረ ይሆን ዘንድ ልብሳችንን ሳይሆን ልባችንን እንቅደድ፤ ለታይታና ለይሉኝታ ሳይሆን ለቤተክርስቲያን በሚያስብ እውነተኛ ልብ ወደ እግዚአብሔር እንማለል፡፡
    
 


    


14 comments:

 1. ተንኮል ባይኖር ምህላ ዘረኝነት ባይፈጠር ሰላምና ፍቅር ይሰፍን ነበር ምህላውም በሠመረ ነበር ዳሩ ግን እያንዳንዱ በየጓዳው ተንኮልን በየመንደሩ ጎጠኝነትን እያወነጋገረ
  ምህላ ጸሎት ከባድ መቅሠፍት ነው፤ ሽማግሎችም(የማይሆን ጸሎት ለቅሥፈት)ይላሉ
  ይህ የምህላ አዋጅ የተቀበረ ፈንጅ ነው ያ ድንገት ፈንድቶ ጥፋት እንደሚያደርስ ይህም
  መጀመሪያ በውጭም በውስጥም ዕርቀ ሰላም ሳይሆን ደግ አባት ስጠን ማለት ምህላ ሳይሆን ድለላ ሆኖ ሌላ ተጨማሪ (የባሰ)መቅሠፍት ሊያስመጣ ይችላል፤እናም መቅደም
  ያለበት ዕርቅ ከዚያም ያባት ምርጫ ሊሆን ይገባ ነበር (ምንተ እንከ ንግበር?)

  ReplyDelete
 2. Degarege. Jel pente.

  ReplyDelete
 3. Enante Yefugnet Lejoch Nachehu. Erke Yematewodu Kefuewech. Betam Yemiasazine Blog new BEWNET WUSHETAMOCH NACHEHU. YEGZIZBHEREN KALE YEMETADERGUT ENGE EYAWAKACHEHUT YEMETESEMUT BICHA ATHUNU. BEWNET ENANTE MULICH YALACHEHU TEHADESOWOCH NACHEU. MENEM BEHONE SUBA IS SUBA NEW. LEBETEKRSTIAN TSELOT BEDEREG MEN KIFAT ALEW. SATAWKUTE BEZU ETHIOPIAWIAN WOGENACHEHUNE EYSZENACHEHUTE NEW.

  ReplyDelete
 4. ተንኮል ባይኖር ምህላ ዘረኝነት ባይፈጠር ሰላምና ፍቅር ይሰፍን ነበር ምህላውም በሠመረ ነበር ዳሩ ግን እያንዳንዱ በየጓዳው ተንኮልን በየመንደሩ ጎጠኝነትን እያወነጋገረ
  ምህላ ጸሎት ከባድ መቅሠፍት ነው፤ ሽማግሎችም(የማይሆን ጸሎት ለቅሥፈት)ይላሉ
  ይህ የምህላ አዋጅ የተቀበረ ፈንጅ ነው ያ ድንገት ፈንድቶ ጥፋት እንደሚያደርስ ይህም
  መጀመሪያ በውጭም በውስጥም ዕርቀ ሰላም ሳይሆን ደግ አባት ስጠን ማለት ምህላ ሳይሆን ድለላ ሆኖ ሌላ ተጨማሪ (የባሰ)መቅሠፍት ሊያስመጣ ይችላል፤እናም መቅደም
  ያለበት ዕርቅ ከዚያም ያባት ምርጫ ሊሆን ይገባ ነበር (ምንተ እንከ ንግበር?)

  ReplyDelete
 5. Asafere nachwe degimo beze geza ende ayenet ware taweralachwe ነገር ግን የምሕላው አላማ ምንድን ነው? እንዲህ ያለውን ምሕላ እግዚአብሔር ይሰማዋል ወይ? የሚሉት ጥያቄዎች መልስ ማግኘት አለባቸው men malet new? awen yeha Chiristina new betam tegermalchwe. enase lerase kale gebawe kawen bwala yehen Website lalemayete enante gen erasachwen meremiru. mechime endematwetwe awekalwe

  ReplyDelete
 6. every thing negative min yeteregemachihu nachihu enanite menafikan?

  ReplyDelete
 7. Tikkil Bilachwal Be Mehibere Kidusan(seyitan) yemimera Sinodos Min Yitebekal Ye Federal Mihila

  ReplyDelete
 8. Aba selamawoch ewunet bilachihual. enem beErase yeMihilaw neger melikam hono sale akahedu alameregnim!

  ReplyDelete
 9. ወይ የናንተ ነገር! ይሔ ደግሞ የማስተባበያ ጽሑፍ መሆኑነው? ፀሎትን የሚቃወም ሁሉ የነእንትና ግብራበር ከመሆን ነጻ አይሆንምና ብዙም አትልፉ ትታወቃላችሁ።

  ReplyDelete
 10. Thank you brothers for your positive comments.
  Please let us do good thing for our church unity. God have a wonderful plan in his hand for our church.why our Ethiopian archbishops didn't invited exiles archbishops to pray?. Here is the big problems in our Orthodox church top leaders mistaken. I am pretty sure we do not see any light from those leaders to become united. Happy Ethiopian New Year for every bodies and do not give up ....to fight evils.

  ReplyDelete
 11. kezih blog lay comment mestet alfelgm neber gin ahun yetesemagnen lemenager feleghu...... Egziabher yikebelewal ayikebelewum yemtlut enante sathonu ersu erasu new melsun yemimels.......lelaw gin abatoch erke eskalfetsemu dres minim madreg ayichilum lalkew ahunm ayagebahm......zim bleh yeraskn nuro nur......lelawun le egziabher asalfeh sit. Sbhat le egziabher,wole woladitu dingle,wole meskelu kibur.

  ReplyDelete
 12. እናነተ የሰላም እና የፍቅር ጠላቶች ናችሁ! አሁን ምህላ ታወጀ ብላችሁ፤ ተቆርቋሪ መስላችሁ በቤ/ክ አባቶች ላይ ትችት ታወረዳላችሁ? አረ እፈሩ፡፡ እናነት ጡት ነካሾች ወየውላችሁ ንስሀ ግቡ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለቀባቸው ጳጳሳቱ እነደሚገደው አስተውሉ፡፡ አሁን ሕዘቡን ለጸሎት በቀሰቀሱ እነሱን ትገዳደራላችሁ፡ እናነተ የቤ/ክ ልጆች ብትሆኑ ኑሮ አባቶቻችሁን ባከበራችሁ ነበር፡፡ ሁሉም ምእመን “እሰይ! እነኳን ጾም ታወጀ፡፡” ብሎ በደስታ ተቀብሎ እየጸለየ ባለበት ወቀት ፍጹም አንድ ‘መንፈሳዊ ነኘ’ ለያውም የተዋህዶ ‘አባል ነኘ’ ብሎ ከሚናገር ሰው የማይጠበቅ ጽሑፍ ትጽፋላችኁ? በእውነት እናንተ የበጎ ነገር ጠለቶች ናችሁ፡፡ እባካችሁ ቆም ብላችሁ ራሳችሁን ተመልከቱ፡፡ በድፍረት እና በትዕቢት ታጅራችሁ ጥርጣሪን አትንዙ፡፡ እናንተ ክርስቶስን የምታመልኩ ከሆነ በእውነት ይህንን ከእርሱ አትማሩም፡፡ እርሱ ፍቅርን የሚሰብክ፣ ቸር፣ ትሑት ፣ ይቅር ባይ አምላክ ነው፡፡ እናነተ ግን ተቃራኒ ናችሁ፡፡ እናነተ እኮ በዓለም ያሉትን የጥላቻ ፖለቲካ ፐሮፓጋዲስቶች የሚነዙትን ሽብር ነው ሀይማኖት ውስጥ ያመጣችሁ፡፡ ምን አለ ይህንን ለእነርሱ ብትተውላቸው፡፡ ማንን ለማሸነፍ ነው ይህን ያህል የምትጋደሉት? በእውነት ቅናተ ቤ/ክ ግድ ብሏችሁ ከሆን፤ ግድየላችሁም ለባለቤቱ በጸሎት አሳልፋችሁ ሰጥታችሁ ፤ በቀረውስ ለራሳችሁ ጽድቅ የተሞላበት ሕይወት እንዲኖራችሁ ተጋደሉ፤ ፈቅርን በመስበክ አገልግሉ፡፡ ደግሞስ ብትበደሉስ አጸፋችኁ እንዲህ መሆን ነበረበት? አሁን እናነተ እንደ ክርስቶስ ፍቀርን እና እርቅን ነው ወይስ እንደ ዳቢሎስ ጥልን የምትዘሩ? ለመሆኑ ከማን ወገን ናችሁ? አረ እባካችሁ እራሳችሁን ፈትሹ፤ ክርስቶስ እንዲህ አይሰበክም፡፡ እርሱ ፍቅር እና ፍቅርን ነው የሰበከ፡፡ እርሱ ልቦና ይስጣችሁ፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 13. ትክክለኛው የ ETOC ወንጌል ተማሩ! mekrez.blogspot.com/

  ReplyDelete
 14. misikeoche!!!!kezihe website yetemerekubete neger...MK yenanete(menafekane) telate endehone..alamana gebachehune kesere meseretu nekeso selawetabachu,selasawekebachu...aye menefekena leka endezihe leke yata weshete newe...zeyegerem!!
  Dear all let us stand for our church,by our time, money,by our profession, thinking,.....to make them deleat website like abaselama by them selves, for the act they are doing for making peoples to hate each other, those who are struggling peoples and our beloved Bishops to be hated by the peoples who don't have information about them!!!

  May GOD be with us in giving strength in uniting our church!!!!

  ReplyDelete