Tuesday, October 30, 2012

የጥቅምት ሲኖዶስ ስብሰባ በአዲስ አበባና በ አሜሪካ እየተካሄደ ነው

ከ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አረፍትም በኋላ ቤተ ክርስቲያናችን ሁለት የተለያየ የሲኖዶስ ስብሰባ እያካሄደች ነው። በበርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሲወያይ የነበረው የአዲስ አበባው ስብሰባ እየተገባደደ ሲሆን በሰሜን አሜሪካ ኮሎምበስ ኦሃዮ የሚካሄደው በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሚመራው ሲኖዶስ በዛሬው ዕለት ስብሰባውን ይጀምራል።  በአሜሪካ ስለሚካሄደው ስብሰባ ፍሬ ፍሬ የሆኑ ነገሮችን የምንዘግብ ሲሆን ስለ አዲስ አበባው ስብሰባ ዐውደ ምህረትን ይመልከቱ፦ http://awdemihret.wordpress.com/

በሁለቱም ወገን ያሉ ብፁዓን አባቶች የሚመሩት ህዝብ ፍላጎት አንድነት መሆኑን ተገንዝበው የህዝቡን ምኞትና የልብ ትርታ እንደሚያዳምጡለት ተስፋ እናደርጋለን።


Thursday, October 25, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን «ወደ ግብጽ እንመለስ» የሚል ዘፈን ዛሬም ቀጥሏል

ማኅበሩ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ታሪክ የሚያጎድፍ ጽሑፍ አወጣ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ 121ኛ ፓትርያርክ ናቸው አለ   
ጌታ እግዚአብሔር እስራኤልን በድንቅና በተአምራት ከግብጽ ምድር ነጻ ካወጣቸው በኋላ በእርሱ ይታመኑ ወይም አይታመኑ እንደሆነ ሊፈትናቸው በምድረ በዳ በኩል ነበር የወሰዳቸው። በምድረ በዳ በገጠማቸው ፈተና ግን በእግር የተለዩአትን ከልባቸው ግን ያላወጧትን ግብጽን እየጠሩ፣ «ከግብጽ ለምን አወጣችሁን? እዚያው ብንሞት ይሻለን ነበር?...» ይሉ እንደነበር ተጽፏል። የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለ1700 ዓመታት ያህል አለአግባብና በግብጾች ሴራ በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ስር በመንፈሳዊ ባርነት ስትማቅቅ ኖራለች። ከጥንት ጀምሮ ቤተ ክርስቲያኗ ራሷን እንድትችል ጥረት ሲደረግ እንደቆየ የቤተክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል። የብዙ ዘመናት ጥረቱ ተሳክቶም በ1951 ዓ.ም ቤተክርስቲያኗ ራሷን ችላ የራሷን ፓትርያርክ ሾማለች። ከዚያ በኋላም ኢትዮጵያዊ የሆኑ 5 ፓትርያርኮችን አሳልፋለች። እንዲህ በመሆኑ ምን የሚጎዳው ወይም የሚጠቀመው ነገር እንዳለ ባይታወቅም፣ ማኅበረ ቅዱሳን ይህን ሕያው ታሪክ በመፋቅ የሌለ ታሪክ በሐመር መጽሔት ላይ አውጥቷል።

Sunday, October 21, 2012

በደብረ ማርቆስ በዘንድሮው የደመራ በዓል ላይ የተሰበከው ወንጌል

Read in PDF
በየዓመቱ መስከረም 16 በኢትዮጵያ ብቻ በድምቀት የሚከበረው የደመራ በዓል ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፅ (እንጨት) የሚሰበክበት እንጂ በእርሱ ላይ የተሰቀለው መድኃኒት ክርስቶስ የሚሰበክበት እንዳልሆነ ይታወቃል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን ያለው ዘላለማዊ እውነት ተሰርዞና ተደልዞ «እኛ ግን ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል እንሰብካለን» በሚለው የስህተት ትምህርት ከተተካም ዘመናት ተቆጥረዋል። ቤተ ክርስቲያናችን የተሰቀለውን ክርስቶስን ትታ የተሰቀለበትን መስቀል እንድትሰብክ ያደረገውና ከእውተኛው መንገድ አስቶ ያወጣት፣ ሰው በላው አጼ ዘርአ ያዕቆብ እንደሆነ ታሪክ ይመሰክራል። ታሪኩን የክርስቶስ ነገረ መስቀል የገባቸው ክርስቲያኖች በሀዘን ሲመለከቱት ነገረ መስቀሉን በዕፀ መስቀሉ የተኩ የነገረ መስቀሉ ጠላቶች ደግሞ ይኮሩበታል። አለመታደል!!

Tuesday, October 16, 2012

አዲስ መጽሐፍ ከዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል - ማኅበረ ቅዱሳን ወይስ ማኅበረ ሰይጣን ክፍል 3

ለሞት እንዳልተኛ ዓይኖቼን አብራ!
መጽሐፉ ምንም እንኳን የዛሬ አንድ ዓመት ከሦስት ወራት በፊት ሙሉ ዝግጅቱ ተጠናቅቆ ወደ ማተሚያ ቤት አምርቶ የነበረ ቢሆንም በአንዳንድ ምክንያቶች የሕትመት ሂደቱ ተቋርጦ አንዲዘገይ ግድ ብለዋል። በዚህ ቆይታ መካከል መጽሐፉ በአራት የሥነ መልኮት መምህራን፣ የሥነ ጽሑፍና የህግ ባለ ሞያዎች እንዲታይና እንዲገመገም ዕድል ፈጥሯል።  መጽሐፉ በይዘቱ 262 ገጽ ሲኖረው በርካታ ጥልቀት ያላቸውን ርዕሰ ጉዳዮች አንሥቶ የሚያትትና የሚያብራራ ነው። ከሞላ ጎደል በእያንዳንዱ ምዕራፍ የመጀመሪያ ገጽም የምዕራፉን አጠቃላይ ይዘት በዐጭሩ ያስቃኛል። በህትመት ረገድም  በከፍተኛ ይዘትና የህትመት ጥራት በምእራቡ ዓለም የህትመት ደረጃ በላቀ ጥራት በአሜሪካን አገር ቺካጎ ከተማ በሚገኘው ትልቁ የህትመት ድርጅት የታተመ ሲሆን እስከ ድህረ ሞት ቅዱስ ፓትሪያሪክ ጳውሎስ ያለውን የማኅበሩ መሰሪ እንቅስቃሴ አካቶ በብዙ ተግዳሮትና ፈተናዎች አልፎ በዛሬው ዕለት ለንባብ መብቃቱን ይፋ ሳደርግ በታላቅ ደስታ ነው።

Monday, October 15, 2012

ለፕትርክናው በማኅበረ ቅዱሳን ከታጩት አንዱ አቡነ ሉቃስ ማናቸው?

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ካረፉ በኋላ ቤተክህነቱ የሐዘን ድባብ እንዳጠላበት ነው። ስድስተኛውን ፓትርያርክ ለመሰየም ትልቅ የቤት ስራ ከፊቱ የተደቀነበት ጠቅላይ ቤተክህነት ማንን መሰየም እንዳለበት ለመወሰን የተቸገረ ይመስላል። እኔ ልሁን እኔ ልሁን የሚል ባይጠፋም፣ አለሁ አለሁ ከሚሉት መካከል፣ ለፕትርክናው የሚመጥን ሰው አለመገኘቱ ግን ብዙዎችን አሳስቧል። ቤተክርስቲያኗን በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መሠረት የሚመራ፣ ቤተክርስቲያኗ በዓለም አቀፍ ደረጃ አግኝታ የነበረውን ክብርና ስፍራ ጠብቃ እንድትቀጥል የሚያደርግ፣ የውስጥ ችግሮቿን ለመፍታት ቁርጠኛ የሆነና ዝግጁነት ያለው አባት ማግኘት ቀላል አይደለም።

Sunday, October 14, 2012

“ያለ ወላዲተ አምላክ አማላጅነት ዓለም አይድንም!” የሚለው ጥቅስ ምንጩ ማነው?

ክፍል 2
በዚህ ርእስ ያቀረብነውን ጽሑፍ ተከትሎ በርካታ ሰዎች ጽሑፉን በመደገፍም በመቃወምም አስተያየቶቻቸውን ሰጥተዋል፡፡ በተለይም ዓለም የሚድነው በማርያም አማላጅነት ነው የሚለውን የክሕደት ትምህርት የደገፉ ሰዎች በእኛ እምነት ምንም አሳማኝ ማስረጃ አቅርበዋል ማለት አንችልም፡፡ አብዛኞቹ በጭፍን የተሞላና የያዝነውን ልማዳዊ የክህደት ትምህርት በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አናርምም፤ ምን ታመጣላችሁ? ያሉ ነው የመሰለን፡፡ አንዳንዶቹ ግን አዳኝነትን የጸጋና የባሕርይ በሚል ከፋፍለው ለማደናገር ሞክረዋል፡፡ በተለይም በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ድረ ገጽ ላይ መምህር ሙሴ በተባሉ ሰው የወጣውንና «ለመሆኑ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም "መድኃኒተ ዓለም" ትባላለችን?... ለምን? ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለውን ግኑኝነትና ልዩነት እንዴት ይገለጻል?» የሚለውን ጽሑፍ መከራከሪያ አድርገው አቅርበዋል፡፡ ይህ ጽሑፍ በዚህና ተመሳሳይ ይዘት ባላቸው አስተያየቶች ላይ ተመሥርቶ «ያለ ማርያም አማላጅነት ዓለም አይድንም» በሚለው የክህደት ትምህርት ዙሪያ መብራራት ያለባቸውን ሐሳቦች እናብራራለን፡፡

Thursday, October 11, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ ሌሎች 13 አገልጋዮችን ለማስወገዝ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተሰማ

Read in PDF
በግንቦት 2004 ዓ.ም ከቤተክርስቲያን በሕገ ወጥ መንገድ ተሰደው ያሉ አገልጋይ ግለሰቦችንና በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ መንፈሳዊ ማኅበራትን እንዲወገዙ ያደረገው ማኅበረ ቅዱሳን የረካ አይመስልም። አሁን ደግሞ በውስጥ የሚገኙና ከማኅበሩ ጋር በአንድም በሌላም መንገድ ያልተስማሙትን፣ በሚሰጡት አገልግሎት ማኅበረ ቅዱሳንን ከጨዋታ ውጪ እያደረጉት የሚገኙትን የቤተክርስቲያን ልጆችን ለማስወገዝ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ሰሞኑን ለማኅበሩ ቁልፍ አባላት ይፋ ማድረጉን ለማኅበሩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ። ማኅበሩ የ13 አገልጋዮችን ስም ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ አገኘሁባቸው ያለው «ኑፋቄም» ከፕሮቴስታንቶች ጋር ይገናኛሉ፤ ተጨባጭ ማስረጃም አለኝ የሚል ነው። የአገልጋዮቹን ዝርዝር ወደፊት እንደአስፈላጊነቱ ይፋ እናደርጋለን።

Tuesday, October 2, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ውስጥ የራሱን ሰው ለማስቀመጥ እየሠራ ነው

የኢትዮጵያ ፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከሚያከናውናቸው ጉዳዮች አንዱ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የሃይማኖት ተቋማት ምዝገባና ፈቃድ መስጠት ነው፡፡ ይህም ሥልጣን ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ በአዋጅ ቁጥር 690/2002 የተሰጠው ሲሆን፣ በዚሁ መሰረት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በስሩ ካዋቀራቸው ክፍሎች መካከል የሃይማኖትና እምነት ተቋማት ዲያሬክቶሬት ጀነራል አንዱ ነው፡፡ ይህን ዲያሬክቶሬት ሲመሩ በነበሩትና በጡረታ በተገለሉት በአቶ መረሳ ረዳ ምትክ ለቦታው የሚመጥን የተማረ ሰው ለመመደብ ከሚኒስትሩ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ጥያቄ መቅረቡን ተከትሎ ማኅበረ ቅዱሳን ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ከሚገኙ አባላቱ  
ማኅበሩ ይህን እያደረገ ያለው መንግስት ይልቁንም ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ በሚገኘው በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ውስጥ ወኪሉን በማስቀመጥ፣ በመንግስት በኩል «ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪነትን የሚያስፋፋ ማኅበር ነው» በሚል በማኅበሩ ላይ የተያዘውን አቋም ለማስለወጥ እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ማኅበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ማኅበሩን በተመለከተ የመንግስታቸውን አቋም ማንጸባረቃቸውን ተከትሎ መደናገጥ ውስጥ ገብቶ የነበረ ሲሆን፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሞት ተከትሎ ደግሞ እፎይታን ያገኘ መስሏል፡፡ ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የተናገሩት የመንግስታቸውን አቋም እንደመሆኑ ማኅበሩ አክራሪነቱን ካልቀየረ በስተቀር የመንግስት አቋም ይለወጣል ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ነው፡፡ ማህበሩ ደግሞ በምንም ተአምር አክራሪ ጠባዩን ሊለውጥ የሚችልበት እድል እንደሌለ ከቀድሞ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በሃይማኖት ሽፋን በቤተክርስቲያኗ ውስጥም ሆነ ከዚያ ውጪ እያከናወነ ካለው ተግባሩ መረዳት ይቻላል፡፡