Thursday, October 11, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ ሌሎች 13 አገልጋዮችን ለማስወገዝ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተሰማ

Read in PDF
በግንቦት 2004 ዓ.ም ከቤተክርስቲያን በሕገ ወጥ መንገድ ተሰደው ያሉ አገልጋይ ግለሰቦችንና በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ መንፈሳዊ ማኅበራትን እንዲወገዙ ያደረገው ማኅበረ ቅዱሳን የረካ አይመስልም። አሁን ደግሞ በውስጥ የሚገኙና ከማኅበሩ ጋር በአንድም በሌላም መንገድ ያልተስማሙትን፣ በሚሰጡት አገልግሎት ማኅበረ ቅዱሳንን ከጨዋታ ውጪ እያደረጉት የሚገኙትን የቤተክርስቲያን ልጆችን ለማስወገዝ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ሰሞኑን ለማኅበሩ ቁልፍ አባላት ይፋ ማድረጉን ለማኅበሩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ። ማኅበሩ የ13 አገልጋዮችን ስም ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ አገኘሁባቸው ያለው «ኑፋቄም» ከፕሮቴስታንቶች ጋር ይገናኛሉ፤ ተጨባጭ ማስረጃም አለኝ የሚል ነው። የአገልጋዮቹን ዝርዝር ወደፊት እንደአስፈላጊነቱ ይፋ እናደርጋለን።
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሞት ሰፊ እድል የፈጠረለት የመሰለው ማቅ እንዲተላለፍለት ለሚፈልገው ሁለተኛ ዙር ውግዘት ከአንዳንድ የመመሪያ ሃላፊዎች ጋር ምክክር እያደረገ መሆኑ ሲታወቅ፣ በቀጣይም ጳጳሳትን በተለመደው መንገድ የማሳመን ሥራ እየሰራ መሆኑ ታውቋል። እንዲህ እንዲህ እያለ እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስታያናት ድረስ በመውረድ እርሱ «ተሐድሶ» የሚል ታፔላ የለጠፈባቸውን አገልጋዮች ሁሉ ከቤተክርስቲያን የመመንጠር እቅድ እንዳለውም እነዚሁ ምንጮቻችን ገልጸዋል።

ወንጌል በውግዘት ይቆማልን?
የማኅበረ ቅዱሳን መንፈሳዊ የሚለው አላማው የቤተክርስቲያን ልጆችን ከቤተ ክርስቲያን ማስወጣት መሆኑ ማኅበሩ የሚገኝበትን ደረጃ የሚያሳይ ነው። ማኅበሩ እንዲህ በማድረግ እግዚአብሔርን እንደሚያስደስት ያስባል። ለዚህ ኢክርስቲያናዊ ተግባሩ የሚሰጠው ምክንያትም «ተሐድሶዎች ቤተክርስቲያንን ሊያፈርሱ ነው የተነሡትና እነርሱን ከቤተክርስቲያን መመንጠር ያስፈልጋል» የሚል ነው። ነገር ግን እርሱ እንደሚያስበው «ተሐድሶ» የሚላቸው ሰዎች አላማ ቤተክርስቲያንን ማፍረስ ነው ወይ? በፍጹም አይደለም። አላማቸው «ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መሰረት እየተመራች አይደለም፤ መጽሐፍ ቅዱስን በሚቃረኑ አስተምህሮዎችም ተሞልታለች። ይህ ደግሞ ከእግዚአብሔር የሚያጣላና ከመንግስተ ሰማያትም የሚያጎድል ነውና ቤተክርስቲያን ማንነቷን ጠብቃ ወደመጽሐፍ ቅዱሳዊው እውነተኛ መሠረቷ መመለስ አለባት» የሚል ነው። እንዲህ ማሰብ የነበረባት ራሷ ቤተክርስቲያኗ ነበረች። እርሷ ግን እንዲህ ማሰብ ቀርቶ እንዲህ ያለውን ሐሳብ የሚያነሱትን ሁሉ ሌላ ስም እየሰጠች ስታሳድድ ነው የኖረችው። ይህ ደግሞ የእግዚአብሔር ጠላት መሆን ነው። ለእግዚአብሔር የቆሙ በመምሰል እግዚአብሔርን መቃወም እንዳለም መታወቅ አለበት።

ማኅበረ ቅዱሳን፣ ለጌታ ክብር ቀንተው «የስሕተት ትምህርቶች ይስተካከሉ፣ ቤተክርስቲያን በደሙ ለዋጃት ጌታ ብቻ ትኑር፤ በእርሱ ላይ ሌሎችን አትደርብ» የሚሉትን የቤተክርስቲያን ልጆች በማሳደዱ እግዚአብሔርን ደስ እንደሚያሰኝ ያምናል። እንዲህ ማሰብ በማኅበረ ቅዱሳን አልተጀመረም። ከጥንት ጀምሮ እንዲህ ያለ አስተሳሰብ ያላቸው ግለሰቦችም ቡድኖችም ነበሩ። አይሁድ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ናቸው። ከአይሁድ መካከል የነበረው ሳውልም ክርስቲያኖችን በማሳደድ ጌታን የሚያገለግል ይመስለው የነበረ ሰው ነው። በደማስቆ መንገድ ላይ ክርስቶስ ሲገለጥለት ግን እርሱ እግዚአብሔርን ለማስደሰት የሄደበት መንገድ የተሳሳተ እንደነበረ ተረዳ። ምክንያቱም ጌታ ተገልጦ «ሳውል ክርስቲያኖችን ስላሳደድህ እጅግ ደስ ብሎኛል» አላለለውም፤ ይልቁንም ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ?» ነው ያለው። የልጆቹ መነካት የእርሱ መነካት ነውና።

ማኅበረ ቅዱሳን ዛሬም እየደገመ ያለው ይህንን ስሕተት ነው። እስካሁን እያደረገ ባለው ነገር እግዚአብሔርን ያስደሰተ ቢመስለውም እውነቱ ግን እግዚአብሔርን እያሳዘነ ነው የሚገኘው። ጌታ የተናገረው ቃል በእርሱ እንዲፈጸምበት በራሱ ላይ እንደወሰነም ያሳያል። «ከምኵራባቸው ያወጡአችኋል፤ ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል። ይህንም የሚያደርጉባችሁ አብንና እኔን ስላላወቁ ነው። ነገር ግን ጊዜው ሲደርስ እኔ እንደ ነገርኋችሁ ታስቡ ዘንድ ይህን ተናግሬአችኋለሁ።» (ዮሐ. 16፥2-4) የሚለውን ቃል ማኅበረ ቅዱሳን እየፈጸመ ነው። ማኅበረ ቅዱሳንን ለቤተክርስቲያን መታደስ የቆሙ እውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጆችን በማሳደዱ አግዚአብሔርን ያገለገለ ቢመስለውም እግዚአብሔርን እያገለገለ ግን አይደለም። ይህ ተግባሩም አብንና ወልድን እንደማያውቅ ያሳያል። ስለዚህ ማኅበረ ቅዱሳን ሆይ፣ ጌታን ስለምን ታሳድዳለህ? የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል።

ማኅበረ ቅዱሳን እንደቀድሞው ሳውል ሆኖ ከቤተክርስቲያን ሊያስወጣችሁ የውግዘት ደብዳቤ እየለመነባችሁ ያላችሁና የእግዚአብሔርን ሥራ የምትሠሩ የቤተክርስቲያን ልጆች ሆይ፣ በቅድሚያ እንኳን ደስ አላችሁ፤ ስለ ጌታ ስም ነቀፋ ደርሶባችኋልና። እጅግ ደስ ይበላችሁ እንጂ አትደንግጡ፤ እንደተጻፈው ይህ ለተቃዋሚዎቻችሁ የጥፋት ለእናንተ ግን የመዳን ምልክት ነው። ይህ ከእግዚአብሔር የተሰጣችሁ ስጦታ ነው። የተሰጣችሁም ስለክርስቶስ ወይም በክርስቶስ ስላመናችሁ ነው። የተጠራችሁት በስሙ ልታምኑ ብቻ ሳይሆን ስለ ስሙ መከራን ልትቀበሉም ነውና (ፊልጵስዩስ 1፥28-29)። ደግሞም እንዲህ የሚል የተስፋ ቃል አላችሁ «ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ የክብር መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ።» (1ጴጥሮስ 4፥14)። ስለዚህ ለማኅበረ ቅዱሳን ስጋዊ አጋሄድ ስጋዊ ምላሽ ለመስጠት በፍጹም አታስቡ። ከዚያ ይልቅ በጸሎት ተጋደሉ፤ በአገልግሎታችሁም ከፊት ይልቅ ትጉ። ለቤተክርስቲያናችሁ መታደስ የሚገባውን ሁሉ ሥሩ። የወንጌል ሥራ እስከተሠራ ድረስ ተቃውሞ መኖሩ የግድ ነው። ይህን ተገንዝባችሁ ከፊት ይልቅ ለጌታ የተለያችሁ እንድትሆኑ ትጉ። ምናልባትም መከራ የደረሰባችሁ ትልቅ ሥራ ስላለ እንደሆነ አስቡ። ምክንያቱም ሐዋርያው ጳውሎስ በአገልግሎቱ ካጋጠመው ልምድ እንዳካፈለን ሥራ የሞላበት ሰፊ በር ሲከፈት ተቃዋሚዎች እንደሚበዙ የታወቀ ነው። በተቃውሞ ውስጥ የተሰራ የወንጌል አገልግሎት ደግሞ ፍሬው ጣፋጭና አመርቂ ነው። ከተቃዋሚዎቻችሁ ጋር ካለው ይልቅ ከእናንተ ጋር ያለው ጌታ እግዚአብሔር ትልቅና አሸናፊ መሆኑን አስባችሁ ስለስሙ የሚከፈለውን ዋጋ ሁሉ በመክፈል ለማገልገል እንድትዘጋጁ እንመክራለን። 

ለማኅበረ ቅዱሳንም መልእክት አለን። ትልቁ ስሕተታችሁ ከታሪክና ከእውነታ መማር አለመቻላችሁ ነው። የምታደርጉትን ሁሉ እያደረጋችሁ ያላችሁት፣ ምንም እንኳን ድብቅ አጀንዳ ያላችሁ መሆኑ ባይታበልም፣ ለሃይማኖታችሁ ቀንታችሁ እንደሆነ እናስባለን። ለሃይማኖታችሁ የቀናችሁትም ለእግዚአብሔር የቀናችሁ ስለመሰላችሁ ይሆናል። ነገር ግን አካሄዳችሁን ብትመረምሩት እየፈጸማችሁ ያላችሁት የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዳይደለ ትረዳላችሁ። በእናንተ አካሄድም የተጀመረውን የእግዚአብሔር መንግሥት ሥራ የምታስተጓጉሉ መስሏችሁ ከሆነ ተሳስታችኋል። የእናንተ የጥንት አባቶች አይሁድ የቅርቦቹም እነ አጼ ዘርአ ያዕቆብ፣ በተቻላቸው መጠን የክርስቶስ ወንጌል እንዳይስፋፋ ከፍተኛ ዘመቻ ከፍተው ነበር። ነገር ግን ወንጌል እያሸነፈና ምድርን እየከደነ መጣ። አጼ ዘርአ ያዕቆብም ከዛሬ 500 ዓመት በፊት እነ አባ እስጢፋኖስን ብዙ መከራና ስቃይ አብልቶ የተሐድሶ እንቅስቃሴያቸውን የቀለበሰ ቢመስልም፣ ከ500 ዓመታት በኋላ የእርሱ ተአምረ ማርያም ዋጋ እያጣና እየተብጠለጠለ ነው። ዛሬ ተአምረ ማርያም በቤተክርስቲያን የሚነበበው ታምኖበት አይደለም። ሐሰተኛና የክሕደት መጽሐፍ መሆኑን ብዙዎች ቢያውቁም ስርአቱን በአንድ ጊዜ መለወጥ ስለማይቻል እንደሆነ ሲናገሩ ይሰማሉ። የአባ እስጢፋኖስ ገድል ግን እያበበ መጥቷል። በፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ የተተረጎመውን ገድላቸውን ብዙዎች አንብበዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ በድጋሚ ታትሞ እንኳ ከገበያ ጠፍቷል። ድጋሚ እንዳይታተም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ላይ ጫና እያሳደራችሁ እንዳለ ይወራል። ያም ሆነ ይህ ወንጌል እያሸነፈ ይሄዳል።

እናንተ ልጆቻቸውም ያደረጋችሁትን መለስ ብላችሁ ብታዩት ተመሳሳይ ኪሳራ ነው የደረሰባችሁ። ማለትም ወንጌልን ከመስፋፋት አላገዳችሁትም። ለምሳሌ፣ ከዛሬ 10 ዓመት በፊት ጥቂት መነኮሳት በኤግዚቢሽን ማእከል ሕዝብ ሰብስበው ባካሄዱት ኮንፍራንስ ምክንያት የእነርሱን ቪዲዮ ለጳጳሳቱ አሳይታችሁ አስወገዛችኋቸው። የመነኮሳቱ አካሄዳቸው ትክክል እንዳልነበረ እንገነዘባለን። ከዚያ በኋላ የተሐድሶ እንቅስቃሴ ቀንዱን እንደተመታና ዳግም እንደማያንሰራራ ገመታችሁ። ከ10 ዓመት በኋላ ግን እጅግ ሰፍቶና ለእናንተ ስጋት ሆኖ ሌላ ውግዘት እንድታስተላልፉ አስገደዳችሁ። አምና በግንቦት ወር የተካሄደው ሕገወጥ ውግዘትም የተሐድሶን እንቅስቃሴ የሚያቆም መስሏችሁ ይሆናል። ነገር ግን ታሪክ ራሱን እንደሚደግም ሳይታልም የተፈታ ነው። የክርስቶስ ተከታዮች ከትናንት እና ከዛሬ ይልቅ ነገ እንደሚበዙና የእናንተ ተረታ ተረቶች ስፍራቸውን ለወንጌል እንደሚለቁ ፈጽሞ አያጠራጥርም። ሰውን ለጊዜው በተረት ማቆየት ቢቻልም የሚያሳርፈው የክርስቶስ ወንጌል ብቻ ስለሆነ እርሱን እስኪያገኝ ድረስ ጉዞው ይቀጥላል።

34 comments:

 1. አሁን ከክርስቶስ ድህነት ተካፋይ የሚያደርገው በክርስቶስ ማመን, በስሙም መጠመቅ, መልካም ስራ ናቸው:: አንተ ግን ልታምን ትችላለህ ነገር ግን ስለ ማቅ ድብቅ ስራ እንዲህና እንዲያ እያልክ የምትዋሸው ከጽድቅ መንደግ ወድቀህ እንደተፈረደብህ አሁንኑ እወቅ::

  ReplyDelete
 2. abet yebetekirstianachin tekorkuariwoch atmeslum??????????????????????? tigermalachihu menafik mehonachihun erasachu geletachut!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 3. Great job MK. This gays could be cleared out and sent gto their house.

  ReplyDelete
 4. Ezaw bebetachihu nuru. atirebishun benatachihu.

  ReplyDelete
 5. አባ ሰላማዎች መልካም ጽሑፍ በማቅረብ ላይ ናችሁና ትጉ! ማቅ ግን ራሱ ፀረ ማርያም ራሱ መናፍቅ የሆነ የወሮ በላ ጥርቅም ሲሆን (የራሷን አበሳ በሰው አብሳ)
  እንደሚሉት ሽማግሎች ማቅ በሌሎች ላይ የስም ማጥፋት ደንጊያ መፈንቀሉና ጀሌዎቹን
  በመጠቀም የውግዘት መርጎቹን ማንካባለሉ አይቀርም፤ ዳሩ ግን እና ዓፄ ዘረዐ ያዕቆብን
  ያሳሳቱ አንዳንድ ያልተማሩ የከተማ መነኩሴዎችና ራሳቸው ዘርዐ ያዕቆብ ከፍርድ እንዳላመለጡ ማቅና ቅምጥሎችም የፈራጁ መቻያን የሚቀበሉበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም
  ምክንያቱም ዘመኑ በማጭበርበር ሰውን ግራ በማጋባትና አማኞችን በማሞኘት የሚኖርበት
  አይዶለምና ይልቁንስ ራሳቸውን መካብ ሠርዘው እንደ ሰው ሆነው ትኅትና እያሳዩ ቢሰነብቱ ይሻላችዋል፤

  ReplyDelete
 6. አባ ሰላማዎች መልካም ጽሑፍ በማቅረብ ላይ ናችሁና ትጉ! ማቅ ግን ራሱ ፀረ ማርያም ራሱ መናፍቅ የሆነ የወሮ በላ ጥርቅም ሲሆን (የራሷን አበሳ በሰው አብሳ)
  እንደሚሉት ሽማግሎች ማቅ በሌሎች ላይ የስም ማጥፋት ደንጊያ መፈንቀሉና ጀሌዎቹን
  በመጠቀም የውግዘት መርጎቹን ማንካባለሉ አይቀርም፤ ዳሩ ግን እና ዓፄ ዘረዐ ያዕቆብን
  ያሳሳቱ አንዳንድ ያልተማሩ የከተማ መነኩሴዎችና ራሳቸው ዘርዐ ያዕቆብ ከፍርድ እንዳላመለጡ ማቅና ቅምጥሎችም የፈራጁ መቻያን የሚቀበሉበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም
  ምክንያቱም ዘመኑ በማጭበርበር ሰውን ግራ በማጋባትና አማኞችን በማሞኘት የሚኖርበት
  አይዶለምና ይልቁንስ ራሳቸውን መካብ ሠርዘው እንደ ሰው ሆነው ትኅትና እያሳዩ ቢሰነብቱ ይሻላችዋል፤

  ReplyDelete
 7. ያንተም ስም ይኖራል ጠብቅ! ምነዉ ፈራህ እንዴ አይዞህ አንተና ጓደኞችህ እድሜ ለአባ ሰላማ ብሎግ ማንነታችሁን እራሳችሁ ስላወጃችሁት ለማህበረ ቅዱሳን ስራ አቅልላችሁለታል፡፡ ባይሆን ቤ/ን ዉስጥ የሰገሰጋችሁአቸዉ አባሎቻችሁ እንዳይጋለጡ ፈርተህ ይሆናል እንጅ አንተንማ አለም ሁሉ ክህደትህን አዉቆልሃል፡፡

  ReplyDelete
 8. ሰውን ለጊዜው በተረት ማቆየት ቢቻልም የሚያሳርፈው የክርስቶስ ወንጌል ብቻ ስለሆነ እርሱን እስኪያገኝ ድረስ ጉዞው ይቀጥላል።
  አሜን እየሱስ ጌታ ነዉ

  ReplyDelete
 9. እንዲህ ያለውን ሐሳብ የሚያነሱትን ሁሉ ሌላ ስም እየሰጠች ስታሳድድ ነው የኖረችው። Ye enat tut nekashoch...yilikunim ketifatachihu bitimaru melkam new. Tewahidon enkuan enante hodamoch,ye gehanem dejoch ayichiluatim !!!

  ReplyDelete
 10. Go hell with your reformation idea! It is your personal feeling; not God's idea.

  ReplyDelete
 11. Gena eyetemenetere yiwotal. Tekula hula. For ever orthodox.

  ReplyDelete
 12. Abaselama, Ethiopia constitution granted to all citizen to practice any part of religen. Criminal mind mk violated law of Ethiopia in the behined bar of poltical game. I was former mk element. The reason of quit from this devil group is not part of religen. Which is part of illegal poltical organization. Finally, old fashioned wogezet not hurt any thing, so it is another way of bedatam shermuta papas to collect money playing with mk. Do not worry. Mr. Mesfin Tewogez still he is live, I gues keep it up you preaching of Geta. If wogezet is meaning ful, why mesfin was not dying? Mk use wogezet for to use confussion. Death to mk Zemawi Zelebanose and Tebate Adamu

  ReplyDelete
  Replies
  1. How dare you to say MK's practice is a crime?
   EOTC has its own rules canons and rules. Particularly the Dogmatic regulations identifies not to be reformed by you reformists. Constitution can rule the nation in that muslims and pagans live. EOTC has rule to rule the Parochials. DOn't just bark. Step aside and practice what so ever that you want without contradicting EOTC's rule. That is what the religion's freedom is.

   Delete
 13. ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የተግባር እንጂ የምላስ ብቻ ወንገል የላትም !! እናንተ የእናት ጡት ነካሽ ውሾች !! የተጣላችሁት ከማትችሉት እግዚአብሔር ጋር መሆኑን ማን በነገራችሁ !!

  ReplyDelete
 14. መወገዝ ብቻ አይደለም !! ገና በህግም ትጠየቃላችሁ !!

  ReplyDelete
 15. please leave our church.we know what we belive.you know, everbody has ability to read and undersatnd about bible, and they decide what they want.but you may be a carrier of abroad mission or you are a parasite of our church.please leave alone or you can go to musilim religion and teach your doctrine

  ReplyDelete
 16. ጌታ ይባርካችሁ ማህበረ ቅዱሳኖች። መናፍቃንን፥ ሁለት ደሞዝተኛ አስመሳይን ከቤታችን ጥረጉልን። ቤተ ክርስቲያናችን የምታድሰው አስተምህሮ የላትም። አልተመቸኝም ያለ 100% የሱን የመሰለ ትምህርት የሚከተሉት ጋር ጴንጤዎች ጋር መሄድ ይችላል። ማቆች በርቱ።

  ReplyDelete
 17. This comment has been removed by a blog administrator.

  ReplyDelete
 18. This comment has been removed by a blog administrator.

  ReplyDelete
 19. This comment has been removed by a blog administrator.

  ReplyDelete
 20. amlak yfredibachihu yetewahdo ljoch gn slaweknachihu atdkemu mk bertu tenkru

  ReplyDelete
 21. እናንተ ሰወች ለምን በራሳችሁ ቤተ ፀሎት የምታመልኩን እዛው አታመልኩም ስለ ቤተ ክርስቲያን የተዋህዶ እምነትን ለሚያምኑት ተውት አምልኮታችን እንዴትና ማንን እንደምናመልክ እናንተ ለኛ ልታስተምሩ አልተፈቀደላችሁም ሀይማኖታችሁ ሌላ ነውና::

  ReplyDelete
 22. migbare seytanoch,yeseytan lijoch nachihuna tiru neger des ayilachihum.

  ReplyDelete
 23. በመጀመሪያ እግዚአብሔር አምላክ ልቦና ይስጣችሁ፡፡ ቢገባችሁ ክርስቲያኖችን እያሳደዳችሁ ያላችሁ እናንተ ናችሁ፡፡ እግዚአብሔር ያከበራቸዉን ቅዱሳንን ባለመክበራችሁ፡፡ ይህች በክርስቶስ ደም የተመሰረተች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳንን እንደየክበራቸዉ ታመሰግናለች ባማላጅነታቸዉም ታምናለች፡፡ አንድም ቀን ወንጌልን ሳታስተምር ቀርታ አታዉቅም፡፡ ቅዳሴዉ፣ ሰዓታት፣ ኪዳን፣ ማህሌት፣ ወ.ዘ.ተ የቤተከርስቲያን አገልግሎት ወንጌል ነዉ፡፡ እናንተ አይነልቦናችሁ ታወረባችሁ እንጂ፡፡
  ስለዚህ መታደስ ያለባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሳትሆን እናንተና መሰሎቻችሁ ናችሁ፡፡ ለምን በዚች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ወስጥ ሁናችሁ ከምትበጠብጡ ራሳችሁን ለይታችሁ እንደ ፕሮቴስታንት እመነቶች የራሳችሁን የእምነት ድርጅት አታቐቁሙም፡፡

  ReplyDelete
 24. Enanite Yewishi Kitiregnosh,Yeethiopian Bete Kirisitiyanin Lemin Atitewatim weyiem sertashu asayun Yemisera beminikef bisha lemin tinoralashu

  ReplyDelete
 25. good massage. keep writing abaselam. the GOOD-NEWS will reach every block of Ethiopia and of course the world. Just keep believing and understand those who don't get it. hopefully they will get it soon. lets be patient with them as our God is patient with us. we should love them and show them how our God is awesome. the first step on preaching the Gospel is to spill or shed our love towards them. May God bless Ethiopia.

  ReplyDelete
 26. በማ/ቅ ጉዳይ ላይ እረፍት የላችሁም በቃ:: ምን ይሻላችኋል እናንተም እያጥላላችሁን ማቅም እያደገ እየጎለማሰ ሄደ::

  ReplyDelete
 27. the writer of this article might be guy

  ReplyDelete
 28. ለምንድነው ይህን ያህል የምትፈሯቸው ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ቤ/ክ እኮ የእነሱ ብቻ አይደለችም!!ይህን ካልተቀበሉ እንዲቀበሉ ይደረጋሉ ስለዚህ እነርሱን አትፍሯቸው እኛንም አታስፈራሩን!!ተሐድሶ ነን ነን በቃ እንኳን የኦርቶዶክስ ቤ/ክ 1650 ዓመት የቆየችው የዛሬ 150 ዓመት ኢትዮጵያ ገብተናል እውነተኛ ወንጌል እንሰብካለን የሚሉትና የተሐድሶ ጀማሪዎች ነን የሚሉትና ኦርቶዶክስን እናድሳለን የሚሉት ራሳቸው ተሐድሶ እያስፈለጋቸው ነውና አትስጉ ተሐድሶው እንደኢዮስያስ ተሐድሶ ለምድሪቱ ሥር ነቀል ሆኖ ስለሚመጣ ወኔ የሚያስፈታ የሰይጣን መሣሪያ ከመሆነ ለተሐድሶው ግብ መምታት የሚያስፈልገውን አስተምህሮ አቅርቡ!!
  ኒቆዲሞስ

  ReplyDelete
 29. keahun behuala wegzet yelm man yilekachewal mk teret teretun yakoalewenetena wengel betewahedo yisebekal yetewegezutem yimelesalu gezew ruk ayedelem

  ReplyDelete
 30. Lemin ke MK gar abrachihu atiserum?

  ReplyDelete
 31. ኒቆዲሞስ… አየህ አይደል መንፈስ ቅዱስ እንዴት እንደሚያናግር አንተን መናፍቁን እንኳን አናገረህ ምንም እንኳን ኦርቶዶክስን ያጥላላህ መስሎህ 1650 አመት የቆየች ብለህ ከጥንት ጀምሮ ከቅዱሳን ሃዋርያትና ከቅዱሳን አበዉ የተቀበለችዉን እዉነት እስከዛሬም የመበቀች መሆኗን አናገረህ በተቃራኒዉ እናንተ ደሃድሶ ነን የምትሉት ደግሞ ገና አሁን የተፈለፈላችሁ ሌላዉ ቀርቶ የሉተር ልጆች እንከኳን እንደሚበላጧችሁ ተናገርክ ገሩም ነዉ፡፡ ለማንኛዉም ቤ/ን በክርስቶስ ደም የተመሰረተች ስለሆነች ሁሌም አዲስ ናት መስራቿ ክርስቶስ ሁሌ አዲስ እንደሆነ ሁሉ፡፡ መቸም ሳራ አረጀች እንደማትል ተስፋ አደርጋለሁ ቅዱስ ጳዉሎስ አጋርን ያሮጌዉ(ኦሪት) ሳራ ደግሞ የአዲሱ(ወንጌል) ኪዳን ምሳሌዎች እንደሆኑ ነግሮናል፡፡ እናም አንተና ወገኖችህ ሳራ አረጀች ስትሉ ወንጌልን እየነቀፋችሁ መሆኑን አስተዉል፡፡ እኛ እንደሆንን ሃዋርያዉ እኛ ከሰበክንላችሁ ዉጭ ማንም ከሰማይም ቢሆን ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን የሚለዉን ትምህርት ስለምናዉቅ የናንተን የተለየ ወንጌል የምንሰማበት ጆሮ የለንም፡፡ ለራስህ ግን በመሰረቱ ላይ እንዴት እንደምትገነባ ተጠንቀቅ!

  ReplyDelete
 32. አለመማርና ተንኮል ተዳብለው በመማቅና በጠንሳሾቹ አንጎል ሥር በመስደዳቸው በቅለው አብበውና አፍርተው እስቲጠወልጉ እስቲደርቁና እስቲረግፉ ድረስ መገምገማቸው አይቀሬ ነው የእወጃቸውም ፍሬ
  ከመልካም ነገር የማይገጥም እሬትና መራራ ነው ዮሐ 9.22--23 እስመ አዘዙ አይሁድ ለእመቦ
  ዘአምነ ቦቱ ከመ ውእቱ ክርስቶስ ይሰደድ እምኵራብ የሰው ልጆች ረፍት የላቸውምና ከርስቶስን የተቀበለውን በክርስቶስ ያመነውን
  ሁሉ ከጉባኤ ይለዩትና ያወግዙት ነበር ማቆችም የነሱን ታምር ያልተቀበለና በክርስቶስ ያመነውን
  ያሳድዱታል፤ ያውም ጽዋቸው እስቲሞላ ነው፤

  ReplyDelete
 33. መጽሐፍ ቅዱስን ጠንቅቆ የማያውቅ ሰባኪ ከዚህ በላይ ማለት አይችልም፡፡ ከፊት ለፊቱ ያገኛትን እየገለበ አንደበቱንና ጽሑፉን በማሳመር እውነትን ያስተማረ ይመስለዋል፡፡ እባክህን እውነትን የምትፈልግ ከሆነ ደግመህ ደጋግመህ መጽሐፍ ቅዱሱን እየዉ፤ በርትተህም ፀልይ ይገለጽልሀል፡፡ የጥላቻ፣ የእልኸኝነትና የጥቅመኝነቱን ጉዞ ተወዉ፡፡ ማንነትህን በማወቄ ደስተኛ ነኝ፡፡

  ReplyDelete