Sunday, October 14, 2012

“ያለ ወላዲተ አምላክ አማላጅነት ዓለም አይድንም!” የሚለው ጥቅስ ምንጩ ማነው?

ክፍል 2
በዚህ ርእስ ያቀረብነውን ጽሑፍ ተከትሎ በርካታ ሰዎች ጽሑፉን በመደገፍም በመቃወምም አስተያየቶቻቸውን ሰጥተዋል፡፡ በተለይም ዓለም የሚድነው በማርያም አማላጅነት ነው የሚለውን የክሕደት ትምህርት የደገፉ ሰዎች በእኛ እምነት ምንም አሳማኝ ማስረጃ አቅርበዋል ማለት አንችልም፡፡ አብዛኞቹ በጭፍን የተሞላና የያዝነውን ልማዳዊ የክህደት ትምህርት በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አናርምም፤ ምን ታመጣላችሁ? ያሉ ነው የመሰለን፡፡ አንዳንዶቹ ግን አዳኝነትን የጸጋና የባሕርይ በሚል ከፋፍለው ለማደናገር ሞክረዋል፡፡ በተለይም በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ድረ ገጽ ላይ መምህር ሙሴ በተባሉ ሰው የወጣውንና «ለመሆኑ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም "መድኃኒተ ዓለም" ትባላለችን?... ለምን? ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለውን ግኑኝነትና ልዩነት እንዴት ይገለጻል?» የሚለውን ጽሑፍ መከራከሪያ አድርገው አቅርበዋል፡፡ ይህ ጽሑፍ በዚህና ተመሳሳይ ይዘት ባላቸው አስተያየቶች ላይ ተመሥርቶ «ያለ ማርያም አማላጅነት ዓለም አይድንም» በሚለው የክህደት ትምህርት ዙሪያ መብራራት ያለባቸውን ሐሳቦች እናብራራለን፡፡

መምህር ሙሴ እንዲህ ብለዋል፤ «መጻሕፍተ አምላካውያትን መሠረት በማድረግ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም እና ቅዱስ መስቀል ‹መድኃኒት› በማለት ታምናለች፣ ታስተምራለች፣ ትመሰክራለች፣ በሥርዓተ አምልኮዋ ጊዜም ትማጸንባቸዋለች፡፡ ይህንኑ ጥንታዊ የቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ በአግባቡ ባለመረዳት የተነሳም አንዳንድ የሚተቹ ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በመሠረቱ መተቸትና አስተያየት መስጠት በጣም የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡ ምክንያቱም በተለይ ኢሙሁራዊ አስተያየትና ጭፍን ተቃውሞ ለማቅረብ ብዙ ስለጉዳዩ ማወቅ ላያስፈልግ ይችላል፡፡ ትችት ለመስጠት ግን ቅድሚያ ስለምትተቸው ነገር በቂ ዕውቀት ሊኖርህ ግድ ነው፡፡ ቢሆንም ግን አሁን ባለው ሁኔታ እነዚህ ጉዳዮች ሰንሰለታቸውን ሳይጠብቁ እየተገለገልንባቸው ስለሆነ እንደ ትልቅ ቁም ነገር የሚያቀርቡት "መድኃኒት ፈጣሪ ብቻ ነው፣ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ብቻ ነው" የሚል ቁንፅል ሐሳብ መነሻ በማድረግ ይህን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ወትውፊታዊ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ለመተቸት ይሞከራሉ፡፡»

 እውን መምህሩ እንዳሉት መጻሕፍተ አምላካውያት (በግእዙ ሰዋስው መጻሕፍተ አምላካውያት አይልም፤ «መጻሕፍት አምላካውያት» ነው የሚለው) ማርያምና ዕፀ መስቀልን መድኃኒት ናቸው ሲሉ ያስተምራሉ ወይ? እንዲህ ቢሆን እኮ እኛ ሐሰተኞች እነርሱ እውነተኞች በሆኑ ነበር፡፡ ምናልባት መጻሕፍት አምላካውያት በተባሉት መጻሕፍት ላይ የጋራ መግባባት የለንም ይሆናል፡፡ መምህር፣ ለእርስዎ አዋልድ መጻሕፍት ሁሉ መጻህፍት አምላካውያት ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡ እውነተኞቹ አባቶች እንዳቆዩልን ግን መጻሕፍት አምላካውያት ብሉያትና ሐዲሳት ብቻ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ቅዱሳት መጻሕፍት ማርያምና መስቀል መድኃኒት ናቸው የሚል ቢያሳዩን ደስ ይለናል፡፡ እኛም ተሳስተናል ለማለት አናፍርም፡፡ ነገር ግን ለአፍዎ እንዲህ አሉ እንጂ፣ በጽሑፍዎ ውስጥ ከመጻህፍት አምላካውያት አንድም ምስክር አላመጡም፡፡

እኛን ጨምሮ ሌሎችም ይህን የክህደት ትምህርት የተቃወሙት፣ መምህር ሙሴ ሐሰት ጽፈው እውነተኛ ነኝ ለማለት እንደሞከሩት ማርያምና መስቀል መድኃኒት ናቸው የሚለውን ትምህርት በአግባቡ ባለመረዳት ሳይሆን፣ ትምህርቱ የክርስትናን መሰረት የሚንድ ክህደት በመሆኑ ነው፡፡ ይህንንም በማስረጃ አስደግፈን እናስተነትናለን፡፡ ከዚያም ማን «ኢሙ[ም]ሁራዊ አስተያየትና ጭፍን ተቃውሞ» እንዳቀረበ አንባቢው ይፈርዳል፡፡

መድኃኒቱ ማነው? በሚለው ነጥብ ዙሪያ፣ ደረጃ አውጥታችሁና ሰንሰለት ቀጣጥላችሁ ለምታሰራጩት ክህደት በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት መሠረት እየቀረበ ያለውን እውነትን ከሐሰት የመለየት አገልግሎት በማቃለል «እንደ ትልቅ ቁም ነገር የሚያቀርቡት ‘መድኃኒት ፈጣሪ ብቻ ነው፣ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ብቻ ነው’ የሚል ቁንፅል ሐሳብ መነሻ በማድረግ ይህን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ወትውፊታዊ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ለመተቸት ይሞከራሉ፡፡» ብለዋል፡፡ ምነው መምህር! መጽሐፋዊ ያልሆነውን የማርያምን «መድሃኒትነት» አግዝፈው መጽሐፋዊውን የኢየሱስን መድኃኒትነት አኮሰሱ? እንዴትስ ይህን ትልቅና ፍጥረቱን ሁሉ የሚያሳርፍና ፈውሰ ነፍስ ወሥጋ የሚያድል መድኃኒት «ቁንጽል» ሲሉ አቃለሉት? ከስምዎ ለጥቆ ያሰፈሩት የትምህርትዎ መግለጫ ነገረ መለኮት እንዳጠኑ ይናገራል፡፡ ታዲያ መድኃኒትዎ ማን እንደሆነ ሳይለዩ ነው ከመንፈሳዊ ኮሌጅ ተመርቀው የወጡት? በጣም ያሳዝናል፡፡ መቼም ማርያምን «መድኃኒት» ማለት ወፍራም እንጀራ ቢያበላዎ እንጂ ለነፍስዎ የሚሆን መድኃኒት እንዳልሆነ ለእንጀራ ሲሉ በማይረባ ዋጋ የሸጡት ህሊናዎ ያውቀዋል፡፡

«ማርያምና መስቀል መድኃኒት ናቸው፤ ይህ ጥንታዊና ሐዋርያዊ ትምህርት ነው» ከማለት በቀር፣ የማርያምንና የመስቀልን መድኃኒትነት ለማስረዳት ስለዚህ ጉዳይ የሚናገር አንድ ጥቅስ እንኳ ከመጽሐፍ ቅዱስ ማቅረብ አልቻሉም፡፡ የመረጡት መንገድ ሌሎች «አዳኝ፣ መድኃኒት» የተባሉ የእግዚአብሔር ሰዎችን ከመጽሐፍ ቅዱስ በመጥቀስና በማነጻጸር እነርሱ «አዳኝ፣ መድኃኒት» ከተባሉ ማርያም «መድኃኒት» ብትባል ችግሩ ምኑ ላይ ነው የሚል ዓይነት የንጽጽር መንገድ ነው፡፡ ይህም ቢሆን ችግር ያለበት አነጋገር ነው፡፡ በቃሉ ላይ እንደ ተጻፈው መድኃኒት እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ እርሱ ከእኔ በቀር የሚያድን ማነው? እግዚአብሔር እንዲህ ይላል «ይናገሩ ይቅረቡም በአንድነትም ይማከሩ ከጥንቱ ይህን ያሳየ ከቀድሞስ የተናገረ ማን ነው? ያሳየሁም የተናገርሁም እኔ እግዚአብሔር፡፡ አይደለሁምን? ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም እኔ ጻድቅ አምላክና መድኃኒት ነኝ፥ ከእኔም በቀር ማንም የለም። እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ፥ እኔ አምላክ ነኝና፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና ወደ እኔ ዘወር በሉ ትድኑማላችሁ።» (ኢሳ 45፡21-22)
«አሁንም እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ እዩ፤ እኔ እገድላለሁ፥ አድንማለሁ፤ እኔ እመታለሁ፥ እፈውስማለሁ፤ ከእጄም የሚያድን የለም።» (ዘዳ. 32፡39)

መምህር ሙሴ ግን ማርያምን «መድኃኒተ ዓለም» ለማድረግ መድኃኒትን የባሕርይና የጸጋ በሚል ከፋፍለዋል፡፡ እርሳቸው ስለመድኃኒት ከመግለጽዎ በፊትም «ቅዱስ፣ ብርሃን፣ ፀሐይ፣ ፈራጅ፣ አምላክ፣» ተብለዋል ካሉ በኋላ፣ መድኃኒት የሚለውን ቅጽል ወይም ስያሜ አምላክ በባሕርዩ ሲጠራበት፣ ቅዱሳን ደግሞ በጸጋ ይጠሩበታል ሲሉ አብራርተዋል፡፡ ለምሳሌም ስለጌታ መድኃኒትነት የተነገረውን ከትንቢተ ዘካርያስ 9፡9 ላይ "አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በይ፤ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሑትም ሆኖ በአህያም በአይህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል" የሚለውን ጠቅሰዋል፡፡ «በመጽሐፍ ቅዱስ ጎቶንያል ‘አዳኝ፣ መድኃኒት’ ተብሎ ተጠርቷል፡፡ መጽ.መሳ.3፡9» ብለዋል፡፡ በተመሳሳይም "የእስራኤል ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም ብንያማዊውን የጌራን ልጅ ናዖድን ግራኙን ሰው አዳኝ አስነሣላቸው፡፡ የእስራኤልም ልጆች በእርሱ እጅ ወደ ምዓብ ንጉሥ ወደ ዔግሎም ግብር ላኩ" መጽ.መሳ. 3፡15» ብለዋል፡፡ በሦስቱ ጥቅሶች ውስጥ እንደእርስዎ ሐሳብ ጌታም ጎቶንያልና ናኦድም «አዳኝ መድኃኒት» ተብለዋል፡፡ አማርኛውም ግእዙም ለሦስቱም የተጠቀመው ቃል ተመሳሳይ ቢሆንም፣ በእንግሊዝኛው ስለጌታ ለተጻፈው “Salvation” የሚለውን ሲጠቀም፣ ስለጎቶንያልና ስለ ናኦድ ለተጻፈው ደግሞ “Deliverer” የሚለውን ነው የተጠቀመው፡፡ ይህ በራሱ የሚነግረን እውነት አለ፡፡ ከዚያ በላይ መሳፍንቱ አዳኝ የተባሉበት ሁኔታ ጌታችን አዳኝ ከተባለበት ሁኔታ እጅግ የራቀ ነው፡፡

ጎቶንያልና ናዖድ አዳኝ ተብለው የተጠሩት የእስራኤልን ልጆች በኃጢአታቸው ምክንያት ተላልፈው ለአሕዛብ ከተሰጡና ለዓመታት ከተገዙላቸው በኋላ ወደእግዚአብሔር አድነን ብለው ስለጮኹ እነርሱን ነጻ እንዲያወጡ መሪ አድርጎ ስላስነሳቸውና ነጻ ስላወጧቸው ነው እንጂ፣ እነርሱ «በጸጋ» የነፍስ አዳኝ ወይም ከኃጢአት የሚያድኑ ናቸው ለማለት አይደለም፡፡ እግዚአብሔር አስነስቷቸው እስራኤልን ከአሕዛብ እጅ ነጻ ያወጡትም በሕይወተ ሥጋ እያሉ ነበር፡፡ አዳኝ መባላቸውም ከላይ እንደተመለከትነው ሕዝቡን በመምራት ከሚገዟቸው እጅ ነጻ ማውጣታቸው ነው እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ባስነሣቸው ታዳጊዎች በኩል ሕዝቡን ያዳናቸውም ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ ስለዚህ ክብሩ የጸጋና የምንተስ ተብሎ ሳይሸራረፍ ተጠቅልሎ ሊሰጥ የሚገባው ለእግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ እነርሱ በዚህ ውስጥ እርሱ ያስነሣቸው ቅዱሳን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ፈጻሚ አገልጋዮች እንጂ አዳኞች አይደሉም፡፡ ሊታዩ የሚገባው በዚህ ደረጃ ብቻ ነው፡፡ ይህ የእነርሱን ትክክለኛ ስፍራ መናገር እንጂ እነርሱን ማቃለል አይደለም፡፡

አንዱ አስተያየት ሰጪም፣ «ወንድሜ እኔን በጸጋ አዳኙንም ከመዝገብህና ከቃልህ አትርሳኝ፡፡ መጽሐፍ በይሁዳ መልዕክት 22 ላይ አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፥ በማለት የእኔን የከንቱውን አዳኝነትም እንኳን ይናገራል፣ እንኳንስ የአምላክ እናት ለመሆን የበቃችውን ቅድስትና ብፅዕት ቀርቶ፡፡» ብሏል፡፡ አንድን በሽተኛ ወደ ወደሚያድነው ሐኪምና መድኃኒት ያደረሰ ሰው አዳኝ አይደለም፤ አዳኝም አይባልም፡፡ በአስተያየቱ መሰረት ወንጌልን ሰብኮ ሰዎችን ወደክርስቶስ የሚያመጣ ከሆነ ይህ አገልግሎት እንጂ አዳኝነት አይደለም፡፡ እንዲህ አይነቱን እገዛና አገልግሎት መስጠት  የሚቻለው በሕይወተ ሥጋ ሳሉ ብቻ ነው፡፡
 
ዛሬ በሕይወተ ሥጋ የሌለችው ድንግል ማርያም የምታድነው ግን እንዴት ነው? የምንድነውስ ከምንድን ነው? የጌታ አዳኝነት የት ሄዶ ነው ያለእርሷ አማላጅነት ዓለም አይድንም የተባለው የሚለው ግልጽ አይደለም፡፡ ክርክሩ ያለው እዚህ ላይ ነው፡፡

ምናልባት እዚህ ላይ ብዙዎች ነቢዩ ኤልሳዕ ከሞተና ከተቀበረ በኋላ፣ ሰዎች አደጋ ጣዮችን ለመሸሽ ሲሉ ሊቀብሩ ይዘው የመጡትን አስከሬን መቃብሩ ላይ ሲጥሉ ሬሳው መነሣቱን ቅዱሳን ከሞቱ በኋላም ሊፈውሱ እንደሚችሉ ማስረጃ አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡ ይህ የተለየ /exceptional/ ክስተት ነው እንጂ ቋሚና ሁሉም ከሞተ በኋላ በመቃብሩ ተመሳሳይ ተአምር እንደሚሠራ የተደነገገ ሕግ አይደለም፡፡  እንዲያማ ቢሆን ሁሉም የሞተበትን ሰው አስከሬን ይዞ እየሄደ ኤልሳዕ መቃብር ላይ እየጣለ ባስነሳ ነበር፡፡ እንዲህ ሲሆን ግን አንመለከትም፡፡ ሊሆንም አይችልም፡፡ ደግሞም ይህ ለአንድ ጊዜ ብቻ የተከናወነ ተአምር እንጂ ከኃጢአት በሽታ የመዳን ነገር አይደለም፡፡

ከክርስትና ትምህርት ውጪ የሆኑ ሰዎች ያለ ማርያም አማላጅነት ዓለም አይድንም ሲሉ ማርያም ከምን እንደምታድን ሊገልጹልን አልቻሉም፡፡ ስለዚህ ዓለም የሚድነው በእርሷ አማላጅነት የሚሉ ሰዎች ይህን ቢያብራሩልን መልካም ነው የሚሆነው፡፡ እንደሚታወቀው ዓለም የዳነውና የሚድነው ስለዓለም ቤዛ ሆኖ በተሰቀለው በመድኃኒታችን በኢየሱስ ቤዛነት ብቻ ነው፡፡ የእርሱም የሚያድነው ከኃጢአት ነው፡፡ ከኃጢአት የሚያድነው መድኃኒትም እርሱው ብቻ ነው (ማቴ. 1፡21)፡፡ ከእርሱ በቀር በጸጋም ይሁን በሌላ መንገድ ደረጃ ወጥቶለት ከኃጢአት እንዲያድን ውክልና የተሰጠው ፍጡር መልአክም ሆነ ሰው የለም፡፡ ማርያም ታድናለች የተባለው ታዲያ ከምንድን ነው? እንዴትስ ነው የምታድነው? «ያለ ማርያም አማላጅነት» ነውና የተባለው አባባሉ የኢየሱስን አዳኝነት የሚያስተሐቅር (የሚያቃልል) አይሆንም ወይ? መልሱን እንጠብቃለን፡፡

30 comments:

 1. Awo aydinim! Enantem niseha kalgebachihu atdinum!

  ReplyDelete
 2. This helps me know who u r? Kehadiwoch.

  ReplyDelete
 3. Enante leka nufakena kihidet new yemtastemrut.Yematrebu nachu degmo eskezare blogachun siketatel mekoyete.

  ReplyDelete
 4. አባ ሰላማዎች እናመሰግናል ፤
  መዳን በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መሆኑ ለሁሉም ግልጽ ሊሆን ይገባል፡፡

  ReplyDelete
 5. It is greate arteculate that living with traditional way of life. Now a day the critical obstacle to preach bible in Ethiopia is MK. Biterly, use church money to attack and killing of truth speaker. If mk is real , why they should have given safe heaven criminal monk such like zelebanose being with aids and zemot. Death to mk peace to Eotc.

  ReplyDelete
 6. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

  ወቅቱ ወርሃ ጽጌ በመሆኑ ፣ የኢኦተ ቤተ ክርስቲያን ፣ ቅድስት ድንግል ማርያምን በተለየ ሁኔታ የምታስብበትና የምታወድስበት በመሆኑ ይኸንን የአባቶች አገልግሎት ለመበረዝ ፣ ለክፉው መንፈስም ዕድል ለመስጠትና በረከታችንን ለማሳነስ መሞከራችሁ ይመስላልና ትግላችሁ አይደንቅም ፡፡

  ባቀረባችሁት ጽሁፍ ላይ የተብራራ መግለጫ እንዳልሰጥበት ፣ የማንግባባ ፣ የሁለት ቤተ እምነት ልጆች መሆናችንን በግልጽ አስቀምጣችሁታልና አልሞክረውም ፡፡ ለመጠቃቀስም

  1.መጽሐፍተ (መጽሐፍት) አምላካውያት የሚባሉት ብሉያትና ሐዲሳት ብቻ ናቸው የሚለው ማሰሪያችሁ ነው ፡፡ በትውፊትና በቅብብል የደረሱን ቅዱሳት መጽሐፍትና ትምህርተ አበው በሙሉ አፈር ይብሉ የማለት ያህል ስለሆነ እኔን እኔን እኔን … ያሰኛል ፡፡

  2.ሌላው ድክመትም አዳኝ የሚለውን የአማርኛ ቃል ምናልባትም ከሥረ መሠረቱ አመጣጡን ለመተንተንና ለመተርጎም ግፋ ቢል ወደ ግዕዝ ይራመዱ እንደሆነ እንጅ ወደ እንግሊዝኛ ቃል ተሻግሮ ምንም ዝምድናና ግንኙነት በሌለው ቋንቋ ለመፍታትና ለማስረዳት መሞከርም ሌላው የመልዕክታችሁ ስህተት ነው ፡፡

  3.እንዲያው የመጽሐፍ ቅዱሱን ቃል ከሥረ መሠረቱ በትክክል እንረዳና እንተርጉም ቢባል እንኳን ፣ በመጀመሪያ በተጻፉበት ቋንቋ (ዕብራይስጥና ግሪክ)፣ ከዛ ባለፈ ደግሞ ከግዕዙ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ፈልጋችሁ ብታስረዱ ትንሽ ያከራክርላችሁ ነበር እንጅ ፣ አስተማሪዎች እንደ ባትሪ ሞልተው የሰጧችሁን ቃል ማስተጋባታችሁ ማንንም አያሳምንም ፡፡ እንግሊዝኛም የመጀመሪያው የመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋ አይደለምና ፡፡

  4.በሰጣችሁን ትርጉም መሠረት ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሱት የአዳኝነት ሥራዎች አገልግሎት ማለት ስለሆነ ማዳን አይባልም የሚል አንደምታ አለው ፡፡ ይኸም ደግሞ ጌታችን ፣ መድኃኒታችን ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የፈጸመውን የማዳን ሥራ አገልግሎት ነው ማለት አይደለም ሊያሰኝ ነውና በማርቆስ ወንጌል 1ዐ፡45 የተጠቀሰውን “የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ ፤ እንዲያገለግሉት አልመጣም” የሚለውን የቅዱስ መጽሐፍ ቃል ያፈርሳል ፡፡ ስለሆነም ከዚህ ቀደም በሥርዓቱ የተብራራው የማዳን ትርጉም የተሟላ ግንዛቤ ስለሚሰጥ መለስ ብላችሁ መርምሩት ፡፡

  5.በጽሁፋችሁና ከጠቀሳችሁት መጽሐፍተ አምላካውያት ውስጥ ፣ ቅድስት ድንግል ማርያም አታድንም የሚል የቃል በቃል የጽሁፍ ማስረጃ አላቀረባችሁልንም ፡፡ ነገር ግን የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንትና አባቶች በመወራረስ ያደረሱንን እምነትና ትምህርት ማስረጃ እንዲቀርብላችሁ ትጠይቃላችሁ ፡፡ ይኸም አመለካከታችሁን ሚዛናዊ አያደርገውምና ፤ እኔም መጀመሪያ እናንተ ተቃራኒዎቹ ያገኛችሁትን ማስረጃ አቅርቡትና እንይላችሁ እላለሁ ፡፡

  6.ሌላው በተደጋጋሚ የጠቀሳችሁት ቃል በሕይወተ ሥጋ ሳሉ ብቻ የሚለው ሐረግ ነው ፡፡ ይኸም “የህያዋን አምላክ ነኝ እንጂ ፣ የሙታን አይደለሁም” የሚለውን የመጽሐፍና ፣ የአምላክንም ቃል ይጣረሳልና የምትጠቀሙበትን መጽሐፍ ትክክለኛነት በውል ፈትሹት

  በተረፈ ነገረ ድኀነት ሲመረመር
  - አምላክ ሰው መሆኑ ፡- ሰው መሆን የጀመረውም በድንግል ማርያም ማኀጸን ነውና
  - የሰዎችን መከራና ችግር እያየ በሰዎች ልክ ማደጉ ፡- ድንግል ማርያም ፣ የገጠመኙ ተካፋይ ጠባቂና ተንከባካቢነቷንም ያስቧልና
  - ድኀነትን አግኝተንበታል ብለን የምንመሰክረው በመስቀል ላይ የቀረበው ሥጋና ደሙ ፣ ከእርሷ የነሳው በመሆኑ ልንክዳት ብንፈልግ እንኳን መካድና መሻር የማንችለው የተሰጠችን በጸጋ የመዳናችን ምክንያት ነች ፡፡ መዳፈር ካልተባለ አንድን ሰው ጠላቱ ቢገድለው በምን ገደለው ተብሎ እንደሚጠየቅ ፤ ሲያድነውም ደግሞ በምን አዳነው ብሎ መጠየቅ ይገባልና ፡፡ የዳንንበት ሥጋና ደም የኰርማና የበግ እስካልሆነ ድረስ ነገረ ድኀነትን በቁንጽል እንደሚያመቸን አንመልከተው ፡፡

  ወስብሐት ለእግዚአብሔር

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቃለ ሕይወት ያሰማልን!!!

   Delete
  2. ቃለ ሕይወት ያሰማልን!!!

   Delete
  3. እናንት የማኅበረ ቅዱሳን ጭነቶች መቼ ይሆን ከመጽሐፍ ቅዱስ በመነሣት ነገሮችን መመልከት የምትጀምሩት?
   አንተ እውነተኛ ነኝ በማለት የምትናገር በተግባር ግን ሆነህ የማትገኝ እንደሆንክ ባሰፈርካቸው ነጥቦች ይታወቃል። በእርግጥ መጻሕፍት አምላካውያት መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ አይደለም፤ ሌሎች በትውፊት የተላለፉ መጻሕፍት ሁሉ ናቸው ከምትል ከአንተ ጋር መግባባት አይቻልም። የኦርቶዶክስን አስተምህሮ በደንብ ሳትረዳ ማኅበረ ቅዱሳን የጫነህን አራገፍክብን እንጂ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መጻሕፍት አምላካውያት የምትለው መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ነው። ሌሎቹ መጻሕፍት መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርገው የተጻፉ እንደሆኑና በመጽሐፍ ቅዱስ ሊመዘኑ እንደሚገባም እምነቷ ነው።

   ለመተቸት በሞከርከው ጽሑፍ ላይ "አዳኝ" የሚለውን የአማርኛ ቃል ለመተርጎም ወደግእዝ መሄድ እንጂ ወደ እንግሊዝኛው መሻገርን ኮንነሃል። አማርኛና ግእዙ እኮ እስራኤልን ከጠላት ነጻ ያወጡትን ነጻ አውጪዎች፣ ሰውን ከኀጢአት ያዳነውን ቤዛም "አዳኝ" ብለው ነው የጠሩት። ቃሉን በየዐውዱ ብንመለከተው አያሳስተንም ነበር። ነገር ግን ከኢየሱስ ሌላ አዳኝ የፈለጋችሁ አንተና ዘመዶችህ በየዐውዱ ሊታይ የሚገባውን "አዳኝ" የሚለውን ቃል ለጥፋታችሁ ተጠቀማችሁበት። ሁሉም ቋንቋ ፍጹም አይደለም። በቃላት ሀብቱ ብዛትና የተለያዩ ነገሮችን በተለያዩ ቃላት በመግለጥ ብቃቱ ደግሞ አንዱ ከአንዱ የተሻለ ይሆናልና አጠቃቀሙ ከዚያ አንጻር ቢታይ የተሻለ ነው። ከዚህ ውጪ ግዕዝን ለኩራት መጥቀስ እውነትን ከእውነትነቱ ፈቀቅ አያደርገውም። ደግሞም አንተ ሲያደንቁ ሰምተህ የግዕዝ አድናቂ እንጂ ግእዝ አዋቂ እንዳልሆንክ መገመት ከባድ አይደለም። ይህን አባባል ሐሰት ለማድረግ እስኪ ግእዙን መሠረት አድርገህ የተነሣውን ሐሳብ በማስረጃ አስደግፈህ አስተባብል! ደግሞስ አንተ እብራይስጥና ግሪኩን ትቀበላለህ እንዴ? ግእዙን መሰረት ያደረገ የተባለውን የ2 ሺሁን መጽሐፍ ቅዱስ አየነው እኮ! በተለይም አዲስ ኪዳኑ ከግሪኩ የተለየ መሆኑን በግርጌ ማስታወሻው ላይ “በግሪኩ እንዲህ ይላል” የሚሉ በርካታ ቃላቶች እንዳሉበት ራሱ በራሱ መስክሯል። “ኪንግ ጀምስ ቨርዥንን” የመሳሰሉ የእንግሊዝኛ ትርጉሞች ከግእዙ ትርጉም የተሻሉ እንደሆኑ የሰማ ሳይሆን ያነበባቸውና ያመሳከራቸው ብቻ ነው የሚያውቀው።

   4ኛውን እርባና ቢስ መከራከሪያ ነጥብ ምላሽ መስጠት አስፈላጊ መስሎ አልታየኝም። የማይሆን የቃላት ጨዋታ ነውና አእምሮህን እንደገና አሰርተህ የጻፍከውን እንድትመረምረው ላንተው በመስጠት ልለፈው።

   "በጽሁፋችሁና ከጠቀሳችሁት መጽሐፍተ አምላካውያት ውስጥ ፣ ቅድስት ድንግል ማርያም አታድንም የሚል የቃል በቃል የጽሁፍ ማስረጃ አላቀረባችሁልንም ፡፡" ብለሃል። ለዚህ መልስ መሰጠት ያለበት አንተም “ታድናለች” የሚል ማስረጃ ከመጻሕፍት አምላካውያት ስታመጣ ቢሆን ይመረጣል። አንድ መሠረታዊ መርህ ግን ልጠቁምህ እወዳለሁ። አንተ የምታራምደው ትምህርት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ቃል በቃል ይጻፋል ብለን መጠበቅ የለብህም። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ በሌላ ገጽታው ከአንተ አቋም በተቃራኒ ሊናገር ይችላል። አሁን የተነሣውን ሐሳብ መሰረት አድርጌ ለማስረዳት ልሞክር፤ መጽሐፍ ቅዱስ "መዳንም በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የተሰጠን ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና" ይላል (የሐዋ. 4፡12)። ስለዚህ ቃል በቃል ባይጻፍም ያለድንግል ማርያም አማላጅነት ዓለም አይድንም የሚለው ትምህርት ይህን መጽሀፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ተቃርኖ የሚገኝ በመሆኑ ሌላ ጥቅስ ፍለጋ ሳይኬድ በክህደት ትምህርትነት ሊፈረጅ ይገባል።

   ስለ6ኛው ነጥብ ዝቅ ብለህ ለሰርጸ ድንግል የሰጠሁትን ምላሽ ተመልከት።

   በመጨረሻም ነገረ ድኅነትን ከድንግል ማርያም ስጋ ጋር ማያያዝ ለምን እንደሚያስፈልግ ግልጽ አይደለም። እውነት ነው ጌታ የተወለደው ከእርሷ ነው። ከእርሷ ስለተወለደ ግን የተሰቀለው የእርሷ ስጋ ነው ማለት ምክንያታዊ አይደለም። ሰው ሁሉ ወላጆቹን አክሎና ራሱን ችሎ መወለዱ እሙን ነው። ነገር ግን በሚሆነውና በሚያደርገው ነገር ሁሉ ራሱን ችሎ የሚያደርግ በመሆኑ ክብሩንም ውርደቱንም ራሱ እንጂ ወላጆቹ በቀጥታ ሊወስዱበትም ሊወስዱለትም አይችሉም። ኀላፊው ራሱ እንጂ ወላጁ ሊሆን በፍጹም አይችልም። ክርስቶስ ጋ ሲመጣም እንዲሁ ነው። እርሱ የነሳው የማርያምን ሥጋ ነው ተብሎ መዳን በማርያም ነው ማለት የአብዬን ለእምዬ መስጠት ነው የሚሆነው።

   Delete
  4. አንተዬ ለምኑ ነው ቃለ ሕይወት? ይህ ሰው የጻፈው እኮ ቃለ ሞት ነው። መች ሐይወት ይገኝበታል? ስለዚህ ምርቃትህን አስተካክል።

   Delete
  5. ቃለ ሕይወት ያሰማልን!!!

   Delete
  6. ማነህ አንተ ፣ የሉተር (ኘሮቴስታንት) ጭነት ፤
   አየህ የኛ ሊቅና መጽሐፍ አዋቂ ፣ ድንግል ማርያም በንጽህናና ፣ በቅድስና ተጠብቃ ባትገኝ ኖሮ ዓለም እስከዛሬም ድኀነትን አያገኝም ነበር ፡፡ ድንግል ማርያም በንጽህና በመገኘቷ ፣ ቅዱስ የሆነው አምላክ ከ55ዐዐ ዘመን በኋላ የሚዋሃደው ቅዱስ ሥጋን አገኘ ፡፡ አምላክም ሰውን ለማዳን በመውደዱ ከድንግል ማርያም ሥጋና ነፍስ ተዋህዶ (ነስቶ)ሰው ሆነልን ፡፡ እልልልልል ታላቁ ምሥጢር ተገለጠልን ፤ የማይታየው ታየ ፤ የማይዳሰሰው በእቅፍ ሆነ ፡፡
   ታድያ ነገረ ድኀነትን ስታጠናው ድንግል ማርያም ባትኖር ኖሮ ጌታችን ፣ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከማን ሥጋ ተዋህዶ ሰው ይሆንና ካሣችንን ይከፍልልን ነበር ? ስለዚህም ዓለም ያለ ድንግል ማርያም አይድንም ነበር ማለት ስህተትነቱ አልተገለጸልኝም ፡፡ እሷ ለባለሟልነት ባትበቃ ኖሮ እስከ ዛሬም ድረስ ለቅድስና የሚበቃ አካል ሲፈለግ ይኖር ነበር ፡፡ አሁንስ አልገባህም ምን ማለት እንደሆነ ?

   እመ ብርሃን ብርሃኗን ትግለጽልህ

   Delete
  7. pls write by this title on eotc blogs

   Delete
  8. ቀጣይ መልስ
   በቀደም በችኰላ አንኳር መልስ አቅርቤ የተቀረውን በጊዜ እጥረት ምክንያት ስላስቀረሁት ዛሬ ቀጥዬልሃለሁ ፡፡
   1. “የኦርቶዶክስን አስተምህሮ በደንብ ሳትረዳ ማኅበረ ቅዱሳን የጫነህን አራገፍክብን እንጂ”
   - ለአሩም ለሽንቱም /ስለ ቃላት አጠቃቀሜ ይቅርታ / ማኀበረ ቅዱሳንን መጥራት ትወዳለህ ፤ ማኀበረ ቅዱሳን ድርሳን አልደረሰ ወይ ገድል አልጻፈልን ፡፡ ከአባቶች ሲያያዝ የመጣውን ትምህርት ነው የሚያስተጋባው ፡፡ አይ ይኸ ከቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት አይገጥምም ፤ በቤተ ክርስቲያናችን እንዲህ አይባልም ነበር ፤ ይኸኛው የማኀበረ ቅዱሳን ጭማሪ ብለህ ዘርዝርና ጭነታችንን እናራግፍልህ ፡፡ በደፈና ግን ማንንም አልቀበልም ፡፡ የተጻፈልንን ብታነበው እንኳን አዲስ ትምህርት ተጨመረ የተባለበት ወቅት ትክክል ባይሆንም ፣ ጸሃፊው ቢያንስ ወደ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን አድርሶታል ፡፡ ማኀበረ ቅዱሳን ደግሞ በኛ ዕድሜ ያለ የወጣት ማኀበር ሲሆን እንደምን ተጣጥሞልኝ ልቀበልህ ፡፡

   2. “የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መጻሕፍት አምላካውያት የምትለው መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ነው” ላልከው ።
   - መጽሐፍት አምላካውያት መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው ብሎ የሚደነግገውን መመሪያህን አቅርብና አስነብበን ፡፡ በተረፈ አዋልድ መጽሐፍቷ በሙሉ ከወንጌል ቃል ስለሚስማሙ ለማስተማሪያ ትጠቀምበታለች ፡፡ ይኸን አውቃለሁ ፡፡

   3. አዳኝ የሚለውን “ቃሉን በየዐውዱ ብንመለከተው አያሳስተንም ነበር። ነገር ግን ከኢየሱስ ሌላ አዳኝ የፈለጋችሁ አንተና ዘመዶችህ በየዐውዱ ሊታይ የሚገባውን "አዳኝ" የሚለውን ቃል ለጥፋታችሁ ተጠቀማችሁበት።” ላልከው
   - በክፍል አንድ የተጻጻፍንበትን መለስ ብለህ አንብበው ፡፡ ልዩነት ስላለው የባህርይና የጸጋ ተብሎ ተለይቷል ፡፡ ጸሐፊው ዛሬም እንኳን በእንግሊዝኛው “Salvation” እና “Deliverer” በማለት ለይቶታል ፡፡ ችግርህ አማርኛው ከሆነ Salvation የሚለውን እንደ ባህርይ አዳኝነት Deliverer” የሚለውን ደግሞ እንደ በጸጋ አዳኝነት አድርገህ ተረዳውና እንስማማ ፡፡

   4. “አንተ ሲያደንቁ ሰምተህ የግዕዝ አድናቂ እንጂ ግእዝ አዋቂ እንዳልሆንክ መገመት ከባድ አይደለም።” ለምትለው ችሎታዬ ይኸና ያ ነው ብዬ አልፎከርኩም ፤ ነገር ግን መንገዱ ጠፍቶብህ ቢሆን እንድታስተካክል ጠቆምኩህ ፡፡ ድኒን ፣ ድኀነት ፣ አድኀነ ፣ አድኃኒ ፣ መድኀን … እያልክ ቃላት ቁጠር

   5. “የ2 ሺሁን መጽሐፍ ቅዱስ አየነው እኮ! በተለይም አዲስ ኪዳኑ ከግሪኩ የተለየ መሆኑን በግርጌ ማስታወሻው ላይ “በግሪኩ እንዲህ ይላል” የሚሉ በርካታ ቃላቶች እንዳሉበት ራሱ በራሱ መስክሯል።”
   - ምኑ ይኸ ብቻ ይደንቅሃል ፤ ገና ብዙ ወደ አማርኛ ያልተተረጐሙ መጽሐፍት አሏት ፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን የክርስትና ሃይማኖት መዘክርነቷን (ከብሉይ እስከ ሐዲስ አሻራ ያልጠፋባት ብቸኛ የምታኰራን እናት ቤተ ክርስቲያን) መሆኗን አትርሳ ፡፡ የአዲስ ኪዳን ወንጌል ትክክለኛ ጽሁፍ ማንም ዘንድ እንደሌለ በእንግሊዝኛ የተረጐሙልህ ሰዎች መስክረዋል ፡፡ ነገር ግን ከሌሎቹ ይልቅ በብዛት ወደ 15ዐዐ ቅጅ ያህል በመገኘቱ የሐዲስ ኪዳንን መጽሐፍ በይበልጥ ተቀባይ እንዲሆን አድርጎታል ፡፡ ይሁን እንጅ እነዚህ 15ዐዐ ቅጅዎች አንዱ ከአንዱ እንደማይገጥም አሁንም የምታመልካቸው ጸሐፊዎች ተናግረዋልና ባለመስማማቱ ብዙ አትደነቅ ፡፡ ቫቲካን ያፈነቻቸውን የጽሁፍ ሰነዶች ይፋ ብታወጣ ምናልባት የኛ የተሻለ እውነታ ሊኖረው ይችላልና እስከጊዜው እንዲሁ እየተወቃቀስን እንቀጥል ፡፡

   6. “4ኛውን እርባና ቢስ መከራከሪያ ነጥብ ምላሽ መስጠት አስፈላጊ መስሎ አልታየኝም።”
   - ጉድህ እንግዲህ ይሄ ነው ፡፡ በወንጌል ቃል ሲመጡብህ የቃላት ጨዋታ ይሆንብሃል ፡፡ ወንጌል እንዲህ አይልም ብለህ ለምን አትክድና አይለይልህም ፡፡ ማናቸው? እኛ መምህር ግርማ ቢያገኙህ እንዲህ እውነታውን እየጋረደ የሚያሳስትህን መንፈስ ይገስጹልህ ነበር ፡፡

   7. ድንግል ማርያም አዳኝ አይደለችም የሚል ቃል ስላላገኘህልኝ ጥያቄዬን አሁንም እንዳይጠፋብህ በኰሮጆ አድርገህ ተቀመጥ ፡፡

   8. ስለ ነገረ ድኀነት ጠለቅ ያለ ግንዛቤ እንዲኖርህ ባለፈው አጭር አንኳር መልስ ስለሰጠሁበት ዛሬ ዳግም አልመለስበትም ፡፡
   እውነቱን እንድናውቅ እግዚአብሔር ይርዳን

   Delete
  9. ይህም የውይይት አስተያየት በመጽሐፍ ታትሞ፣ የቅዱሳን መጻሕፍት ክፍል ነው መባሉ የማይቀር መሆኑ እርግጥ ነው። (ይብላኝ ለወደፊቱ ትውልድ) ይቅርታ ግን በስሜት ፈረስ እየጋለቡ "ቃል ህይወት ያሰማልን" ማለት የመጽሐፍ ቅዱሱ ክርስትና ባህርይ አይመስለኝም።

   እንደ ቤርያ ሰዎች የሚነገርረውን፣ በየድርሳናቱ የሚጻፈውን "ነገሩ እውነት ይሆንን?" ብሎ ኢየሱስና የርሱ ሐዋርያት የእግዚአብሐር ቃል አድርገው የተቀበሏቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት ከመመርመር ይልቅ የተጻፈውን ሁሉ፣ አባ እንትና ያሉትን ሁሉ በጸጋ መቀበል ተገቢ አይመስለኝም። (የሐዋ. ሥራ 17፡10፣ 11)

   የሚያምኑበትን ማብራራት እንኳ የማይችሉ፣ አንድ ጥያቄ በተነሳ ቁጥር መረጃው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሲጠፋ "አይ.. በአዋልድ መጻሕፍት ውስጥ እንዲህ ተብሏል" እያሉ የአስተማሪዎቻቸው የገደል ማሚቱዎች የሆኑ ምዕመናንን ለህይወት ሳይሆን ለ"ቃለ ህይወት ያሰማልን" ማከማቸት እጅግ ከንቱ፣ የከንቱም ከንቱ ነው።

   Delete
  10. የገንዘብ ጥማተኞች ፍላጎታቸውን ለማርካት የማይሠሩት ፣ የማይፈጥሩት ብልሃት የለም ፡፡ ይኸንንም የመሰለ ሃሳብ ከየቦታው ለቃቅመው መጽሐፍ ብለው እንደሚያወጡት እኔም አልጠራጠርም ፡፡

   ቢሆንም ግን የተገለጸው ሃሳብ የሚያስማማን ሃቅና ቁም ነገር እስካለው ድረስ በመጽሐፍ ቢታተምና ለማያውቅ እንዲያውቅ ቢደረግ በግሌ አልቃወምም ፡፡ ፈረንጅ የሚጽፈው ብቻ ሁል ጊዜ ልክ ነው ብሎ ለሚተኛው ሰነፍ ሁሉ ፣ ጭንቅላቱን ትንሽ ተጠቀመበት ማለት ነው ፡፡ በተረፈ ግን ማንም ቀለም ለቅላቂ ስለጻፈ፣ የሃይማኖት መጽሃፍ ተብሎ ወደ ቤተ ክርስቲያናችን አይገባም ፡፡ አባቶቻችን ዋና ሥራቸው የሃሰት ትምህርቶችን ፣ ልብ ወለድና ሠፈር በቀል የሆኑትን አዳዲስ ኑፋቄዎች በሩቁ ማምከን በመሆኑ ፣ ቅጥር ግቢ እንኳን የመድረስ ዕድል የለውም ፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በትርጉም የማይስማማውን በሙሉ ያርቁታል ፤ ያስወግዱታል ፡፡ ማኀበረ ቅዱሳንም በዘመናችን የተገኘ የማይክዱት የቤተ ክርስቲያን ዋና ዘበኛ ነው ፡፡ ቢያንስ እንደነዚህ ዓይነቶቹን ቅጥረኞችና ጥቅመኞች ያጋልጣቸዋል ፡፡

   በአሁኑ ወቅት ግን ትንሽ ማንበብና መረዳት የቻለ ሁሉ እየቀላቀለ በመጻፍ ፣ ለማመሳሰል የሚሞክረው በዝቷልና የሥራ ጫና ይኖርባቸዋል ፡፡ ለማንኛውም ግን አሁንም ቤተ ክርስቲያናችንን ከዲቃላ ትምህርት ይጠብቋታል ፡፡ አንሰጋም ፡፡

   Delete
 7. enante lemin tachberebiralachu and aquam yinurachu ortodoxin lekek adriguat enante mechem ortodox athonum memeret mebarek yasfeligal. awo dingil mariam yegna medagnachin nat!!!!!!!!

  ReplyDelete
 8. TEBAREK!! ANONYMOUS OCT 15,2012 7:23. GREAT ARTICLE IF THEY UNDERSTAND IT HAS A ROAD FOR ETERNAL LIFE

  ReplyDelete
 9. ሰርጸ ድንግልOctober 16, 2012 at 1:50 AM

  ጥያቄ
  ጌታ የህያዋን አምላክ እንጂ የሙታን እንዳልሆነ እራሱ ባለቤቱ ኢየሱስ የተናገረዉን ትምህርት አዉቃለሁ፡፡
  ሆኖም "ዛሬ በህይወተ ስጋ የሌለችዉ ድንግል ማሪያም እንዴት ታማልዳለች" ብለሃልና ከዚሁ መጽሃፈ አምላካዊ(ሃዲስ ኪዳን) ሳትወጣ ድንግል ማሪያም ማረፏን (መሞቷን) የሚያፈጋግጥ ጥቅስ ንገረኝ? ከምን ተነስተህ በህይወተ ስጋ የለችም አልክ?፡፡

  ReplyDelete
 10. አዬ ሞኞ ትልቁ ስሕተትህ መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው ስለማን ለመመስከር እንደሆነ አለማወቅህ ነው። ጌታ በወንጌል እንደተናገረው መጻሕፍት የሚመሰክሩት ስለጌታ ነው (ዮሐ. 5፡39)። እግረ መንገዳቸውን ግን ስለሌሎች ሊናገሩ ይችላሉ፤ ዋና አላማቸውም የጌታን ክብር መግለጥ ነው። ስለዚህ ማርያም ማረፏን የሚያረጋግጥ ጥቅስ አምጣ ማለትህ "ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ" ነው የሚሆነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ማእከል እርሷ ባለመሆኗ መጽሐፍ ቅዱስ ስለእርሷ ማረፍ አልተረከልንም። እንዲተርክልንም ልንጠብቅ አይገባንም። ሰው ስለሆነች ግን የሞትን ጽዋ መቅመሷ የማይቀር እውነት ነው። አንተ እያልክ ያለኸው አልሞተችም፤ በሕይወተ ሥጋ አለች ነው? እንዲህ የሚል ቃልም ካለ ከአንተ ከሊቁ መስማት እፈልጋለሁ። ጌታ የሕያዋን አምላክ የተባለው እኮ ቅዱሳን ቢያንቀላፉም ነፍሳቸው በጌታ ዘንድ አለች፤ ሕያዋን ናቸው ማለት ነው እንጂ የሞትን ጽዋ አይቀምሱም ማለት አይደለም። በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ተብሎ በጌታ የተነገረላቸው አብርሃም ይሥሐቅ ያዕቆብ ናቸው፤ እነርሱ እንዳንቀላፉና በሕይወተ ሥጋ እንደሌሉ እናውቃለን። ቢያንቀላፉም ቅሉ ነፍሳቸው በጌታ ዘንድ እንዳለች ይታወቃልና ሕያዋን እንጂ ሙታን አይባሉም። በዚሁ መሠረት የጌታ እናት ድንግል ማርያም ከዚህ ዓለም በሞት የተለየች ብትሆንም ነፍሷ ከቅዱሳን ነፍሳት ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ስለምትገኝ ሕያው ናት። ከዚህ ውጪ ሕያው ናት የምንልበት መንገድ ካለ መነጋገር ይቻላል። ስለዚህ እባክህ ወንድሜ ነገሮችን በተሰጠህ አእምሮ በማስተዋል ለመመርመር ሞክር እንጂ የተሰጠህን ሁሉ ዝም ብለህ አትጋት።

  ReplyDelete
 11. ሰርፀ ድንግልOctober 23, 2012 at 12:36 AM

  የተጠየከዉን ብቻ መልስልኝ ዝም ብሎ በይሆናል የሚነገር ሃይማኖት የለም፡፡ እኔ ድንግል ማርያም አላረፈችም አላልኩም ማረፏን ግን ማረጋገጫም ስላለኝ ነዉ አንተ ግን ስለማረፏም የምትናገረዉ በግምት ነዉ፡፡ ሌላዉ ደግሞ ሰለማሪያም ሞት መጽሃፍ ቅዱስ እንዲነግረን አንጠብቅም ላልከዉ ስለምን ይሆን የሌሎች እዱሳን እረፍት የተነገረዉ እን ይስሃቅ እነ ዮሴፍ እና ሌሎችም እረፍታቸዉ የተነገረዉ የመጽሃፍ ቅዱስ ማእከል ሁነዉ ነዉ እንዴ፡፡ እራስህ አንድ ነገር አስተዉል በብሉይ ከነበሩት ቅሱሳን ይልቅ በሃዲስ የነበሩት ሃዋርያት አይኖቻቸዉ ጌታን ስላዩ ብጹአን ተብለዋል ከስጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ የነሳላት ቅድስተ ቅዱሳን፤ ጌታ ለመድሃን መክንያት ያደረጋት እመ አምላክ እንዴት ትከብር፡፡
  ዞሮ ዞሮ ሰዉ ስለሆነች ትሞታለች ላልከዉ ሰዉ ሁነዉ እስካሁን ሞትን ያልቀመሱ እንዳሉ መጽሃፉ ሊነግርህ ይችላል፡፡ ይሆናል ብሎ ግምት ግን ለ እምነት አይሰራም ስለዚህ አሁንም ቢሆን ግምትህን ትተህ ሞተች የሚል መረጃ እቅርብ፡፡
  እኛ ኦርቶዶክሳዉያንማ እረፍቷን ከነቀኑ ልንነግርህ እንችላለን፡፡ ምን እርሱን ብቻ እርገቷንም ልንመሰክርልህ እንችላለን፡፡ በዉስጥህ ያለዉ መንፈስ አሸናፊዉ ክርስቶስን በእርሷ ስጋ ተከልሎ ድል እንደነሳዉ ስለሚያዉቅ እንዲሁም ደግሞ ሄዋን በዉዳሴ ከንቱ አሸንፎ ከገነት ማባረር ቢችልም በዳግማዊት ሄዋን በኩል ክርስቶስ ዳግመኛ ገነትን ለአዳም እንደከፈተለት ስለሚያዉቅ ስሟ ሲጠራ መድረሻ ያጣል ይህንን እናዉቃለን ስለሆነም መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ እናቱ ትሆን ዘንድ በመረጣት በድንግል ማሪያም በኩል አልፎ ለድህነት የሚሆን ስጋዉንና ደሙንም እንደሰጠን እንመሰክራለን፡፡ ኖህን በመርከብ እንዳዳነዉ ሁሉ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሠርጸ ምን ያለኸው ልብ አውልቅ ነህ ጃል? በማርያም መሞት ከተስማማን ማስረጃው ሊያጣል አይገባም ነበር። አንተ ማስረጃ አለኝ የምትለውና ቀኑን ጭምር እነግርሃለሁ የምትለው መቼም መጽሐፍ ቅዱስን ምንጭ አድርገህ እንዳልሆነ ተስፋ አደርጋለሁ። ተአምረ ማርያም ግን ጥር 21 የማርያም እንዳረፈች ይናገራል። ከዚህ ውጪ እስኪ ማርያም መሞቷን የሚናገር ክፍል ከመጽሐፍ ቅዱስ አውጣና አሳየን? መጽሐፍ ቅዱስ የማርያምን ሞት እንዲነግረን መጠበቅ የለብንም፤ ደግሜ እላለሁ መጠበቅ የለብንም። አንተ እንዳልከው መጽሐፍ ቅዱስ የሌሎቹን ሁሉ ሞት አይናገርም። መናገር ያለበትን ጽፎልናል። የጻፈውም የመጽሐፍ ቅዱስ ማእከላዊ ሐሳብ ስለሆኑ አይደለም። መጻፍ ስለነበረበት ግን ተጽፏል። መጻፍ የሌለበት ደግሞ አልተጻፈም። በዚሁ መሰረት የድንግል ማርያም ሞት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተመዘገበም። የእርሷ ብቻ ሳይሆን ሞታቸው ያልተጻፈ ቅዱሳን ብዙ ናቸው። አንተ የይስሃቅንና የዮሴፍን ጠቅሰሃል። እስኪ ልጠይቅህና ስለማቴዎስ ሞት፣ ስለጴጥሮስ ሞት የተጻፈበትን ቦታ ንገረን? የሁሉም ሞት ለምን እንዳይጻፍ እንዳደረገ የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው።
   ሞትን ያልቀመሱ አሉ። ነገር ግን እነርሱም በመጨረሻ መሞታቸው አይቀርም። የእነርሱ እስካሁን ሞትን አለመቅመስ ግን በምንም መንገድ ለድንግል ማርያም አለመሞት ዋስትና ሊሆን አይችልም። በመጨረሻም አንድ እንድመልስልህ የጠየቅከኝን ጥያቄ በዚህ መልክ እመልስልሃለሁ፥ አንተ አልሞተችም የሚል ጥቅስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ስታቀርብ እኔም ሞተች የሚል ጥቅስ አመጣለሁ።

   Delete
 12. ሰርፀ ድንግልOctober 26, 2012 at 11:07 PM

  ልብ አዉልቅ የሆንከዉ አንተ ነህ፡፡ ሲጀመር አላረፈችም አላልኩም፡፡ ልንገርህና እናንተ ከሃዲስና ከብሉይ ሌላ አንቀበልም የምትሉ ናችሁ እኔ ደግሞ የምልህ ከሁለቱ ዉጭ የማትቀበሉ ከሆነ የማርያምን ማረፍ ማን ነገረህ ነዉ እንጅ ያልኩት አላረፈችም አላልኩም፡፡ አዋልድ መጽሃፍትንና ትዉፊትን የማትቀበሉ እስከሆነ ደረስ ታምረ መሪያምን ለምን ጠቀስከዉ? ስለሞቷ ስለነገረህ ነዉ፡፡ ሞትን ያልቀመሱት መጨረሻ ይቀምሱት ዘንድ ቢገባቸዉም አሁን ግን ህያዉ ናቸዉ፡፡ ዙሮ ዙሮ የኔ ጥያቄ ለራሳችሁ አላማ ሲሆን ከቅዱስ መጽሃፍ ዉጭ ናቸዉ ከምትሉት አዋልድ እንዲሁም ከምትቃወሙት ቅዳሴ ጭምር መጥቀስ አቁሙና ብሉይና ሃዲስ ኪዳንን ብቻ ተጠቀሙ (እንደ ፕሮቴስታንት) ካልሆነ ግን እየወላወላችሁ አታስቸግሩ፡፡ አንዴ መጽሃፈ አማለካዉያን አንዴ ደግሞ ከአዋልድ አትበሉ ነዉ፡፡ አሁንም ቢሆን የማትቀበለዉን ታምረ ማሪያም ማምለጫ መስሎህ ጠቀስከዉ እንጂ አምነህበት አይደለም፡፡የጳዉሎስንና የጴጥሮስን መሰዋት ታምናለህ? ካመንክስ ማን ነገረህ? እልሃለሁ፡፡ በተረፈ ያልተባል እየጠቀስክ ልብ አታዉልቅ፡፡

  ReplyDelete
 13. MARY - MOTHER OF CHRIST, MOTHER OF THE CHURCH

  963 Since the Virgin Mary's role in the mystery of Christ and the Spirit has been treated, it is fitting now to consider her place in the mystery of the Church. "The Virgin Mary . . . is acknowledged and honored as being truly the Mother of God and of the redeemer.... She is 'clearly the mother of the members of Christ' ... since she has by her charity joined in bringing about the birth of believers in the Church, who are members of its head."500 "Mary, Mother of Christ, Mother of the Church."501

  I. MARY'S MOTHERHOOD WITH REGARD TO THE CHURCH

  Wholly united with her Son . . .

  964 Mary's role in the Church is inseparable from her union with Christ and flows directly from it. "This union of the mother with the Son in the work of salvation is made manifest from the time of Christ's virginal conception up to his death";502 it is made manifest above all at the hour of his Passion:

  Thus the Blessed Virgin advanced in her pilgrimage of faith, and faithfully persevered in her union with her Son unto the cross. There she stood, in keeping with the divine plan, enduring with her only begotten Son the intensity of his suffering, joining herself with his sacrifice in her mother's heart, and lovingly consenting to the immolation of this victim, born of her: to be given, by the same Christ Jesus dying on the cross, as a mother to his disciple, with these words: "Woman, behold your son."503

  965 After her Son's Ascension, Mary "aided the beginnings of the Church by her prayers."504 In her association with the apostles and several women, "we also see Mary by her prayers imploring the gift of the Spirit, who had already overshadowed her in the Annunciation."505

  . . . also in her Assumption

  966 "Finally the Immaculate Virgin, preserved free from all stain of original sin, when the course of her earthly life was finished, was taken up body and soul into heavenly glory, and exalted by the Lord as Queen over all things, so that she might be the more fully conformed to her Son, the Lord of lords and conqueror of sin and death."506 The Assumption of the Blessed Virgin is a singular participation in her Son's Resurrection and an anticipation of the resurrection of other Christians:

  In giving birth you kept your virginity; in your Dormition you did not leave the world, O Mother of God, but were joined to the source of Life. You conceived the living God and, by your prayers, will deliver our souls from death.507  969 "This motherhood of Mary in the order of grace continues uninterruptedly from the consent which she loyally gave at the Annunciation and which she sustained without wavering beneath the cross, until the eternal fulfilment of all the elect. Taken up to heaven she did not lay aside this saving office but by her manifold intercession continues to bring us the gifts of eternal salvation .... Therefore the Blessed Virgin is invoked in the Church under the titles of Advocate, Helper, Benefactress, and Mediatrix."510

  970 "Mary's function as mother of men in no way obscures or diminishes this unique mediation of Christ, but rather shows its power. But the Blessed Virgin's salutary influence on men . . . flows forth from the superabundance of the merits of Christ, rests on his mediation, depends entirely on it, and draws all its power from it."511 "No creature could ever be counted along with the Incarnate Word and Redeemer; but just as the priesthood of Christ is shared in various ways both by his ministers and the faithful, and as the one goodness of God is radiated in different ways among his creatures, so also the unique mediation of the Redeemer does not exclude but rather gives rise to a manifold cooperation which is but a sharing in this one source."512

  ReplyDelete
 14. . . . she is our Mother in the order of grace

  967 By her complete adherence to the Father's will, to his Son's redemptive work, and to every prompting of the Holy Spirit, the Virgin Mary is the Church's model of faith and charity. Thus she is a "preeminent and . . . wholly unique member of the Church"; indeed, she is the "exemplary realization" (typus)508 of the Church.

  968 Her role in relation to the Church and to all humanity goes still further. "In a wholly singular way she cooperated by her obedience, faith, hope, and burning charity in the Savior's work of restoring supernatural life to souls. For this reason she is a mother to us in the order of grace."509

  ReplyDelete
 15. "This motherhood of Mary in the order of grace continues uninterruptedly from the consent which she loyally gave at the Annunciation and which she sustained without wavering beneath the cross, until the eternal fulfilment of all the elect. Taken up to heaven she did not lay aside this saving office but by her manifold intercession continues to bring us the gifts of eternal salvation .... Therefore the Blessed Virgin is invoked in the Church under the titles of Advocate, Helper, Benefactress, and Mediatrix."510

  970 "Mary's function as mother of men in no way obscures or diminishes this unique mediation of Christ, but rather shows its power. But the Blessed Virgin's salutary influence on men . . . flows forth from the superabundance of the merits of Christ, rests on his mediation, depends entirely on it, and draws all its power from it."511 "No creature could ever be counted along with the Incarnate Word and Redeemer; but just as the priesthood of Christ is shared in various ways both by his ministers and the faithful, and as the one goodness of God is radiated in different ways among his creatures, so also the unique mediation of the Redeemer does not exclude but rather gives rise to a manifold cooperation which is but a sharing in this one source."512

  II. DEVOTION TO THE BLESSED VIRGIN

  971 "All generations will call me blessed": "The Church's devotion to the Blessed Virgin is intrinsic to Christian worship."513 The Church rightly honors "the Blessed Virgin with special devotion. From the most ancient times the Blessed Virgin has been honored with the title of 'Mother of God,' to whose protection the faithful fly in all their dangers and needs.... This very special devotion ... differs essentially from the adoration which is given to the incarnate Word and equally to the Father and the Holy Spirit, and greatly fosters this adoration."514 The liturgical feasts dedicated to the Mother of God and Marian prayer, such as the rosary, an "epitome of the whole Gospel," express this devotion to the Virgin Mary.515

  III. MARY - ESCHATOLOGICAL ICON OF THE CHURCH

  972 After speaking of the Church, her origin, mission, and destiny, we can find no better way to conclude than by looking to Mary. In her we contemplate what the Church already is in her mystery on her own "pilgrimage of faith," and what she will be in the homeland at the end of her journey. There, "in the glory of the Most Holy and Undivided Trinity," "in the communion of all the saints,"516 The Church is awaited by the one she venerates as Mother of her Lord and as her own mother.

  In the meantime the Mother of Jesus, in the glory which she possesses in body and soul in heaven, is the image and beginning of the Church as it is to be perfected in the world to come. Likewise she shines forth on earth until the day of the Lord shall come, a sign of certain hope and comfort to the pilgrim People of God.517

  IN BRIEF

  973 By pronouncing her "fiat" at the Annunciation and giving her consent to the Incarnation, Mary was al ready collaborating with the whole work her Son was to accomplish. She is mother wherever he is Savior and head of the Mystical Body.

  974 The Most Blessed Virgin Mary, when the course of her earthly life was completed, was taken up body and soul into the glory of heaven, where she already shares in the glory of her Son's Resurrection, anticipating the resurrection of all members of his Body.

  975 "We believe that the Holy Mother of God, the new Eve, Mother of the Church, continues in heaven to exercise her maternal role on behalf of the members of Christ"

  ReplyDelete
 16. tewoled hulu biset yilugnal..kesetoch hulu telyetshe yetebarksh hoy keljesh meheret lemgnelen..amen .kezih beterfe kaldengel amalagenet alem ayedenm yetesasate kebad sihetet new ...yaltesafe atanbebu...eyesusen atetlu..meheret yemilemenew kersu eko new yalersu menem men yemihon neger yelem lib yistenl.amen

  ReplyDelete
 17. My brothers and Sisters

  I try to read all the above texts, and really feel sorry, every body except some who have biblical knowledge try to express well, otherwise most comments are from the unknown source may be from the devil.
  on John 14:6 Jesus Himself said;" I am the way, the truth, and the life: no man come to the Father, but by me". What does it mean? why don't you read the bible instead of putting under the pill? I give special comment for those who said and write "ያለ ወላዲተ አምላክ አማላጅነት ዓለም አይድንም!" Be careful you are worshiping the devil please find the righteous father whose name is Jesus. If you read the bible it says "Marry herself got the life through Jesus". She is died at the age of 64 as our witchcraft doctor write her history. Don't live in shameful and blind world please come to Jesus the right Savior who give his life on the cross for you and for me.

  ReplyDelete
 18. This article helps me know who You are? U R Kehadiwoch.
  Metsihaf Kidus lay tadiya Kidist Dingil Mariyamin 'Atamalidim' Yemil Ale? Yelem. lemanignawim Lib Yisitachihu.

  ReplyDelete