Monday, October 15, 2012

ለፕትርክናው በማኅበረ ቅዱሳን ከታጩት አንዱ አቡነ ሉቃስ ማናቸው?

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ካረፉ በኋላ ቤተክህነቱ የሐዘን ድባብ እንዳጠላበት ነው። ስድስተኛውን ፓትርያርክ ለመሰየም ትልቅ የቤት ስራ ከፊቱ የተደቀነበት ጠቅላይ ቤተክህነት ማንን መሰየም እንዳለበት ለመወሰን የተቸገረ ይመስላል። እኔ ልሁን እኔ ልሁን የሚል ባይጠፋም፣ አለሁ አለሁ ከሚሉት መካከል፣ ለፕትርክናው የሚመጥን ሰው አለመገኘቱ ግን ብዙዎችን አሳስቧል። ቤተክርስቲያኗን በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መሠረት የሚመራ፣ ቤተክርስቲያኗ በዓለም አቀፍ ደረጃ አግኝታ የነበረውን ክብርና ስፍራ ጠብቃ እንድትቀጥል የሚያደርግ፣ የውስጥ ችግሮቿን ለመፍታት ቁርጠኛ የሆነና ዝግጁነት ያለው አባት ማግኘት ቀላል አይደለም።
 
ቤተክህነቱ በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ፣ ማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ ለውስጥ እያደረገ ባለው እንቅስቃሴ አቡነ ገብርኤልን፣ አቡነ ማትያስንና አቡነ ሉቃስን ለፕትርክና እንዲወዳደሩ አጭቷቸዋል እየተባለ እየተነገረ ነው። ከእነዚህ መካከል የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ዕረፍት ተከትሎ «እኔ እንግሊዝኛ ስለምችል ፓትርያርክ መሆን ያለብኝ እኔ ነኝ» ሲሉ የተደመጡትን አቡነ ሉቃስን ማጨቱ ማኅበሩ የሚመርጣቸው ሰዎች ማንነት የማኅበሩን ዝቅጠት የሚያመለክት ነው እየተባለ ነው። የቀድሞውን መሪጌታ ኃይለስላሴ የአሁኑን አቡነ ሉቃስ ከመቀሌ 100 ኪሎ ሜትር ገደማ ላይ ከምትገኘው አጉላይ ከተባለችው ስፍራ ጀምሮ በሚያውቋቸው ዘንድም ለጵጵስና ሲመረጡ ከገረማቸው በላይ አሁን በማኅበሩ በኩል ለፓትርያርክነት እጩ ሆነው እንዲቀርቡ መታሰባቸው ከፍተኛ ግርምትን እንደፈጠረባቸው እየተናገሩ ነው። እነዚህ ወገኖች መጰጰሳቸው ሲገርማቸው እንዳልኖረ አሁን ደግሞ በራሳቸው የእኔን ምረጡኝ ቅስቀሳና ለማኅበሩ በዋሉት አንዳንድን ውለታ፣ በተለይም ከሰሞኑ እንኳ «በውስጣችን ያሉና ያለተወገዙ ተሐድሶዎችን ማውገዝ አለብን» በሚለው አቋማቸው የማኅበሩን ቀልብ ስለሳቡና ምናልባትም ሐዋሳ ላይ ብዙ የኖሩ በመሆናቸው ከሐዋሳ ገብርኤል በአቡነ ገብርኤል ተገፍቶ የወጣውንና በውጪ የሚገኘውን ሕዝብ ለማስወገዝ ብርቱ መሣሪያ ይሆናሉ ስለተባለ የማኅበሩ አንድ ዕጩ ሊሆኑ ችለዋል ይላሉ ታዛቢዎች።

የአቡነ ሉቃስን ማንነት በተወሰነ መልኩ ይፋ የምናወጣው የአባቶችን ስም ለማጥፋት ወይም በእርሳቸው ድካም ለመፍረድ እንዳልሆነ ግን ለመግለጽ እንወዳለን። ቤተክርስቲያኗ እመራበታለሁ በምትለው የምንኩስና ስርአት የማይመሩ የአንዳንድ አባቶች ሕይወት ቤተክርስቲያኗን እያስነቀፈ መሆኑንና በየፍርድ ቤቱም እየተከሰሱ የቤተክርስቲያን ስም እየጎደፈ በመሆኑ፣ ያንን ለማጥራት በቀጣይ በሚመረጠው አባት ላይ ከፍ ያለጥንቃቄ እንዲወሰድና የቤተክርስቲያኗን ስምና ዝና ሊያጎድፍ ሰው በመንበሩ ላይ ተቀምጦ ኋላ የከፋ ነገር እንዳይከሠት ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲደረግ ለማመላከት ነው። ከዚህ ቀደም የአቡነ ሚካኤልን ሚስትና ልጅ የተመለከተውን ዘገባ ባወጣን ጊዜ፣ አንዳንዶች ሐሰት ነው ሲሉ ነበር። አቡነ ሚካኤል ያልካዱትንና ተቀብለው ሲረዷቸው የነበሩትን ልጃቸውንና ባለቤታቸውን በመካድ ነገሩን ለመሸፋፈን የሞከሩትና ህጋዊ ወራሾቻቸውን ከጨዋታ ውጪ ለማድረግ ልዩ ልዩ ሴራ ሲሸርቡ የነበሩት አባ ሳሙኤል፣ ጉዳዩ ይበልጥ እንዲታወቅና ሰፊ የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኝ ነው ያደረጉት እንጂ እውነታውን ሊሸፍኑት አልቻሉም። ከአንድ ወር በፊት ይኸው ዜና በፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት ሬዲዮ ጣቢያ ላይ በሚተላለፍ «ኢትዮፒካሊንክ» በተባለ የመዝናኛ የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ በውስጥ አዋቂ ወሬዎች ላይ የአቡነ ሚካኤል ዜና ቀርቦ እንደነበርና፣ ነገሩ ጦዞ ለዲኤንኤ ምርመራ አስከሬናቸው ሊወጣ መሆኑ ተዘገቧል። ለምን ዜናው ይፋ ሆነ ተብሎም «ኢትዮፒካሊንክ» በነአባ ሳሙኤል ፊታውራሪነት ተከሰሰ። በዚህና በሌሎችም ወሬዎች ምክንያት ፕሮግራሙ ኦንዲቋረጥ መደረጉን ይህም ዜና በቅርቡ በወጣው ቁም ነገር መጽሔት ላይ ተዘግቧል። እውነትን ለመደበቅ በጣርን ቁጥር እውነት ራሷን መግለጧ አይቀርም።

አቡነ ሉቃስ ማናቸው? የዛሬው አቡነ ሉቃስ የቀድሞው መሪጌታ ኃይለሥላሴ ከመመንኮሳቸው በፊት አጉላይ በተባለው ስፍራ ሚስት አግብተው በትዳር ሲኖሩ እንደነበር ከታመኑ ምንጮች የተገኙ መረጃዎች ይጠቀማሉ። ከዚያም ወደ ሀዋሳ መጥተው በጥቁር ራስነት (ሳይመነኩሱ) ለዓመታት ቆይተዋል። በዚያም ሲኖሩ በስጋ አንድ ፍሬ ማፍራታቸውን ከወደ ሀዋሳ እየተነገረ ሲሆን፣ «ልጃቸው ነኝ አስተምረውኛል፤ ለዚህም ተጨባጭ ማስረጃ አለኝ» የሚል ልጃቸው ብቅ ብሏል። ለስራ ጉዳይ አዲስ አበባ ሲመላለሱ በነበረበት ጊዜም ያርፉ የነበረው 4 ኪሎ አካባቢ በነበረውና አሁን በመልሶ ማልማት መርሀግብር በፈረሰው ጸደይ ሆቴል ውስጥ እንደነበረና ያድሩ የነበረውም «ሌጣቸውን» እንዳልነበር ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ሁሉ ይመሰክራሉ።

እውን እንደ እነዚህ ያሉትና ያለባቸውን የስነምግባር ችግር «ተሀድሶዎችን ማውገዝ አለብን» በሚል ግብዝነት ለመሸፈን የሚያስቡ ሰዎች ቤተክርስቲያንን እንዲመሩ ቢደረግ ቤተክርስቲያኒቱ ወዴት ነው የምታመራው? ስለዚህ ሁሉም የየራሱን ፓትርያርክ ለማስቀመጥ ከሚሯሯጥ ይልቅ የአባቶች ማንነት በሚገባ ሊጠና ይገባል። ለስብከተ ወንጌል መስፋፋት የሚተጋ፣ ቤተክርስቲያኒቱ ባለችበት እንድትረግጥ ሳይሆን ወደተሻለ መንፈሳዊነት እንድትመጣ የሚሠራ፣ ለሁለንተናዊ ተሐድሶዋ የሚያስብ አባት በመንበሩ ላይ እንዲያስቀምጥ ለቤተክርስቲያን ቅን መሪን የሚሰጠውን ቅዱስ እግዚአብሔርን ልንለምነው ይገባል።  


 

23 comments:

 1. Gosh! Ena min yitebes?

  ReplyDelete
 2. thanks guys and great spiritual job.

  ReplyDelete
 3. This is a good evidence that shows how you are working for devil, to accomplish hidden agenda of
  1- protestant
  2- politics
  3- secularism
  4- evil aspect of globolization

  ReplyDelete
  Replies
  1. May God bless you

   Delete
  2. Thank you- this is what these guys try to achieve... You can see the tone on thier writing it is totally unspritual... they look a hateful people. May God mercy them! I am really upset when I see how people think like a devel.

   Delete
 4. I urge all eotc nech lebash hulu which mest, bale and lege of elements of mk which key enemy of Jesus and Eotc it time to demolish them then go to heaven.

  ReplyDelete
  Replies
  1. yehe kerestianawi menged aydelem setanawi engi

   Delete
 5. የመዳን ቀን ዛሬ ነው፤ ዛሬ ሳይሆን አሁን፡፡ ንስሃ ግቡ፤...

  ReplyDelete
 6. astesasebachihu be mi'erabawian tebekilo yeEtthiopiawianin maninet aremeredatachihu yanenim yanenim tizebarikalachihu.
  maferiawoch! leteketayochachihu azenikulachiew.

  ReplyDelete
 7. great abaselama,keep up good job.

  ReplyDelete
 8. የራሳችሁን ጉድፍ ከአይናችሁ ማን ያውጣላችሁ?

  ReplyDelete
 9. who are you criticizing our fathers? you are one of those dirty protestant missionaries who dusguise your self in the name of 'orthodox'. your ideas are all those of heretic protestants and why don't you describe yourself as protestant? you are one of those dirty so called 'evangelicals' which preach devilish teachings which does not describe our God. get out of our church you stupid protestant!!! leave alone our church you son of diablos. you are simply flesh-enclosed satan!!!!!!

  ReplyDelete
 10. "ለሁለንተናዊ ተሐድሶዋ የሚያስብ አባት በመንበሩ ላይ እንዲያስቀምጥ ለቤተክርስቲያን ቅን መሪን የሚሰጠውን ቅዱስ እግዚአብሔርን ልንለምነው ይገባል።" Ayachihut aydel Gudachihun Erasachihun Geletachihu

  ReplyDelete
 11. "ለሁለንተናዊ ተሐድሶዋ የሚያስብ አባት በመንበሩ ላይ እንዲያስቀምጥ ለቤተክርስቲያን ቅን መሪን የሚሰጠውን ቅዱስ እግዚአብሔርን ልንለምነው ይገባል። " Atirebum Menafikan Endehonachihu Bsirachihu Titawekalachihu!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 12. ፅሁፋችን ማንነታችሁን በደንብ ይገልጣልና ተቆርቃሪ ለመምሰል አትሞክሩ!

  ReplyDelete
 13. The sole problem of this church is mahbere kidusan in one end who is fully political mahiber and you who is menafikan. mahbre kidusan is like esist changing they color now and then and doesn't take a minute to think of the wise ethiopians who have the capacity to judge and identify them. Aba selama is purely running after the teachnings of luther who is against the ancient teachings of christianty. I think this much information is enough for you to show you up we are there!

  ReplyDelete
 14. WEREGNOCH ATHUNU!!!

  ReplyDelete
 15. so what you want from EOTC we know you,that you are not from us devil can become as light angel so you are his messenger don't use our name as umbrella.

  ReplyDelete
 16. so what do you want from orthodox church .you are not our brothers in religions stop using our church as umbrella we are enough for our self

  ReplyDelete
 17. I was accept you as religions grumps who are free from politics but know when you write about abun Lukase you have wrote the falls statement we need only to hear from you the word of goad live it for MAhiberkidusan

  ReplyDelete
 18. 1. "...እኔ ልሁን እኔ ልሁን የሚል ባይጠፋም፣ አለሁ አለሁ ከሚሉት መካከል፣ ለፕትርክናው የሚመጥን ሰው አለመገኘቱ ግን ብዙዎችን አሳስቧል...". Who is to judge that? You! It seems like you have someone in mind...may be some Pastor!

  2. "...የአቡነ ሉቃስን ማንነት በተወሰነ መልኩ ይፋ የምናወጣው የአባቶችን ስም ለማጥፋት ወይም በእርሳቸው ድካም ለመፍረድ እንዳልሆነ ግን ለመግለጽ እንወዳለን።...".So, what do you call this except 'Ye sim matfat'. Have some moral if you call yourself a Christian!

  3. "...ቤተክርስቲያኗ እመራበታለሁ በምትለው የምንኩስና ስርአት የማይመሩ የአንዳንድ አባቶች ሕይወት ቤተክርስቲያኗን እያስነቀፈ መሆኑንና በየፍርድ ቤቱም እየተከሰሱ የቤተክርስቲያን ስም እየጎደፈ በመሆኑ፣ ያንን ለማጥራት በቀጣይ በሚመረጠው አባት ላይ ከፍ ያለጥንቃቄ እንዲወሰድና የቤተክርስቲያኗን ስምና ዝና ሊያጎድፍ ሰው በመንበሩ ላይ ተቀምጦ ኋላ የከፋ ነገር እንዳይከሠት ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲደረግ ለማመላከት ነው።..." This proves you are not an Orthodox! So, why are you so concerned unless the devil in you is so troubled by the positive happenings in our church in recent days? 'lemasmesel enkuan' at least say ቤተ ክርስቲያናችን !

  4. "...እውን እንደ እነዚህ ያሉትና ያለባቸውን የስነምግባር ችግር «ተሀድሶዎችን ማውገዝ አለብን» በሚል ግብዝነት ለመሸፈን የሚያስቡ ሰዎች ቤተክርስቲያንን እንዲመሩ ቢደረግ ቤተክርስቲያኒቱ ወዴት ነው የምታመራው? ..." You think there are no Tehadisos! You are one of them...loser! It's true you should be condemned unless you repent.

  5. If possible don't post such 'ento fento'. But if the devil in you insists you have to write, please tell him to mention credible sources for all writings or they are all 'ALUBALTS' to confuse innocent faithfuls.

  ReplyDelete
 19. if you organized to free the church from habit to low why you condemn its bad administration many traditional /spiritual / scholars now cringe at the door of addis ababa diocese by NIBURED ELIAS woh is not wiling to hire educated once with out receiving money so why you sleep please help us!!

  ReplyDelete
 20. Aye Abaslamaweyan endwe balm laY yalew dabilos kenanet gare hono alelaqeqe alachehu yehe hulu seme matefate enaneta ymateflegeachew Abatoche endayemertu new Betkeresetiyanene lemebetebet Egezeabeher yasebachu meneme alachehu meneme amelak yrasu yhonewen bbotawe yaseqemetal menalebat kehteyatachen bezat endalfew gize egna lemeqetat kalefeleg bmulu lebe enagralhu yerasune agnegaye yemertal weyeme yaseqmetal beEgziabeher betamenu yesegafeqade bayenorebachehu eresu yewededewen yadergebelachu btselot tetgu neber gene alhoneme menefesawi sayehone segawiw heyewetacheu ashenefachu Egeziabeher yasebachehu

  ReplyDelete