Sunday, October 21, 2012

በደብረ ማርቆስ በዘንድሮው የደመራ በዓል ላይ የተሰበከው ወንጌል

Read in PDF
በየዓመቱ መስከረም 16 በኢትዮጵያ ብቻ በድምቀት የሚከበረው የደመራ በዓል ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፅ (እንጨት) የሚሰበክበት እንጂ በእርሱ ላይ የተሰቀለው መድኃኒት ክርስቶስ የሚሰበክበት እንዳልሆነ ይታወቃል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን ያለው ዘላለማዊ እውነት ተሰርዞና ተደልዞ «እኛ ግን ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል እንሰብካለን» በሚለው የስህተት ትምህርት ከተተካም ዘመናት ተቆጥረዋል። ቤተ ክርስቲያናችን የተሰቀለውን ክርስቶስን ትታ የተሰቀለበትን መስቀል እንድትሰብክ ያደረገውና ከእውተኛው መንገድ አስቶ ያወጣት፣ ሰው በላው አጼ ዘርአ ያዕቆብ እንደሆነ ታሪክ ይመሰክራል። ታሪኩን የክርስቶስ ነገረ መስቀል የገባቸው ክርስቲያኖች በሀዘን ሲመለከቱት ነገረ መስቀሉን በዕፀ መስቀሉ የተኩ የነገረ መስቀሉ ጠላቶች ደግሞ ይኮሩበታል። አለመታደል!!

እንደ ጥምቀቱ በዓል ሁሉ «እናንት የጸጥታ አስከባሪዎች በሕግ አምላክ ዘፈኑን አስቁሙልን፤ ይህ የሃይማኖታችንን ስርአት የምንፈጽምበት እንጂ የዘፈን ቦታ አይደለም» በሚል አባታዊ ማሳሰቢያ ቃለ ወንጌል ማሰማት የጀመሩት የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ፣ ሁሉ ጸጥ ብሎ እንዲሰማ ካደረጉ በኋላ ቀደም ብሎ የሰንበት ተማሪዎች ስለዕፀ መስቀሉ ታሪክ ያሳዩትን ትርኢት በመጥቀስ «የዕፀ መስቀሉ ታሪኩ በወጣቶቹ እንዳያችሁት ነው፤ እውነተኛውና ልናውቀው የሚገባ የነገረ መስቀሉ ታሪክ ግን እርሱ አይደለም። በመስቀል ላይ የተፈጸመው የክርስቶስ መከራና ስቃይ ነው። እንድንሸከመው የታዘዝነውም ይህንን መስቀል ነው። እኛ ግን መሸከም አልቻልንም።» በማለት ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ እስካሁን በሚገባ ያላስተዋሉትንና ያላወቁትን እውነተኛና መዳኛ የሆነውን መከራ መስቀል እንዲያውቁ ሰፊ ትምህርት ሰጥተዋል።

ብፁዕነታቸው እውነትን መስክረዋል። ለኦርቶዶክሳውያን ሲሰበክላቸው የኖረው ለእነርሱ ኃይል፣ ጽንእ፣ ቤዛና መድኃኒተ ነፍስ የሆነው የክርስቶስ መከራ ሳይሆን ዕፀ መስቀሉ ነው። ይህም ጣፋጩን ምግብ መመገብና እርሱኑ ማድነቅ ትቶ፣ ምግብ ላይሆን ምግቡ የቀረበበትን ሳህን እንደማድነቅ ነው የሚቆጠረው። የክርስቶስ የመስቀል ላይ ፍቅር የተሰበከለት ሰው ሕይወቱ እንደሚለወጥና ራሱን ለሞተለት ጌታ አስረክቦ በእረፍትና በሰላም እንደሚኖር የታወቀ ነው። የተሰቀለው ክርስቶስ ሳይሆን ዕፀ መስቀሉ ሲሰበክለት የኖረው ኦርቶዶክሳዊው ሕዝብ ግን ለዚህ አልታደለም፤ ያለ ልብ ሰላምና ዕረፍት እንዲሁ አለ። የልብ ሰላምና ዕረፍት የሚገኘው በተሰቀለው ክርስቶስ እንጂ እርሱ በተሰቀለበት መስቀል አይደለምና።

እስከ መቼ ነው ሕዝቡን ከሞተለት ጌታ ከመድኃኒቱ ጋር የማናገናኘው? ለምን የተሰቀለውን ትተን የተሰቀለበትን እንሰብካለን? የክርስቶስ ደም የፈሰሰው እኮ እኛን ኃጢአተኞችን ለመቀደስ ነው እንጂ እነአጼ ዘርአ ያእቆብ እንዳሳቱን ዕንጨት ለመቀደስ አይደለም። እንዲህ ማሰብማ ክቡር የሆነውን የክርስቶስን ደም ማቃለል ነው የሚሆነው። ዕፀ መስቀሉ የተሰቀለውን የሚያሳስብ አርማ ከመሆን ያለፈ ተግባር እኮ የለውም። ስለዚህ ጌታ ለድኅነተ ዓለም የተሰቀለበትን መስቀል ሳይሆን መስቀሉ ላይ የተሰቀለውን ጌታ እንስበክ።

ለቤተ ክርስቲያናችን እንደ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ያሉ አባታዊ አደራቸውን ተገንዝበው ሰውን ሳይፈሩና በወንጌሉ ሳያፍሩ ስለክርስቶስ መድኃኒትነት በሥልጣን የሚናገሩና የሚሰሙ፣ ልማድንና የወንጌልን እውነት ለይተው በማስተማር ሕዝቡን ከልማዳዊ ሃይማኖተኛነት ወደትክክለኛ መንፈሳዊነት የሚመሩ አባቶች ያስፈልጋሉ። 
 

29 comments:

 1. Ere twen atbeklun atamtatun sle nesiehete netsuhan dingle mariam blachehu.

  ReplyDelete
 2. good job his grace abune markos this is a good father we need. keep it up

  ReplyDelete
 3. Ante bemigeba yemesekele teregume yegebah alemeselegnem . Kechaleke ketsehufocheh befite selemetetsefew neger bemigeba tenekekeh ewek

  ReplyDelete
 4. Meskel hailine,meskel tsinine, meskel bezane,meskel medihanite nefisine. Meskel Hailachine new (Kidus Paulos)--Feniditachihu mutu. You can't win the truth with rediculos talks. Dedeboch

  ReplyDelete
 5. ABA MARKOS YIBERTU AYIMEREN YADINUT YANIGIZE YEGETA KAL YASHENIFALK

  ReplyDelete
 6. ABATACHIN ABUNE MARKOS YEWENGEL GEBERENA YMAHIBERE KIDUSAN TELATI NACHEW YIBERTU HAYMANOIT ABEW MINI ENDEHON KERISO BELAYI MANI YAWIKALK

  ReplyDelete
 7. ere ere wenigel ahun gena tesebeke!maferiya hula enaneten bilo getan awaki yeyihuda neger new tiz yemilegn shitow teshito ledihoch biset yalew .ledihoch asibo endyaydele yitawekal. enanitem lewengel asibachu endayidele endihu

  ReplyDelete
 8. It is not b/c u say, We know it already. It is 4 u gospel is new thing, whom ur fathers & fore fathers were worshipping idols.Not for Gojjamians. Jesus christ is believed & worshipped for about 2,000 years.

  ReplyDelete
 9. የተሰቀለው ክርስቶስOctober 22, 2012 at 2:37 PM

  የተሰቀለው ክርስቶስ ሳይሆን ዕፀ መስቀሉ ሲሰበክለት የኖረው ኦርቶዶክሳዊው ሕዝብ ግን ለዚህ አልታደለም፤ ያለ ልብ ሰላምና ዕረፍት እንዲሁ አለ። የልብ ሰላምና ዕረፍት የሚገኘው በተሰቀለው ክርስቶስ እንጂ እርሱ በተሰቀለበት መስቀል አይደለምና። "yes, our soul needs the word of God," when do we get it? In our church? yes, we have to get in orthodox church this is the time and the moment.

  From Texas

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቀደም ንግሥቶች እንኳን ስለሚያከብሩትና እንደሚከበሩበት ስለሚያውቁ የሚያጌጡት በመስቀሉ ሆኖ ነበር ፡፡

   ልብ ይበሉ ፣ በዘመነ ኦሪት (ዘመነ ፍዳ) ኮርማና ፍየል እያረዱ ደሙን በመርጨት ኃጢአታቸውን ያስተሰርዩ ፣ ራሳቸውንም ይቀድሱ እንደ ነበር በሙሴ መጽሐፍ ተጽፎልናል ፡፡ ደም የነካው ሁሉ የተቀደሰ እንደሚባልም ይኸው መጽሐፍ ይናገራልና ከሚከተሉት ኃይለ ቃሎች ረጋ ብለው ይመርምሩት ፡፡

   - "በመሠዊያውም ላይ ካለው ደም ከቅብዓት ዘይትም ወስደህ በአሮንና በልብሱ ላይ፥ ከእርሱም ጋር ባሉት በልጆቹና በልብሶቻቸው ላይ ትረጨዋለህ፤ እርሱም ልብሶቹም፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹ ልብሶቻቸውም ይቀደሳሉ።" ዘጸ 29፡21

   - “አሮንም በአመት አንድ ጊዜ በቀንዶቹ ላይ ማስተስረያ ያደርጋል፤ በአመት አንድ ጊዜ ለልጅ ልጃችሁ ማስተስረያ በሚሆን በኃጢአት መሥዋዕት ደም ማስተስረያ ያደርግበታል። ለእግዚአብሔር ቅድስተ ቅዱሳን ናት።” ዘጸ 3ዐ፡1ዐ

   - “ሁሉንም ትቀድሳቸዋለህ፥ ቅድስተ ቅዱሳንም ይሆናሉ፤ የሚነካቸውም ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።” ዘጸ 3ዐ፡29

   - “ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውንም መሠዊያ ዕቃውንም ሁሉ ትቀባዋለህ፥ መሠዊያውንም ትቀድሳለህ፤ መሠዊያውም ቅድስተ ቅዱሳን ይሆናል።” ዘጸ 4ዐ፡1ዐ

   በኮርማ ደም ይህን ያህል ቅድስናና ምሕረት ከተገኘ ፣ ኢየሱስ በክቡር ደሙ የቀደሰው መስቀሉማ ምን ያህል ከፍ ያለ ክብር ይኖረውና የመስቀሉን ነገር ለመካድ ይዳፈራሉ ፡፡ በዘመናችን በኢየሱስ መሥዋዕትነትና በክቡር ደሙ አገልግሎትን የፈጸመበት መስቀል ተቀድሶልናልና በእምነት ሆነን እንገልገልበት ፡፡ ድውዩን ይፈውሳል ፤ በአጋንንት የተለከፈውን ነጻ ያወጣል ፤ ዲያብሎስን ያንቀጠቅጥልናል ፡፡ ለማያምኑ ግን ግንድ ወይም ሜንጦ ሆኖ ይታያቸዋልና ልቦናቸውን ይመልስ እላለሁ ፡፡

   Delete
 10. አባ ሰላማዎች ዋሾዎች ስለኆናችሁ ምናችሁንም አላምንም ፡፡ ምክንያቴም ከዚህ ቀደም ከአንድም ሁለት ጊዜ ስትዋሹ በማስረጃ ተረጋግጦባችኋልና ነው ፡፡ ማስረጃዎቹም እኒሁላችሁ ፡-
  1. ነፍሳቸውን ይማርና !!! ሟች አቡነ ጳውሎስ ተማሪዎች ሲመረቁ አደረጉት ብላችሁ ያስነበባችሁን ጽሁፈ ምእመኑን የሚከፋፍል ፣ ቤተ ክርስቲያንንም ወደ ጦር ሜዳነት የሚቀይራት ነበር ፡፡ ነገር ግን ሌሎች ብሎጐች ንግግራቸውን ቃል በቃል ስላስነበቡን ቅጥፈት አንድ አልኩላችሁ
  2. አሁንም ነፍሳቸውን ይማርና !!! የሟች አቡነ ጳውሎስ የቀብር ሥነ ሥርዓት ሲፈጸም ፣ ቀብራቸው ደማቅ መሆኑ ባይካድም በናንተ ድረ ገጽ ግን የቀረበልን የህዝብ ፎቶ የአቡነ ሸኑዳ ቀብርን ነበር ፣ ያንንም በጉግል ስላረጋገጥን ቅጥፈት ሁለት አልኩላችሁ
  3. አሁን ደግሞ በመስቀል ልጆቻቸውን የሚባርኩትን ፣ ከእጃቸውም የማያጠፉትን አባት ይኸው ዕጸ መስቀልን ... አሉት እያላችሁ ከምእመን ጋር ለማጋጨት ትሞክራላችሁ ፡፡ ያላችሁትን ሁሉ ቢሉትም እንኳን በእናንተ ጭንቃላት የሚላወሰውን መጥፎና የተሳሳተ ግንዛቤ ይዘው አይሆንም ፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ዕጸ መስቀሉን እሰከ ዛሬም ኢየሱስ ነው ብላ አላስተማረችም አታስተምርምም፡፡ ነገር ግን ሰይጣን ድል የተመታበት አውድማ ስለሆነ ፣ ክቡር ደሙ የፈሰሰበትና መስዋዕት የቀረበበት የድኀነት አገልግሎት የተፈጸመበት አርማችን ስለሆነ እናከብረዋለን ፣ እንሳለመዋለን ፡፡ ለማያምኑት እንጨት ወይም ብረት ሊሆንባቸው ይችላል ፡፡ ለምናምን ግን የሰይጣን መቅጫ አለንጋ ፣ በመስቀሉ ራሳችንን አማትበን ዲያብሎስ ከፊታችን ፣ ከመንገዳችን ፣ ከአካባቢያችን የምናርቅበት ክቡር ክርስቲያናዊ መሣሪያችን ነው ፡፡

  ReplyDelete
 11. 700 ምእመናን ወደ እናት ቤተ ክርስቲያናቸው ተመለሱ አትም ኢሜይል

  ጥቅምት 12 ቀን 2005 ዓ.ም.

  በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ


  በቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ሐዲስ ለማ በየነ አማካኝነት፥ ለ31ኛው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አጠቃላይ መንፈሳዊ የሰበካ ጉባኤ የቀረበው ሪፖርት፤ ለ28 ዓመታት ያህል በሰዩ ወረዳ ሹሻ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያንና በአጥቢያው የሚገኙ ምእመናን ከእናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናቸው በመለየት የቆዩትን ሁለት ቀንደኛ የተሐድሶ መናፍቃን መሪዎች ተውግዘው መለየታቸውን አመለከተ፡፡  በተሐድሶ መናፍቃን ሴራ በየዋህነት የተወሰዱ ምእመናንን በንስሐ ለመቀበልና መናፍቃኑ “የሹሻ ቅዱስ ገብርኤል ምክር ቤት ” በሚል ስያሜ ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድነት የተነጠሉትን በብፁዕ አቡነ ሄኖክ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ትዕግሥት የተሞላበት በሳል አመራር የሹሻ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያንን ለማስመለስ ስድስት ወራት መውሰዱን ሥራ አስኪያጁ መጋቤ ሐዲስ ለማ በየነ አስረድተው፤ ምእመናኑ ባለማወቅና በመናፍቃኑ ስውር ሴራ ተታለው ከቤተ ክርስቲያን ተለይተው መቆየታቸው እንዳሳዘናቸውና በመጨረሻ ግን የተለዩአትን እናት ቤተ ክርስቲያንን ለመቀላለቀል መቻላቸው እንዳስደሰታቸው በመግለጽ፡- “የሰባክያነ ወንጌልና የአገልጋይ ካህናትን ችግር ለመቅረፍ በመላው ዓለም የሚገኙ የቅድሰት ቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጆች ከሀገረ ስብከቱ ጎን በመቆም የተቻላቸውን ድጋፍ እንዲያበረክቱልን በታላቅ ትሕትና እጠይቃለሁ” ብለዋል፡፡  በመናፍቃኑ ተታለው የቆዩት ምእመናን መጋቢት 19 ቀን 2004 ዓ.ም በሹሻ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን መጽሐፈ ቄደር በተደረሰበት ማየ ንስሐ ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድነት ተቀላቅለዋል፡፡

  ReplyDelete
 12. sahnun snay mgbu tiz yilenal yirbenal.Meskelun sinaym endihu krstos yirbenal.Legna yehonew yitasebenal.Mgbin snakebr kenemakrebiyaw new.WENSEGD WUST MEKAN HABEKOME EGREEGZIENE enkuan demu feso letesewabet!!!!!!!!
  COULD YOU SHOW US A WORD IN THE BIBLE THAT SAYS DON'T RESPECT CROSS???

  ReplyDelete
 13. MANDELA YETASEREBETN(ROBIN DESET)TEBKO MASGOBGNET YEMANDELAN KIBIR YIKENSEWALN???SLE MESKEL MESBEK MALETM KRSTOSN MASEB NEW.SLE BANDIRA SNAWERA SLE HAGER ENDEMNAWERAW HULU!!!!!!!IF YOU HATE Z.YAKOB WHY NOT YOU QUOTE ST.YARED WHO SUNG A LOT ABOUT THE ST.CROSS AND ITS HONOUR.little knowledge(kunstelenet)is dangerous!!!you don't know or you are intentionally taking only part of the whole to serve your hateful approach towards EOTC.

  ReplyDelete
 14. ሰርፀ ድንግልOctober 23, 2012 at 1:22 AM

  ጳዉሎስ እኮ እኛ ግን የተሰቀለዉን ክርስቶስን እንሰብካለን ያለዉ እኔ የጳዉሎስ ንኝ እኔ የአጵሎስ ነኝ እያሉ ላስቸገሩት ሰዎች እንጅ ክርስቶስ ስለተሰቀለበት መስቀል ላወሩ ሰዎች አይደለም፡፡ እንደዉ ዝም ብሎ ጥቅስ አገኘሁ ተብሎ አይለጠፍም፡፡ ባይገባህ ነዉ እንጅ ሃጢያታችንን ያስተሰርይ ዘንድ የበግና የኮርማ ባልሆነ ደም እጅ ወዳልሰራዉ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ ተብሎ በብርሃነ አለም ጳዉሎስ የተነገረለት እፀ መስቀሉ ነዉ፡፡ እፀ መስቀሉ ነዉ እጅ ያልሰራዉ ቅድስተ ቅዱሳን የተባለዉ፡፡ ለነገሩ ዲያቢሎስ የድህነታችን እራስ ከሆነዉ ከጌታችን ከመድሃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጀምሮ ለእኛ ድህነታችንን የሚያበስሩትን ለሰይጣን ደግሞ ሽንፈቱን የሚመሰክሩበትን በሙሉ ይቃወማል፡፡ ለዚህ ነዉ ድህነት የተጀመረባትን ድንግል ማሪያምን እና የተፈጸመበትን መስቀል ሲቃወም የሚኖረዉ፡፡ ለማንኛዉም እግዚአብሄር የሟቹን ሞት የማይወድ አምላከ ምህረት ነዉና ማስተዋሉን ይስጥህ፡

  ReplyDelete
 15. I like abune markos he is moderate in eotc fathers.

  ReplyDelete
 16. Please, put his sermon as an audio or as a transcription (at least in its paraphrased form). Let the people hear what the bishop said and let them decide themselves.

  Thank you,

  ReplyDelete
 17. Why leave z tewahedo.

  ReplyDelete
 18. Aba selama, my name is woltemariam. I married, but I got sex with kesis Girma, and now I decided to change my religion. Bc he got married too. I feel guilty. Why those,eotc priest did stupid? Here in Atlanta. I was,former Sunday school atendee.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወደ ተዋሕዶ እምነትሽ ለመመለስ ወስነሽ ከሆነ ፣ ስላለፈው ዘማዊነት ምግባርሽ ንስሃ መግለጽ የጀመርሽው ፣ ተመጣጣኝ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እንዲሰጥሽ ፣ ወደ ካህን (ነፍስ አባት)ሄደሽ ዳግም በግንባር ተናዘዢ ፡፡ አለበለዚያ ራስን ደብቆ በሜዲያ መግለጹ ኑዛዜ ሊሆን አይችልም ፡፡ በጸሎት እንድናስብሽ ከሆነ እግዚአብሔር በሠራ ኃጢአት ይቅር ይበልሽ ብያለሁ ፡፡

   Delete
 19. ጉድ ነው ዘንድሮ፤ ልጅ ለናቷ ምጥ አስተማረች እንዲሉ፤ ለጎጃም ስለ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ልታስተምሩና ልታርሙ ሞከራችሁ? አሁን በጣም ትልቅ ስተት ተሳሳታችሁ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. I appriciate u dear brother!

   Delete
 20. ምነው ዕኮ የሰው ልጆች በሆነ ባልሆነው ፈጠራ ሲናኮሩ የሚኖሩ?ስሞች የሀይማኖት ዘርፎችና የሥነ ምግባር ዓይነቶች፡ ሓዲስ ኪዳን ከመመሥረቱ በፊት በተመሠረተ ጊዜና ከተመሠረተ በኋላ እስካሁንም ድረስ ወደፊትም በቀጣይነት የነበሩ ያሉና የሚኖሩ ናቸው። በብሉይ ኪዳን ዘመን እምነትን አስመልክቶ
  ስምየኒ መሓሪ ወመስተሣህል በማለት አንድ ስም መኖሩን፤በሐዲስ ኪዳን ዘመን ደግሞ ይትቀደስ ስምከ
  በማለት ያው ስም የሚመሰገን መሆኑን በሥርዓተ አምልኮት መንገድ ካሥረዳ በኋላ ሥነ ምግባርን አስምልክቶ ተፋቀሩ በበይናቲክሙ እርስ በርሳችሁ ብትፋቀሩ ሰዎች ናችሁ አለዚያ ግን በኮች ናችሁ
  ይላልና የሰው ልጆች ስሙን የማይጠሩ ስሙን ስሙን የማያከብሩ ስሙን የማያፈቅሩ ፈጣሪን የማይፈሩ
  ከሆኑ ተቀጽላዎች ሳይሆኑ ተግድራዎች ናቸውና ወዮ!!!ስሙ ማን ይባላል ባንድ አረፍተ ነገር ይመልሱ

  ReplyDelete
 21. ሀ/ጊዮርጊስና አቡነ ፋኑኤል የት ገባችሁ ከ አቡነ ጰውሎስ ጋር ተቀበራችሁ እንዴ ......ዝባዝንኬ ማውራት አይተቅምም ቀቀቀቀቀቀ በሳቅ

  ReplyDelete
 22. abune markosen ketwhaedo legoc lematalat new eng temectewacehu aydelem.adisu strategie yeha new?kahadiwoc nachu.

  ReplyDelete
 23. መስቀል መድሃኒታችን መስቀል መመኪያችን መስቀል የነብሳችን መዳኛ ታዲያ መስቀል ይህን ሁሉ ከተባለ ኢየሱስ ምን ሊባል ነው? ምድረ ከሃዲ ሁሉ አትሳቱ እውነቱን ያዙ ኢየሱስ መድሃኒያለም (የአለም መድሃኒት) ተባለ እንጂ መስቀል የአለም መድሃኒት አልተባለም የመስቀሉ ነገር ተባለ እንጂ መስቀሉ አልተባለም መስቀል የተዘጋጀው ሰውን ሰቅሎ ለመግደል እንጂ ለሌላ ነገር አይደለም በመስቀል ላይ የተሰቀለ የተረገመ መሆኑን ሁላችንም ጠንቅቀን እናውቃለን ስቅላታችንን ተክቶ የተሰቀልንን ማምለክ ሲገባን ያልሆነ ጣጣ ውስጥ መግባት ሌላ መርገም ነው. ጌታ ሆይ መምጣትህን እንናፍቃለን!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ኢየሱስንማ መድኃኒታችን ፣ ብርሃናችን ፣ ሕይወታችን ነው ብለን እንመሰክራለን ፡፡ ርሱም ነኝ ብሎናልና ፡፡ ድኀነታችን የተፈጸመው በመስቀል ላይ በፈሰሰው በቅዱስ ደሙና አሳልፎ በሰጠን ሕይወቱ ነው ፡፡ መስቀሉም በክቡር ደሙ ተቀድሷልና እናከብረዋለን ፡፡ የመስቀሉን ተአምር እናንተ እንደ አሠልጣኞቻችሁ ስለማትቀበሉ ነው እንጅ ፣ የአገር ቆሻሻ ተከምሮበት እንዲቀበርና እንዲረሳ ለማድረግ የሞከሩት በሚፈጽመው ድንቅ ተአምር (ሙት እያስነሳ ፣ ድውይ እየፈወሰ በማስቸገሩ) ነበር ፡፡ ሰውን ለመስቀልና ለመግደል ይገለገሉበት የነበር እስከ ጌታ ስቅለት ነው ፡፡ ከዛ በኋላ ግን ንጉስ ቆስጠንጢኖስ መስቀሉ ተአምር ማድረጉን ስለሰማና በጦር ሜዳ ስላረጋገጠ /ሊሸነፍበት የነበረውን ጦርነት በመስቀሉ ኃይል ድል ማድረግ ስለቻለ/ ክርስትናንም በመቀበሉ ፣ በመስቀል መቸንከርና መሞትን በአዋጅ ከልከሏል ፡፡ እናንተ ዛሬም እንዲያ ትጠቀሙበት ከሆነ ውጉዝ ናችሁ ፡፡ በተረፈ የምታስነብበን በንባብ ካገኘኸው እውቀት ከሆነ ፣ አንተ ሰዎች በአሕዛብነት በነበሩበት ዘመን መሬታቸው እንዳይረክስ ከፍ አድርገው እንደሚሰቅሉ ያለውን ታሪክ ብቻ ነው ያጠናኸው ማለት ነው ፡፡ ቀጠል አድርግና ስለ ክርስትና ታሪክም አንብብ ፤ ነገሩን ከሥረ መሠረቱ ስለጀመርከው መልሱን ራስህ ታገኘዋለህ ፡፡ አይዞህ በርታ !!!

   እንዳትክደኝ ወይም ያ በዘመኑ የነበረ እንዳትል ፣ ዛሬም ጠበል ወደ አለበት አካባቢ (እንጦጦ)ብትሄድ ካህኑ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብለው በክቡር መስቀሉ የህሙማንን ግንባር ሲያስነኩ ፣ ኮረንቲ እንደያዘው ወይም እንደተቆነጠጠ ህጻን እያጓራ መለፍለፍ ይጀምራል ፡፡ በዱላ ብዛት ነው እንዳትል ፣ ተጠምቀው ሲወጡ አንዳች ምልክት እንኳን አይታይባቸውም ፡፡ ይኸም የሚያሳየው ጌታ የባረከልን መስቀል ዛሬም ፈዋሽ መሆኑን ነውና ይልቁን በረከት እንዳያመልጥህ ፤ ንስሃ ገብተህ ተሳለም ፡፡ እንደ ወንጌል ቃል ከሆነ ደግሞ እግዚአብሔር በፈቀደ በቁራጭ ጨርቅ ፣ በጥላ ፣ በእጅ መጫን ሁሉ እንድንድንበት ፣ እንድንፈወስበት አድርጓል ፡፡ ቅዱስ ደሙ የፈሰሰበት መስቀል ደግሞ እንዴታ የበለጠ አይፈውሰን ፣ አያድነን ብለን የማያምኒትን እንሞግታለን፡፡

   Delete
 24. ለኦርቶዶክሳውያን ሲሰበክላቸው የኖረው ለእነርሱ ኃይል፣ ጽንእ፣ ቤዛና መድኃኒተ ነፍስ የሆነው የክርስቶስ መከራ ሳይሆን ዕፀ መስቀሉ ነው። ይህም ጣፋጩን ምግብ መመገብና እርሱኑ ማድነቅ ትቶ፣ ምግብ ላይሆን ምግቡ የቀረበበትን ሳህን እንደማድነቅ ነው የሚቆጠረው.....According to this statement you confess you are not an Orthodox. I'm glad to know that. I hope others will also do! Just a piece of advise, don't meddle yourself into someone's religion if you are not part of it. I don't think God is happy because you are doing this. Stop your gorilla fight and think of your life. I pity you so much! " An idle mind is the Devil's workshop"!

  ReplyDelete
 25. በዚህ ጊዜ እባካችሁ ቅሌትንና ውርደትን አታስተምሩን፡፡ የአርዮስ ፈለግ ይጠቅመናል ብላችሁ ከተለያችሁ በኋላ በቤተክርስቲያን ስም መቀላወጥ ለምን አስፈለገ? ባለማወቅ ተታላችሁ አታምታቱ የምትመለሱበት ቀን እስኪደርስ ባይሆን እንዲህ ካለዉ ቅልዉጥናችሁ ታቀቡ፡፡ ለነፍሳችሁ እዘኑላት እውነት ለመናገር የያዘ ይዟችሁ እንጂ እውነቱ ጠፍቷችሁ አይደለም፡፡ ዛሬም ተመለሱ . . .

  ReplyDelete