Thursday, October 25, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን «ወደ ግብጽ እንመለስ» የሚል ዘፈን ዛሬም ቀጥሏል

ማኅበሩ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ታሪክ የሚያጎድፍ ጽሑፍ አወጣ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ 121ኛ ፓትርያርክ ናቸው አለ   
ጌታ እግዚአብሔር እስራኤልን በድንቅና በተአምራት ከግብጽ ምድር ነጻ ካወጣቸው በኋላ በእርሱ ይታመኑ ወይም አይታመኑ እንደሆነ ሊፈትናቸው በምድረ በዳ በኩል ነበር የወሰዳቸው። በምድረ በዳ በገጠማቸው ፈተና ግን በእግር የተለዩአትን ከልባቸው ግን ያላወጧትን ግብጽን እየጠሩ፣ «ከግብጽ ለምን አወጣችሁን? እዚያው ብንሞት ይሻለን ነበር?...» ይሉ እንደነበር ተጽፏል። የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለ1700 ዓመታት ያህል አለአግባብና በግብጾች ሴራ በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ስር በመንፈሳዊ ባርነት ስትማቅቅ ኖራለች። ከጥንት ጀምሮ ቤተ ክርስቲያኗ ራሷን እንድትችል ጥረት ሲደረግ እንደቆየ የቤተክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል። የብዙ ዘመናት ጥረቱ ተሳክቶም በ1951 ዓ.ም ቤተክርስቲያኗ ራሷን ችላ የራሷን ፓትርያርክ ሾማለች። ከዚያ በኋላም ኢትዮጵያዊ የሆኑ 5 ፓትርያርኮችን አሳልፋለች። እንዲህ በመሆኑ ምን የሚጎዳው ወይም የሚጠቀመው ነገር እንዳለ ባይታወቅም፣ ማኅበረ ቅዱሳን ይህን ሕያው ታሪክ በመፋቅ የሌለ ታሪክ በሐመር መጽሔት ላይ አውጥቷል።

ግብጾች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኢትዮጵያዊ የሆነ ፓትርያርክ እንዳትሾም «ኢትዮጵያውያን ከሊቃውንቶቻቸው መካከል የራሳቸውን ጳጳስ አይሹሙ» የሚል መሰረት የለሽ አንቀጽ በስርዋጽ አስገብተው ልዩ ልዩ ደባ ሲፈጽሙብን ኖረዋል፡፡ በርካታ ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶችንና ልምምዶችን ወደ ቤተክርስቲያን እንዲገባ በማድረግ፣ በተለይም በርካታ በዓላትን በመሥራት ኢትዮጵያውያን ስራ ፈት እንዲሆኑና በአባይ ወንዝ እንዳይጠቀሙ ለማድረግ ልዩ ልዩ ደባ ሲፈጽሙ ቆይተዋል። ምስጋና ለእግዚአብሔር ይሁንና በአባቶቻችን ብርቱ ተጋድሎ ቤተክርስቲያናችን ከግብጾች መንፈሳዊ ጭቆና ነጻ ወጥታለች። ከፕትርክና ጋር በተያያዘም ታሪኳን አንድ ብላ ጀምራለች። የመጀመሪያው ፓትርያርክም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ናቸው። ከዚያም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ እያለ እስከ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ድረስ በድምሩ 5 ፓትርያርኮችን አሳልፋለች። ታሪኳ ሲነገርና ሲዘከር የቆየው በዚህ መንገድ ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የግብጻውያን ስም አጠራር እየጠፋ ከሄደም 50 ዓመታት አልፈዋል። ይሁን እንጂ ለቤተክርስቲያን ከእኔ በላይ አሳቢ ላሳር የሚለው ማኅበረ ቅዱሳን ሞቶ የተቀበረውን ግብጾች በቤተክርስቲያናችን ላይ የነበራቸው የበላይነት ለመመለስና በማሰብ የቤተክርስቲያንን ታሪክ ማበላሸትን ስራዬ ብሎ ይዟል።

ማኅበሩ የቤተክርስቲያናችንን ክብር የሚነካና ከዚህ ቀደም ተነግሮም ተሰምቶም የማያውቅ በቤተ ክርስቲያናችን የነጻነት ታሪክ ላይ ጥቁር ነጥብ የሚጥልና የሚያጠፋ አዲስ ታሪክ ለንባብ አብቅቷል። ወትሮም ቢሆን ስለእኛ ፓትርያርክ ከሚናገር ይልቅ ስለግብጾች ቢያወራ ደስ የሚለውና አውርቶ የማይጠግበው ማኅበረ ቅዱሳን፣  በሐመር የመስከረም 2005 ልዩ እትሙ ይፋ እንዳደረገው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ራሷን ብትችልም፣ ማኅበረ ቅዱሳን ግን ራሷን የቻለችበትን ታሪክ ፍቆና ሰርዞ፣ የመጀመሪያውን ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስን የመጀመሪያው ፓትርያርክ በማለት ፋንታ 117ኛ ፓትርያርክ ናቸው ብሏል። በዚሁ የማኅበረ ቅዱሳን አቆጣጠር መሠረት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ደግሞ 121ኛ ፓትርያርክ አድርጎ ቆጥሯቸዋል፤ እንዲህ ሲል «ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊት የምትባለው ጌታ ከሾማቸው ከሐዋርያት አንስቶ ያልተቋረጠ ክትትል ያለው የሢመት ሐረግ ሲኖር ነው። ለምሳሌ የእኛ ከቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ አንሥቶ ሳይቋረጥ እስከ ቄርሎስ ስድስተኛ (116ኛው) ፓትርያርክ ከደረሰ በኋላ ለእኛ 117ኛ ሆነው አባ ባስልዮስ ኢትዮጵያዊ ተሾሙ። አሁን 121ኛው አባ ጳውሎስ ሆኑ ማለት ነው።» (ሐመር መስከረም 2005 ገጽ 24)።

እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ ላይ የተሾሙት ግብጻውያን ጳጳሳት በፓትርያርክ ማዕርግ የተሾሙ አልነበሩም። በግብጹ ፓትርያርክ ሥር የነበሩ ናቸው። ሕጉ ቢፈቅድላቸውም ሌሎች ኢትዮጵያዊ ጳጳሳትን ለመሾም እንኳ ፈቃደኞች አልነበሩም። ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ጀምሮ ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለውን የራሷን ፓትርያርክ አንድ ብላ ነው መሾም የጀመረችው። ከዚያ ጊዜ አንሥቶ ቤተ ክርስቲያናችን የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ጥገኛ መሆኗ ቀርቷል። ከግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጋርም እኩል መብት ያላት ቤተክርስቲያን ሆናለች።

አሁን ያለው ሁኔታ ይህ ሆኖ ሳለ ማኅበረ ቅዱሳን የቤተክርስቲያንን ታሪክ ለማፋለስ ምን አነሳሳው? ማንም ብሎት የማያውቀውን ታሪክ ሊጽፍ እንዴት ደፈረ? የኢትዮጵያ ፓትርያርኮችን ታሪክ አንድ ብሎ እንዳይጀምርና የግብጻውያን ጳጳሳት ተቀጽላ ማድረግ ለምን አስፈለገ? ቤተክርስቲያናችን ሐዋርያዊት የምትባለው የግብጽ ቤተክርስቲያን ተቀጽላ ስትሆን ነው ማለትስ ከምን የመጣ ነው? ማንም ቢሆን ቤተክርስቲያናችን በግብጽ ቤተክርስቲያን ቅኝ አገዛዝ ሥር አለአግባብ ለ1700 ዓመታት መቆየቷን አይክድም። ይህን ዘመን የምናስታውሰውም በመንፈሳዊ ቁጭት እንጂ እንደማኅበረ ቅዱሳን በኩራት አይደለም። ምክንያቱም በግብጾች የደረሰብን ግፍና ጭቆና በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ምንም እንኳ ማኅበረ ቅዱሳን ወደግብጽ እንመለስ እያለን ቢሆንም።

እነአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ «በሃይማኖተ አበው ቀደምት ወፍልጠተ ውሉድ ደኃርት» ላይ ግብጾች ያታለሉንን ፖለቲካዊ ማታለል እንዲህ ሲሉ ነበር የገለጹት «ጳጳስ የሚሆን ሰው ጥንቱኑ ሲፀነስ በናቱ ራስ ላይ፥ ኋላም ሲወለድ በሕፃኑ ላይ ነጭ ርግብ ከሰማይ ወርዶ ያርፍበታል፤ ይህ ምልክት ያልታየበት ሰው፥ ስንኳን ጥቊሩ ኢትዮጵያዊ ቀዩ ግብጽ ቢሆን ጳጳስ ለመሆን አይበቃም እያሉ የጣፉትና የለጠፉት ማስታወቂያ ቃል ነው። ይህም ፖለቲክ እስከ ዛሬ ለግብጾች ሲሠራ ሲያገለግል ኢትዮጵያንም ሲያታልል ኖሯል።» (ገጽ 20)።

ግብጾች ሲታልሉን የኖሩት እንዲህ ባለ ተረታ ተረት ነው። ግብጾች ያታለሉን ሕጉ ስለፈቀደላቸው ሳይሆን በኒቅያ ጉባኤ ሕጉ የሰጠንን መብት ለራሳቸው በሚመቻቸው መንገድ በማጣመምና በመለወጥ ነው። ሠለስቱ ምእት በዘመናቸው የነበረውን ዓለም ለአራት ከፍለውና አራት መናብርትን ለሮምያ፣ ለእስክንድርያ፣ ለኤፌሶንና ለአንጾኪያ ከሰጡ በኋላ፣ ለሁለቱ ታላላቅ አገሮች ለሥልቅ (ለባግዳድ) እና ለኢትዮጵያ ከአራቱ የማያንስ ከሌሎች አህጉር የሚበልጥ መካከለኛ ሕግና ማዕርግ እንዳቆሙ የሚያትተው ሃይማኖተ አበው ቀደምት፣ የኢትዮጵያው ጳጳስ ከእስክንድርያው ተሹሞ ሊቀጳጳስ እየተባለ ከበታቹ የፈለገውን ያህል ለየአህጉሩና ለያውራጃው ጳጳሳትንና ኤጲስ ቆጶሳትን ይሾም ዘንድ በ፵፩ኛው አንቀጽ ተደንግጓል ይላል። ግብጾች ግን ድንጋጌውን ለራሳቸው በሚመች መንገድ ተርጉመውና የራሳቸውን ሐሳብ አክለው ኢትዮጵያዊ ጳጳስ እንዳይሾም በማድረግ ለብዙ ምእት ኣመታት መንፈሳዊ ጭቆና ሲያደርሱብን ኖረዋል።

መንፈሳዊ ነጻነታችንን ተጎናጽፈን ባለንበት በዚህ ዘመን አላዋቂዎቹና ምንም ጠያቂ የሌለባቸው የማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች ነጻነታችንን የሚጻረርና የቤተክርስቲያናችንን ክብር የሚነካ ነገር ሲጽፉ ዝም መባላቸው ይገርማል። አባቶች ጳጳሳት ለመሆኑ ይህን የማኅበረ ቅዱሳን ክብረ ነክና ቤተክርስቲያን አዋራጅ ታሪክ እንዴት አያችሁት? ይህን አጉራ ዘለል ማኅበር የማትገስጹትስ እስከ መቼ ነው? ለቤተክርስቲያን ቆሜያለሁ፣ ከእኔ በላይ ላሳር እያለ በተቃራኒው እየሠራ ያለውን አፍራሽ ተግባር ለመቃወም ድምጻችሁን የማታሰሙትስ እስከ መቼ ነው?

33 comments:

 1. በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የማትነዙት ፕሮፓጋንዳ የለም ማለት ነው::

  ReplyDelete
 2. if u know church history, yes what Hamer wrote is correct. Are you telling me that EOTC was without Patriarch for the 1700 years? Read and comrhend, okay!

  ReplyDelete
 3. Demo bilachihu bilachihu, Gibtsoch beal serulachihu alachihu? Gudd new eko, eshi, befit Orthodox alachu ahun demo Gibts, "sira fett" endinihon aregechin. yigermal. Sira fett yehonachihutis enate nachihu, kehadi, yilik nisiha gibu yemir, leEgnam leEnantem fikir yibejal. Mekad, ante kifu, anchi kifu mebabal min yadergal esti. bayihon yikir belun yikir enibelachihu ena nisiha engiba. Andit Haymanot, Andit Emnet, yekedemechiw Orthodox tewahedo bicha natt.

  ReplyDelete
 4. So what... who are you? If the article is wrong, we have our father to correct it. Why you are so desperate... The article is to show our church is from the apostels...where is in the article it says we should go back to Egypt ..

  what is wrong with this በኋላ ለእኛ 117ኛ ሆነው አባ ባስልዮስ ኢትዮጵያዊ ተሾሙ... are you saying The History of Ethiopian Orthodx Church starts from አባ ባስልዮስ ...You wish.. we have long long history and you may not understand. The main reason why you are so disturbed becasue you don't want to hear unlike yours ( protestants) our church is direct from the apostles... and we will count form the apostel ( saint Mark) all the way to this generation and to the time to come.
  Protestnats took exit long time ago and still they are going in different highways and freeways.

  ReplyDelete
 5. Do you know why? Because they know nothing about the Ethiopian Orthodox Tewahdo Church history; just they came into the church by making short cut. any way, as you said it, we have freed from the abundant of the Egibshan politicians. May the Almighty God bless your ministry and mission.

  ReplyDelete
 6. Do you know why? Because they know nothing about the Ethiopian Orthodox Tewahdo Church history; just they came into the church by making short cut. any way, as you said it, we have freed from the abundant of the Egibshan politicians. May the Almighty God bless your ministry and mission.

  ReplyDelete
 7. አባ ሰላማዎች ዛሬ እውነት የአባሰላማ ልጅነት የሚገልጽ ጽሑፍ ስለጻፋችሁ ላመሰግናችሁ ወደድኩ
  እነዚህ በቅዱሳን ስም ማህበረ ቅዱሳን በማለት ራሳቸውን በንግድና በፖለቲካ ስም ያደራጁ ሰዎች ባለፈው ሀምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ከ20ኛ በዓለ ሲመት ጋር 53ኛ የቤተክርስቲያንዋን የነፃነት በዓል ማክበራቸው እየታወቀ ድሮውም ቢሆን እነዚህ ፖለቲከኞች የራሳቸውን ፓትርያርክ እውቀትና መልካም ሥራ በዓለም ተቀባይነት አግኝቶ የዓለም አባትነት በተገኘበት ሁኔታ እንናኳ የብፁዕ ወቅዱስ ሲኖዳ መፃህፍትን ሲተሮጉሙና ሲጽፉ ስለራሳቸው ጽፈው አያውቁም እኒህ መበለቶች ሀይማኖት ሲባል ትዝ የሚላቸው ላዕላዊ ታህታዊ ግብጽ ነው ለራሳቸው ክብር ባይኖራቸው ኢትያጵያዊያን ፓትርያርኮችን ከግብጾች በመቁተራቸው ወራዶች ናቸው እላለሁ ተለጣፊዎች ለማለትም እወዳለሁ ገና አባይም ለግብጽ ይገባል ከማለት አይቆጠቡምና አወቅሽ ሲሉዋት መጽሀፍ አጠበች፡፡

  ReplyDelete
 8. በአገራችን የክርስትና እምነት የተጀመረው ከሃምሳ ዓመታት በፊት አይደለም ፡፡ በዚህ ገለጻ የምንስማማ ይመስለኛል ፡፡ በመሆኑም ስለ አገራችን የክርስትና ታሪክ ሲነገር የግድ በግብጾች አመራር ሥር የነበርንበትን ዘመንም መካድ ወይም መሻር አንችልም ፡፡ ለአገራችን የመከራ ዘመንና የሚያሳፍር ቢሆንም ቆርጠው ሊጥሉት አይገባም ፡፡ ከነድክመቱ ፣ ከነጉዳቱ ሊተረክ ፣ ትውልድም በመቀባበል ሊማርበትና ፣ ሊገነዘበው ግድ ይላል ፡፡ እናንተ ከሃይማኖት አበው ቀደምት ከጠቀሳችሁልን በተጨማሪ እጅግ የሚያንገሸግሽ ታሪካችን የእስላም ሼክ ሁሉ ጳጳስ ተብሎ ተልኮልን መስጊዱን ማስፋፋቱ መገለጹ ነው ፡፡ ያም ቢሆን እንኳን ታሪካችን ነውና ሊዘለል አይቻልም ፡፡ የስንክሳር መጽሐፍትን ለሚፈትሽ ሌሎች ታሪኮችንም ያገኛል ፡፡

  እንዲያውም የሚገርመው የቋንቋ ግርዶሽ በመኖሩ በጳጳስ ትመራለች ለመባል ያህል አባት ካህን ተብዬው ይመጣልናል እንጅ አስተዳደሩንና አገልግሎቱን የሚያከናውኑት የአገራችን ካህናትና ሊቃውንት እንደ ነበሩ የጠቀሳችኋቸው ጸሃፊ አክለው ገልጸውታል ፡፡ ግብጽ በሙስሊም ወራሪዎች በተከበበችና ግንኙነቱ በተዳከመበት ወቅትም ፣ የአገሩን ሠርዶ በአገሩ በሬ ብለው ፣ ሥልጣነ ክህነቱን በሥርዓቱ ባያገኙትም (ተክለሃይማኖት)የህዝብ አገልግሎት እንዳይቋረጥ ፣ እኒያ ቀናዒ ሃይማኖተኛ አባቶች ለፍተዋል ፡፡ ታድያ የነዚህንስ ቆራጥ አባቶች መከራና ድካም ለመዘከር ከሃምሳው ዓመታት ታሪካችን ትንሽ ገፋ ማድረጉ ሳይሻል ይቀራል ትላላችሁ? ያንን ሁሉ ከሻርነውማ ክርስትና በአገራችን የገባው የዛሬ ሃምሳ ዓመት ነው ተብሎ አዲስ ድርሰት መጻፍ ሊያስፈልግ ነው ፡፡

  በተረፈ አሁን ተመልሰን በግብጽ አመራር ሥር እንሁን የሚል ምኞት ቀርቦ ከሆነ ፣ በአጭሩ እብደት ነው እለዋለሁ ፡፡ በተረፈ ግን ታሪክ በመልካምነትና በመጥፎነት ቢፈረጅም እንዳለ ለትውልድ መዘከር ይኖርበታል ፡፡ የባሪያ ሥርዓት እጅግ አሳፋሪና አስቀያሚ ቢሆንም በዛ ሥርዓት ውስጥ ትውልድ ስላለፈ የግድ ከታሪክ መዝገብ ገብቶ ይጻፋል ፡፡ ያን በማወቃችን ብዙ ልንማር ፣ ባለፈው ልንቆጭና የበለጠ ፣ የተሻለም ለመሥራት ያተጋናልና ነው ፡፡ አስተያየቴ ከጽሁፋችሁ በመነሳት እንጅ ምን እንደጻፉ ስላነበብኩ አይደለም ፡፡ የግንዛቤ ችግር ካለብኝ በማብራሪያ ልታረም እችላለሁ ፡፡

  ReplyDelete
 9. Aba Selama, your war with MK is just like Iran and Iraq war, I can not wait to see your war ends. Evry article you post never pass mentioning MK, what is your objective? The more you write against MK, MK keeps doing the good job and getting more love from EOT christians.

  ReplyDelete
 10. ጉድና ጅራት ከኋላ ነው ይባል የለ?ቀስ በቀስ ከሃይማኖተኝነት አጀንዳ ወደ ፖለቲካ ይገባል ይሏችኋል ይሄ ነው!!ቀድሞም ለነገሩ ሃይማኖቱን ሽፋን አድርጎ ቤ/ክ መሽጎ ተቀመጠ እንጂ መንግሥት ሃይማኖት ክልል አይገባም ብሎ ስላሰበ እኮ ነው::ታሪክ ነው?እስከዛሬ እኛ እግዚአብሔር ረድቶን ይቅር ካልናቸው ከጎረቤት ጋር በሰላም መኖር ይሻላልስለሚል በማለት ያልነው አንሶ እንደው ከግብጾች ጋር እንቆጠርየመጣው ሹመተኛ ግብጻዊ እስላምም ተቆጥሮ ይሆን እንዴ እባካችሁ?በታሪክ የማንዘነጋው ማን ነበር ስሙ?አስኬማውን ምሽግ አድርጎ መስጊድ አሰርቶልን ሄደ እኮ!እንደገና የሚገርመው የሚደረገው ሴራ ውስጥ እነርሱም አሉበት ማለት እኮ ነው እንጂ ለጤና አይደለም መቼም ይህንን የጻፉት ለማንኛውም እግዚአብሔር ይርዳቸው አንደኛውን የፓርቲ ስም ሰጥተው ራሳቸውን ቢገልጹ መልካም ቢሆን!!አለች አሉ ገበያ የወጣች ዕብድ ሴት!!
  ኒቆዲሞስ

  ReplyDelete
 11. Tadia yeh menu new wenjel, begibts ser eyalen 116 patriark raschnen kechalen behuala degmo 5, so what? begebts ser eyalen legna papas bilekulenem patriarkachen gen 1 neber, menm fire yelelew neger yetsahchihut.

  ReplyDelete
 12. wuy wuy enante endet aynet sihtet agegnachihu ebakachihu! Maferiawoch ena tadia betekrstianachn eske 1951 yet neberech litlu new?

  ReplyDelete
  Replies
  1. mawo you are very flush. the head of the church is only Jesus Christ. not the Coptic church .they were condemn us not to select our archbishop from our educated / have you read this sentences /Ethiopian never elect archbishops from their secular es / is it the word of god ? do you believe we are not equal with Egyptians in front of god? human beings equal in front of his creature >

   Delete
 13. Beka emiwora tefa? You invite me to read Hamer and then I become the witness for Mahibere kidusan that mk is the backbone of the church. an ideal mind is the workshop of a divil. So divil is trying his experiment on you to distroy EOTC but he can't as it is clearly stated in the bible.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Beka emiwora tefa? You invite me to read Hamer and then I become the witness for Mahibere kidusan that mk is the backbone of the church. an ideal mind is the workshop of a divil. So divil is trying his experiment on you to distroy EOTC but he can't as it is clearly stated in the bible

   Delete
  2. WHEN START THE RELATION WITH FOX .YES INDEED WHEN THE HISTORY OF EOTC REMEMBERED WE REMEMBERED HOW EGYPTIAN PLAY A BAD GAME ON OUR CHURCH BECAUSE OF THIS WE HATE THEM EN THE OTHER SIDE YES THEY ARE OUR PARENTS AND ENEMIES NUMBER ONE THEY WERE NOT COM TO ETHIOPIA TO TEACH US THE BIBLE BUT TO MAKE US LAZY NOT TO USE OUR RIVER ABAY, OUT OF THE WORD OF GAD THEY THOUGH US NOT TO WORK MANY DAYS BY GIVING THEM NAMES LIKE LIDETA /TADEWOS/ BETA SO...ON NOW WE ARE THE POOREST WHEN THEY ERE THE REACH EST, OUR POVERTY IS THE RESULT OF THEIR JEALOUSY THOUGH ,BECAUSE OF THIS WE NEVER REMEMBER THEM IN GOOD WAY STILE THEY ARE STILL TIRING TO TAKE OUR LAND IN JERUSALEM .SO IT IS A BIG MISTAKE TO COUNT OUR HIERARCHY WITH THEM

   Delete
  3. አባ ኮዳ ምነው ካልጠፋ ስያሜ በአባለ ዘር በሽታ ስም ተጠራህ ? ለአንተ መጠሪያነት ቢስማማህም ለሚረዳው አንባቢ ያስቀይማል ፤ ቶሎ ቀይረው ፡፡ አየህ ታሪክ ቢመርም ቢጣፍጥም መጠቀሱና መጻፉ ለትምህርት ይሆናል ፡፡ በደፈናው መዝለሉ ግን እጅግ ስህተትን ይወልዳል ፤ አዲስ የልብ ወለድ ታሪክ ፈጠራንም ይጋብዛልና ደግ አይደለም ፡፡ ያለፈ የቤተ ክርስቲያን ታሪካችንን ስላወቅህ ይኸው አንተ እንኳን መቆጨት ቻልክ ፡፡ ከዚህ ከተበላሸ ፣ ከተጎዳንበት ታሪካችን ተነስተን ፣ የሚስተካከለውን አስተካክለን ፣ የሚሻረውን ሽረን ለወደፊት ጉዞአችን በሥርዓቱ ብናመቻች ለተሻለ እድገት እንበቃለን ፡፡ ስለሆነም ታሪክን እንደገና እንድገመው ካልተባለ ፣ ለትምህርት በመነገሩ አንዳች ክፋት አይኖረውም እላለሁ ፡፡

   አንዳንድ የዋሆች አሁን ያለውን የቤተ ክርስቲያናችን ሲኖዶስ ከሶስት ስለተከፈለ በመቆጨት ከግብጾች አስተዳደር ባንወጣ ይኸ ጉድ አይመጣብንም ነበር ፡፡ አሁንም የዚህን ዘመን ፈተና በመመረርና ፣ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት በማሰብ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ፣ ከግብጽ ባንለይ ኖሮ የሚል ጽሁፍ ሲያስነብቡ ሰንብተዋል ፡፡ ስሜታቸውን መጋራት ቢቻልም ፣ በመፍትሄነት የሚያቀርቡትን ምኞት ግን መቀበል አይቻልም ፡፡ ስለዚህም ታሪክ መጠቀሱ ሊያስተምረን ይችል እንደሁ እነጅ ጉዳት አይኖረውምና ማኀበረ ቅዱሳን ስለተናገረውና ስለጻፈው ብቻ በጭፍን ሁሉን መጥላት ትክክል አይሆንም ፡፡

   የሃይማኖት ታሪካችንም ቢሆን ከግብጾች ክህነት አይጀምርም ፤ አለፍ ብሎ ከኦሪቱምና በፊትም ከጸሃይ አምልኮ እንደሆነ ይተረካልና ሁሉም የት መጣነቱን እንዲያውቅ በሥርዓትና እንደአግባቡ መጠቀስ ይኖርበታል ፡፡ አሁን ሰለጠኑ የሚባሉት አገሮች በድንጋይ ፣ በተራራ ፣ በፀሃይ ... በሚያመልኩበት ዘመን አገራችን እግዚአብሔርን ታመልክ ነበር ፡፡ እነርሱ ጋር ክርስትና በጦርነትና በመስዋዕትነት ሲጀመር አገራችን በራሷ ጃንደረባ ወንጌል ተሰበከላት ፤ ሐዋርያት ሲመጡም ያለፈተና አስተማሩ ፡፡ ከሦስተኛው ምዕተ ዓመት ጀምሮ ደግሞ ከግብጽ ተቆራኘን ፡፡

   Delete
 14. gud "aba selama" you are really crazy.

  ReplyDelete
 15. You have little mind. Before you wrote to support or againest just make sure come with the tabe in concret evidence. Otherwise, you make full blessing to get some thing in mk criminal village. I assure you stay way from devil mk. Most mk element women in carrier of blood pathogen disease aids, bc they shared one for to five ratio. Above writer I called you today blockhead.

  ReplyDelete
 16. Aba selama, jIt is time now to be burry deveil Mk which is time to be strong, a time to be weak or a time to be loose. A real Christian love Jesus willing to serve true. The enemy of Jesus that came from taliban mk now we act to demolish them. I urge all eotc every where unite together say some go to heaven. Death to mk.

  ReplyDelete
 17. kahun behuala mk minem bota yelewem tebiku ke tikit geze behuala hulunim tesemalachehu lemehonu gibitsoch le ethiopia telat enji wedaj mech hono yawekal mk hulem ye gibits tegegna new ke ethiopia ortodox emnet kemegelets yilek ye gebts tarik bitsf yiwedal gin ayawkutim mk bezum atezeleyee yet endemetewedeki atawkimenaaaa

  ReplyDelete
 18. ሰላማዎች ሰላም ውላችሁ ሰላም አደራችሁ ለሊቃውንት ስትሉ አብራችሁን አልቅሱ የመርካቶ ሌባ ሰርቆ ሲያመልጥ ከቡኃላ ያሉት ሌባ ሌባ ሲሉ እሱም ሌባ ሌባ በማለት ነው የሚያመልጠው የአሁኑ ግን በስራው ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
  የዚህ ሳምንት ጉድ ልንገራችሁ ጸያፍ ካልተባለ ብርድ በጣም የበረታ ጊዜ( ቆማጣ ያሳቅፋል )ይባላል የወቅቱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስበከት ዋና ስራ አስኪያጅ ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ በጠቅላይ ቤተክህነት መክትል ስራ አስኪያጅ ሆነው በሰሩባቸው ዓመታት የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች መኪናና ልብስ በማየት ቅናት ቢያበግናቸው ከጠቅላይ ቤተክህነቱ ም/ስራ አስኪያጅነት በተጨማሪ የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል አስተዳዳሪ ሆነው ተመደቡ ሆኖም ውሎ ሳያድር ሹመታቸው ከተጻፈበት መስርያቤት ሳይወጣ ተቀደደባቸው / አዶኒያስ / ከዛች እለት ጀምረው ዘረፋና ሙስና በሀገረ ስበከቱ ሰፍነዋል ሀገረ ስበከቱ በአራት መከፈል አለበት በማለት ቤተክህነቱን ሲንጡት መቆየታቸው የአደባባይ ምስጢር ነው .ታድያ የጠሉት ይወርሳል የፈሩት ይደርሳል ሆነና በአንድ ዓመታቸው 74 ሰራተኞች በፈተና ከ 3800 በላይ ሠራተኞች ያለፈተናና ምዘና በሙስኝነት ሲቀጥሩ፤ ከተቀጣሪወቹ የሚቀበሉት ገንዘብ አስደንጋጭ መሆኑ ተቀጣሪዎቹ ይናገራሉ በመሰረቱ ይህ ጉዳዩ እውነት ወይም ውሸት ለማለት ለሚፈልግ አውነት ፈላጊ የምንነግረው በዚህ ዓመት ከላይ የተጠቀሱት ያህል ለመቀጠራቸው የመዝገብ ቤቱን መዝገብ በማገላበጥ ማረጋገጥ የሚቻል ሲሆን ያለፈተናና ምዘና በድብብቆሽ እና በሙስና ለመቀጠራቸው ደግሞ ለቅጥራቸው የተደረገ ቃለጉባኤ ሆነ ፈተና ሊቀርብ ያማይችል መሆኑን ነው .ነገር ግን ብዙ ፤የብዙ ብዙ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በደጅጠኝነት እንደ ሆስፒታል ቀኑንና ማታውን ሀገረ ስብከቱ ከበው በሚታዩበት ጊዚመሆኑን ስናይ በእጅጉ አዝነናል የሰውየው ቆብና አቋምም እንደ ሀብታም መቃብር በእብነ በረድ የተዋበ ውስጥ ግን ያው መሆኑን ያስገነዝበናል ወደዋናው ጉዳይ ስመልሳችሁ በጥቂት ቀናት ብዙ ብሮች ያስገነላቸው የሀገረ ስበከቱ ዋና ስራ አስኪያጅነት እድሜ ለማስቀጠል ሲሉ በጉባኤ ፊት አንዲት ውሸት ቢናገሩ ይችን ይብር ሙዳይ የሆነት ዋና ስራ አስኪያጅነት ለማግኘት የሚጠባበቁ ሰዎች ከብርሃን ፍጥነት በፈጠነ ላልሰማ ሁሉ በማሰማት ወንበረቻውን ቢነቀንቁባቸው ሲሰድቡት የነበረና ከሰኞ እስከ ማክሰኞ በደረቅ ቀን የኮቴ ያስከፍሉት የነበረ የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ኃላፊ ሁሉ ማስተንቀቂያ እየፃፉ እና ማእከላዊ መንግስት ከእኔ ጋር ነው በማለት / እድሜ ለኢህ አደግ ስርአት ዚህ አይነት ሞችላፎች ይቅርና አጽማቸው የከሰከሱና ደማቸውን አፍስሰው ዲሞክራሲ ያሰፈኑትን ክቡራን ታጋዮችም በመስና ላይ ሲወድቁ በቃኝ ለመባላቸው ምስክሮች ከእኛ ወዲያ ማንይሆናል፡፡ የሆኖ ሁኖ በዚህ ሁኔታ እያስፈራሩ የድጋፍ ፊርማ እነዲፈርም እያደረጉ ከመሆናቸውም በላይ የመንበረ ፓትርያርክ ጽ/ቤቱ ልዑክ በመሆን ነገር ሲሰሩበት የቆየውን ማህበረ ቅዱሳንም አባላቱን ጽ/ቤታቸው ድረስ በመጥራት አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እንዳትከፋፈል አግዙን ማህበሩን ከመንግስት አካላት ድጋፍ እንዲያገኝ በሀገረ ስበከቱ ስም የድጋፍ ደብዳቤ እጽፍላችሁ አለሁ በጠቸማሪም የማህበሩ አባላትን በታላላቅ አድባራት እና ገዳማት በስብከተ ወንጌል ሀላፊነት እመድብላችህ አለሁ ካለን ትርፍ ቢሮም አንድ ቢሮ ያለኪራይ እሰጣችህአለሁ ማለታቸው ዎይ! ጭንቅ አያስብልም / ቀድሞ ነበረ እነጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ / ከቢሮአቸው እስከ አድባራት በመውረድ ክብራቸውን በመሸጥ ገንዘብ ለቀማ ላይ የቆዩት ዋና ስራ አስኪያጅ የቀራባቸው ክብር ቢኖራቸው ጺማቸው ብቻ ነው ይልቁንም ሶሪያቸው ከፍ አድርገው ቢታጠቁት ከፍተኛ ዋጋ ሊያወጣላቸው እንደሚችል ብንጠቁማቸው ከሙዳየ- ምጽወት ገንዘብ ስለሚሻል ነው ፤ከየት መጥቶ የሚሰጣቸው መሰላቸው!!ኢኢኢ………

  ReplyDelete
 19. Please go to school....>..
  do not mess around for nothing.....

  ReplyDelete
 20. አይ አላዋቂ ኢትዮጵያ ውስጥ የተሾትን ቢሆን የጠቀሰው 111 ናቸው 119 ናቸው የሚሉም አሉ:: ስለዚህ 111 እና 5 116ኛ በሆነ:: ነገር ግን እናንት የምትሉትን ሳይሆን በግብዕጽ የተሾሙትን ከማርቆስ እስከ 116ኛው የግብጽን ፓትሪያርኮች ታሳቢ ያደረገ ቆጠራ ነው እንጂ እንደ አንድ ሀገረ ስብከት ኢትዮጵያን የመሩትን ኤጵስ ቆጶሳትና ሊቃነ ጳጳሳት አይደለደም:: ነገሩም ታሪክ ነው እንደእናንተ ቢሆን ህግና ስርአት አይሰራም:: የራሳችንን ፓትሪያርክ ማንንም ሳናስፈቅድ እንምረጥ እንደምትሉ እርግጠኛ ነኝ:: ለነገሩ መጻህፍትን በደንብ መመርመር ብትችሉ ባልተሳሳታችሁ ነበር:: ይህ የጥራዝ ነጠቅ እውቀት ችግር ነው::

  ReplyDelete
 21. I visit your site very frequently, but I don't seem to find anything that does not oppose MK, what is your main adgenda here? I am not supporting MK or you, but it seems to me in reading most of your article you are a "Tehadiso" if you are just come out and admit it. It does not mean anytghing it should be respected. The only problem I have with you is that don't try to tell me or other Orhodox Tewahedo followers as you are an "Orthodox Tewahedo " follower as well I don't think you are.

  ReplyDelete
 22. “የሚውጠዉን ፈልጎ ሰይጣን እንደሚያገሳ አንበሳ . . . ይዞራል” በርቱ አልላችሁም፤ ያጥፋችሁም አልልም ያስታግሳችሁ፣ በላያችሁ የሰፈረዉንም ይገላግላችሁ፤ እውነቱን ይግለጥላችሁ!

  ReplyDelete
 23. EOTC beal akbra deheyech, eshi muslim ethiopians lemn aladegum? Mechem enesu beal ayakebrum.Be wise,it is not easy just to impose un-bibilical religious doctrines on EOTC unless they verified and adopt it. Pls, refer history of king Susynios and Portuguese.

  ReplyDelete
 24. “ማኅበረ ቅዱሳን ግን ራሷን የቻለችበትን ታሪክ ፍቆና ሰርዞ፣ የመጀመሪያውን ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስን የመጀመሪያው ፓትርያርክ በማለት ፋንታ 117ኛ ፓትርያርክ ናቸው ብሏል።” ብላችሁ የጻፋችሁት ማስተዋል የጎደላችሁ መሆኑን ያሳያል:: ምክንያቱም “በኢትዮጵያ ላይ የተሾሙት ግብጻውያን ጳጳሳት በፓትርያርክ ማዕርግ የተሾሙ አልነበሩም። በግብጹ ፓትርያርክ ሥር የነበሩ ናቸው።” ስትሉ በኢትዮጵያ ላይ የተሾሙት ግብጻውያን ጳጳሳት ኢትዮጵያን እንደ አንድ የግብጽ ሀገረ ስብከት እንነበረችና ራሳችሁ መልሳችሁታል:: የግብጽ አንድ ሀገረ ስብከት ከሆነች ደግሞ ፓትርያርኳ የግብጽ ፓትርያርክ ነበሩ ማለት ነው:: ታዲያ ማህበሩን ስለምትጠሉት ብቻ ሀቅን ለምን ትክዳላችሁ?

  ReplyDelete
 25. አይ አላዋቂ ኢትዮጵያ ውስጥ የተሾትን ቢሆን የጠቀሰው 111 ናቸው 119 ናቸው የሚሉም አሉ:: ስለዚህ 111 እና 5 116ኛ በሆነ:: ነገር ግን እናንት የምትሉትን ሳይሆን በግብዕጽ የተሾሙትን ከማርቆስ እስከ 116ኛው የግብጽን ፓትሪያርኮች ታሳቢ ያደረገ ቆጠራ ነው እንጂ እንደ አንድ ሀገረ ስብከት ኢትዮጵያን የመሩትን ኤጵስ ቆጶሳትና ሊቃነ ጳጳሳት አይደለደም:: ነገሩም ታሪክ ነው እንደእናንተ ቢሆን ህግና ስርአት አይሰራም:: የራሳችንን ፓትሪያርክ ማንንም ሳናስፈቅድ እንምረጥ እንደምትሉ እርግጠኛ ነኝ:: ለነገሩ መጻህፍትን በደንብ መመርመር ብትችሉ ባልተሳሳታችሁ ነበር:: ይህ የጥራዝ ነጠቅ እውቀት ችግር ነው::

  ReplyDelete
 26. Pretty section of content. I just stumbled upon your blog and in accession capital to assert that I get actually enjoyed account
  your blog posts. Any way I'll be subscribing to your augment and even I achievement you access consistently rapidly.
  My blog ; personal development plan

  ReplyDelete
 27. Hello! I simply wish to give you a big thumbs up for your great information you
  have here on this post. I am coming back to your site for more soon.
  Feel free to visit my blog ; laser tattoo removal cost

  ReplyDelete
 28. Having read this I thought it was extremely enlightening.

  I appreciate you taking the time and energy to put
  this informative article together. I once again find myself personally spending a significant amount
  of time both reading and leaving comments. But so what, it was still
  worthwhile!
  My web-site ... Alanya Oba

  ReplyDelete
 29. Perhaps you are interested in contrasting laser whitening procedures
  with topical solution options. If you are too busy to make to your dental and medical appointments during
  the regular work week, you may want to consider going to a Saturday dentist.

  Plaque, the nasty bacteria in your mouth, build up every day.


  Also visit my web-site; keyword

  ReplyDelete