Friday, November 30, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን ብሎግ ደጀሰላም የወሬ እጥረት ያጋጠመው ይመስላል

ክፍተቱ የተፈጠረው ከቤተክህነት ወሬዎችን የሚለቃቅመውና የሚያቀብለው ማንያዘዋል ግብጽ ስለሚገኝ ነው

ማኅበረ ቅዱሳን የእኔ አይደለም እያለ የሚያስተባብለውና የእርሱ መሆኑ ግን የሚታወቀው «ደጀሰላም» የወሬ እጥረት ያጋጠመው መሆኑ እየታየ ነው፡፡ ራሱም ኅዳር 18/2005 ፖስት ባደረገው ጽሑፍ  «በየአካባቢያቸው ያለውን የቤተ ክርስቲያንን ሁኔታ በመከታተልሪፖርትየሚልኩልን ፈቃደኛ ደጀ ሰላማውያንአለንእንዲሉን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን» ብሏል፡፡ የወሬ እጥረቱ የተፈጠረው እንደእርጎ እንትን በየቦታው ጥልቅ የሚለውና የደጀሰላም ዋና ወሬ አቀባይ የሆነው ማንያዘዋል ለግብጹ ፓትርያርክ ባኣለ ሲመት ከጳጳሳት ጋር ተለጣፊ ሆኖ በማኅበሩ ወጪ ወደግብጽ ስለሄደና እስካሁን ድረስ በአገር ውስጥ ስለሌለ ነው ተብሏል፡፡ ማንያዘዋል ለአንድ ወር ቆይታ በማኅበሩ 32 ሺ ብር ወጪ ተደርጎለት የሄደ መሆኑ ቢታወቅም እርሱ ግን የከፈለልኝ የቲዎሎጂ ማኅበሩ በማለት ያስወራ እንደነበር ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡  ማኅበሩ በገጠር አብያተ ክርስቲያናትናት በገዳማት ስም ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር የሚሰበስበውን ገንዘብ እንዲህ ባለመንገድ እንደሚያባክን ይህ አንዱ ማሳያ ነው፡፡

Thursday, November 29, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ «ብላክ ማርኬት» እንዳለው ተሰማ

ድብቅ አላማ ይዞ በሃይማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀሰው ማኅበረ ቅዱሳን በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ ህገወጥ የውጭ ምንዛሪ ቢሮ በድብቅ መክፈቱን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ እንደ ምንጮቻችን ከሆነ ማኅበሩ ለዚህ ህገወጥ ተግባር የሚጠቀምበት ቢሮ በስም «የቲዎሎጂ ምሩቃን ማኅበር» እየተባለ የሚጠራውና የቲዎሎጂ ምሩቃን በአባልነት የሌሉበትና ማንያዘዋልን ጨምሮ ጥቂት የማቅ «የቲዎሎጂ ምሩቃን» አባላት የሚገናኙበት ቢሮ ነው ብለዋል፡፡ ቢሮው ቀድሞ ከነበረበት ከቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲወጣ ከተደረገ በኋላ ማኅበረ ቅዱሳን በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ ቢሮ እንዲያገኝ አድርጓል፡፡ ይህን ያደረገውም የውጭ ምንዛሬውን ጨምሮ ሌሎች ድብቅ ስራዎችን ለመስራትና ለመጠቀም አስቦ እንደሆነ ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡ ቢሮው የማቅ ሌላው ቢሮ ነው እያሉም ነው፡፡ ማኅበሩ የዶላር ዩሮና ፓውንድ ምንዛሬዎችን የሚያካሂደው በድብቅ ሲሆን ከውጪ አገር ዶላር ይዘው የሚመጡና ዶላር የተላከላቸው የማኅበሩ አባላትና አንዳንድ ጳጳሳትም ዶላር ዩሮና ፓውንድ በዚሁ ቢሮ እንዲመነዝሩ እንደሚደረግ የደረሰን መረጃ ያመለከታል፡፡ መንግስት የዶላር እጥረት አጋጥሞኛል በሚልበት በዚህ ወቅት ማቅ እንዲህ እያደረገ መሆኑ ጉዳዩን አነጋጋሪ አድርጎታል፡፡

Monday, November 26, 2012

«አለው ነገር» የተሰኘ አዲስ ኦርቶዶክሳዊ የዝማሬ ሲዲ በዘማርያን ትዝታው፣ ምርትነሽና ዘርፌ

‘ማልደራደርበት‘ ማልቀብረው እውነት
አንገት ‘ማያስደፋኝ የማላፍርበት
ኢየሱስ የሚለው ስም እስትንፋሴ ነው
እውነቱ ይሄው ነው


አንዱን መዝሙር ለቅምሻ ጋብዘናል- ሌላውን ገዝተው ያዳምጡ

እነዚህ ስንኞች የተወሰዱት ከአንድ የግጥም መድበል ውስጥ እንዳይመስላችሁ፤ ዲ/ን ትዝታው ሳሙኤል ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን እና ዘማሪት ዘርፌ ከበደ በጋራ ከሳተሙትና «አለው ነገር» የሚል ርእስ ከተሰጠው የዝማሬ ሲዲ ላይ የተወሰደ ነው፡፡ እውነት ነው ኢየሱስ የሚለው ስም ለእውነተኛ ክርስቲያን እስትንፋስ ነው፡፡ አንገት የማያስደፋና የማያሳፍር የማይቀበርና ለድርድር የማይቀርብ ስም ነው፡፡ እውነትም ኢየሱስ በሚለው ስም ላይ ድርድር የለም!!!

Sunday, November 25, 2012

መዳንም በሌላ በማንም የለም

  • ዛሬ በኢየሱስ ስም መስበክ መናፍቅ አሰኝቶ ያስወግዛል
  • ገድለ ተክለ ሃይማኖት የተክለ ሃይማኖትን ስም የጠራ ይድናል ይላል
 «መዳንም በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የተሰጠን ከሰማይ በታች ሌላ የለም» የሐዋ 12፥4
ይህን ቃል የተናገረው ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ነው። የተናገረውም በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ነው። ይህን ቃል ለመናገር ያበቃው ሲወለድ ጀምሮ ሽባ የሆነ ሰው ነበር። ሰውዬው ለመሥራት ለመሮጥ፣ ለመቅደም፣ ለመታገል የማይችል ምስኪን ሰው ሆኖ በወላጆቹ ላይ ወድቆ የሚኖር ሰው ነበር። ጥዋትና ማታ በቤተ መቅደስ በር ላይ እያመጡ ይጥሉታል፣ ከሕዝብ ምጽዋት እየለመነ የዕለት እንጀራውን ያገኛል። ከዚህ ሕይወት የሚያወጣው ሌላ እድል አያገኝም፣ ተስፋው በሙሉ በሰው ስጦታ ላይ የተመሠረተ ነው። አንድ ቀን በትክክል ቆሜ እራመዳለሁ ብሎ አስቦ አያውቅም፣ የሚያስበው በቀን ምን ያህል ምጽዋት እንደሚያገኝና ኑሮውን እንደሚገፋ ብቻ ነው። በዚህ ሁኔታ ከ40 ዓመት በላይ አሳልፏል።

Wednesday, November 21, 2012

ወደ ፍ/ቤት ሽማግሌ ይላካል አይላክም በሚል «አባ» ሳሙኤልና ጠበቆቻቸው ሳይስማሙ ቀሩ

የአባ ሚካኤል አስከሬን ወጥቶ እንዲመረመር ፍርድ ቤት ከወሰነ ወዲህ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የገቡትና ነገሩን በሽማግሌ ለመጨረስ እየተንቀሳቀሱ ያሉት «አባ» ሳሙኤል ወደ ፍ/ቤት ይሄዱልኛል ያሏቸውን ሽማግሌዎች ያዘጋጁ ቢሆንም በጠበቆቻቸው በኩል ግን ሀሳቡ ተቀባይነት ሳያገኝና ሽማግሌም ሳይላክ መቅረቱ ተነግሯል፡፡ በጠበቆቹ በኩል የቀረበው ሐሳብ ተገቢነት ያለውና ህጋዊውን መንገድ የተከተለ  ሲሆን፣ «አባ» ሳሙኤልን «እርስዎ ጳጳስ ሆነው የሽምግልና ሕግን እንዴት አያውቁም? ሽምግልና እኮ እየተካሰሱ ባሉት ሁለት ወገኖች መካከል የሚከናወን የእርቅ ሂደት እንጂ ከፍርድ ቤት ጋር አይደለም፡፡ በፍ/ቤት ሕግ እንዲህ አይነት ሽምግልና ተሰምቶም ታይቶም አያውቅም» ብለዋቸዋል ተብሏል፡፡ አክለውም «ሽማግሌ መላክ ካለብንም መላክ የምንችለው የአባ ሚካኤል ልጅ ነኝ ወደሚለው ወደ ዮሐንስ ነው፡፡» ብለዋል፡፡

Monday, November 19, 2012

የግንቦት 15ቱ ውግዘት መነሻ፣ ሂደት፣ ፍጻሜና ቀጣዩ ሲገመገም

ክፍል 7
read in PDF

በልዩ ልዩ ወቅታዊ ጉዳየች ምክንያት ገታ አድርገነው የነበረውን የግንቦት 15ቱን «ውግዘት» የተመለከተ ዘገባችንን ካቆምንበት እንቀጥላለን፡፡ ከሳቴ ብርሃን በተሰኘው ማህበር ላይ የቀረበው ሌላው «ኑፋቄ» የሚከተለው ነው።


«5ኛ. ‘በአባቶቻችን አፈርን’ በተሰኘው መጽሐፋቸው፦
«ሀ. እንደ ፈጣሪ ያለ ክብርና ምስጋና የሚገባቸው ፍጡራንና የእጅ ስራዎች ያሏት ቤተክርስቲያን ባዕድ አምላኪ ወይም ባለብዙ አማልክት ካልተባለች ምን ልትባል ትችላለች» በማለት ቤተክርስቲያናችንን በመንቀፍ ጽፈዋል፡፡ 2003 ዓ.ም. እትም ገጽ 39»

አሁን ይህ ጠንከር ያለ አስተያየት እንጂ ኑፋቄ እንዴት ሊሆን ይችላል? ኑፋቄ እኮ በሃይማኖት ትምህርት ላይ ጥርጥር ሲፈጠር የሚሰጥ ስያሜ ነው፡፡ እንዲህ ያለው ጠንከር ያለ አስተያየት ግን ራስን ለመመልከትና ለማስተካከል የሚረዳ ጠቃሚ ምክር ተደርጎ ነው መወሰድ ያለበት፡፡ የኑፋቄ መመዘኛ ሚዛኑን የጣለ ወይም የጠፋበት የመሰለው የግንቦቱ ሲኖዶስ ውግዘት ያሳለፈባቸው አብዛኞቹ ነጥቦች ከኑፋቄ ቁጥር የሚገቡና የሚያስወግዙ አልነበሩም፡፡ አንዳንዶቹ እንዲያውም ቤተክርስቲያኗ ተቀብላ ራሷን ልታርምባቸው የሚገቡ ጠቃሚ አስተያየቶችና ምክሮች ናቸው፡፡

Saturday, November 17, 2012

ይድረስ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት - አባ ሠረቀብርሃን ወ/ሳሙኤል

 ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል በቅዱስ ሲኖዶስ የትምህርት ማሰልጠኛ መምሪያ ሃላፊ በቤተ ክርስቲያን አንድነት ዙሪያ ላይ ያተኮረ ደብዳቤ ለብፁዓን አባቶች ጽፈዋል።

አባ ሰረቀ የጻፉትን ደብዳቤ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

Thursday, November 15, 2012

ሰበር ዜና: የአባ ሚካኤል አስከሬን ተቆፍሮ እንዳይወጣ ለማድረግ «አባ» ሳሙኤል ወደፍርድ ቤት ሽማግሌ ሊልኩ መሆናቸው ተሰማ

ሰኞ ዕለት ባወጣነው ዘገባ እንደ ገለጽነው የልደታ ምድብ ችሎት ባለፈው አርብ[1] የአባ ሚካኤል አስከሬን ወጥቶ የዲኤንኤ ምርመራ እንዲካሄድበት ወስኗል፡፡ ይህን ውሳኔ ተከትሎ እውነት የምትገለጥበት ጊዜ መቅረቡ ያሳሰባቸውና የሚይዙ የሚጨብጡትን አጥተው የሰነበቱት «አባ» ሳሙኤል በዓለም ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም በማያውቅ አሰፋሪ ሁኔታ ሲኖዶስ ወስኖ በደብዳቤ የጠየቀውንና ከፍርድ ቤት በኩል ምላሽ ያጣበትን ጉዳይ በሽምግልና ለመጨረስ በማሰብ ዛሬ ኅዳር 6/2005 ዓ.ም ለፍርድ ቤት ሽማግሌ ለመላክ መወሰናቸውንና ለዚሁ ጉዳይ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ፡፡

Monday, November 12, 2012

የሟቹ ብፁእ አቡነ ሚካኤል አስከሬን ወጥቶ እንዲመረመር ፍርድ ቤት ትእዛዝ አስተላለፈ

ሲኖዶስ «የአባ ሚካኤል ጉዳይ የሓይማኖት ጉዳይ ነውና ፋይሉ ይዘጋ» ሲል ያቀረበው መቃወሚያ ውድቅ ተደርጓል
ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ዕለት የልደታ ምድብ ባስዋለው ችሎት የብፁዕ አቡነ ሚካኤል አስከሬን ተቆፍሮ ውጥቶ የዲኤንኤ ምርመራ እንዲካሄድና ውጤቱ ለህዳር 25/2005 እንዲቀርብ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ የሟቹ ብፁእ አቡነ ሚካኤል ልጅ የዮሀንስ ሚካኤል የወራሽነት ጉዳይ በፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቶ በስር ፍርድ ቤት ዮሐንስ ያቀረበው ማስረጃ የእነ «አባ» ሳሙኤል ቡድን ካቀረበው መከላከያ ይልቅ አሳማኝ ሆኖ በመገኘቱ ውሳኔ ያገኘና ልጅነቱ የተረጋገጠ መሆኑን ከዚህ ቀደም ዘግበን የነበረ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡ ጉዳዩ በይግባኝ ተይዞ ክርክሩ ቀጥሎ የነበረ ሲሆን የተለየ ማስረጃ ማቅረብ ያልቻለውና ጉዳዩን አፍኖ ማስቀረት የፈለገው የእነ «አባ» ሳሙኤል ቡድን ፋይሉን ለማዘጋትና ክሱን እንዲቋረጥ ለማድረግ ያልቆፈረው ድንጋይ አልነበረም ተብሏል፡፡ ለዚህም ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ህልፈት በኋላ አለሁ አለሁ ማለታቸውን በእጥፍ የጨመሩትና ሁሉንም ነገር እኔ ካላማሰልኩ የሚሉት «አባ» ሳሙኤል በግል ከመንቀሳቀስ አንስቶ የሲኖዶሱን አባላት አስተባብረው ጉዳዩ የሃይማኖት ነውና ፍ/ቤት ሊመለከተው አይገባም የሚል ደብዳቤ እስከማጻፍ የደረሰ ሴራ ሲጎነጉን ከርመዋል። በልደታ ምድብ ችሎት ጉዳዩን የተመለከተው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በ29/2/2005 ዓ.ም በዋለው ችሎት የአባ ሚካኤል አስከሬን ወጥቶ የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ እንዲደረግና ውጤቱ ለህዳር 25 እንዲቀርብ ውሳኔ ማስተላለፉ ታውቋል፡፡

Sunday, November 11, 2012

አቃቤ መንበር ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ሲኖዶሱን አልሰበስብም ብለው አሰናበቱ

ወደ ሀገረ ስብከታቸው መመለሳቸውም ታውቋል
አክሱሞች አጣሪውን ቡድን አልተቀበሉም አባ ሰላማም ይልቀቁልን ብለዋል

በአቃቤ መንበር ብፁእ አቡነ ናትናኤልና በG8 የጳጳሳት ቡድን መካከል የተፈጠረው ውዝግብ ተካሮ ትናንትና አርብ ብፁእ አቡነ ናትናኤል በአቋማቸው ጸንተው በቃኝ ከዚህ በኋላ አልሰበስባችሁም ብለው ከወጡ በኋላ ከሰዓት በኋላ ሳይመለሱ ቀርተዋል። ጳጳሳቱም ተሰብስበው ቢጠብቋቸው ሳይመጡ በመቅረታቸው ስብሰባውን ሳያካሂዱ ተበትነዋል። በቀጣይ የሚሆነው ባይታወቅም በአሁኑ ጊዜ ወደሀገረ ስብከታቸው መመለሳቸው ተዘግቧል። በአቃቤ መንበርነት ከተሾሙ ወዲህ ወደ ሀገረ ስብከታቸው ሲሄዱም የመጀመሪያቸው ነው ተብሏል።

Friday, November 9, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን “ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ” የተባለ የንግድ ተቋም መመሥረቱ ተሰማ

በቤተክርስቲያን ስም ሃይማኖትን ሽፋን አድርጎ ፖለቲካዊ አላማውን ለማሳካት ላለፉት 20 ዓመታት  ሲንቀሳቀስ የቆየው ማኅበረ ቅዱሳን አሁን ካለው በበለጠ ኢኮኖሚያዊ ክንዱን ለማፈርጠምና በገንዘብ ሀይል ያሻውን ለማድረግ በማሰብ በቤተክርስቲያን ጥላ ስር ሆኖ ልዩ ልዩ የንግድ ተቋሞችን ከፍቶ ቀረጥ ሳይከፍል ከሌሎች ቀረጥ ከፋይ ነጋዴዎች ጋር እየተወዳደረ የቆየ ሲሆን፣ የንግድ ሜዳውን ይበልጥ ለማስፋት «ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ» መመስረቱ ተገለጸ። ይህ የተገለጸው ማኅበሩ ለኅዳር 1/2005 በቸርችል ሆቴል ባዘጋጀው መርሀግብር ላይ አክስዮን የሚገዙ ሰዎች እንዲገኙለት በበተነው የግብዣ ደብዳቤ ላይ ነው።

Thursday, November 8, 2012

አቃቤ መንበር ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የቋሚ ሲኖዶስን አልመራም ብለው ከስበሰባ መውጣታቸው ተነገረ

Read in PDF
ሮብ እለት በ28/2/2005 በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ በተደረገው የቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ስብሰባውን በጸሎት እንዲያስጀምሩ ለቀረበላቸው ጥያቄ «የእኔን አቃቤ መንበርነት መች ተቀበላችሁና ነው በጸሎት የማስጀምረው? ህጉ የሚለው የሚሾምን ሰው ሥራ አስኪያጁ ያቀርባል ፓትርያርኩ ይሾማል ነው። አሁን ግን የምትሾሙ የምትሽሩ እናንተ ሆናችኋል። ታዲያ እኔ የእናንተ አሻንጉሊት ነኝ? ስልጣኔ ምን እንደሆነ በዛሬው እለት እንድታሳውቁኝ እፈልጋለሁ። እስከዚያው ግን ስብሰባውን አልመራም» ብለው ከስብሰባው መውጣታቸውን ምንጮቻችን ተናግረዋል። አባ ሳሙኤል «እኛ ላይ እኮ በድረገጽ እየተጻፈብንና ስማችን እየጠፋ ነው» በማለት ሊያግባቧቸው ቢሞክሩም ብፁእነታቸው ፈቃደኛ አልሆኑም። የቋሚ ሲኖዶስን ስልጣን በጎን ቀምቶ ፈላጭ ቆራጭ እኔ ነኝ የሚለው የእነ «አባ» ሳሙኤል ቡድን አላንቀሳቅስ ካላቸውና ስልጣናቸው የሚፈቅድላቸውን ስራ እንዳይሰሩ ካደረጋቸው ወዲህ በአቃቤ መንበሩና በዚህ ቡድን መካከል ውጥረቱ እያየለ መጥቷል። የዛሬውም አቃቤ መንበሩ ከስብሰባው መውጣት ውጥረቱ የደረሰበትን ከፍተኛ ደረጃ የሚያሳይ ነው ይላሉ ታዛቢዎች።

Monday, November 5, 2012

ዐቃቤ መንበር ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን የG8 አባላት የሆኑት ሦስቱ የጉድ ሙዳዮች አላሠራ ስላሏቸው የሕግ ያለህ እያሉ መሆናቸው ተሰማ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የሾሟቸው ነገር ግን ተመልሰው ጠላት የሆኗቸውና ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በማበር ልዩ ልዩ ሤራዎችን በመጠንሰስና በማሳደም እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ድረስ ሲያሳዝኗቸው የኖሩት የጉድ ሙዳዮች አባ ሳሙኤል፣ አባ አብርሃም እንዲሁም አባ ሉቃስ፣ ከዐቃቤ መንበር ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ጋር መጋጨታቸው ተሰማ። የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ዜና ዕረፍት ተከትሎ “እንዳሻን እናደርጋቸዋለን” በሚል የመረጧቸውንና ከሾሟቸው በኋላ» ግን ቋሚ ሲኖዶስ እያለ ዐቃቤ መንበሩን እንረዳለን በሚል ተመሳጥረው የተሰየሙትና 8 አባላት የሚገኙበትና «G8» እየተባሉ የሚጠሩት የጳጳሳት ቡድን፣ እንደፈለጉት ያልሆኑላቸውን አቡነ ናትናኤልን አላሰራ ብለው ሲያስቸግሯቸው እንደቆዩ የገለጹት ምንጮቻችን አሁን ነገሩ ጦዞ ወደአልተፈለገ አቅጣጫ እንዳያመራ ተሰግቷል ይላሉ።

Sunday, November 4, 2012

የቤተ ክርስቲያን አንድነት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል

በአገር ቤትም በአሜሪካም በስደት ያሉት ሲኖዶሶች ስብሰባቸውን አድርገው የአቋም መግለጫዎችን አውጥተዋል። ከቤተክርስቲያን አንድነት ጋር ተያይዞ የወጡት መግለጫዎች ሲፈተሹ ግን ቀሪው የቤት ስራ የቤተ ክርስቲያንንን አንድነት ለማምጣት ቀላል እንዳልሆነ መገመት አያስቸግርም። የአዲስ አበባው ሲኖዶስ በአንድ በኩል የዕርቅና የሰላም ሂደቱ እንዲቀጥል ፈቃዱ መሆኑን ቢገልጽም የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ወደ መንበራቸው መመለስን አልተቀበለም። ለስድስተኛ ፓትርያርክ ምርጫም በዝግጅት ላይ ነው።

ለዚህ እየቀረበ ያለው አንዱና  ዋናው ምክንያት አቡነ ጳውሎስን 5ኛ ፓትርያርክ ብለን እንደገና ወደ 4ኛ ፓትርያርክ አንመለስም የሚል ነው። ይሁን እንጂ ፓትርያርክ ሳይሆኑ ወደ አገር ቤት ገብተው በፈለጉት ስፍራ ተከብረው መቀመጥ እንደሚችሉ ሲኖዶሱ ወስኗል። ከዚህ ቀደም ለዕርቁ ሂደት ትልቁ እንቅፋት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ናቸው እያሉ ሲናገሩ የነበሩ አንዳንድ ጳጳሳት ከእርሳቸው ህልፈት በኋላ በያዙት አቋም እንቅፋት እየሆኑ ያሉት እነርሱም መሆናቸውን እያንጸባረቁ ነው።

Saturday, November 3, 2012

በ4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሚመራው ሲኖዶስ 34ኛ ጉባኤ ተጠናቀቀ

 በስደት የሚገኘውና በ4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሚመራው 34ኛው የሲኖዶስ ጉባኤ በሰሜን አሜሪካ ኮሎምበስ ኦሃዮ ተጠናቀቀ።  በጉባኤውም ማጠናቀቂያ ላይ ቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫ ያወጣ ሲሆን መግለጫው የሲኖዶሱ ጉባኤ ያተኮረባቸውን አበይት የውይይት ነጥቦች ያንጸባርቃል።

ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ቀልብ ያልሳበው የአዲስ አበባው የጥቅምት ሲኖዶስ ስበሰባ ተጠናቀቀ

እንደ ወትሮው የመገናኛ ብዙሃንን ቀልብ ያልሳበውና በአብዛኛው ሲኖዶስ ለተባለው የቤተክርስቲያን የበላይ አካል በማይመጥኑና ተራ አጀንዳዎች ሲወያይ የሰነበተው የአገር ቤቱ ሲኖዶስ ስበሰባ ባለፈው ሳምንት ጥቅምት 21/2005 ዓ/ም ተጠናቋል። በማኅበረ ቅዱሳን እዝ ስር በመሆን ቅዱስ ፓትርያርኩን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ለመጣል አንድ ሆነው የነበሩት ጳጳሳት ከቅዱስነታቸው ዕረፍት በኋላ ያለ መሪ ፓትርያርክ በዐቃቤ መንበር አንድነታቸውን ጠብቀው መቀጠል እንዳልቻሉ በታየበት በዚህ ስብሰባ ላይ ፓትርያርክ ጳውሎስ የሲኖዶስ ስበሰባ ለሚያገኘው ትኩረት ዋና እንደነበሩ መታዘብ ተችሏል። ሲኖዶሱ በዋናና ለቤተክርስቲያን መንፈሳዊ እድገትና ጥንካሬ የሚረዱ፣ ቤተክርስቲያንም በአገራችን ተገቢ ሚናዋን እንድትጫወት የሚያደርጉ አጀንዳዎችን ከመቅረጽና ከመወያየት፣ ጠቃሚ ውሳኔዎችንም ከማሳለፍ ይልቅ በአብዛኛው ተራ በሆኑና ሲኖዶስ ላይ ሳይደርሱ መፈታት ባለባቸው ጥቃቅን አጀንዳዎች ላይ ሲወያይ አብዛኛውን ጊዜውን ማቃጠሉ፣ የሲኖዶሱ አባላት የሚገኙበትን ደረጃ ያሳየ ክስተት ሆኖ አልፏል።

Friday, November 2, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን ውስጡ እየተቃወሰ መሆኑን የሚያሳዩ ምልከቶች እየታዩ ነው

ቤተ ክርስቲያንን ለመቆጣጠርና በራሱ መንገድ ለመምራት እየተንቀሳቀሰ ያለው ማኅበረ ቅዱሳን ውስጡ በልዩ ልዩ ችግሮች እየታመሰ መሆኑን ምንጮቻችን እየተናገሩ ነው። የማኅበሩ ሁነኛ የሚባሉ አገልጋዮችም በልዩ ልዩ ችግሮች መጠላለፋቸው እየተሰማና እየታየም ነው። ከእነዚህም መካከል፦ ደሴ ቀለብ፣  ኅሩይ ስሜ፣ ኅሩይ ባየ፣ አባይነህ ካሴ፣ ያሉበት ሁኔታ ለዚህ ትልቅ ማሳያ ነው ይላሉ።

እንደምንጮቻችን ከሆነ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፊሎሎጂ ትምህርት ክፍል መምህር፣ የማቅ የግእዝ አስተማሪና የሐመር መጽሔት ቋሚ አምደኛ የሆነው ደሴ ቀለብ በአሁኑ ሰዓት የአእምሮ ሕመምተኛ ሆኖ፣ ሥራውን ሳይሠራ ደሞዝ እየተከፈለው እንደሚገኝ ምንጮቻችን ጠቅሰው፣ የዲፓርትመንቱ ኃላፊ የሆነው ዶ/ር አምሳሉ ተፈራ ስለ ግለሰቡ ችግር በተዳጋጋሚ ለማቅ ያሳወቀ ሲሆን፣ ደሴ ሳይሰራ ደሞዝ መከፈሉ ከታወቀ በእርሱ ላይ ችግር እንደሚያስከትልበት እየተናገረ ነው። ደሴ ቀለብ በአሁኑ ወቅት ከስድስት ኪሎ በላይ እንደማይወጣና ከ4 ኪሎ በታች  እንደማይወርድ የታወቀ ሲሆን፣ በማኅበሩ ህንጻ አካባቢ ሲዞር ይውላል ነው የተባለው። ምናልባትም ማኅበሩ በሚታማበት የድግምት አሰራሩ አንዳች ነገር አዙሮበት ይሆናል የሚል ግምት አሳድሯል። ይህን ሰው እግዚአብሔር እንዲፈውሰው ምኞታችን ነው።

Thursday, November 1, 2012