Monday, November 19, 2012

የግንቦት 15ቱ ውግዘት መነሻ፣ ሂደት፣ ፍጻሜና ቀጣዩ ሲገመገም

ክፍል 7
read in PDF

በልዩ ልዩ ወቅታዊ ጉዳየች ምክንያት ገታ አድርገነው የነበረውን የግንቦት 15ቱን «ውግዘት» የተመለከተ ዘገባችንን ካቆምንበት እንቀጥላለን፡፡ ከሳቴ ብርሃን በተሰኘው ማህበር ላይ የቀረበው ሌላው «ኑፋቄ» የሚከተለው ነው።


«5ኛ. ‘በአባቶቻችን አፈርን’ በተሰኘው መጽሐፋቸው፦
«ሀ. እንደ ፈጣሪ ያለ ክብርና ምስጋና የሚገባቸው ፍጡራንና የእጅ ስራዎች ያሏት ቤተክርስቲያን ባዕድ አምላኪ ወይም ባለብዙ አማልክት ካልተባለች ምን ልትባል ትችላለች» በማለት ቤተክርስቲያናችንን በመንቀፍ ጽፈዋል፡፡ 2003 ዓ.ም. እትም ገጽ 39»

አሁን ይህ ጠንከር ያለ አስተያየት እንጂ ኑፋቄ እንዴት ሊሆን ይችላል? ኑፋቄ እኮ በሃይማኖት ትምህርት ላይ ጥርጥር ሲፈጠር የሚሰጥ ስያሜ ነው፡፡ እንዲህ ያለው ጠንከር ያለ አስተያየት ግን ራስን ለመመልከትና ለማስተካከል የሚረዳ ጠቃሚ ምክር ተደርጎ ነው መወሰድ ያለበት፡፡ የኑፋቄ መመዘኛ ሚዛኑን የጣለ ወይም የጠፋበት የመሰለው የግንቦቱ ሲኖዶስ ውግዘት ያሳለፈባቸው አብዛኞቹ ነጥቦች ከኑፋቄ ቁጥር የሚገቡና የሚያስወግዙ አልነበሩም፡፡ አንዳንዶቹ እንዲያውም ቤተክርስቲያኗ ተቀብላ ራሷን ልታርምባቸው የሚገቡ ጠቃሚ አስተያየቶችና ምክሮች ናቸው፡፡

የዚህ አስተያየት አቀራረብ ጠንከር ያለ በመሆኑ አስተያየት ተቀባዩን ከሩቁ የሚገፈትር ሊሆን ይችላል፡፡ የአስተያየቱ ደካማ ጎን ይህ ካልሆነ በቀር ግን ቤተክርስቲያኗ ይህን ለማስተባበል የምትችልበት አቅም የላትም፡፡ ቤተክርስቲያኗ እንደተባለው ልክ እንደፈጣሪ የሚመለኩ ፍጡራንና የእጅ ሥራዎች (የእደጥበብ) ውጤቶች ያሏት መሆኑን ማንም ሊያስተባብል አይችልም፡፡ ማርያምና መስቀል የፈጣሪ ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል ተብለው በመስተብቁእ ዘመስቀል ይወደሱ የለም ወይ? በሌሎችም ገድላገድሎችና መልካመልኮች ውስጥ ለተለያዩ ፍጡራን ተመሳሳይ ነገር ተብሎላቸው የለም ወይ? ይህን አሌ ማለት አይቻልም፡፡ አንዳንዶች ግን የአክብሮት እንጂ የአምልኮት አይደለም በማለት ለባእድ አምልኮቱ ሌላ መልክ ለመስጠት ይፍጨረጨራሉ እውነታውን ግን መለወጥ አይቻልም፡፡ ሊቃውንቱ ነገሩን በዚህ መልክ ከፋፍለው በማቅረብ ስህተት እንዳልተፈጠረ ለማግባባት ቢሞክሩም በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ ያለው ግንዛቤና በተግባር የሚታየው ቤተክርስቲያኗ ባለብዙ አማልክት ናት የሚያሰኝ ነው፡፡ ኧረ እውነቱን እንነጋገር ካልን በቤተክርስቲያኗ እየተመለከ ያለው እግዚአብሔር ብቻ ነው? ቤተክርስቲያኗ የምትታወቀውስ በእግዚአብሔር ነው ወይስ በማርያም እና በሌሎች ፍጡራን? ይህን ለመመለስ መጽሐፍ መጥቀስ አያስፈልግም በሕዝቡ ህይወት የሚንጸባረቀውን ብቻ ማየቱ በቂ ነው፡፡ ቤተክርስቲያኗ እንዲህ ናት ቢባልም በውስጧ ያሉ ከዚህ ባእድ አምልኮ የራቁ ሊቃውንትና ምእመናን የሏትም ማለት ግን አይደለም፡፡ ስለዚህ ሲኖዶሱ ይህን ጠንከር ያለ ትችት መልኩን ቀይሮ ኑፋቄ ከሚለው ቤተክርስቲያኗ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለች ቢመዝንበትና ሁሉን በእግዚአብሔር ቃል መሰረት እያረመ ቢያስተካከል ቤተክርስቲያን ትታደሳለች፡፡

ቤተክርስቲያን ጌታ ካሰመረላት መስመር ወጥታ በራሷ ምህዋር ላይ መጓዝ ስትጀምር በተግሳጽ ቤተክርስቲያንን መናገሩ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ይህ ለቤተክርስቲያን መስተካከል ጠቃሚ ነውና ቤተክርስቲያን ምላሿ «ለምን እነቀፋለሁ?» መሆን የለበትም፡፡ እንዲያውም ተግሳጹን ተቀብላ ራሷን መመርመር ነው ያለባት፡፡ በዮሐንስ ራእይ ውስጥ በሚገኙበት ተጨባጭ ሁኔታ ምክንያት ከዚህም የበለጠ የተነቀፉ አብያተ ክርስቲያናት ነበሩ፡፡ «የምንቀፍብህ ነገር አለ» እያለ የነቀፋቸው ደግሞ ራሱ ጌታችን ነው፡፡ የነቀፋቸውም ንስሃ እንዲገቡና እንዲስተካከሉ ነው፡፡ ከእነዚያ አብያተ ክርስቲያናት ብዙዎቹ ዛሬ የሉም። ምናልባትም ተግሳጹን ስላልተቀበሉና እኔ ፍጹም ነኝ በሚለው አቋማቸው ስለጸኑ እንደጠፉ እንገምታለን፡፡ ዛሬም ቤተክርስቲያን የአክብሮትና የአምልኮት በሚል ቅይጥ አምልኮን ከመፈጸም መውጣትና ብቻውን አምላክ የሆነውን እርሱን ብቻ ማምለክ ይጠበቅባታል፡፡

«በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል። በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር። እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው። ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥ ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ተጐናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፥ እንድታይም ዓይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ። እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና ንስሐም ግባ። እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።»   (ራእ. 3፡14-20)

«ለ. እግዚአብሔር እስካሁን ባለው አሰራሩ የማንንም ጸሎት በሞቱ ቅዱሳን በኩል ተቀብሎ አያውቅም» ሲሉ የእርሱን ተማላጅነትና የቅዱሳንን አማላጅነት ይቃወማሉ፡፡ 2003 ዓ.ም. እትም ገጽ 66»
በዚህ ነጥብ ላይ መጽሐፉ ያነሣው ሐሳብ እግዚአብሔር እስካሁን ባለው አሰራር መሰረት በሞቱ ቅዱሳን በኩል የማንንም ጸሎት ተቀብሎ አያውቅም የሚል ነው፡፡ ይህ ግን የእግዚአብሔርን ተማላጅነት የቅዱሳንን አማላጅነት መቃወም አይደለም፡፡ መጽሐፉ እግዚአብሔር በሞቱ ቅዱሳን በኩል ጸልዩ አላለም የሚል ሐሣብ ነው ያለው እንጂ እግዚአብሔር ተማላጅ አይደለም፤ ቅዱሳን በደፈናው አይማልዱም ማለቱም አይደለም። ሲኖዶሱ ይህን ኑፋቄ ያለው ምናልባት ከመጽሐፉ አገኘኋቸው ያላቸው ኑፋቄዎች 3 ስለሆኑ እንዳያንስ አስቦ ሊሆን ይችላል፡፡

እግዚአብሔር ደስ ከሚያሰኙት ነገሮች መካከል አንዱ በሕይወተ ሥጋ ያሉ ቅዱሳን (በክርስቶስ ደም የተዋጁና በእምነት ጸድቀው በበጎ ምግባር የክርስቶስ ተከታዮች መሆናቸውን የሚያስመክሩ ሁሉ) ስለሌሎች ምልጃ ማቅረባቸው መሆኑ ተጽፏል፤ «እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው። አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፥ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፤» (1ጢሞ. 2፡1-6)። መቼም ይህ ስላንቀላፉ ቅዱሳን እንዳልተጻፈ ግልጽ ነው፡፡ መልእክቱ በሕይወት ለነበረው ለጢሞቴዎስና በእርሱ በኩል ይህን መልእክት ማንበብ ለሚችሉ በሕይወተ ስጋ ላሉ ቅዱሳን የተላከ ነውና፡፡

ይሁን እንጂ ምልጃውን ማቅረብ የተቻለው በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ባለው አንድ መካከለኛ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መሆኑም ሊሰመርበት ይገባል፡፡ አንዱ ስለሌላው በክርስቶስ ስምና በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር እንዲጸልይ ታዟል «በዚያን ቀንም ከእኔ አንዳች አትለምኑም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል። እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ።» (ዮሐ. 16፡23-24)። ከዚህ በቀር በአንቀላፉ ቅዱሳን በኩል ጸልዩ ተብሎ አልታዘዘም፡፡ ያንቀላፉ ቅዱሳን ሕያዋን ቢሆኑም እኛና እነርሱ በመንፈስ ካልሆነ በቀር ቀጥተኛ ግንኙነት ስለሌለን እኛ ከእነርሱ ጋር መነጋገርም ሆነ ጸልዩልን ማለት አንችልም፡፡ ለነገሩ በአጸደ ስጋ ካሉትስ ጋር ቢሆን በአካል ተቀራርበን ካልተያየን በቀር በመንፈስ እንጂ በስጋ እኮ ተለያይተናል፡፡

በአጸደ ነፍስ ወደመኖር ከተሸጋገሩ በኋላ በዚህ ምድር ላይ ስለሚያውቁት ነገር መለመን ቢችሉና ዕድሉ ቢሰጣቸው እንኳን የሚለወጥ ነገር አለመኖሩን ጌታ በምሳሌ ካስተማረው ከአብርሃም ከባለጠጋውና ከደሃው አልዓዛር ታሪክ መማር እንችላለን፡፡ ባለጠጋው እኮ አብርሃምን ለምኖታል። የለመነው አንድም ስለራሱ - በጣቱ ውሃ ነክሮ ምላሱን እንዲያበርድለት አልዓዛርን እንዲልክለት፤ አንድም አልዓዛርን በምድር ወዳሉት ዘመዶቹ እንዲልከውና ለዘመዶቹ እንዲመሰክርላቸው እንዲያደርግ ነበር፡፡ ሁለቱም ልመናዎች ግን በአብርሃም ዘንድ ተቀባይነት አላገኙም፡፡ (ሉቃ. 16፡19-31)፡፡ በምድር ስላሉትም ሙሴና ነቢያት አሉላቸው እነርሱን ይስሙ አለ እንጂ በአጸደ ነፍስ ብሆንም ማማለድ እችላለሁና ለእነርሱ አታስብ እኔ እጸልይላቸዋለሁ አላለም፡፡

የአሁኖቹ «ሊቃውንት» ሽረውት ካልሆነም የቤተ ክርስቲያኗ ትምህርት የነበረው ቅዱሳን በምድር ላይ ሳሉ ያቀረቡት ምልጃ ነው የሚሠራው እንጂ ካንቀላፉ በኋላ ምልጃ ማቅረብ የለባቸውም የሚል ነው፡፡ የውዳሴ  ማርያም ትርጓሜ ይህንኑ ያሳረዳል፡፡ ሊቃውንት ሰአሊ ለነ ቅድስት ለሚለው ንባብ የሰጡት ትርጓሜ «ዐይኑ ዐ ቢሆን አእምሮውን ለብዎውን ሳዪብን፤ አሳድሪብን፤ አልፋው አ ቢሆን ለምኚልን ማለት ነው፡፡ ልመናስ እንኳን በሷና በሌሎችም የለባቸውም በቀደመ ልመናዋ የምታስምር ስለሆነ እንዲህ አለ እንጂ» በማለት ነው፡፡ ታዲያ በአጸደ ስጋ ምልጃ የለም ማለት ትክክለኛ ትምህርት እንጂ እንዴት ኑፋቄ ሊሆን ይችላል?

«ተክለ ሃይማኖት የወንጌል መልእክተኛ ሳይሆኑ ባልታዘዘው መንገድ ወንጌል በጡንቻ አስፋፍተዋል» በማለት ጻድቁን ዘልፈዋል፡፡ 2003 ዓ.ም. እትም ገጽ 101»
አቡነ ተክለ ሃይማኖት አወዛጋቢ ሰው ናቸው፡፡ እንደነኪዳነ ወልድ ክፍሌ ያሉ ተጠያቂ ሊቃውንት ጻድቁ የሚሏቸው ተክለሃይማኖት በ7ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩ በቅድስናቸው በትምህርታቸው የተመሰከረላቸው መሆናቸውን ሲተርኩ አሁን ተክለሃይማኖት የሚለውን ስምና የተጋድሎ ታሪካቸውን  የወረሱት የደብረ ሊባኖሱ ተክለሃይማኖት የተለየ ታሪክ ያላቸው ሰው መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡ ለዕጨጌዎች ቀዳሚያቸው የሆኑት የደብረ ሊባኖሱ ተክለሃይማኖት የሚታወቁበት አንዱ ነገር በ13ኛው መቶ ክፍለዘመን የእናታቸው የእህት ልጅ የሆነውን ይኩኖ አምላክን ያነገሱ መሆናቸው ነው፡፡ አገራቸውም ከብሔረ ሳይንት ነው ይላሉ፡፡ ስለ እርሳቸው የሚናገር መጽሐፈ ገድል እንዳለም ጠቅሰው ገድሉ ያገቡ ህጋዊና ባለጠጋ ካህን እንጂ ድንግል መነኮስ አለመሆናቸው ይናገራል ብለዋል፡፡ በአንዳንድ ደብርና ገዳም በተለይም በወይንጌ ዘብሔረ ወግዳ እንዲሁም በግራርያ ዘበጌምድር በሚገኘው መጽሐፈ ገድል እንዲህ የሚል ጽሑፍ አለ «ሰው እንዳያየውና እንዳያነበው እንደጎንደሮችም ‘አቦ ብልኀት ዕጨግነት ከሚስት’ ብሎ እንዳያላግጥ እስከ ዛሬ ተሰፍቶ ተጣብቆ ተደርቶ ታትሞና ተዘግቶ ተቀምጧል፡፡» እኒህ ተክለ ሃይማኖት ለ12 ዓመት ያህል አብዛኛውን ሥጋዊትና ዘማዊት መንግስትን ከነገደ ዛጔ ወደ ነገዳቸውና ወደ ዘመዳቸው በማፍለስ እንዳሳለፉ ይተርካሉ፡፡ የቀረውን ከሃይማኖተ አበው ቀደምት ወፍልጠተ ውሉድ ደኃርት ማንበብ ነው፡፡

ኑፋቄ ተብሎ የተጠቀሰው ሐሳብ አነጋገሩ እንደሚያስቆጣ አያጠራጥርም፡፡ ሆኖም የተክለሃይማኖት ጉዳይ የሃይማኖት ጉዳይ አይደለምና ኑፋቄ ተብሎ ሊያስወግዝ አይገባውም ነበር፡፡ ተክለሃይማኖት የወንጌል ሰባኪ ናቸው ወይስ ፖለቲከኛ የሚለውን ለማጣራት ቤተክርስቲያን በሯን ልትከፍት ይገባል እንጂ ተክልዬ ተዘለፉ ብሎ ማውገዝ ወፈገዝት መሆን ነው፡፡

31 comments:

 1. I believe in the One Holy Catholic Apostolic ChurchNovember 20, 2012 at 12:04 AM


  እውነተኛ ክርስትና የእሑድ ብቻ ሃይማኖት አይደለም- የምንተነፍሰው አየር፣ የልባችን ምት፣ በሥሮቻችን ውስጥ ያለ ደም፣ የህልውናችንም መሠረት ነው እንጂ፡፡ ይኹን እንጂ እውነተኛ ክርስትና፣ እውነተኛ ደቀ መዝሙርነት፣ ክርስቶስን በእውነት መከተል ዋጋ ያስከፍላል፡፡ በ2000 ዓመታት ታሪኳ ቤተክርስቲያን ክርስቶስን የተከተለችባቸው ጊዜያት ነበሩ፡፡ ክርስቶስን የመከተል ቋንቋ እየተናገረች እውነታው ሲታይ ግን የዓለም ተከታይ ኾና የተገኘችባቸው በርካታ ጊዜያትም አሉ፡፡ አንድ ሰው ቤተክርስቲያን ውስጥ ኾኖ ቤተክርስቲያኗን ከጥፋት መንገዷ እንድትመለስ ቢጮኽ ያ ሰው የቤተክርስቲያን ጠላት ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ ቤተክርስቲያኒቱ እጅግ የሚያስፈልጋት ሰው ግን እርሱ ነበር፡፡ ታሪክ እንደሚያስረዳው ቤተክርስቲያን የዓለምን ዕውቅና የፈለገችባቸው ጊዜያት ነበሩ፡፡ ዕውቅናውን ባገኘች ጊዜ ግን ወንጌልን አሳልፋ ሰጥታ፤ በዚህም ተስፋዋን ጥላ ነበር፡፡

  ቤተክርስቲያን ወንጌልን ስትተው ማዕከሏና የወደፊት ህልውናዋ የኾነውን መልእክቷን ታጣለች፡፡ ቤተክርስቲያን በወንጌል ላይ እምነት ስታጣ ለባህል መልእክት ባርያ ትኾናለች፡፡ እነዚህ ችግሮችም ቀስ በቀስ የቤተክርስቲያኗን የወደፊት ህልውና መሠረት ይገድሉታል፡፡ እግዚአብሔር ግን በአንድ ቅርንጫፍ ብቻ የሚኖር አይደለም፡፡ ወንጌል እያስገመገመ እንደሚኼድ ግሩም ወንዝ ነው፡፡ ሊበራሊዝም አያግደውም፤ ጭቆና አያፍነውም፤ ቢሮክራሲ አያንቀውም፤ የአገልጋዮች ስንፍናም አይገድለውም፡፡ አንድ ቤተክርስቲያን እውነተኛውን ወንጌል መመልከትና እርሱንም ከመስበክ ፈቀቅ ስትል እግዚአብሔር ሌላ ቤተክርስቲያን፣ ሌላ ትውልድ፣ ሌላ ሕዝብ ያስነሣል፡፡ አንድ ታሪካዊ ቅርንጫፍ በባህል ሲዋጥ እግዚአብሔር ሌላውን ቅርንጫፍ ስለ እውነት ያስነሣል፡፡

  I found it from one sermon and translated it in to Amharic for I thought it to be relevant.

  ReplyDelete
 2. የተዋሀዶ ልጆች መሠረታችንን ለማፅናት ቤተክርስቲያናችንን፣ ሥርዓታችንን፣ ማንነታችንን ለማወቅ በእምነታችን ፀንተን ለመኖር....... www.eotcmk.org and http://multimedia.eotc-mkdusan.org/ በመስመር ላይ ናቸው እንዲሁም ሐመር--- ስምዐ ጽድቅ---- እንጐብኝ... እናንብብ... መሠረታችንን እናፅና፡፡

  መሠረታችንን ካፀናን ደግሞ ተመሳስሎ የሚመጣ የቤተክርስቲያን ጠላት የበግ ለምድ የለበሰው መናፍቅ... መርዙን ማር ማር እስኪል ድረስ አቀላቅሎ ቢመጣ እንኳን መሠረታችን የፀና ነውና ድካሙ ከንቱ ይሆናል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. እነዚህ የጠቀስካቸው ብሎጎች እኮ ተረታተረት እና ወጋወግ ብቻ ሆኑ መቼ ክርስቶስን አሳዩን? ቸል ያልናቸው ለዚያ ነው፡፡ ስለዚህ አንድ ጊዜ ስለበራልን ወደጨለማ መመለስ አይሆንልንም፡፡ ይልቅ የያዝከውን ዝክንትል ሁሉ እንዲህ ባለው አንጀት አርስ ጽሁፍ መርምርና ራስህን አስተካከል መዳን የሚገኘው በክርስቶስ እንጂ በኦርቶዶክስ አይደለም፡፡

   Delete
 3. menfknachen tetache yehne anbebuበስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

  ይህ ምዕራፍ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእርሱን ማንነት ገልጦ ያስተማረበት ምዕራፍ ነው። በዚህም ትምህርቱ እርሱ የበጎች እረኛ እንደሆነ የበረቱም በር እርሱ መሆኑን ተናግሯል። እውነት የባህርይ ገንዘቡ ስለሆነም ትምህርቱን “እውነት እውነት እላችኋለሁ” በማለት ጀምሯል። በዚህም አማናዊ በሆነ ትምህርቱ “ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ፥ በሌላም በኲል የሚገባ ሌባ፣ ወንበዴም ነው” ብሏል። ሊቃውንት እንደሚነግሩን ይኽን ስለ ሦስት ምክንያት ተናግሮታል።

  ፩ኛ፦ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምዕራፍ ዘጠኝ እንደተመለከትን ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ዕውር ሆኖ የተወለደውን ብላቴና በምራቁ ጭቃ አድርጐ በሰሊሆም ጠበልም እንዲጠመቅ በማድረግ ፈጽሞ ስለፈወሰው አይሁድ ብላቴናውንም ወላጆቹንም አስቸግረዋቸው ነበር። ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ፦ “ይህ ሰው (ኢየሱስ) ከእግዚአብሔር አይደለም፥ ሰንበትንም አይከብርምና” እያሉ ብላቴናውን ተከራክረውታል። ብላቴናው ግን፦ “ኃጢአተኛ ሰው እንዲህ ያለ ተአምራት ማድረግ (በደረቅ ግንባር ላይ ዓይን መፍጠር) እንዴት ይችላል? . . . እርሱ ነቢይ ነው” አላቸው። ይኸውም፦ የነቢያት አለቃ ሙሴ፥ ከእግዚአብሔር አግኝቶ፥ “እግዚአብሔር ከወንድሞቻችሁ መካከል (ከእናንተ ወገን) እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋልና እርሱን ስሙት” በማለት ለእስራኤል ዘሥጋ የነገራቸው ቃለ ትንቢት ነው /የሐዋ.7፡37/። ምክንያቱም በብዙ መንገድ ሙሴ ለኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነውና። የነቢያት አምላካቸው ኢየሱስ ክርስቶስ “ነቢይ” መባሉም ነቢያት በአንድም ሆነ በሌላ ምሳሌዎቹ በመሆናቸው ነው።

  ደጋግመው በጠየቁት ጊዜም “አትሰሙኝም እንጂ ነገርኋችሁ፥ እንግዲህ ምን ልትሰሙ ትሻላችሁ? እናንተም ደቀመዛሙርቱ ልትሆኑ ትሻላችሁን?” ብሎ ሳይፈራ ተከራከራቸው። በዚህን ጊዜ “ራስህ በኃጢአት የተወለድህ አንተ እኛን ታስተምራለህን?” ብለው ከምኲራብ አወጥተውታል። በዚህም ንግግራቸው በጌታ ቃል፡- “የእግዚአብሔር ሥራ ሊገለጥበት ነው እንጂ እርሱ አልበደለም፥ ወላጆቹም አልበደሉም” የተባለውን ሰው በልበ ደንዳናነት ኰነኑት። ከቤተ መቅደስም አስወጡት /ዮሐ.9፡3/። ጌታችንም አግኝቶት “አንተ በእግዚአብሔር ልጅ ታምናለህን?” አለው። ብላቴናውም፦ “አቤቱ፥ አምንበት ዘንድ እርሱ ማነው?” ብሎ መለሰለት። ጌታችን ኢየሱስም “የምታየው፥ ከአንተ ጋርም የሚነጋገረው እርሱ ነው” አለው። ይኸውም “ነቢይ ነው” እንዳለ በምሳሌው እንዳይቀር “አምላክ ወልደ አምላክ” ብሎ እንዲያምን ነው። እርሱም “አቤቱ ፥ አምናለሁ” ብሎ ሰገደለት። ከዚህ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፦ “እኔ የማያዩት እንዲያዩ (አላዋቆች ነን የሚሉ ሐዋርያት አዋቆች ይሆኑ ዘንድ) የሚያዩትም እንዲታወሩ (አዋቆች ነን የሚሉ ፈሪሳውያን አላዋቆች ይሆኑ ዘንድ) ለፍርድ መጥቻለሁ። (ላመነብኝ ልፈርድለት ላላመነብኝ ልፈርድበት፥ ለሰው መፈራረጃ ለመሆን ከሰማይ ወርጃለሁ)” አለው። በዚህን ጊዜ ይኽንን የሰሙ ፈሪሳውያን፦ “እኛ ደግሞ ዕውሮች ነን?” አሉት። ጌታችን ኢየሱስም “ዕውሮችስ ብትሆኑ ኃጢአት ባልሆነባችሁ ነበር፤ (ነውረ ሥጋ ከመንግሥተ ሰማይ አያወጣምና)፤ አሁን ግን እናያለን (እናውቃለን) ትላላችሁ፥ አታዩምም፤ (አታውቁምም)፤ ስለዚህም ኃጢአታችሁ ጸንቶ ይኖራል፤ (ንስሐ ስለማትገቡ ኃጢአታችሁ አይሰረይላችሁም)” አላቸው /ዮሐ.9፡41/። እንግዲህ በዚህ ምክንያት ማለትም “ለሰው መፈራረጃ እሆን ዘንድ መጥቻለሁ” ብሎ በመናገሩ ለምሕረትም እንደመጣ ለማጠየቅ ይህን ምዕራፍ (አንቀጸ አባግዕን) አስተምሯል።

  ፪ኛ፦ ይህ ዕውር ሆኖ ተወልዶ ጌታ የፈወሰው ብላቴና ፈሪሳውያን እንዴት እንዳየ ደጋግመው በጠየቁት ጊዜ አርሱም ደጋግሞ እውነቱን ነግሯቸዋል። በተጨማሪም፦ “እናንተም ደቀ መዛሙርቱ ልትሆኑ ትሻላችሁን?” ብሎም ጠይቋቸዋል። እነርሱ ግን “አንተ የእርሱ ደቀመዝሙር ሁን፥ እኛስ የሙሴ ደቀመዛሙርት ነን። እግዚአብሔር ሙሴን እንደተነጋገረው እናውቃለን፥ ይህን ግን ከወዴት እንደሆነ አናውቅም” ብለውታል። በዚህን ጊዜ «. . . ከወዴት እንደሆነ፥ አታውቁምና እጅግ ድንቅ ነው፤ ነገር ግን ዓይኖቼን አበራልኝ። ይህ ሰው ከእግዚአብሔር ባይሆን ኖሮ ምንም ማድረግ ባልቻለም ነበር” ብሎአቸዋል። ስለዚህ “ከወዴት እንደሆነ አናውቅም” ብለውት ስለነበረ ከወዴት እንደሆነ ለማጠየቅ አንቀጸ አባግዕን ያስተምራቸዋል።

  ፫ኛ፦ “ቸር እረኛ አይደለህም፤ ይልቁንም ሕዝቡን ታስታለህ” ብለውት ስለ ነበር አሳች እንዳልሆነ ይልቁንም ቸር እረኛ መሆኑን ለማጠየቅ ነው። ይኽንንም፦ “ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ፥ ቸር ጠባቂ ስለ በጎቹ ነፍሱን ይሰጣል። ጠባቂ ያይደለ፥ በጎቹም ገንዘቡ ያይደሉ ምንደኛ ግን፥ ተኲላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፤ ተኲላም መጥቶ በጎቹን ይነጥቃቸዋል፥ ይበትናቸዋልም። ምንደኛስ ይሸሻል፥ ስለ በጎቹም አያዝንም፥ ምንደኛ ነውና” በማለት የቸር እረኛና የምንደኛ ልዩነት በንጽጽር እያስረዳ አስተምሯቸዋል /ወንጌል ቅዱስ አንድምታ፣ ገጽ.505-506/።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምነው የተጫንከውን አራገፍክብን? አንተ ምን ታደርግ አባ ሰላማ ብሎግ ነው ይህንንም ነጻነት የሠጠህ፡፡ እንደማቅ ብሎጎች እየመረጠ መልእክቶችን ሞደሬት ቢያደርግ ኖሮ እንዲህ አትሆንም ነበር፡፡ አሁን ይህ ያራገፍክብን ከተጻፈው መልእክት ጋር ምን ግንኙነት አለው? ደግሞስ ምንደኛው ማነው? አወገዝን ያሉት በየጓዳው እየወለዱ በየፍርድ ቤቱ እየተጎተቱ የሚገኙት በጋብቻም በምንኩስናም ያልታመኑት በአልጠግብ ባይነት ሁሉ እያላቸው ለገንዘብ ሲሯሯጡ 7 ሚሊዮን መንጋ ያሰረቁ እነ «አባ» አይደሉምን? ስለዚህ ከመጻፍህ በፊት ደጋግመህ አንብብ እባክህ

   Delete
 4. አባ ሰላማዎች እውነቱን ልንገራችሁ ይህንን አባባል ምንፍቅና ነዉ የማይለዉ ራሱ መናፍቅ ነዉ፡፡ ወዲያ ወዲህ አትበሉ መጽሐፍ ቅዱስን ያወቃችሁ መስሏችሁ የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር ዝቅ አታድርጉ፤ እርሱ የመረጣቸዉንም ዋጋ አታሳጧቸዉ፤ ሌላ ትርጉምም አትስጡት፤ በዚህ የምትነቀፉት እናንተ አስመሳዮች የቤተክርስቲያን ጠላቶች እንጅ አባቶች አይደሉም፡፡ እውነትን ተግታችሁ የምትፈልጉ ከሆነ ይገለጥላችኋል፡፡ ድብቅ አጀንዳችሁ ግን ስለተገለጠ በቤተክርስቲያን ስም አትሯሯጡ፡፡

  ReplyDelete
 5. አንተ የፕሮቴስታንት ተላላኪ መሆንህ የተገለጠ ነው:: በጠማማ መንገዳችሁ እስከመቼ ትሄዳላችሁ? የጥፋት ባሮች ሆይ:- ከጥፋታችሁ የምትመለሱ መቼ ይሆን? አይሁድ : ጸሀፍት : ፈሪሳውያን : መናፍቃንና የጥልቁ ሰራዊቶች ሁሉ የሚሸበሩት ክርስቲያኖች ኢየሱስ ክርስቶስን "ጌታችን" : "መድሃኒታችን" : "አምላካችን" በለው ሲጠሩ አይደለምን? አምላካችንን ለሞት ያበቃውስ "ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ታደርጋለህን?" የሚለው የወገኖችህ ክህደት አይደለምን? ቅድስት ቤተክርስቲያንን ትቃወም ዘንድ ያሰለጠነህ ርኩስ መንፈስ ምንኛ ክፉ ነው?! ከጥፋት ባሮች እንደሆንክ ይታወቅ ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ : ጌታ : መድሃኒት በመባሉ መንፈስህ ተቆጣ:: ይልቅም እንደታናሽ ወንድምህ ስሙን ለመዘነጣጠል ተነሳህ:: የምትውልና የምታድር ከመናፍቃን የሞት አዳራሽ እየተሳደብክ ነውና:: የመናፍቃን ምንደኛ ሆይ :- ሰማይና ምድር እስኪያልፉ አምላካችንን "አምላካችን" : ጌታችንን "ጌታችን" : መድሃኒታችንን "መድሃኒታችን" እያልን በፅናት እንጠጠብቀዋለን:: አምላካችን ሲመጣ ለሁሉ እንደየ ስራው ያስረክበዋል:: አመፀኞች ግን ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንደማይገቡ እናውቃለን!

  ReplyDelete
 6. ያንቀላፉ ቅዱሳን ሕያዋን ቢሆኑም እኛና እነርሱ በመንፈስ ካልሆነ በቀር ቀጥተኛ ግንኙነት ስለሌለን እኛ ከእነርሱ ጋር መነጋገርም ሆነ ጸልዩልን ማለት አንችልም፡፡ ለነገሩ በአጸደ ስጋ ካሉትስ ጋር ቢሆን በአካል ተቀራርበን ካልተያየን በቀር በመንፈስ እንጂ በስጋ እኮ ተለያይተናል፡፡

  u tell us the truth unknowingly. what orthodox church says is as u stated. yes we didn't have physical contact. The madiator b/n us & dead holly people is the holly spirit. That is what orthodox says. "ke Geta menfes beker yesewun hasab man yakal" we are happy that the father gave us the holly spirit to work b/n us & Marry, Angels... Holly people dead or alive understand what is going on through the holly spirit. B/c holly spirit is the one who fills the world. All, who believe in the trinity, in death & resurrection of Christ... are the same & communicate each other through the holly spirit, whether dead or alive. No d/c. please don't create a big gap b/n dead & alive."Binmotim, binorim ye Geta nen." Even dead holly people are much knowledgable than we persons in the world.

  "Ahun bedingizgiz endemnay nen. Behuala gin ene rasie endetawoku akalehu."

  Thanks u didn't mention " kemote Anbessa yalmote wusha yishalal" like ignorant protestants who didn't understand scriptures in detail.

  ReplyDelete
  Replies
  1. The madiator b/n us & dead holly people is the holly spirit. That is what orthodox says. ለዚህ ማስረጃህ ምንድን ነው? መንፈስ ቅዱስ እኛ ወደእግዚአብሔር እንዴት መጸለይ እንዳለብን ስለማናውቅ ይረዳናል ተባለ እንጂ እኛንና ያንቀላፉ ቅዱሳንን የሚያገናኝ መካከለኛ ነው ማለት ያልተጻፈ አንባቢ ያሰኛል፡፡ መንፈስ ቅዱስ እኛን ካንቀላፉ ቅዱሳን ጋር የሚያገናኝበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ለመሆኑ ያንቀላፉትን እንተውና በሕይወት ያለነውና በዓለም ተበትነን የምንገኘው ቅዱሳን ግንኙነታችን በመንፈስ ነው ሲባል ምን ማለት ነው? በጸሎት እንነጋገራለን ማለት ነው? በፍጹም አይደለም፡፡ እኛ እነማን እንደ ሆኑ የማናውቃቸው እነርሱም የማያውቁን በጌታ ግን የሚታወቁ የአንዲቱ ቤተክርስቲያን አባላት አሉ ማለት ነው፡፡ ከዚህ ውጪ እኛ ከእነርሱ ጋር እነርሱም ከእኛ ጋር ከዚህ የተለየ ግንኙነት የለንም፡፡ ካንቀላፋን በኋላም ከዚህ የተለየ ነገር አይኖርም፡፡ አንተ «ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ ዛሬስ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ አውቃለሁ።» የሚለውን የተለመደና ሙታን ሳቢ ለሆነ ከንቱ ሀሳባችሁ ድጋፍ አድርጋችሁ የምትጠቅሱትን ጠቅሰሃል፡፡ አሁን ይህ ቅዱሳን ሲሞቱ ሁሉን ወደማወቅ ይሸጋገራሉ የሚል መልእክት አለው ብለህ ታስባለህ? ይህ እኮ ወደፊት ጌታ ሲገለጥ የሚሆነውን ነገር ነው የሚያሳየው፡፡ «የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም። ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።» (1ዮሀ. 3፥1-2) አብርሃም ሙሴንና ነቢያት አወቀ የሚለውን አልተቀስክምሳ? ለምን ይሆን ምናልባት አብርሃም በአጸደ ነፍስ ሆኖ እንደማያውቃቸው እስራኤል የመሰከሩትን አስተውለህ ከሆነ መልካም ነው ካላስተዋልክ ጥቅሱ ይኸውልህ «አብርሃም ባያውቀን እስራኤልም ባይገነዘበን አንተ አባታችን ነህ አቤቱ፥ አንተ አባታችን ነህ፥ ስምህም ከዘላለም ታዳጊያችን ነው።» (ኢሳ. 63፥16)

   Delete
  2. Dear anonymous
   Totally I don't agree with ur idea. Knowing all thing is the character of God. But God shared his character to us. By grace with the help of the holly spirit saints can know what is going on.Don't u read history of Elijah, Elsae, peter, paul... please tell me how they can understand what is going on around them except with the help of the holly spirit? To make it clear, peter knows Hanah & sepira steal from their gift to church through the holly spirit & u know it what happened to them.
   I fully believe Michael, Marry... can know what I pray through holly spirit.

   USA & others know what is going on around the world through satelite which is a material. please , please don't u think the angels who are spirits,saints,who are people of God,lead by the holly spirit, who are around us all the time couldn't know what is going on in this world?

   one of ur mistake
   «አብርሃም ባያውቀን እስራኤልም ባይገነዘበን አንተ አባታችን ነህ አቤቱ፥ አንተ አባታችን ነህ፥ ስምህም ከዘላለም ታዳጊያችን ነው።» (ኢሳ. 63፥16)

   does it mean Abrham don't know us? It doesn't. If it is, in the scripture what u mentionned how he knows Mussie & Prophets? Bible do not contadict each other except our understanding.It is a kind of expression that, even though persons ignore us u don't let alone us.which is real. The love of God can not be compared with any creature including Abrham & Israel.Saints, Angels loved us with the love of God, since they are his people. Loving humans is the original character of God.

   Delete
  3. What about st.paul saying

   " But we understand every thing through the spirit of God" Saints know every thing.

   Delete
  4. ኅሊና መቼም ስሙ የሴት ይመስላልና አንቺ እያልሁ ለመጻፍ እገደዳለሁ፡፡ ወንድ ከሆንሽም ይቅርታሽን እጠይቃለሁ፡፡ ሁሉን ማወቅ የእግዚአብሔር ባሕርይ መሆኑን ጽፈሻል። እውነት ነው። ይህን ባሕርይ ግን እግዚአብሔር ለማንም አላጋራም፤ አያጋራምም። ሁሉን ዐዋቂ (ማእምረ ኲሉ) በሁሉ የሚገኝ (ምሉዕ በኲለሄ)ሁሉን ቻይ (ከሃሌ ኲሉ) እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ከእነዚህ መካከል የተሰወረውን አንዳንድ ጊዜ ሲገልጥላቸው ቅዱሳን ያውቃሉ። እንደጠቀስሽው ለምሳሌ ኤልሳዕና ጴጥሮስ በስፍራው ሳይገኙና ለማወቅ ተፈጥሮአቸው የማይፈቅድላቸውን ነገሮች አውቀዋል፡፡ እነዚያን ነገሮች ያወቁት ግን እግዚአብሄር ለዚያው ጊዜ ስለገለጸላቸው ነው እንጂ ሁሉን የማውቅ ባህርይን ከእግዚአብሔር ስለተካፈሉ አይደለም፡፡ እንዲህ ቢሆንማ ኖሮ ኤልሳዕም ሆነ ጴጥሮስ ሁል ጊዜ ባወቁ ነበር፡፡ ነገር ግን ያላወቁበት ጊዜ ነው፡፡ ለምሳሌ ኤልሳዕ «ወደ ተራራው ወደ እግዚአብሔር ሰው በመጣች ጊዜ እግሮቹን ጨበጠች ግያዝም ሊያርቃት ቀረበ የእግዚአብሔርም ሰው። ነፍስዋ አዝናለችና ተዋት እግዚአብሔርም ያንን ከእኔ ሰውሮታል አልነገረኝምም አለ።» (2ነገ. 4፡27)፡፡ አናንያና ሰጲራ በስውር የሰሩትን መንፈስ ቅዱስ ገልጦለት ያወቀውና የፍርድ ቃል የስተላለፈባቸው ጴጥሮስም ከዚህ በኋላ ቆርኔሌዎስ ባስጠራው ጊዜ የተጠራበትን ምክንያት አላስተዋለም ነበር፡፡ «ስለዚህም ደግሞ ብትጠሩኝ ሳልከራከር መጣሁ። አሁንም በምን ምክንያት አስመጣችሁኝ? ብዬ እጠይቃችኋለሁ አላቸው።» (የሐዋ.ስራ 10፥29)ከዚህም የምንረዳው ቅዱሳን ሁሉን ወደማወቅ እንዳልተሸጋገሩና እግዚአብሔር የሚሠራው ሥራ ሲኖር የተሰወረውን እንደሚገልጽላቸው ነው፡፡ በእርግጥ አንቺ «ሚካኤልና ማርያም በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የምጸልየውን ያውቃሉ ብዬ በእርግጠኝነት አምናለሁ ብለሻል» መብትሽ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ግን አይደለም፡፡ በቅድሚያ ያንቺን ጸሎት ለእነርሱ የሚገልጽበት ምክንያት ምንድን ነው? እነርሱስ የአንቺን ጸሎት ማወቅ ልምን አስፈለጋቸው? ጸሎት እኮ የሚቀርበው ለእግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ለአንተ ጸሎት ይቀርባል ተብሎ ተጽፏልና፡፡
   ከሁሉ የሚገርመው ግን አሜሪካና ሌሎችም አገራት በዓለም ዙሪያ የሚሆነውን በሳተላይት ማወቃቸውን ለዚህ ማስረጃ አድርገሽ ማቅረብሽ ነው፡፡ ይህ በፍጹም ለመንፈሳዊው ነገር ምሳሌ ሊሆን አይችልምና ሌላ ምሳሌ ብትፈልጊ ሳይሻል አይቀርም፡፡ አብርሃም ባያውቀን የሚለውን ጥቅስ ተቅሰሽ የሰጠሽው መከራከሪያም ብዙ የሚያዋጣ አይደለም፡፡ አብርሃም ሙሴና ነቢያት አሉላቸው እነርሱን ይስሙ ማለቱ በሁሉን አዋቂነቱ ያወቀው ሳይሆን ከላይ እንዳስረዳሁት እጊአአብሔር ስለገለጸለት ነው፡፡ ታዲያ አንቺስ የእስራኤልን ንግግር እንዴት አየሽው? «አብርሃም ባያውቀን እስራኤልም ባይገነዘበን አንተ አባታችን ነህ አቤቱ፥ አንተ አባታችን ነህ፥ ስምህም ከዘላለም ታዳጊያችን ነው።» (ኢሳ. 63፥16) በእርግጥ እንዳልሽው መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በርሱ አይጋጭም፡፡ የሚጋጨው ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ የሆነ ሐሳብ ይዘን ወደመጽሐፍ ቅዱስ ስንጠጋና በግድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስናደርገው ያን ጊዜ ይጣላል፡፡ ስለዚህ ኅሊና እግዚአብሔር ለሰው ያካፈለው ባሕርይ አለ፡፡ ለሰው ያላካፈለውና የራሱ ብቻ የሆኑ ባሕርያትም አሉት፡፡ ሁሉን አዋቂነት፣ በሁሉ ስፍራ መገኘት ሁሉን ቻይነት፡፡

   Delete
 7. ይህ አቋም የአባ ሰላማ ድረ ግጽ ነው ወይስ የአንድ ግለሰብ ነው ? ጻድቃን ፥ ሰማዕታት እንዲሁም ድንግል ማርያም ዛሬ በሕይዎተ ሥጋ ስለሌሉ ሊያምልዱን አይችሉም የሚለው ነገር የፕሮተስታንት እምነት ስለሆነ እንዴት ይህ ግለሰብ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባል ሊሆን ይችላል? እኔ እስካሁን አባ ሰላማ የመናፍቃን ልሳን ነው የሚለውን ሃሳብ አልቀበለውም ነበር። ዛሬ ግን ተረድቻለሁ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስምህ ከበደ ቦጋለ ነው አይደል? እኔ ግን ቀለለ ድርግም አለ ብዬሃለሁ፡፡ ለመሆኑ አንተ ማን ሆነህ ነው ለአንድ ብሎግ እውቅና ሰጪ የሆንከው? ጻድቃን ፥ ሰማዕታት እንዲሁም ድንግል ማርያም ዛሬ በሕይዎተ ሥጋ ስለሌሉ ሊያምልዱን አይችሉም በመባሉ አባሰላማ ድረገጽን ተሳስቷል ከምትል እንዲህ ያለውን ውዳሴ ማርያም ትርጉም ለምን ተሳስተሃል አትለውም፡፡
   አይ ቀለለ

   Delete
 8. who has skill to make a critique. is Dn Mulugeta Woldegeriel?

  ReplyDelete
 9. Yihin yetsafkew mewegez ayigebagnim tilaleh?

  ReplyDelete
 10. Wuyyt melkam new! Negeroch le kift bemadreg mekeraker melkam new be masreja gin medegef alebachew.
  " abo bilht echegnet ke mist"bilew gonderoch alagetubachew bilachual .min siladeregu?

  Pls pray before u write such kind of articles.it would mis lead many souls.if evidences are available it our duty to search n believe .

  ReplyDelete
 11. እስራኤላውያን በባቢሎን ምርኮ ለበርካታ አመታት በተሰቃዩ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ስለ እነርሱ በግልጽ ቃል ምልጃ አቅርቧል፡፡ ይህም ምልጃው በዚህ መልኩ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግቧል፡- ‹‹የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ፦ አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ እነዚህ ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው? አለ።›› (ዘካ1.12) መልአኩ ይህን ልመና ባቀረበ ጊዜ ‹‹እግዚአብሔርም መልሶ ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረው መልአክ በመልካምና በሚያጽናና ቃል ተናገረው።›› ይላል፡፡ (ዘካ1.13)
  ታሪኩን ልብ ብሎ ያነበበ ሰው ይህ ‹‹መልካምና የሚያጽናና ቃል›› ምን ይሆን? ማለቱ አይቀርም፡፡ መቼም ‹‹የማትምራቸው እስከ መቼ ነው?›› ለሚለው የልመና ቃል ‹‹ምሬአቸዋለሁ ወይም እምራቸዋለሁ›› ከሚል ውጭ የሚያጽናና ቃል ሊኖር አይችልም፡፡ ይህም በግምት የቀረበ ሐሳብ ሳይሆን መልአኩ ለዘካርያስ ባስተላለፈው የመጨረሻ ቃል ይታወቃል፡፡ ‹‹ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ኢየሩሳሌም በምሕረት ተመልሻለሁ ቤቴ ይሠራባታል በኢየሩሳሌምም ላይ ገመድ ይዘረጋበታል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፦ ደግሞም እንዲህ ስትል ስበክ። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከተሞቼ ደግሞ በበጎ ነገር ይረካሉ እግዚአብሔርም ደግሞ ጽዮንን ያጽናናል፥ ኢየሩሳሌምንም ደግሞ ይመርጣል።›› ብለህ ስበክ ብሎ ልኮታል፡፡ (ዘካ1.16-17

  መልአኩ የለመነው ምን ነበር? ምሕረት አልነበርምን? ፈጣሪ ደግሞ በምሕረት ተመልሻለሁ ሲል መለሰ፡፡ የመልአኩ አማላጅነት ተቀባይነት አግኝቷ ማለት ነው፡፡ መላእክት ያማልዳሉ ስንል ይህን የመሳሰሉ ጠንካራና በርካታ መረጃዎችን ከመጽሐፍ ቅዱስ አግኝተን ነው እንጂ ከራሳችን ፍላጎት ተነሥተን አይደለም፡፡
  በነገራችን ላይ ይህን ጥቅስ በተመለከተ ገጠመኜን ላውጋችሁ፡፡ አንድ ቀን ከአንድ መናፍቅ ጋር በአጋጣሚ የሃይማኖት ጉዳይ ተነሣና መነጋገር ጀመርን፡፡ ርእሱም ስለመላእክት አማላጅነት ሆነ፡፡ በዚህ ጊዜ ለማስረዳት ይህን ጥቅስ ጠቀስኩለት፡፡ ምን አለ መሰላችሁ? ‹‹መላአኩ እኮ የማትምራቸው እስከ መቼ ነው? አለ እንጂ አልለመነላቸውም፤ ማራቸውም አላለም፡›› ብሎኝ እርፍ፡፡ እኔም እሺ ታዲያ እንዲህ ሲል ምን ማለቱ ነበር? አልኩት፡፡ እርሱም መልሶ ‹‹መቼ ልትምራቸው አስበሃል? ብሎ ቀጠሮ ነው የጠየቀው›› ሲል ደመደመ፡፡ ምንም እንኳን የምንማረው ለመናፍቃን መልስ ለመስጠት ብለን ባይሆንም እንዲህ ዓይነት ዓይን ያወጣ ድርቅና ሊያጋጥማችሁም እንደሚችል አትርሱ፡፡
  እንደዚህ መናፍቅ አተረጓጎም መልአኩ የጠየቀው ‹‹እስከ መቼ›› ብሎ ቀጠሮ ከሆነ መልሱ ‹‹በዚህ ጊዜ›› የሚል እንጂ ‹‹በምሕረት ተመልሻለሁ›› የሚል አይሆንም ነበር፡፡ ጥያቄው ምን እንደነበር ከመልሱ በመነሣት ማወቅ ይቻላል

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thanks brother/sister. I faced like u. By the way u know the failurity of we EOC followers, We do not read bible. If all EOC member is encouraged to read bible, before protestants preaches them, every one can not be converted. The problem is, they read bible after they join protestant church & they fill like they get a special new thing. They will not hear u wt ever u say. I started to read bible & Pop shinoda III books before four years. I have got so many things & changed my life. I know every thing about d/t sects. When protestant come & started to say their thing, I challenge them from the bible. on majority they know some scriptures only. They haven't seen scriptures what u indicated & others. what they mention is always the same from person to person. I think every body know it.
   Not only the intercession of saints & angels, they have also alot of crazy doctrines which u can challenge them by the bible they hold. Their wrong view on baptism, holy communion, deeds in salvation. Their wrong view of christ as a mediator by comparing it with the intercession of saints & angels.
   on what u say,when I indicate the scripture u mentionned for one protestant he said to me. "It is real that the angels intercede in the old testament, but not in new" ha ha ha. I asked him where in the bible did u get this? but he doesn't.

   What about the other in the Tinbite Daniel which says
   " bemechereshaw zemen sile hizb ligoch yemikom talaku Michael yinesal" eeeeeellllllllllllllllll min yibalal engdih.

   Delete
 12. የዚህ ብሎግ ጸሃፊዎች!! ምነው? እውነት አታውቁም እንዴ? መዋሸትስ ቢሆን የሚመስል ዉሸት እኮ ጥሩ ነው፥
  ቤ/ን በአለት ላይ እንደተመሰረተች እያወቃችሁ፣ ለማፍረስ ባትጥሩ መልካም ነው። ልፋት ብቻ ይሆንባችኋል

  ReplyDelete
 13. የጻድቃን ፥ የሰማዕታት እንዲሁም የቅድስት ድንግል ወላዲት አምላክ ማርያም አማላጂነታቸው በህይዎተ ሥጋ ሳሉ ነው እንጅ ከዚህ ዓለም ከተለዩ በሁዋላ አይሰራም የሚለው የመናፍቃን እምነት እኮ ከሞት በሁዋላ ሕይዎት መኖሩን እንደመካድም ጭምር መሆኑ ነው። ለመሆኑ ምልጃን በሚመለከት የምንጨነቀው ለሥጋዊ ሕይዎታችን ብቻ ነው እንዴ ? መናፍቃኑ ዘለዓለማዊ ሕይዎት እንዳለን የሚያምኑ አለምሆናቸው የቅዱሳንን ምልጃ በምድረ ሥጋ መወሰናቸው ነው። እኛ ግን ከሞት በኋላ ሕይዎት አለ ብለን ስለምናምን ጻድቃን በአጸደ ነብስ ሁነው በምድረ ሥጋ ላለነው ይማልዳሉ ብለን ነው የምናምነው።

  ReplyDelete
 14. ውድ አንባብያን እስቲ አስተውሉ ትዝ ይበላችሁ መናፍቃን ባገራችን መስፋፋት ሲጀምሩ በየአውቶቡስ ማቆሚያ ሰው በሚሰበሰብበት ሁሉ በስጋም ሆነ በነፍስ ሌላ የሚያማልድ የለም ነበር ማታለያቸው የኦርቶዶክስ ቤ/ክ ስትጠናከርና ሰባክያን ሲበዙ ስለ ቅዱሳን አማላጅነት ከበቂ በላይ ማስረጃዎች ሲቀርቡና ለመሆኑ እናንተ መናፍቅ ሆናችሁ ሳለ ልጸልይልህ/ሽ የምትሉ ከሆነ ጌታ ያከበራቸው ቅዱሳን እማ እንዴት አያማልዱም ሊባሉ ይችላሉ? ተብለው ሲጠየቁና መልስ ሲያጡ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በስጋ ያማልዳሉ በነፍስ ግን አይደለም ማለት ጀምረዋል፡፡ እናንተ ደጀ ሰላም ተብየዎች ደግሞ ራሳችሁ መናፍቅ ስለሆናችሁ ለመናፍቃን አስተሳሰብ ጠበቃ ሆናችሁ ትከራከራላችሁ፡፡ ቅዱሳን ባአጸደ ነፍስም እንደሚያማልዱ ቤ/ክ በቂ መረጃ አላት ተናግራለች ትናገራለችም። ችግሩ ግን የናንተ ልብ እኛ ብቻ ነን አዋቂዎች እኛ ያልነው ነው ትክክል ስለምትሉና ለማመን ልባችሁ ስላልተዘጋጀ አትቀበሉትም ወይም ሌላ መከራከርያ ሀሳብ ይዛችሁ ትመጣላችሁ። ይህ ደግሞ የታወቀ የመናፍቅ ጠባይ ነውና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ምዕመናን አንባብያን ይህን ተረድታችሁ ራሳችሁን እንድትጠብቁ እመክራለሁ በኦርቶዶክስ ቤ/ክ ውስጥ ሆነው ምዕመናንን እንዲጠራጠሩ ግራ እንዲጋቡ ሃይማኖታቸውን በእድሳት ሽፋን እነዲቀይሩ ሌት ተቀን የሚተጉ አውቆ የተኛን ሰው ቢቀሰቅሱት አይሰማም እንደሚባለው የማይሰሙ ያስቆሮቱ ይሁዳዎች ካልሆኑ በስተቀር አኦርቶዶክሳውያን ሊባሉ ከቶ አይችሉም አይገባምም እና ኑፋቄአቸውን በማንበብ አጉል ጥርጥር እንዳትገቡ ራሳችሁን ጠብቁ። እባብ ሰውን የሚነድፈው በምላሱና በጥርሱ ባጠቃላይ በአፉ በሚተፋው መርዝ ነው። መናፍቃንም ሰውን የሚያሰናክሉት ከአፋቸው በሚወጣው ኑፋቄ ነውና ተጠንቀቁ። AnonymousNovember 21, 2012 12:09 AM ዘካ 1፡16-17 ያለውን ጠቅሰህ ስለ ቅዱሳን አማላጅነት ለሰጠኸው መልስ በበኩሌ ላመሰግን እወዳለሁ፡፡ ልቦና ላለው ለሚያስተውል ይህ በቂ ማስረጃ ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. እርማት፡- ይህንን እርማት የምጽፈው AnonymousNovember 22, 2012 12:59 AM በሚለው ስር የተጻፈውን አስተያየት የጻፍኩት ነኝ። እርማቱም እናንተ ደጀ ሰላም(Deje Selaam) ተብዬዎች ደግሞ ራሳችሁ መናፍቅ ስለሆናችሁ ለመናፍቃን አስተሳሰብ ጠበቃ ሆናችሁ ትከራከራላችሁ በማለት በጻፍኩት አባባል ላይ ደጀ ሰላም(Deje Selaam) የሚለው ቃል በታይፒንግ ግድፈት በስህተት የተጻፈ ነው። ለማለት የፈለኩት እናንተ ተሐድሶ ተብዬዎች ነው። ስለዚህ እናንተ ተሐድሶ ተብዬዎች ደግሞ ራሳችሁ መናፍቅ ስለሆናችሁ ለመናፍቃን አስተሳሰብ ጠበቃ ሆናችሁ ትከራከራላችሁ። በሚለው ታርሞ እንዲነበብ ከታላቅ ይቅርታ ጋር አንባብያንን እጠይቃለሁ። የአስተያየቴ መሰረታዊ አላማ ስለ ብሎጎችን ለመናገር ሳይሆን በቤ/ክ ተቃዋሚዎች ላይ ተቃውሞዬን ለመግለጽ ምዕመናን እንዲጠነቀቁ ለመምከር ነው።

   Delete
 15. በቅዱሳን መላእክት ማዳንና ተራዳኢነት ውስጥ የእግዚአብሔር ሥልጣንና አዛዥነት በረቂቅ አለበት፡፡ እግዚአብሔር ሰዎችን ለማዳን በምንም መንገድ ቢሠራ በዛ ውስጥ የእርሱ ሥልጣንና ሥራ የማይጠረጠር ነው፡፡ መላእክት ያለ ፈጣሪ ትእዛዝና ፈቃድ አንዳች ሊሠሩ አይችሉም፡፡ ፈጣሪ ግን ያለ መላእክት አጋዥነት የፈለገውን የሚሠራ ሁሉን ቻይ አምላክ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ፈጣሪ ይህን ሠራ ስንል መላእክትን ላይጨምር ይችላል፡፡ መላእክት ይህን አደረጉ ስንል ግን በምንም ተአምር ከፈጣሪ ውጭ ሊሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ መናፍቃን ‹‹ጌታ፣ እግዚአብሔር ይህን አደረገ›› ብቻ እንድንል የሚፈልጉት ቅዱሳንን ላለማስገባት ነው፡፡ እኛ ኦርቶዶክሳዊያን ቅዱሳን መላእክትንና ቅዱሳን ሰዎችን ይህን አደረጉ የምንለው እግዚአብሔርን ከማመን ጋር ስለ ቅዱሳን ክብር ለመመስከር ነው፡፡

  እሳት በባሕርይው የሚፋጅ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እንጨትና ብረት ግን ብቻቸውን ሳሉ ቢነኳቸው አያቃጥሉም፡፡ ነገር ግን ከእሳት ጋር ከተዋሐዱ /ከጋሉ/ በኋላ ቢነኳቸው ይፋጃሉ፡፡ እሳት የተዋሐደው ብረት የማያቃጥልበት ምንም ሁኔታ የለም፡፡ ካላቃጠለ ወይ እሳት አልተዋሐደውም ወይም ደግሞ እሳቱ ራሱ አያቃጥልም ማለት ነው፡፡ እንደዚሁም እግዚአብሔር በባሕርይው አዳኝ ነው፡፡ መላእክት አያድኑም ካልን ወይ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር አይደለም ማለት ነው ወይም ደግሞ እግዚአብሔር ራሱ አያድንም እንደማለት ይቆጠርብናል፡፡ ስለዚህ ‹‹መላእክት ያድናሉ›› ስንል የሚያድን እግዚአብሔር ከእነርሱ እንደማይለይ እየመሰከርን መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡

  ReplyDelete
 16. እግዚአብሔር የቅዱሳንን አማላጅነት እንድንጠቀም ጠይቆናል !
  5. ሙሴ ስለ እስራኤል ሕዝቦች ያደረገውምልጃ፡ -
  - ሕዝቡ የወርቁን ጥጃ አምልከዋልና እግዚአብሔር ሕዝቡን ሊያጠፋ ፈለገ፡፡
  - ሊያደርገው የፈቀደውንም ቀጥታ አልፈጸመውም ለወዳጁ ለነቢዩ ሙሴ አማከረው፣ ስለ
  ሕዝቡም ያማልድ ዘንድ እድል ሰጠው፣ ሙሴም በእድሉ ተጠቅሞ አማለዳቸው
  እግዚአብሔርም ተቀበለው፡፡
  - “እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ከግብፅ ምድር ያወጣኸው ሕዝብህ ኃጢአት ሠርተዋልና ሂድ፥
  ውረድ። ካዘዝኋቸው መንገድ ፈጥነው ፈቀቅ አሉ ቀልጦ የተሠራ የጥጃ ምስል ለራሳቸው
  አደረጉ፥ ሰገዱለትም፥ ሠዉለትም። እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ
  ናቸው አሉ ሲል ተናገረው። እግዚአብሔርም ሙሴን፦ እኔ ይህን ሕዝብ አየሁት፥ እነሆም
  አንገተ ደንዳና ሕዝብ ነው። አሁንም ቍጣዬ እንዲቃጠልባቸው እንዳጠፋቸውም ተወኝ
  አንተንም ለታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ አለው። ሙሴም በእግዚአብሔር በአምላኩ ፊት ጸለየ፥
  አለም። አቤቱ፥ ቍጣህ በታላቅ ኃይልና በጽኑ እጅ ከግብፅ ምድር ባወጣኸው በሕዝብህ ላይ ስለ
  ምን ተቃጠለ? ግብፃውያንስ። በተራራ መካከል ሊገድላቸው፥ ከምድርም ፊት ሊያጠፋቸው
  ለክፋት አወጣቸው ብለው ስለ ምን ይናገራሉ? ከመዓትህ ተመለስ፥ ለሕዝብህም በክፋታቸው
  ላይ ራራ። ዘራችሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፥ ይህችንም የተናገርኋትን ምድር ሁሉ
  ለዘራችሁ እሰጣታለሁ፥ ለዘላለምም ይወርሱአታል ብለህ በራስህ የማልህላቸውን ባሪያዎችህን
  አብርሃምንና ይስሐቅን እስራኤልንም አስብ። እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ ሊያደርግ ስላሰበው
  ክፋት ራራ።” ዘፍጥ 32፡7-14፡፡

  ReplyDelete
 17. pope shenoda 3..1) There is a major and essential difference between the Advocacyጠበቃ of our Lord and intersession ምልጃ of the Saints: ............the Advocacy of Christ is a propitiatory(ካሳመክፈል) ...This means that our Lord is our advocate when we sin having made Himself the propitiation ለሃጥያታችን ካሳ መክፈልን of our sins, who paid the wages of sin on our behalf. Christ's advocacy with the Father is based on the fact that He has carried -instead of us- the iniquity of us
  all (Is 53:6).
  In this capacity He stands as a mediator between God and men. As a matter of fact, He is the
  only mediator between God and men; having satisfied the Divine justice required by the Father,
  and granting men the forgiveness of their sins by dying on their behalf as a propitiation for their
  sins.
  This is the meaning of the words of St. John the Apostle for he says: "If any man sin, we have an
  advocate with the Father, Jesus Christ the righteous: And He is the propitiation for our sins: and
  not for our sins only, but also for the sins of the whole world". (1Jn 2:1,2)
  This clearly exemplifies the propitiatory nature of Christ's advocacy. It is an advocacy on behalf
  of a sinful man; "if any man sin". A sinful man needs a propitiation. And the only One who
  offered this propitiation is Jesus Christ the righteous. Only he can be our advocate, through the
  blood He shed on our behalf.
  The same intent appears in St. Paul's designation of the Lord Christ as the only mediator between
  God and men: "one mediator between God and men, the man Christ Jesus; Who gave Himself a
  ransom for all" (1Ti 2:5). He mediates being the Redeemer who gave Himself and paid the
  wages of sin on our behalf.
  No one would argue this unique role of the Lord Christ as sole advocate of man-kind.
  Intercession of the Saints on behalf of men has nothing to do with propitiationካሳ and redemption. It
  is intercession on our behalf before Christ.

  ReplyDelete
 18. ነብያትን ይስሙ [ሉቃስ 16:19]

  ነዌ ባለጠጋው ሃብቱን አከማችቶ
  እለት ከእለት ባለም ተመቻችቶ
  ይኖር ነበር አምላክን ረስቶ
  ደሃው አላዛርም በደጁ ተኝቶ
  አንድ ቀን ጌታዬ ያዝንኛል ብሎ
  ቀን ይቆጥር ነበር በቁስል ተወርሶ
  ቁራሽ ፍርፋሪን አገኛለሁ ብሎ።

  ያ ባለጠጋ በልቡ ሳይራራ
  በንቀት አየው ሲወጣ ሲገባ
  ቀኑ ደረሰና ያ ደሃ ተጠራ
  በአብርሃም እቅፍ መልካም ቦታ አገኘ
  ነዌ ባለጠጋ ሃብቱ መች ጠቀመው
  ቀኑ ሲደርስ እርሱም ሞት አገኘው
  መልካም ስላልነበር በምድር የሰራው
  በሲኦል ክፉ ሆኖ አገኘው
  በስቃይ ሳለ አሻቅቦ አብርሃምን አየው
  አላዛርንም በእቅፉ ቢያየው
  የጣቱን ጫፍ በውሃ ውስጥ ነክሮ
  ምላሴን ቢያርሰው
  አብርሃም አባት ሆይ አላዛርን እባክህን ላከው
  ብሎ አላዛርን ሻተ በምድር ለናቀው።
  አብርሃም መልሶ
  አንተ በምድር ሳለህ መልካምን ተቀበልክ
  አላዛርም ደግሞ እንዲሁ ክፉውን
  ሁሉን ተቀብሏል አሁን ግን ይፅናናል
  በኛና በናንተ ታላቅ ገደል ሆኗል።
  ነዌ ይህን ግዜ 5 ወንድም አሉኝ
  እነርሱም ደግሞ እንደኔ እንዳይሆኑ
  አላዛርን ላከው ሁሉን ይንገርልኝ፤
  ሙሴና ነብያት ለነርሱ አሏቸው
  እነርሱንም ይስሙ መንገድ ይሁኗቸው
  ሰምተው ቢፈፅሙት ህይወት ይሁናቸው
  ብሎ መለሰለት እኛ እንድንሰማቸው።


  /ተክለ መድህን/

  ReplyDelete
 19. @Anonymous November 21, 2012 9:43 AM

  እንዳንተ አይነቷ እብድ ቤቷን አቃጥላ እሰይ በራልኝ አለች አሉ፡፡

  ReplyDelete
 20. Please see on what our Lord and Savior King of Kings Alpha and Omega Jesus Chrsit taught us about intercession of the Saints after leaving thier flesh.

  Gospel of Luke 16 (KJV)
  [19] There was a certain rich man, which was clothed in purple and fine linen, and fared sumptuously every day:
  [20] And there was a certain beggar named Lazarus, which was laid at his gate, full of sores,
  [21] And desiring to be fed with the crumbs which fell from the rich man's table: moreover the dogs came and licked his sores.
  [22] And it came to pass, that the beggar died, and was carried by the angels into Abraham's bosom: the rich man also died, and was buried;
  [23] And in hell he lift up his eyes, being in torments, and seeth Abraham afar off, and Lazarus in his bosom.
  [24] And he cried and said, Father Abraham, have mercy on me, and send Lazarus, that he may dip the tip of his finger in water, and cool my tongue; for I am tormented in this flame.
  [25] But Abraham said, Son, remember that thou in thy lifetime receivedst thy good things, and likewise Lazarus evil things: but now he is comforted, and thou art tormented.
  [26] And beside all this, between us and you there is a great gulf fixed: so that they which would pass from hence to you cannot; neither can they pass to us, that would come from thence.
  [27] Then he said, I pray thee therefore, father, that thou wouldest send him to my father's house:
  [28] For I have five brethren; that he may testify unto them, lest they also come into this place of torment.
  [29] Abraham saith unto him, They have Moses and the prophets; let them hear them.
  [30] And he said, Nay, father Abraham: but if one went unto them from the dead, they will repent.
  [31] And he said unto him, If they hear not Moses and the prophets, neither will they be persuaded, though one rose from the dead.

  Can you say , you read the Bible? Let God open your eyes!

  ReplyDelete
 21. «ሀ. እንደ ፈጣሪ ያለ ክብርና ምስጋና የሚገባቸው ፍጡራንና የእጅ ስራዎች ያሏት ቤተክርስቲያን ባዕድ አምላኪ ወይም ባለብዙ አማልክት ካልተባለች ምን ልትባል ትችላለች» ለተባለው

  ቤተ ክርስቲያን ፍጡርንና የእጅ ሥራዎችን ፈጣሪ ነው ብላ ያስተማረችበትን ወቅት ፣ ቦታና መጽሐፍ ማስነበብ ብትችሉ እኔም አብሬአችሁ እሞግት ነበር ፡፡ ነገር ግን መጽሐፍ “...ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ። ሮሜ 13፡7” በማለት ስለሚያስተምር ቅዱሳንን ታከብራለች ፡፡ እኛም እንድናከብር ታስተምራለች ፡፡ ይኸ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን ባዕድ አምላኪ ወይም ባለብዙ አማልክት አያስብልም ፡፡ ስለዚህም ጸሐፊው በግንዛቤ ተሳስተዋል ፡፡ ቅዱሳኑ እንዲከበሩ ያደረጋቸው መጀመሪያውኑ እግዚአብሔር መሆኑን መዝ 84፡11 ፤ ምሳሌ 21፡21 የሚለውን ይመልከቱ ፡፡

  «ለ. እግዚአብሔር እስካሁን ባለው አሰራሩ የማንንም ጸሎት በሞቱ ቅዱሳን በኩል ተቀብሎ አያውቅም» ሲሉ የእርሱን ተማላጅነትና የቅዱሳንን አማላጅነት ይቃወማሉ፡፡ ለተባለው

  ይኸን እንዲህ ደፍሮ ለመጻፍ ከሰዎች መሃከል ሄዶ አይቶ ማን ተመልሷል ? “ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል። ሉቃ 15፡7” ማለት ምን ማለት ነው ? የማይሰሙ ፣ እኛንም የማይከታተሉና በመንፈስ ግንኙነት የማያደርጉ ከሆነ ማን የምሥራቹን እየነገራቸው በእኛ ሁኔታ ይደሰታሉ ? “የጌታ ዓይኖች ወደ ጻድቃን ናቸውና፥ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል፥ 1 ጴጥ 3፡12” “እግዚአብሔር ከኅጥኣን ይርቃል፤ የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል። ምሳሌ 15፡29” ፤ የጊዜ ገደብ እንዳልተደረገ ልብ ይሏል ፤ "እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም? ራዕ 6፡1ዐ" ማለትስ ከሞቱ በኋላ አርፈው መተኛታቸውን የሚያስረዱን ኃይለ ቃሎች ይሆኑ ? እግዚአብሔር የሕያዋን አምላክ መሆኑንም በተደጋጋሚ በመጽሐፍ ተገልጿልና ይኸም ሌላው ስህተት ነው ፡፡

  ሐ . “ተክለሃይማኖት የወንጌል ሰባኪ ናቸው ወይስ ፖለቲከኛ” ለሚለው ጥያቄ ፣

  ታሪካችን መለስ ተብሎ በጥሞና ቢፈተሽ ፣ መጽሐፍ ቅዱሱም ረጋ ተብሎ ቢመረመር የቤተ ክርስቲያን ካህናት ንጉሥን መቀባት አንዱ ሥራቸው ሆኖ እናገኘዋለን ፡፡ የካህን ዘር ንጉሥ መሆን አይችልም የሚል ህግ ስለሌለን (የሌዊ ዘር ስላልሆንን) ፣ ምናልባት ባጋጣሚ ከቤተ ዘመድ ለዛ ክብርና ሥልጣን የሚበቃ ወገን ቢኖር ፤ መቀባቱ አይተጓጎልም ፡፡ አፄ ቴዎድሮስን ፣ አፄ ዮሐንስን የቀባው ካህን ፖለቲከኛ ስለሆነ ሳይሆን ሥርዓቱና ደንቡ ስለሚያስገድደው ፈጽሞታልና ፖለቲከኛ አልተባለም ፡፡ አቡነ ተክለሃይማኖትም የወንጌል አገልጋይ ሆነው ሳለ ንጉሥ ቢቀቡ ፣ መቀባት ከሥራቸው አንዱ ስለሆነ ነው እንጅ ፖለቲከኛ ስለሆኑ ነው ማለት ስህተትና ወገንታዊነት ይሆናል ፡፡


  ReplyDelete
 22. ቅዱሳንን በጸሎታችሁ እርዱኝ አግዙኝ እያልን እንደገና ህይወት ወደ ሚሰጠን ጌታ መቅረብ እንችላለን?ቅዱስ ጳውሎስ በዕብ ፭፦፯፡፲ ላይ "በሥጋው ወራት ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ ካለ በኋላ ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸውም" ይላል ። እንግዲህ ጌታ በሥጋው ወራት የፈጸማት ምልጃ ለሚታዘዙለት ሁሉ ማለትም ያመነ የተጠመቀ ይድናል ብሎ ያዘዘውን ትዕዛዝ ለሚፈጽሙ ፣ ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘለዓለም ህይወት አለው ላለው መመሪያ ተገዥ ለሆኑ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትዕዛዜ ይህች ናት ላለው ሕግ ለሚታዘዙለት ሁሉ ለዘላለም መዳን ምክንያት ሆኖላቸዋል። ማር ፲፮፦፲፮ ፣ ዮሐ ፮፦፶፫ ፣ ፲፭፦፲፪

  የማንታዘዝለት እና አመጸኞች ፣ በተለያዩ ምክንያቶች ህግጋቱን የምንሸራርፍ ደካሞች ከሆንን ግን ንስሐ እየገባን ፣ ስለ ኃጢአታችን ፣ እያለቅስን በደላችንን እያስታወስን የክርስቶስን ውለታ በመርሳታችን ወዮልኝ! ወዮታ አለብኝ! እያልን ቅዱሳንን በጸሎታችሁ እርዱኝ አግዙኝ እያልን እንደገና ህይወት ወደ ሚሰጠን ጌታ መቅረብ እንችላለን።ቅዱሳነን መለመን ጋር በምንም አይጋጭም ከኢየሱስ አዳኝነት ጋር በምንም አይቃረንም

  ReplyDelete