Sunday, November 11, 2012

አቃቤ መንበር ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ሲኖዶሱን አልሰበስብም ብለው አሰናበቱ

ወደ ሀገረ ስብከታቸው መመለሳቸውም ታውቋል
አክሱሞች አጣሪውን ቡድን አልተቀበሉም አባ ሰላማም ይልቀቁልን ብለዋል

በአቃቤ መንበር ብፁእ አቡነ ናትናኤልና በG8 የጳጳሳት ቡድን መካከል የተፈጠረው ውዝግብ ተካሮ ትናንትና አርብ ብፁእ አቡነ ናትናኤል በአቋማቸው ጸንተው በቃኝ ከዚህ በኋላ አልሰበስባችሁም ብለው ከወጡ በኋላ ከሰዓት በኋላ ሳይመለሱ ቀርተዋል። ጳጳሳቱም ተሰብስበው ቢጠብቋቸው ሳይመጡ በመቅረታቸው ስብሰባውን ሳያካሂዱ ተበትነዋል። በቀጣይ የሚሆነው ባይታወቅም በአሁኑ ጊዜ ወደሀገረ ስብከታቸው መመለሳቸው ተዘግቧል። በአቃቤ መንበርነት ከተሾሙ ወዲህ ወደ ሀገረ ስብከታቸው ሲሄዱም የመጀመሪያቸው ነው ተብሏል።
 
የአቡነ ናትናኤልን ሳይመለሱ መቅረት ተከትሎ «አባ» ሳሙኤልም «የተሳሳትነው እርሳቸውን ስንሾም ነው። እርሳቸውን መሾም አልነበረብንም ትልቅ ስህተት ሰርተናል፡፡ ፓትርያርክ ስንሾምም ተመሳሳይ ስህተት እንዳንደግም መጠንቀቅ አለብን» ማለታቸው ተሰምቷል። ይህም የሚያሳየው «አባ» ሳሙኤል ራሳቸውን ሻሚና ሻሪ አድርገው የሚመለከቱ፣ በቤተክርስቲያን በአባቶች መካከል የኖረውን ትልቅ የመከባበር ባህል በመናድ ቤተ ክርስቲያኗን ወደ ስርአተ አልበኝነት እየለወጧት መሆኑን ነው። ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ አሁን በአባቶች መካከል እየታየ ያለው መናናቅና ያለመደማመጥ፥ የበላይ አባትን ያለመፍራትና የማዋረድ አባዜ ቤተ ክርስቲያኗን ወደትልቅ ውድቀትና ኪሳራ የሚመራት አካሄድ መሆኑን ሁኔታውን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች እየተናገሩ ይገኛሉ። ለቀጣዩ ትውልድ ትቶት የሚያልፈው ጠባሳም በቀላሉ የሚገመት አይደለም፡፡

ቀጣዩ ምን እንደሚሆን ባይታወቅም ለቤተክርስቲያን ስርአት ደንታ የሌለው «የጎረምሶቹ ጳጳሳት» የነ«አባ» ሳሙኤል ቡድን ከዚህ ቀደም ለማድረግ ዝቶ እንደነበረው ያለ መሪ አባት በራሱ መሰብሰቡን ተግባራዊ እንደሚያደርግ ይጠበቃል። በግንቦቱ ሲኖዶስ ስብሰባ መጨረሻ ላይ ቅዱስነታቸው በማኅበረ ቅዱሳን ተረቆ የመጣውንና ማኅበሩ በቤተ ክርስቲያኒቱ ከመጠቀም በቀር ለቤተ ክርስቲያን ያደረገው ነገር ባለመኖሩ ስለማኅበሩ የተጻፈውን ትክክለኛ ያልሆነ ነገር አላነብም በማለታቸው፣ የእነ«አባ» ሳሙኤል ቡድን «እርሶ ካላነበቡ የራሳችንን ተወካይ ወክለን መግለጫውን እንዲነበብ እናደርጋለን» በማለት ዝቶ የነበረ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን በመጨረሻም ቅዱስነታቸው መግለጫውን አነበቡ። የማኅበሩ ሰዎችም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ስለማኅበራችን ይነገርልናል ብለው ቢጠብቁም አንድም ነገር ሳይጠቀስ በመታለፉ ቅሬታ ተሰምቷቸው እንደነበር የሚታወስ ነው።  

ይህ በእንዲህ እንዳለ ርእሰ ሀገረ አበዊነ አክሱም ላይ የሀገረ ስብከቱን ሊቀጳጳስ አንፈልጋቸውም ይነሱልን በሚል የቀጠለውን ውዝግብ ተከትሎ አጣሪ ኮሚቴ ተሰይሞ ወደ ስፍራው ሄዶ የነበረ ቢሆንም አጣሪ ቡድኑ ተቃውሞ ገጥሞታል። አቡነ ጎርጎርዮስ የጉድ ሙዳዩ አባ አብርሃምና ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ አጣሪ ሆነው የሄዱ ሲሆን፣ በተለይ አባ አብርሃም ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። «እናንተ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስና በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት ጮቤ የረገጣችሁ አይደላችሁም እንዴ? አሁን ልትወሩን ነወይ የመጣችሁት? በተለይ እርስዎ (አባ አብርሃምን ነው) ታቦተ ጽዮን እዚህ የለችም እያሉ ሲያወሩ የነበሩ አይደሉም? አሁን ምን ሊሰሩ መጡ?» ብለዋቸዋል። በዚህ ጊዜ አቡነ ጎርጎርዮስ ማልቀሳቸውን ምንጮቻችን ተናግረዋል። ማኅበረ ቅዱሳን በጳጳሳቶቹ በኩል ያስወሰነውንና አሁን ያሉትን ንቡረእድ በማንሳት በምትካቸው የማኅበረ ቅዱሳን ቀኝ እጅ የሆኑትን ንቡረእድ ዮሐንስን ለማስቀመጥና በሌሎች ሀገረ ስብከቶች የለመደውን አክሱም ላይ ለመፈጸምና ተጠቃሚ ለመሆን የያዘው እቅድም ከሽፎበታል።

በርእሰ ሀገረ አበዊነ አክሱም ለተነሳው ውዝግብ በአስማትና በድግምት ሥራ የሚታወቁት የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ አባ ሰላማ ሲሆኑ በየመንደሩ «አጠምቃለሁ» እያሉ በሚፈጽሙት ያልተገባ ተግባር ምክንያት መሆኑ ሲታወቅ «ሀገረ ስብከታችንን ለቀው ይውጡልን» የሚለው ተቃውሞም ከዚህ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። የአክሱም ቤተክህነት ሃላፊዎች ለአጣሪው ቡድን በሰጡት ምላሽ «እንዲያውም የአክሱም ሊቀጳጳስ ፓትርያርኩ ነውና ከዚህ በኋላ ሌላ ጳጳስ አንፈልግም በቦርድ እንተዳደራለን» ማለታቸው ተዘግቧል። ጉዳዩ ወደአላስፈላጊ ግጭት ውስጥ እንዳይገባ በማሰብ የዞኑ መንግስት አካሎችም የአባ ሰላማን መነሳት እንደሚደግፉ ምንጮቻችን ገልጸዋል። በተያያዘም የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ዛሬና ነገ (ቅዳሜና እሑድ) በአባ ሰላማ ቤት ስብሰባ ላይ መሆናቸው ታውቋል።

ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በሕይወት እያሉ በግንቦት 2004 የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ የአክሱም ጉዳይ ተነስቶ የነበረ መሆኑ ሲታወስ፣ የማኅበረ ቅዱሳን ብሎጎች አባ ሰላማ እንደ ተበደሉ ቅዱስነታቸው ደግሞ እንደበደሉ አድርገው ሲዘግቡ ነበር። እውነታው ግን አሁን ይፋ እየሆነ ነው። ሕዝቡም አባ ሰላማ ጓዛቸውን ለቀው ይውጡልን እያለ ነውና። በዚህ ወቅት ታዲያ እነዚያ ብሎጎች በጉዳዩ ላይ ዝምታን መርጠዋል።

18 comments:

 1. Please keep playing to the Almighty GOD He will fight against them. Our shelter is our God we are the winners of battle of the enemy.

  ReplyDelete
 2. “የአክሱም ሊቀ ጳጳስ መሆን ያለበት ቅዱስ ፓትሪያሪኩ ነው” የተባለው ትክክል ስለሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ የህዝቡን ጥያቄ ሊቀበለው ይገባል እንላለን፡፡

  ReplyDelete
 3. ቴዎድሮስ፡- ከዚያ አንድ ነገር ነው የምፈልገው ቲቢ ጆሽዋ የሚያንቀሳቅሰው ፀጋ የፈወሰው ሰው አይመለስበትም በጣም ብዙ አገልግሎቶቹ ያስወጣው ወንድ አጋንንት አይመለስም፡፡ ይሄ የቲቪ ጆሽዋ አገልግሎት ነው፡፡ እኔ በራሴ አገልግሎት ቲቪ ጆሽዋን ብመስል ደስ ይለኛል፡፡ አንድ የወሰንነውና ያባረርነው ነገር ባይመለስ ጥሩ ነው፡፡ ግን ኢየሱስ እንደሚመለስ ይናገራል ሰባት እጥፍ ፈልጎ እንደሚገባ ይናገራል፡፡ ስለዚህ አባትም አምላክም ባልም ሆነን ብንከላከል ምን አለበት? ሰዎች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሙላት መድረስ አለባቸው፡፡ እስካልደረሱ ግን እንደ አባትም ባልም ሆነን መጠበቅ አለብን፡፡

  ጌሤም፡- መንፈሳዊ ሶኬት የምትለው ነገርስ ስለማብሪያና ማጥፊያ ንገረን?

  ቴዎድሮስ፡- አምስቱ ስሜቶች ማብሪያና ማጥፊያ ናቸው፡፡ ሰዎች ከቸርቹ ስለወጡና ቸርቹ ላይ የማጥፋት ዘመቻ ስለፈለጉ እንጂ ሳይገባቸው ቀርቶ አይደለም፡፡ ቡዳ የሚባል መንፈስ አለ ሰይጣኑ በአይኑ ነው የሚበላው ቡዳ በአይኑ ከበላ የእግዚአብሔር መንፈስ በአይን አይሰራም እንዴ? ያም መንፈስ ነው ይሄም መንፈስ ነው፡፡ ዋናው ከሚሰማው ውስጥ ኮንታክት አድርጎ ራዕይ ሊያይ ይችላል፡፡ እነዚያ አምስቱ ማንም ሰው ከመንፈሳዊው አለም እኔ ወደ እርሱ የምሄድበት በር ማለት ነው፡፡ አንዳንድ ሰው ተክለህ አይነሳም እጅ ትጭንበታለህ ደብል ኮንታክት ነው፡፡ በድምፅ ትፀልያለህ ደረት እመታለሁ በዚያ መሀል እኔ መናፍስቶቹ አለቅም ሲሉ አንዳንዴ እግር እመታለሁ ጣቴን ጆሮላይ እከታለሁ አደባባይ ላይ በማገለግልበት ሲስተም ውስጥ ነው የምሰራው፡፡ በጨለማ ብቻ ይሰራል ብለው አወሩ እንጂ እኔ በአደባባይ ነው የማደርገው፡፡ አንድ ቦታ እመታለሁ እኔ የማየው ራዕዩን ዓለም ነው እነኚህ ሁሉ የከሰሱኝ መድረክ ላይ የመሰከሩ ናቸው፡፡

  ጌሤም፡- አንድ እህት ባለፈው መፅሔት ላይ ስትናገር ብዙ ጊዜ ከባሌ ጋር ግንኙነት ሳላደርግ የቆየሁበት ምክንያት አንተ በህልምዋ በመንፈስ ግንኙነት ስለምትፈፅም ይሄንንም ጠይቃህ ይሄ ከባድ ነገር አይደለም ፀጋዬ ከአንቺ ጋር ህብረት ሲያደርግ ነው ከከበደሽና ምናልባት ካልደረስሽበት አነሳልሻለሁ ብለህ እንዳነሳህላት ተናግራለች፡፡ ምንድን ነው?

  ቴዎድሮስ፡- አዎ በጊዜው አንድ ጥያቄ አይደለም ያመጣችው አስር ጥያቄ ነው፡፡ ስለመንፈሳዊ ሽፋን በተመለከተ ጥያቄዎች አመጣች፡፡ በጊዜው ሴሚናር ስሰጥ ሁሉንም መልስ እሰጥበታለሁ ብያለሁ፡፡ ከባልዋ ጋር አስታርቄ ቤቷ ከመመለስ ውጭ እርሷ ስለምትለው አላውቅም አሁን ተወናጭፋ ወጥታለች

  ReplyDelete
  Replies
  1. ያልገባኝ ጭውውት ስለሆነ ፣ እባክህ የምፈታበትን ጫፉን አስይዘኝ ፡፡

   Delete
  2. ውሃ ይሙላብህ!!!!!

   Delete
  3. Thanks brother. They seem as innocent when they complain about EOC members.But People of pentes are also such kind. do u read also there he put every body in doggy style & he says" every body say, ye Tewodros tsega yigbabign" I laughed so many days with this guy. The protestants culture is more prone to do non christian things than EOC. Since no dogma & kenona there.

   Delete
  4. ምንድነው ንግሩ ወሬው ንፍሮ ቆሎ ሆነብን ከጽሁፉ ጋር ምንድነው ግንኙነቱ ከላይ ካለው ጋር ስብከት ነው ነጥቡ አልግባኝም

   Delete
 4. that's thru they are right እናንተ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስና በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት ጮቤ የረገጣችሁ አይደላችሁም እንዴ? አሁን ልትወሩን ነወይ የመጣችሁት? በተለይ እርስዎ (አባ አብርሃምን ነው) ታቦተ ጽዮን እዚህ የለችም እያሉ ሲያወሩ የነበሩ አይደሉም? አሁን ምን ሊሰሩ መጡ?»

  ReplyDelete
 5. good job, ewunetu gena yewetal, egeziabeher serawu talak new.all bishops need to be good leaders not a cheaters.

  ReplyDelete
 6. ARE YOU GUYS FROM ETHIOPIAN ORTHODOX CHURCH OR AGAINST ?TO ANSWER THIS QUESTION PLESASE TAKE YOUR TIME LESSON TO YOUR HEART BE HONEST TO YOURSELF. THE QUESTION IT'S HARD UNLESS YOU LAY !SO REMEMBER TELL ME THE TRUTH?

  ReplyDelete
 7. YES. WE ARE. We are the believers and followers of the Ethiopian Orthodox Tewahdo Chruch. Our Fathers who live in Axmu had done a wonderful job. Believe it or not, Aba Abrhan, Aba Samuel, Aba Lukas, aba selam, so on, they are not true bishops but they are the enemies of the Church as well as the enemy of the true scollars of the church. We really appreciate the government of Tigray, he is right. The voice of the fathers of Axum must be heard.

  ReplyDelete
 8. አቡነ አብርሃም ማለት የእናንተ ወገን ናቸው እንዴ? ስለምን ምክንያት ታቦተ ጽዮን የለችም ማለትደፈሩ ወይስ እንደ ተለመደው ስማቸውን ለማጥፋት አቅዳችሁ ነው ይህን የምታስነብቡን ? ከዚህ ቀደም ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብና ከታሪክ አንጻር በማለት ታቦተ ጽዮን ኢትዮጵያ ውስጥ የለችም የሚል የድምዳሜ ጽሁፍ አስነብባችኋል ፡፡ ታድያ አንድ ወገን ሆናችሁ ሳለ ዛሬ ስለምን መገፋፋት ፈለጋችሁ ወይስ የአቋም ለውጥ አምጥታችኋል ማለት ይሆን ? እንዲያ ማለትስ ዛሬ ስህተት መሆኑን ከማን ተማራችሁ ፡፡ አቡነ ጳውሎስ ሳይቀሩ አለችን ብለው በአደባባይ የመሰከሩትን እናንተ የታቦት ተቃዋሚ ስለሆናችሁ አንዴ በቁጥር ፣ አንዴ በሌላ ምክንያት እየደረደራችሁ ብዙ ጽፋችኋል ፡፡ ሃሳባችሁን አርማችሁ ከሆነ መታደስ ማለት እንዲህ ነው ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Very interesting comment!! Yes these people are contradicting themselves. I clearly remember what the bloggers said about Tabote Tsion. They claimed we don't have it at all and now they are saying it does exist. What a contradiction!!! Shame on the blogger.

   Delete

  2. አቡነ አብረሃም ከአሁን ቀደም ታቦተ ጽዮን የለችም ብለው በመናገራቸው አሁን የአክሱም ነዋሪዎች እንደነቀፉዋቸው ነው ደጀ ሰላም የዘገበችው፡፡
   ደጀ ሰላም ከአሁን ቀደም ስለታቦተ ጽዮን የመጣችበትን ዘመንና የአመጣጥዋን ሁኔታ አስመልክታ ያቀረበችው ሀተታ ግን በጣም በጣም ትክክል ነው ምክንያቱም ስለታቦተ ጽዮን የሚወራው ተረት ተረት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይጋጫል፡፡
   ታቦተ ጽዮን በእኛ ዘንድ ትኑር አትኑር ፈጣሪ ነው የሚያውቀው፤ ስለታቦተ ጽዮን የሚወራው ግን ትክክል አይደለም፤ ታሪክ /ገድል/ ጸሐፊዎች አስተካክለው ሊጽፉት ይገባል፤ በጣም የሚያሳዝነው ግን የተዋህዶ ልጆች ዕውነት ሲነግሩዋችሁ ተሃድሶ መናፍቅ ጴንጤ እያላችሁ መንጫጫት አይገባም፡፡

   Delete
  3. ባለ AnonymousNovember 15, 2012 9:55 PM አስተያየት
   - ደጀ ሰላም አቀረበች ያልከውን መረጃ ትክክል የምትልበት ምክንያት በምላስህ ቀምሰህ ነው ወይስ በዘመኑ አንተ ነበርክና ነው ምስክር ለመሆን የበቃኸው ?
   - ስለ ታቦተ ጽዮን የሚወራው ግን ትክክል አይደለምስ ለማለት ምክንያትህ ምንድር ነው ?
   - ራስክን በራስህ ደስ የሚልህን ስም መሰየም ስለፈለግህ "የተዋህዶ ልጆች ዕውነት ሲነግሩዋችሁ ተሃድሶ መናፍቅ ጴንጤ እያላችሁ" ብለህ አንተው ጻፍክ እንጅ ፣
   ማንም አስተያየት ሰጭ እነዚህን የጻፍካቸውን ስሞች አልተጠቀመም ፡፡ አባ ሰላማዎች ከዚህ በፊት የሚያራምዱትን አቋም ቀይረው ቢሆን መታደስ ማለት ይኸ ነው ተብሏል ፡፡ የቤተ ክርስቲያን ዶግማና ቀኖናን እናድስ ከሚሉ የራሳቸውን የተሳሳተ አመለካከት ሲያቃኑት ቃሉን በአግባብ መጠቀም ይቻል ይመስለኛል

   Delete
 9. ብጹዕነታቸው በመደበኛ የአቃቤ መንበረ ፓትሪያሪክ ተግባራቸውን እያከናወኑ ነው


  · ብጹዕ አቡነ ናትናኤል ቅዳሴ ቤት ለማክበር ወደ አገር ስብታቸው ሄደው መንበረ ፓትሪያሪክ ባለፈው እሁድ ተመልሰው የአቃቤ መንበረፓትሪያሪክ አገልግሎታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ።
  · በተሃድሶ መናፍቅነት የሚጠረጠረው መምህር አእመረ አሸብር ከስብከተ ወንጌልና ሃዋሪያዊ መምሪያ ኃላፊነቱ ተነስቷል
  · የቤተክረስቲያኒቱን ተቋማዊ ሰላም በማያናጋና ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ቤተክርስቲያኒቱ ለማደረግ ያሰበቸውን አስተዳደራዊ ለውጥ የሚያደናቅፉና ቤተክርስቲያኒቱን በከፍተኛ ሁኔታእየጎዱ የሚገኙ ሓላፊዎች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ መውሰድ እንደሚቀጥል ይጠበቃል።

  ዝርዝሩ፡-
  በተሃድሶ መናፍቅነት የሚጠረጠረው መምህር አእመረ አሸብር ከስብከተ ወንጌልና ሃዋሪያዊ መምሪያ ኃላፊነቱ ተነስቶ የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ መልዓከ ሰላም አምደ ብርሀን ተመድበዋል። በተለይ ባለፈው ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ “ ያሬድ ድጓ የደረሰው ወንጌል ተምሮ ነው፣ ለወንጌል አገልግሎት ቅድሚያ መሰጠት አለበት፣ ወንጌል ትኩረት አልተሰጠውም ……” በተለይ ደግሞ ሰባኪያን በተመለከተ በተናገረው ንግግር ህገወጥና ተሃድሶ የሚባሉትን በመምሪያው ስር ከሆኑ ፈቃድ በመስጠት ወደ ህጋዊ መስመር የማስገባት ሥራ እንደስራና ወደ ፊትም አጠናቅሮ እንደሚቀጥልበት ብጹዓን ሊቃነጳጳሳት ባሉበት መናገሩ አሰላለፉ ከማን ጎን እንደሆነ ግልጽ እንዳደረገ ተነግሮለታል። በተለይም እንደ አሰግድ ሳህሉ ዓይነት የሙሉ ወንጌል እምነት ድርጅት አባል ህጋዊ ከለላ በመስጠትና ኦርቶዶክሳውያን ደግሞ በማጉላላት የሚታወቀው መ/ር አእመር አሸብር ችግሩ ጎልቶ ስለወጣ ከኃላፊነቱ እንዲነሳ ተደርጎል።

  አቃቤ መንበረ ፓትሪያሪክ አባ ናትናኤል ወደ አገረስብከታቸው አርሲ - አሰላ አዲስ ቅዳሴ ቤት ለማክበር መሄዳቸውን ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ አኅጉረስብከት ሥራአስኪያጆች ምደባ ወቅት በአቃቤ መንበረፓትሪያሪኩና ሥራአስፈጻሚ ኮሞቴው መካከል ተፈጥሮ የነበውንና መጨረሻ ላይ ስምነት የደረሱበትን መጠነኛ የሃሳብ ልዩነት በማስታከክ የተሃድሶ መናፍቃን ልሳን የሆኑት እነ አባሰላማ ድረገጽ ብጹነታቸው “ስራአስፈጻሚ ኮሚቴውን አልሰበስብም” ብለው ወደ አገስብከታቸው ሄዱ በማለት ያለቸውን ተምኔት ጽፏል። ብጹነታቸው ወደ አገስብከታቸው የሄዱት አዲስ ቅዳሴ ቤት ለማክበር እንዲሁም የማኅበረቅዱሳን አሰላ ማዕከል ጠቅላላ ጉባኤ ለመገኝት እንደሆነ ምንጮቻን ተናግረዋል። ከባለፈው እሁድ ጀምሮ ብጹዕነታቸው በመደበኛ የአቃቤ መንበረ ፓትሪያሪክ ተግባራቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ።

  የቤተክርስቲያኒቱን ወቅታዊ ሁኔታ የሚከታተሉ ወገኖች ብጹዓን አባቶች ቤተክርስቲያን የቆመችው መስቀለኛ መንገድ መሆኑን መላልሰው እንዲያስቡ እየጠየቁ ነው። ብጹዓን አባቶች የሌላ ሦስተኛ አካልን ጣልቃ ላለማስገባት እየከፈሉት ያለው ሰማዕትነትና እያሳዩት ያለው ጥብዓት ልብ የሚነካ ቢሆንም የሚኖሩ የሃሳብ ልዩነቶች በሃይማኖትና በመካከር ለመፍታት ካልተቻለ ወደ መከፋፈል ሊወስዱ የሚችሉ ምልክቶች እየታዩ መሆናቸው ጉዳዩን አሳሳቢ ያደርገዋል። ቤተክርስቲያን ባለፉት ሃያ ዓመታት የገጠሟትን ችግሮች ለመፍታት የተገኘውን ይህን ወርቃማ ጊዜ በአግባቡ አለመጠቀም በእግዚአብሔርም በታሪክ ፊት ተወቃሽ ያደርጋል። ለዚህም በ2001 ዓ.ም ቤተክርስቲያን ገጥሟት የነበረውን መልካም አጋጣሚ የጨለማው ሲኖዶስ አባላት አባቶችን በመከፋፈል መንግስት ጣልቃ የሚገባበት እድል አግኝቶ ፈንጥቆ የነበረው ተስፋ እንዲሁ እንደጠፋ የምናስታውሰው ነው።

  ዛሬም በቤተክርሰቲያናችን የቆመችበት መስቀለኛ መንገድ ብጹዓን አባቶች በማስታወስ፣ ለመንጋው የሚጨነቅ ትጉህ እረኛ ለመውለድ ምጥ ላይ የምትገኘውን ቤተክርስቲያን ደገኛ ሀኪም በመሆን ሊያገላግሏት ይገባል። ለምጣዱ ሲባል ችግሮችን በጽናትና በስፍሐ ልቦና ማለፍ ይጠይቃል። በተለይም በአሁኑ ሰዓት የቤተክርስቲያኒቱ ተቋማዊና መንፈሳዊ ውድቀት እንዲፋጠን የሚፈልጉት ከውስጥም ከውጭ ያሉ አጽራረ ቤተክርስቲያን በአባቶች ዙሪያ ማንጃበባቸው ፣ የምትፈጠር ጥቂት ክፍተት ወደ አልተፈለገ ግርግር በማምራት የሚገባበት ቀዳዳ ያጣውን መንግስትን እድል እንዳይሠጠው ተፈርቷል።

  ለዚህ ማሳያ የሚሆነው በብጹዕ አቡነ ሣሙኤል ሰብሳቢነት የሚመራው ህገ ቤተክርስቲያን ማሻሻያና የፓትሪያሪክ መምረጫ ቋሚ ህግ አጥንቶ እንዲያቀርብ በቅዱስ ሲኖዶስ የተቋቋመው ኮሚቴ ስራ ቢጀምርም አንድ ሊቀ ጳጳስና የማኅበረቅዱሳን የህግ ባለሞያዎች እየተሳተፉ እንዳልሆነ ምንጮቻችን ዘግበዋል። ቅዱስ ሲኖዶስ ለኮሚቴው በአባልነት የመረጣቸው አንድ ሊቀጳጳስና የማኅበረቅዱሳን ህግ ባለሙያዎች ለምን መሳተፍ እንዳልፈጉ ለጊዜው ባይታወቅም ኮሚቴው በተቀመጠለት የጊዜ ገድብ የተሰጠውን ስራ ማጠናቀቁ የሚያሰጋ ሲሆን ሁሉም የኮሚቴው አባላት ባልተሟሉበት የሚሰራውን ስራ ታማኝነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባዋል። ይህንን ችግርም አቃቤ መንበረ ፓትሪያሪኩ ከሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ጋር በመሆን እንደሚፈቱት ይጠበቃል።

  ReplyDelete
 10. Still you are playing with mud lie kids.WHEN IS THE TIME THAT WILL GROW? YOU ARE ALWAYS DIMINISHING.SORRY.

  ReplyDelete
 11. I am not a supporter of any groups ,I am just an Ethiopian Christian and follower of Ethiopian Orthodox church. I suspect that this blog has its own hidden agenda. We all know that Ethiopian Orthodox church has facing many challenges , not only with this kind of so called blog but also by Yodit Gudit and Giragn Mohammed. And that was a direct attack from unbelievers.but this blog is really much worse than those all combined in working hard for the disintegration and failure of our church.

  ReplyDelete