Monday, November 12, 2012

የሟቹ ብፁእ አቡነ ሚካኤል አስከሬን ወጥቶ እንዲመረመር ፍርድ ቤት ትእዛዝ አስተላለፈ

ሲኖዶስ «የአባ ሚካኤል ጉዳይ የሓይማኖት ጉዳይ ነውና ፋይሉ ይዘጋ» ሲል ያቀረበው መቃወሚያ ውድቅ ተደርጓል
ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ዕለት የልደታ ምድብ ባስዋለው ችሎት የብፁዕ አቡነ ሚካኤል አስከሬን ተቆፍሮ ውጥቶ የዲኤንኤ ምርመራ እንዲካሄድና ውጤቱ ለህዳር 25/2005 እንዲቀርብ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ የሟቹ ብፁእ አቡነ ሚካኤል ልጅ የዮሀንስ ሚካኤል የወራሽነት ጉዳይ በፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቶ በስር ፍርድ ቤት ዮሐንስ ያቀረበው ማስረጃ የእነ «አባ» ሳሙኤል ቡድን ካቀረበው መከላከያ ይልቅ አሳማኝ ሆኖ በመገኘቱ ውሳኔ ያገኘና ልጅነቱ የተረጋገጠ መሆኑን ከዚህ ቀደም ዘግበን የነበረ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡ ጉዳዩ በይግባኝ ተይዞ ክርክሩ ቀጥሎ የነበረ ሲሆን የተለየ ማስረጃ ማቅረብ ያልቻለውና ጉዳዩን አፍኖ ማስቀረት የፈለገው የእነ «አባ» ሳሙኤል ቡድን ፋይሉን ለማዘጋትና ክሱን እንዲቋረጥ ለማድረግ ያልቆፈረው ድንጋይ አልነበረም ተብሏል፡፡ ለዚህም ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ህልፈት በኋላ አለሁ አለሁ ማለታቸውን በእጥፍ የጨመሩትና ሁሉንም ነገር እኔ ካላማሰልኩ የሚሉት «አባ» ሳሙኤል በግል ከመንቀሳቀስ አንስቶ የሲኖዶሱን አባላት አስተባብረው ጉዳዩ የሃይማኖት ነውና ፍ/ቤት ሊመለከተው አይገባም የሚል ደብዳቤ እስከማጻፍ የደረሰ ሴራ ሲጎነጉን ከርመዋል። በልደታ ምድብ ችሎት ጉዳዩን የተመለከተው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በ29/2/2005 ዓ.ም በዋለው ችሎት የአባ ሚካኤል አስከሬን ወጥቶ የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ እንዲደረግና ውጤቱ ለህዳር 25 እንዲቀርብ ውሳኔ ማስተላለፉ ታውቋል፡፡
ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ከማስተላለፉ በፊት ቀደም ሲል እንደዘገብነው ዮሐንስ የአባ ሚካኤል ልጅ መሆኑን በበቂ ማስረጃና ምስክር በፍርድ ቤት ያስወሰነ ቢሆንም ከሐሙስ እለቱ የፍርድ ሂደት ቀደም ብሎ «አባ» ሳሙኤልና ማንያዘዋል  የቤተክህነት ሰራተኞችን ፒቲሽን በማስፈረም ፋይሉን ለማዘጋት የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ሙከራ አድርገው እንደነበርና በጉዳዩ ላይ የቤተክህነት ሰራተኞች ለሁለት እንደተከፈሉና የታሰበው ሰልፍም ሳይካሄድ እንደቀረ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሰልፉን መክሸፍ ተከትሎ የግለሰብ የመብት ጉዳይ ሆኖ በፍርድ ቤት የተያዘውንና ክርክር ሲደረግበት የቆየውን ጉዳይ ወደሲኖዶስ በመውሰድ የሃይማኖት ጉዳይ በማስመሰልና ውሳኔ በማሳለፍ “ጉዳዩ የሃይማኖት ስለሆነ ፋይሉን እንዲዘጋ” ሲኖዶሱ ይወስንና በደብዳቤ እንዲጠይቅ ተደርጓል፡፡ ጠበቃም አቁሞ ተከራክሯል፡፡ ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን ደብዳቤ አልተቀበለውም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ «ጉዳዩ የግለሰብ መብት እንጂ የሃይማኖት ጉዳይ አይደለም» የሚል ነው። ዮሐንስ ልጅ ስለሆንኩ ወራሽ ነኝ የሚል በማስረጃ የተደገፈ ጥያቄ አንስቷል፡፡ ተቀባይነትም አግኝቷል፡፡ አንድ ሰው ወላጁን የማወቅ መብት አለው፡፡ ዮሐንስ ልጅ ነኝ ሲል ተከራክሮ ሲረታ ውሳኔውን የተቃወሙ ሰዎች ይግባኝ ጠይቀዋል፡፡ ጉዳዩም «እወርሳለሁ - አትወርስም» የሚል ነበር፡፡

ዮሐንስም «ልጅነቴ በበቂ ማስረጃዎች የተረጋገጠ ቢሆንም ተከራካሪዎቼ አልቀበል ካሉ ልጅነቴን ማረጋገጥ በሚቻልበት በማንኛውም መንገድ በዲኤንኤ ጭምር የማረጋገጥ መብቴን ፍርድ ቤት ሊያስከብርልኝ ይገባል፤» የሚል ጥያቄ ባቀረበው መሰረት ፍ/ቤቱ ልጅነቱን ለማረጋገጥ የዲኤንኤ ምርመራ ተደርጎ ውጤቱ ለኅዳር 25 እንዲቀርብ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ በ«አባ» ሳሙኤል መሪነት ሲከራከሩ የነበሩት የአባ ሳሙኤል የስጋ ዘመዶች በደረቁ «ልጅ አይደለም፤ እርሳቸው እኮ ጳጳስ ናቸው፤ ጳጳስ ደግሞ መውለድ አይችልም» ከሚል መከራከሪያ በቀር ያቀረቡት እዚህ ግባ የሚባል ማስረጃ አልነበረም፡፡  ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ለመቃወም ቢሞክሩም፣ እንደተጠቀሰውም ከቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ አካል ከቅዱስ ሲኖዶስ የተጻፈ ደብዳቤ በማቅረብ «ጉዳዩን ፍርድ ቤት አይይብን» የሚል ሐሣብ ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱን የሚያሳምን ሆኖ አልተገኘም፡፡ ሰዎች ሁሉ «ጳጳስም ቢሆን» በህግ ፊት እኩል በመሆናቸው የአባ ሚካኤል አስከሬን ተቆፍሮ እንዲወጣና የዲኤንኤ ምርመራ እንዲደረግና ውጤቱ በተጠቀሰው ቀን እንዲቀርብ ወስኗል፡፡ ይህ ውሳኔ እስከ ህዳር 25/2005 ድረስ ተፈጻሚ ካልሆነ ተከላካዩ የእነ «አባ» ሳሙኤል ወገን ዮሐንስን ልጅነት እንደተቀበለ ተቆጥሮ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተፈጻሚ እንደሚሆን በውሳኔው ላይ ተመልክቷል፡፡ ሲኖዶሱም ጉዳዩ የሃይማኖት ባለመሆኑ እንደማይመለከተውና ከዚህ በኋላ በጉዳዩ ላይ ጥያቄ ማቅረብ እንደማይችል ትእዛዝ ተላልፏል፡፡ የመብትን ጉዳይ የሃይማኖት ጉዳይ አድርጎ ለሲኖዶስ ያቀረበው የ«አባ» ሳሙኤል ቡድን በዲኤንኤ ምርመራው ላይ ደባ እንዳይፈጽም አስፈላጊው ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ብዙዎች ይመክራሉ፡፡

የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተከትሎ የእነ «አባ» ሳሙኤል ወገኖች ከፊታቸው ሁለት የማይፈልጓቸው አማራጮች ተደቅነዋል፡፡ የመጀመሪያውና ትክክለኛ የሚሆነው አማራጭ የዮሐንስን ልጅነት አምኖ ወራሽነቱን መቀበል ነው፡፡ ይህ ግን ሊወርሱ የቋመጡለትን የአባ ሚካኤልን ዳጎስ ያለ ገንዘብና ሀብት የሚያስቀርባቸው፣ መሰሎቻቸውን ጳጳሳትም ተአማኒነት የሚያሳጣ ይሆናል፡፡ ሁለተኛው ዮሐንስ ልጅ አለመሆኑን በተጨባጭ ማስረጃ ማስተባበል ነው፡፡ ለዚህ የቀረው ማስረጃ ደግሞ የዲኤንኤ ምርመራ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የከፋው አማራጭ  ነው፡፡ ለሁሉም ኅዳር 25 ቀን መልሱን ይሰጣል፡፡

ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስነታቸው ጊዜ ጀምሮ የካህናትና ዳቆናትን የመብት ጥያቄዎች በመደፍጠጥ የሚታወቁትና የመብት ጥያቄዎችን የሃይማኖት ጥያቄ በማድረግና መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም የሚለውን ህገመንግስታዊ አንቀጽ በተሳሳተ መንገድ በመጥቀስ የተከፈቱ የክስ መዝገቦችን እያዘጉ ብዙዎችን ሲያሰቃዩ የኖሩት «አባ» ሳሙኤል ለዮሐንስ የመብት ጥያቄ ሃይማኖታዊ ካባ ደርበው መቅረባቸው ብዙዎችን አሳዝኗል፡፡ እኚህ ሰው ሌላ ዘዴ የላቸውም ወይ እስከማለትም አድርሶአል፡፡ አባ ሚካኤል ያልካዱትንና በሕይወት እያሉ ዮሐንስ ልጄ ነው በማለት ገንዘብ እየቆረጡለት ያሳደጉትንና ያስተማሩትን የአብራካቸውን ክፋይ ዮሐንስን እነ አባ ሳሙኤል መካዳቸው የተደበቀ የእነርሱ ጉድ እንዳይወጣና ተመሳሳይ ጥያቄ እንዳይቀርብባቸው ከወዲሁ ለማለባበስ አስበው ያደረጉት መሆኑን ብዙዎች እየተናገሩ ነው፡፡ በዮሐንስ የተጀመረው ይህ የልጅነት ጥያቄ ወደሌሎች ጳጳሳት እንዳይዛመትም ተፈርቷል፡፡ ከዚህ ቀደም እንደገለጽነው በዚህ ጉዳይ ተመሳሳይ ጥያቄ ሊነሳባቸው የሚችሉ «ጳጳሳት» እንዳሉና አባ ሉቃስ፣ አባ አብርሃም፣ አባ ዲዮስቆሮስ፣ የሚጡና የምስራቅ ባል «አባ» ሳሙኤል በምሳሌነት እንደሚጠቀሱ ይታወቃል፡፡

             

22 comments:

 1. My Goodness!!! Save us Lord. it is so bad and awful. I am really disappointed. Why Aba Samuel have been doing like this? If Yohans is the son of Aba Michael, of course, he has a right to know about his father and anything that belongs to Aba Michael belongs to the children of Aba Michael. The judge is right. But we have to know the act of Aba Michael is different from our belief. If he did that, he had done it against himself and his God. So, please!! we do not believe in person, but we believe in the Almighty God. On the other hand, it is good for the church, maybe, from now on, they bishops will learn from this. Anyway, may God Bless our true faithful fathers of the Church.

  ReplyDelete
 2. wayo wayo wayo gooooood new woyo ........

  ReplyDelete
 3. Yihinin yetsafkews yeyetignaw "papas" lij neh? Ye "Aba Diabilos?"

  ReplyDelete
 4. it is really a shame for aba samuel. what kind of person is he?

  ReplyDelete
 5. ጉድ በል ጎንደር እንዲህ ነው ቅሌት አሳ ገርጓሪ ዘንዶ ያወጣል የሚባለው እዲህ ያለው ሰው አኮ ነው ምናለ ይሄ ሳሙኤል የሚባል ክፉ “መነኩሴ” (አግብቶ ምንኩስና ባይኖርም ነኝ ስለሚል ነው) አርፎ ቢቀመጥ

  ReplyDelete
 6. ማኅበረ ቅዱሳን እና ወዳጆቹ ጳጳሳት አንድ የማይጠረጠሩበት ጉዳይ አለ፡፡ አሱም የአመንዝራነት ሃህሪያቸው ነው፡፡ ሳሙኤል ሉቃስ ዲዮስቆሮስ አብርሃም(ራጉኤል አካባቢ የሚጠራበት ስሙ ቹቹ) እና ሌሎቹም የነሱ ወዳጅ ጳጳሳት ቀሚስ ባዩ ቁጥር ቀሚሳቸው እየወለቀ የሚቸገሩ ናቸው፡፡ ከማኅበረ ቅዱሳን ሰዎችም በላቸው ደጀኔ አባይነህ ዳንኤል ክስረት(የዳኒ እማ ተዉት አርርቆ መውለድን ጥቅም መጀመሪያ እንደሰማ አሪፍ ነኝ ብሎ ያደረገው ነገር አንድ ጎጃም አነድ ከአዲስ አባባ መውለድ ነበር) በኃላ የአራርቆ መውለድ ትክክለኛ ትርጉም አንድ ከተማ ላይ ከተለያዩ ሴቶች ወውለድ ነው ብሎ አዲስ አበባ ከዚህችም ከዚያችም ወውለድ ጀመረ፡፡ አሁን ደግሞ በየሀገሩ እየዞረ ስለሆነ ማን ያውቃል እዛም እዛም ይኖረው ይሆናል ጊዜ እስኪገልጠው እንጠብቃለን፡፡) ማንያዘዋል ደግሞ ወንድ ወደድ(Gay) ነው ይባላል፡፡
  በዚህ ከቀጠሉ አሁን በጀመሩት የቀደመውን እውነት በርዞ እና ከልሶ ቤተክርስቲያንን ወደ ራሳቸው አስተሳሰብ መግፋት አካሄድ የተነሳ ልክ መዝፈን ሀጢአት አለመሆኑን በስመአ ጽድቅ ጋዜጣ እንዳስነበበቡን ዝሙትም መፈጸምም ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው ይሉን ይሆናል፡፡ መጠበቅ ነው አቦ
  የአባ ሚካኤለን ልጅ ግን በጣም አድንቄዋለሁ፡፡ በርታ ወንድሜ መብትህን ለማንም ከንቱ አዳሪ አሳልፈህ አትስጥ

  ReplyDelete
  Replies
  1. I don't think Dn. Daniel will do like u mention. But it is good for Ethiopia, to have so many children of him that have sharp mind like him.

   Emayreba chinklat kemitelalef...

   Delete
 7. የቀን ማስተካከያ
  ቀኑ ሀሙስ ከቀኑ 3፡30 ላይ ነው፡፡ ሌላው ዘገባ ሁሉ ግን እውነት ነው፡፡

  ReplyDelete
 8. "ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ከማስተላለፉ በፊት ቀደም ሲል እንደዘገብነው ዮሐንስ የአባ ሚካኤል ልጅ መሆኑን በበቂ ማስረጃና ምስክር በፍርድ ቤት ያስወሰነ ቢሆንም ...." ምንድነው የምትሉት?

  ReplyDelete
 9. Egziooo Egzioo Egzioo mk weyem ms gudachenin endayawetubin belew eyeferuachehu le 100 alekaw lewetaderu dikuna kisena ere sentun neger seyadergulachehw yekoyutin papasat ene aba samuealn enanetew abaselamawoch gudachehun awetetachehu arefachehu egziooooooo yimarenn amen

  ReplyDelete
 10. ሁላችንም ለትምህርት እንዲሆነን እውነት በየትኛውም የጥበብ መንገድ መውጣቷ የሚደገፍ ነው ፡፡ ዘገባችሁን በበጎ ተመልክቼዋለሁ ፡፡ ነገር ግን በመደምደሚያችሁ ላይ ፣ የተገኘውን ውጤት አሜን ብለን እንዳንቀበል "የ«አባ» ሳሙኤል ቡድን በዲኤንኤ ምርመራው ላይ ደባ እንዳይፈጽም አስፈላጊው ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ብዙዎች ይመክራሉ፡፡" የሚል ደንቃራ አስቀምጣችኋል ፡፡ በዚህ አባባል ምን ማስጠንቀቂያ ለመስጠት እንደተፈለገ የገባኝን በግልጽ ልጠቁም ፡፡
  1. ከሬሳው ላይ ናሙና የሚወስደውን ሰው በሌላ ናሙና እንዲቀይር መደለል
  2. ወይንም በሟቹ ስም የሌላ ሬሳ ናሙና ማስመርመር
  3. የዲኤንኤ ውጤት ሰጪውን ክፍል ማሸነፍ /በጣም አስቸጋሪና የማይሞከር ፣ የማይታሰብም ዘዴ/

  ስለዚህም ተበደልኩ የሚል ወገን ተከታትሎ ፣ ነገሮች በአግባቡ እንዲከናወኑ መታገል ይኖርበታል ፡፡ የህግ አስፈጻሚ ክፍሉም ትእዛዙ በትክክል ለመፈጸሙ ምስክር እንዲሆን ጉዳዩን የሚከታተል ቡድን መመደብ ይኖርበታል ፡፡ ይኸ ሁሉ ጥንቃቄ ከተወሰደ በኋላ ግን የሚመጣውን ውጤት ማንኛውም ሰውና ወገን መቀበል የግድ ይኖርበታል ፡፡ እኛም ለወደፊቱ እንማራለን ፡፡

  ReplyDelete
 11. OMG it is a big shame!

  ReplyDelete
 12. Wutetu min bihon des Yilachwal?lene atimelisu lehilenachu gin melis tagegnlachihu?Yemitnafiqut sira yehonebachihu Yesewun wudqt ena Ye betkirsteyan wudqt newu gin sewu besewunetu biwodik Yasaznal gin lihon yichilal betekirsteyann gin ....

  ReplyDelete
 13. yihin keman temarachihu?Ke geta?

  ReplyDelete
 14. Ante woym enante bezemenachihu kezeh yebelte hateyat Yelebachihum?geta silalagaletachihu enge....

  ReplyDelete
 15. በወጣት ዮሐንስ ጉዳይ በጣም ሀሳብ ገብቶኛል ምክንያቱም እነዚህ የነፍሰ ገዳዩ ቡድን ጉዳይ አስፈጻሚዎች ልጁን እንዳያስገድሉት አንድ ታላቅ ጸሐፊ ያለው ትዝ ይለኛል፦ << በአለማችን ላይ እጅግ ታላላቅ ወንጀሎች የሚፈጸሙት በሃይማኖት አባቶችና ሀይማኖተኛ ነን በሚሉ ግለሰቦች ነው>> እባካችሁ ለዚህ ወንድማችን እራሱን እንዲጠብቅ ብትመክሩት በኍላ ከማዘን ያድነናል። ከዚህ በተረፈም የእውነት አምላክ ይጠብቀው እውነቱንም ያውጣለት ሌላ ምን ይባላል።

  ReplyDelete
 16. it is really serprizing

  ReplyDelete
 17. I think you guys (abaselam) are happy since an orthodox bishop is expected to have done this. Why you are always against the church? It is because since you are ...

  I personally agree that if Yohannes is the bishops son, why he didn't legally claim while the bishop was alive?

  ReplyDelete
 18. je what?????egzzio meharene kristos..awyw tewahedo..amlak yitbkish enji abatochachen enkwan Men endenekachw alawkem.. but the thing is they can put down there kob and live like any body else bekobe mekelel lemen asfelge//??GO GET MARRED ITS ALLOWED THE KOB IS ONLY FOR THOS AMLAK LEMERETACHEW.

  ReplyDelete
 19. ABA SELAMA OR ABA WAR ? YOU ARE NOT ORTHODOX SO WHY YOU TALK ABOUT ORTHODOX WHY YOU EVEN TRAY TO PRETEND ? YOU CAN'T GETTING BETTER BY DOING BAD STAFF YOU ARE LAYING, YOU ARE TRAYING TO DIVIDE ETHIOPIAN ORTHODOX CHURCH PEOPLE BUT IT'S NOT GANNA HAPPEN. BECAUSE THE CHURCH BUILT BAY GOD .NOW ARE YOU FIGHING WITH GOD? SO LEAVE US ALOWN DON'T WASTE YOUR TIME JUST LOOK YOURSELF .MATTHEW 16-:-18

  ReplyDelete
 20. “. . . ከእናንተ መካከል ሐጢአት ያልሰራ ቢኖር ይዉገራት . . .” ሁሉን ነካካችሁት ማን ቀራችሁ? ማኅበረ ቅዱሳንንማ የወገባችሁ ቅማል አድርጋችሁት የማትሉት የላችሁም፡፡ ለእናንተ ሥራ የማይመቹ ጳጳሳትን እንኳን ስህተት ተገኝቶባቸዉ ባይገኝባቸዉ መለጠፉን ታዉቁበታላችሁ፡፡ ምንም በሉት ምን እንደናንተ ላሉት የቤተክርስቲያን/የኢየሱስ ክርስቶስ/ ጠላቶች የጎን ውጋት የሆኑትን እነዚህን ወገኖች በደንብ እንዳዉቃቸዉ እያደረጋችሁኝ ስለሆነ አመሰግናችኋለሁ፡፡

  ReplyDelete
 21. ከእናንተ መካከል ሐጢአት ያልሰራ ቢኖር ይዉገራት . . .” ሁሉን ነካካችሁት ማን ቀራችሁ? ማኅበረ ቅዱሳንንማ የወገባችሁ ቅማል አድርጋችሁት የማትሉት የላችሁም፡፡ ለእናንተ ሥራ የማይመቹ ጳጳሳትን እንኳን ስህተት ተገኝቶባቸዉ ባይገኝባቸዉ መለጠፉን ታዉቁበታላችሁ፡፡ ምንም በሉት ምን እንደናንተ ላሉት የቤተክርስቲያን/የኢየሱስ ክርስቶስ/ ጠላቶች የጎን ውጋት የሆኑትን እነዚህን ወገኖች በደንብ እንዳዉቃቸዉ እያደረጋችሁኝ ስለሆነ አመሰግናችኋለሁ፡፡

  ReplyDelete