Thursday, November 15, 2012

ሰበር ዜና: የአባ ሚካኤል አስከሬን ተቆፍሮ እንዳይወጣ ለማድረግ «አባ» ሳሙኤል ወደፍርድ ቤት ሽማግሌ ሊልኩ መሆናቸው ተሰማ

ሰኞ ዕለት ባወጣነው ዘገባ እንደ ገለጽነው የልደታ ምድብ ችሎት ባለፈው አርብ[1] የአባ ሚካኤል አስከሬን ወጥቶ የዲኤንኤ ምርመራ እንዲካሄድበት ወስኗል፡፡ ይህን ውሳኔ ተከትሎ እውነት የምትገለጥበት ጊዜ መቅረቡ ያሳሰባቸውና የሚይዙ የሚጨብጡትን አጥተው የሰነበቱት «አባ» ሳሙኤል በዓለም ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም በማያውቅ አሰፋሪ ሁኔታ ሲኖዶስ ወስኖ በደብዳቤ የጠየቀውንና ከፍርድ ቤት በኩል ምላሽ ያጣበትን ጉዳይ በሽምግልና ለመጨረስ በማሰብ ዛሬ ኅዳር 6/2005 ዓ.ም ለፍርድ ቤት ሽማግሌ ለመላክ መወሰናቸውንና ለዚሁ ጉዳይ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ፡፡


እንደ ምንጮቻችን ከሆነ «አባ» ሳሙኤል ሽማግሌ ለመላክ እየተንቀሳቀሱ ያሉት ከማንያዘዋል ጋር በመሆን በፍርድ ቤት አካባቢ የሚገኙና ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ንክኪ ያላቸውንና የማኅበሩ አባላት የሆኑ ዳኞችንና የህግ ሰዎችን በማሳመን የአባ ሚካኤል አስከሬን ተቆፍሮ እንዳይወጣ እንዲያደርግና ፍርድ ቤቱም ከአሁን በኋላ ጉዳዩ የሃይማኖት ነውና አይመለከተኝም ብሎ ፋይሉን እንዲዘጋ ለማድረግ ነው፡፡ ዋና የማሳመኛ ነጥብ አድርገው ያቀርባሉ ተብሎ የሚጠበቀው «የአባ ሚካኤል አስከሬን ወጥቶ እንዲመረመር ከተደረገ ቤተክርስቲያን ትዋረዳለች፤ ስለዚህ ቤተክርስቲያን እንዳትዋረድ ይህ ጉዳይ እንዳይነሣ ተደርጎ መቀበር አለበት» የሚል ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህን እውነት በማፈን ቤተክርስቲያን ትዋረዳለች እንጂ አትከበርም፡፡ እንዲህ ያለውን የቆብ ውስጥ ገበና በመግለጥ በእግዚአብሔር ቃል ውስጧን ብተፈትሽና ችግሮቿን ብትፈታ ወደእግዚአብሔርም ፊቷን ብትመልስ ያ ነው ለቤተክርስቲያን ክብሯ፡፡ ጉዳዩ የሚዲያ ሽፋን ያገኘና ቤተክርስቲያን ውስጥ በይፋ የሚታወቅ ጉዳይ በመሆኑ፣ አባ ሚካኤል ያልካዱትንና ተቀብለው ልጃቸውን በማሳደግ ለቁም ነገር ያበቁበትን ይህን እውነት ለማፈን የሚደረገው ሩጫ ለቤተክርስቲያን ከማሰብ ሳይሆን በአባ ሚካኤል የተጀመረው ይህ ጉዳይ፣ ወደሌሎቹ ተረኞች እንዳይዛመት በተለይም የእነ«አባ» ሳሙኤልን ጸሐይ የሞቀውና አገር ያወቀው እንኳን ከጵጵስና ከደህና አቶነት ውጪ የሚያደርገው የተበላሸ ታሪክ ከአሁኑ የበለጠ ጉዳት እንዳይደርስበት በማሰብ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ፡፡

«አባ» ሳሙኤል በታሪክ ተሰምቶም ተደርጎም የማያውቀውን በሕግ ብቻ የሚሠራውን ፍርድ ቤትን በሽምግልና ለመጠምዘዝ የጀመሩት ጉዞ ሰውዬው የሚገኙበትን ደረጃ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ ጉዳዩ በሽምግልና እንዲያልቅ ከተፈለገም መደረግ የነበረበት ከአባ ሚካኤል ህጋዊ ልጅ ከዮሐንስ ሚካኤል ጋር መደራደርና ስምምነት መፍጠር ከዚያም በሁለቱ ወገኖች ስምምነት ጉዳዩን ፍርድ ቤቱ እንዳቋርጥ ማድረግ ነበር፡፡ ማንአለብኙ «አባ» ሳሙኤል ግን ይህን ህጋዊ መንገድ ትተው በሕግ ብቻ የሚመራውንና በህግ መሰረት ብይን የሚሰጠውን ፍርድ ቤትን እንሸማገል ብለው ለመጠየቅ መነሳታቸው ብዙዎችን አስገርሟል፡፡ ፍትህን በአመጽ መንገድ እንጂ በትክክለኛውና በእውነተኛው መንገድ ማግኘት የማይችሉና የማይፈልጉም መሆናቸውንም አስመስክሯል፡፡

ጉዳዩ በእውነተኛ ፍርድ እስካልተቋጨ ድረስ የማያርፉትና ከጳጳስ በማይጠበቅ ሁኔታ ምእመናንን በአለም ፍርድ ቤት በመክሰስና በመካሰስ ወደር ያልተገኘላቸው «አባ» ሳሙኤል በገንዘብ ሃይል ጭምር ይህን አጣብቂኝ ውስጥ የገባ ጉዳይ አፍኖ ህገወጥ መንገዶችን ሁሉ በመጠቀም ለማስቀረት የማቆፍሩት ጉድጓድ እንደማይኖር ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡ በዚህ ረገድ ልምድ ካለው ማኅበረ ቅዱሳን ጋር ግንባር መፍጠራቸው ደግሞ አንዳንዶችን አሳስቧል፡፡ ለዚህም የፍርድ ሂደቶችን በህገወጥ መንገዶች እንዲቋረጡ በማድረግ የተካነው ማህበረ ቅዱሳን የህግ ሰው ሆኖ ሳለ የቀድሞው አባሉ «ዲያቆን» የአሁኑ «ቄስ» (ዲቁናውም ቅስናውም የክብር ነው) እሸቱ ታደሰ ናዝሬት ላይ የፈጸመውን ሴቶችን የመድፈር፣ ገንዘብ የማጭበርበርና የነፍስ ግድያ ሙከራ ወንጀል በፖሊስ ፕሮግራም ሲተላለፍ ቆይቶ የት እንደደረሰ ሳይታወቅ ጉዳዩ ተድበስብሶ እንዲቀር እንዳደረገና እሸቱ ተገቢውን ቅጣት ሳያገኝ ከ8 ወራት እስራት በኋላ በዋስ ተፈቶ ወዲያው የሐመር መጽሔት አዘጋጅ ሆኖ መሾሙን ያስታውሳሉ፡፡ ይሁን እንጂ የአባ ሚካኤልን ጉዳይ የያዘው ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ለውጦ የ«አባ» ሳሙኤልን ምድር ላይ የሌለ «ሽምግልና» ተቀብሎ የፍርድ ሂደቱን ያቋርጣል የሚል ሐሳብ እንደሌላቸው ብዙዎች ግምታቸውን ይናገራሉ፡፡ ለሁሉም ጉዳዩ የደረሰበትን እየተከታተልን ለመዘገብ እንሞክራለን፡፡


 [1] እርማት    
ሰኞ እለት ባወጣነው የአባ ሚካኤል ዘገባ ላይ የፍርድ ሂደቱ የተካሄደው ሐሙስ እለት ነው የሚለው በስሕተት ስለሆነ አርብ በሚለው እንዲስተካከል፣ ሶስተኛ አንቀጽ ላይም «በ«አባ» ሳሙኤል መሪነት ሲከራከሩ የነበሩት የአባ ሳሙኤል የስጋ ዘመዶች» የሚለው «የአባ ሚካኤል የሥጋ ዘመዶች» በሚለው እንዲስተካከል በታላቅ ትህትና ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡

24 comments:

 1. አሁን ጉዳዩ ትክክለኛ መሥመሩን ይዟል ፡፡ ስለዚህም ምርመራው ተካሂዶ ውጤቱን መጠበቁ ለባለጉዳዮችም ፣ ለእኛም ለዜና ተከታታዮቹ መልካም ይሆናል ፡፡ ሌሎች የሚታሙ አባቶችም ፣ ተመሳሳይ ስህተት ፈጽመው ከሆነ ፣ የንስሃ ዘመንን የሚፈጥርላቸው ይሆናል በበጎ ጎኑ እንመልከተው ፡፡

  በተረፈ ግን አባ ሚካኤል በሕይወት እያሉ ወጣቱን እየረዱ ማሳደጋቸው ህጋዊ የልጅነት ማዕረግን አያሰጥም ፡፡ እንኳንስ በርሳቸው ደረጃ ያለ አባት ፣ በአገራችን ያሉ ትናንሽ ክርስቲያኖችም ልጄ ብለው ያልወለዱትን ያሳድጋሉ ፡፡ ታሪኩን በትክክል ለመጥቀስ ተዘነጋኝ እንጅ ፣ ከቀደሙት አባቶች መካከል እንዲሁ አንዷ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ አማጋጠኝ ብላ በመነሳቷና ጉዳዩ በሽማግሌዎች በመታየቱ ፣ የተወነጀሉት አባት ያላደረጉትን አዎ ጥፋተኛ ነኝና ይቅርታ አድርጉልኝ ብለው የእምነት ቃል በመስጠታቸው ተወግዘው ፣ ከማኀበረሰቡ ተለይተው ሞቱ የሚል ታሪክ አለ ፡፡ በሚገነዙበት ሰዓት የተገለጠው እውነታ ግን ፣ ተወግዘው ፣ ተለይተው ፣ በወንድ ስም መንኩሰው የነበሩት ሰው በተፈጥሮ ፆታቸው ሴት ሆነው መገኘታቸው ነበርና ፤ አባ ሚካኤል አሳደጉ ማለትን እንደ ህጋዊ ቃል መደጋገሙ አንባቢን ወደ ተሳሳተ መደምደሚያ ይወስዳል ፡፡

  ReplyDelete
  Replies

  1. As to me Menafikan will provide alot of money from their donors to change the result, i.e. They will enforce to make the DNA result match. B/c they want it for their purpose.They want EOC followers to lack trust on their spritual fathers.

   Delete
 2. እናንተ ጉዶች! ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ፣ አባቶችን ለማዋረድ፣ምዕመናን በአባቶች ላይ ጥላቻ እንዲያድርባቸውና ሃይማኖታቸውን እንዲጠሉ ለማድረግ የምታደርጉት ሁሉ እንደሚያስጠይቃችሁ እወቁ::በእውነተኛው ዳኛ በእግዚአብሔር ፊት ትቀርባላችሁ::ለመሆኑ ሥራ የላችሁም?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ጉደኛው ማነው? እውነትን ለመሸፈን የሚሮጡት አባ ሳሙኤል ወይንስ አባ ሰላማ ብሎግ? እኛ እኮ ሁሉንም እንከታተላለን፡፡ አባ ሳሙኤል በሐሰት አይወንጀሉ፣ ስማቸው አይጥፋ እንጂ ቅሌታቸውን ለመሸፈን ስንል የቤተክርስቲያንን መዋረድ አንሻም፡፡ ከአባ ሳሙኤል ክብር ይልቅ የቤተክርስቲያናችን፣ የእግዜአብሔር ክብር ይበልጥብናል፡፡ ደግሞ ደርሶ ተቆርቋሪ መሳይ . . . !!!

   Delete
 3. good job i am in U.S.A I want listen the court decision. The court should be follow according to the law . NO BODY IS ABOVE THE LAW
  TELL TO THE FAKE BISHOPS.

  ReplyDelete
  Replies
  1. really good job for you and your heretic brothers

   Delete
 4. What if the D.N.A is negative. If የአባ ሚካኤል is not the biological father, Who is taking the warrant. It will be a graving mistake for those advocatting against E.O.T.C.
  According to the Bible, there are many fathers that are not biological. Example, Joseph was the father of Jesus and Jesus had many people that he calls brothers. So I beleive the D.N.A will be negative.

  ReplyDelete
 5. Gin lemin ye aba michaelin askren aba samuel serkew wesedewutal yemilewun satzegibu kerachihu?

  ReplyDelete
 6. SHIMGLNAM YABATN NEWR MEDEBEKIM(like Sem did to his father Noah)MENFESAWI SRA NEW.SO,YEABA SAMUEL DRGIT MNU LAY NEW NEWRU?

  ReplyDelete
 7. እናንተ ጉዶች! ምን ማለት ነዉ ጉደኛ ማን ነዉ ? ዝም ብለ አትናገረ ጉደኛማ እነ አባ ሳሙሄል ናቸዉ አንተም የእነርሱ ግሩብ ነህ መሰለኝ እዉነት ሁልግዜም እዉነት ነዉ ቢመሽም መንጋቱ አይቀርም እያንዳንዱ የሚሰሩት ስራ በአዳባባይ ትዉጣላች እስከ ዛሬ ቤተክርስቲያንን የተጫዉቱባት ይበቃታል ከአሁን በኋላ ግን ህይዉቱን ይሰጣል እያንዳንዱ ምህምን አነ አባ ሳሙሄል እና መሰሎቻቸዉ እኮ ለ ድቆንና አይበቆም ለደብተራነት እንጂ ይልቁስ ዘመዶች ለእዉነት እነሙት ቤትርስቲያናችንን እናፅዳ

  ReplyDelete
 8. Mk has come to the church in one clear and concise purpose. The first agenda to take over employement position in any where avialable and fit for them. Secondely, to take over political power from gov. The tools that used technicaly un q ualified monk, bishop and non ethical bozene women. Immagine, the bishop such like, aba abrham, zelebanose officialy sex with men, but never blame them in this shameful ethics. Now, it is relevant for other shermuta bishop to create good understanding of eotc followers this man DNA test is best solution to get out illusion. Fu....mk......Deep darkeness to mk.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምኑን ከምኑ አገናኘኸው ? ተመርማሪ አባ ሚካኤል ፤ ባለጉዳይና ህጋዊ ልጅ ነኝ ባይ ደግሞ ወጣት ፤ ታድያ ማኀበረ ቅዱሳንን ስለምን ቀላቀልከው ፡፡ እሱም አባት ነው ተብሎ ይሆን ፡፡ አየህ ስለወጋችን እውነትን የሚፈልግ ሰው በጭብጥ ላይ እንጅ በጥላቻ መንፈስ መንጎድ የለበትም ፡፡ ከወንድ ጋር በግላጭ ተኝተዋል ስለምትላቸው አባቶችስ ማስረጃህ ምንድር ነው ? አየህ የጻፍከው ሁሉ በጥላቻና ስም በማጥፋት ላይ የተንጠላጠለ ነው ፡፡ ከላይ የተገለጸውን የጽሁፍ ፍሬ ነገር ሁሉ ዋጋ ያሳጣል ፡፡ በጥላቻ ላይ የተመሠረተ ያስመስለዋልና ፡፡

   Delete
 9. Don't write this kind of evil news which doesn't have a true base. Please don't be happy to disclose the sins of others. This doesn't comply with Jesus Christ's lesson.

  Kindly focus on your own sins and pray.

  ReplyDelete
  Replies
  1. you fellow!!! actually it is not a lie but it is a mere fact. it was broadcasted through Fana Broadcasting Corporation.

   Delete
 10. አባ ሳሙኤልና ማኅበረ ቅዱሳኖች እውነትን በመቅበር፣ ውሸትን በማንገስ የተካኑ መሆናቸው ማንም ያውቀዋል፡፡ የሚያሳዝነው ግን ተከታዮቻቸው ይህንን አይተው ልቦናቸውን ወደ እግዚአብሔር አለመመለሳቸው ነው፡፡ በኃጢአት ላይ ኃጢአት. . . !!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ውጤቱን ሳታውቅ አጠቃላይ መግለጫ አትስጥ ፤ የራስክን አመለካከት ብቻ አስቀምጥ ፡፡ ምርመራው አባ ሚካኤልን ነጻ ቢያደርጋቸው የነገር ማጠፊያህን ምን ልታደርገው ነው ?

   Delete
 11. Thanks Aba Samuel. You are doing great. It is normal that Menakikan hate u. They know u r a good servant of EOC.

  ReplyDelete
 12. EGZIOO LEKA BEKUMACHEN MOTENAL ENE ABA SAMUEAL(ABA TEKESTE) ABA ABRHAM (Qes) ABRHAM ayee yihen min telalachehu tewareden ere sentu abate new eyale endayemeta feruu

  ReplyDelete
 13. የብሎጉ ስም መልካም ‹‹አባ ሰላማ›› እናንተ ሃሜተኞች ወሬኞች የምታዉቁ ከሆነ ወንጌላዊ ነን የምትሉ ከሆነ ቅዱስ ቃሉን አታስተምሩም፡፡ አሁን አሁን ስረዳ ለካስ የወንጌል እዉቀቱ ስለሌላችሁ ነዉ ሀሜት ላይ ያተኮራችሁት ፡፡ በጌታ ስም ልለምናችሁ እንዲህ ቁጭ ብላችሁ ስለሰዉ የሰራዉንም ያልሰራዉንም ስታወሩ ወደራሳችሁ መመልከቻ ጊዜ ሳታገኙ ንጉሱ እንዳያመልጣችሁ፡፡ ደግሞም የሰዉ ሃጢያት መግለጥ የዲያቢሎስ መንፈስና ስራ እንጂ ከእግዚአብሄር አይደለም ፡፡ ጌታማ በደልን የሚከድን ነዉ የሚገልመዉ ግን ሰይጣን ነዉ፡፡ ታላቁን ካህን እያሱን አንኳን ከመክሰስ ወደኋላ አላለም እናም እናንተም የሱ ልጆች ወደ መሆን እንዳታድጉ እፈራለሁ እናም እራሳችሁን መርምሩ ስል እመክራለሁ፡፡ እግዚአብሄር ከናንተ ጋር ይሁን ከ ሃጢያት ቁራኛነትም ይፍታችሁ፡፡

  ReplyDelete
 14. ብጹዕ አቡነ ናትናኤል ቅዳሴ ቤት ለማክበር ወደ አገር ስብታቸው ሄደው መንበረ ፓትሪያሪክ ባለፈው እሁድ ተመልሰው የአቃቤ መንበረፓትሪያሪክ አገልግሎታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ።
  · በተሃድሶ መናፍቅነት የሚጠረጠረው መምህር አእመረ አሸብር ከስብከተ ወንጌልና ሃዋሪያዊ መምሪያ ኃላፊነቱ ተነስቷል
  · የቤተክረስቲያኒቱን ተቋማዊ ሰላም በማያናጋና ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ቤተክርስቲያኒቱ ለማደረግ ያሰበቸውን አስተዳደራዊ ለውጥ የሚያደናቅፉና ቤተክርስቲያኒቱን በከፍተኛ ሁኔታእየጎዱ የሚገኙ ሓላፊዎች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ መውሰድ እንደሚቀጥል ይጠበቃል።


  ዝርዝሩ፡-
  በተሃድሶ መናፍቅነት የሚጠረጠረው መምህር አእመረ አሸብር ከስብከተ ወንጌልና ሃዋሪያዊ መምሪያ ኃላፊነቱ ተነስቶ የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ መልዓከ ሰላም አምደ ብርሀን ተመድበዋል። በተለይ ባለፈው ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ “ ያሬድ ድጓ የደረሰው ወንጌል ተምሮ ነው፣ ለወንጌል አገልግሎት ቅድሚያ መሰጠት አለበት፣ ወንጌል ትኩረት አልተሰጠውም ……” በተለይ ደግሞ ሰባኪያን በተመለከተ በተናገረው ንግግር ህገወጥና ተሃድሶ የሚባሉትን በመምሪያው ስር ከሆኑ ፈቃድ በመስጠት ወደ ህጋዊ መስመር የማስገባት ሥራ እንደስራና ወደ ፊትም አጠናቅሮ እንደሚቀጥልበት ብጹዓን ሊቃነጳጳሳት ባሉበት መናገሩ አሰላለፉ ከማን ጎን እንደሆነ ግልጽ እንዳደረገ ተነግሮለታል። በተለይም እንደ አሰግድ ሳህሉ ዓይነት የሙሉ ወንጌል እምነት ድርጅት አባል ህጋዊ ከለላ በመስጠትና ኦርቶዶክሳውያን ደግሞ በማጉላላት የሚታወቀው መ/ር አእመር አሸብር ችግሩ ጎልቶ ስለወጣ ከኃላፊነቱ እንዲነሳ ተደርጎል።

  አቃቤ መንበረ ፓትሪያሪክ አባ ናትናኤል ወደ አገረስብከታቸው አርሲ - አሰላ አዲስ ቅዳሴ ቤት ለማክበር መሄዳቸውን ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ አኅጉረስብከት ሥራአስኪያጆች ምደባ ወቅት በአቃቤ መንበረፓትሪያሪኩና ሥራአስፈጻሚ ኮሞቴው መካከል ተፈጥሮ የነበውንና መጨረሻ ላይ ስምነት የደረሱበትን መጠነኛ የሃሳብ ልዩነት በማስታከክ የተሃድሶ መናፍቃን ልሳን የሆኑት እነ አባሰላማ ድረገጽ ብጹነታቸው “ስራአስፈጻሚ ኮሚቴውን አልሰበስብም” ብለው ወደ አገስብከታቸው ሄዱ በማለት ያለቸውን ተምኔት ጽፏል። ብጹነታቸው ወደ አገስብከታቸው የሄዱት አዲስ ቅዳሴ ቤት ለማክበር እንዲሁም የማኅበረቅዱሳን አሰላ ማዕከል ጠቅላላ ጉባኤ ለመገኝት እንደሆነ ምንጮቻን ተናግረዋል። ከባለፈው እሁድ ጀምሮ ብጹዕነታቸው በመደበኛ የአቃቤ መንበረ ፓትሪያሪክ ተግባራቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ።

  ReplyDelete
 15. aba samuealen yemaywek abt yebel gen enkuan abanet ye betekerseteyan abal mehonachew yemeyasafer endesachew hayemanotachenen yakelel aneget yasedefa yelem lenegeru sew AMLAKE endale seyamen yeferal kalamene sew men yetebekal????

  ReplyDelete
 16. አባ ሰላማዎች የአባ እስጢፋኖስንና የአባ ጢሞቴዎስን ጉዳይስ ለምን ታድበሰብሳላችሁ;
  የአባ እስጢፋኖስ ልጅ (የልቤ ነጋ) በአሁኑ ሰዕት በቅ/ሥላሴ ኮሌጅ የአባ ጢሞቴዎስ ሾፌር ነው፡፡ የአባ ጢሞቴዎስ ልጅ (ኢሳኢያስ) በአሁኑ ሰዓት አውስትራሊያ የሚገኝ ነው፡፡ ቀደም ሲል እኮ አጋልጣችሁ ነበር አሁን ለምን ጉቦ ተቀበላችሁ ወይስ ለምንድነው የሚሸፈንላቸው!!

  ReplyDelete
 17. I am eagerly waiting the courts decision. Things are on the right track.

  ReplyDelete