Wednesday, November 21, 2012

ወደ ፍ/ቤት ሽማግሌ ይላካል አይላክም በሚል «አባ» ሳሙኤልና ጠበቆቻቸው ሳይስማሙ ቀሩ

የአባ ሚካኤል አስከሬን ወጥቶ እንዲመረመር ፍርድ ቤት ከወሰነ ወዲህ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የገቡትና ነገሩን በሽማግሌ ለመጨረስ እየተንቀሳቀሱ ያሉት «አባ» ሳሙኤል ወደ ፍ/ቤት ይሄዱልኛል ያሏቸውን ሽማግሌዎች ያዘጋጁ ቢሆንም በጠበቆቻቸው በኩል ግን ሀሳቡ ተቀባይነት ሳያገኝና ሽማግሌም ሳይላክ መቅረቱ ተነግሯል፡፡ በጠበቆቹ በኩል የቀረበው ሐሳብ ተገቢነት ያለውና ህጋዊውን መንገድ የተከተለ  ሲሆን፣ «አባ» ሳሙኤልን «እርስዎ ጳጳስ ሆነው የሽምግልና ሕግን እንዴት አያውቁም? ሽምግልና እኮ እየተካሰሱ ባሉት ሁለት ወገኖች መካከል የሚከናወን የእርቅ ሂደት እንጂ ከፍርድ ቤት ጋር አይደለም፡፡ በፍ/ቤት ሕግ እንዲህ አይነት ሽምግልና ተሰምቶም ታይቶም አያውቅም» ብለዋቸዋል ተብሏል፡፡ አክለውም «ሽማግሌ መላክ ካለብንም መላክ የምንችለው የአባ ሚካኤል ልጅ ነኝ ወደሚለው ወደ ዮሐንስ ነው፡፡» ብለዋል፡፡
ይህን መቀበልና ከዮሐንስ ጋር ያላቸውን የክስ ሂደት በሽማግሌ መጨረስ ሽንፈትና ሞት መሆኑን የተረዱት «አባ» ሳሙኤል ግን ሐሳቡን መቀበል አልፈለጉም፡፡ ምክንያቱም ነገሩን በሽማግሌ መጨረስ የሚቻለው ዮሐንስ የአባ ሚካኤል ልጅ መሆኑን በመቀበል መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ለነገሩ በተደጋጋሚ ለመግለጽ እንደሞከርነው አባ ሚካኤል ልጃቸው መሆኑን ሳይክዱ እየረዱ እንዳሳደጉትና ለቁም ነገር እንዳበቁት በ«አባ» ሳሙኤልም ጭምር የታወቀ ነው፡፡ ይህ ነገር ይፋ መውጣቱ ግን ምእመናን ለጳጳሳት ያላቸው ክብር ግምት እንዲቀንስ የሚያደርግ በመሆኑ ከዮሐንስ ጋር ነገሩን በሽምግልና መጨረስ የማይታሰብ ነገር ነው፡፡ ውሳኔውን መቀበልም በሕግ ፊት የነገሩን እውነተኛነት ማረጋገጥ ነው፡፡ ከሁለቱ ክፉ ምርጫዎች የቱን እንደሚመርጡ የተቸገሩ የሚመስሉት «አባ» ሳሙኤል ሽማግሌ መላክ አለበት በሚለው አቋማቸው እንደጸኑ መሆናቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች እየተናገሩ ነው፡፡ ሳይማሩ የጠመጠሙት «አባ» ሳሙኤል ሽማግሌዎቹን እኔ አዘጋጅቻለሁ እናንተ የፍ/ቤቱን መንገድ ስለምታውቁት መንገዱን አሳዩኝ ብለው በአቋማቸው ቢጸኑም ጠበቆቹ የአባ ሳሙኤል ሀሳብ ከአንድ ጳጳስ የማይጠበቅና ያልተማረ ሰው እንኳን ያስበዋል ተብሎ የማይጠበቅ በመሆኑና ፍ/ቤትም በህግ የያዘውን ጉዳይ በህግ አግባብ ከመጨረስ በቀር የተጣላውና የተካሰሰው ወገን ስለማይኖር ሽምግልና የሚባል ነገር ስለማያስተናግድና ሀሳቡ ህጋዊ ባለመሆኑ ውድቅ በማድረግ ሳይተባበሯቸው ቀርተዋል፡፡

በዚህ የተበሳጩት «አባ» ሳሙኤል «እኔ እያመመኝ ነው፤ ዕረፍት ማድረግ አለብኝ» በሚል ወደ ኢየሩሳሌም መሄዳቸው ተሰምቷል፡፡ ምናልባትም በዚህ ሰበብ የፍርዱን የመጨረሻ ውሳኔ ላለማየት በሚል ይሁን ወይም በእርግጥ አሟቸው ለጊዜው የታወቀ ነገር ግን የለም፡፡

11 comments:

 1. Ke websitu anat lay yederederachihutn ye papasat photo ebakachihu atifut. Min yadergliachihual?

  ReplyDelete
 2. good let him go.... he is a mafya, fulish gang. The truth will come out whether he is thair or not. May be he is going to ask asailom in seytan house. that is his home, shame on him. Leba.

  ReplyDelete
 3. So sad to hear kind of this controversy from church leader and Maheber kidusan . Why our orthodox church leaders and MK go crazy. Please, would you tell those not stand with our God word and proud them selves. One day, God reveal like that to the public. Just lets pray ..............have nice thanksgiving day.

  ReplyDelete
 4. ተረት ተረት የላም በረት........?ይህ መንፈሳዊ ብሎግ ወይስ ወሬ አመላላሽ?

  ReplyDelete
 5. can you tell us the profit you get from the verdict, you guys? i didn't get the intentions other than digging and exposing out the sin of others while hiding your own. OK, if it is , then, is it biblical? completely no, if so are you christian? no, no, no?

  ReplyDelete
 6. Egziooo Abetu min ensema yihon zemenu kifu hono egnam kifu honen yebtekresteyan semua eyekefa ers bers eyetbelalan min yihon mechereshachen ASA GOREGUAR ZENDO YAWETAL Mk yemeseraw sera betam yasazenal yebtekersteyan lijochn eyasadede bewech ena behager yaluten teadeso, menafik eyale yalesim sim eyeste yebase gud ametabin And PAPAS lij alew tebelo kemekabir askeren siweta egzioooooo yimaren

  ReplyDelete
 7. ድሮ ድሮ ጳጳሳት ተልአኮአቸውን አውቀው አባት እንደ መሆናቸው መጠን ለህሉም እንኳን በሀይዘኖት ለሚመስላቸው ቀርቶ ለእግዚአብሄር ፍጡር ሁሉ የሚራሩ የሚፆሙ የሚጸልዩ የሚሰግዱ የሚመጸውቱ ነበሩ በአኗኗራቸው ሁሉ ለክርስቲያን ልጆቻቸው አርአያ ነበሩ ዛሬ ዛሬ ያሉት ጳጳሳት ለስጋዊ ክብራቸው በእጅጉ የሚጨነቁ ለስልጣን የሚሞቱ ሕግ አውጭነትንና ሕግ አስፈፃሚነትን ለራሳቸው በማድረግ ቤተክርስቲያንን እያለቡዋት ሳይሆን ደምዋን እየመጠጣዋት መሆናቸው ለዚህም ከመብላታቸውና ከመጥገባቸው የተነሳ /ሰብሀ ወገዝፈ ወርህበ ወሀደጎ ለእግዚአብሄር ፈጣሪሁ/ ተኝተው የሚያድሩ የሚሾረምጡ ሴቶችን የሚያስከትሉ ፓንቲ ገዘትው የሚየበረክቱ ጉዶች ላይ ደርሰናል በዚህ ጥቂት አባቶች ቢኖሩንም ብዙዎቹ አመንዝራዎች ናቸው ለምን አባት እንላቸዋል ለምን በጭራሮ ጠርገን ቤተክርስቲያንዋን አናፀዳትም በእወነቱ ለዚች ቤክርስቲያን እየደከማችሁ ናችሁ ግን እባካችሁ ወጣቱ ክፍል በእነዚህ ግብስብሶች እጁን እነዲያነሳ የቤተከህነት አስተዳደር በጥቁር ራስ እንዲመራ ለማድረግ እንስራ ደመወዛቸው ከሰው በላይ ቀለብ በነፃ ህክምና በነፃ መኖር በነፃ በህዝብክርስቲያን በተሰራ ቤት ሽርሙጥና እና ወንዲያ አዳሪነትን አስፋፍተዋል እንጥረጋቸው እላለሁ አዲስ አበባ ሀገረ ስበከት ለ 4አራት የቆራረቱጣት እኮ በዚች ከተማ በመሆን ለመፀለይ አ ደለም ለማምነዘር እኮነው

  ReplyDelete
  Replies
  1. anete yemeteferde mane honhe new? menafeqe

   Delete
 8. እግዜር የተጣላው ትውልድ ቢነግሩት አይሰማ ቢያዩት አይለማ ዝም ብሎ ሲያስተውሉት ጠማማ
  ካህናቱን መነኰሳቱን እንዲሁም ቃልቻዎቹን ይሁን ይበላቸው! ምን አለ ጳጳሳቱን ቢዘሏቸው!
  ሕዝ 9.5---7 በሥውር የሚመለክት ሥውር ሾተል ጨብጦ እያሳደዳቸው ነው ዕኮ ለምን የዘመኑ
  ትውልድ ተጨማሪ በደል እና ግፍ ያደርስባቸዋል?(በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ)ኧረ ተዉ!

  ReplyDelete
 9. This is really amazing. I think Aba Samuel should stop acting like this because Yohans has a right to know his father and claim his father's money and any priority. In my opinion, trying to cover any problem or mistake is not a good selustion of the problem. Besides, Yohans is supported by the new law of the bishops and Arch bishops. The Lawyers of aba micheal are right, there is no way to solve this cause by sending some people to the court

  ReplyDelete
 10. ኧረ ጉድ ነው ዕኩሌቶቹ ተቀደስን አንዳንዶቹ ታደስን ሌሎችም በውሸት በቃን ነቃን እንብላ እንጠጣ
  እንደሰት እያሉ ይህችን ጥንታዊት ቤተ ክስቲያን ሊቀራመቷት! አይጣል! ጳውሎስንም የቆረንቶስ ወስላቶች
  ግራ ሊያጋቡት ተቃርበው ነበር፤1ቆሮ 15 32--33 እናም አንዳንድ የዋሃን ካህናትና ብልሆች ምእመናን ራሳችንን እንጠብቅ አደራ!ግራ እንዳንጋባ በነበረው እንሂድ።

  ReplyDelete