Monday, November 26, 2012

«አለው ነገር» የተሰኘ አዲስ ኦርቶዶክሳዊ የዝማሬ ሲዲ በዘማርያን ትዝታው፣ ምርትነሽና ዘርፌ

‘ማልደራደርበት‘ ማልቀብረው እውነት
አንገት ‘ማያስደፋኝ የማላፍርበት
ኢየሱስ የሚለው ስም እስትንፋሴ ነው
እውነቱ ይሄው ነው


አንዱን መዝሙር ለቅምሻ ጋብዘናል- ሌላውን ገዝተው ያዳምጡ

እነዚህ ስንኞች የተወሰዱት ከአንድ የግጥም መድበል ውስጥ እንዳይመስላችሁ፤ ዲ/ን ትዝታው ሳሙኤል ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን እና ዘማሪት ዘርፌ ከበደ በጋራ ከሳተሙትና «አለው ነገር» የሚል ርእስ ከተሰጠው የዝማሬ ሲዲ ላይ የተወሰደ ነው፡፡ እውነት ነው ኢየሱስ የሚለው ስም ለእውነተኛ ክርስቲያን እስትንፋስ ነው፡፡ አንገት የማያስደፋና የማያሳፍር የማይቀበርና ለድርድር የማይቀርብ ስም ነው፡፡ እውነትም ኢየሱስ በሚለው ስም ላይ ድርድር የለም!!!
ይህ የዝማሬ ሲዲ ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ጀምሮ ለምእመናን ቀርቧል። በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ አድባራትና ገዳማት በየበአላቱ ቀን ሞንታርቦ በያዙ ሚኒባሶችና በየመዝሙር ቤቱ ሁሉ እየተሸጠ መሆኑንና ታክሲ ውስጥ፣ በተለያዩ ንግድ መደብሮችና በየካፌውና ሬስቶራንቱ ሁሉ እጅግ እየተደመጠ ይገኛል፡፡ 12 ዝማሬዎች የተካተቱበት ይህ የዝማሬ ሲዲ በውስጡ አስሩ ጌታን የሚያከብሩ፣ ፍቅሩን የሚሰብኩ፣ አዳኝነቱን የሚያውጁና የሚማጸኑ፣ ፈራጅነቱን የሚያዘክሩ፣ ወደንስሀ የሚመሩና መሰል መልእክቶችን ያካተተ ሲሆን ለማርያም የቀረቡ ሁለት ዝማሬዎችም አሉበት። የዝማሬዎቹን ግጥምና ዜማ የደረሱት ደግሞ አብላጫውን መጋቤ ሐዲስ በጋሻው ደሳለኝ ሲሆን በመቀጠል ዲ/ን ትዝታው ሳሙኤል እንዲሁም ዘማሪ ሀብታሙ ሽብሩ አንድ ዜማ መድረሱን ስቲከሩ ያስረዳል። 

ዝማሬው እንዲህ እየተደመጠና ብዙ ምእመናን የአምልኮት ጥማታቸውን እያረኩበት ቢገኝም በዚህ ደስ ያልተሰኘውና የመልካም ነገር ሁሉ ጠላት ሆኖ ከቀድሞ ጀምሮ የእነበጋሻውን ዝማሬዎች በመቃወም የሚታወቀው ማኅበረ ቅዱሳን የእርሱ ግዛት በሆኑ አንዳንድ ደብሮች ውስጥ በድምጽ ማጉያ «እነዚህ የተወገዙ መናፍቃን ስለሆኑ መዝሙራቸውን እንዳትገዙ» የሚል ቅስቀሳና ዘመቻ ከፍቶባቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ በዚያው ልክ ዝማሬዎቹ በብዙዎች ዘንድ መደመጣቸውን ቀጥለዋል፡፡ ወንጌል ሲቃወሙት ይብሳልና፡፡

መጋቤ ሐዲስ በጋሻው፣ ዲያቆን ትዝታው፣ ዘማሪት ምርትነሽ እና ዘማሪት ዘርፌ የቤተክርስቲያን ልጆች ናቸው፡፡ በጋሻውን «መናፍቅ ነው» ብለው ለመክሰስ የሞከሩ ቢሆንም እስካሁን ተቀባይነት አላገኙም፡፡ ሌሎቹ ግን ማኅበረ ቅዱሳን በየጓዳው «መዝሙራቸው ዘፈን ነው» እያለ ከሚያብጠለጥላቸው በቀር ኑፋቄ ተገኝቶባችኋል ተብለው እስካሁን ስማቸው አልተነሳም፡፡ ይሁን እንጂ «የእነርሱ ዝማሬዎች በወጡ ቁጥር ተቀባይነታቸው ይጨምራል፤ እኔ ደግሞ አልደመጥም» በሚል ቅናት እንደሚያሳድዳቸው እርሱን ጨምሮ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ ማህበረ ቅዱሳንና ጀሌዎቹ በአዲሱ ሲዲ ዝማሬዎች እጅግ የተበሳጩ ይመስላል፡፡ ቅስቀሳቸው ባይዝላቸውም በተቆጣጠሯቸው ደብሮች እንዳትገዙ እንዳታዳምጡ እያሉ መለፈፋቸውን ቀጥለዋል፡፡ ሰው በተፈጥሮው የከለከሉትን ነገር ይበልጥ እንደሚፈልገው አልተገነዘቡ ይሆን?

ይህ በእንዲህ እንዳለ ወላጆቹ ማንነቱን ይገልጣል ብለው ያወጡለትንና ትክክለኛ ማንነቱን የሚገልጠውንና «እንዳሻው» የተባለውን ስሙን አዲስ አበባ ሲገባ ኋላቀር ስም ነው በሚል አፍሮበት ምህረተ አብ ሆኛለሁና በዚህ ስም ጥሩኝ ያለው ምህረተ አብ አሰፋ ሃይማኖትን ከሃይማኖት በማጋጨት አተርፍበታለሁ ብሎ የያዘው የሲዲ ንግድ ስለተቀዛቀዘበትና «አለው ነገር» የተሰኘው አዲሱ የዝማሬ ሲዲ ተቀባይነት እያገኘ በመምጣቱ፣ ህዳር 12 ቀን አውቶብስ ተራ በሚገኘው አዲሱ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የተሰበሰበውን ሕዝብ “የ3ቱን ዘፋኞች ዘፈን እንዳትገዙ የተወገዙ ናቸው በቅርብ ቀን ደግሞ የሚወገዙ አሉ ጠብቁ” በሚል በነበጋሻው ላይ ጦርነት ከፍቶ መዋሉ ተሰምቷል፡፡ በቤተ ክርስቲያኑ አካባቢ በመኪና ላይ ሞንታርቦ «አለው ነገር» የተሰኘውን የዝማሬ ሲዲ እያስተዋወቁ የሚገኙትን እንዲያባርሩ ወሮበሎች የላከባቸው ሲሆን፣ አባረው ሲመለሱም «ምእመናንን ለእነዚህ እውነተኛ የቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ ወጣቶች እልል በሉላቸው» ብሎ አስተዋዮችን ሳይሆን እንዳደረጓቸው የሚሆኑትን ምእመናን እልል አሰኝቷል፡፡

ቤተክርስቲያኗ እንዲህ ማንም «እንዳሻው» የሚፈነጭባት መሆኑ የሚያሳዝን ሲሆን ወዴት እያመራች ነው? የሚል ጥያቄ እንዲነሳም ያደርጋል፡፡ እንዴት አንድ ሰባኪ ነኝ የሚል ሰው ለእግዚአብሔር ክብር የቀረበውንና በብዙዎች ተቀባይነት ያገኘውን መልካም ዝማሬ «ዘፈን» ሲል ይጠራል? ወጣቱን ትውልድ አለማዊ ዘፈን እንደማእበል እያናወጠው በሚገኝበት በዚህ ክፉ ዘመን ዘፈንን አስትቶ በየንግድ መደብሩ፣ በየታክሲውና በየካፌው ሁሉ እየተደመጠ ያለውንና ጥሶ መግባትና ተጽእኖ መፍጠር የቻለውን ዝማሬ ዘፈን ብሎ መጥራት እጅግ ያሳፍራል፡፡ ለመሆኑ እንዳሻው እንዲህ ለማለት እርሱ ማነው?

የቀድሞው እንዳሻው የአሁኑ ምህረተ አብ ከወላጆቿ ሀብት ይደርሰኛል ብሎ በሀብት ምክንያት ያገባትን ሚስቱን «ቤተሰቦችሽ የገቡልኝን ሱቅ እንከፍትላችኋለን የሚለውን ቃላቸውን አላከበሩልኝም» በሚል ምክንያት ሌላ ሰበብ ፈልጎ ከፈታት 2 አመት እየሆነው ነው፡፡ የቀድሞ ሚስቱ በአሁኑ ሰአትም ከእህቶቿ ጋር ለንደን ትገኛለች፡፡ ከዚያም አንዲት ክርስቲያን መሆን የምትፈልግ ሙስሊም ልጃገረድን አስተምርሻለሁ ብሎ ከተጠጋትና በእጮኝነት ይዞ አገባሻለሁ ካላት በኋላ ክብረ ንጽህናዋን ወስዶ ስለካዳት ልጅቱ ከሳው ጉዳዩ እንዳልተቋጨና በፍርድ ተይዞ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡ ታዲያ ይህ ሰው የግል ሕይወቱን ሳያስተካክልና በነጭ ቀሚስ ተሸፍኖ ለእግዚአብሔር ክብር የቀረበውን ዝማሬ ለማቃለልና «ዘፈን» ለማለት እንዴት አላፈረም? ያሳዝናል!

ለማንኛውም ተቃውሞው ቢቀጥልም እነዚህ ድንቅ ዝማሬዎች መደመጣቸውን ቀጥለዋል፡፡ በጋሻው የደረሰውና ዘርፌ በውብ ድምጽዋ የዘመረችውም ዝማሬም ሰሚ ጆሮ ካለ በተቃውሞ ለተነሡባቸው ነገር ግን ለማይችሏቸው ተቃዋሚዎቻቸው ትልቅ መልእክት አለው፡፡

አለው ነገር /2/ እግዚአብሔር እንዲህ አብዝቶ ዝም ካለ
ጠላቴ ሆይ ደስ አይበልሽ ቢመሽም ለእኔ ቀን አለ
38 comments:

 1. Ahehehe wedet wedet fiyel wedya kizmzim wedeh man EYESUS atbelu Alachew ena. Neke nen

  ReplyDelete
 2. Please, Abba Selama don't tell us other people's sin.

  Just give us what is best for us, the Word of God. Tell us why the song will be good to our spirituality. Give us some biblical analysis of the poems. That is what will make people understand the message and convince them to buy the album. Surely, I will buy the album.

  ReplyDelete
  Replies
  1. GETA EGZIABEHER YIBARKIH DEGMOM YELIBIHN MESHAT YISTIH.

   Delete
 3. Doesn't the Church acquitted Begashaw from the Heresy charges against him? Why then Mhreteab said that (if he really said that)? Doesn't he believe in the authority of the Synod? The Problem with EOTC is everyone tries to be not only a teacher but also an authority of the faith. But this is not Orthodoxy.

  ReplyDelete
 4. betam arif mezzmur new wadjewalwe

  ReplyDelete
 5. Great News! I cant wait to buy the CD. It is quite known that MK does not want such songs which praise the almighty GOD. It is because of his father devil the enemy of GOSPEL.

  ReplyDelete
 6. አንድ ነገር ግርም ይለኛል! ይሄውም ኢየሱስ የሚለው ስም ለእውነተኛ ክርስቲያን እስትንፋስ ነው ይላል፡፡ ፕሮቴስታንቶች አንድ ነገር ሲደጋግሙ እሰማ ነበር ይሄውም ኢየሱስ ጌታ ነው:: እሺ ይሁን ምናልባትም የእነሱ ፀሎተ ሃይማኖት ሊሆን ይችላል ግን አይደለም:: ኢየሱስ ጌታ ነው የሚሉት ለኦርቶዶክስ ምስክርነት ለመስጠት መሆኑን ሳስብ ደግሞ ግርምቴ ይጨምርብኛል:: ይህን ቃል እነሱ ብቻ ቢሆኑ ባልገረመኝ ኦርቶዶክስ ነን የሚሉም አለማወቃቸው እንጂ:: ኢየሱስን የማያምን ኦርቶዶክስ አለ ወይስ ኦርቶዶክስ ኢየሱስን ለማመኑዋ የተሀዲሶንና የፕሮቴስታንት ቡራኬ ያስፈልጋት ይሆን?
  አንዳንዴም ኦርቶዶክሶች ማርያምን እንጂ ኢየሱስን አያውቁትም ይላሉ ትላላችሁ:: ለመሆኑ ማርያምን የወደድንበትን ምክንያት ጠይቃችሁን ታውቃላችሁ? እኛ ኢየሱስን አይደለም ኢየሱስን የወለደችን እናት የመውለድዋ ምስጢር ድንቅ እያለን ክብር ለሱዋም እንሰጣለን እናመሰግናታለንም:: “ትውልድ ሁሉ ያመሰግነኛል” እንዳለች ስለ ራሷ መመስገን የተናገረች ብቸኛዋ ቅድስት እናት:: አንዳንዶች ግን ስለ ራሷ ምስጋና ፈልጋ አታውቅም ሲሉ ከመጽሀፍ ቅዱስ ጋር ሲጋጩ ይታያል:: ይህ እርሷ ያለመፈለጉዋን መዕሀፍ ቅዱስ ሁሉን በልባ ትጠብቀው ነበር በልም የእርሱዋ ፈቃድ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ስለራሷ ትውልድ ሁሉ ያመግነኛል ስትል መናገሩዋንም ማስታወስ ተገቢ ነው
  ሌላው የጽሁፉ ርእስ ስለ መዝሙራቸው መሰሎኝ ነበር ግን የማይካካው ታሪክ የለም አላዋቂ ጻፊ መሆኑን ያስመሰክራል:: አሁን ስለ ምህረተ አብ ስለ ማህበረ ቅዱሳን ማንሳት ለምን አስፈለገ? እናንተ ስለሌላው ስታነሱ ሌላው ስለእናንተ ቢያነሳ ለምንስ ትበሳጫላችሁ? ሁሉም እናነተን አይደግፍም ሁሉም እናነተን አይቃወምም ልዩነት ይኖራል:: ስለእውነት የኦርቶዶክስን አስተምህሮ ስትቃወሙ ልታጠራጥሩን ትችሉ ይሆናል:: ነገር ግን አሳማኝ ምክንያት ማቅረብ ባለመቻላችሁ ግን ሌላ እድል ከመክፈት ያለፈ ፋይዳ የለውም::

  ReplyDelete
  Replies
  1. ተናግረህ ሞተሃል፡፡ የት ቦታ ነዉ ማርያም ትዉልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል ያለችዉ ትዉልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል ማለት ያመሰግኑኛል ማለት ነዉ አለማወቅህ ሳይሆን የሚያበሳጨዉ አለማወቅህን አለማወቅህ ነዉ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ኢየሱስን አታዉቀዉም አልተባለም፡፡ እየተባለ ያለዉ እሱ የሁሉ ፈጣሪና ጌታ ሆኖ ሳለ ለእርሱ ብቻ የተገባዉን ምስጋና ለፍጡራን እየተሰጠ ነዉ፤ ይሄ ደግሞ ኑፋቄ ነዉ፣ነዉ፡፡
   ይህንን አለማመን ያንተ ድርሻ ነዉ፡፡ የፈለግኸዉን ነገር ማመስገንም መብትህ ነዉ፣ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ እንነጋገር ካልክ ግን ተሳስተሃል፡፡ ስህተትህ ደግሞ ቃሉን አጣምመህ ማቅረብህ ነዉ፡፡ ወደድህም ጠላህም ወደ መንግስተ ሰማያት ለመግባት ቁልፉ ፣አንዱ፣ ራሱን ለሰዉ ልጆች ሲል ለመስቀል ሞት አሳልፎ በመስጠት የሞተዉ፣የተቀበራዉ፣ ከሞትም የተነሳዉ፣በአብ ቀኝ ያለዉ፣ ለሰዉ ልጆች እንደ ስራቸዉ ሊከፍል ዳግመኛ የሚመጣዉ እሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነዉ፡፡ ለዚህ ስም የማይገዛና የማንበረከክ ቢኖር እሱ ከሐሰት አባት ከዲያቢሎስ ነዉ፡፡ ዲያቢሎስ ይህንን ስም ሲጠራ መስማት አይሻም፡፡
   ፕሮቴስታንት ወይም ኦርቶዶክስ መሆን አይደለም ቁም ነገሩ፤ ዋናዉ ነገር በስሙ ማመን ነዉ፡፡ በስሙ እመን ትድናለህ፡፡ የእነገሌ፣ የእነገሌ ጠበቃ ሆኜ እቀጥላለሁ ካልክም መብትህ

   Delete
  2. ትዉልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል ማለት ያመሰግኑኛል ማለት ነዉ? አንተ አውቀህ ሞተሃል ብታቅ ኖሮ ባልሳትክ ነበር:: ሌላው ብጽእት ማለት ምን ማለት ነው? ለነገሩ ለአንተ አዋቂ ፈረንጂ እንጂ የኢትዮጵያ ሊቃውን አይደሉም:: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ኢየሱስን አታዉቀዉም አልተባለም ትላለህ ታዲያ ካልተባለ ስለ ኢየሱስ ደጋግመህ ቱሪናህን ትነፋለህ:: ለምንስ ኢየሱስን ማህበረ ቅዱሳን እንደማያምን ግልጽ አደረገ እያልክ በበሬ ወለደ ቅርሻትህ ጆሮአችንን ታገማለህ? ስለ ኢየሱስ አንተን ብሎ ሰባኪ በፊትም ወደ ጠንቋይ እየሄድክ ቤተ ክርስቲያን ስታስነቅህ የኖርከው አንተ ነበርክ::


   እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ እንነጋገር ካልክ ግን ተሳስተሃል፡፡“እግዚአብሄር የቀደሰውን ክቡር ብትለው ከንቱ ነገርን ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው በዚያን ጊዜ በእግዚአብሄር ደስ ይልሃል፤ በምድርም ከፍታዎች ላይ አወጣሃለሁ”ኢሳ 58፡13የሚለውን ቃል ስለማታውቀው

   Delete
  3. አይ ያንተ ነገር! ይቺ ሰኔ ጎለጎታ ከመድገም ያላለፈችዉ እዉቀትህ ፈተና የምትሆንብህ ከሆነ ምናለ አርፈህ ብትቀመጥ?
   “ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ እግርህን ከሰንበት ብትመልስ፥ ሰንበትንም ደስታ፥ እግዚአብሔርም የቀደሰውን ክቡር ብትለው፥ የገዛ መንገድህንም ከማድረግ ፈቃድህንም ከማግኘት ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፥በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፥ በምድርም ከፍታዎች ላይ አወጣሃለሁ፥ የአባትህንም የያዕቆብን ርስት አበላሃለሁ የእግዚአብሔር አፍ ተናግሮአልና።” ትንቢተ ኢሳይያስ 58/13-14
   ይህንን ክፍል የጠቀስክበት ምክንያቱ ገብቶኛል፡፡ ነገር ግን ክፍሉ የሚናገረዉ በብሉይ ዘመን ከነበረዉ የኦሪት ሕግ ጋር በተያያዘ፣ በሰንበት(ለእግዚአብሔር በተለዬና በተቀደሰዉ ቀን) ሕዝቦች ሁሉ ደስ እያላቸዉ፣ በራሳቸዉ መንገድ ከመሄድ(ስጋዊ ተግባርን ከማከናወን) ታቅበዉ እርሱን እንዲያመልኩና እንዲያከብሩ እንጅ አንተ እንዳሰብከዉ አይደለም፡፡
   የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ኢየሱስን አታዉቀዉም አልተባለም የሚለዉን አሁንም ልድገምልህ አልተባለም፡፡ ኢየሱስን፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም፣ ማህበረ ቅዱሳንም፣ ሌላዉ ቀርቶ ሰይጣንም ያዉቁታል፡፡ አንተ ያልገባህ ማወቅ ማለት ምን እንደሆነ ነዉ፡፡ ማወቅ ብቻዉን ምንም ማለት አይደለም፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ስጋ ለብሶ መጥቶ ስለበደላችን በመስቀል ሞት የሞተዉ እርሱን እንድናዉቀዉ ብቻ ሳይሆን የህይዎታችን ጌታና አዳኝ አድርገን በፍጹም ልባችን እንድንከተለዉ ነዉ፡፡
   ኢየሱስ የሚለዉ ቃል ሲነሳ ለምን ጸጉራችሁ እንደሚቆም አይገባኝም፡፡ፈረንጅ የምትጠላ ከሆነ ያንተ ችግር ነዉ፡፡ ማርያም ራሷ እስራኤላዊ መሆኗን አታዉቅ ይሆን?

   Delete
 7. In my town town Hawassa every body protestant or orthodox says "Eyesus", "Eyesus", "Eyesus"... , but nothing special miracle I saw in this town.

  Any one who can answer? does the name Eyesus is greater than the name " Ab" B/c every body here is considered as christian/Arada when they say
  " beyesus sim" but not "besme Ab". Ohhhhhhhhhhh personally I have a special relation with Ab than Jesus. In bible we are sure that Ab is God, but not sure with the devinity of christ. B/c there are verses that indicate that he is not. Don't give me any name. I read bible what I understand is this.

  ReplyDelete
  Replies
  1. What do you mean? are you opposing the name JESUS? Don't you know the name christian(If you are christian) is drived from Christ? What do you believe if you not believe in this name?

   Delete
  2. እህት ማርታ የጸሐፊዎቹን ዓላማ እያሳካሽላቸው ስለመሰለኝ ትንሽ በመሃይምነት የተረዳሁትን ለማለት ፈለግሁ ፡፡ የጸሐፊዎቻችን ዓላማቸው ምንድር ነው ብትይኝ ፣ ቀላሉ መልሴ በዚህም በዛም ብለው በኦርቶዶክስ አማኝ ማኀበረ ሰብ ላይ ውዥንብር መፍጠርና ከእምነቱ እንዲወጣ ማድረግ ነው ፡፡

   አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስምና በአካል ሦስት ብለን ስንጠራ በዘመን መቀዳደምና በሥልጣን መበላለጥ እንደሌለባቸው አብረን በመረዳት ነው ፡፡ አብ አባት ነው ፤ ወልድ ደግሞ ልጅ ነውና ከአብ ተገኝቷል ፤ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ሕይወት ነውና ከአብ ሠርጿል ፡፡ የሁለቱም መገኛ አብ ስለሆነ ግን አብ አንጋፋ ወይም ታላቅ ፤ ወልድና መንፈስ ቅዱስን ደግሞ ትንሽ አድርገን መገመት አይገባንም ፡፡ ምክንያቱም በአገዛዝ በህልውናና በሥልጣን ሦስቱም እኩል ስለሆኑ ነው ፡፡

   ኢየሱስ ከሌሎቹ በተለየ የመወለድ ባህርይ ስላለው ፤ የአዳምና ልጆቹን በደል ካሳ ለመክፈል ፍጹም ሰው ሆነ ፤ በመስቀል ላይ ስለ እኛ ኃጢአት ነፍሱን በፈቃዱ ሰጥቶ ሞተ ፤ በአርማትያሱ ዮሴፍ መቃብር ተቀበረ ፤ በሦስተኛው ቀን በራሱ ሥልጣንም ተነሳ ፤ ወደ ጥንት ክብሩም የእኛን ሥጋ እንደ ተዋሃደ ተመልሶ በአባቱ ቀኝ ተቀመጠ ፡፡ ከንቱ የነበረው አዳም በኢየሱስ በኩል ከበረ ፡፡

   ይኸ ማለትም ፣ መስዋዕትነቱ በርሱ በተለየ አካል ስለተፈጸመ ኢየሱስን መስዋዕታችን ፤ የበደል ካሳችን በማለት እናከብረዋለን ፤ እናመሰግነዋለን ፡፡ እርሱ በመስቀል ላይ በተለየ አካሉ በደላችንን ሲሸከም ፣ የአብና የመንፈስ ቅዱስ ፈቃድም ጭምር በመሆኑ ምስጋናችንን ለአብና ለመንፈስ ቅዱስም ጭምር እናቀርባለን ፡፡ መነጣጠልና መመልከት የሰዎች ባህሪ ስለሆነ ፤ ከሦስቱ አንዱን ገንጥለን በመመስከራችን የምንጸድቅ እስኪመስል ድረስ ሊቆቻችን እያስተማሩን ነውና ሁሉንም ምሥጢር በአግባቡ እንድንረዳው በግል መጸለይ ይገባል ፡፡

   Delete
  3. I think you doctrinal interpretation or teaching about the Holy Trinity is correct. However, why do you accuse the writer for nothing? The writer is not protesting the Holy Trinity. You may want to disagree with them on other issues. Praise to the Holy Trinity, the Most High!

   Delete
  4. Unless you have another mission to deny the Trinity, your comment is irrelevant.

   Delete
  5. ስለ ስላሴ ያቀረብከው ገለጻ የሚያረካ ነው። "ከሦስቱ አንዱን ገንጥለን በመመስከራችን..." የሚለው ላይ መጠየቅ የምፈልገው እየሱስ ለሓዋርያቱ በስሙ ( በ እየሱስ ስም) አጋንንት እንዲያወጡ ና ድውያንን እንዲፈውሱ ልኳቸዋል:: ሌላ ቦታ ላይ "በርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፣ እርሱን ስሙት" ብሎ አብ እራሱ ስለ እየሱስ መስክⶂል። ይህንን እንዴት ታየዋለህ?

   Delete
  6. መልስ
   በቅድሚያ በሰጠሁት አስተያየት ላይ አመለካከታችሁን ያሰፈራችሁ ሁሉ ጌታ ይባርካችሁ ፣ ሰላማችሁንም ያብዛላችሁ ፡፡

   ወንድም ሙሴ የኢየሱስን ትምህርት መጥቀስህ የአብንም ምስክርነት ማውሳትህ መልካም ነው ፡፡ እኔም ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ እንዳልባል ኢየሱስ ካስተማረው ቃል እልፍ አልልም ፡፡ ከተግባባን የሚከተሉትን ጥቂት ኃይለ ቃሎች በጸሎት መንፈስ ተመልከታቸውና የምታስተምረኝ ካለ ለመታረም ፈቃደኛ ነኝ ፡፡ ምነው አንተም ገነጣጠልካቸው እንዳትለኝ ፤ የመጽሐፍ ቃሉን እንዳለ ነው ያስቀመጥኩት ፡፡ አጠቃላይ አቋሜ ላይ ከመጣህልኝ የማምንው በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ነው ፡፡

   እኔና አብ አንድ ነን። ዮሐ 10:30

   እኔን ስንኳ ባታምኑ አብ በእኔ እንደ ሆነ እኔም በአብ እንደ ሆንሁ ታውቁና ታስተውሉ ዘንድ ሥራውን እመኑ።ዮሐ 10:38

   በእኔ የሚያምን በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በእኔ አይደለም፤ እኔንም የሚያይ የላከኝን ያያል ዮሐ 12፡44-45

   እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ ስለ ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ። ዮሐ 14:11

   እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ። ዮሐ 12:49

   ትእዛዙም የዘላለም ሕይወት እንደ ሆነች አውቃለሁ። ስለዚህ እኔ የምናገረውን አብ እንደ ነገረኝ እንዲሁ እናገራለሁ። ዮሐ 12:50

   እኔ ከእግዚአብሔር ወጥቼ መጥቻለሁና፤ እርሱ ላከኝ እንጂ ከራሴ አልመጣሁምና። ዮሐ 8:42

   አብ ልፈጽመው የሰጠኝ ሥራ፥ ይህ የማደርገው ሥራ፥ አብ እንደ ላከኝ ስለ እኔ ይመሰክራልና። ዮሐ 5:36

   Delete
  7. ውድ ወዳጄ
   እኔም ብፍጹም ቅንነት ለመማርና ለመታረም ዝግጁ ነኝ:: ለዛሬው የማምንውንና በ ልቤ እውነት ሆኖ የተስማኝን ለመግለጽ እፈልጋለሁ።

   ያቀረብካቸው ጥቅሶች የአብንና የወልድን አንድነት ምስጢር የሚያሳዩ ቢሆንም፡ እየሱስ ለምን ተነጥሎ መታየት ወይም መሰበክ እንደሌለበት የሚያስረዱ አልመሰለኝም። አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ሲሆኑ፤ ሶስቱንም በየራሳቸው የተግባር ድርሻ እናውቃቸዋለን፡፡ በተናጠል መታወቃቸው ና መጠራታቸው አንድንታችውን፤ መለኮታዊ ማንነታቸውንም ሆነ ክብራቸውን አይሸራርፈውም ወይም አንዱን ከሌላው አያበላልጣቸውም፡፡ በተመሳሳይ እየሱስን ነጥሎ መስበክ የስላሴን እውነት ማጨለም አይደለም ብዬ አምናለሁ። ይልቁንም የ እየሱስ ስም መግነን ለእግዚአብሔር አብ ክብር መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል፡፡ ከላይ ከጠቀስኩት የአብ ምስክርነት በተጨማሪ፤ ጳውሎስ በፊሊጵስዮስ መልዕክቱ እግዚአብሔር ከስሞች ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ስም ለእየሱስ እንደሰጠው ጠቅሶ “ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥ ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው” ፊል 2:10-11 ይላል።

   አንተ በትክክል እንዳስቀመጥከው “ኢየሱስ የአዳምና ልጆቹን በደል ካሳ ለመክፈል ፍጹም ሰው ሆኖ ፤ በመስቀል ላይ ስለ እኛ ኃጢአት ነፍሱን በፈቃዱ ሰጥቶ ሞተ ፤ በአርማትያሱ ዮሴፍ መቃብር ተቀበረ ፤ በሦስተኛው ቀን በራሱ ሥልጣንም ተነሳ ፤ ወደ ጥንት ክብሩም የእኛን ሥጋ እንደ ተዋሃደ ተመልሶ በአባቱ ቀኝ ተቀመጠ ፡፡ ከንቱ የነበረው አዳም በኢየሱስ በኩል ከበረ ፡፡”

   በመሆኑም፡ እየሱስን መስዋዕታችን ፤ የበደል ካሳችን በሞቱ የዘላለምን ሕይወት የሰጠን በማለት እናከብረዋለን ፤ እናመሰግነዋለን፡፡ ከዚያም አልፎ፡ እየሱስ ሓዋርያቱን እንዳዘዘው የቤተክርስትያን ተልእኮ የሆነውን ለብዙዎች መዳን ምክንያት የሆነውን/የሚሆነውን የመስቀሉን ድንቅ ስራ ለአለም ሁሉ እንናገራለን::

   Delete
  8. ወንድም ሙሴ ሁለታችንም አንድ ምዕራፍ ላይ ነን ፡፡ ልዩነታችን እኔ እግዚአብሔር ተነጥሎ ሳይሆን በሦስትነቱና አንድነቱ መሰበክ አለበት ማለቴ ላይ መሰለኝ ፡፡

   ወደ ኋላ መለስ ብለን የአይሁዳውያንን እምነት ከመጽሐፍ ብንፈትሸው ፤ እግዚአብሔር አብን አባት ብሎ ለመቀበል ቅንጣት የምታህል ችግር አልነበራቸውም ፡፡ ነገር ግን መሲሁን እየጠበቁ ባለበት ሁኔታ ኢየሱስ ተወለደ ፡፡ ይህን ኢየሱስን ፣ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ፣ ክርስቶስ ርሱ ነው ብሎ ለመቀበል ግን እጅግ ድካም ነበረባቸው /እንደ እስልምና አይሁድም እግዚአብሔር ወለደ የሚለውን ቃል አይቀበሉም/፡፡

   በመጽሐፍ ከቀረበልን መከራከሪያ ሃሳቦቻቸው ጥቂቱን ለመጥቀስ
   - መሲህ ቢሆን የሙሴን ህግ አይሽርም /ሰንበትን ፣ ራስን የማጽዳት ሥርዓት ፣ የተለምዶ ጾማቸውን ስላላከበረ/
   - የሚጠበቀው ክርስቶስ ከማን እንደሚወለድ አይታወቅም /ኢየሱስ ግን እናቱ ማርያም አባቱ አናጢው ዮሴፍ እንደሆነ ያውቃሉ/
   - መሲሁ ዘለዓለማዊ ንጉሥ ነው የሚሆነው /ኢየሱስ ግን እሞታለሁ ብሎ መስክሯል/
   - መሲህ ባለ ብዙ ግርማና ፣ ሁሉም በራሱ ፍላጐት የሚማረክለትና የሚከተለው መሪ ነው
   - ክርስቶስ መለኮታዊ ዝርያ አይኖረውም /ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ በማለቱ /ዮሐ 19፡7/
   - መሲህ ቢሆን የኢየሩሳሌምን ገናናነት ፤ የእሥራኤልን ነጻነት ይመልሳል /ኢየሱስ ግን ለምድራዊ የሥጋ ነጻነት አልመጣም/….. ሌሎች ብዙ ምክንያቶችንም መደርደር ይቻላል ፡፡

   እንግዲህ እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ ነውና ፤ ይህን ስንፍናቸውን ስለተረዳ ፤ በተደጋጋሚ ልጁ መሆኑን በመመስከር ቃሉን ሰጥቷል /በዮርዳኖስ ባህርና በደብረ ታቦር ተራራ/ ፡፡ “ስለ ራሴ የምመሰክር እኔ ነኝ፥ የላከኝም አብ ስለ እኔ ይመሰክራል።” ዮሐ 8:18 በማለት የአብ ምስክርነት እንዳለው ልጅም በበኩሉ ተናግሯል ፡፡ “የእግዚአብሔር የባህርይ ልጅ መሆኑንም በተደጋጋሚ ለማስረዳት ሞክሯል /ዮሐ 10:36 ፣ ዮሐ 11፡4/ ፡፡ ዲያብሎስ እንኳን እንዳቅሙ አስቀድሞ ማረጋገጥ የፈለገው ይህንኑ የኢየሱስን የእግዚአብሔር ልጅነት ነበር /በገዳመ ቆሮንቶስ በጾሙ ወራት ያቀረበለትን ፈተና ያስታውሷል/

   ይኸን ሁሉ ዝርዝር መዞር ያስፈለገኝ ኢየሱስን በእግዚአብሔር ልጅነቱ መቀበል ካልቻልን ፤ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የገለጸው ፍቅሩ ይደበዝዝብናል /አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድርስ ዓለሙን ወዷልና (ዮሐ 3፡16) ማለት አንችልም/ ፤ እግዚአብሔር በተዋሕዶ የፈጸመው መስዋዕትነቱ ይሻራል ለማለት ፈልጌ ነው ፡፡ ስለነዚህም ምክንያቶች በወንጌል ኢየሱስን የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነና ርሱን እንድናምን በይበልጥ መስበክ አስፈልጓል ፡፡ አብ ይህን ቃልና ምስክርነት ሲሰጠን እየሱስም ስለ አብና ስለራሱ ያስተማረውን ደግሞ እጠቅሳለሁ ፡፡

   የላከኝንም (አብን)የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው ዮሐ 5፡24
   በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው። ዮሐ 6፡47
   ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር (አብን)እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። ዮሐ 14:1 (በቅንፍ ያሉ ቃሎች የኔ የግንዛቤ ትርጉሞች ናቸው)

   በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እኔ አደርገዋለሁ። ዮሐ 14:13
   አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንዲሰጣችሁ፥ ዮሐ 15:16

   በተረፈ በሥላሴ ቸርነት መግለጫ ውስጥ በባሪያው መልክ ሊሆንና ሥጋዊ ባህሪያችንን ልዋሃድ የፈቀደ ኢየሱስ ስሙ ሊገን ፣ በመስቀል ላይ ስለከፈለውና ስለእኛ ስለአደረገው ውለታው ሁሉ ሊመሰገን ይገባል የሚልን መልዕክት አልቃረንም ፡፡

   ውይይታችን ስለ አብና ኢየሱስ ብቻ መሆኑ ፣ በመንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔርነት ላይና መመለክ ልዩነት የሌለን ስለመሰለኝ ነው ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ቀልድ እንደማይኖር ጌታም አስተምሮናል ፡፡
   እግዚአብሔር ጸጋውን ለሁላችንም ያድለን ፤ አሜን

   Delete
 8. Mar mar alew kenferen Mariam elalehu zarem
  Yelbie eko nesh degua enate Emebetie
  Z. Mirtnesh

  ReplyDelete
 9. ምሕረተአብም ሆነ የማኅበረ ቅዱሳን ጀሌዎች የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሲነሳ ገና ገና እንደ አዶ ከበሬ ያስገዝፋቸዋል፡፡ ፀረ ክርስቶሶች ናቸውና. . . . . . ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. I agree 100% with you.

   Delete
  2. you brothers says that EOTC do not deny Jusus but you confirmed that

   Delete
  3. ante b men seltanek new sewen megestis yemetechelew ortodox kehonk ketetegnawen emnet yaz [astesaseb] atesasat mahebere kidusan yeteshalu nachew

   Delete
 10. Jesus christ the son of God is lord forever whether you belive or not.Please do not give his glory to others.keep on your eyes on jesus only.

  ReplyDelete
 11. The devil is using Mahibere Kidusan and Mehretab so becareful people.
  The blog and the mezmur is good, thank you and God bless.

  ReplyDelete
 12. ኢየሱስ ክርስቶስን ወልደ አብ ወልደ ማርያም በተዋሕዶ የከበረ ብሎ የማያምን የኦቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ አጋጥሞኝ አያውቅም። ለምን ነው ሐሰት የምትመሰክሩት ? 'ቃል ሥጋ ኮነ ወሐደረ ላእሌነ'' የሚለው የማንን ሥጋ ነው ኢየሱስ ሥጋው አድርጎ ከእኛ ጋር የተዛመደው ? የቅድስት ድንግል ማርያምን አይደለም ወይ? ጻድቃንን ፥ ሰማዕታትን፥ መላእክትን እኮ የምናከብረው ክብር ከሰጭው ማለት ከክርስቶስ ስለተሠጣቸው ነው እንጅ ከራሳችን እመንጭተን አይደለም። እርሱ ያከበራቸውን ማክበራችን እንዴት በደል ሁኖ ሊቆጠርብን ይችላል ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. Silzihe egnam anten enakibrih malet new?

   Delete
 13. Hulem Telat siraw metekemiawn eyefelege getan mekawem new aygermenim.

  ReplyDelete
 14. Telat dirom siraw yihew new Aygermegnm

  ReplyDelete
 15. MK is a destructive element in the church. They are enemies of the Gospel. Why do they engage in blackmail and defamation? I think that is their nature which is very similar to that of satan, their father.

  ReplyDelete
 16. Jesus King of Kings!

  ReplyDelete
 17. እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው፤
  በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው።
  በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማሪያም ያገኛል። የዮሐንስ ወንጌል 10/10

  ReplyDelete
 18. go head guys say everyday Jesus is great. He is the Liopn of Judah Amen.......................

  ReplyDelete
 19. That is what matters. Work. Go work. Publish books, audio cds, spiritual songs, etc.

  Let the people know what is being Christian is all about. Being Christian is to be a friend of Christ our Lord.

  Christian is what we are called for following the footsteps of Jesus up to the Cross, like our Lady Holy Virgin Mary, the true example and model of Christians.

  ReplyDelete
 20. genzeb lela Eyesus lela menew and sew lehulet getoch megezat aychelem yemilewen resachehut commercial mezmur ale ende negerun metew new yemishalew

  ReplyDelete
 21. TEHADISO NACHIHU WEYIM PENTE BOTH ARE THE SAME!

  ReplyDelete
 22. First every one should save his own life then worry about others,to do this we must follow our forefathers,because they know the correct way that leads to the kingdom of GOD.By judging other individuals,or groups we can not save our own soul,but lossing it this is because JUDGMENT Judgment is only to GOD,but not to sinners like us and other people.

  ReplyDelete