Thursday, November 29, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ «ብላክ ማርኬት» እንዳለው ተሰማ

ድብቅ አላማ ይዞ በሃይማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀሰው ማኅበረ ቅዱሳን በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ ህገወጥ የውጭ ምንዛሪ ቢሮ በድብቅ መክፈቱን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ እንደ ምንጮቻችን ከሆነ ማኅበሩ ለዚህ ህገወጥ ተግባር የሚጠቀምበት ቢሮ በስም «የቲዎሎጂ ምሩቃን ማኅበር» እየተባለ የሚጠራውና የቲዎሎጂ ምሩቃን በአባልነት የሌሉበትና ማንያዘዋልን ጨምሮ ጥቂት የማቅ «የቲዎሎጂ ምሩቃን» አባላት የሚገናኙበት ቢሮ ነው ብለዋል፡፡ ቢሮው ቀድሞ ከነበረበት ከቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲወጣ ከተደረገ በኋላ ማኅበረ ቅዱሳን በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ ቢሮ እንዲያገኝ አድርጓል፡፡ ይህን ያደረገውም የውጭ ምንዛሬውን ጨምሮ ሌሎች ድብቅ ስራዎችን ለመስራትና ለመጠቀም አስቦ እንደሆነ ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡ ቢሮው የማቅ ሌላው ቢሮ ነው እያሉም ነው፡፡ ማኅበሩ የዶላር ዩሮና ፓውንድ ምንዛሬዎችን የሚያካሂደው በድብቅ ሲሆን ከውጪ አገር ዶላር ይዘው የሚመጡና ዶላር የተላከላቸው የማኅበሩ አባላትና አንዳንድ ጳጳሳትም ዶላር ዩሮና ፓውንድ በዚሁ ቢሮ እንዲመነዝሩ እንደሚደረግ የደረሰን መረጃ ያመለከታል፡፡ መንግስት የዶላር እጥረት አጋጥሞኛል በሚልበት በዚህ ወቅት ማቅ እንዲህ እያደረገ መሆኑ ጉዳዩን አነጋጋሪ አድርጎታል፡፡
 
ማኅበሩ ይህን ህገወጥ ስራ እንዲሰራ የመደበው ሃይለ ማርያም አያሌው ዘላሊበላ የተባለውና በአሁኑ ጊዜ የምሩቃን ማኅበር ተብዬው ምክትል ሊቀመንበር መሆኑም ታውቋል፡፡ ምክትል ሊቀመንበር የሆነው ለሽፋን እንደሆነና ዋና ስራው ግን የማቅን የምንዛሬና ሌሎች ህገወጥ ስራዎችን ማከናወን እንደሆነ የሚናገሩት ምንጮች ግለሰቡ ከእጁ ትልቅ ቦርሳ እንደማይለይና እስከ 50 ሺህ ብር የሚደርስ ገንዘብ ለምንዛሬው ይዞ እንደሚንቀሳቀስ ተናግረዋል፡፡ ከአንዳንድ ከማህበሩ ጋር ንክኪ ካላቸው ኪራይ ሰብሳቢ የመንግስት ሰራተኞች ጋር በመመሳጠርም ኮንዶሚኒየም ቤት ላልተመዘገቡ የማህበሩ አባላት በህገወጥ መንገድ እንዲያገኙ ማድረግ የሃይለ ማርያም አያሌው ሌላው ስራ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮቻችን ኮንዶሚኒየም ያልተመዘገቡ አባላትን 20 ሺህ ብር በማስከፈል በፎርጅድ መረጃዎች ስማቸው ኮምፒውተር ላይ እንዲገባ የሚያደርግ ሲሆን ሲረከቡ ደግሞ 70 ሺህ ብር እንዲከፍሉ እንደሚያደርግ ምንጮቻችን ገልጸው እስካሁን ከ50 በላይ ኮንዶሚኒየም ቤቶችን ለማኅበሩ አባላት ማሰጠቱን ተናግረዋል፡፡ በዚህ ህገወጥ ስራ በሚሰበስበው ገንዘብ ለራሱ ጆሞ ሳይት ላይ በ200 ሺህ ብር ባለሱቅ ኮንዶሚኒየም ቤት እና በ30 ሺህ ብር 2 ጋሪ ከነፈረሶቹ ገዝቶ እያከራየ መሆኑንም ምንጮቻችን የገለጹ ሲሆን ቤቱን ከማህበሩ እውቅና ውጪ ገንዘብ ወጪ አድርጎ በመግዛቱ ከማቅ ጋር ጭቅጭቅ ውስጥ ገብቶ እንደነበረና ካለረፋችሁ እኔም ሌላውን ሚስጢር እንዳላወጣ በማለት ስላስፈራራ ጉዳዩ ተከድኖ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ሃይለ ማርያም የላሊበላ ሰው በመሆኑና ባለጊዜዎቹንና የወንዙን ሰዎች እነአባ ህዝቅኤልን ስለተማመነ ቤተክህነት ውስጥ እንደልቡ እየተንቀሳቀሰ ነው ይላሉ፡፡  

16 comments:

 1. RASACHUN ASFOGRACHU....EHADIGOCH ENDEHONACHU!!

  ReplyDelete
 2. ጉድ ጉድ ጉድ ነው።ማቅ መቀመቅ እየወረደ ነው። ይህ ግፋኛ ማህበር የቅዱሳኑን ስም ተላብሶ black market ከፍቶ በቤተ ክህነት ግብ በድፍረት ይነግድ ገባ። እግዚአብሔር አምላክ ገና ገና ያጋልጠዋል።በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የሚነግድ ደፋር እባብ ነው። በሃይማኖት ስም የሚነግድ ያ የሐሰት አባት ሐሰትን ከውስጥ አውጥቶ ይናገራል፡ ዮሐ ም 8 ላይ እንደተባለው ማቅ በአንደበቱ ቅዱስ በሥራው ግን እርኩስ ስራ የሚሰራው ክፉ የጨለማ ሰይጣን ነው። ገና ገና ብዙ ጉዱ ይወጣል ። ትግሱት ይስጠን ። የቀደመው የይሁዳ ሥራ ዛሬም እየደገመ ነው። ምክንያቱም ከነዋይ ጋር ትስስር ስላሌው። ይሁዳ ጌታውን ለሞት አሳልፎ የሰጠው ለገንዘብ ብሎ ነበር። ዛሬም የይሁዳ እርሾ የሆነው ማቅ ቤተ እግዚአብሔርን በገንዘቡ ጳጳሳቱንና አንዳንድ ካህናትን ቆልፎ ይዞዋቸው እያባላቸው ነው። የተላኩበትን ትተው ዛሬ ለስልጣንና ለገንዘብ ብቻ ሆኖዋል ሩጫውና ድካማቸው። አባ ሰላማዎች በርቱ እውነቱን ከማውጣት ዝም አትበሉ። የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. yibalal bilo were yelem ergitegna hunachuh awru, degimom yetsafachuhit minim ayasdaminm yetilacha yimaslal!

   Delete
 3. Hailemariam, Gobez! Anbesa! Esey!

  ReplyDelete
  Replies
  1. አረ ባክህ!! ጭለማ እንደ አንተ አይነቱ ጭለማ እኮ ነው የማቅ አባል እየሆነ ቤተክርስቲያኒቱን ወደ ጽልመት እየመራት ያለው፡፡ክርስትናው ቀርቶ በኢትየፐጵያዊነት እንኳ ቢያንስ በሚያሳፍረው ነገር ለማፈር ሞክር

   Delete
 4. Do you surprise by that? We will see more from Mahibere Seitan. They have no any religious element. They are simply a group of "Mafia". Shame to hear them calling themselves"Kidusan".

  ReplyDelete
 5. ወይ ጉድ የማቅ ነገር ግርም ይለኛል

  ReplyDelete
 6. meche yehon ewnet yemtnagerut???? benente bet mengistnena mehaberun magachatachehu new. yematerebu (Good for nothing) mehaberu yerasun sira yeketlal enantem kesashnetachehun tiketlalachihu lela yemimeta neger yale aymeslegnem. kis tewuna sira seru. yemitekemachu sira newna, kis gin goteto siol yewsdachihual.Asebubet. websitachehu mehaberun kemikes tsehuf wechi lela menem neger yelewem. Benegerachin lay yenanten web-site manbeb kejemrku behual salasbew yemehaberu degafi hognalehu bekirbum abalenet lemeteyek eyetezgajehu new. edmyachu yeterna tshufachihun bemanbebe badonetachehun terdchalehu beantsaru degmo yemehaberun tiru gon mayet chialehu.

  ReplyDelete
  Replies
  1. እውነትን መቀበል ከፈለክ ይህ እውነት ነው፡፡
   ከቤተክህነት ስራተኞች አንዱ

   Delete
  2. የአይጥ ምስክር ድንቢጥ አሉ ፡፡
   የቤተ ክህነት ሰራተኛ ከሆንክና ይህን ወንጀል ካወቅህ ስለምን ለፖሊስ በምስጢር ጠቁመህ እንዲያዙ አላደረግክም ወይስ የጥቅም ተካፋይ ሆነህ እንዳይጎድልብህ ከሁለት ወገን ማገልገልህ ይሆን
   እዚህ ላይ ለንባብ መቅረቡ ወንጀሉን አንባቢ እንዲመረምር ታስቦ ወይስ በነገሩት የሚሄድ በጎተቱት የሚከተል እንስሳ መስሎአችሁ
   ለአንባቢ የሚቀርብ ዜና ሲያጥር አንድም እንደ አንዳንዶች ከአካባቢያችሁ ቤተ ክርስቲያን ነክ ዜና ላኩልን ብሎ ትብብር ይጠይቃል ፤ ሌላው ደግሞ እንደዚህኛው የበሬ ወለደ ልብ ወለድ ድርሰት ጽፎ ያስነብባል ፡፡
   ወንጌሉን የሚያስተምር ፣ የሚመረምር ፣ ለመገንዘብ የሚያስቸግሩ ዘሮችን የሚፈታ ሊቅ ጠፍቶ ባለበት እንዲህ ሥራ መፍታት ምን ይባላል ፡፡

   Delete
  3. ቀለሟ አልታይ ያለች አስተያየቴ ፣ ሦስተኛ መሆኗ ነው መሰል
   የአይጥ ምስክር ድንቢጥ አሉ ፡፡
   የቤተ ክህነት ሰራተኛ ከሆንክና ይህን ወንጀል ካወቅህ ስለምን ለፖሊስ በምስጢር ጠቁመህ እንዲያዙ አላደረግክም? ወይስ የጥቅም ተካፋይ ሆነህ እንዳይጎድልብህ ከሁለት ወገን ማገልገልህ ይሆን?
   እዚህ ላይ ለንባብ መቅረቡ ወንጀሉን አንባቢ እንዲመረምር ታስቦ ወይስ በነገሩት የሚሄድ በጎተቱት የሚከተል እንስሳ መስሎአችሁ?
   ለአንባቢ የሚቀርብ ዜና ሲያጥር አንድም እንደ አንዳንዶች ከአካባቢያችሁ ቤተ ክርስቲያን ነክ ዜና ላኩልን ብሎ ትብብር ይጠየቃል ፤ ሌላው የታደለው ደግሞ እንደዚህ የበሬ ወለደ ልብ ወለድ ድርሰት ጽፎ ያስነብባል ፡፡
   ወንጌሉን የሚያስተምር ፣ ቃሉን የሚመረምር ፣ ለመገንዘብ የሚያስቸግሩ ዘሮችን የሚፈታ ሊቅ ጠፍቶ ባለበት እንዲህ ሥራ መፍታት ምን ይሉታል ? ወይስ ዋና ህመማችሁን ገንዘብ ነው ልበል?

   Delete
 7. yewahoc nacehu.mk endehone atokomutem.mengest endesemacehu abayen gedeben bemiesael lemeta new belu.betam asazenacehug.

  ReplyDelete
 8. If u are confident with bible & Jesus why don't u post comments which question devinity of Jesus? Is that is not ur agenda to teach with such question.

  u r obsessed with MK not truth.

  ReplyDelete
  Replies
  1. You are not the first person to question the divinity of Christ, so don't feel so special. It was dealt with way before you came to existence. Maybe you should read some church history and come to your senses. Jesus is God incarnate, period.

   Delete
 9. ለምን የራሳችሁን ሥራ አትሠሩም በቃ ዝም አሉአችሁ ዝም አትሉም የቤ/ክ አምላክ ማስተዋሉን ይስጣችሁ

  ReplyDelete
 10. በእኔ አመለካከት የወንጌልን እውነት መግለጥ የማኅበረ ቅዱሳንንና የሌሎችንም ቤተክርስቲያኒቱን የተጣቧትን ተውሳኮች እኩይና ሰይጣናዊ ስራ ማጋለጥ ተገቢ ነው፡፡ በቅዱሳን ስም እየተጠራ የሰይጣንን ስራ የሚሰራውን ማቅን ከማጋለጥ የበለጠ ስራ የለም፡፡ ስለዚህ አባ ሰላማዎች በሁለቱም አቅጣጫ በርቱልን፡፡ እናንተ ይህን ብሎግ ከመጀመራችሁ በፊት የማቅ ብሎጎች ብቻቸውን አባ ጳውሎስን እያብጠለጠሉ ሚዛናዊ ያልሆኑ ወሬዎችን ያናፍሱ ነበር፡፡ እነርሱ ብቻም ትክክል ይመስሉን ነበር፡፡ ዛሬ ግን ያ ተለውጧል፡፡ አሁን ሰዉ አባ ሰላማስ ምን አለ? የሚለውን ለማንበብ ከፍተኛ ጉጉት አድሮበታል እንጂ ደጀሰላም ያለውን ብቻ ተቀብሎ ዝም አይልም፡፡ የአባ ሰላማ መረጃዎችን ከማቅ መንደር ፈልፍሎ ማውጣቱ ማቆቹ ደስ አያሰኛቸውም ስለዚህ ለምን የራሳችሁን ስራ አትሰሩም ወዘተ የሚል የማዳከሚያ አስተያየት ይሰነዝራሉ፡፡ በእኔ ግምት ስራችሁን እየሰራችሁ ነውና በርቱ፡፡

  ReplyDelete