Friday, November 30, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን ብሎግ ደጀሰላም የወሬ እጥረት ያጋጠመው ይመስላል

ክፍተቱ የተፈጠረው ከቤተክህነት ወሬዎችን የሚለቃቅመውና የሚያቀብለው ማንያዘዋል ግብጽ ስለሚገኝ ነው

ማኅበረ ቅዱሳን የእኔ አይደለም እያለ የሚያስተባብለውና የእርሱ መሆኑ ግን የሚታወቀው «ደጀሰላም» የወሬ እጥረት ያጋጠመው መሆኑ እየታየ ነው፡፡ ራሱም ኅዳር 18/2005 ፖስት ባደረገው ጽሑፍ  «በየአካባቢያቸው ያለውን የቤተ ክርስቲያንን ሁኔታ በመከታተልሪፖርትየሚልኩልን ፈቃደኛ ደጀ ሰላማውያንአለንእንዲሉን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን» ብሏል፡፡ የወሬ እጥረቱ የተፈጠረው እንደእርጎ እንትን በየቦታው ጥልቅ የሚለውና የደጀሰላም ዋና ወሬ አቀባይ የሆነው ማንያዘዋል ለግብጹ ፓትርያርክ ባኣለ ሲመት ከጳጳሳት ጋር ተለጣፊ ሆኖ በማኅበሩ ወጪ ወደግብጽ ስለሄደና እስካሁን ድረስ በአገር ውስጥ ስለሌለ ነው ተብሏል፡፡ ማንያዘዋል ለአንድ ወር ቆይታ በማኅበሩ 32 ሺ ብር ወጪ ተደርጎለት የሄደ መሆኑ ቢታወቅም እርሱ ግን የከፈለልኝ የቲዎሎጂ ማኅበሩ በማለት ያስወራ እንደነበር ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡  ማኅበሩ በገጠር አብያተ ክርስቲያናትናት በገዳማት ስም ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር የሚሰበስበውን ገንዘብ እንዲህ ባለመንገድ እንደሚያባክን ይህ አንዱ ማሳያ ነው፡፡
 
ማንያዘዋል ወደግብጽ ከሄደ በኋላ «ማንያዘዋልና ማኅበሩ ለግብጽ ካላቸው ፍቅር የተነሳ አባይ እንዳይገደብ ይጠይቃል» እየተባለ ቤክህነት አካባቢ እየተቀለደ ነው፡፡ ከእርሱ ጋር ተሾመ በየነ የተባለ የማታ የቲዎሎጂ ተማሪና የወቅቱ የቲዎሎጂ ምሩቃን ማኅበር ተብዬው ሰብሳቢ ዘውዴ ገ/እግዚአብሔር በተባለች የማኅበረ ቅዱሳን ቀንደኛ ሰው ስፖንሰር ተደርጎ መጓዙ ተሰምቷል፡፡ ማኅበሩ ከማንያዘዋል በተጨማሪ ወደግብጽ ለፓትርያርኩ በኣለ ሲመት ሄደው ከነበሩትና ጥቅሜን ያስጠብቁልኛል ብሎ ለፓትርያርክነት ካጫቸው መካከል አንዱ ለሆኑት ለወዳጁ ለአቡነ ሉቃስ አንድ ሺ ዶላር የኪስ ገንዘብ መስጠቱም ተሰምቷል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ማንያዘዋል ሙሉ ጊዜውን በፓትርያርክ ምርጫ ላይ እንዲያውልና ለማኅበሩ የሚጠቅም ስራ እንዲሰራ ለማድረግ በማሰብ ከቲዎሎጂ ማኅበሩ ሰብሳቢነት እንዲለቅ መደረጉን ምንጮቻችን ገልጸው ማቅ በቀጣዩ ፓትርያርክ ምርጫ ላይ የራሱን ተጽእኖ ለማሳደርና ለእርሱ ታማኝና ታዛዥ የሆነ ፓትርያርከ በመንበሩ ላይ ለማስቀመጥ ውስጥ ውስጡን ከፍተኛ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡  
   

7 comments:

 1. Is there any body that understands well and explain to me what the word dog and puppy stands for in the following verses of the New Testament?

  Matt 7:6 በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ፥ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፥ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ።

  Matt 15: 22 እነሆም፥ ከነናዊት ሴት ከዚያ አገር ወጥታ። ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ፥ ማረኝ፤ ልጄን ጋኔን ክፉኛ ይዞአታል ብላ ጮኸች።
  Matt 15: 24 እርሱም መልሶ። ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም አለ።
  Matt 15: 26 የልጆችን እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገባም አለ።
  Matt 15:27 እርስዋም። አዎን ጌታ ሆይ፤ ቡችሎችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ አለች።

  Mark 7: 26 ሴቲቱም ግሪክ፥ ትውልድዋም ሲሮፊኒቃዊት ነበረች:: ከልጅዋ ጋኔን ያወጣላት ዘንድ ለመነችው።
  Mark 7:27 ልጆቹ በፊት ይጠግቡ ዘንድ ተዪ የልጆቹን እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገባምና አላት።
  Mark 7:28 እርስዋም መልሳ። አዎን፥ ጌታ ሆይ፥ ቡችሎች እንኳ ከማዕድ በታች ሆነው የልጆችን ፍርፋሪ ይበላሉ አለችው።

  Phil 3:2 ከውሾች ተጠበቁ፥ ከክፉዎችም ሠራተኞች ተጠበቁ፥ ከሐሰተኛም መገረዝ ተጠበቁ።

  Rev 22:15 ውሻዎችና አስማተኞች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትንም የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. እንዴት ነው ጎበዝ ጥያቄዬን ንፋስ መታት እኮ ፤ የሚሞክራት ሰው ጠፋ ፡፡ ወይስ እስልምና ውሻ ነጂስ ነው የሚለውን ትምህርት እኔም ክርስትናም እንዲሁ ይላል ብዬ ልቀበል ፡፡

   Delete
 2. Why not they hire reporters. They are merchants having multi-million capital. lol

  ReplyDelete
 3. wayni mathe nawe gen kalae wanegale yametasenabebune huli sela aned mahebare beka ayagebanem wanegalen betha sebakune latefute enetaleyelathewe ya keesetose feker ayelayan

  ReplyDelete
 4. እውነት ነው። ምንጫቸው የገንዘብ ብዛት ነበር።ገንዘቡንም የምሰጡዋቸው የሰንበት ት/ቤተ መዘምራንም አስራታቸው ለቤተ እግዝአብሔር እንጅ ለማህበረ ቅዱሳን መስጠት የለብንም እያሉ ገሸሽ በማለታቸው ነው። ያላቸውን ገንዘብ ለጳጳሳቱ ጉርሻ እያደረጉ በመሆኑ መንገዱ ሁሉ እግዚአብሔር እየዘጋበት ነው። የውሸት ወሬውም ከደጀ ሰላም እየጠፋ የመጣው ከገንዘቡም እጥረት ጋር በመሆኑ ወሬ አቀባዮች አባቶች ፊታቸውን ከማቅ እያዙሩ ስለሆነ ነው። የዋልድባም ወሬ ይሄው ማግኘት ተስኖዋቸው ምንጩ እየደረቀባቸው ዉሸቱ ሆሉ አለቅባቸው። አሁን ሌላ የዉሸት ነገር እየፈለጉ አንደ አጋሻው ሌላ ግዜ የእርቅ ነገር አልያም ዛሬም እንደትላቱ ስለ ዉግዘት መጮህ ብቻ ነው። ይገረማል ይደንቃል።

  ReplyDelete
 5. sele selam senawera selam megemer yalebet keyet endehone mawek yaleben yemeslegnal .selam be betekerstiyanachen endisefen kefelegen lemen egna lemesmamat anemokerem ewnet new akahedachehun kemaymesel sew gar hebret atefteru tebelual .ene yemeteyekachu neger binor enante ye lela maheberen sem hule eyanesachu kemetesedbu lemen sew ewnetegnawen mengd yezo endihed tekuretachu mastemar lay ayhonem? weyse ye enanten dekemet be lela maheber sem bematfat lemeshefen eyemokerachu new? BETEMELESULEGN DES YELEGNAL

  ReplyDelete