Sunday, November 4, 2012

የቤተ ክርስቲያን አንድነት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል

በአገር ቤትም በአሜሪካም በስደት ያሉት ሲኖዶሶች ስብሰባቸውን አድርገው የአቋም መግለጫዎችን አውጥተዋል። ከቤተክርስቲያን አንድነት ጋር ተያይዞ የወጡት መግለጫዎች ሲፈተሹ ግን ቀሪው የቤት ስራ የቤተ ክርስቲያንንን አንድነት ለማምጣት ቀላል እንዳልሆነ መገመት አያስቸግርም። የአዲስ አበባው ሲኖዶስ በአንድ በኩል የዕርቅና የሰላም ሂደቱ እንዲቀጥል ፈቃዱ መሆኑን ቢገልጽም የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ወደ መንበራቸው መመለስን አልተቀበለም። ለስድስተኛ ፓትርያርክ ምርጫም በዝግጅት ላይ ነው።

ለዚህ እየቀረበ ያለው አንዱና  ዋናው ምክንያት አቡነ ጳውሎስን 5ኛ ፓትርያርክ ብለን እንደገና ወደ 4ኛ ፓትርያርክ አንመለስም የሚል ነው። ይሁን እንጂ ፓትርያርክ ሳይሆኑ ወደ አገር ቤት ገብተው በፈለጉት ስፍራ ተከብረው መቀመጥ እንደሚችሉ ሲኖዶሱ ወስኗል። ከዚህ ቀደም ለዕርቁ ሂደት ትልቁ እንቅፋት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ናቸው እያሉ ሲናገሩ የነበሩ አንዳንድ ጳጳሳት ከእርሳቸው ህልፈት በኋላ በያዙት አቋም እንቅፋት እየሆኑ ያሉት እነርሱም መሆናቸውን እያንጸባረቁ ነው።

በአዲስ አበባው ሲኖዶስ በኩል ሆኖ ነገሩን ላየው ሰው ፓትርያርክ መርቆሬዎስን ወደመንበረ ፕትርክናቸው መመለስ ታሪክን የማዛባት ነገር እንደሚያስከትልና የፓትርያርክ ጳውሎስን ሕጋዊነት በጥያቄ ውስጥ እንደሚከት ይታወቃል። ከዚህ አንጻር የፓትርያርክ መርቆሬዎስ ወደፕትርክና መመለስ የማይታሰብ ይሆናል። ጥያቄው ግን ከሁሉ በፊት የቤተክርስቲያን አንድነት ይቀድማል ወይስ እንዲህ ያለውን ታሪክ ማስጠበቅ?

በአሜሪካ የሚገኘውና ሕጋዊው እኔ ነኝ የሚለው ሲኖዶስ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው ከቤተክርስቲያን ሰላምና አንድነት የበለጠ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ እንደሌለ ገልጾ የአዲስ አበባው ሲኖዶስ ፓትርያርክ መርቆሬዎስን ወደመንበራቸው ለመመለስ ከተስማማ ቅዱስ ሲኖዶሱ አንድ፣  እረኛው አንድ  ቤተክርስቲያኒቱም አንድ ይሆናሉ ብሎ እንደሚያምን ግልጽ አድርጓል። ይህን የሰላምና የአንድነት በር ከፍቶ እየጠበቀ ባለበት በዚህ ወቅት የከፋ ስሕተት በመፈጸም ቤተክርስቲያንን ወደ በለጠ ጥፋት እንዳያስገቧትም በአዲስ አበባ ለሚገኙት ጳጳሳት ጥሪ አቅርቧል። የአዲስ አበባው ሲኖዶስ ለ6ኛ ፓትርያርክ ምርጫ እየተዘጋጀ መሆኑን ከመገናኛ ብዙሃን መስማቱንና በሰላምና በአንድነት ጉባኤው እየቀረበ ያለው ነገር የሚቃረን ሆኖ እንዳገኘው የሚገልጸው በአሜሪካው የሚገኘው ሲኖዶስ ድርጊቱ የቤተክርስቲያንን አንድነት በር ይዘጋል። ላለፉት 21 ዓመታት የቤተክርስቲያንን አንድነት በታላቅ ተስፋ እየተጠባበቁ ያሉትን የምእመናንን ልብ ያሳዝናል፣ የቤተክርስቲያንንም ክብር ያዋርዳል ሲል የውጤቱን አስከፊነት አስረድቷል። ስለዚህ የአዲስ አበባው ሲኖዶስ ፓትርያርክ ከመሾሙ በፊት ሌላ የታሪክ ጠባሳ ጥሎ እንዳያልፍ በእርጋታና በዝግታ ውሳኔውን ደግሞ እንዲያጤነው አሳስቧል። ያለፈው ችግር መፍትሔ ሳያገኝ በአንድ መንበር ላይ በአንድ ዘመን እንደገና ሁለት አባት ማስቀመጥ ከቀኖና ውጪ መሆኑን የገለጸው በአሜሪካ የሚገኘው ሲኖዶስ 4ኛውና ሕጋዊው ፓትርያርክ በሕይወት እያሉ ሌላ ፓትርያርክ ለመሾም ማሰብ ከቀኖና ውጪ ነው ብሏል። ሆኖም ከሰላምና አንድነት ጉባኤው የቀረበለትን ጥሪ ተቀብሎ ለአንድነቱ ይጠቅማሉ ሕገ ቤተክርስቲያንን ያስጠብቃሉ ያላቸውን አጀንዳዎች ቀርጾ ለውይይቱ ልኡካንን እንደሚሰይምና እንደሚልክ አስታውቋል። ለስኬታማነቱም በኢትዮጵያ የሚገኙ አበው ካህናት መነኮሳትና ምእመናን ሁሉ በጸሎት እንዲያሳስቡ፣ ለፓትርያርክ ምርጫ እየተዘጋጁ ያሉትን ጳጳሳት ሌላ ታሪካዊ ስሕተት ከመፈጸማቸው በፊት ድምጻቸውን በማሰማት የቤተክርስቲያንን አንድነት እንዲያስጠብቁ ጥሪ አስተላልፈዋል። መንግሥትም ለመለያየቱ ምክንያት እንዳይሆንና በቤተክርስቲያኗ ውሳኔ ላይ በቀጥታም ሆ በተዘዋዋሪ መንገድ ተጽእኖ እንዳያሰድር ጥሪ አቅርቧል።

በዚህኛውም ሲኖዶስ ቦታ ሆነን ካየነው ፓትርያርክ መርቆሬዎስ እያሉ ሌላ ፓትርያርክ መሾም ማለት እስካሁን የነበረውን ችግር ይበልጥ ማስፋት ሆኖ ነው የሚታየው። እየተካሄደ ባለው የእርቅ ሂደት ላይም የራሱን አሉታዊ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል። ቤተክርስቲያን እንደተከፈልች እንድትቀጥልም ያደርጋል።

ስለዚህ ሁለቱም ወገኖች እርቁን ሊያደናቅፍና ቤተክርስቲያንን ሊለያይ የሚችል ውሳኔ ከማሳለፍ ይልቅ ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው። ከራሳቸው ክብር ይልቅ ለቤተክርስቲያን አንድነት ሊያስቡ ይገባል። በማንኛውም ምክንያት ቢሆን  አንድ ፓትርያርክ ከመንበሩ ተነስቶ ሌላ ፓትርያርክ ከተሾመ በኋላ ተመልሶ ወደ መንበሩ ሊመለስ የሚችልበት አጋጣሚ ሊኖር እንደሚችል ማሰብም መልካም ነው። ምንም እንኳን ጉዳዩ የተለያየ ቢሆንም የእስክንድርያው ሊቀጳጳሳት ቅዱስ አትናቴዎስ ከመንበሩ በተደጋጋሚ የተሰደደበትና በቦታው ሌላ ሊቀጳጳስ የተሾመበት፣ በኋላም ወደ መንበሩ የተመለሰበት አጋጣሚ እንደነበረ በቅንነት ማሰብ መልካም ነው። በዚህ ወሳኝ ወቅት አንደኛው ወገን ካልተሸነፈና ለቤተክርስቲያን አንድነት ካላሰበ ቤተክርስቲያን ለሁለት ተከፍላ ትቀጥላለች ማለት ነው። ለሰላምና አንድነት ጉባኤውም ስራው ከባድ ይሆናል። ስለዚህ አባቶች ሁላችሁ ስለቤተክርስቲያን አንድነት አስቡ እንላለን።

8 comments:

 1. Gena ahun tiru neger tsafachehu. Yelmedbachehu eski. Lebonam yestachehu wede betekrstiyanem yemelsachehu.

  ReplyDelete
 2. it is a shame for protestants ( menafkans/tequlas ) for their interfering in the orthodox church in favor of stealing our sheep. it is crystal true that you ( the protestant bloggers) are highly demanding the separation of our fathers, b/c we know that devil does not need unity- look how the protestants are divided in to 100000 domination still being breeding like protozoa. so, how can we believe that you want the church's unity. OK, your paradox is clear, you will have life only if there is separation , it is laughing that you pretends "AGREEMENT OF THE 2 SYNOD" FUNNY....

  ReplyDelete
 3. bet kisritiyan le hult tekefal ke qetelech, ltehnidiso menafikan ijig amechi yihonal. silzeh lzihu mekefafe ymisru wegenoch ayitefumin btselotachiu iriduachew.

  ReplyDelete
 4. መናፍቁ ሆይ! ያንተ ልብ ነው ለሁለት የተከፈለው፡፡ ቤተ ክርስቲያን አትከፈልም አሐቲ ናት አባ መርቆሬዎስ በራሱ ጊዜ ነው ምእመናንን በትኖ ወደ ሰዶማዊያን ምድር (አሜሪካን) የተሰደደው፡፡

  ReplyDelete
 5. I really admire this news. Indeed our church must revise her self. The previous fault must be corrected, as for me, and the time is today. H.H. Merqorewos must be restituted to his holy see and the AA synod must accept this truth. They must bother for the unity of the TEWAHEDO Church. Rejecting the reconciliation and rushing for newly Patriarch seems they badly aspire to assume the see. Nevertheless, it is a divine office which needs modesty and purity of spirit. Our fathers those who are in Addis and States must surrender them selves for the Lord and be simple hearted. Unless it will be the most drastic situation for the EOTC, which never happened in its own history. So let all of pray, let all blogs contribute for the reconciliation and let our religious figures (both in Ethiopia and USA) be diligent in your decisions. Let the Almighty Lord solve this chaotic challenge in our Church.

  ReplyDelete
 6. በእውነት ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቀኖና ከቆማችሁና በጳጳስ ላይ ጳጳስ አይሾምም በአንድ ጊዜ አንድ ፓትርያርክ ብቻ ይሆናል:: የሚለውን ህግ እንደዚህ አክርራችሁ የምትከራክሩለት ከሆነ ለምን ፳ ዓመታት ፈጀባችሁ? ለምን ሌላ ሰኖዶስ ለአቡነ መርቆርዮስን በመጠቀም አቋቋማችሁ?
  ለምን ጽላቷ ተሰዳለች በማለት ከ፵ ሚሊዮን በላይ የሚሆነውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ቤተ ከርስቲያን የለህም አላችሁት?
  ለምን ዛሬ አቡነ መርቆርዮስ ይመለሱ እንደምትሉት ሌላ ሰኖዶስ ከማቋቋማም ይልቅ ሕዝቡን አልቀሰቀሳችሁም?

  ReplyDelete
  Replies
  1. Wow!
   You raised the best point.
   ያሁኑ ማደናበሪያ ሃሳብ በየምክንያቱ ከአገር ሲሰደዱ ተቀባይ አባት እንዳይቸግራቸው ለመወዳጀት የያዙት አቋም ነው እንጅ ለቤተ ክርስቲያኗ አንድነት አስበው አይደለም ፡፡ በአንድ ወገን የአገር ቤቶቹን አባቶች እየዘነጠሉ በሌላው ደግሞ ስለ ሰላም ተቆርቋሪ መስሎ ስለ አንድነት መናገር አይቻልም ፡፡

   Delete
 7. Eyesusin ligedlut silu wede gibtse tesedede merqorios degmo wede america. Eyesus wedehageru temelese teseqlom mote. How about merqorios? Trust me it will happen the same way.

  ReplyDelete