Thursday, November 8, 2012

አቃቤ መንበር ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የቋሚ ሲኖዶስን አልመራም ብለው ከስበሰባ መውጣታቸው ተነገረ

Read in PDF
ሮብ እለት በ28/2/2005 በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ በተደረገው የቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ስብሰባውን በጸሎት እንዲያስጀምሩ ለቀረበላቸው ጥያቄ «የእኔን አቃቤ መንበርነት መች ተቀበላችሁና ነው በጸሎት የማስጀምረው? ህጉ የሚለው የሚሾምን ሰው ሥራ አስኪያጁ ያቀርባል ፓትርያርኩ ይሾማል ነው። አሁን ግን የምትሾሙ የምትሽሩ እናንተ ሆናችኋል። ታዲያ እኔ የእናንተ አሻንጉሊት ነኝ? ስልጣኔ ምን እንደሆነ በዛሬው እለት እንድታሳውቁኝ እፈልጋለሁ። እስከዚያው ግን ስብሰባውን አልመራም» ብለው ከስብሰባው መውጣታቸውን ምንጮቻችን ተናግረዋል። አባ ሳሙኤል «እኛ ላይ እኮ በድረገጽ እየተጻፈብንና ስማችን እየጠፋ ነው» በማለት ሊያግባቧቸው ቢሞክሩም ብፁእነታቸው ፈቃደኛ አልሆኑም። የቋሚ ሲኖዶስን ስልጣን በጎን ቀምቶ ፈላጭ ቆራጭ እኔ ነኝ የሚለው የእነ «አባ» ሳሙኤል ቡድን አላንቀሳቅስ ካላቸውና ስልጣናቸው የሚፈቅድላቸውን ስራ እንዳይሰሩ ካደረጋቸው ወዲህ በአቃቤ መንበሩና በዚህ ቡድን መካከል ውጥረቱ እያየለ መጥቷል። የዛሬውም አቃቤ መንበሩ ከስብሰባው መውጣት ውጥረቱ የደረሰበትን ከፍተኛ ደረጃ የሚያሳይ ነው ይላሉ ታዛቢዎች።

ቡድኑን እያሽከረከሩ ያሉትና ለታላቅ አባት ያላቸውን ንቀት መስቀል ባለመሳለም የሚያሳዩት «አባ» ሳሙኤል በዛሬው እለት የአቃቤ መንበሩን መስቀል ሳይሳለሙ መቀመጣቸውን የተናገሩት ምንጮቻችን፥ ይህን የንቀትና የትእቢት ተግባር በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ላይ ሲፈጽሙ እንደነበርና ቅዱስነታቸውን አቃጥለው ለሞት እንዳበቋቸው ሁሉ አቃቤ መንበሩም ላይ ተመሳሳይ ነገር እንዳይፈጸም ስጋታቸውን የሚገልጹ አሉ። እንዲያውም አቃቤ መንበሩ አንድ ነገር ቢሆኑ አባ ፊልጶስና ሶስቱ የጉድ ሙዳዮች - አባ ሳሙኤል አባ ሉቃስና አባ አብርሃም ተጠያቂዎች መሆን እንዳለባቸው ይጠቁሟሉ።

የቋሚ ሲኖዶስን ስልጣን የቀማውን ቡድን እንዲሰይሙ አቡነ ናትናኤልን ያግባባቸው የእርሳቸው ቀራቢ የነበረው የቀድሞው የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም ሲሆን፣ እንዲህ የተደረገውም «ሌሎች ቀድመውኝ ቢያወሩትም እኔጋ ግን ያለው በምስልና በድምጽ የተደገፈ መረጃ ነው» በሚል ማቅ የህሊና እስረኛ ያደረጋቸውንና በጥቅም የያዛቸውን ጳጳሳት እዚህ ቡድን ውስጥ እንዲካተቱ በማድረግ እንዳዋቀረው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት እያረቀቁ ያለው ህግም ፓትርያርኩ ከመባረክ ውጪ ምንም ስልጣን እንዳይኖረው የሚያደርግ እንደሆነና በዚህ በኩል ማቅ አስተዳደሩን ለመቆጣጠር እንዲያመቸው በወኪሎቹ በኩል እየሰራ መሆኑ ታውቋል። በአቃቤ መንበሩ ላይ የጳጳሳቱ ቡድን እያሳየ ያለውም በቀጣዩ ፓትርያርክ ላይ ሊያደርጉ ያቀዱትን ነው የሚሉ አሉ። በአሁኑ ሰአት አቃቤ መንበር ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ከመባረክ ውጪ በስልጣናቸው ምንም እያደረጉ አይደለም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አቡነ ፊልጶስ የአቡነ ናትናኤልን መስቀል ሊሳለሙ ሲቀርቡ «ዞር በሉ» ብለው ፊት እንደነሷቸው ምንጮቻችን ገልጸዋል። እየማሉ በመካድ የሚታወቁት አባ ፊልጶስ ዘመዶቻቸውንና የወንዛቸውን ልጆች በአሁኑ ወቅት ቦታ ቦታ እያስያዙ መሆናቸውና ይህም ህግን ተከትሎ ማለትም እርሳቸው ለአቃቤ መንበሩ አቅርበው በአቃቤ መንበሩ መሾም ሲገባቸው አቃቤ መንበሩን ከጨዋታ ውጪ በማድረግ ውስጥ ውስጡን ሥራቸውን እየሰሩና ለይምሰል ግን መስቀላቸውን ለመሳም መቅረባቸው ስላናደዳቸው ነው አቃቤ መንበር ናትናኤል አባ ፊልጶስን ፊት የነሷቸው ተብሏል። አባ ፊልጶስ ሁለት እህቶቻቸውን በቅርቡ እያንዳንዳቸውን የ3700 ብር ደሞዝተኛ አድርገው ወደላሊበላ መላካቸው ታውቋል። እያደረጉ ባለው ሹም ሽርም በአቡነ ጳውሎስ ጊዜ አስተዳደር ላይ ይሰሩ የነበሩትን ቀሲስ ዮሐንስን ከቦታቸው አንስተው ተንሳፋፊ ያደረጓቸው ሲሆን ጉባኤ አርድእትን ለማፍረስ በዋናነት የማቅ እጅ ሆኖ ያገለገለውን ሰለሞን ቶልቻን በቦታው ተክተዋል። 

በተያያዘም የማኅበረ ቅዱሳን ድረገጽ ደጀሰላም አንድ ጊዜ «የኦሮሞ ተወላጅ ፓትርያርክ ለማስቀመጥ እየሰሩ ነው፡፡» በሌላ ጊዜ ሌላ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍቶባቸው የነበሩትን ቀሲስ በላይ መኮንንን ከጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲንነት እንዲነሱ ከአባ ፊልጶስ ደብዳቤ የተጻፈላቸው መሆኑ ታውቋል። ከደብዳቤው መጻፍ በፊት የቀረበው ምክንያትም ብሄራቸውን በሚነካ መልኩ «እርሱ የጳውሎስ ኮሌጅ ዲን ሊሆን አይገባም» የሚል መሆኑ ታውቋል። ቀሲስ በላይ ውሳኔውን እንደማይቀበሉ እየተናገሩ ነው ተብሏል። በዚህ ሁሉ ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳንና የጳጳሳቱ ቡድን  ምን ያህል ተቀናጅተው እየሰሩ እንደሆነ እየታየ ነው።

ከታሪካቸው መበላሸት የተነሳ ፓትርያርክ የመሆን ህልማቸው እንደማይሳካ የተረዱት «አባ» ሳሙኤል በቀጣይ ልማት ኮምሽንን ለቀው የኢየሩሳሌም ጳጳስ መሆን እንደሚፈልጉ ምንጮቻችን ተናግረዋል።

11 comments:

 1. Additional Information:

  1. Megabi Kahinat Haileselassie Tirota kewotu behuala ahun beabune philipos temelisew ye kahinat astedader memiria halafi hunewal. Yih malet ahun hulet memiria halafi ale malet new....

  2. Diro abune kerlos (komata menekusie new) sira askiage hunew addis 74 wolloye ketirew besinodos teteyikew neber.Be ahunu gezie degimo Aba philipos ena aba hizikael wolloye yalihone beteley be abune paulos gezie mahibere kidusan mestekakel alebet bilew ytagelu likawintin be masaded be mitikachew wolloye ena ye mahibere kidusan telalaki yehonutin eyasikemetu yegegnal 1. Aba hiruyigre be ahunu seat addis ababa sira askiaj - Egzioooooooooo. Yih sew america ewosidachihu alehu eyale ye bete kihinet sitochin eyedefere bete chemarim musium yemiseru menekosat gar tegneto bemegegnetu neber ke sunday school wede garaji (menfesawi fird bet yetelakew) - begibir ke Mahibere kidusanu efrem eshete ena ke abune abirham gar yimesaselal.

  3. Be ahunu Gezie, Ato tesfayen deribo yizot yeneberewin kiriy bet ye Audit memiria Halafi leneberut memhere Fisiha (WolloYe) Tesetual. Debidabe Tetsifual

  4. Ke Aratu Sira Askiyaj le addis ababa, Andu teshuami maletim ke hagerachew lij/Papas gar endiseru Memihir Seritse (Ye Megabi Biluy Aemere mikitil yeneberut) Teshumewal.

  5. Dr. Mesfin Tenagne ke America wode Addis Ababa bemegegnet be kirb ye limat commission commissioner a siderigew endemiyashumachew Abune Hizikael, Abune Matias/ Canada, Abune Philipos, Abune Kerilos ena Abune Gebireal gar eyetedewawelu simiminet lay derisewal tebilual.

  Ato Mesfin Tegegne, be ewunetu and memiria memirat akitot yetebarere serategna endeneber yitawokal. Minim ayinet ye limat timihirt ena limid yelelew, Masters yalisera, america ager ye medical board examination wosido le sust gizie yewodeke, ye kihinet ageligilot yalneberew yekibir kess new. Neger gin Wolloye bemehonu bicha yishomal tebilual.

  Cher worie yaseman, kkkkk

  ReplyDelete
 2. እኔ የሚገርመኝ ለወሬ ያላችሁ ቅርበት ነዉ፡፡ ክፉ ክፉዉን እንጅ በጎ የሆነዉን እንዳትዘግቡ ያደረጋችሁ ማንነታችሁ ስለሆነ ምንም ማለት አያስፈልግም፡፡ ለነገሩ እናንተ ምንታደርጉ መስሎ ከውስጥ ሆኖ ወሬ የሚያቀብላችሁ ነዉ እንጅ፡፡ ለዚያ ሰዉ ወዮለት ነዉ የተባለዉ . . .፡፡ የክፉ ወሬ ነጋሪዎች እጣ ፋንታ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ አይደል? ከዚህ ያድነን! ማስተዋሉን ይስጣችሁ!፡፡ እናንተ አውሩ፤ እነርሱ በቅንነት ተመስገን፣ የሚያደርጉትን አያዉቁምና ይቅር በላቸዉ እያሉ ሥራቸዉን ይሰራሉ፡፡ አስተዉሉ! አስተዉሉ! አስተዉሉ!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይህን ለዘመዶችህ ለደጀ ሰላሞች(ማቅ) ንገር

   Delete
  2. You don't know what they did... the majority of their witing are fictions. I just see how they think their readers are... We don't only one source of information so that they could not fool us more than one...

   Delete
  3. Aye mesfin tenagneeeeeeeeeeeeee. Kezih america ager degimo lela mist agibito eyenore new yalew. Yediro mistu, Dr. Ayda yemitibalem MK erisun abara lijochuan yiza be ahunu gizie Botswana teseda tinoralech. Mejemeria kahin kehone mistun ena yewoledachewin lij besin sirat basadege. Washington Tekemito lela set kemiyabaliggggg. Egzioooo, yikir belew amilakachin. Yih hatiatu lelijochu endayiterif egna sile erisu enitseliyalennnnnnnnnnnnnnn

   Delete
  4. የአባ ሰላማንም መንገድ አልደግፍም፡፡ ያንተንም ወይም ያንቺንም አመለካከት አልደግፍም፡፡ ችገር አለ ለማስተካከል ግን ችግሩን እንመን፡፡ አባቶች የተባሉት እግዚአብሔርን በማወቅና በመፍራት ወደ እውነት መምጣት አለባቸው፡፡ ይህ ጊዜ እግዚአብሔር የሰጠን የንስሐ ጊዜ ነውና እንጠቀምበት፡፡

   Delete
 3. Why u not start wotaderawi tegel set messay mk besebeseba ayalu just identify by nech keza use mesarya and gedel go heaven. Aba abrham mesfin kitun kebakidus eykeba yebedawo nebere. Then now he needs him back to adis to get his kit again. Death to all mk.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Egziabher lib yistih,

   Delete
 4. I will give $1000000 us dollar to demolish mk fundemetalist tererist in all over the world. Mr. Mesfin is officialy gay. He is lover of Aba abrham, that key stone reason he decide to back in to Ethiopia. Death to all mk.

  ReplyDelete
 5. Mk beslogan ymotal bleh atlfa wedaje !!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 6. I was recommended this website by my cousin. I'm not sure whether this post is written by him as nobody else know such detailed about my problem. You're amazing!
  Thanks!

  My site Psn Code Generator

  ReplyDelete