Saturday, December 15, 2012

4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ያለፈቃዳቸውና ሳይታመሙ ከስልጣን እንዲወርዱ እንደተደረጉ የሚጠቁሙ ሰነዶች

ደብዳቤዎቹ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ያለፈቃዳቸው፣ የጤና ችግርም ሳይኖርባቸው ከመንበራቸው እንዲወርዱ መደረጋቸውን ያሳያሉ። በተለይ ቅዱስነታቸው የጻፉት ደብዳቤ ይህንን ግልጽ ያደርገዋል። በወቅቱ የነበረውን የመንግስት ተጽዕኖም በጊዜው ከነበረው ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ታምራት ላይኔ የተጻፈው በጀትን የማገድ ደብዳቤ ግልጽ ያደርገዋል።


 • በሰነዶች ላይ ኢሳት ያቀረበውን ሰፋ ያለ ዘገባም ያዳምጡ10 comments:

 1. በኢሳት የቀረበውን ዘገባ ቀደም ሲል ስላዳመጥኩት አስተያየት እንዲሰጥበት የራሴን ላስቀድም ፡፡ ታሪኩን በቀረበልን መረጃ መሠረት ስረዳው ፤ ሁሎችም አባቶች ስህተት ፈጽመዋል የሚል መደምደሚያ ላይ እደርሳለሁ ፡፡ ምክንያቶቼን ተመልከቱልኝ ፡-

  1. የነገሩ መነሻ የሆነው አቡነ መርቆርዮስ ወንድሞቻቸውንና ልጆቻቸውን (እንደ ተባለውና እንደ ተረጋገጠው) በተጽእኖ ምክንያት ዋሽተው ማሳሳታቸው ነው ፡፡ በክርስትናችን መዋሽት መቼ እንደሚፈቀድና እንደ ኃጢአት እንደማይቆጠር ግልጽ አይደለም እንጅ ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ፣ የተባረኩ ውሸታሞች ታሪክንም ያስነብበናል ፡፡ ይኸ ርሳቸው የፈጸሙት ስህተት ፣ አብርሃም ራሱን ለማዳን ከፈጸመው ድክመት ይነጻጸር ወይ ከሌላ አንባቢ ለራሱ ይፍረድ ፡፡ ታሪካችንን ስንመረምር ግን የቤተ ክርስቲያን አንጋፋ መሪ ራሱን የካደና ፤ ፍጹም ለእውነት ስለእውነት የቆመ ፤ እግዚአብሔርንና በአደራ የተሰጠውን መንጋ ሊያገለግል ፣ ሊጠብቅ ፣ ሊመራ የሚታገል ፤ ለቤተ ክርስቲያንና ስለወገኑ ክብር ለመሞት እንኳን የተዘጋጀ ፤ ራሱን በቁሙ ገንዞ የሚያኖር ፣ ስለምንም ቢባል ለራሱ ጥቅምና ደኀንነት ሲል የማያደላ ነው ፡፡ የቅርብ ዘመን ትዝታ የሆነውን የአቡነ ጴጥሮስን ታሪክን ያስታውሷል ፡፡

  2. ቤተ ክርስቲያናችን የምትተዳደርበትና የምትመራበት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አላት ፡፡ ይኸንን ደግሞ የተቀሩት አባቶች አቡነ መርቆርዮስ በሕይወት መኖራቸውንና ጤናማ መሆናቸውን እያወቁ ፣ ሌላ አዲስ አባት በወንበራቸው በመሰየም የራሳቸውን የስህተት አስተዋጽዖ ፈጽመዋል ፡፡ ይኸ አሠራራቸው ህጋዊ ስለመሆኑ የቤተ ክርስቲያንን ውስጠ ምስጢር የሚያውቁ አባቶችና ሊቃውንት የሚሉት አላቸው ፡፡

  3. አሁንም ሌላው ስህተት ደግሞ አቡነ መርቆርዮስ መንበራቸውን በጫናም ይሁን በፈቃዳቸው ለቀው ወደ ውጭ አገር ከወጡ በኋላ ፣ በስደት የሚገኙትን አባቶች አሰባስበው አዲስ መንበር ሰይመው ፣ እኔ ነኝ ህጋዊ አባት ብለው በአንዷ ቤተ ክርስቲያን ሁለት መንበር እንዲፈጠር ማድረጋቸው ነው ፡፡ ይኸን የመሰለ ድክመት ከሚያደርጉ ፣ በተሰደዱበት አገር ገዳም ገብተው በጾምና በጸሎት ቢሰነብቱ ፣ ቤተ ክርስቲያን የአሁኑ ችግር ባለቤት አትሆንም ነበር ፡፡

  4. በኢትዮጵያ በወቅቱ የነበሩት አባቶች ፣ አቡነ መርቆርዮስ ያጋጠማቸውን እክል በሆነ መንገድ (በቃል ወይም በጽሁፍ) ካስረዷቸው ወይም ከጠቆሟቸው ፣ ያንን ፈተናና መከራ የራሳቸውም ችግር አድርገው በመቁጠር ፤ ወደ ሌላ የምርጫ ርምጃ ከመግባትና እሳትን በእሳት ከማለት ቢቆጠቡ ኖሮ ፣ ዛሬ ቤተ ክርስቲያናችን ከምትገኝበት ትልቅ ፈተና አትገባም ነበር ፡፡

  ስለዚህም እላለሁ ፤ በደልን በመቆጣጠርና ነጥብ በመሰጣጠት ከሆነ ፣ አንድ እንኳ ጤናማና አሸናፊ የሚሆን አባት የለንም ፡፡ ሁሎችም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ደክመው ተገኝተዋል (እግዚአብሔር ይቅር ይበለኝ)፤ ነገር ግን አሁንም ያንን ለታሪክ ትተው ፣ ማድረግ የሚገባቸውን ሁሉ ፈጽመው ፣ የሚፈልገውን ስምምነት ቢፈጥሩ ለቤተ ክርስቲያናችንንና ለአገራችን ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል እላለሁ ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. በጣም የሚያሳዝንና የሚያስተዛዝብ አስተያየት ነው። እውነተኛውን መስመር ጠብቀው የተሰጣቸውን አደራ ለመወጣት በመጋደል ላይ የሚገኙትን ብጹዕ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሪዎስን ማመስገንና ቡራኬያቸውን በመቀበል ፋንታ ለወንጀለኞቹና ለአጥፊዎቹንና ለምን አልተመቹም በማለት መርዘኛና እኩይ ነገር መናገር እራሱ ተናጋሪውን ያስደስት ይሆናል እንጅ አብዛኛዎቹን የሃይማኖታችንን ጉዳይ እግር በእግር የምንከታተ ሰዎች ሊያታልሉን አይችሉም። በዚህ ድረገጽ ላይ የተቀመጡትን እነዚህን መረጃዎች መመልከታችንን ደግሞ በትክክል ወያኔ እንዴት ቤተክርስቲያናችንን ከጥቂት ጥቅመኞች ጋር መጫወቻ እንዳደረጋት ያረጋግጣል።

   Delete
  2. Mimen minin enqua andande bemititsifew balisimamam bezih tintaneh gin esimamalehu

   Delete
 2. mk yelembetem ende abune merekoruose kelsetanachew bewredu gize? enaten eko yemateletu negrese selale lastwasaheu beye new..hahahhaha

  ReplyDelete
 3. Could not find the documents. Please fix the link.

  ReplyDelete
 4. መጽሐፈ ምሳሌ 6፤16 እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው ሰባተኛውንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፋለች እርሷም በወንድም አማማች መካከል ጠብን የሚዘራ ነው። የቀደመው የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት የነበረው ታምራት ላይኔ የሰጠው መልስ ምን ያህል በሌብነት የቆየ ሰው መሆኑን ይገልጣል።ቀድሞዉንም ፕሮተስታንት ለመሆን አላማና እቅድ ስለነበረው የኦርቶዶክስ ሀይማኖትን እንድከፋፈልና እንድጠፋ ስያልም የነበረው ህልሙን ሰጣን በሰጠው አጋጣም የፈለገውን አደረገ። ቀጥሎም ፓትርያርኩን ከስልጣን እንድ ለቁ የአደረከኝ እኔ ነኝ ብሎ እንደ ንስሐ ያቀረበው ቃል እጅግ ያሳዝናል። ምክንያቱም ይህን የእምነት ክህደት ቃሉ ለከንቱ ውዳሴ በሰዎች ፍት ታመኝነት ለማግኝት በማለት ያቀረበው ነበር። ንስሐ ስባል ለሰማያዊ አባቱ የሰራውን ሐጢአት ማናዘዝ እና ከእርሱም ምህረት ማግኘት እንጅ በሰዎች ፍት እንድህ አድርገ ነበር እወቁልኝ በማለት ለከንቱ ታይታ እራስ አማኝ ለማስመሰል ማቅርብ እዉነትኛ የክርስቶስ ተከታይ አያሰኝም። በእርግጥ እዉነትኛ ክርስቲያን ነኝ ብሎ እራሱን የምጠራ ሰው የሰበረውን ወይንም የፈጸመውን ስሕተት መልሶ መጠገን ስችል ነው። ታምራት ላይኔ የበደለው እግዚአብሔርንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኞችን ነው። ስለዚህ ይህ ሰው ይቅርታ መጠየቅ ያለበት የበደለውን የተዋህዶ ክርስቲያኖችን የኢየሱስ ከርስቶስን ልጆች ነበር። ቅዱስ መጽሐፍም በመጀመሪያ ደረጃ እንድህ በማለት ይናገራል አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ በሗላም መጥተህ መባህንነ(ስጣታህን ጸሎትህን) አቅርብ ። አብረኸም በመንገድ ሳለህ ከባለጋራህ ጋር ፈጥነህ ተስማማ ባለጋራህ ለዳኛ እንዳይሰጥህ ማቴ 5፤25። ስለዚህ ታምራት የበደለው የኢትዮጵያ ኦትቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያኖችን ነው እንደ እግዚአብሔር ቃል ይህን የበደለውን በሀሰት የፈጸመውን ተንኮል አንድሻርለት በይፋ ይቅርታ መጠየቅ ነበረበት እርሱ ግን አልጠየቀም። አሁን ጌታን ተቀብየለሁ ብልም እዉነት ግን አይደለም የጌታ ስም እየነገደበትና ለራሱ ስጋዊ ጥቅም መጠግያ ያደረገው ሰው ነው።

  ReplyDelete
 5. Minew esatin sitabteletilu alneber ende zare yesun zegeba akerebachihu?

  ReplyDelete
 6. መቼስ እኛ ኢትዮጵያውያን ራሳችንን ከዓለም የለየንባቸው ምክንያቶች አጅግ ብዙ ናቸው። ሌላው ሕዝብ የራሱ የሆነ ወግና ባህል የሌለው ይመስል በወጎቻችንና በባህሎቻችን ያለመጠን እንመካለን። በሌላው ዓለም ተራራና ሸለቆ፣ ወንዝና ተረተር፣ ሜዳና ኮረብታ…. የሌለ ይመስል በመልክዓ ምድራችን ሳይቀር እንኮፈሳለን። …. ዓለምንና ሞላዋን የፈጠረው እግዚአብሔርስ ቢሆን፣ ከሌሎቹ አገሮች ይልቅ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የተለየ አጀንዳ፣ የተለየ እንክብካቤ፣…. የተለየ ጉዳይ እንዳለው እናስባለን። የብሉይ ኪዳኑ የእግዚአብሔር ሕዝብ እስራኤላውያን እንደነበሩ ሁሉ፤ እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ያደረገው አዲስ ኪዳን በዓለም ከሚኖሩ ሕዝቦች ይልቅ ከእኛ ከኢትዮጵውያኑ ጋር እስኪመስል ድረስ “የክርስቲያን ደሴት” የሚል “የክርስትና ስም” ለራሳችን አውጥተናል።በቀደመው ኪዳን በእግዚአብሔር በራሱ ተሰጥቶ የነበረውን የግርዘት ሕግ ወደ አዲሱ ኪዳን የጸጋ ሥርዓት ሊቀላቅሉ የነበሩትን እነ ኬፋን ፊት ለፊት የተቃወመው ሐዋርያው ጳውሎስ፣ ለገላትያ ክርስቲያኖች በጻፈው መልክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ ውስጥ፡- “ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፣ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን!” እያለ መላእክት እንኳን ሳይቀሩ ሌላ ወንጌል ቢሰብኩ ከመርገም እንደማያመልጡ ካስጠነቀቀ፤ እንኪያስ! በሕጉና በነቢያት ያልተጻፈውን፣ በክርስቶስ ወንጌል ያልተሰበከውን እንዲህ ያለ እንግዳ ትምሕርት ወደ ክርስትና ጨምረው፣ ዛሬም ድረስ ያለ እፍረት እየሰበኩና እያስተማሩ፣ እያሳቱና እየሳቱ የክርስቶስን ወንጌል የሚያጣምሙት የሐይማኖት ልጆች፣ ምድራቸውም ሆነች ራሳቸው ከዚህ ሐዋርያዊ እርግማን እንዴት ሊያመልጡ ይችላሉ?? በጭራሽ አይችሉም!!!!! የወንጌሉ ባለቤት የሆነውና ከሰማይ በታች ያሉ ሰዎች ሁሉ (ኢትይጵያውያንም ሳይቀሩ) በእምነት እየጠሩ ይድኑበት ዘንድ የተሰጣቸው አንድ ስም ነው። ክርስቶስና ጌታ የሆነው የሕያው እግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ስም!!! ይህ በምድርም ሆነ በሰማያት ከሚጠሩት ስሞች ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያለው የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በምድሪቱ ሰማያት ላይ መንገስ፣ መወደስ፣ መጠራት፣…. ሲጀምር፤ በኢትዮጵያ ምድር ላይ እውነተኛው የእግዚአብሔር ክብር ይመጣል። ሰሞኑን በአንድ የውጭ አገር ኤምባሲ ቢሮ ውስጥ ድንገት የተገናኝን ስድስት የምንሆን ኢትዮጵያውያን ያደረግነው ውይይት ነው ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ። ከስድስታችን ውስጥ ሁለቱ ከሃያ ዓመታት በፊት ዩኒቨርስቲ ውስጥ አብረው ይማሩ የነበሩና ይኖሩበት ከነበረው “የባዕድ ምድር” ከረዥም ጊዜ በሗላ ተመልሰው በድንገት እዚያው ቢሮ ውስጥ የተገናኙ ጓደኛሞች ናቸው። የሌሎቹን ጓደኞቻቸውን ስም እየጠሩ ያሉበትን ይጠያየቃሉ፤ በጣም በሚገርም ሁኔታ ሁሉም ከኢትዮጵያ ውጪ ናቸው። “ከሁሉ በላይ እኔን የሚያበሳጨኝ” አለ አንደኛው፤ “ከሁሉ በላይ እኔን የሚያበሳጨኝ ፊደል ቆጥሬ ዲግሪዬን እስከምይዝ ድረስ በነጻ ያሰተማረችኝን አገሬን መጥቀም ያለመቻሌ ነው።”

  ከዚህ ወንድም የቁጭት ንግግር ቀጥሎ፣ ኢትዮጵያ ለአያሌ ዘመናት በድህነትና በችግር እየማቀቀች ባለችበት ሁኔታ ውስጥ፣ አገራቸውን በእጅጉ ሊጠቅሙና የሕዝባቸውን ኑሮ ሊለውጡ የሚችሉ አያሌ ኢትዮጵያውያን ጉልበታቸውንና እውቀታቸውን ለየባዕድ አገሩ በዶላር የሚሸጡበትን ምክንያት እየተነተነና የአገሪቱን የፖለቲካ ሥርዓት እየኮነነ ውይይቱ ቀጠለ። በዚህ መኸል አንዲት እህት፡- “እኔ ግን ኢትዮጵያ ላይ እየደረሰ ላለው መከራና ችግር ምክንያቱ የፖለቲካ ሥርዓቱ ብቻ አይመስለኝም” አለች። ሌላ ምን ሊሆን እንደሚችል ለማወቅ የጓጉ ወደ አሥር የሚጠጉ አይኖች ልጅቷ ላይ አፈጠጡ። “ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴትና ቅድስት አገር ከመሆኗ የተነሳ ዲያብሎስ ያመጣብን ፈተና ነው” አለች። የሁሉም ሰው ስሜት ሟሸሸ። አሁን እኔን የሚመለከተኝ ርዕስ በመከፈቱ ጉሮሮዬን ጠራረኩና- “አይደለም የኔ እሕት፤ ነገሩ የተገላቢጦሽ ነው” ከማለቴ እነዚያ አይኖች በሙሉ እኔ ላይ አፈጠጡ። “በምድራችን ላይ ዘመናትን ላስቆጠረው ችግርና ጉስቁልና ምክንያቶቹ፣ ጠንክረን ካለመስራታችን ጋር ተዳምሮ፣ በክርስትና ስም የሚደረገው ባዕድ አምልኮ ያመጣብን መርገም ነው” አልኩ ፍርጥም ብዬ። written and Posted by Tibebe Belay at 6:01 PM /2012/07/blog-post

  ReplyDelete
 7. ለ አባ ሰላማ ብሎግ አዘጋጆች

  የጌታ ሠላም ይብዛላችሁ፡፡ ብሎጋችሁን በቋሚነት እከታተላለሁ፡፡ መረጃ፣ ትንታኔ እና ትምህርት አገኝበታለሁ፡፡
  ምናልባት የሚጠቅማችሁ ከሆነ አንድ መረጃ ወደ እናንተ ለማድረስ ዛሬ ከአንባቢነት ወደ ተሳታፊነት ተዛውሬአልሁ፡፡
  በብሎጋችሁ ከወጡና ክፍተኛ ተነባቢነት ካገኙት ጽሑፎች ቀዳሚው በዲያቆን ዳንኤል ክብረት እና በዲያቆን ሙሉጌታ ኃለማርያም መካከል ተነስቶ የነበረው ውዝግብ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሰሞኑን ደግሞ ዳንኤል በጎንደር በወሎ እና በጎጃም ያደረገውን አንድ ሳምንት ጉዞ (በብሎጉ ላይ ሳታዩት አልቀረም) ‹‹ የቤተክርስቲያኒቱን ቅርስ ለመዝረፍ ነው›› በማለት ዲያቆን ሙሉጌታ ኃለማርያም ደብዳቤ ለጎንደር ማዕከል (የማኅበረ ቅዱሳን ቅርንጫፍ) የጻፈ ሲሆን ለዚሁ የዳንኤል የዘረፋ ተግባር ተሳታፊ ነበር የተባለ የጎንደር ማዕከል ሰባኬ ወንጌል ዲን ሙሉቀን በማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል በዲን ሙሉጌታ በተጻፈ ደብዳቤ ደሞዙ ተቆርጦበታል፡፡ ሰባኬ ወንጌሉ ለዳንኤል በማድላት የንዑስ ማዕከሉን ሰብሳቢ አሳስቶ የገዳማቱን ቅርሶች ለመበርበር ሚያስችለው ድጋፍ ደብዳቤ እንዲጻፍለት ተባብሮአል የሚል ክስ የቀረበበት ሲሆን ከባድ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤም ተሰጥቶታል፡፡
  ይህንንም ተከትሎ ዲያቆን ሙሉቀን (ሰባኬ ወንጌሉ) የቀረበብኝ ክስ አግባብ የሌለው ነው፡፡ ከዳንኤል ጋር መታየት በማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ ወንጀል ሆኗል፣ እኔ ዳንኤልን ተከትዬ ጉብኝት የሄድኩት በመሠረቱ ፈቃድ ጠይቄ እና ተፈቅዶልኝ ሳለ ዲያቆን ሙሉጌታ ዲያቆን ዳንኤልን ስለማይወደው ብቻ ደሞዜ አስቆርጦብኛል የማስጠንቀቂያም ደብዳቤ አጽፎብኛል፡፡ በማለት ጉዳዩን ወደ ህግ ለመውሰድ በዝግጅት ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡

  ‹‹ሌባ ሲካፈል እንጂ ቀድሞውንስ ሲሰርቅ መች ይጣላል››

  ReplyDelete
 8. We appreciate you Aba Selam website . Please keep continue on your good and fair task.

  ReplyDelete