Saturday, December 1, 2012

ያመነች ብፅእት ናት

«ከጌታ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅእት ናት» ሉቃ 1፥45
እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማኝ ከሚባሉ የእግዚአብሔር ሰዎች ሁሉ ታላቋ ናት። የድንግል ማርያም ታላቅነት እጅግ ከምናስበው በላይ ነው። አካላዊ እና መለኮታዊ ቃልን በማህጸኗ ተሸክማ ወልዳለች፤ ከጽንሰቱ ጀምራ በልደቱ፣ በእድገቱ፣ በአገልግሎቱ፣ከዚያም በሞቱ፤ ሞቶ ካረገ በኋላም እስከ ሕይወቷ ፍጻሜ ድረስ ጌታን ያገለገለች ታላቅ እናት ናት። መጽሐፍ «ሌላውም በመልካም መሬት ወደቀ አንዱም መቶ አንዱም ስድሳ አንዱም ሠላሳ ፍሬ ሰጠ» ማቴ 13፥8 ይላል። ይህ ቃል በጌታ መንግሥት የሥራ ልዩነት እንዳለ እና ክብሩም በዚያው ልክ ክፍ እና ዝቅ የሚል መሆኑን የሚያስረዳ ነው። ከዋክብት ጸሐይና ጨረቃ በክብር እንደሚለያዩ ቅዱስ ጳውሎስ ጽፏል 1ቆሮ 15፥40-41። በዚህ መሠረት የድንግል ማርያም ፍሬ ቢታሰብ ከመቶ በላይ ነው ምክንያቱም እግዚአብሔርን እንደ ድንግል ማርያም ያመነ እና ያገለገለ የለም ማለት ይቻላል።
 እኛ ጌታን በማገልገላችን ደስተኞች ነን፤ ዋጋም እንቀበላለን። ዛሬ ብንጎዳም በሰማይ ክብሩ ይቆየናል ብለን እናምናለን። ይህን ስናስብ ትልቅ ደስታ ይሰማናል። ሐዋርያው ጳውሎስ «ሊገለጥ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን ያሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ» ብሏል። ሮሜ 8፥18። እንግዲህ ለኛም ገና የሚገለጥ ክብር አለ። በዚህ ትንሽ እና እንከን የበዛበት አገልግሎታችን ይህን ያህል ክብር ከጠበቅን የድንግል ማርያም ክብርማ ምን ያህል ይሆን?
ጌታን 9 ወር ሙሉ በማህጸኗ በመሸከም አገልግላለች፤ በልደቱም የናትነቷን ድርሻ በመወጣት ለሕጻናት እንደሚገባ አስፈላጊውን ሁሉ እንክብካቤ በማድረግ አሳድጋዋለች። ጡቷን በማጥባት ጠላት ሊገድለው በሚፈልገው ጊዜ እስከ ግብጽ ደረስ በስደት ተንከራታለች። ዛሬ ተሰደድን እያልን የምንጮኽ አገልጋዮች ሁሉ ከዚያው ከጓሮ እልፍ ያልን አይመስለኝም። እመቤታችን እንዳደረገችው እናድርግ የሚል ሙግት ውስጥ ለመግባት ሳይሆን የርሷን ስናስበው የኛው ቀላል ነው ለማለት ነው።
ጌታ ሠላሳ ዓመት ሞልቶት ተጠምቆ የራሱን ተልእኮ እስኪ ጀምር ድረስ በእመቤታችን ኃላፊነት ሥር ነበር። እርሷ የቀዳችውን እየጠጣ እርሷ የጋገረችውን እየበላ ነበር የኖረው። በመከራው ጊዜ እንጀራ የበሉት ሁሉ ሲክዱ፤ አለንልህ ሲሉ የነበሩ ሁሉ ወደ ኋላ ሲሄዱ፤ እስከ መስቀል ደረስ ያገለገለችው የቁርጥ ቀን እናቱ ናት። ሞቶ ተነሥቶ ካረገ በኋላም ከሐዋርያቱ ጋር ሆና በጸሎት ትተጋ ነበር የሐው 1፥14። በመሥቀሉ ሥር እያለች ልጅ እንዲሆናት ጌታ የሰጣት ቅዱስ ዮሐንስ ለወንጌል አገልግሎት ሲሄድ አብራው እንደሄደች ታሪክ ያስረዳል። ዮሐንስ በደሴተ ፍጥሞ ሲታሠር አብራ በመንከራተት በትንሽ ጎጆ ተወስና ዘመኗን በጸሎትና በሀዘን አሳልፋ በሰላም አርፋለች። በስጋ የወለደችው ልጇ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ሞተ፤ በጸጋ የተሰጣት ልጇ በደሴት ውስጥ ታሥሮ ሞተ። የመቤታችን ያገልግሎት ዘመን በመከራ ያለቀ ነው። እመቤታችን የኖረችበት ቤትና ሞታ የተቀበረችበት ቦታ ዛሬም ዮሐንስ በታሰረበት ደሴት አካባቢ የሚገኝ ሲሆን ብዙዎች የኛ አባቶች ግን ኑሮዋና መቃብሯ በጌቴ ሴማኒ ነው ይላሉ።
 እግዚአብሔርን ማገልገል የሚቻለው በእግዚአብሔር ጻጋና ሞገስ ብቻ መሆኑን ስንቶቻችን እናውቃለን? እመቤታችን ይህን የረጅም ዘመን አገልግሎት በመልካም የፈጸመችው በፊቱ ሞገስ ስላገኘችና የእግዚአብሔር ጸጋ ስለበዛላት ነው። መልአኩም ከሰማይ ወርዶ «ጸጋን የተመላሽ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አግኝተሻል» ነበር ያለው። በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ ማግኘት የመጨረሻ ክብር ነው። እግዚአብሔር ሲያከብር ሞገሱን ነው የሚሰጠው።
 የእመቤታችን እምነት አስደናቂ ነው፤ ያለወንድ ዘር ልጅ ትወልጃለሽ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም ስትባል «እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች» ሉቃ 1፥37። እንዲህ ዓይነት እምነት ለማን አለው? ያለ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ ስትባል ማን ታምናለች? በዚህ የተነሣ ዘመዷ ኤልሳቤጥ እምነቷን በማድነቅ «ከጌታ ዘንድ የነገሩሽ እንደሚፈጸም ስለምታምኚ ብፅእት ነሽ» አለቻት፤ በእርግጥም እመቤታችን ብፅዕት ናት።
እመቤታችን ቅድስት ናት፤ ቅድስናዋ ልዩ ነው የምንለው ዝምታዋን በማየት ነው። ልጇ ከተጸነሰ ጀምሮ እስከ አረገ ድረስ እመቤታችን ስለጌታ ተዓምራት፤ እየሆነ ስላለው የእግዚአብሔር ምሥጢር ታውቃለች። ይህን ምሥጢር ግን ለጎረቤት እንኳን ሳትናገር በልቧ ጠብቃው ትኖር ነበር። ይህ ግሩም ቅድስና ነው። ጌታ የእውሮችን ዓይን ካበራ በኋላ ለማንም አትንገሩ ይል ነበር፤ ይህን የሚለው የሰዎችን የወሬ ጠባይ ስለሚያውቅ ያለጊዜው እንዳይገልጡት ነው። እመቤታችን ግን ማንም አትናገሪ ሳይላት በልቧ ጠብቃው ኖራለች። እኛ ህልም ዐይተን እንኳ ሳንናገረው ብንቀር በዓይን እንደገባ አቧራ ይቆጠቁጠናል። ይህን የምለው እራሳችንን እንድንኮንን ሳይሆን የድንግል ማርያምን ጸጋ እንድናደንቅና ለራሳችን ትምህርት እንድንወስድ ነው።
 እመቤታችን ትሑት ናት። እግዚአብሔርም ትሕትናዋን ስለተመለከተላት አመስግናዋለች «ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች መንፈሴ በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች የባሪያውን ትሕትና ተመልክቷልና እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል» ብላለች ሉቃ 1፥48-49። እኛም ቅድስት እናታችን ምሳሌያችን ስለሆነች እጅግ እናከብራታለን እንወዳታለን። ከዚህ ውጭ የምናድርገውን የስሜት ነገር ግን በፍጹም አትቀበለውም እኛም አናደርገውም።
 እመቤታችን የጌታ እናት ነኝ ብላ የተለየ መብት እና ሥልጣን እንዲሰጣት አልጠየቀችም። ጌታን ወልዳ ማሳደግ በቂ አገልግሎት እንደሆነ ስላወቀች ትውልድ ሁሉ ብጽእት ይሉኛል ብላለች። አዎ አሜን ብለን ብፅእት እንላታለን። ነገር ግን እመቤታችን ጠላት እንደሚዋሽባት አይደለችምና ያልተባለውን አንልም።
ጠላት «የወርቅ ምንጣፍ አስነጥፋ በወርቅ ዙፋን ላይ ተቀምጣ አመስግነኝ» አለች በማለት ዋሽቶባታል። [ውዳሴ ማርያም ትርጉም]። በተዓምረ ማርያም ደግሞ በስሜ ስሙን የሰየመውን፤ በስሜ ቤተ ክርስቲያን ያሠራውን፣ በስሜ ድግስ ያበላውን ማርልኝ ስትል ለስሟ ክብር እንዲሰጥ ጠይቃለች በማለት ጠላት ዘርዓ ያዕቆብ እናታችንን ተሳድቧል፡። የግብር ልጆቹም አውቀው ይሁን ሳያውቁ  በዜማና በንባብ እየተሳደቡ ነው። ማርያምን ያከበሩ እየመሰላቸው ያዋርዳሉ።
 እመቤታችን የመዳን መንገድ እንዴት እንደሆነ ከማንም በላይ ታውቃለች። መዳንም በሌላ በማንም የለም ብሎ ጴጥሮስ ሲናገር እመቤታችን እዚያው ነበረች። ጌታ በኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም ብሎ ሲያስተምር እመቤታችን ትሰማ ነበር። ዮሐንስም ወንጌሉን ሲጽፍ እመቤታችን ነበረች፤ ከዚህም በላይ በመንፈስ ቅዱስ የተሞላች ስለሆነች እውነቱን ሁሉ ታውቃለች። ታዲያ እንዴት ይህን ሁሉ አልፋ በስሟ መዳን እንዲገኝ ሌላ የመዳን መንገድ ትጠይቃለች? ይህ የጠላት ክስ አይደለምን? ጸሎትስ ወደ እኔ ጸልዩ ለስእሌ ስገዱ ብላለችን? ይህ ትሕትናዋን ይገልጣልን? ኧረ ተዉ ቅድስት ብፅዕት የሆነች እናታችን ድንግል ማርያምን አትሳደቡ ኧረ የዳኛ ያለህ?
 ተስፋ ነኝ

35 comments:

 1. ክፍል አንድ
  ዘርዓ ያዕቆብ የ 14ኛው ክፍለ ዘመን መሪና ክርስቲያን ሲሆን ትምህርቱ በየፈረንጁ አገር ሁሉ በላቲንና በእንግሊዝኛ ተተርጉሞ በዓለም ለተበተኑ ክርስቲያኖች የተሰደደ ስለመሰለኝ ፤ አንዳንድ የቅድስት ድንግል ማርያም አማኞች የሚጽፉትን ለማየት ሞከርኩ ፡፡ ይኸኛው ጽሁፍ ገለልተኛ ከሚባሉ ወገኖች የቀረበ ስለሆነ አንብቡና ዘርዓ ያዕቆብ ትምህርቱን ኢትዮጵያ ውስጥ ፈጥሮ አሳስቶን ቢሆን ለራሳችሁ ፍረዱ ፡፡

  The commonly held teachings of Mariology can be derived from her function as Mother of God (Theotokos), a term first used around 320 and formally approved by the Council of Ephesus in 431. Mariologists argue that Mary, who enabled God the Savior to be born, has a position more exalted than any other creature. She is the Queen of Heaven. Moreover, since her motherhood was indispensable to God's redemptive activity, Mary is essential to the final, spiritual perfection of every creature. Accordingly, although she was not involved in their original physical creation, Mary is, in this ultimate sense, the Mother of God's Creatures. This includes being Mother of Humans, a title found in Ambrose but popularized around 1100, and Mother of Angels, a term first found in the thirteenth century.

  Mary's involvement in salvation makes her co - redemptrix along with Christ. Irenaeus contrasted Eve's disobedience, which brought humanity's downfall, with Mary's obedience, which "became the cause of salvation both for herself and the human race." Beginning in the twelfth century references appear to her redemptive work not only in Christ's birth but also at the cross. Most Mariologists insist on both. While Jesus offered his sinless person to appease God's wrath, Mary, whose will was perfectly harmonious with his, offered her prayers. Both atoned for our sins, although Christ's satisfaction was primary and wholly sufficient. Mary's mediatory role includes her present intercession for sinners. This was seldom mentioned before the twelfth century, when popular piety regarded Mary as more lenient than her Son, the Judge.

  ይቀጥላል

  ReplyDelete
 2. ክፍል ሁለት
  Mary's exalted role implies Mariological assertions about her life. If Mary had ever been stained by sin, she would have been God's enemy and unfit to bear him. Consequently, she must have been "immaculate" (wholly free from any sin) from the instant she was conceived. The immaculate conception, hotly debated in the Middle Ages and early modern era, was opposed by Thomas Aquinas and his followers. But in 1854 Pius IX declared it an official dogma.

  Mary's immaculate conception implies that she possessed a "fullness of grace" from the first instant. Further, she was immune to the slightest sin throughout her life. Mariologists also stress Mary's perpetual virginity. This includes, first, her virginity in partu: that Jesus was born without opening any part of her body; second, that she remained a virgin throughout her life. Though Mary's perpetual virginity, and especially her sinlessness, were challenged by some early fathers, they were generally accepted by Augustine's time. Proponents of perpetual virginity often assumed that anything else would contradict her purity. Finally, Mariologists teach that after her death Mary was assumed bodily into heaven. No clear reference to the assumption of Mary appears before the sixth century. It was not generally accepted until the thirteenth and was promulgated by Pius XII in 1950.

  Protestants have criticized Mariology because many assertions apparently lack biblical foundation. Scripture does not mention her immaculate conception or assumption. Her perpetual virginity is challenged by references to Jesus' sisters and brothers (Mark 3:31; 6:3; John 2:12; 7:1 - 10; Acts 1:14; Gal. 1:19; Mariologists claim they were cousins). Moreover, the Gospels do not present Mary unambiguously as sinless and in continuous accord with Christ's will. Protestants have also argued that Mariology exaggerates the contribution that any human can make to divine redemption. Luther and Calvin saw Mary as a human who in herself was nothing; she was enabled to bear Christ wholly through God's grace. Conservative Protestants argue that most Mariological excesses, her roles as Mother of God's Creatures, co - redemptrix, intercessor; her immaculate conception; and her "fullness of grace", spring from overestimating the human role in redemption, which was perhaps already implied by Irenaeus. This ancient theological issue may be the most fundamental one surrounding Mariology.

  ምንጭ ፡ http://mb-soft.com/believe/txn/mariolog.htm

  ምክር ፡ ምክር ፡ በጎጥ ጭንብል ፊታቸውን ከልለው የሃይማኖትን ቃጭል እያሰሙ የቤተ ክርስቲያናችንን ነባር ትምህርት በዘመን አመጣሹ የሉተር ትምህርት ሊበርዙ የሚታገሉ ብዙ አሉና ትምህርታቸውን መርምሩ ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Betikikel wondimalem enmeremiralen.

   Delete
 3. ይኸንንም ማስረጃ አክሉበት

  Early writings
  For the attitude of the Churches of Asia Minor and of Lyons we may appeal to the words of St. Irenaeus, a pupil of St. John's disciple Polycarp; he calls Mary our most eminent advocate. St. Ignatius of Antioch, part of whose life reached back into apostolic times, wrote to the Ephesians (c. 18-19) in such a way as to connect the mysteries of Our Lord's life more closely with those of the Virgin Mary. For instance, the virginity of Mary, and her childbirth, are enumerated with Christ's death, as forming three mysteries unknown to the devil. The sub-apostolic author of the Epistle to Diognetus, writing to a pagan inquirer concerning the Christian mysteries, describes Mary as the great antithesis of Eve, and this idea of Our Lady occurs repeatedly in other writers even before the Council of Ephesus. We have repeatedly appealed to the words of St. Justin and Tertullian, both of whom wrote before the end of the second century.
  As it is admitted that the praises of Mary grow with the growth of the Christian community, we may conclude in brief that the veneration of and devotion to Mary began even in the time of the Apostles.

  ምንጭ ፡ http://www.newadvent.org/cathen/15464b.htm

  መደምደሚያ ፡
  ስለ ድንግል ማርያም ማስተማርና መጻፍ የተጀመረው በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ሳይሆን በሐዋርያቱና ተከታዮቻቸው እንደሆነ ያቀረብኳቸው ጽሁፍች ማስረጃዎቼ ናቸው ፡፡ ታድም ስለምን ምክንያት ዘወትር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖትና ነገረ ማርያም በተነሳ ቁጥር ይኸን የሃይማኖት አርበኛ በተደጋጋሚ ያነሱታል የሚል ጥያቄ ለአንባቢ ሁሉ አቀርባለሁ ፡፡
  ጭንብላችሁን አውልቁና ሃይማኖትን ብቻ አስተምሩ ፡፡  ReplyDelete
  Replies
  1. ስለማርያም የተሳሳተ ትምህርት በአገራችን የተስፋፋው ዘርአያዕቆብ መሆኑ አይካድም፡፡ ከእርሱ በፊትም ከ5ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወዲህ የተነሱ አባቶችም በዚህ ጉዳይ ላይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ትምህርት አስተምረዋል፡፡ ቁምነገሩ ይህ ሳይሆን ትምህርቱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው አይደለም የሚለው ነው፡፡ እስኪ የትኛው ሐዋርያና ነቢይ ነው ዛሬ ስለማርያም በሚነገረው መልክ ያስተማረ? የነቢያትም ሆነ የሐዋርያት የትምህርት ማእከል ክርስቶስ እኮ ነው፡፡ ስለዚህ እውነቱ ይህ ነውና በኋላ የተጀመረውንና ከመጽሐፍ ቅዱስ አላማ ያፈነገጠውን ትምህርት ሐዋርያት ጀመሩት ማለት ትልቅ ስህተት ነው፡፡ እስኪ ሐዋርያት ካስተማሩት መካከል ማስረጃ አቅርብና እንከራከር፡፡

   Delete
  2. why are you quoting a catholic dogma? All of this you copied and pasted is a Catholic teaching not Orthodox. I challenge you to find an Orthodox teaching that accepts Immaculate conception and co - redemptrix; you'll find none. This is the problem with the ETOC; we'll accept anything as long as it glorifies St. Mary even if it clearly contradicts the bible and early church fathers. Let me quote you a real orthodox teaching regarding Immaculate Conception and co - redemptrix

   St. Mary & The Original Sin:
   The Orthodox Church, whose love towards St. Mary is deeprooted, considers her more holy than all the heavenly creatures, whilst a natural member of the human race. We do not however, set her apart from the human race by assuming that she was born without original sin, as if she was born not of human
   seed.
   This reality is declared in the following Theotokia:

   “How deep is God’s abundance and wisdom,
   that the womb under judgement
   brought forth children by incurring pain;
   she became a fountain of immortality,
   bringing forth Emmanuel without human seed,
   so that He might destroy corruption of our nature”.
   Thus, the Church makes a distinction between St. Mary’s life before and after the moment of divine Incarnation.
   In another Theotokia we say:

   “The Holy Spirit filled you completely,
   filled every part in your soul and body,
   O Mary, the mother of God”.
   St. Mary, herself declared her joy to God, her Saviour…
   for indeed she was in need of salvation.
   To this effect St. Ambrose says:

   “When the Lord wanted to redeem the world, He began
   His work with Mary, that she, through whom salvation
   was prepared for all, should be the first to draw the fruit of salvation from the Son”.

   St. Augustine also says:

   “Mary sprang from Adam, and died in consequence of
   sin; Adam died in consequence of sin; and the flesh of the Lord, sprang from Mary, and died to destroy sin”.

   Regarding co - redemptrix
   No Orthodox theologian calls St. Mary “Coredemptrix”, and no worship is offered to her, but only veneration and praise….
   In other words, in the Orthodox Church there is anaccurate line that divides Christ from St. Mary, His Mother.

   ምንጭ: http://www.saint-mary.net/coptic_faith/SaintMaryintheOrthodoxConcept.pdf

   Book: St. Mary in the Orthodox Concept by Fr. Tadros Y. Malaty (pages 64-66)

   Delete
  3. ewnt
   የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከካቶሊክ የተለዩት በማርያም ላይ ባላቸው ልዩነት አይደለም ፡፡ መጀመሪያ የተለያዩበትን መርምር ፡፡ የማርያምን ትምህርት መቃወም የተጀመረው በኘሮቴስታንቱ መሪ ሉተር ነው ፡፡ ከዛ በፊት ይኸ ርሱ ያነሳው ልዩነት በሐዋርያቱ ዘመን ቢኖር ኖሮ ይጻፍልን ነበር ፡፡ እምነታችን ሲመሠረት ካቶሊኮች ነበሩ መሪዎቻችን ፤ ኋላ ላይ ግን የዶግማ ልዩነት በመፈጠሩ ኦርቶዶክስ (ኦርየንታል)በማለት አባቶች ከማኀበሩ ተለዩ ፡፡ ነገረ ማርያም በዛ ወቅት በልዩነት አልተጠቀሰም ፡፡ ስለዚህ ካቶሊክ ስለጻፈው ብቻ አላነብም አትበል ፡፡

   Delete
  4. @Anonymous Dec. 5, 2012 8:04 AM

   Did you even read the citation I posted? You completely ignored the Orthodox teaching and you accept the Catholic dogma just because it glorifies St. Mary. You said "የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከካቶሊክ የተለዩት በማርያም ላይ ባላቸው ልዩነት አይደለም ፡፡" I didn't say that is the reason they separated. My argument is there is a difference in Orthodox and Catholic Churches when it comes to Immaculate Conception and co - redemptrix. The teaching of Immaculate Conception and co - redemptrix came way after the two churches split. Immaculate Conception at the year 1854 (1403 years after the split). I know the history of the two churches and what lead them to separation in the council of Chalcedon at the year 451 A.D.; two different views on the nature of Christ.

   The thing you need to keep in mind is, the nature of Christ isn't the only difference. Later on even after the two churches split, the Catholic Church added other dogmas that weren't previously taught by the early church fathers. For instance, the Catholic Church believes the Holy Spirit proceeds from the Father and the Son. They added this teaching in the year 589 A.D. after the two churches already split (138 years later). As you probably already know, we reject this teaching because it was always taught the Holy Spirit proceeds from the Father alone.

   The Catholic dogma of Immaculate Conception and co - redemptrix is also rejected because it's a later addition. The Orthodox faith is Apostolic and we don't just invent dogmas as we go along.

   I challenge you again, cite me an Orthodox church that accepts the Immaculate Conception and co – redemptrix; you’ll find none.

   Delete
  5. ጥንተ አብሶ አንተ የግብጾችን እኔ ደግሞ የአገራችን አባቶች ጽፈው ያቀረቡትን ተመርኩዤ ነው የጻፍኩትና ፤ ስደት ከፈለግህ እንዲያ በለኝ ፡፡ እኔ ግን ቤተ ክርስቲያናችን የምታስተምረንን ከካቶሊክ ቢመሳሰልም የምቀበለው የኛ አባቶች ያስተማሩኝን ነው ፡፡ አቡነ ሸኑዳና ተከታዮቻቸው የጻፉት ሁሉ የቤተ ክርስቲያናችንን ዶግማና ቀኖና ማስተካከያ መጽሐፍ ሊሆኑ አይገባም ፡፡
   አመሰግናለሁ

   Delete
  6. ewnt
   ከላይ ስለ ድንግል ማርያም ትምህርት አፄ ዘርዓ ያዕቆብ አምጥቶ ቤተ ክርስቲያናችንን አሳሳተ የሚል አንደምታ ስላነበብኩ ፤ አይ በአራተኛውና በአምስተኛው ምእት ዓመት ሌሎች ቀድመው ጽፈዋል ፤ ሐዋርያቱም ስለ ድንግል ማርያም መከበር ቅሬታ ያሰሙበት ሥፍራ የለም ፡፡ ሉቃስ ምስሏን ሳይቀር ስሎ ሲያቀርብ የተቃወመው አልተቃወሙም ፡፡ ስለዚህ ዘርዓ ያዕቆብን መውቀሱ ትክክል አይደለም በማለት ማስረጃ ይሆን ዘንድ የማያምኑ ወይም ገለልተኛ ጸሃፊዎች ለንባብ ያስቀመጡትን እንድትመዝኑ አመጣሁ ፡፡

   አንተ ደግሞ ከተጻፈው ሁሉ ነቅሰህ ስለ ጥንተ አብሶ አንስተህ እንከራከር ትለኛለህ ፡፡ ይኸ ርዕስ ተከራክረንበት ብዙ ተባብለንበት ፋይሉ የተዘጋ ስለሆነ ጊዜ ካለህ ሁሉንም በጥሞና አንብበህ ለራስህ የሚሆነውን አቋም እንድትይዝ የሚመረገውን አድራሻው ጐልጉየ አምጥቻለሁ ፡፡

   http://www.abaselama.org/2012/06/blog-post_15.html
   http://www.abaselama.org/2012/07/blog-post.html
   http://www.abaselama.org/2012/07/blog-post_06.html

   መልካም ጥናት ይሁንልህ
   እግዚብሔር ይርዳህም

   Delete
  7. @Anonymous December 5, 2012 4:02 PM & 4:36 PM

   I don't want to say much because clearly you don't have much knowledge on this issue. Read church history, maybe then you can come to your senses.

   You said "እኔ ግን ቤተ ክርስቲያናችን የምታስተምረንን ከካቶሊክ ቢመሳሰልም የምቀበለው የኛ አባቶች ያስተማሩኝን ነው ፡፡" My friend, do you have any idea who St. Augustine is? Do you know kidus Qarlos? St. Ambrose? These are early church fathers we all respect; the true defenders of the Orthodox faith. They all testified St. Mary was a human being like you and me and so she was born with original sin. Why do you blindly discredit these fathers? All ORIENTAL ORTHODOX CHURCHES follow their teaching (Armenian Orthodox, Syrian Orthodox, Indian Orthodox, Coptic Orthodox). Read read read. Being Ethiopian doesn't matter when it comes to faith. Open up Haymanote Abew and point to me an Ethiopian Father in there. NONE. You see it doesn't matter, all it matters is they speak the truth.

   Delete
  8. You guys seem to be a little outdated.

   First, do you know that there is no difference between the Orthodox and the Catholic Churches in Christology?

   If you don't believe me look at the following links where you will get common declarations by the Church fathers   Second, the Catholic Church doesn't believe or teach to worship Mary. This is a total lie. But, she venerates her as theotokos.   Delete
  9. ewnt
   ኢሳ 1፡9 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር ይላልና እንድንድነበት የተገባ ንጹህ ሥጋና ነፍስን ርሱ በጥበቡ ጠብቆልናል ፡፡ ይኸም በድንግል ማርያም በኩል ሆነ ፡፡

   “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ፣ ሥርዓተ አምልኮትና የውጭ ግንኙነት” በተባለ መጽሐፍ ገጽ 49 ላይ ስለ ጥንተ አብሶ የጻፉልን እንዲህ ይነበባል ፡፡

   “አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ከአዳም ዘር የተላለፈ ኀጢአት /ጥንተ አብሶ/ ያላገኛት መርገመ ሥጋ ፣ መርገመ ነፍስ የሌለባት ገና ከመወለዷ አስቀድሞ በአምላክ ኀሊና ታስባ ትኖር የነበረች በሰው ልማድና ጠባይ ከሚደርሰው ሥጋዊ አሳብና ፈቃድ ሁሉ የተጠበቀች ከተለዩ የተለየች ንጽሕት ፣ ቅድስተ ቅዱሳን ናት” መሓል 4፡7 ፡፡ “ምልዕተ ፀጋ ምልዕተ ክብር ሆይ ደስ ይበልሽ” ተብላ በቅዱሳን መላእክት አንደበት በቅድስናዋ ተመስግናለች ፤ ትመሰገናለችም” ሉቃ 1፡28-3ዐ ፡፡ “እመቤታችን በውስጥ በአፍኣ በነፍስ በሥጋ ቅድስት ስለሆነች ፣ እግዚአብሔር ለልጁ ማደሪያ መርጧታል ፤ ማኀደረ መለኮት እንድትሆን አድርጓታል ፡፡ አምላክን ለመውለድ ያስመረጣትና ያበቃት ፣ ድንግልናዋ ፣ ንጽሕናዋ ነው ፡፡ /ሕርያቆስ ቅዳሴ 45 ፤ መዝ 132 ፡13/ ፡፡ ንጽሐ ሥጋ ፣ ንጽሐ ነፍስ ፣ ንጽሐ ልቡና ለእመቤታችን ገንዘቦቿ ናቸው፡፡”

   ይህን በ18 (፲፰) የቤተ ክርስቲያናችን አባቶችና ሊቃውንት የቀረበውን ቃል ፣ በአራት (፬) የቤተ ክርስቲያን መምህራን የተፈተሸውንና ለኀትመት የበቃውን መጽሐፍ ወደጐን ገፍቶ ማዶ ማዶ ማየት ለእኔ አይሆንልኝም ፡፡ ሲመችህ ጊዜ ወስደህ ከላይ በተሰጡት አድራሻዎች የቀረቡ ክፉም ደግም አስተያየቶች ስለሚገኙ አንብባቸው ፡፡

   Delete
  10. ለሽማግሌው AnonymousDecember 5, 2012 10:36 PM

   የተዛባብህን ትምህርተ ሃይማኖት ብታስተካክለው ወይም ብታጠራው በማለት ከላይ በተቀመጡት አድራሻዎች ከተጻፈው መሃል ይህን ቀንጭቤ አምጥቻለሁ ፡፡

   ክርስቲያኖች ኦርየንታል ኦርቶዶክስ የሚለውን መለያ ስም ለራሳቸው ያገኙት /የሰጡት/ የኬልቄዶንን ጉባዔ /እኤአ 451 ዓ.ም./ ውሳኔ አንቀበልም በማለታቸው ምክንያት ብቻ ነው ፡፡ ይኸውም ካቶሊኮች መለኮትንና ሥጋን አልተዋሃዱም ፤ በዚህም ምክንያት ኢየሱስ አንድ ጊዜ በሥጋው ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በመለኮቱ ፣ እንደ ፈለገ እያፈራረቀ ሥራዎቹን አከናውኗል ፤ ሥጋ የሥጋን ፣ መለኮት ደግሞ የመለኮትን ድርሻ ፣ ለየግላቸው በመሆን ፈጽመዋል በማለት ፤ የአባ ልዮንን አንድ አካልና ሁለት ባህርይ ፍልስፍና ስለሚያራምዱና ፣ በመስቀልም ላይ ደግሞ ተለያይተዋል በማለታቸው ነው ፡፡ ሌላውም የምንለይበት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መንፈስ ቅዱስን ከአብና ከወልድ ይሠርጻል በማለት ከእኛ ዶግማ ስለምትለይ ነው ፡፡ እኤአ 1ዐ54 ዓ.ም. ከምሥራቅ ኦርቶዶክስም (ግሪክ)ለመለያየት ከተጠቀሱት ዋነኛ የልዩነት ምክንያትም አንዱ ይኸ ነው ፡፡

   የኦርየንታል ኦርቶዶክሶች ደግሞ መለኮትና ሥጋ ተዋህደው ፍጹም አንድ አካል ሆነዋል (ንብረትና ሃብት ተወራርሰዋል ፤ ማለትም አንድ አካልና አንድ ባህርይ ሆነዋል) በማለት ተለይተዋል፡፡

   ይኸም ማለት የኦርቶዶክስነት ስያሜ የተገኘው የድንግል ማርያምን ከጥንተ አብሶ ነጻ መሆንና አለመሆንን ጉዳይ አክሎ በመግለጽ አይደለም ማለት ነው፡፡ ስለዚህም በጥንተ አብሶ ትርጉም ከሌሎች አኀት አብያተ ክርስቲያናት መለየት ከማኀበሩ ውጭ ነን አያሰኘንም ፡፡ እንደዚህ በምንለይበት ሁሉ ከአካልነት የምንከፈል ቢሆንማ ፣ የኢኦተቤክ ከሌሎች ተለይታ ለታቦት ክብር ሰጥታ በየአደባባዩ ስትታይበት ፣ ጥምቀትዋን እየዘከረችና ለዓለም እየመሰከረች ስታስተዋውቅ ፣ ደመራዋንም በያመቱ ደምረነ ምስለ እለ ይድኀኑ በማለት እያቀጣጠለች ስትዘምር ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎቿንም ቁጥር ሰማንያ አንድ ነው ብላ ስታስነብብ … አውግዘው መለየት ነበረባቸው ፡፡ ከዚህም የተነሳ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በኒቅያ 318ቱ ሊቃውንት ፣ ኋላም በኤፌሶን 2ዐዐው ሊቃውንት የወሰኑትን ትምህርተ ሃይማኖት ስለተቀበለችና ስለያዘች ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ትባላለች ወደፊትም በዚሁ ትቀጥላለች፡፡

   የካቶሊኮች ዶግማ ስለነገረ ማርያም የሚያስተምረው ከኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ጋር ይመሳሰላል፡፡ ለመጥቀስም ያህል
   - ቅድስት ድንግል ማርያም ከጥንተ አብሶ ነጻ መሆኗን
   - ዘላለማዊ ድንግልናዋን ፣
   - ከግብረ ኃጢአት ነጻ መሆኗን ፣
   - እመ አምላክ (የአምላክ እናት)መባሏንና
   - ድኀረ ሞተ ሥጋ ማረጓን

   Delete
  11. @Anonymous December 6, 2012 8:42 AM

   I've read the book and I know some Ethiopian Church fathers accept it. But also there are some Ethiopian church fathers that reject it (ex. the late Abune Paulos). The problem is, we only accept those who say she's free from the original sin and label those who reject the teaching "tehadiso". The word "ንጽሕት" doesn't necessarily imply she's free from the original sin. Depending on the context, it could mean she has never committed sin throughout her life. And this is true we all believe this. So as I see it, the ETOC has a mixed and ambiguous opinion. We can't generalize and assume everyone accepts it. That's why you need to look beyond the Ethiopian Church and research for your own. Plus as I have said Qerlos, St. Augustine, St. Ambrose all said she died just like every human being because of the Original sin. These fathers lived in the 5th century. There is no better testimony than them.

   "አምላክ ከሾማቸው ከመምህራን ይህን ረቂቅ ትምህርት ተምረናል፤ እርሱን አስተማሩን፤ ይህም ትምህርታችን ለማያምኑ የተሠወረ ነው፤ ለምእመናን ግን የተገለጸ ነው፤ ጻድቃን ያውቁታል። ኃጥአን ግን አያውቁትም።" ሃ.አ. ምዕ 10: 17
   እንዳሉት፥ የኦርቶዶክስ ነገረ መለኮት ዶግማ በኦሪት በነብያት በሐዋርያት ተደጋግመው ባልተነገሩ ነገሮች ላይ አይመሠረትም። So don't expect me to believe a teaching that originated in the 20th century while ignoring the widespread overall testimony of the early church fathers.

   “Mary sprang from Adam, and died in consequence of sin; Adam died in consequence of sin; and the flesh of the Lord, sprang from Mary, and died to destroy sin” St. Augustine

   "ቅድስት ድንግል ሰማያዊት ናት የሚል ቢኖር ውጉዝ ይኹን" ሃ.አ. ምዕ 123: 8

   Delete
  12. ewnt
   ምድራዊ የዘር ሃረጓ በቤተ ክርስቲያናችን ተሟልቶ ስለተጻፈልን እኔም ድንግል ማርያም ሰማያዊት አካል ናት አላልኩም ፡፡ ይህን የመሰለ ቋንቋና ትርጉም ኘሮቴስታንቶቹ የተጠቀሙት ፣ ካቶሊኮችን በተከራከሩበት ጊዜ ነው ፡፡ ነገር ማጣመም ካልሆነ በስተቀር ካቶሊኮችም እንዲያ እንደተባለው ድንግል ማርያምን ሰማያዊ አካል አድርገው አያምኑም ፡፡ ምክንያቱም አምላክ ሰው ሆነ የሚለውን ዶግማ ያበላሽባቸዋልና ነው ፡፡

   ስለሞት ምንነት ብዙ የማናውቀው ምስጢር አለ ፡፡ ጌታም ሞተ ፣ ድንግል ማርያምም ሞተች ፣ እኛም ሞታችን በመስቀሉ መስዋዕት ኃጢዓታችን ተሽሯል ፣ ሞታችንም ቀርቷል ብለን የምናምነው እንኳን ቀናችን ሲደርስ እንሞታታለን ፡፡ ይኸ የምናውቀውን መሞትና አለመሞት የአዳም ኃጢአት መሥፈሪያ አልመሰለኝም ፡፡ ምክንያቱም ሄኖክና ኤልያስ በመሃል ህያው እንደሆኑ ተሰውረዋልና ፡፡

   በተረፈ በግሌ ሃይማኖትን ከአባቶች ይበልጥ ጠልቄ አላውቃትም ፡፡ የማነበውን እንኳን በውል ለመረዳት ብዙ መድከም አለብኝ ፡፡ ይህንን ደካማነቴን ስለምገነዘብ የሚያስተምሩኝን ልተችና ልሽር ቀርቶ ፣ እንዴት ሆነ ብዬ ገብቼ ልዳክርበት አስቤው አላውቅም ፡፡ ጥበቡ ያላችሁ ብዙ መርምሩና ብርሃናችሁን ለራሳችሁ አድርጉት ፡፡ እግዚአብሔር ፊት ሁላችንም ፣ አስተማሪም ተማሪም ፣ ጥበበኛና ሊቅም ቢሆን መሃይምም ተሰልፈን እንደ ሥራችንና እንደየእምነታችን ለመቀበል ለፍርድ እንቀርባለን ፡፡ ተያይዞ ወደ ገደል እንዳይሆን አንተም እምነትህ ለራስህ ትሁንልህ ፡፡ እኔ ግን ቅዱስ የሆነው አምላክ ከአደፈ ስጋና ነፍስ ተዋሃደ ብዬ ምን ጊዜም አልመሰክርም ፡፡

   Delete
  13. @AnonymousDecember 6, 2012 3:55 PM

   Thank you for your response. "እኔ ግን ቅዱስ የሆነው አምላክ ከአደፈ ስጋና ነፍስ ተዋሃደ ብዬ ምን ጊዜም አልመሰክርም ፡፡" ልክ ነህ፤ እኔም እንዲህ ብዬ አልመሰክርም፤ ይህ ፍጹም ክህደት ነው። you miss understood me. At the annunciation, the Holy Spirit sanctified the Virgin Mary before the incarnation.

   I really respect your view and thank you for your advice my brother. May God bless you. I'm nobody; I'm nothing but dust and ashes. Forgive me if I offend you or anyone who reads this. My advice to you is to respect all sources and dig deep. Have an open mind and always look things from all angles. I sent you a link at the bottom, it will explain everything. God bless you

   http://medhanialemeotcks.org/wp-content/uploads/2011/01/Mary_the_Mother_of_Jesus1.pdf

   Delete
  14. ewnt
   ክርስቲያን የሆኑ አማኞች ስለ ድንግል ማርያም ከጥንተ አብሶ ነጻ መሆን ከሃይማኖተ አበው ጠቅሰው የጻፉትን ማስረጃ ስላገኘሁ በአጭሩ አስነብባለሁ ፡፡

   1. «ወለደት ድንግል ዘፀንሰቶ እንዘ ኢተአምር ብእሴ በስጋ ዘፈጠሮ ለርእሱ ወወለደቶ ዘእንበለ ደነስ ወሕማም ወኢረሰስሐት በሐሪስ ሐፀነቶ ዘእንበለ ፃማ ወድካም ወአጥበቶ ዘእንበለ ድካም ወአልሐቀቶ በሕግ ዘሥጋ ዘእንበለ ትካዝ ።»
   ትርጉም « ለተዋሕዶ የፈጠረውን ሥጋ ያለ ወንድ ዘር ያለ ኃጢአት ያለምጥ ወለደችው የአራስነት ግብርም አላገኛትም ያለድካም ያለመታከት አሳደገችው ያለድካም አጠባችው ለስጋ በሚገባ ሕግ ምን አበላው ምን አለብሰው ሳትል አሳደገችው» ሃይማኖተ አበው ዘአትናትዮስ ፳፰፡፲፱

   ያለ ኃጢአትና ያለምጥ ወለደችው የሚለው ቃል ትኩረት ይደረግበት ፤ ምክንያቱም በሔዋን በኩል በእርግማን ከመጣው የሴቶች ልማድ ፍጹም ነጻ ስለሚያደርጋት

   2. « ከመገባሪ ጠቢብ ሶበ ይረክብ ግብሮ ዘይትጌበር ይገብር እምኔሁ ንዋየ ሰናየ ከመዝ እግዚእነ ሶበ ረከበ ሥጋሃ ቅዱስ ለዛቲ ድንግል ወነፍሳ ቅድስት ፈጠረ ሎቱ መቅደስ ዘቦቱ ነፍስ » ሃይ አበ ዘአፈወርቅ 66 ፡ 14
   ትርጉም « ጥበበኛ ንጹህ አፈር ባገኘ ጊዜ ጥሩ እቃ እንደሚሰራበት ጌታችንም የድንግል ንጹህ ሥጋዋን ፣ ንጹህ ነፍሷን ባገኘ ጊዜ ይዋሃደው ዘንድ ነፍስ ያለውን መቅደስ ሰውነቱን ፈጠረ «
   ንጹህ ነፍስና ሥጋ የሚለው አገላለጽ አፈጣጠሯ በአዳማዊ ኃጢአት ያልተበከለ መሆኑን ያስረዳል ፡፡

   3. ቅዱስ ኤራቅሊስ በሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 48 ቁጥር 31 ስለ እመቤታችን ንጽህና ለጠባቂነት የታጨላት ዮሴፍ አለመረዳቱን ሲመሰክር እንዲህ ይላል
   « ኢያእመረ እስመ ዘተፈጥረት እምነ ጽቡር ጽሩይ ትከውን መቅደሶ ለእግዚአብሔር »ትርጉም « የእግዚአብሔር መቅደሱ ማደርያው ትሆነው ዘንድ ከንጹህ አፈር (ዘር) የተፈጠረች መሆኗን አላወቀም »
   ከሊቁ ከቅዱስ ኤራቅሊስ ንግግርም ድንግል ማርያምን በንጽህና ፈጠራት አለ እንጂ ከፈጠራት በሁኃላ አነጻት አላለም ፡፡

   Delete
  15. ለ ewnt
   በአስቀመጥከው አድራሻ የተጻፈውን ጽሁፍ ከዚህ ቀደም አንብቤዋለሁ ፡፡ ጸሐፊውም ትልቅ አባታችን ፣ ሃይማኖታችንን በሥርዓቱ እንደ ተማሯት መናገራቸው ብቻ ሳይሆን ሥራቸው የሚመሰክርላቸው ፣ አሉን የምንላቸው የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ መሆናቸውን አውቃለሁ ፤ አምናለሁም ፡፡ ቀሲስ ይኸን ጽሁፍ ለምን ወደ ህዝብ ንባብ እንደ አመጡት ምክንያቱን ብትረዳ እኔን ብዙ አትታገለኝም ነበር ፡፡

   ይኸን ጽሁፍ አደባባይ ላይ ከማውጣታቸውና ለንባብ ከማብቃታቸው በፊት ርሳቸው የደረሱበትን እውነታ /አንዳንድ ሌሎች አባቶችንም ይጨምራል/ ፣ ሌሎች ደግሞ በተለየ ስለሚረዱትና በአንዷ ቤተ ክርስቲያን ሁለት ዓይነት ትምህርት የሚያስተምሩ መምህራን ስላፈራች ፤ ይህ እንዲስተካከል ለሚመለከተው ክፍል ማለትም ኢትዮጵያ ላለው ሲኖዶስ (በተደጋጋሚ ይመስለኛል) ጥያቄ ያቀርባሉ ፡፡ ሲኖዶሱ ግን የዶግማ ጥያቄ መሆኑን ቢረዳም እንኳን ፣ በአግባቡ በወቅቱ አስቸኳይ መልስ ከመስጠት ይታቀባል ፡፡

   ይኸ ደግሞ በአሜሪካ ያሉትን አባቶች በተለይም በርሳቸው ላይ የስም ማጥፋት ሥራ ፣ የማርያም ጠላትና የማርያም ወዳጅ የመባባል ዓይነት አምባጓሮ ስላስነሳ ፤ እውነት አለኝ የሚሉት አባታችን ቀሲስ ከሌሎች አኃት ቤተ ክርስቲያን አባቶች መልስ እንዲያገኙ ጥያቄ አቀረቡ ፤ በዛም ርሳቸው በሚሉት መልክ ከሌሎች ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናት መልስ ተሰጠ ፡፡ ይኸን ታሪክ ልጠቅስ የተገደድኩት እንዲህ በየብሎጉ እየለጠፉ ነገርን ወዲያ ወዲህ ከማለት ፣ የሚቆረቁረው አማኝ መጀመሪያ መሥመሩን ጠብቆ መልስ ይሰጥበት ዘንድ ለሲኖዶስ ጥያቄ ያለመሰላቸት ማቅረብ አለበት ፡፡ ያን ሳያደርጉ ተሯሩጦ መንጋው ጋር መጥቶ በደፈናው ላስተምር ፤ ይኸ ነው እውነቱ ማለት ትልቅ ስህተትና ማደናበር እንደሆነ ይሰማኛል ፡፡

   የርሳቸው ትምህርት እንዲህ የወጣው አንድም እምነታቸው ትክክል መሆኑን መግለጽ ስለሚገባቸውና ከልጆች አሉባልታ መዳን ስላለባቸው ፤ ሌላውም በምንተእፍረት የታፈነውን በሥርዓቱ ሄደው እውነትን የሚገልጣት ስላጡ ፤ ይኸንኑ ለኀብረተሰቡ ለማሳወቅ ፤ አንድም በሙያቸውና እምነታቸው የቤተ ክርስቲያኗ ችግር ይመለከተኛል ፤ ጉዳዩም ያገባኛል ፤ ሁለት ዓይነት ትምህርት መሰጠቱ ትክክል አይደለም ለማለት ይመስለኛል ፡፡

   በቤተ ክርስቲያናችን ሟች አቡነ ጳውሎስ (ነፍሳቸውን ይማርልን)በመመረቂያ ጽሁፋቸው ያሰፈሩትን ቃል እንኳን በግንባር ሲጠየቁ በሲኖዶስ ፊት እንደ አቋም አልተከራከሩለትም ፡፡ የመመረቂያ ጽሁፍ የእምነት መግለጫ ስላልሆነ ለምን አላደረጉም ብዬ አልኰንናቸውም ፡፡

   ይኸንኑ ጉዳይ ቆሞስ በመጽሐፍ ጠቅሰው (ገና አላነበብኩትም) ለሕዝብ በማቅረባቸው ፤ ባለፈው ዓመት የግንቦት ስብሰባ አንድ ጥያቄ ሆኖ ተነስቶባቸው መልሳቸውን ይዘው እንዲቀርቡ በይደር ታልፈው እንደ ነበር አስታውሳለሁ ፤ አባታችን በሥጋ ሞት በማረፋቸው ነገሩ ሳይታይ ጥቅምትም አለፈ ፡፡

   ይኸ እንግዲህ የሚያሳየው ከመሃከል አንዳንድ መጽሐፍትን የተረዱ አባቶች ቢኖሩም ፣ ቤተ ክርስቲያንን የሚመሩት አባቶች (ሲኖዶስ) ግን እምነታቸው ቅድስት ድንግል ማርያም ጥንተ አብሶ እንዳላገኛት ነው (ከላይ የጠቀስኩት መጽሐፍም አስረጅ ነው)፡፡ ክብረ ነገስት የሚጠቅሰውም ይህንኑ አቋም ያጠናክራል ፡፡ የቤተ ክርስቲያን መመሪያንና ትምህርትን መከተል ደግሞ እንደ አማኝ ግዴታዬ በመሆኑ የማላፍርበት አቋሜ ጥርት ያለ ነው ፡፡ እስከ አሁንም በተደጋጋሚ ተገልጿል ፡፡

   በተረፈ መንፈስ ቅዱስ አነጻት የምትለውን ለምን መቀበል እንደሚያስቸግር ከላይ ለንባብ ባስቀመጥኳቸው አድራሻዎች ሰፍሯል ፡፡ ለጊዜው በአጭሩ ለማስነበብ
   1.ከርሷ ቀደም ብለው በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉት እነ ኤልሳቤጥን ከጥንተ አብሶ አላነጻቸውም
   2.በመንፈስ ቅዱስ በኩል ከበደል መንጻት ከተገኘ ፤ ዶግማችንን ማስተካከል ግድ ይላል ፤ ምክንያቱም በደል የሚነጻው በኢየሱስ ደምና በመንፈስ ቅዱስ መሞላት በኩል ማለት ስለሚሆን
   3.አምላካችን ሰው ሆነ (ለማያምኑ ትልቅ መሰናከያ ቃል) ፣ መከራንና ስቃይን ተቀበለ ከማለት ይልቅ ለሁላችንም መንፈስ ቅዱስን በመላክ ከተወራራሽ ኃጢአት ማንጻት ፣ ለፈጣሪአችንም ቀላሉ መንገድ ይሆን ነበር ያሰኛል ፤ የጌታ ደሙ የፈሰሰውም ለከንቱ ነው ማለት ያስችላል

   ያም ሆነ ይህ ለንባብ ስላተጋኸኝ አመሰግንሃለሁ ፡፡ ባስነበብከኝ ጽሁፍ በአንዳቸውም አልተከፋሁም ፤ የእውነት አመለካከት ልዩነት እንዳለን ግን ለማስረዳት ሞከርሁ ፤ አንተም እንደዛው ፡፡

   አመሰግናለሁ
   እግዚአብሔር ሁላችንንም በጸጋው ይጎብኘን ፡፡ አሜን

   Delete
 4. ካ ካ ካ... የስትራተጂ ለውጥ መሆኑ ነው? ነቄ!!!

  ReplyDelete
 5. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !December 1, 2012 at 9:43 PM

  Thank You,Tesfa.

  ReplyDelete
 6. I LIKE THIS. GOD BLESS YOU. ABBA

  ReplyDelete
 7. ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በቀደመ ክብሩ ካለማየት፣ ዛሬ አማላጅ ነዉ ብሎ ከማመን፣ የፍጡርንና የፈጣሪን ሥራ ከመቀላቀል የከፋ ሐጢአት የለም፡፡ ይህ የሃይማኖት ክህደት ነዉ፡፡ እባክህ እንዲህ ከማለትህ በፊት ግራ እንደገባህ ለራሱ ለፈጣሪ ንገረዉ፣ ድንግል እናቱንም አማልጂኝ በላት በተሰበረ ልብ ከጠየቅህ እዉነቱ ይገለጥልሃል፡፡ ዘርአያዕቆብ፣ ማንትሴ፣ ማንትሴ እያልክ አታጭበርብር፡፡ መንፍቅናዉ ይጎዳሃልና እባክህ ተመለስ፡፡ ሥለክብሯ ከትናንቱ ዛሬ የተሻለ ብለሃል፡፡ ግን አሁንም ይቀርሃል፡፡ እየነቀፍከዉ ያለዉ የመዉጊያዉን ብረት ስለሆነ የቀረህን ተመልክተህ አስተካክል፡፡ እርሱ ይርዳህ!

  ReplyDelete
 8. Melkam bilehal bezihu ketil. Geta yibarkih.

  ReplyDelete
 9. አይ ተስፋ……… በማር የተለወሰ መርዝ አቀረብክልን………አይ ያንተ ነገር

  ReplyDelete
 10. ምን ልበልህ በፍቅርዋ የተደርገልኝን ብነግርህና ባሳይህ ለኔ ቅርብ ናት ከልጅዋ አማልዳ ጸጋን አብዝታልኛለች
  ተሰቀለችልን ሞተችልን ያለ ማን አማኝ ያለኮ የለም ታማልዳለች በቃ ይህን ነው ኦርቶዶክስ ያለው ፡፡

  ReplyDelete
 11. TEMESGEN BTSET YEMILEWNE KAL MAMENEH BERASU MELKAM NEW LELAWU NEGER BEHIDET YGELETLHAL WONEDME SLE DINEGEL MARYAM MANENET SLE KBRUWA LE EGNA LE ORTODOCSAWYAN TEWT ATNEGERUNE LENATE GETA LBONA YSTACHIHU ERSU YAKEBERACHEWUNE KIDUSAN MENKEFUNE TEWNA SLEKIDUSANE KEBER TEMARU SYMARU MASTEMAR SLEMAYCHAL LELAW GETA ERASU BEWONGEL BENE YMIYAMNE BINOR ENE YEMSERAWNE YSERAL KEZIHEM BELAY YSERAL YALEWNE YKALUNE MISTIRE BEDEB YETERDACHIHU AYMESLEGNIMNA KALUNE BEDEB MERMRUT SEW BEMAWOKEM BALEMAWOKM YBEDLALNA GETA ERASU LBONA YSTACHIHU::

  ReplyDelete
 12. ዘወትር ከአባታችን ሆይ ቀጥሎ በምናደርሰው ‹‹በሰላመ ገብርኤል›› በተሰኘው የጸሎት ክፍል ውስጥ ‹‹በሐሳብሽ ድንግል ነሽ በሥጋሽም ድንግል ነሽ›› የሚል የምስጋናና የምስክርነት ቃል ይገኛል፡፡ በተመሳሳይ መንገድ በመልክዓ ማርያም ውስጥም ‹‹ሰላም ለሕሊናኪ ሐልዮ ሠናያት ልማዱ ወገቢረ ምሕረት መፍቅዱ›› ማለትም ‹‹ምሕረት ማድረግ ለሚወድ መልካም መልካሙን ማሰብ ልማዱ ለሆነ ሕሊናሽ ሰላም እላለሁ!›› የሚል የምስጋና ቃል አለ፡፡
  የተአምረ ማርያም መቅድም ደግሞ የድንግል ማርያምን ሕሊና ከመላእክት ሕሊና ጋር ያስተያይና በልጦ ሲያገኘው በመደነቅ እንዲህ እያለ ያመሰግናል፡፡ ‹‹ሥጋዊ ነገር ከማሰብ መጠበቅ ከአዳም ልጆች ለማን ተሰጠው? ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ለመላእክት እንኳን አልተቻላቸውም፡፡ በቀደመው ወራት ያልተሰጣቸውን ሽተው በድለው ከሰማይ ወደ ምድር ወርደዋልና፡፡›› ከዚህም ጋር አያይዞ ‹‹የእመቤታችን ማርያም አሳብ እንደ አምላክ አሳብ ነው፡፡›› ይህም አሳብዋ ንጹሕና መልካም ብቻ መሆኑን ያስረዳናል፡:
  እኛ ክርስቲያኖች ‹‹እግዚአብሔርን እንድንመስል›› ታዘናል፡፡ (1ጢሞ4.7-8፤ 1ቆሮ11.1) ይህም በመልክ አይደለም፡፡ በሥራና በአመለካከት እንጂ፡፡ እግዚአብሔርን በአመለካከት መምሰል የማይቻል ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔርን ምሰሉ አንባልም ነበር፡፡ በመልክ ስለመምሰል የሚናገር ቢሆን ኖሮ ደግሞ መልክን የሚፈጥረው ፈጣሪ ስለሆን ‹‹ምሰሉ›› አንባልም ነበር፡፡ የሚደንቅ ነው! እኛ ፈጣሪን በአሳብና በአመለካከት እንድንመስለው ታዘዝን፡፡ ድንግል ማርያም ግን መስላ ስለተገኘች ‹‹አሳብዋ እንደ አምላክ አሳብ ነው፡፡›› የሚል ምስክርነት ተሰጠላት፡፡
  ቀደም ሲል ስለ ድንግል ማርያም ፍጹም የሕሊና ድንግልናና በጎነት ከአዋልድ መጻሕፍት ያስቀደምኩት ሆን ብዬ ነው፡፡ ይህንን ትምህርት መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት እንደሚደግፈው ማሳየት ያስፈልጋልና እነሆ!
  ብዙ ሰዎች ስለ ድንግል ማርያም የሕሊና ንጽሕና ስንናገር በምን አውቃችው ነው? ለማለት ይዳዳቸዋል፡፡ በእርግጥ እኛ እንኳን የድንግል ማርያምን ሕሊና የኃጥአንንም ሕሊና የምናውቅበት ችሎታ የለንም፡፡ የጻድቃን ሕሊና ከኃጥአን ይልቅ እጅግ ይጠልቃል፡፡ የድንግል ማርያም ሕሊና ደግሞ ከሁሉ ይልቅ ጥልቅ ነው፡፡ ‹‹መንፈሳዊ ሰው በማንም አይመረመርም እርሱ ግን ሁሉን ይመረምራል›› ከተባለ ሰው ፍጹም መንፈሳዊት ድንግል ማርያምን ሊመረምር እንዴት ይችላል? (1ቆሮ2.15)


  ታዲያ ‹‹በሐሳብሽ ድንግል ነሽ›› እያላችሁ ጠዋትና ማታ የምትዘምሩት የእርሷን ሐሳብ በምን አውቃችው? ለሚሉን መልሳችን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ድንግል ማርያም አሳብ ስለሚናገር ነው እንላቸዋለን፡፡ የት ቦታ ቢሉንም ቅዱስ ሉቃስ ሲጽፍ ‹‹ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው ብላ አሰበች›› ይላል፡፡ (ሉቃ1.29) ‹‹አሰበች›› ማለቱን ልብ በሉ፡፡ ይህን አለች ቢል ሰምቶ ነው፤ ይህን ሠራች ቢል አይቶ ነው ይባላል፡፡ ‹‹አሰበች›› ሲል ምን እንላለን? የክርስቲያኖች መልስ አንድ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ምን እንዳሰበች ገልጾለት ነው እንላለን፡፡ ሰይጣንና መናፍቃን የሚሉት አያጡምና ምናልባት ገምቶ ነው ሊሉ ይችላሉ፡፡ መቼም በዚህ አይሳቅም!!! መጸለይ ነው እንጂ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቃለ ሕይወት ያሰማልን
   አትጥፋ ፤ ምናልባት ቢለወጡ ገፋ አድርገህ ግለጽላቸው ፡፡

   Delete
 13. አንድን ነገር ለመተቸት ስለምትተቼው ነገር ማንነትና ምንነት ማወቅ ተገቢ ነው። ለመሆኑ አንተና መሰሎችህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተመሠረተችው በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ መሆኑን ያነበብከው በየትኛው የቤተክርስቲያን ታሪክ ላይ ነው?

  ReplyDelete
 14. Awrew lemin yikotal?

  Yetun yahil asamerku bileh bititsif ketewahidoawian lib dingilin yemitinkelibet haile atagegnm.

  Yekidusan kibir bemigerm huneta lezelalem yaberal. Ye dingilma endet?

  Getan yemisadeb andebet dingilin ema endet?

  Amlake kidusan lib yistachihu.

  Iyesus Kiristos tilant zarem negem hiyawuna fitsum AMLAKACHIN new. Yih yelibachin desta new Enatachin Maryam tesfachin dildiyachin nat.

  ReplyDelete
 15. Biruck hun wondime. Melkam tenagirehal.

  ReplyDelete
 16. በመንፈስ ቅዱስ የተሞላች ስለሆነች እውነቱን ሁሉ ታውቃለች። ታዲያ እንዴት ይህን ሁሉ አልፋ በስሟ መዳን እንዲገኝ ሌላ የመዳን መንገድ ትጠይቃለች? ይህ የጠላት ክስ አይደለምን? ጸሎትስ ወደ እኔ ጸልዩ ለስእሌ ስገዱ ብላለችን? ይህ ትሕትናዋን ይገልጣልን? ኧረ ተዉ ቅድስት ብፅዕት የሆነች እናታችን ድንግል ማርያምን አትሳደቡ ኧረ የዳኛ ያለህ?
  ተናግረህ ሞተሐል መቃብር አፍ አታላይ ሞላጫ ሌባ መናፍቅ ኦርቶዶክስ ለመምሰል በልብህ የሌለውን ፍቅርና ተቆርቋሪነት ልትነግረን ትፈልጋለህ ለዚያውም ለኦርቶዶክስ አማኝ ሂድና ይህንን በአዳራሽህ ስበክ ትቀምሳለህ ፍቅርዋ አልገባህም አርፈህ ቁጭ ብለህ አትዘላብድ ተሳዳቢስ አንተ የዳኛ ያለህ ትላለህ ደግሞ ዳኛውን አማላጅ ያልክ ደፋር የሞቱትን አባቶች ትወቅሳለህ ትሰድባለህ ስምህ ሌላ ምግባርህ ሌላ እውነቱን እግዚያብሄር ይግለጥልህ!!!!

  ReplyDelete
 17. ተስፋ ! እባክህ፣ ተው! መቃወም ያለብህን ነገር ተቃወም! ጽሁፍህ፣ ጥሩ ነበር ግን መደምደሚያው ተራ ወሬ ሆነ፣ እስኪ ልጠይቅህ? በደሳሳ ጎጆ ተጥላ፣በረሃብ በጥም ተንገላታ፣ መሞቷን የሚናገር መጽሃፍ ካለ ም/ ቁጥሩን ብትነገረን? በወርቅ ወንበር ተቀምጣ!የሚለው ለምን ቅር አለህ?? የጌታ እናቱ እኮናት ፣ ምን ይሄ ይገርምሃል? አንተ ተንትነህ ከጻፍከው እውነት በላይ አይደለም፣ በወርቅ ወንበር መቀመጥ። መለኮት የተዋሃደው ስጋ እኮ የማርያም ነው ፡፡ የመዳኒታችን እናት ፣ ወደን እኮ አይደለም የጸጋ ስግደት የምንሰግድላት። ለድህነታችን ምክንያት ስልሆነች እኮ ነው። ታስታውሳለህ ዘፍ፡ 18 ያለውን የ እ/ርን ና ያብርሃምን ንግግር? በሰዶም 5 ጻድቃን ሰወች ስላል ተገኙ ነው ሰዶም የጠፋችው። ቢገኙ ግን ሰዶም አትጠፋም ነበር። አየህ ወንድሜ ድንግል ማርያምም በዘመኗ ሙሉ ሆና ባትገኝ ለሰው ልጅ ምክንያተ ድህነት አትሆንም ነበር። እንደውም ደስስስስ ሊልህ ነው የሚገባው ፣ ለምን ተቃጠላለህ እሱ ባከበራት በወደዳት ?? ለነገሩ እሷን ለማክበር እንዲሁም ለማመስገን ልክ እንደ ኤልሳበጥ በመንፈስ ቅዱስ መሞላት ያስፈልጋል። የጌታን እናቱም ሆነ በርሱ ዙሪያ ያሉትን ለመቀበል ትሁት መሆን ያስፈል ጋል አንተ ደግም የመንግስተ ሰማያት መግቢያ ትኬት የኮረትክ ነው የምትመስለው፡ ይህ የትእቢት መንፈስ ነው፡፡ ትእቢት ደግሞ የዲያቢሎስ ነው ። ሃዋርያው ያለውን ታስታውሳለህ? ገና ምን እንደምንሆን አውቅም አለ፡ በየ ደብዳበውም በጨረሻ ጸልዩልኝ ፤ አቤት ትህትና !!! እስኪ እራስህ በዚይ ቃል ውስጥ እየው፣ ውስጥህን አዳምጠው? አምላካችን ስለ እናቱ ስለ ድንግል ማርያም ብሎ ይማርህ!!! የትእቢትን መንፈስ ያርቅልህ።

  ReplyDelete
 18. Please, Christians. Stop Squabbling each other the sword of the Jihadists is coming near. Come together and pray. Please. Please. Please. We are not called to fight against each other like this. Our fathers have given us what we need to believe in The prayer of Faith (tselote haymanot). That is what matters! Stop over emphasizing words and phrases. Please, we are all the fractures of the One Holy Catholic Apostolic Church, which is always on the way of renewal and repentance.

  ReplyDelete