Monday, December 10, 2012

በአቡነ ሚካኤል ልጅ የውርስ ጉዳይ የተደረገውን ክርክር ሲኖዶሱ የከፍተኛ ፍርድ ቤትን የመጨረሻ የውሳኔ ቀን ሳይጠብቅ በአቋራጭ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወሰደው

Read in PDF

ታላላቅ ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን መመልከትና ውሳኔዎችን ማሳለፍ የሚጠበቅበትና በአሁኑ ወቅት ጥቂቶች የሚያሽከረክሩት ቅዱስ ሲኖዶስ ከደረጃው እጅግ ዝቅ ብሎ እንደሌሎቹ ጳጳሳት ሊሸፈን ያልቻለ የአንድን ጳጳስ ገመና ለመደበቅ ሲል ሃይማኖታዊ ያልሆነና ከግለሰብ መብት ጋር የተያያዘ ጉዳይን የሃይማኖት ጉዳይ አስመስሎ ሥልጣኑን አለአግባብ በመጠቀም የግለሰብ መብትን በመጋፋት ስራው መቀጠሉ ተሰማ፡፡ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልጅነትን ማረጋገጥ ሰብአዊ መብት እንጂ የሀይማኖት ጉዳይ አይደለም በማለት የአቡነ ሚካኤል አስከሬን ተቆፍሮ እንዲወጣ እና የዲኤን ኤ ምርመራ እንዲደረግ ይህ የማይደረግ ከሆነ ደግሞ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተፈጻሚ ይሁን ብሎ የወሰነው ውሳኔ ተፈጻሚ እንዳይሆን ሲል ሲኖዶስ ባቋራጭ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ሌላ አቤቱታ አቀርቧል፡፡ አቤቱታው ለከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዳቀረበው አይነት «ጉዳዩ የሀይማኖት ጉዳይ ነውና ፍርድ ቤት ሊመለከተው አይገባም» የሚል ነው፡፡
ይህን የአቤቱታ ሂደት ሲከታተሉ የነበሩት የጉዳዩ ዋና ተዋናይ እና የአቡነ ሚካኤልን ሀብት ለመውረስ ሲሉ የቤተክርስቲያኒቱን ገመና አደባባይ እንዲወጣ ያደረጉት አባ ሳሙኤል መሆናቸው ታውቋል፡፡ አባ ሳሙኤል ለህዳር 25 የተቀጠረው ጉዳይ ሌላ አቅጣጫ እንዲይዝ በማድረግ ኢየሩሳሌም ሆነው ጉዳዩን በስልክ ሲከታተሉና ሲመሩ እንደነበር ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡
የሲኖዶሱ አቤቱታ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንዲገባ ከማነሳሳት ጀምሮ አቤቱታው ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እንዲቀርብ በሲኖዶሱ ሲወሰን ሹፌራቸው በልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ መምሪያ መኪና ግብር አበሮች የሆኑ የቤተክህነት ሰዎችን እና ጠበቆችን እንዲያመላልስ አዘውት እንደነበር ታውቋል፡፡ ባለፈው ኅዳር 18 ማክሰኞ ዕለት ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሄደውም አቤቱታውን አስገብተዋል፡፡ አቤቱታውን በተመለከተም የከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀጠሮ በነበረበት ህዳር 25 ቀን ሁለቱም ወገኖች እንዲቀርቡ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የወሰነ ሲሆን፣ ለህዳር 25ቱ ቀጠሮ የአቡነ ሚካኤል ልጅ እንዲቀርብ እንዲደረግ የተሰጣቸውን መጥሪያ ለዮሐንስ ሳይሰጡት ይልቁንም በሀሰት ቃለ መሀላ አላገኘነውም በማለት መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እጃቸውን ጭነው በመማል የቀረቡ ቢሆንም፣ ልጁ ግን ቤተክህነት አካባቢ ባሉት እውነት እንድትወጣ በሚፈልጉ ሰዎች አማካይነት በድብቅ እየሆነ ያለው ነገር ስለተነገረው በዕለቱ ሊቀርብ ችሏል፡፡
በዕለቱ የልጁን መቅረብ ያልጠበቁት በመሆኑ በዚያ የተገኙት የአባ ሳሙኤል ጋሻ ጃግሬዎች እጅግ ሲደናገጡ ተስተውለዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የሁለቱንም ወገን ክርክር ከሰማ በኋላም ጉዳዩ የሃይማኖት ጉዳይ ነው አይደለም የሚለውን ውሳኔ ለመወሰን ለጥር 2/2005 ሌላ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
የአቡነ ሚካኤል ልጅ ዮሐንስ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ በህግ ትምህርት በ2003 የተመረቀ ሲሆን፣ ከልጅነቱ ጀምሮ የአቡነ ሚካኤል የልብ ወዳጅና መሰላቸው የሆኑት አባ ሳሙኤል በደንብ የሚያውቁት መሆኑን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ አቡነ ሚካኤል ሲያርፉ ግን ሀብታቸውን በአደራ የተቀበሉት አባ ሳሙኤል ምስጢሩን የሚያውቁ ሰዎችን እየጠሩ «ይህንን ምስጢር ብታወጡ ለሕይወታችሁ በጣም ያሰጋችኋል» በማለት ይህንንና ሌላውንም ምስጢር እንዳያወጡ ለማስፈራራት ይሞክሩ እንደነበር ምንጮቻችን አክለው ያስረዳሉ፡፡ አንደኛው ጥብቅ ምስጢር እንዲሆን የተፈለገው የአባ ሚካኤል ሚስት ሌላ ልጅ እንዳይወልዱ በአባ ሳሙኤል ገንዘብ አቀባይነት ውርጃ እንዲፈጽሙ ማድረጋቸው ነው፡፡ አንዳንዶቹ ግን ለእውነት እንጂ ለእርስዎ ማስፈራሪያ አንኖርም በማለት ለሚጠይቃቸው ህጋዊ አካል የሚያውቁትን ምስጢር እንደሚናገሩ ገልጠውላቸዋል ተብሏል፡፡ አባ ሳሙኤል ከምስጢር አዋቂዎቹ አልፈው የአቡነ ሚካኤልን ልጅ ዮሐንስንም ጠርተው ለማስፈራራት ሞክረው ነበር ተብሏል፡፡ ዮሐንስ ግን ባለው የሕግ እውቀት እና የመንፈስ ጥንካሬ ሁሉን እያወቁ የካዱት የአባ ሳሙኤል ማስፈራሪያ ሳያንበረክከው መብቱን ለማስከበር መፈናፈኛ ስላሳጣቸው፣ «ጳጳስ አይወልድም» በማለት ሲከራከሩ ቆዩ፡፡ እንዴት «ጳጳስ አይወልድም» ይባላል? ይህ ሊሰራ የሚችለው እኮ እንደታማኞቹ ጳጳሳት አንድ ጳጳስ በድንግልና ለመኖር የገባውን ቃል ጠብቆ ወደ ሴት ካልሄደ ነው፤ ወደ ሴት ከሄደ ግን መውለዱ የማይቀር ነገር ነው፡፡ አባ ሳሙኤል ይህን እንኳን ማገናዘብ የማይችሉ ሰው መሆናቸው ትልቅ ትዝብት ላይ ጥሏቸዋል፡፡
እኚህ ጉደኛ ሰው አሁን ደግሞ በእውነት ማሸነፍ ሲያቅታቸው የማታ ማታ «ጉዳዩ የሃይማኖት ነው» የሚለውን ማምለጫቸውን እሳቸውና መሰሎቻቸው በመንፈስ ቅዱስ ስም እያመካኙ ያሻቸውን ውሳኔ በግብታዊነት እየወሰኑ በአንባገነንነት የሚያዙበትን ሲኖዶስ መሳሪያ አድርገው ይዘው ብቅ ብለዋል፡፡ አባ ሳሙኤል «ጳጳስ አይወልድም» የሚለው መከራከሪያቸው ውሃ የማይቋጥር መሆኑን ዘግይተውም ቢሆን ሲረዱ እንደለመዱት የመብትን ጉዳይ የሃይማኖት ጉዳይ ነው ማለታቸው የሰውዬውን ጭካኔ የሚያሳይ ሆኗል፡፡ ቀደም ብለውም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅና ጳጳስ እያሉ ለሚያደርሱት የአስተዳደር በደልና ግፍ ሲከሰሱ የክሱን ፋይል የሚያስዘጉትና አልዘጋ ሲልም በማንአለብኝነት ጆሮ ዳባ የሚሉት የሐይማኖት ጉዳይ ነው እያሉ መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ሲሆን ሁልጊዜ ግን የሚያዋጣና ትክክለኛ ነው ማለት አይደለም፡፡ የልጅ መውለድ እና የአለመውለድ ጉዳይ በሕግ ፊት የፍትሐብሔር ጉዳይ ነው፡፡ ነገሩን ሐይማኖት የሚደርገው ምንም ምክንያት የለም፡፡ አባ ሚካኤል ልጅነቱን ተቀብለው ልጄ ብለው አሳድገውት እያለ አባ ሳሙኤል ለገንዘብና የእርሳቸውና የሌሎቹም ተመሳሳይ «ኬዝ» እንዳይቀሰቀስ ብለው እንዲህ መንቀዥቀዣቸው የሚያስተዛዝብ እና ቤተክርስቲኒቱንም የሚያሳፍር ተግባር ሆኗል፡፡ ጉዳዩ ወደ ሕግ ክርክር ሳይሄድ መፍታት እየተቻለ አባ ሳሙኤል ግን በድርቅና ወደ ሕግ ከገፉትና  ሂደቱ ጫፍ ላይ ሲደርስ ጉዳዩ የሐይማኖት ነው ማለታቸው አሰፋሪ ነው፡፡
የአቡነ ሚካኤል ልጅ የሚገባውን የአባቱን ንብረት ማግኘት አለበት፤ ሕግም ይደግፈዋል፡፡ የሲኖዶሱም ህገ ደንብ ጳጳስ ለቅርብ ዘመዶቹ ሐብቱን እንዲያወርስ ፈቅዷል፡፡ በ1991 ዓ.ም የወጣውንና ጳጳሳት ለቤተሰቦቻቸው ሀብታቸውን እንዲያወርሱ የሚደነግገውን ህግ እንዲጸድቅ ያደረጉት ቤተሰብ ያላቸው ጳጳሳት መሆናቸው ሲታወቅ፣ አቡነ ጳውሎስ በሕይወት እያሉ ይህ ሕግ ይሻሻል ቢሉም የሀሳቡ ዋና ተቃዋሚ ባለትዳሩ ጳጳስ አባ ሳሙኤል ነበሩ፡፡ አሁን ደግሞ አይሻርም ያሉትና የተከራከሩለት ሕግ ተፈጻሚ ይሁንና የአባ ሚካኤል ልጅ ዮሐንስ ከአባቱ ሀብት የሚደርሰውን ይውረስ ሲባሉ ዋና ተቃዋሚ ሆነው ቀርበዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ የአባ ሳሙኤል ጠበቆች እና የእነ አባ ሳሙኤል ቡድን በሀሳብ መለያያታቸው እየሰፋ መጥቶ ወደ ጠብ እያመሩ መሆኑ ታውቋል፡፡ ጠበቆቹ ባላቸው የህግ እውቀት መሰረት የአቡነ ሚካኤል ልጅ የሚከራከርበትን ሐብት እና ንብረት ላይወርስ የሚችለው የዲኤንኤ ምርመራው ልጅ አለመሆኑን ካረጋገጠ ብቻ መሆኑን ስለሚያውቁ የዲኤንኤ ምርመራው አንዲካሄድ ይፈልጋሉ፡፡ የዲኤንኤ ምርመራው ከተካሄደ ውጤቱ ምን እንደሆነ የሚያውቁት እነ አባ ሳሙኤል አሁን ያላቸው ተቃውሞ አስከሬኑ ተቆፍሮ አይወጣም ዲ ኤን ኤ ምርመራም አይካሄድም የሚል ነው፡፡ ይህን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ቢቀበል እንኳ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ተፈጻሚ አድርጎ ነው፡፡ ስለዚህ አስከሬኑ አይውጣ ካላችሁ ልጅነቱን አምናችኋል ማለት ነውና ገንዘባችንን ስጡን የሚል ጥያቄ ጠበቆቹ መጠየቅ መጀመራቸው እና በዚህም ምክንያት አለመግባባቱ ስር እየሰደደ መሄዱ ተሰምቷል፡፡    

8 comments:

 1. Egzioo mind new minesemaw wegennn ere gudddd Aba samuael endezhi dereja lay dersewal?

  ReplyDelete
 2. የሪፖርቱ ድክመቶች
  1. አባ ሳሙኤል ለህዳር 25 የተቀጠረው ጉዳይ ሌላ አቅጣጫ እንዲይዝ በማድረግ ኢየሩሳሌም ሆነው ጉዳዩን በስልክ ሲከታተሉና ሲመሩ እንደነበር ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡
  ስልክ ተቀባዩ ማን ነበር ? ምንጮቻችሁ ወይስ አባ ሳሙኤል ፡፡ ምንስ እንደሚነጋገሩ በምን ተረዳችሁ ?
  2. የአቡነ ሚካኤል ልጅ የሚገባውን የአባቱን ንብረት ማግኘት አለበት፤ ሕግም ይደግፈዋል፡፡
  የልጅነት እውቅና ከፍርድ በፊት በምን አረጋግጣችኋል ወይስ በይሆናል ደመደማችሁ ?

  በዜናችሁ እንዲህ ሊሆን የሚችለውን ከማይችለው ስትቀላቅሉት ጽሁፋችሁን ፍሬ ያሳጣዋልና አርሙት ፡፡
  ReplyDelete
  Replies
  1. Ylejune Lejente eko ferde bête aregagetetotl. kerekeru eko yeketelew yeferede betu wesane endesare beyegebege new.

   Delete
  2. ፍርድ ቤት የማያወላዳና የመጨረሻ ውሳኔ ቢሰጥማ የዲኤንኤ ምርመራ አይታዘዝም ነበር ፡፡ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በአይተሽና ሰምተሽ የሰጠው ፍርድ ትክክልና ሃቅ መሆኑ የሚረጋገጠው ከዚህ ውጤት በኋላ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ፍርዱን ሲያጸናው ነው ፡፡ ይግባኝ እስከ ተባለና ፍርድ ቤቱ የይግባኝ መብትን እስከ አከበረ ድረስ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ብይን ሊጸና አይችልም ፡፡ ልጅም ያለ አባት እንዳልተወለደ ብናውቅም ፣ ከመጨረሻ ፍርድ በፊት የሟች ልጅ ነው ማለትና መደምደም ትክክል አይደለም ፡፡ ስለዚህም ለአንባቢ የተወሰነና የተደመደመ አስመስሎ ማቅረቡ ስህተት ይሆናል ፡፡

   Delete
 3. Min nekachihu Papas mehon Yalebet Yewelede new Mewledin Yekelekelew manew ?Misiit Yalew Weldo Yasadege Papas mehon yichilal Ahun Degimo Berkatawochu Weldew Yemiyasadigu Nachew America Yalutis papasat Semonun Selam ketefetsere tisemalachihu

  ReplyDelete
 4. አባ ሳሙኤሉ የሲኖዶሱ ተወካይ ወይም ምስለ አበሎ
  የሆናበትን ደብዳቤ ለፍርድ ቤቱ አቅርብ የሚል ምነው ጠፋ
  ጉዳዩ በዮሐንስና በአባ ሚካኤል ስለሆነ አባ ሳሙኤሉ ምን አገባው
  እንደነዚህ ያሉ እንኩዋን የቤተ ክርስቲያን መሪነት ሳይሆን
  ክርስቲያን ለመባል የሚያበቃ ምንም የላቸውም

  ReplyDelete
 5. አባ ሳሙኤል ላይ እንዲህ ማነጣጠራችሁ ለምንድን ነዉ? ለጥፋት ተልእኮአችሁ ስላልተመቿቹህ ነዉ? በተደጋጋሚ ማኅበረ ቅዱሳንንና እኒህን አባት ስትወጉአቸዉ አያለሁ፡፡ በዚህ ድርጊታችሁ ከህዝብ ልብ እንዲወጡ ለማድረግ ነዉ አይደል? አትድከሙ እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ያደርጋቸዋል፤ እናንተም ክፉ ወሬአችሁን ታቅፋችሁ ትቀራላችሁ፡፡

  ReplyDelete
 6. WYE sami mitune kolege gibe eyasegeba betemari fit Yemikelew jegena

  ReplyDelete