Tuesday, December 11, 2012

በዳላስ ቴክሳስ ለሦስተኛ ጊዜ የተካሄደው የሁለቱ ሲኖዶሶች የሰላምና አንድነት ጉባኤ የጋራ መግለጫ

Read in PDF

ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የጉባኤው ዋና አጀንዳ፦ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ ቅድስት አገራቸው ኢትዮጵያ ስለሚመለሱበት ጉዳይ

በመግለጫው መሰረት ቅዱስነታቸው ወደ አገራቸው ይመለሱ በሚለው ከሁለቱም ወገን በመጡ ልዑካን ዘንድ ተቀባይነት አገኝቷል።  ቅዱስነታቸው እንዴት ወይም በምን ሁኔታ ይመለሱ በሚለው ነጥብ ላይ ግን ስምምነት አልነበረም።

የኢትዮጵያ ልኡካን አቋም፦ ቅዱስነታቸው መሰረታዊ ፍላጎታቸው ተሟልቶላቸው፣ ክብራቸውና ደረጃቸው ተጠብቆ በመረጡት ቦታ ይኑሩ የሚል ነው።

የሰሜን አሜሪካ ልኡካን አቋም፦ ቅዱስነታቸው ከነሙሉ ሥልጣናቸው ወደ መንበራቸው ሊመለሱ ይገባል የሚል ነው።

በነዚህ ሁለት የተለያዩ አቋሞች ላይ ስምምነት ስላልተደረሰ አራተኛ ጉባኤ በሚመጣው ጥር 16-18 2005 / (January 24-26,2013) በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ እንዲካሄድ ወስነዋል።  እስከ  አራተኛው  ጉባኤ ድረስ  ልኡካኑ የየራሳቸውን ሲኖዶስ አባላት (ምልዓተ ጉባኤ)  ሲያግባቡና ሲያሳምኑ ይቆያሉ። 

የሁላችንም ጉጉት የአንድነቱ ድርድር ጫፍ ላይ እንዲደርስ ነበር፤ ሆኖም ግን የአራተኛውም ጉባኤም ቅርብ ስለሆነ በትዕግስት እንጠብቃለን። የቤተ ክርስቲያን አንድነት የመላው ኦርቶዶክሳዊ ጥያቄ መሆኑን ተረድተው አባቶች አንድነትን ያመጣሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን።
 

6 comments:

 1. እግዚአብሔር ለዚህች ቀን ስላደረሰን የተመሰገነ ይሁን ፡፡ ከጨለማ የተሻለ የተስፋ ብርሃን የሚሰጥን ምልክት አሳይቶናልና፡፡

  ልረዳቸው ያልቻልኳቸውን ሁለት ጥያቄዎችና በተረዳሁት መሠረት መፍትሄ የመሰለኝን ሃሳብም እጠቁማለሁ ፡፡

  1. “ቅዱስነታቸው ወደ አገራቸው ይመለሱ የሚለው መሠረታዊ ሐሳብ በሁላችንም በኩል ተቀባይነትንና ስምምነትን አግኝቷል ፡፡” የሚለው መግለጫ ስለ ቪዛ (ከአገር የመውጣትና የመግባት መብት) ነገር የሚናገር መስሎኛልና ፤ ያ ማለት ደግሞ መንግሥትን የሚመለከት ጉዳይ ነው ፡፡ ይኸን በተመለከተ የቤተ ክርስቲያን አስተዋጽኦና ተጽእኖ ምን ቢሆን እንዲመለሱ ተስማምተናል ለማለት ቻሉ ?

  2. “ቅዱስነታቸው መሠረታዊ ፍላጎታቸው ተሟልቶላቸው ፣ ክብራቸውና ደረጃቸው ተጠብቆ በመረጡት ቦታ ይኑሩ” ፤ እዚህ ላይ መሠረታዊ ፍላጎታቸው የተባለው ምግብና ውሃ ፣ መጠለያ ፣ ልብስ ፣ ግፋ ቢል ደግሞ መጓጓዣና አንዳንድ ወጭ መሸፈኛ ማለት እንደሆነ እገምታለሁ ፤ ሙሉ ክብራቸው ደግሞ የተነጠቁት የፓትርያርክነት ሥልጣን መሆኑን ለማንኛችንም ግልጽ ነው ፤ በፈለጉት ቦታ ሲባልም በኢትዮጵያ አለያም በአሜሪካ ወይም በ... ማለት ስለሆነ ስለምን ምክንያት “ከነሙሉ ሥልጣናቸው ወደ መንበራቸው ሊመለሱ ይገባል” ከሚለው የአቋም መግለጫ ጋር አልስማማ ብሎ እንደ አንድ ልዩነት ተቆጠረልን ?

  ከመግለጫው በሰፈረው የስምምነት ቃል መሠረት ፣ እንደተረዳሁት ሁለቱም ወገኖች ለአቡነ መርቆርዮስ ሙሉ ክብራቸው እንዲመለስላቸው ስለተስማሙ ፣ የኢትዮጵያ ፓትርያርክነታቸውን ማደስና መቀበላቸው ማለት ስለሚሆን ወደ ሥልጣናቸው እንዲመለሱ መሥራት ፤ ለወከላቸውም አካልና አባላት መግለጫቸውን እያቀረቡ ማወያየት ያስፈልጋል ፡፡ ለተግባራዊነቱ ምናልባት የመንግሥት ተጽእኖ ዛሬም የሚያሰጋ ሆኖ ቢገኝ ፣ ዘመኑ ባመጣው ቴክኖሎጂ ቡራኬና ሌላም አስፈላጊ መልእክቶችን ካሉበት እያስተላለፉ ፤ በወኪል (በአቃቤ ፓትርያርክ) በመታገዝ የቤተ ክርስቲያኗን ተገልጋዮች አንድ አድርገው በመምራት ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ ይችላሉ ፡፡ ቀና ልብና ፍቅር ካለን የማይታሰበው ይሞከራል ፤ የማይቻለውም ይፈጸማል ፡፡

  ለዚህች ለአጭር ዘመናችን ለዘለዓለም እንደ ሐውልት የሚቆምን ድክመት ለትውልድ እንዳናስተላልፍ አሁንም እግዚአብሔር ይርዳን !!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ። ጥሩ እይታ ነው። ሁሉም እንዳንተ/ች ቢያስተውል የት በደረስን።

   Delete
 2. I do hope that we all desire to face the truth. If so, the following are the main results of the EOTC reconciliation meeting in Dallas during Dec. 4-8, 2012:

  (a) It has failed completely as it did not result in the achievement of both fundamental objectives, namely:
  (i) The lifting of the mutual "wugzet";
  (ii)The prevalence of peace and unity.
  (b) It was astonishing to note that the fathers were pretending to accept the principles of peace and partaking jointly in dining and the holy communion whereas, in accordance with church doctrine, they should have, first of all, resolved the formal wugzet on each other and Miimenan + Kahnat in general.
  (c) In conclusion, it's obvious that after meeting three times, the current church leaders are continuing with their unholy design to sow and strengthen division within EOTC.
  (d) It's time that Miimenan stop expecting much from them and think of taking an effective action themselves.

  ReplyDelete
 3. this is a good report from Aba Selama. Ebakachihu endezih zegibu. Yerasachihun hasab bicha atanafsu!

  ReplyDelete
 4. what is gone happen all this kesoch (mendelakke yelemedu) hezbun leulet lesoste yekefelu

  ReplyDelete
 5. እግዚአብሔር በኣንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውልም፥፥ ጎበዝ እናስተውል፥፥


  አቡነ መርቀርዮስ ሁሉንም ነገር ለእግዚኣብሔር ሰጥተዋል፥፥ እግዚኣብሔርም ሰማ

  ከእርሳቸው ስደት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ሚና ያላቸው ግለሰቦች ወይንም አካላት

  ክንፈ ሞተ
  ታምራት ታሰረ
  አዲስ አበባ ሲኖዶስ ጳጳሳት ተከፋፈሉ አስከ መደብደብ ተደረሰ
  ለእርቅ ዲሲ መጥቶ ... ሲመለስ ቦሌ ላይ አረፈ
  አቡነ ጳውሎስ ኣረፉ
  መለስ ሞተ

  ቤተ ክርስቲያኒቱ ያሳለፈችውን አመታት እናስተውል፥

  ዊኪ ሊክ አጋለጠ
  በፕሬዘዳንቱ አንደበት እውነቱ ተገለጠ

  ይህ ሁሉ አጋጣሚ ወይንስ የአምላክ ድምጽ?

  በቀጣዩስ አቡነ መርቆርዮስ ምን ያዩ ይሆን። ክእርሳቸው ብዙ ተማርኩ
  ፋአኦ

  ReplyDelete