Thursday, December 13, 2012

በጥቂት ግለሰቦች አምባገነንነት ቤተ ክህነት ከኢየሩሳሌም ድርጅትና ከሌሎች አስጎብኚ ድርጅቶች ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ መግባቱ ተሰማ

ማኅበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያኗ ከቱሪስት መስህቦቿ ተጠቃሚ እንዳትሆንና እርሱ ተጠቃሚ የሚሆንበትን  ስራ እየሰራ ነው
ቤተ ክህነቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን ፓትርያርክ ተክቶ ቤተክርስቲያኗን የሚመራውን አባት ለማስቀመጥ ከፊት ትልቅ የቤት ስራ ተደቅኖበት ባለበትና በጳጳሳት መካከል ውዝግቡ ባየለበት በዚህ ወቅት፣ የቤተክርስቲያኗን ገንዘብና ሀብት በማባከን ሥራ የተጠመዱ አንዳንድ ጥቅመኞች የግል ቢዝነሳቸውን በቤተክርስቲያኗ ሀብትና ንብረት ላይ እየሰሩ ሀብት ለማጋበስ እየተሯሯጡ ይገኛል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ከገዳማት መምሪያ የተነሳውና የውጪ ግንኙነት መምሪያ ሀላፊ ሆኖ ቢመደብም የመምሪያው ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ አልቀበልም ብለውት ተንሳፎ የሚገኘው ሰለሞን ቶልቻ ሲሆን ቤተክህነት ከኢየሩሳሌም ድርጅትና ከሌሎችም አስጎብኚ ድርጅቶች ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ እንዲገባ ምክንያቱ ሰለሞን ተቀባይነት ባላገኘውና በሌለው ስልጣን የውጭ ግንኙነት መምሪያ ስራ አስኪያጅ ነኝ በሚል ለሪፖርተር ጋዜጣ የሰጠው መግለጫ ነው ተብሏል፡፡
ሰለሞን ቶልቻ ቤተ ክህነት የቱሪዝም ተቋም ልትመሰርት ነው በሚል መግለጫ የሰጠው ቀደም ሲል የቱሪዝምና የቅርስ አገልግሎት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በቅዱስ ሲኖዶስ መወሰኑን መነሻ በማድረግ ነው፡፡ በዚህ አቅጣጫ ብዙ ሊሰሩ የሚገባቸው ስራዎች እያሉ ያን ወደጎን በመተው፣ ግለሰቡ አስጎብኚ ለመሆን የነበረውን ህልም በአጋጣሚው ለማሳከት በዚህ አቅጣጫ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ታውቋል፡፡ በዚህም ምክንያት ረጅም እድሜ ያስቆጠረውንና አንጋፋውን የኢየሩሳሌም ድርጅትና ሌሎችንም ፈቃድ አውጥተው እየሰሩ የሚገኙትን አስጎብኚ ድርጅቶች ከጫወታ ውጪ ለማድረግ አልሞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ሲታወቅ፣ የገዳማት መመሪያ በነበረበት ጊዜ ገዳማትን ለዚህ አላማ የሚውሉበትን ስራ መስራት ሲገባው አንድም የሰራው ስራ የለም ተብሏል፡፡ በገዳማት መምሪያ የሰራው ስራ ባለመኖሩም መነሻነት የገዳማት መመሪያ ሃላፊ መሆን ያለበት መነኩሴ ነው በሚል በሲኖዶስ ውሳኔ ሰለሞን ከመምሪያ ሃላፊነቱ መነሳቱ ይታወሳል፡፡
ቤተክርስቲያኗ በሚገባ ልትጠቀምበት የሚገባ ብዙ የቱሪስት መስህብ የሆኑ ታሪካዊ ቦታዎች በአገር ውስጥ ያሏት ሲሆን፣ በኢየሩሳሌምም ይዞታዎች እንዷላት ይታወቃል፡፡ እነዚህን የገቢ ምንጭ ሊሆኗት የሚችሉ ቦታዎችንና ቅርሶችን በአግባቡ ለመጠበቅና ከገቢው ተጠቃሚ ለመሆን መጀመር ያለበት አስጎብኚ ድርጅት መክፈትና ወደ ኢየሩሳሌም የሚደረጉ 2 አመታዊ ጉዞዎችን ማዘጋጀት ነወይ የሚለው ለብዙዎች አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ ይህ ለግል ጥቅም ከመቆም እንጂ ለቤተ ክርስቲያኗ ከማሰብ አለመሆኑን ብዙዎች እየተናገሩ ነው፡፡ መግለጫውን ተከትሎ የኢየሩሳሌም ድርጅት ሀላፊዎች መግለጫውን ከጋዜጣው ላይ ኮፒ በማድረግ ለአቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ለአቡነ ናትነኤልና ለሌሎቹም ሊቃነ ጳጳሳት በማቅረብ ተቃውሟቸውን ያሰሙ ሲሆን፣ አቡነ ናትናኤልም ሌሎቹም ጳጳሳት ስለተባለው ነገር ምንም የሚያውቁትና በሲኖዶስም የተወሰነ ነገር አለመኖሩን በመግለጽ የተሰጠው መግለጫ የግለሰቦች እንጂ የቤተክርስቲያኗ አቋም አለመሆኑን አስረድተዋቸዋል ተብሏል፡፡
ሰለሞን ቶልቻ ቀደም ብሎ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር የሆኑትን ክብርት ወ/ሮ በላይነሽን አታልሎ ለቤተክርስቲያን ጉዳይ ነው በሚል ለስብሰባ ቀጠሮ በማስያዝ አባ ፊልጶስንና አባ ህዝቅኤልን ይዞ በመሄድ ስለዚሁ ጉዳይ ያነጋገረ ሲሆን፣ በታሪክ ሆኖ የማያውቅ ለተራ ፓስፖርት ወደውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አባ ፊልጶስ እንዲጽፉ በማድረግ በውጭ ጉዳይ በኩል ቪዛ እንዲሰጥ አስደርጓል ይላሉ ምንጮች፡፡ በውጭ ጉዳይ በኩል ቪዛ ለዲፕሎማቶችና ልዩ ፓስፖርት ለሚይዙ እንጂ ለተራ ሰው የማይሰጥ መሆኑ ሲታወቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቪዛውን ለነሰለሞን እንዴት እንደፈቀደላቸው ለብዙዎች ጥያቄ ሆኗል፡፡ «አምባሳደሯን ወ/ሮ በላይነሽን ይዣለሁ ቪዛ አስመታላችኋለሁ» በማለትም በኢየሩሳሌም ድርጅትና በሌሎችም የጉዞ ወኪሎች ሰዎች እንዳይሄዱ በመቀስቀስ ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡
መግለጫውን ተከትሎ አባ ህዝቅኤል፣ ተስፋዬ ውብሸት፣ እስክንድርና ሰለሞን ቶልቻ ያለሲኖዶሱ እውቅና 39 ሺህ ብር ከቤተክህነት ካዝና በተስፋዬ ትእዛዝ ወጪ በማድረግ ወደ ኢየሩሳሌም ህዳር ወር መጨረሻ ላይ ሄደው ነበር፡፡ ተስፋዬ በምክትል ስራ አስኪያጅነቱ ወጪ ሊያደርግ የሚችለው እስከ 2 ሺ ብር ብቻ ሲሆን በማን አለብኝነትና ስራ አስኪያጁ አባ ፊልጶስ ስለሆኑ ገንዘቡን ወጪ አድርጎ ሄደዋል፡፡ አብረዋቸው የተጓዙት አባ ህዝቅኤል ሰዎች ስፖንሰር ሆነው እንደሚሄዱ የተነገራቸው ሲሆን ከተመለሱ በኋላ ግን እንዲፈርሙ ሲነገራቸው ተቃውመዋል ተብሏል፡፡ «በቤተክርስቲያን ገንዘብ መሆኑን መቼ ነገራችሁኝ፤ እንዲያ ቢሆንማ አልሄድም ነበር፤ ሰው ሸፍኖልን ነው ብላችሁ አይደለም ወይ የሄድነው» በሚል አልፈርምም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
በአሁኑ ጊዜ ስርአት አልበኝነት በሰፈነበትና ማህበረ ቅዱሳንና ጥቂቶች እንዳሻቸው እየሆኑ ባለበት ቤተክህነት ውስጥ በዚህ ረገድ ምክትል ስራ አስኪያጁ ተስፋዬ ውብሸትና ተንሳፎ የሚገኘው ሰለሞን ቶልቻ አቻ አልተገኘላቸውም ሲሉ ምንጮች ይናገራሉ፡፡
ሰለሞን ቶልቻ ከቅድስት ስላሴ በዲፕሎማ የተመረቀ ሲሆን በመጀመሪያ በኮተቤ ኪዳነምህረት፣ ከዚያም በቅድስት ሥላሴ ተመድቦ የነበረ መሆኑ ሲታወቅ፣ ከዚያም የአንድ በድምጽ ማጉያ አዟሪነት የተመደበ ቄስ ሚስት አስኮብልሎ እንደጠፋና ቄሱ ከሶ ሶስት ወር እንዳሳሰረው ጉዳዩን የሚያውቁ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ ማፍያዎችን መሰብሰብ ስራቸው የነበረው የዚያን ጊዜው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ አባ ተከስተ (የአሁኑ አባ ሳሙኤል) የቄስ ሚስት ቀምቶ ስሙ የጠፋውን ሰለሞንን ከሰባኪነት ወደቢሮ ስራ አዛውረው ወደሩፋኤል ቤተክርስቲያን ላኩት፡፡ በዚያም ሙዳየ ምጽዋት የሚያዞሩ ደጀ ጠኚዎችን ቋሚ ሰራተኛ አስድርጋችኋለሁ ብሎ ከመቶ አስር ከሚያገኟት አነስተኛ ገቢ ላይ እየተቀበለ ቋሚ ሳያስደርጋቸው ብዙዎችን በመበዝበዙ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተባሯል፡፡ ከዚያ ወደአስኮ ገብርኤል፣ ቀጥሎም ወደእንጦጦ አባ ተከስተ አዛውረውታል፡፡ በእንጦጦ ማርያምም በፈጸመው ጥፋት ቢሮው ታሽጎበት የተባረረ ሲሆን በግለሰቡ ላይ ሮሮ በመብዛቱ አቡነ ጳውሎስ በቅርበት ለመከታተል በሚል ወደመንበረ ፓትርያርክ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ሰባኪ አድርገው አዛውረውት ነበር፡፡ በዚያም ሳለ በርካታ የማጭበርበር ስራዎችን የሰራ መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ፡፡
ሰለሞን «ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም» የተባለውን የአማከለ ገበየሁን መጽሀፍ ሳያስፈቅድ በሀገር ውስጥ በማሳተም ተጠቃሚ የሆነ ሲሆን የመጽሀፉ ባለቤት ጉዳዩን በቅንነት ተመልክተው ምንም እርምጃ አልወሰዱበትም ተብሏል፡፡ ሰለሞን «ጂኤም ተራቭል ኤጀንት» በተባለ አስጎብኚ ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ የሰራ ሲሆን አሰሪው እምነት ጥሎበት ሳለ ብዙ ገንዘብ ዘርፎት መኪና መግዛቱና ሱሉልታ ላይ ቤት መስራቱ ታውቋል፡፡ ሰለሞን ወደኢየሩሳሌም ሄዶ እዛው ሊቀር ፈልጎ የነበረ ሲሆን የጉልበት ስራ ጀምሮ አልሆንልህ ሲለው ጥሎ ወደኢትዮጵያ እንደተመለሰ ምንጮች ተናግረዋል፡፡
ሰለሞን በአቡነ ፊልጶስ ፊርማ ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስራ ወደ ገዳማት መመሪያ ተዛውሮ በቆየባቸው ጊዜያት ማህበረ ቅዱሳንን ተጠግቶ  ጋር አብሮ መስራት የጀመረ ሲሆን፣ ከቤተክርስቲያን ይልቅ ለማህበሩ ጥቅም እንደቆመ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የዚህ አንዱ ማሳያም የጠቅላይ ቤተ ክህነት መምሪያ ሃላፊዎች ጉባኤ አርድእትን ለመመስረትና ለቤተክርስቲያን የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት ይበልጥ ለመወጣት እየተነጋገሩ ባለበት ጊዜ መረጃውን ሌላ መልክ በመስጠት ለማህበሩ ሸጦ ማህበሩን በመቀስቀስ የጉባኤ አርድእት እንቅስቃሴን ለማሰናከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሁኑ ጊዜ በቤተክርሲያኗ ቅርሶችና ታሪካዊ ቦታዎች በዋናነት ተጠቃሚ የሆነው ማህበረ ቅዱሳን በቱሪስት መስህቦቿ ዙሪያ ሲኖዶስ የወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ የራሱን ጥቅም ለማስከበር እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ከዚህ በፊት በቅርስ መመሪያው ሃላፊ በመምህር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል የቤተ ክርስቲያን ቅርሶችና ታሪካዊ ቦታዎች ለቤተክርስቲያን ጥቅም እንዲሰጡ ለማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ጥናት አቅርበው ጥናቱም ተቀባይነትን አግኝቶ ለአቡነ ጳውሎስ ቀርቦ የነበረ ሲሆን እርሳቸውም ጉዳዩን ወደ አባ ፊልጶስ ይመሩታል፡፡ አባ ፊልጶስ ግን ደብዳቤውን ያፍኑትና በዚያው ይቀራል፡፡ ደብዳቤው ወደእርሳቸው ከተመራና ከታፈነ በኋላ ወዲያው ማህበረ ቅዱሳን በቱሪዝም ዙሪያ ለመስራት በቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ህንጻ ውስጥ ተከታታይ ስልጠናዎችን ሲሰጥ ቆይቶ የቅርስና ገዳማት መምሪያ በስሩ አቋቁሟል፡፡ ያልታተሙ ጥንታዊ መጻህፍትን በማሳተምና በመሸጥ መጻህፍቱን ይዘው የተገኙ ገዳማት እንዳይጠቀሙ ማህበረ ቅዱሳን ጣልቃ እየገባ ተጠቃሚ መሆኑ ሲታወቅ፣ ለዚህም የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን ገድል በሌላው ድካም ገብቶ ባቋራጭ በማሳተሙና በመሸጡ ከቅርስ መምሪያው ሃላፊ ከመምህር ዳንኤልና ከገዳሙ ጋር ተጣልቷል ተብሏል፡፡ ማህበሩ የቤተክርስቲያኗን ቅርስና ታሪካዊ ቦታዎች በመጠቀም ለራሱ ገቢ ለማግኘት ቤተክርስቲያኗ ባቋቀዋመችው መምሪያ ስራ ጣልቃ እየገባ ሲሆን፣ መምሪያውን በመሳሪያነት ለመጠቀም በአሁኑ ጊዜ መምሪያውን በሚገባ ይዘው እየሰሩ የሚገኙትን መምህር ዳንኤልን አስነስቶ ተንሳፋፊ የሆነውን ሰለሞን ቶልቻን ለማስቀመጥ እየታገለ መሆኑ ታውቋል፡፡     


11 comments:

 1. Mk , which was recognized by his excellecey late pm melese zenawi as fundementalist organization in the horn very close to Alshebab. We eotc stand together to demolish mk for ever in the holy land of Ethiopia. The founder of mk that who have planted Eshock in our ancient church was Wolie aba Gorgorioes. He was died by car accident. Arm strugle is the only solution to cleaned this terrerist in church field. Now, it very simple to lememetat the target group. All eotc do some , if any thing worth to demolish mk from church land. Kewolo gorbet yeshalal bado bet. Do not trust wolie as father. Aba,Felipose and his collagues full time working as beater, cheater and fucker of Mk non educated fake deacon sadely Solomon kitu keba kidus eyekeba aba felipose yadregewal. Similarely, Dr. Mesfin victomized by aba abrham. So, we stand together to practice the legacy of pm melese to protect horn form terreist mk, alshebab, and others. Death to all mk elements. Fredom to our church. long live to Aba Markose that he broke dowen tert preaching in the table of eotc.

  ReplyDelete
 2. አምበርብር ከእንጦጦDecember 14, 2012 at 11:52 AM

  አባ ሰላማ ብሎግ የክፉዎችን ክፉ ስራ መግለጣችሁ ጥሩ ነውና በርቱ፡፡ በሰለሞን ዙሪያ ሁለት የማውቃቸውን መረጃዎች ላክልላችሁ ከዚህ ቀደም በአቡነ ጳውሎስ ዘመን ወደባሌ ሲጓዙ በአንድ ላይ በመኪና አደጋ ህይወታቸው ካለፈው ከአቡነ ዮሴፍ እና አቡነ ኤልያስ ኪስ ውስጥ ገንዘብ ሲፈትሽና ሲወስድ ታይቶ አይንህ ላፈር የተባለና ከዚህ የተነሣ ወደዚያ ደርሶ የማያውቅ አረመኔ ነው፡፡ ሁለተኛ ከእንጦጦ ማርያም ቤተክርስቲያን የተባረረው እርፈ መስቀል ሰርቆ ሲወጣ ከኪሱ ወድቆ እጅ ከፍንጅ ተይዞ ነው፡፡ ይህ መነገር ያለበት ታሪኩ ነው፡፡ ይህች ጉደኛ ቤተክርስቲያን እውተኞችን እየገፋች እንደሰለሞን ያሉትን ሌቦችና ዘራፊዎች አቅፋ መያዟ ይገርመኛል፡፡ እነሰለሞንን በሌብነታቸው እያበረታታ ያሳደገውና ለዚህ ቁምነገር ያበቃው የማፍያዎቹ አባት የያኔው አባ ተከስተ የዛሬው ጳጳስ ነኝ ባይ ሳሙኤል መሆኑ ከቶም ሊረሳ አይገባም፡፡

  ReplyDelete
 3. wow wow wow....የማቅ ድህረ ገጽ በሃይማኖት ስም ማወናበዱ አልሳካ ስለው ወደ ቀደመው ድብቅ የፓለትካ አላማው እየዞሩ ነው። እነሆ ደጄ ሰላም የማቅ ድህረ ገጽ ከእሳት ትቭ ጋር በድብቅ ፈጽመው የነበሩትን ጋብቻቸው ይፋ አደረጉ። የእሳት ቲቭ በግልጽ የፓለትካ ድርጅ መኖኑ እየታወቀ ማቅ ድህረ ገጽ ደጄ ስላም ላይ ተለጥፎ እየታየ ነው።ነገር ግን እግዚአብሔር እያጋለጠው ነው። ይህ ነው ማቅ ስውር አላማዉ። መንፈሳዊ አለመሆኑን በእግልጥ በአደባባይ እየታየ ነው። እግዚአብሔር ይመስገን ይህ ክፉ መንፈስ አላማው እራሱን ገሀድ አወጣ !!!! ከእነ በቀር ቅዱስ የለም የሚለው ዲያብሎስ እቅዱ ቤተ እግዚአብሔር መከፋፈል ስለሆነ ዛሬም የማያቀላፋ ክፉ መንፈስ የቀደመው ዲያብሎስ ነው።

  ReplyDelete
 4. ስለሰለሞን የጻፋችሁትን ሳነብ ሰለሞን ቶልቻ ከገዳማት መምሪያ ከተነሣ በኋላ ባለፈው ሮብ 3/4/2005 የገዳማት መምሪያ ሀላፊ ነኝ ብሎ ከአንድ ዶክተር በገዳማት ስም እርዳታ ጠይቋል፡፡ ዶክተሩ በመጀመሪያ ቃል የገቡለት ቢሆንም ዶክተሩን የሚያውቅ አንድ ሰው የሰውዬውን ማንነትና ከማህበሩ ጋር ያለውን የዝርፊያ መዋቅር በሚገባ ስላስረዳቸው ለሰለሞን ሊሰጡ የነበረውን ድጋፍ ሳይሰጡት ቀርተዋል፡፡ ሰለሞን በዚህ ተግባር ከማቅ ጋር አንድ መሆኑን አስመስክሯል፡፡ ማቅ ለገዳማት የማደርሰው እያለ በርካታ የድጋፍ ገንዘቦችን ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር እየተቀበለ ወደራሱ ካዝና እንደሚያስገባና በስማቸው የተለመነባቸው ገደማት ግን ምንም ነገር እንዳላገኙ የሚታይ እውነት ነው፡፡ ሰለሞንም በዚሁ መንገድ ከገዳማት መምሪያ ከተነሳ በኋላ የመምሪያው ሀላፊ ነኝ ብሎ እርዳታ በጎን መጠየቁ ሰውዬው ምን ያህል የጥቅም ሰው እንደሆነ ያሳያል፡፡ ሰው ካለ ሰውዬው አንድ ቢባል ጥሩ ነው፡፡

  ReplyDelete
 5. memehir solomonen bemegeba enawkachewalen yetesafew bemulu weshet new yeweyzero ejegayehu were new atidekemi manime ayekebelishem

  ReplyDelete
 6. Ebakachu betbetakristiyan sim atinagdu dagmo silegadamat makorkor jamarachu ebakachu siletanakabachu ezawu kamanafikan gar bitikalakalu yishalachuhal wanbede manafikan aba diyabilosoch

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስለ ገዳማት ሳይሆን በገዳማት ስም የሚሠራውን ግፍና የሚፈጸመውን ዝርፊያ ነው ነገር አታጣም፡፡

   Delete
 7. tultula hulu! MK legedamat men endesera kegedamatu teykachu teredu bado fishkachehun kemenfatachu befit. Chigeru ewnetun lalemayetem hone lalemesmat joroachehun defnachu chelema west mekemetachu new. Yebrhan amlak birhanun yabralachu!

  ReplyDelete
 8. Solomon Tolcha genzeb kaye mistun yakateral.

  ReplyDelete
 9. Azeb ke arat kilo

  Slemon esty and negeer letyeke,weyzero Ejigayehu gar betam wedage alneberkem? Abune paulos kemotu behale enka enena ante Ejigayehu bero altegenanenme end? lastaweshe lezehe yabekune abune paulos nachew eyalk setalkes enem neberku ayzoshe belehe edewelelshalehu endalkat erestehe new ahun semaun yemtatefaw betam tegermalehe lante selot yasfelgal!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 10. ሰለሞን ቶልቻ በፍቅረ ነዋይ የተለከፈ ሰው ነው ለገንዘብ ሲል ሚስቱን ከማቃጠር ወደኋላ አይልም ያኔ የኮሌጅ ተማሪ ሆኖ ደብረ ሊባኖስ አብረን ሄደን ነበር የሚያሳዝነው ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የገንዘብ ፍቅሩ ሀይለኛ ስለነበርና እጅግ ስላየለበት በገንዘቤ ተሳፍሬ ሄጄ ባዶ ኪሴን አልመለስም ብሎ ደብረ ሊባኖስ ላይ ኮቱን አውልቆ በማንጠፍ የኮሌጅ ተማሪ ነኝ ገንዘቤን ሌባ ሰረቀኝ ስለተክልዬ እርዱኝ ብሎ በመለመን ብር ሰብስቦ ተመልሷል የገንዘብ ነገር ከዛን ጊዜ ጀምሮ ያደገበት ስለሆነ ዛሬ እነዚህን ነገሮች አደረገ ብላችሁ ታሪኩን ስታወጡ ብዙም አልደነቀኝም ሰለሞን ከዚህ የከፋ እንጂ ያነሰ ነገር እንደማያደርግ ይታወቃል አሁን ደግሞ ከማቅ ጋር በፍቅር ውስጥ ስለሆነ የሚያደርገውን አያውቅም

  ReplyDelete