Monday, December 17, 2012

በክርስቶስ ላይ አታመንዝሩ

 እዚህ ስዕል ላይ በተጻፈው ጽሑፍ ኦርቶዶክሳውያን ይስማማሉ ብዬ አላምንም፡፡ ይህን ጽሁፍም በስእሉ ላይ የጻፉ ሰዎች ኦርቶዶክሳውያን ናቸው ማለት ይከብዳል፡፡ በጽሑፉ የሚስማሙ ካሉ ግን አመንዝራዎች ናቸው፡፡ በክርስቶስ ላይ ያመነዘሩ ስለሆኑም ክርስቲያንም ተብለው ሊጠሩ አይገባም፡፡ ስእሉ ከፌስ ቡክ ላይ የወረደ ነው፡፡
ማመንዘር ሚስትን/ባልን ትቶ የሌላውን ሚስት/ባል መመኘትና ዝሙት መፈጸም ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ ይህን ሳይሆን በእግዚአብሔር ላይ የሚፈጸመውን መንፈሳዊ ምንዝርና እዳስሳለሁ፡፡ በቅድሚያ ቃሉ ምን ይላል?

«ሌሎች አማልክትን ተከትለው አመነዘሩ ሰገዱላቸውም እንጂ መሳፍንቶቻቸውን አልሰሙም አባቶቻቸውም ይሄዱበት ከነበረ መንገድ ፈጥነው ፈቀቅ አሉ አባቶቻቸው ለእግዚአብሔር ትእዛዝ እንደ ታዘዙ እንዲሁ አላደረጉም።» መሳ. 2፡17
«እንዲህም ሆነ ጌዴዎን ከሞተ በኋላ የእስራኤል ልጆች ተመለሱ፥ በኣሊምንም ተከትለው አመነዘሩ በኣልብሪትንም አምላካቸው አደረጉ።» መሳ. 8፡33
«የአባቶቻቸውንም አምላክ በደሉ፥ እግዚአብሔርም ከፊታቸው ባጠፋቸው በምድሩ አሕዛብ አማልክት አመነዘሩ» 1ዜና. 5፡25
ጥቅሶቹ ባል በሚስቱ ሚስትም በባልዋ ላይ ሌላ ወደው እንደሚያመነዝሩ ሁሉ የእግዚአብሔር ህዝብም በእግዚአብሔር ላይ የአህዛብ አማልክትን ተከትለው ማመንዘራቸውን ያሳያሉ፡፡ መጽሐፉ እግዚአብሔርን መተውና ሌላውን መከተል አመንዝራነት መሆኑን ሲናገር እግዚአብሔር የሕዝቡ ባል ህዝቡ ደግሞ ሚስት መሆኑን ነው የሚያመለክተው «ከዳተኞች ልጆች ሆይ፥ እኔ ባላችሁ ነኝና ተመለሱ ይላል እግዚአብሔር አንዱንም ከአንዲት ከተማ ሁለቱንም ከአንድ ወገን እወስዳችኋለሁ፥ ወደ ጽዮንም አመጣችኋለሁ» ኤር. 3፡14፡፡ በብሉይ ኪዳን የእስራኤል ህዝብ እግዚአብሔርን ትተው ሌሎችን አማልክት የተከተሉበት ያ የአመንዝራነት ሕይወት በሐዲስ ኪዳንም እንዳይደገም ሐዋርያት በጽኑ አስጠንቅቀዋል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል «በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤ ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ።» 2ቆሮ. 11፡2-3፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ የቆሮንቶስን ሰዎች ዛሬም እኛን ምን እያለን ነው? አንዲት ክብሯን የጠበቀችና ወንድ ያልነካት ንጽሕት የሆነች ድንግል ሴት በትክክለኛ የጋብቻ ሕግ ለአንድ ወንድ እንደምትታጭ እኔም እናንተን ለአንድ ወንድ ለክርስቶስ አጭቻችኋለሁ እያለን ነው፡፡ ነገር ግን የክርስቶስ ብቻ እንዳትሆኑና ለእርሱ ያላችሁን ፍቅርና ለእርሱ የምትሰጡትን አምልኮት ውዳሴና ክብር አምላክ ላልሆኑ ለሌሎች እንድታጋሩ በተንኮል የሚሠራው ሰይጣን ሔዋንን ባሳተበት የተንኮል መንገድ እናንተንም እንዳያስትና በእርሱ ላይ አመንዝራ እንዳትሆኑ ብዬ እፈራለሁ ማለቱ ነው፡፡ እኛ የክርስቶስ እንጂ የሌሎች አይደለንም፡፡ ወደፊትም የእርሱ ብቻ እንጂ የሌሎች ልንሆን አይገባንም፡፡ እኛ፣ ማለትም ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ሙሽራ ወይም ሚስት ነን፡፡
«ዮሐንስ መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ ከሰማይ ካልተሰጠው ሰው እንዳች ሊቀበል አይችልም። እናንተ። እኔ ክርስቶስ አይደለሁም፥ ነገር ግን። ከእርሱ በፊት ተልኬአለሁ እንዳልሁ ራሳችሁ ትመሰክሩልኛላችሁ። ሙሽራይቱ ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚሰማው ሚዜው ግን በሙሽራው ድምጽ እጅግ ደስ ይለዋል። እንግዲህ ይህ ደስታዬ ተፈጸመ።» ዮሐ. 3፡27-29
«ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና። ዳሩ ግን ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ እንዲሁ ሚስቶች ደግሞ በሁሉ ለባሎቻቸው ይገዙ። ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤ እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ። እንዲሁም ባሎች ደግሞ እንደ ገዛ ሥጋቸው አድርገው የገዛ ሚስቶቻቸውን ሊወዱአቸው ይገባቸዋል። የገዛ ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል፤ ማንም የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ከቶ የለምና፥ ነገር ግን የአካሉ ብልቶች ስለሆንን፥ ክርስቶስ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን እንዳደረገላት፥ ይመግበዋል ይከባከበውማል። ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ» ኤፌ. 5፡23-32
«ሰባቱም ኋለኛዎች መቅሠፍቶች የሞሉባቸውን ሰባቱን ጽዋዎች ከያዙት ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ። ወደዚህ ና፥ የበጉንም ሚስት ሙሽራይቱን አሳይሃለሁ ብሎ ተናገረኝ።» ራእ. 21፡9
ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ሙሽራ ብቻ እንደሆነችና የሌላ ልትሆን እንደማትችል ጥቅሶቹ ያመለክታሉ፡፡ አንድ ነገር ግን ፈጽሞ መዘንጋት የለብንም፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ እባብ የተባለው ሰይጣን ሔዋንን ያሳታት በተንኮል እንደሆነ ሁሉ ዛሬም እኛን የሚያስተንና ለክርስቶስ ብቻ እንዳንሆንና ሌሎችን እንድንከተል የሚያደርገን በልዩ ዘዴና ስልት (በተንኮል) መሆኑን ነግሮናል፡፡ ስለዚህ ዛሬ እንደ እስራኤል ሕዝብ ሌሎች አማልክትን ነው የተከተልነው ብለን በግልጽ እንድናስብ አያደርግም፡፡ ድርጊታችን ሲታይ ግን በክርስቶስ ላይ ሌሎች ውሽሞችን እንደያዝንና በክርስቶስ ላይ እያመነዘርን እንደሆነ ያሳያል፡፡ ዛሬ ጣኦት ተብሎ የሚጠራ ጣኦት የለንም፡፡ ስሙ የጣኦት ያልሆነ ጣኦት ግን ሞልቶናል፡፡ ለምሳሌ ሥዕልን ጣኦት ብለን አንጠራውም ለሥእል ያለን አመለካከትና እየሰጠነው ያለው አምልኮትና ስግደት ግን ሥዕልን ጣኦት አድርጎብናል፡፡ ይህ ሰይጣን በተንኮሉ እኛን በማሳት ሥዕልን በስልት እንድናመለክው እያደረገ ከመሆኑ የተነሳ የሳትንበት መንገድ ነው፡፡ ይህን ስህተት ከማረምና ጣኦት የሆነብንን ሥእል ጣኦት ነው ከማለት ይልቅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ለማድረግ ሥዕልን ባልተጻፈለት ጥቅስ ለማስደገፍና መጽሀፍ ቅዱሳዊ ለማስመሰል እንሞክራለን፡፡ ስለሥዕል የተጻፈ ነው ብለን ከምንጠቅሳቸው መካከል «የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው?» ገላ. 3፡1 የሚለውን ነው፡፡ ቢቸግር ነው እንጂ ይህ ስለሥዕል እንደማይናገር እናውቃለን፡፡ የገላትያ ሰዎች ክርስቶስን ከመከተል ወደኋላ ስላፈገፈጉ ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ ቀለምነት እንደ ተሰቀለ ሆነ በአይነ ልቡናችሁ ተሥሎ ነበር፤ ስለምን ከእርሱ ወደኋላ ተመልሳችሁ የኦሪት ተከታይ ሆናችሁ? የሚል መልእክት አለው እንጂ ዛሬ እንደምናደርገው የስነ ስቅለቱ ሥዕል በግዙፍ ቀለም ተስሎ ነበር ማለት አይደለም፡፡ ሌሎች ከኦሪት የምንጠቅሳቸው መከራከሪያዎቻችንም ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ናቸው፡፡
ሥዕል በመጽሐፍ ቅዱስ የተከለከለ ልምምድ ነው፡፡ «እግዚአብሔር በኮሬብ በእሳት ውስጥ ሆኖ በተናገራችሁ ጊዜ መልክ ከቶ አላያችሁምና እጅግ ተጠንቀቁ እንዳትረክሱ፥ የተቀረጸውን ምስል የማናቸውንም ነገር ምሳሌ፥ በወንድ ወይም በሴት መልክ የተሠራውን፥ በምድር ላይ ያለውን የእንስሳን ሁሉ ምሳሌ፥ በሰማይም በታች የሚበርረውን የወፍን ሁሉ ምሳሌ፥ በምድርም ላይ የሚሽከረከረውን ሁሉ ምሳሌ፥ ከምድርም በታች በውኃ ውስጥ የሚኖረውን የዓሣን ሁሉ ምሳሌ እንዳታደርጉ፥ ዓይኖችህን ወደ ሰማይ አንሥተህ አምላክህ እግዚአብሔር ከሰማይ ሁሉ በታች ላሉት አሕዛብ ሁሉ የሰጣቸውን ፀሐይንና ጨረቃን ከዋክብትንና የሰማይን ሠራዊት ሁሉ ባየህ ጊዜ፥ ሰግደህላቸው አምልከሃቸውም እንዳትስት ተጠንቀቅ።» ዘዳ. 4፡15-19፡፡
እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት ሐሳባችን ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ቅድስና ሊለወጥ እንደሚችል ቅዱስ ጳውሎስ ስጋቱን ገልጾአል፡፡ ልብ እንበል! ዛሬ ሰይጣን ለክርስቶስ ብቻ እንድንሆን የታጨነውን እኛን በክርስቶስ ላይ ሌሎችን እንድንደርብ የሚያደርገን በግልጽ ሰይጣን ነኝ ብሎ፣ ወይም እናንተን የክርስቶስ ብቻ ሳይሆን በክርስቶስ ላይ ሌሎችን ውሽሞች እንድትይዙ ነው የመጣሁት ወዘተርፈ በማለት እንዳልሆነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ይህን የሚያደርገው በተንኮል አሰራር ነው፡፡ ሰይጣን በተንኮል ሲሰራ ለእኛ ያዘነ መስሎ፣ የተሳሳተውን ትምህርት ትክክለኛ አስመስሎ በማቅረብ ነው፡፡ እኛ የክርስቶስ ብቻ ሆነን ሳለ ዛሬ የክርስቶስም የሌሎችም እንድንሆን ያደረገው በዚሁ መንገድ ነው፡፡ ብዙው ሰው ግን በሰይጣን ተንኮል ስለተታለለ ይህን ማስተዋል አልቻለምና በተንኮል የቀረበለትን የሰይጣንን ሐሳብ ተቀብሎ በማስተናገድ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ቅድስና ሐሳቡ ተለውጧል፡፡
ዛሬ ሰይጣን በተንኮሉ ህዝቡን እያሳተና ለክርስቶስ ብቻ እንዳይሆን ለማድረግ እየሰራ ያለበት አንዱና ዋነኛው ስልት የቅዱሳንን ስም በመጠቀም ህዝቡ አምልኮትን፣ ዝማሬን፣ ስግደትንና ውዳሴን በቅዱሳኑ ስም እንዲያቀርብ ማድረግ ነው፡፡ ለዚህም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ለዚሁ የተሳሳተ ትምህርትና ልምምድ አጣመው እንዲጠቀሙበት ያደርጋል፡፡
ቅዱሳን እነማናቸው?
ብዙዎች ቅዱሳን የሚሏቸው በተጋድሎ ውስጥ ያለፉና ያንቀላፉ የቀደሙ ሰዎችን ብቻ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ቅዱሳን የሚላቸው ግን ዓለም ሳይፈጠር በክርስቶስ ኢየሱስ የተመረጡትን ሁሉ ነው ኤፌ 1፡3፡፡ ይህም ትናንት የነበሩ ዛሬም ያሉ ለወደፊቱም የሚነሡትን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ለአማኞች ቅድስናቸው ነው፡፡ 1ቆሮ. 1፡31፡፡ በክርስቶስ የተቀደሱ ከመሆናቸው የተነሣ እነዚህ ቅዱሳን በኑሯቸው ሁሉ እየተቀደሱ ይሄዳሉ፡፡ በቅዱስ አጠራር የተጠሩትም ለዚሁ አላማ ነው፡፡ 1ጴጥ. 1፡15-16፤ 2ጢሞ. 1፡9፡፡ ስለዚህ ቅዱሳን የሚባሉት የቀደሙትና ዛሬ በሕይወት የሌሉት ብቻ ሳይሆኑ ዛሬ በሕይወት ያለነው ለወደፊቱም የሚነሡ ሁሉ ናቸው፡፡ ሩጫቸውን በድል ጠናቀቁት ብቻ ሳይሆኑ ዛሬ በትግል ውስጥ ያለነውም ነን፡፡ የትናንቶቹ በፈጸሙት መንፈሳዊ ገድል እየታወሱ መታሰቢያቸውም ከእግዚአብሔር ቤት ሳይጠፋ ይኖራል፡፡ አሁን በትግል ላይ ላለነው ቅዱሳን የተጋድሎ ሕይወታቸው ትልቅ ትምህርትና ምሳሌ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ያንቀላፉት ቅዱሳን በምድር ላይ በሚደረገው ነገር ተሳትፎ የላቸውም፡፡ በቅርቡ በሞት የተለዩን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በሕይወት ሳሉ በነበራቸው ስልጣንና ሀላፊነት አሁን ምንም ሊያደርጉ እንደማይችሉ ሁሉ ቅዱሳንም በምድር ላይ በሚሠራውና በሚደረገው ነገር ሁሉ ምንም ተሳትፎም ሆነ ድርሻ የላቸውም፡፡ እነርሱ ሩጫውን ጨርሰዋል፡፡ ሌላ ሩጫ የለባቸውም፡፡ ሽልማታቸውን ከታማኙ ጌታ እየጠበቁ በክብር አሉ፡፡

መጽሐፍ ቅዱሳዊው ቅድስና የሚገኘው ከላይ በገለጽነው መንገድ ቢሆንም በትውፊት ከቤተ ክርስቲያን የሚሰጥ የቅድስና ማእረግ ግን አለ፡፡ ይህ ማእረግ በዚህ ምድር እንጂ በሰማይ እውቅና የለውም፡፡ አንዳንድ አመፀኞች ቅዱስ የሚል ማእረግ ተጎናጽፈው ስንመለከትም ነገሩ አጠያያቂ ይሆንብናል፡፡ ለምሳሌ ብዙ ቅዱሳንን የፈጀውና አምልኮተ ጣኦትን ወደቤተክርስቲያን በጉልበት ያስገባው አፄ ዘርአ ያዕቆብ በምን መስፈርት ይሆን ቅዱስ የተባለው? በምን መስፈርትስ ይሆን ተቀባይነት ባይኖረውም ታቦት የተቀረጸለት? የበኣል ቀን የተለየለት? መልክ የተደረሰለት? እንደ እግዚአብሔር ቃል በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የዘላለም ሕይወት ባለቤት የሆኑትንና በእርሱ ሥራ የተቀደሱትን ብቻ ቅዱሳን የማለት ድፍረት አለን እንጂ በእኛ መስፈርት ሰውን ቅዱስ ማለት አስቸጋሪ ፍርድ ነው «ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል» ተብሏልና ይህን ለእርሱ ብንተው ይሻላል 2ጢሞ. 2፡19፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ቅዱሳን የሚላቸው ዓለም ሳይፈጠር በክርስቶስ የተመረጡትንና ስለእግዚአብሔር ቃልና ስለመንግሥቱ መስፋት የተጋደሉትን ሲሆን እኛ ግን ከእነርሱ ውጪ በሌላ አላማና ምክንያት የተጋደሉትንና ልዩ ልዩ መከራ የደረሰባቸውን ሁሉ «ቅዱሳን» እያልን መሰየማችን ለቅዱሳን ያለን አመለካከት መጽሐፍ ቅዱሳዊ እንዳይሆን አድርጎታል፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቅዱስ የተባሉት በምን ምክንያት ነው? መንግስትን ከዘጔ ወደ ሰለሞናዊው ስርወ መንግስት ለመመለስ በመታገላቸውና ለዚህ ውለታቸው ሲሶ መንግስት ለቤተክርስቲያን በማስገኘታቸው? ወይስ ሌላ ምክንያት ይኖር ይሆን? በቅርቡ አቡነ ጴጥሮስ ሰማእት ተብለዋል፡፡ አቡነ ቴዎፍሎስም እንደዚሁ፡፡ የአቡነ ጴጥሮስ ሰማእትነት ለአገራቸው በፈጸሙት አኩሪ ገድል ከሆነ ያስማማናል፡፡ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ሰማእት ለመባል ግን የክርስቶስ ታማኝ ምስክር ሆኖ ስለ ክርስቶስ ስም መከራ መቀበል የግድ ይላል፡፡ የአቡነ ቴዎፍሎስም በዚሁ መሠረት ነው መታየት ያለበት፡፡

በቅዱሳን ስም የሚቀርበው አምልኮት፣ ዝማሬ፣ ስግደት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ወይ?
ስለቅዱሳን ስናስብ ያለፉትን ቅዱሳን ከሌሎች ክርስቲያኖች የተለዩና ቅድስናን በራሳቸው ጥረት ያገኙ አድርገን ነው የምናስበው፡፡ ስህተታችን የሚጀምረው እዚህ ላይ ነው፡፡ ማንም ሰው በራሱ ብቁ ሊሆን አይችልም፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም «ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳችን እንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም፤» ብሏል፡፡ (2ቆሮ. 3፡5)፡፡ ያለፉት ቅዱሳን ብቃትን ያገኙት ከእግዚአብሔር ነው፡፡ በእግዚአብሔር ጸጋ ለጌታ በመኖርና መልካሙን ገድል በመጋደል አንዱ ከሌላው ልዩነት ቢኖረውም ሁሉም ግን ፍጡር መሆኑ መረሳት የለበትም፡፡ ስለዚህ በራሳቸው ጥረት እንደተቀደሱ ቆጥረን በስማቸው ልዩ ልዩ አምልኮት መፈጸም የለብንም፡፡ ይህ በክርስቶስ ላይ ማመንዘር ይሆናል፡፡ ዛሬ እየሆነ ያለውም ይህ ነው፡፡ ለአንዱ ለእግዚአብሔር ብቻ ሊቀርቡ የሚገባቸው የአምልኮት መገለጫ የሆኑት ዝማሬ፣ ስግደት፣ ውዳሴ ወዘተርፈ የአምልኮትና የአክብሮት የሚል ደረጃ ወጣላቸውና ቅዱሳን ለተባሉት ሰዎች በአክብሮት ስም ይቀርቡላቸው ጀመር፡፡ አንዳንዶች ይህን ልምምድ ቅዱሳንን ማክበር ሲሉ ቢጠሩትም ትክክለኛ ስሙ ግን  ቅዱሳንን ማምለክ ነው፡፡

መጥምቁ ዮሐንስ በእርሱና በክርስቶስ መካከል ያለውን ልዩነት በሙሽራና በሚዜ መካከል እንዳለው ልዩነት ነው የገለጸው፡፡ ሙሽራይቱ ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው ቆሞ የሚሰማው ሚዜው ግን በሙሽራው ድምፅ ደስ ይለዋል ነው ያለው፡፡ ስለዚህ ሙሽሪት ቤተክርስቲያን (ያንቀላፉትም ዛሬ ያለነውም ቅዱሳን) አምልኮትን ሁሉ ለአንዱ ውዷ ለክርስቶስ ብቻ የምታቀርበው እንጂ እንደሚዜ ለሚቆጠሩትና የቤተክርስቲያን አካላት ለሆኑት ቅዱሳን አታቀርብም፡፡ የቤተክርስቲያን አካል የሆኑትን እነርሱንም ጭምር እንወድስ ካልን ግን በክርስቶስ ላይ ምንዝርና እየፈጸምን ነው፡፡

ለነገሩ ቅዱሳን እኛ እንደምናስበው ሳይሆን በትክክለኛው መንገድ ከእኛ ጋር አንዱን ውዳችንን ክርስቶስን ያመልኩታል እንጂ እንደእነርሱ ላለው ሰው ማንኛውንም ሰው አምልኮት አያቀርቡም፡፡ ለእነርሱ ቢቀርብላቸውም አይቀበሉትም፡፡ ቅዱስ ጳውሎስና በርናባስን የልስጥራን ሰዎች እንደ አምላክ ቆጥረው ሊሰዉላቸው ባፈለጉ ጊዜ « ልብሳቸውን ቀደው ወደ ሕዝቡ መካከል እየጮኹ ሮጡ፥ እንዲህም አሉ። እናንተ ሰዎች፥ ይህን ስለ ምን ታደርጋላችሁ? እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን፥ ከዚህም ከንቱ ነገር ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእነርሱም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ዘወር ትሉ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን።» የሐዋ. 14፡14-15፡፡ ልብ እንበል ሐዋርያት ጳውሎስና በርናባስ የሰዎቹን ድርጊት «ከንቱ ነገር» ብለው ነው ጠሩት፡፡ 

ምናልባት እነዚህ አሕዛብ ናቸውና በዚያው በለመዱት በአምልኮተ ጣዖት መንገድ ነው ሊሰዉላቸው የፈለጉት የሚል ተከራካሪ ሊኖር ይችላል፡፡ እግዚአብሔርን የሚያውቁት ሐዋርያው ዮሐንስ ለመልአኩ ቆርኔሌዎስም ለጴጥሮስ ያቀረቡትን ስግደት ያልተቀበሉትስ ለምን ይሆን? ዮሐንስ ለመልአኩ በሰገደ ጊዜ «እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና አለኝ።» ነበር ያለው፡፡ ራእ. 19፡10፡፡ ቆርኔሌዎስ ለጴጥሮስ በሰገደ ጊዜ ልክ ነህ የሰገድከው ለቅዱሳን የሚገባውን የአክብሮት ስግደት ነውና ችግር የለውም አላለውም፡፡ «ተነሣ፤ እኔ ራሴ ደግሞ ሰው ነኝ ብሎ አስነሣው።» ሐዋ. 10፡26፡፡ ቅዱሳን በዚህ ምድር እያሉ እንዲህ ያለው አምልኮት ይቀርብላቸው ዘንድ ተገቢ እንዳይደለ ከተናገሩና ካልተቀበሉት ካንቀላፉ በኋላ ይቀበሉታል ማለት ዘበት ነው፡፡ ስለዚህ ዛሬ ለቅዱሳን በአክብሮት ስም የሚቀርበው ዝማሬ ስግደትና ውዳሴ ሁሉ ምንጩ መጽሐፍ ቅዱስ አይለም፡፡
  
ቅዱሳን የሚቀርብላቸውን አምልኮት ዝማሬና ስግደት ያውቁታል? ይቀበሉታል?
ዛሬ በስማቸው የምናደርገውን አምልኮት ዝማሬና ስግደት ሁሉ ቅዱሳን አያውቁትም፡፡ ቢያውቁት ኖሮም ባልተቀበሉትም ነበር፡፡  ቅዱሳን ሕያዋን ቢሆኑም በዚህ ምድር ላይ የሚሠራውን እያንዳንዱን ነገር የማወቅ ችሎታ የላቸውም፡፡ ቅዱሳን ለባዊት ነፍስ ብትኖራቸውም እንደእግዚአብሔር ሁሉን አያውቁም እንጂ ይህ ሁሉ ነገር በስማቸው የሚቀርብ መሆኑን ቢያውቁ ኖሮ ቀድሞ ካደረጉት የበለጠ በማድረግ እንዲህ ያለውን አምልኮት «ከንቱ ነገር ነው» ብለው በጭንቅ ያስተዉን ነበር፡፡ ስለዚህ በእነርሱ ስም የሚቀርበውን ሁሉ እንደማያውቁትና እንደማይቀበሉት ማወቅ ይኖርብናል፡፡ ለእነርሱ የሚቀርብ እንዳልሆነም ማስተዋል አለብን፡፡ እዚህ ላይ ይህን እውነት መቀበል የማይፈልጉ ሰዎች ከዚህ ቀደም እንደሚያደርጉት ያን የፈረደበትን መከራከሪያ አብርሃም ከእርሱ በኋላ የነበረውን ሙሴን አውቆታልና ቅዱሳን ቢያንቀላፉም በዚህች ምድር ላይ የምተሰራውን ሁሉ ልቅም አድርገው ያውቃሉ እንደሚሉ አልጠራጠርም፡፡ በዚሁ ጉዳይ ላይ ሌላ ማብራሪያ ካስፈለገ ወደፊት እመለስበታልሁ፡፡

የቅዱሳን መታሰቢያ የሚደረገውስ በዚህ መንገድ ነወይ?
የቅዱሳን መታሰቢያ በምን መልክ ነው የሚደረገው? አሁን በእኛ ዘንድ እንደሚደረገው ባለ መንገድ እንደማይደረግ ግን በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡ ቅዱሳን በዚህ ምድር ሳሉ ለአምላካቸው ባላቸው ፍቅርና ታማኝነት በሰሩት በጎ ሥራና በተጋደሉት መልካም ገድል ስማቸው ሲታወስ ኖራል፡፡ ይህ ነው መታሰቢያ የተባለው እንጂ በእነርሱ ስም አምልኮት (መዝሙር፣ ስግደት ውዳሴ ……) ይቀርባል የሚል ፍቺ የለውም፡፡ በወንጌል ተጽፎ እንደምናነበው በጌታ እግር ላይ ዋጋው ውድ የሆነ ሽቶ ስላፈሰሰችው ሴት ጌታ የተናገረው እንዲህ የሚል ነው «እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ወንጌል በዓለም ሁሉ በማናቸውም ስፍራ በሚሰበክበት እርስዋ ያደረገችው ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል።» ማቴ 26፡1፡፡ ሌሎቹም ቅዱሳን በሕይወት ሳሉ ያደረጉት እየተነገረና እየታሰቡ ይኖራሉ እንጂ ለአምላክ ብቻ ሊቀርብ የሚገባውን መዝሙር፣ ስግደትና ውዳሴ በእነርሱ ስም ማቅረብ አምልኮተ ጣኦት ነው የሚሆነው፡፡ ምክንያቱም በቅዱሳን ስም የሚቀርበው መዝሙር፣ ስግደት፣ ውዳሴና ቅዳሴ የሚደርሰው ወደ ቅዱሳኑ ሳይሆን በስማቸው እየነገደ ወዳለውና ከጥንቱ ጀምሮ የእግዚአብሔርን ክብር ለራሱ ሊያደርግ ወደሚፈለገው ወደሰይጣን መሆኑን በሚቀጥለው ነጥብ ሥር እንመለከታለን፡፡

የአምልኮቱ የዝማሬውና የስግደቱ ትክክለኛ ተቀባይ ማነው?
እስካሁን እንዳየነው ቅዱሳን ከእኛ ጋር እግዚአብሔርን የሚያመልኩ እንጂ በአክብሮት ስም ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን አምልኮት የሚቀበሉ ወይም የሚጋሩ አይደሉም፡፡ ቢቀበሉ ግን ያው እንደሰይጣን መሆናቸው ነው፡፡ እርሱ ነውና የእግዚአብሔርን ክብር ለራሱ ሊያደርግ የፈለገውና በዚህ ምክንያት የወደቀው፡፡ ስለዚህ በቅዱሳን ስም የሚቀርበው ልዩ ልዩ አምልኮት የሚደርሰው ለቅዱሳኑ ሳይሆን በስማቸው ለሚነግደውና ከመጀመሪያው መመለክ ለሚፈልገው ክፉ መንፈስ ነው፡፡

በማስተዋል ካየነው ያንቀላፉ ቅዱሳንንና መላእክትን ጨምሮ እኛ የአንዱ የክርስቶስ ብቻ ነን እንጂ እንደኛ ያለው የሌላ ቅዱስ ሰው ወይም ቅዱስ መልአክ አይደለንም፡፡ መልአኩ ለዮሐንስ ያለው ምንድነበር? «ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤» አለ እንጂ እኔ የተለየሁ ነኝ አላለም፡፡ አሁን እየሆነ ያለው ግን ቅዱሳንን ከእኛ ጋር ጌታን የምታመልኩ ናችሁ ሳይሆን በግድ ከእኛ የተለያችሁ ናችሁና በአክብሮት ስም ልዩ ልዩ አምልኮት ሊቀርብላችሁ ይገባል የሚል ነው፡፡ ይህን የምለው ቅዱሳን ፍጡራን መሆናቸውን ለማሳየት እንጂ ክብራቸውን ለማቃለል እንዳልሆነ ግን በቅንነት ተረዱልኝ፡፡ ስለዚህ ዛሬ በቅዱሳኑ ስም የሚደረገውን ሁሉ እያደረግን ያለነው መጽሐፍ ቅዱስ ፈቅዶልን ሳይሆን ክፉው መንፈስ ሔዋንን በተንኮሉ እንዳሳታት እኛንም በረቀቀ መንገድ አስቶን ለቅዱሳን የአክብሮት መዝሙር፣ ስግደት፣ ውዳሴ፣ ውስጡ ሲፈተሽ ግን አምልኮት እንድናቀርብ በማድረግ ነው፡፡ ሰይጣን የስንቱን ቅዱሳንና ቅዱሳን ይሁኑ አይሁኑ የማይታወቁትን ሰዎች ስም ሁሉ በመጠቀም ሲያታልለን እንደኖረና ዛሬም እያታለለን እንዳለ አለማወቃችን ግን እጅግ ያሳዝናል፡፡

ሰይጣን ስም እየቀያየረ አንዴ በአንዱ ስም በሌላ ጊዜ ደግሞ በሌላው ስም ለእግዚአብሔር ብቻ ሊቀርብ የሚገባውን አምልኮት በሌሎች ስም ለራሱ ሲያደርግ እንደኖረ ከቶም መዘንጋት የለበትም፡፡ እስኪ የሩቁን ትተን ከጥቂት አመታት ወዲህ የተጠቀመባቸውን ስሞች እንይ፡፡ ሸንኮራ ዮሐንስ፣ ጻድቃኔ ማርያም፣ ኩክየለሽ ማርያም፣ ወይብላ ማርያም፣ መግደላዊት ማርያም፡፡ የአንዳንዶቹ ስም አሁንም ከአውደምህረት ባይወርድም አሁን ዋናው ተረኛ ስም ደግሞ አርሴማ ሆኗል፡፡ አርሴማ አርመናዊት ሰማእት እንደሆነች ይነገራል፡፡ ከዚህ ቀደም ግን በኢትዮጵያ አትታወቅም ነበር፡፡ ሰማእት የሆነችው በክርስቶስ ስም ይሁን አይሁን መፈተሽ ያለበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ይህች ሴት እውነተኛ ሰማእት ብትሆን እንኳ በስሟ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኞች ዘንድ ከኢትዮጵያ እስከ አሜሪካ እየተደረገ ያለው ነገር ሁሉ ትክክል አይደለም፡፡ ከተጋድሎ ሕይወቷ የምንማረው መንፈሳዊ ትምህርት ካለ ያን መውሰድ እንጂ በስሟ መዘመር፣ በስሟ ስለት መሳል፣ በስሟ መስገድ፣ ወዘተርፈ አምልኮተ ጣኦት ነው፡፡ በስሟ የሚደረገው ሁሉ ለእርሷ ክብር የሚደረግ ቢመስለንም እንኳን ስህተት ነው፡፡ ያም ቢሆን ተቀባዩ ሰይጣን እንጂ ሌላ ማንም ሊሆን አይችልም፡፡

አሁን ተረኛው ስም አርሴማ ሆኗል፡፡ ቀድሞ ገናና የሆኑት ሌሎቹ ስሞች ነፍሶባቸው በሌሎች ስሞች እንደተተኩ ሁሉ ነገ ደግሞ አርሴማ የተባለው ስም ነፍሶበት «ተአምር ሰሪ» ተብሎ የምንተዋወቀው ሌላ አዲስ ስም (የሚታወቅ ስምም ሊሆን ይችላል) እንደሚመጣ ግን ምንም አትጠራጠሩ፡፡

ከሰይጣን ባሻገር በቅዱሳን ስም ከሚደረጉ «ከንቱ ነገሮች» በስተጀርባ ሰይጣን በጀመረው መንገድ የሚጓዙና ልዩ ልዩ ስሞችን የሚያስተዋውቁ ሰዎች እንዳሉና በሚያስተዋውቋቸው ስሞች እንደሚነግዱና ትርፋማ እንደሆኑ ለአፍታም መዘንጋት የለበትም፡፡ እገሌ የሚባል ጻድቅ አለ ታምር ሰሪ ነው ገዳሙን ጎብኙ በሚል የጉዞ ማህበር እያዘጋጁ ቀረጥ የማይከፈልበትን ብዙ ገንዘብ ያጋብሳሉ፡፡ ሌሎቹ ተመሳሳይ አላማ ያላቸው ሰዎችም ያ ቦታ ሩቅ ከሆነ ዳግማዊ እገሌ በሚል በቅርብ ቤተክርስቲያን በማነጽ የእገሌ ታቦት ጉደኛ ነው እያሉና እያስባሉ ህዝቡን የሚበዘብዙ አሉ፡፡ ይህ የእንጀራ ጉዳይ ስለሚሆን እነዚህ ሰዎች ወንጌል ቢነገር ፈቃደኞች አይደሉም፡፡ ወንጌል እንዲህ ያለውን የሰይጣን አሰራር የሚያጋልጥና ህዝቡን እንዲህ ካለው ከንቱ አምልኮት ወደ አምልኮተ እግዚአብሄር ፊቱን እንዲመልስ የሚያደርግ መልካም ዜና ነውና፡፡ ስለዚህ ወንጌል ከመሰብክ ይልቅ ሰይጣን አምልኮትን ሊቀበልባቸው እያስተዋወቃቸው ያሉትን ስሞች ይበልጥ በማስተዋወቅ ስራ ተሰማርተዋል፡፡ በዚህም  የሰይጣንን ተልእኮ እየፈጸሙ መሆናቸውን ግን አላሰተዋሉም፡፡

ክርስቲያኖች ሆይ እባካችሁ እናስተውል እኛ እኮ በውድ ዋጋ በክርስቶስ ክቡር ደም የተዋጀን ነንና ያልገዛን ሊነዳን፣ ያልሞተልን ሊኖርብን አይገባም፡፡ «በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።» ተብለናልና እንኳን ለሌላው ልንሆን ይቅርና የራሳችንም አይደለንም፡፡ 1ቆሮ 6፡19-20፡፡ ስለዚህ በክርስቶስ ላይ አናመንዝር፡፡

«በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤ ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ።» 2ቆሮ. 11፡2-3፡፡

ከጸጋ ታደለ


  

63 comments:

 1. ለዚህ ሁሉ እናንተም aba selamawoch ተጠያቂ ናችሁ ቀላል እና ግልጽ ስህተቶች እንዳይስተካከሉ የናንተ መኖር አስተዋጾ አድርግል እንዚህ ስህተቶች አንድ ሰው ለማስተካከል ቢነሳ ተሃድሶ ይባላል ስህተት መሆኑ እየታወቀም ብምን ማስረጃ ሲባል የናንተን ጽንፈኛ የሆነ እና የትንታዊ አባቶችን ታሪክ ያላገናዘበ yeprotestant astemhron sayamnezek yewate bechfn የተመራ tehadso yitekesal ለዚህም mkidusan እናንተን እንደ ማስረጃ እየተጠቀመ የፈለገውን ሰው ለማጥቃት አስችሎታል በቃ ተሃድሶ የሚባል ነገር አለ የት ነው ያለው ?....ሂዱ አባ ሰላማን ተመልከቱ ዪባላል ስለዚህ ማህበሩን የተቃውመ የቤትክርስትያን ስህተቶችን ነቅሶ ያውጣ ሁሉ ተሃድሶ ባይሆንም ተሃድሶ ተብሎ ይብጠለጥላል ማስረጃ ሲባል አባ ሰላማ!!1 አለቀ ደቀቀ አፋችንን ማዝጊያ ያው እናንተ ናችሁ!!!for example... አንዳንድ ሥዕሎች ላይ የቤተክርስትያን ያልሆነ ነገር ብዙ ጊዜ አንብቢያለሁ ለምሳሌ...የአርሲዋ እመቤት የሚል የመቤታችነን ሥዕል የሚመስል ሥዕል ብዙ ጊዘ ተመልክቻለኡ ለመሆኑ ቅድስት ማርያምን የአርሲ እምቤት ያረጋት ማነው??? ምናልባት ብትባል ትክክል የሚሆነው የትህትና እመቤት የአለም እመቤት የአዳኛችን እናት እመብርሃን ነበረ ይህን ሥዕል ሳይ ትዝ ያለኝ ጉዳይ! አለ! ትዝ ያለኝ አወዛጋቢዋ ድንግል ማርያም ነኝ ባይዋ ሴት ነቺ አገር ጉድ ስታሰኝ የነብረችው ማርያም ልትሆን አትችልም አይደለችም!!!!! ታዲያ ማናት? የአርሲዋ እመቤት ትሆን እንዴ? ይመስላል መቼም በጤናው አይደለም እንድዛ የምትቀባጥረው! ምናልባት የርሱ መንፈስ ዪሆን? ራሱን የአርሲዋ እመቤት እያለ የሚጠራ ክፉ መንፈስ ገብቶባት ሊሆን ይችላል! ለምን ብንል የአርሲዋ እመቤትየሚለው ስእል ከመቤታቺን ቅድስት ማርያም ጋር የሚያገናኘው ነገር ፈጽሞ የለም!!!!!!!ሌላው ቀርቶ አንድ ብቻ ሴት አይደለችም ራሳቸውን በመቤታቺን ቦታ የተኩት ብዙ ናቸው! መንፈሱ ብዙ ሰው ላይ በአንድ ጊዜ መግባት እንደሚችል አስታውሱ!! ማርያም በዚህ ዘመን ጌታን ለመውለድ ተገለጠች ቢባሉ ምን ይላሉ?
  እንደ አይሁድ ገና ጌታ ይወለዳል ቢባሉስ?
  መለኮት ግንቦት 1/1999 ተፀንሶአል ይህንንም በ3 ቀን ሱባኤ ጠይቁ ቢባሉስ?በጊዜው የተከሰተችው ሴት ከዚህ በፊት ተሰምቶም ሆነ ታይቶ የማይታወቅ ተግባር ስለፈጸመች ብዙዎችን ጉድ አሰኝታ ነበር ፤ ከሰማይ የወረደ መና ነው በማለት ብዙዎችን ምንነቱ ያልታወቀ ምግብ አብልታቸዋለች ፤ ይህ ሁሉ ሲደረግ ስለ እሷ ሽንጣቸውን ገትረው የሚከራከሩ ብዙ ነጫጭ የለበሱ ሴቶችን አስከትላ ገድሏን ሲመሰክሩላት ሲመለከቱ ይህ ነገር ህልም እንጂ እውን አይመስሎትም !!!አንድ ከጎንደር የመጣች ሴትም በዚሁ አመቤቴ ታናግረኛለች በማለት ብዙ ታላለቅ ሰዎችም የተከረየችበት ቤት ድረስ እንደሚሄዱ እና ሴትየዋ እራሷን አለማዊ መናኝ ነኝ በማለት እና መንፈስ ቅዱስ እንደሚታያት እና እመቤታችን እንደምታናግራት ነው የምትናገረው ሁለት ልጆች ሲኖራት የመጀመሪያዋ ከሌላ ሰው የተወለደች ሲሆን ሁለተኛውም ከሌላ ወንድ የተወለደ ነው፡፡ ይህን ስራ ከጀመረች ወደ 20 አመት ይሆናታል ካህን የሚያደርገውን ሁሉ ታደርጋለች ለምሳሌ ቄደር ማስጠመቅ፣ ንስሃ ለሷ መናዘዝ፣ ቅባቅዱስ መቀባት የመሳሰሉትን ነገሮች ታደርጋለች ለምን ይሄ እኮ የካህን ስራ ነው ስትባልም እመቤቴ በልዩ ትዕዛዝ ለኔ ሰጥታኝ ነው ካህናቶች ሴቶችን በሚቀቡበት ጊዜ እየተሰናከሉ ስለሆነ ይህን ስልጣን ለሷ እንደተሰጣት ትናገራለች የንስሃ ልጆቼ ከምትላቸውም አስራት ትወስዳለች፡፡ ባልና ሚስትንም አፋታለች መፀሀፍም አላት የራሷገድል !!!! እኔ 100 percent እርግጠኛ ነኝ እንዚህ ሴቶች መንፈስ ገብቶባቸው እንጂ በጤናቸው አይደለም ! ታድያ እኛስ orthodoxawyan ስእሉን ሁሉ ከማግበስበስ ምን ተጽፎበታል ምን ይላል ማለት አይገባምን? yiketlal

  ReplyDelete
  Replies
  1. አባ ሰላማ ምን አጠፋ፡፡ እንደዚህ ያለውን ስህተት ዝም ብሎ ከማለፍ ይልቅ እንድንማርበት ማድረጉ ያስመሰግነዋል እንጂ አያስወቅሰውም፡፡ በዚህ ነገር አባ ሰላማ ተጠያቂ ሊባል አይገባም፡፡ እንዲያውም በሃይማኖታችን ስም እየተፈጸመ ያለው የአምልኮ ባእድ ልሞምድ ሁሉ መጋለጥ አለበት፡፡ ይህን ሸፍኖ መኖር አይጠቅምም፡፡ ከዚህ ይልቅ ቢጋለጥ መፍትሄ ይገኛል፡፡ ስለዚህ አስተያየት ስንሰጥ በዋናው ጉዳይ ላይ መነጋገር እንጂ ዋናውን ጉዳይ የሳተ አስተያየት በመስጠት ማደናገር የለብንም፡፡ አሁን ጥያቄው በቅዱሳን ስም እየተደረገ ያለው አመንዝራነት ነው አይደለም? የሚለው ይመስለኛል፡፡ ጽሁፉ ይህን በሚገባ አሳይቷልና ቆምብለን ራሳችንን መመርመር ነው ያለብን፡፡ እያደረግነው ያለው አምልኮት ሁሉ ወደሰይጣን ኪስ የሚገባ ከሆነም በጣም ከስረናል፤ ጌታንም አስቀንተነዋልና ከዚህ ሁሉ ብቻውን አምላክ የሆነውን እግዚአብሔርን ብቻ ለምን አናመልክም?

   Delete
  2. የአርሲዋ እምቤት GUDAY.....http://www.eotc- patriarch.org/Saint%20Gebriel.pdf...በአርሲ ሀገረ ስብከት በመርቲ ወረዲ ሌዩ ስሙ ፈረቀሳ በተባለ ሥፍራ የቅደስ ገብርኤሌ ቤተ ክርስቲያንመገንባት በብፁዕ አቡነ ናትናኤሌ መንበረ ፓትርያርክ እና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሉቀ ጳጳስና ብፁዓን ሉቃጳጳሳት በተገኙበት የመሠረት ዴንጋይ ኅዲር 1 ቀን 2005 ዓ.ምተቀምጧሌ፡፡
   ይህ ቦታ አምልኮ ባእድ የሚመለከትበት ቦታ የነበረ ሲሆን መንፈሱየአርሲዋ እመቤት በሚሌ ይጠራ ነበረ
   ቦታው የበሽተኞች መዋያ የነበረ ሲሆን ከአሁን በኋሊ የምህረትና ፈውስ አዯባባይ እንዱሁም የእግዚአብሔርዴንቅ ሥራ የሚፈጸምበት ሆኗሌ!! አሁንም
   በአርሲ ሀገረ ስብከት በመርቲ ወረዲ ሌዩ ስሙ ፈረቀሳ በተባሇው አካባቢ በቅደስ ገብርኤሌ ስም ጥቅምት 19
   እና ግንቦት 19 ቀን የሚከበረውን ከቤተ ክርስቲያን ትውፊትና ሥርዓት ውጪ የሆነውን የአምሌኮ ሥርዓት
   ሇማክሸፍ ሲሆን ይህ የባእዴ አምሌኮ ከ1885 ዓ.ም ጀምሮ ይፈፀም የነበረ ሥርዓት በመሆኑና በወ/ሮ ሻበሻ ወርቅ
   ይመር እንዯተመሠረተም ይነገራሌ፡፡
   ይህ የባዕዴ አምሌዕኮ መሥራች ወዯ አርሲ ከመምጣቷ በፊት የተሇያዩ ቦታዎችን በማዲረስ በ1887 ዓ.ም
   ፈረቀሳ በተባሇው አካባቢ የዕምነት ሥራውን በማጠናከር ዴንበሯን በማስፋፋት ይዛው ቆይታሇች በ1912 ጥቅምት
   19 ቀን በማረፏ በየዓመቱ ይህንን ቀን የአምሌኮ ሥርዓቷን በማጠናከር በዘመኑ አጠራር የአርሲዋ እምቤት በሚሌ
   ብዙ የቤተ ክርስቲያኗን ምዕመናን በማንሳት ሊይ የምትገኝ በመሆኑ ይህ የቅደስ ገብረኤሌ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን
   የባዕዴ አምሌኮው በሚፈፀምበት ቦታ ሊይ መመሥረቱ የሚያስዯንቅ እንዲሌሆነ ተገሌጿሌ፡፡በአካባቢው ብዛት
   ያሊቸው የእስሌምና እምነት ተከታዮች የሚኖሩበት ቢሆንም ይህ የባእዴ አምሌኮ ሥርዓት ሇብዙ ጊዜያት
   የሚወገዴበትን ዘዳ በማሰብና የተሇያዩ ሥራዎችን በመሥራት ሊይ እንዯነበሩ ተጠቁሟሌ፡፡
   በእስሌምና እምነት አጠራር ሞሚናት በባዕዴ አምሌኮ ተከታዮች ዘንዴ የአርሲዋ እመቤት በመባሌ
   የሚታወቀውን የእምነት ሥርዓት ከመሌአኩ ቅደስ ገብርኤሌ በዓሌ ጋር በመቀሊቀሌ ሇብዙ ዘመናት ሲመሇክ
   መቆየቱና አስተማሪና መካሪ እንዱሁም ተገቢ የአምሌኮ ስፍራ በማጣቱ ጥቂቱ በማወቅ አብዛኛውን ባሇማወቅ
   ሇቅደስ ገብርኤሌ ስዕሇት ሇማዴረግ እና በማቅረብ ሲሌ በአምሌኮው ታዴሞ መቆየቱ ተጠቅሷሌ፡፡
   የብዙ ዓመታት ጥረትና ጸልት የቅደስ ገብርኤሌ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ በአካባቢው ነዋሪ ሇሆኑ በርካታ
   ምዕመናን በእግዚአብሔር ጥሪ መሠረት ይህ ባዕዴ አምሌኮ በኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ተዋሕድ ቤተ ክርስቲያን
   የተወገዘ መሆኑን በማስተማርና በማሳመን በአካባቢው የሚገኙ የእስሌምና እምነት ተከታዮችም የእርሻ ማሳቸውን
   ሇቤተ ክርስቲያን ማሠሪያ ከመፍቀዲቸው በተጨማሪ በዕሇቱ በተዯረገ መዋጮ የብር1200 በመሇገሥ የግንባታው
   ፈቃዯኝነታቸውን የገሇፁ ሲሆን በዕሇቱም የቀበላውን ሉቃነ መናብርትና የሙስሉሙን ማኅበረሰብ በመወከሌ
   በሰጡት አስተያት እንዯገሇፁት ይህ ተግባር ከጥንት አባቶቻችን ሲያከናውኑት የነበረውን ተጋዞና ተባብሮ የመኖር
   ምስጢር ወረሰን ከመሆኑም በተጨማሪም ተረዲዴተን ሀገራችንን ሇማሳዯግ እንጥራሇን ይህ ቤተ ክርስቲያን
   መሠራቱም እኛንም የሚያስዯስትና የብዙ ችግሮች መፍትሔ ይሆናሌ ብሇዋሌ

   Delete
  3. አርሲዋ እመቤት ጉዳይ.......................................http://www.eotc-patriarch.org/Saint%20Gebriel.pdf..ለዘመናት ከቤተ ክርስቲያን ትውፊት ሥርዓት ውጭ በሆነ መልኩ የአርሲዋ እመቤት የሚል መንፈስ የአምልኮ ባእድ ሲፈጸምበት በነበረው አካባቢ ለቤተ ክርስቲያን ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡
   በአርሲ ሀገረ ስብከት በመርቲ ወረዳ ልዩ ስሙ ፈረቀሳ በተባለ ሥፍራ የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ለመገንባት በብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ እና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ብፁዓን ሊቃ ጳጳሳት በተገኙበት የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡

   ኅዳር 1 ቀን 2005 ዓ.ም ለቤተ ክርስቲያን ግንባታ በተቀመጠው የመሠረት ድንጋይ ላይ ብፁዕ አቡነ ናትኤል እንደገለፁት የዛሬው ቀን ለክርስቲያኖች ልዩ ከመሆኑ አንጻር ብቻ የምንመከተው አይደለም የእግዚአብሔርንም ድንቅ ሥራ ያየንበትና የማዳኑም ሥራ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረ መጥቶ ዛሬም በግልጽ የሚታይ ሆኖ ይገኛል፡፡ይህ ቦታ ባዕድ አምልዕኮ የሚመለከትበት ቦታ የነበረ ሲሆን የዛሬው በዓል ለኛ በሕይወት ላለነው ብቻ ሳይሆን በሕይወት ለሌሉትም ጭምር ነው የእግዚአብሔር ሥራ ሁል ጊዜ ቢሆንም ለተለየ ሥራ ደግሞ የተለየና የተመረጠ ቀን አለ፡፡እናንተ ለእግዚአብሔር መመስገኛ አገልግሎት የሚውል ቤተ ክርስቲያን ለመገንባት እንዲህ ስትተጉ እርሱም ዋጋችሁን አያስቀርባችሁም፡፡ከዚህ በፊት ይህ ቦታ የአርሲዋ እመቤት በሚል የዲያቢሎስ መፈንጫና የበሽተኞች መዋያ የነበረ ሲሆን ከአሁን በኋላ የምህረትና ፈውስ አደባባይ እንዲሁም የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ የሚፈጸምበት ሆኗል አሁንም ለፈጣሪያችሁ በገባችሁት ቃል መሠረት የቤተ ክርስቲያኑ ግንባታ በጥራት በፍጥነት ተከናውኖ ቤተ ክርስቲያኗ ለምዕመናን የምትሰጠውን የተሟላ አገልግሎት እድታጠናክር የተለመደ ክርስቲያናዊ ትብብራችሁና መረዳዳታችሁ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በማለት ገልፀዋል፡፡

   Delete
  4. የአርሲዋ እመቤት የሚለው ስእል ቤተ ክርስቲያን በፍጹም አይወክልም!!! የድንግል ማርያም ስእል በፍጹም በጭራሽ አይደለም የዲያቢሎስ ማደናገሪያ ነው !!!!!!! እንደዚህ አይነት ነገር ካያችሁ ለቤትክርስትያን አመልክቱ ://www.eotc-mkidusan.org/site/index.php/-mainmenu-18/1137-2012-11-15-14-36-09ኅዳር 6 ቀን 2005 ዓ.ም.
   በእንዳለ ደምስስ

   “በአርሲ ሀገረ ስብከት በመርቲ ወረዳ ልዩ ስሙ ፈረቀሳ በተባለ ሥፍራ ከ120 አመታት በላይ የአርሲዋ እመቤት” በሚል የባዕድ አምልኮ ሥርዓት ሲፈጸምበት በነበረ ሥፍራ ላይ የባዕድ አምልኮ ሥርዓቱን በማጥፋት ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ገብርኤልን ቤተ ክርስቲያን ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ኅዳር 1 ቀን 2005 ዓ.ም. አኖሩ፡፡

   ብፁዕነታቸው በሥፍራው ለተገኙት ምእመናን በሰጡት ቃለ ምዕዳን “ከዚህ በፊት ይህ ቦታ የአርሲዋ እመቤት በሚል የዲያቢሎስ መፈንጫ፡ የሕሙማን መዋያ የነበረ ሲሆን ከአሁን በኋላ ግን የምሕረትና የፈውስ አደባባይ እንዲሁም የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ የሚፈጸምበት ሆኗል” ብለዋል፡፡ ለአካባቢው ምዕመናን ባስተላለፉት መልዕክትም የቤተ ክርስቲያኑን ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ የተጣለባቸውን ሓላፊነት ይወጡ ዘንድ አሳስበዋል፡፡

   ይህ የባዕድ አምልኮ ሥርዓት ከ1885 ዓ.ም. ጀምሮ ወ/ሮ ሻበሻ ወርቅ ይመር በምትባል ሴት በሥፍራው እንደተመሠረተና ምዕመናንን በማሳሳት ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እንዲያፈነግጡ በማድረግ እስካረፈችበት እሰከ ጥቅምት 19 ቀን 1912 ዓ.ም ድረስ ቆይታለች፡፡ ነገር ግን በወቅቱ ሲከተሏትና የመሠረተችውን የባዕድ አምልኮ ሥርዓት ሲያከናውኑ የነበሩ ተከታዮቿ “የአርሲዋ እመቤት”፤ የአካባቢው ሙስሊሞች ደግሞ “ሞሚናት” በሚል አጠራር ሥርዓቱን በማጠናከር በዚሁ ቦታ ላይ በቅዱስ ገብርኤል ስም በየዓመቱ ጥቅምት 19 እና ግንቦት 19 ቀን በከፍተኛ ሁኔታ የባዕድ አምልኮ ሥርዓቱን ለብዙ ዘመናት ሲያከናውኑት እንደቆዩ ይነገራል፡፡

   የብዙ ዘመናት ጸሎት ሰምሮ በብፁዕ አቡነ ናትናኤል መመሪያ ሰጪነትና ድጋፍ ሀገረ ስብከቱና የወረዳው ቤተ ክህነት እንዲሁም ምእመናን ባደረጉት ጥረት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነትና ሥርዓት መሠረት ባዕድ አምልኮ መፈጸም የተወገዘ መሆኑን በማስተማርና በማሳመን የመሠረት ድንጋዩ እንዲቀመጥና የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን እንዲሠራ ስምምነት ላይ ተደሷርል፡፡

   በአካባቢው የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮችም የእርሻ ማሳቸውን ለቤተ ክርስቲያን መሥሪያ በመፍቀድ ከ1200,00 ብር በላይ በማዋጣት መለገሳቸውን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፡፡

   Delete
 2. iyesus yene bemehonu betam korahu!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ere benath/sh iyesus yanchi/ante bcha aydelem yegham new yhie glawinet ena egoism biker ayshalm!!!

   Delete
  2. ኢየሱስ የዓለም መድሀኒት ነው፡፡ ከዓለም መካከል ደግሞ አንዱ አንተ ነህ እርሱ የአንተ አዳኝ ሊሆን ነው የመጣው ስለዚህ በጅምላ ብቻ ሳይሆን በግልህም ልታምነውና አዳኝህ ልታደርገው ይገባል፡፡ ልብ በል የምትጠየቀው በግልህ እንጂ በድርጅትህ አይደለም፡፡ ስለዚህ የግል መድሀኒት የሚለውን በጭፍን ከማብጠልጠል ይልቅ ራስህን ጠይቅ፡፡ ኢየሱስን ብታምን የአንተም ይሆናልና ኢየሱስ የእኔ በመሆኑ ኮራሁ ባለው ሰው አትቅና፡፡

   Delete
  3. የትኛው መፅሀፍህ ላይ ነው ኢየሱስን እንደ ግል አዳኝህ አርገህ ተቀበል የሚለው? እስኪ ምዕራፍና ቁጥሩን ንገረን። ብቻ የጴንጤ አለቆቻችሁ የነገሯችሁን ዝባዝንኬ ሁሉ ቤተ ክርስቲያኗ ላይ ታዝረበርባላችሁ።

   Delete
  4. አንድ ሰው ለህመሙ መድሃኒት እንዳለዉ ማወቁ ብቻ........ከበሽታው ሊያድነው አይችልም......... መድሃኒቱን ሊተቀም ይገባዋል........ ልክ እንደዚሁ ሁሉ........ ክርስቶስ ለሃጢያት ፍቱን መድሃኒት ነው.......... ነገር ግን ሃጢያተኛ ግን ክርስቶስ የሃጢያት መድሃኒት መሆኑን ማወቁ አያተርፈዉም......... የግዴታ መድሃኒቱን ክርስቶስን ሊወስድ ሊዉጥ ሊያምን ያስፈልገዋል....... ይህ ማለት ደግሞ መድሃኒቱ ለሁሉም ቢሆን የሚድነዉ ግን የተጠቀመ ብቻ ነው.........

   Delete
 3. ..ተአምረ ማርያም....ተአምረ ማርያም ምንጩ ምንድርነው? ትውፊት ነው ወይስ አፈ ታሪክ
  ወይስ ተረት? ለምን ምንጩ መጽሐፍ ቅዱስ አልሆነም? መጽሐፍ ቅዱስ
  መጽሐፍ ቅዱስ የወጡ ጥቂት ምንባቦች መጽሐፉን ክርስትና እንዲሸት
  ተብለው ከዐውዳቸው ተፈንቅለው በውስጥ ተስገዋል። ይህን የሚያህሉ
  ግዙፍ ትምህርቶች ሲሰጡ በመጽሐፍ ቅዱስ መፈተሽ አያስፈልግም
  ነበር? ሌሎችም መፈተሻዎች አሉ። መጽሐፉ እርስ በርሱ ይጋጫል ወይስ
  አይጋጭም? ከሌሎች መሰል መጽሐፎች ጋርስ ይስማማል ወይስ
  ይጣላል? በአፈጣጠሩስ ተዓማኒነትን የጨበጠ ነው? ከታሪክና ከተረት
  ወደ የቱ ይቀርባል? ወደ የቱስ ያዘነብላል? ታሪካዊ ከሆነ ታሪኩ ከሌላ
  ምንጭ ጋር ሊስተያይ ይችላል?
  ተአምረ ማርያምን አንብቤ ከፈጸምኩ በኋላ በውስጡ ካገኘኋቸው
  ሕጸጾች መካከል ዋና ዋና የምላቸው እነዚህ ናቸው፤የደፈረሰ ምንጭ። ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው የእትሙ አሳታሚው
  አይታወቅም። መታወቁ መልካም የሚሆነው ጥያቄንና አጠያያቂ
  ጉዳዮችን ለመነጋገር እንዲያስችል ነው። አሳታሚውን በተመለከተ
  መጽሐፉ ከእትም ወደ እትም የሚሸጋገረው ከገቢ ምንጭ ጋር በተያያዘ
  መልኩ ሊሆን ይችላል። የደፈረሰው ምንጭ ግን የመጀመሪያ ደራሲውን
  የሚመለከት ነው።መጽሐፉን ትኩረት
  ሰጥተን ስንፈትሸው ግን በ15ኛው ክፍለ ዘመን ጳጳሳቱ ኢትዮጵያ ውስጥ
  ከገቡ በኋላ አከናወኑት የተባለውን ኢትዮጵያዊ ታሪክ በውስጡ ይዞ
  ስለሚገኝ ከግብጽ ነው የመጣው መባሉን ለማመንና ከዚያ ክፍለ ዘመን በፊት የተጻፈ ነው ለማለት የሚያስችለንን ድፍረት እንድናጣ
  ያደርገናል።ተአምረ ማርያም በውስጡ እንደተጻፈው በእርግጥ ከመንበረ ማርቆስ
  ከተገኘ ከዚያ ወዲህ በመንበረ ማርቆስ ይህ መጽሐፍ መኖሩ የታወቀ ነው
  ይሆን? ወደ መንበረ ማርቆስ ከመግባቱ በፊትስ የት ነበር? ወይስ እዚያ
  ነው የመነጨው? የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ይህ መጽሐፍ ኖሮአት
  ያውቃል? ወይም ይህን መጽሐፍ ንብረቴ ነው ብላ ታውቃለች? በዐረብኛ
  የተጻፈ ብዙ መቶዎች ዓመታት ያስቆጠረ የምንጭ መጽሐፍስ አለ?
  እንዲያው በዐረብኛ ተጽፎ ከሆነ ተብሎ ከታሰበ ለማለት ነው እንጂ
  የምንጩ ጽሑፍ በግብጽ ስለመኖሩ የሚናገር ምንም አመላካች ነገር
  በመጽሐፉ ውስጥ የለም። ከግብጽ ውጪ ስለመኖሩም አመልካች ነገር
  የለም። የምችለውን ያህል ውጪያዊ ምንጮችን ከመጻሕፍትም፥ ከመረጃ
  መረብም በመፈለግ ይህን የአገራችንን ተአምረ ማርያም የሚመስል
  ወይም እንደ ምንጭ ሆኖ ሊጠሩት የሚቻል ቀራቢ ሰነድ ላገኝ
  አልቻልኩም። ተገልጠው ከተሰደሩ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን የሰነድ
  ስብስቦችም ውስጥ እንኳ ይህ ተአምር የለም።በሌላ ገጽታው ግን ተአምረ ማርያም የተተረጎመ ሳይሆን በኢትዮጵያ
  ውስጥ የተሠራ አገር በቀል መጽሐፍ መሆኑን የሚገልጡ እጅግ በርካታ
  ማስረጃዎችን በውስጡ የታቀፈ ጽሑፍ ነው። ይህ ማለት የወዲያ ታሪኮች
  ከግብጽ ከመጡት የተሰሙ ወይም የተነገሩ ሊኖሩ መቻላቸው ሳይዘነጋ
  ነው። በግብጽ ውስጥበግብጽ ውስጥ በዐረብኛ ቋንቋ ስለ ማርያም እየተጻፈ የኢትዮጵያ
  ቦታዎች እጅግ ተዘርዝረው ተጽፈዋል። እነሽሬ፥ ተከዜ፥ ዋሊ (ዋልድባ?)፥
  ሸዋ፥ ደዋሮ፥ ሙገር፥ ወግዳ፥ መርሐ ቤቴ፥ ኢፋት፥ ትግራይ፥ የረር፥
  አግዓዚ፥ ደብረ ብርሃን፥ ዳሞት፥ ጎጃም፥ አክሱም፥ መጠራ፥ ጣና፥
  ሀዘሎ፥ ደብረ ወገግ፥ ዝቋላ፥ ወዘተ፥ የኢትዮጵያ ሰዎች እነ ሠረቀ ብርሃን፥ ያሉ ገዳማትና ግልጽና የታወቁ ያልሆኑ ቦታዎችም
  ጭምር ተጠቅሰዋል። አስከናፍር፥ ዘሚካኤል፥ ዘርዑ፥ ያሬድ
  ዘርዓ ያዕቆብ፥ ዘርዓ ክርስቶስ፥ ዘርዓ ሐዋርያት፥ ወዘተ፥ በኢትዮጵያ የሆነ
  ታሪካዊ ክስተት የነደቀ እስጢፋ ዝርዝር ታሪክ ሁሉ መጽሐፉ ከውጭ ሆኖ ስለ ኢትዮጵያእየዘገበ የነበረ ሳይሆን እውስጥ ሆኖ እየተናገረ ያለ መጽሐፍ መሆኑንይፋ ያደርገዋል።የመጽሐፉ ደራሲዎች ሦስት ሆኑና ከዚህ የተነሣ መጽሐፉ እርስ በርስ
  የሚጋጩ ብዙ ነገሮች ኖረውበታል። ቅራኔዎቹና ግጭቶቹ ከመጽሐፍ
  ቅዱስ ብቻ ሳይሆን እርስ በርሱም ከታሪክም ጋር ነው። ምናልባት
  ሲጠናቀቅ አንድ ሰው ነው የደበለውና ቅራኔዎቹን ሳያስታርቅ፥
  ግጭቶቹንም ሳይከረክም በእያንዳንዱ ምዕራፍ ጅማሬና ድምዳሜ
  ተመሳሳይ አንቀጾችን መለጠፉ መጽሐፉ የአንድ ሰው እጅ እንጂ የማኅበር
  እንዳይመስል አድርጎታል። 2. የተቃለለ ክርስቶስ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምናየው ኢየሱስ
  ለመሞትና ለኃጢአታችን ስርየት ደሙን ለማፍሰስ ከማርያም ሥጋን ነስቶ
  ሰው የሆነ አምላክና ፈጣሪ ጌታና እግዚአብሔር ነው።
  በተአምረ ማርያም ውስጥ ከአምላክና ጌታ ይልቅ የተነገረውን በፍጥነት
  የሚፈጽም ቀልጣፋ ተላላኪና አገልጋይ ሆኖ ነው የቀረበው።ኢየሱስ የማርያም ልጅ
  መሆኑ ወይም ከድንግል ማርያም ሥጋን መንሳቱ እውነት ሳለ ሁሉ
  በእርሱ የተፈጠረ ፈጣሪ ነውና የማርያምም ፈጣሪ መሆኑ ጥያቄ ውስጥ
  የማይገባ እውነት ነው።ኢየሱስ የተጠየቀውን ሁሉ በቅልጥፍና
  የሚፈጽም፥ የተሳሳተ ነገር ጠይቃ እንኳ ቢሆን አሳቡን ስለ ልመናዋ ሲል
  የሚቀይር ለስላሳ ልጅ ነው። አንዳንዴ ስታስፈራራው፥ ለምሳሌ፥
  ኢየሱስን ክዶ ማርያምን ያመነን አንድ ሰው ይቅር እንዲለው በለመነችው
  ጊዜ እንደማይሆን ሲነግራት፥ ልብሷን ቀዳ፥ “እኒህን ጡቶቼን
  እቆርጣቸዋለሁ” ብላ ፍርዱን አስቀይረዋለች፤ ምዕ. 110ን ተመልከቱ።
  ኢየሱስም አሳቡን ቀይሮ ይቅር አለው። በታሪኮቹ ሁሉ፥ ከትንሣኤ በኋላ
  እንኳ፥ ኢየሱስ በሚታይባቸው ጊዜያት ሁሉ እንደ ባለ ግርማ አምላክ
  ሳይሆን እንደ ሕጻን ሆኖ ነው የሚታየው። እዚሁ ምዕራፍ 110 ላይ እንኳ
  ኢየሱስ ከዙፋኑ ተነሥቶ በደረቷ ላይ ተቀምጦ ተብሎ ተጽፎአል። በምዕ.
  90 ልጇ የተሰቀለባት አንዲት ሴት ማርያም ልጇን ከተሰቀለበት
  ካላወረደችው እሷም፥ “ልጅሽን (ኢየሱስን) ከጭንሽ እወስደዋለሁ”
  አለች። ኢየሱስ ሁሌ በማርያም ጭን ተቀምጦ የሚኖር ብቻ ሳይሆን
  ነጥቀው የሚወስዱትም ዓይነት ነው።ኢየሱስ የቀረበበት አቀራረብም ከማንነቱ አውርዶ ያቃልለዋል። በተአምረ
  ማርያም ሕጻኑ ኢየሱስም ሲራገም አይጣል ነው፤ ማርያምም ስትበቀልና
  ስትራገም የተለመደ መሆኑ በቀጣዩ ነጥብ ይታያል። በምዕ. 101 ቁ. 108፥
  ያፈለቀውን ውኃ ለአገሩ ሰዎች መራራ ይሁንባቸው የጠጣውም አይዳን
  ብሎ ባረከው ይላል። ረገመው ላለማለት ባረከው አሉት እንጂ ቃሉ
  ግልጽ እርግማን ነው። በቁ. 125 ግመሎችን ድንጋይ ሁኑ ብሎ
  አደነገያቸው። [“እስከ ዛሬ ድረስ ደንጊያ ሆኑ” ይላል። ኋላ ኢትዮጵያ
  ቆይተው ሲመለሱ ነፍስ ተዘርቶባቸው ተመልሰው ግመል ሆነው ዕቃ
  ተጭነው እንደሄዱ የተረሳ ይመስላል።] በቁ. 159 ኢየሱስ የግብጽን አገር
  ምድሩንም ሕዝቡንም መርገሙ ተጽፎአል። ይህ እዚህ መርገም
  የሚያፈስሰው ኋላ ላይ ገና አፉንም አልፈታም የተባለው ኢየሱስ ነው።
  ግጭቱን ብንተወው እንኳ ይህ የተአምረ ማርያም ፈጣሪዎች የፈጠሩት
  እንጂ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም። የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ
  ያስተማረውም ያደረገውም ጠላትን መርገም ሳይሆን መውደድ ነው። ተአምረ ማርያም እንደ ስሙ የማርያም ተአምራት
  መጽሐፍ ነው። ተአምራቱ ብዙና የተለያዩ ናቸው። ማርያም ብቻ ሳትሆን
  በስሟ የሚደረጉ ነገሮች ሁሉ ክብራቸውና ክብደታቸው እጅግ ነው።
  ለምሳሌ፥ በተአምር 12 ውስጥ 78 ሰዎች የበላ ጭራቅ በማርያም ስም
  ውኃ ስላጠጣ ሞቶ ወደ ሲዖል እንዲሄድ ጌታ ፈረደበት። ማርያም ቀርባ
  78ቱ ነፍሳትና ውኃው በሚዛን ይደረጉ ብላ ተደርጎ የውኃው ክብደት
  መዝኖ ጌታ አሳቡን ቀይሮ ወደ መንግሥቱ ያስገባዋል። በአምሳለ
  እግዚአብሔር የተፈጠሩ 78 ሰዎች ነፍሳት ከጥርኝ ውኃ መቅለላቸው
  አሳዛኝ ነው።

  ReplyDelete
 4. የዚህ መጽሐፍ ማርያም ስትፈልግ ርኅሩኅ ሳትፈልግ በቀለኛ ናት።
  ለምሳሌ፥ በምዕ 35 አንድ እስላም ዘራፊ የዘረፈው በገዳም የሚኖር ቄስ
  ወደ ማርያም ስዕል ሄዶ ተማጸነ፤ ጸልዮ ሲወጣ ዘራፊው ወድቆ እጁ
  ተሰብሮ አጥንቱ ገጦ ወጥቶ አየው። እስላሙ ይቅርታ ሲጠይቀው
  ሽማግሌው ማርያም ይቅር ብትልህም ባትልህም እንደወደደች አለው፤
  ይህ ሰው ቄስ ሆኖ ስለ ይቅርታ አያውቅም። ቄስ ነው እንጂ ክርስቲያን
  አይደለም ማለት ነው። ክርስቲያን ቢሆን ክርስቶስን ሊመስል ይሞክር
  ነበር። ማርያምም በስዕል አድርጋ በቄሱ ላይ ደፍሯልና ይቅርታ
  አይገባውም አለች። ስለዚህ እስላሙ ወንጌልም ሳይሰማ፥ ይቅርያም
  ሳያገኝ ሞተ። በ33፥39 ላይ ማርያም የይቅርታ ሳጥን ተብላለች እዚህ ግን
  ተቃራኒ ናት። በቀለኛና ባህርይዋ በሁኔታ ላይ የሚደገፍ ነው።
  በምዕ. 39ም በቀለኛ ማርያም ትታያለች። ሌላ እስላም ዘራፊ ገዳም ዘርፎ
  ሲሄድ ሰዎች አግኝተው ገደሉት፤ ከቤተ ሰቡ 10 ሰዎች ከዘመዶቹ 18
  ገደሉና የተዘረፈውን አምጥተው ለገዳሙ ሲመልሱ በቁ. 35፥
  “ልቡናችንን እርሱን ለመግደል ያነሣሳችን ማርያም እንደሆነች ፈጥነን
  አወቅን” አሉ። ቁጥር 26 ላይ ለመግደል ያነሣሳቸውን “በበረሃ ያለው
  መጣብን” ነው ያሉትና ማርያምና በበረሃ ያለው ያሉት እነዚህ ሁለቱ
  አንድ ናቸው ማለት ነው። ማርያም ሰዎችን አስነሥታ ታስፈጃለች።
  የሚያሳዝነው መነኮሳቱም በዚህ ነገር ፍጹም ደስታ ተደሰቱ። ኃጢአተኛ
  ሲድን ሳይሆን ሲሞት የሚደሰቱ መነኮሳት ወንጌልን ያውቃሉ ይባላል?
  በምዕ. 98 ከአንድ ሽማግሌ አስተማሪያቸው ጋር ፍልሰቷን ለማክበር
  ሲሄዱ አስተማሪያቸውን ወደ ገደል የጣሉ 40 ተማሪዎች በእሳት ጦር
  እየወጋ የሚገድላቸው መልአከ ሞት አዘዘችና በአንዴ አለቁና
  ሽማግሌውን ግን ወደ በዓሏ መከበሪያ አደረሰችው። በምዕ. 15 አንድ
  ግመል ጫኝን ጎድኑን ወግታ ስትገድለው ትታያለች። ደራሲዎቹ
  ማርያምን በቀለኛ ሲያደርጓት እርሷን ለማግነን ሲሉ አስቀያሚ ቀለም
  እየቀቧት መሆናቸውን እንኳ አያውቁም። ወይስ አውቀው ነው አያደረጉ
  ያሉት?
  የተአምረ ማርያሟ ማርያም በቀለኛ ብቻ ሳትሆን ቀናተኛም ናት። በምዕ.
  92 የአንድ ንጉሥን ወጣት ልጅ እርሱ ከሚወዳት የበለጠ እርሷ
  እንደምትወደውና እንደምትቀናበት፥ ሚስት ሳያገባ እንዲኖርም
  እንደመከረችውና በእጇ ስዕሏን እንደሰጠችው ተጽፎአል። ንግግራቸው
  የሁለት ፍቅረኞች ይመስላል። ልጁ ሲሞትም ብዙ መላእክት እና ደም
  ግባቷ ያማረች ማርያም መጥተው በሰው ሁሉ እየታዩ ይዛው ሄደች።
  በእግዚአብሔር የተደነገገ ጋብቻ የተናቀበትና የተዋረደበት እንደዚህ ያለ
  መጽሐፍ አላነበብኩም። ያላገቡ እንዳያገቡና ድንግልናቸውን ለማርያም
  ስዕለት አድርገው እንዲሰጡ የሚበረታቱበት ብቻ ሳይሆን የተጋቡ እንኳ
  ከተቀደሰ መኝታ የሚከለከሉበት ነው።

  ReplyDelete
 5. በምዕ. 84 ሰንበትን የሻረ አንድ አገልጋይ ድዳ ሆነ። ጌታው ወደ ማርያም
  ጸለየና ፈወሰችው። የተሻረው ሰንበት ነው። የምትጠየቀው ደግሞ
  ማርያም ከሆነች እርሷ የሰንበት ባለቤት ናት ማለት ይመስላል። በምዕ.
  110 እግዚአብሔርን ክዶ ማርያምን ግን አልክድም ያለ ሰው በማርያም
  ኢየሱስን አስፈራሪነት ይቅርታ ሲያገኝ ይታያል። እግዚአብሔርን ክዶ
  ማርያምን ማምለክ ክቡር ቦታ አግኝቶአል። ጌታ እግዚአብሔርን ክዶ
  ማርያምን አለመካድ ወይም ማምለክና ማንን የማግነን ጉዳይ ነው? አንዳንድ ሰዎች ማርያምን እንደሚያከብሩ እንጂ እንደማያመልኩ
  የሚናገሩት የቃል ጨዋታ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን እየጠሉ ራዕየ
  ማርያምን በቃል እየሸመደዱ “እንወዳታለን እንጂ፥ እናከብራታለን፥ የጸጋ
  ስግደት እናቀርብላታለን እንጂ . . . አናመልካትም” ማለት የራስ ድለላ
  ነው። እንዲህ ከላይ እንደጠቀስኳቸው ያሉቱ ምዕራፎች የሚናገሩት
  እየተከበረች ሳይሆን እግዚአብሔርን ተክታ እየተመለከች መሆኗን ነው።
  ደግሞ ማክበርስ ከሆነ መከበር የሚገባው ማን ብቻ ነው? ይህ እኮ
  አንድን ባለሙያ ሰው ለማድነቅና ለማመስገን ከስዕሎቹ ወይም ከቅርጾቹ
  አንዱ ፊት ሄጄ ለሥራው ውጤት ምስጋናና ውዳሴን ብደረድር
  እንደማለት ነው። ይህ እንዲህ በሚለው በሮሜ 1፥25 ቃል ፈጽሞበፈጣሪም ፈንታ የተፈጠረውን ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው፤ ማክበር ወይም ማምለክ የቃል ጉዳይአይደለም። መስተዋል ያለበት ተግባሩና ድርጊቱ ነው። ለእግዚአብሔር
  ብቻ እንጂ ለሌላ ለማንም መደረግ የሌለበትን ነገር ለሌላ ማድረግ፤
  የተወገዘ ነው፤ ተአምራት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ጊዜያት የተደረጉ ሲሆን
  የተአምራት ዋነኛ ግብ የእግዚአብሔር ክብር ነው። በተአምረ ማርያም
  በተደረጉት ተአምራት ግን ክብር እግዚአብሔር ሲሰጥ ከቶም
  አይታይም። እያንዳንዱ ምዕራፍ ሲጀምር የእመቤታችን ተአምር . . .
  ብሎ ይጀምርና ሲጨርስ በረከቷና . . . ይደርብን ይላል። ሲጀምር
  ማርያም፥ ሲጨርስ ማርያም። ክብር ለማርያም እንጂ ለእግዚአብሔር
  የሚባል ቋንቋ የለም። በምዕ. 28 ጌታ ለሐዋርያት በገነት ተገለጠላቸው ይላል። በአካል ገነት
  ገብተው ማለት ነው። በምዕ. 54 የአንድ ደብር አለቃን ወደ ሰማይ
  አሳረገችው። ሳይሞቱ የሚነጠቁበትም ነው። በ77 የለማኙን ፊት በዳቦ
  የገመሰው ሰው ሞቶ ሲዖል ሄደ። ማርያም፥ “የለም ይህ የኔ ነው” ብላ
  ወደ ሲዖል እንዳይወርድ ተከራከረች። ዳቦውን የተቀበለው ፊቱ የተገመሰ
  ለማኝ ሄዶ መሰከረና ሰውየው ሲዖል መግባት ቀርቶለት ነፍሱ
  ተመለሰችና ከሞት ዳነ። ጌታ እየተሳሳተ ወይም እየተጸጸተ አሳቡን
  የሚቀይር ወይም የሰው ምስክር የሚያስፈልገው የሰው ዳኛ መምሰሉም
  መታለፍ የሌለበት ስሕተት ሆኖ ሳለ ለማኙ በምን አካል ወደ ዙፋን ቀርቦ
  መሰከረ? በአካል ወይስ ያለአካል? በምዕ. 30 ካህን ዘራፊዎችን ግደሉ አባለ ዘራቸውንም ስለቧቸው ብሎ
  ሲያዝ ይታያል። ለነገሩ ከተገደሉ በኋላ ብልት ዋጋ የለውም፤ ግን
  የተደረገው ሁሉ ተደርጎ ይህ ሁሉ በማርያም አማላጅነት ተደረገ ብሎ ይደመድማል። የተአምረ ማርያሟ ማርያም አባለ ዝርም እንዲሰለብ
  ታደርጋለች።
  በምዕ. 85 ከገዛ ሚስቱ ጋር መተኛቱ እንደ ኃጢአት ሆኖበት አባለ ዘሩን
  የቆረጠ ሰው ይገኛል። ይህ ሰው ከደም ፍሰት የተነሣ ሞቶ መንግሥተ
  ሰማያት ሄዶ በማርያም ትእዛዝ ነፍሱ ወደ ሥጋዋ ተመለሰችና በሕይወት
  ኖረ። መንግሥተ ሰማያት ከገባ በኋላ ነፍሱን ብትመልስም ቅሉ ብልቱን
  ግን አልቀጠለችለትም። የሽንት መሽኛ ቀዳዳ ብቻ ተደርጎለት መንኩሶ
  ኖረ። በተአምረ ማርያም ትዳር የቀለለ ብቻ ሳይሆን የረከሰ ነገር ነው።
  ከመነኮሰች በኋላ በፈቃደ ሥጋ ተሸንፋ ከገዳም የወጣችና ያገባች ሴት
  በመካንነት ተቀጥታ ወደ ገዳሟ ተመለሰች። ሌሎችም ይህም የመሰሉ
  ታሪኮች ታጭቀውበታል።

  ReplyDelete
 6. ያፈነገጠ ተፈጥሮ። በተአምረ ማርያም ውስጥ የበዙ ከተፈጥሮ
  ሥርዓት ጋር የማይስማሙና የሚቃረኑ ነገሮች ይነበባሉ። በምዕ. 70
  አንድ ሰው ሥጋ ወደሙን ከወሰደ በኋላ አውጥቶ በንብ ቀፎው ውስጥ
  አደረገው። በኋላ ሥጋ ወደሙ ወደ ብርሃንና የማርያም ስዕልነት
  ተለወጠ።በምዕ. 59 አንድ የቤተ ክርስቲያን ጠባቂ አንድ ቀን ከራት በኋላ የሥጋ
  ድቀት አግኝቶት ዝሙት ፈጸመ። በመልአክ ተነክቶ የሴት መርገም
  ደረሰበትና ከዚያ በኋላ ማርያም ያደረገችበትን ይህን ነገር አገር ላገር
  እየተናገረ በመዞር ኖረ። መልአክ ቢነካውም ይህን ያደረገችው ማርያም ናት። ይህች የዚህ መጽሐፍ ማርያም ምንም ነገር ማድረግ ትችላለች።
  ሰብዓዊ ተፈጥሮንም ትቀይራለች። የወር አበባ ካየ ማኅጸን ተሠራለት
  ማለት ነው። ማመንዘሩ ኃጢአት ሳለ ቅጣቱ ሴት መደረግ ወይም እንደ
  ሴት መደረግ ከሆነ ይህች ማርያም ሴትነቷንም ትጠላዋለች ማለት
  ይሆን?
  በምዕ. 107 ብዙ ኃጢአት ፈጽማ ተስፋ የቆረጠች ተቅበዝባዥ የሆነች
  ሴት ታሪክ ይገኛል። ይህች ሴት ወደ በረሃ ሂዳ ጊንጥ አገኘችና
  ዋጠችው። መርዙ በሰውነቷ ተሰራጭቶ ስትሰቃይ የማርያም ስዕል
  መጥቶላት በዚያ ሆዷን እያሸች ማርያምን ለመነች። ማርያም ወደ ቄስ
  ልካት ለዚያ ቄስ ተናዝዛ አምጣ ወለደች። የወለደችው ሕጻንን ሳይሆን
  40 ትልልቅና ትንንሽ ጊንጦችን ነው። ወደ አፍ የገባ ወደ እዳሪ
  እንደሚወጣ ጌታ የተናገረው ስሕተት ተደርጎ ወደ ማሕጸን ገብቶ በ40
  ተባዝቶ ወጣ! እንደዚህ ትምህርት ከሆነ ሴቶች ላም እንወልዳለን ብለው
  በመፍራት ወተት መጠጣት ማቆም አለባቸው። ወይም አስር ዶሮ
  እንወልዳለን ብለው እንቁላል መብላት መተው ይኖርባቸዋል። ደግሞ
  ሁሉም እንደየወገኑ እንዲዋለድ በፍጥረት መጀመሪያ የተነገረውም
  ተሰረዘና ሴት ጊንጥ ወለደች። ለተአምሩ ትክክልነት ሲባል መጽሐፍ
  ቅዱስ መስተካከል አለበት።
  ጊንጥ ብቻ ሳይሆን ሌላም የከፋ ወሊድ ታሪክ አለ። በምዕ. 55 የሌላ ሴት
  ባል የቀማች አንዲት ሴትና ሌላኛዋ ሴት በማርያም ታቦት ፊት
  እውነተኞች መሆናቸውን ይማማላሉ። የቀማችው ሴት ኃጢአተኛ
  ኖራለችና እርጉዝም ነበረችና ቆይታ ወለደች። የወለደችው ሕጻን ሳይሆን
  በትል የተሞሉ ሁለት የላም፥ ሁለት የበግ ቀንዶችን ነው። ይህች ሴት
  እብድ ሆና እየዞረች ይህንኑም ያደረገችው ማርያም መሆኗን እየተናገረች
  ቆይታ ሞተች። ቀንዶቹ ደግሞ ከማኅጸን እንደወጡ እንኳ አልተቀበሩም።
  በማርያም ቤተ ክርስቲያን መስኮቶች ተሰክተው ይኖራሉ። የትኛዋ ቤተ
  ክርስቲያን እንደሆነች እንኳ ቢናገሩ ጉዱ ይታይ ነበር።ይኼ ሁሉ የተደረተባት ድሪቶ ማርያምን እንደሚያሳዝናት የታወቀ ነው።
  በእውነቱ የተአምረ ማርያሟ ማርያም ደራሲዎቹ በመልካቸው
  እንደምሳሌያቸው የፈጠሯት እንጂ የመጽሐፍ ቅዱሷ ማርያም ከቶም
  አይደለችም። እምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን
  ከተባለለት ከኢየሱስ ሰዎች ዓይናቸውን እንዲያነሡ፥ እንዲያውም
  ከቶውኑ እንዳያዩት ተብሎ የተፈጠረችና ማርያም ተብላ የተሰየመች ሴት
  ናት እንጂ የመጽሐፍ ቅዱሷ ማርያም ዛሬም ብትጠየቅ ያኔ እንዳለችው፥
  የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ የምትል ናት።

  ReplyDelete
 7. በተአምር 3 ማርያምን ለመቅበር ሲሄዱ ሐዋርያት ሁሉ ጥለዋት ተበተኑ
  ከዮሐንስ በቀር ይላል። ልክ ጌታ ሲያዝ እርቃኑን በነጠላ ከሸፈነው
  ዮሐንስ በቀር ሁሉ እንደሸሹ ይህንንም የጻፈው ይህ ደቀ መዝሙር
  መሆኑ እንደተጻፈ እዚህም የፍልሰቱን መጽሐፍ የጻፈ እርሱ መሆኑ
  ተጽፎአል። የዚህ ምዕራፍ ግጭት ከምዕ. 6 ጋር ነው። በተአምር 3
  ጥለዋት ተበተኑ ሲል በተአምር 6 ፈጽሞ እንዳልጣሏት፣ ግን ገንዘው፥
  ታቅፈው፥ ተሸክመው እጅ ነስተው በጌቴሴማኒ ቀበሯት እንጂ
  አልጣሏትም ይላል። የቱ ነው ትክክል? ምዕ. 3 ወይስ 6? ለነገሩ የተለያዩ
  ሰዎች ያዋጡት መጽሐፍ ስለሆነ እንዲህ እርስ በርሱ ቢጋጭ
  አያስገርምም።
  በምዕ. 10 ኢየሱስ በዋሻ ውስጥ መወለዱና በጨርቅ መጠቅለሉ ሳይሆን
  የበለስ ቅጠል መልበሱ፥ በምዕ. 11 ደግሞ በጨርቅ መጠቅለሉ ተጽፎአል።
  በመንገድ መካከል ተወለደም ይላል። ይህ የራስ ከራስ ግጭት ነው።
  መልአክ ሄዶ ለሰብዓ ሰገል እንደነገራቸው፥ ሰብዓ ሰገል ደግሞ ሽቱም
  አምጥተውለት እንደነበር ተጽፎአል። እነዚህ ሁሉ የተጻፈ ታሪክን
  የሚያፋልሱ ናቸው።
  ከንጉሥ ልጇ ደም በፈሰሰ ደሟ እኛን ንጹሐን አድርጋ . . . ይላል ምዕ.
  12፥54። የማን ደም ነው የፈሰሰ? የማን ደም ነው ያዳነ? የማርያም ደም
  ያዳነ በሆነማ ኖሮ ክርስቶስ ምነው በመስቀል መዋሉ? ቃሉ በኤፌ. 2፥13
  የሚለው አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ
  ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል ነው እንጂ ከልጇ በፈሰሰው
  በማርያም ደም ቀርባችኋል አይልም። ጳውሎስ ኤፌሶንን ሲጽፍ ማርያም
  ሞታ ወይም ተአምረ ማርያም እንደሚለው አርጋ ስለነበረ ጳውሎስ
  ይህንን ማወቅ ነበረበት። ቆላ. 1፥19 በመስቀሉ ደም ሰላም ማድረጉን
  ይናገራል፤ ሌላ ደም አይናገርም። ዕብ. 9 በሙሉው ይህንን ደም
  ይናገራል እንጂ የማርያም ደም አይልም። 1ጴጥ. 1 የተዋጀንበትን ክቡር
  ደም የክርስቶስ ደም ይለዋል እንጂ የማርያም አይለውም።በተአምር 32 ስለ አንዲት ዘማዊት ይናገራል። እንደ ሙሴ ሕግ
  እንድትወገር እንደተፈረደ ይናገራል ደግሞም ቤተ መቅደስ ውስጥ ገብታ
  ይላልና ደግሞም በአዲስ ኪዳን ኃጢአተኛን በድንጋይ መውገር የለምና
  ይህ የብሉይ ኪዳን ዘመን ይመስላል። እንዳይባል ደግሞ ዘማዊቷ
  የማርያምን ስዕል አግኝታ ለመነች ይላል። መልእክቱ ወደ ስዕል ለምኖ
  መፍትሔ ማግኘት ቢሆንም በመቅደስ ውስጥ የማርያም ስዕል ሊኖር
  አይችልም። የቤተ ክርስቲያን መቅደስ ነው ከተባለ ደግሞ በቤተ ክርስቲያን ወይም በክርስትና ዘመን ኃጢአተኛን መውገር ከየት የመጣ
  ፍርድ ነው? እርስ በራሱ የተማታ ታሪክ ነው።
  ሰይጣን መንፈስ ነው እንጂ ስጋዊ አካል አይደለም። በምዕራፍ 34
  ሰይጣንን ማርያም በጥፊ አጩላው ልቡናውን ሲስት ይታያል። በምዕራፍ
  51 ደግሞ የመነኮሳትን ምድጃ ስላፈረሰ አንድ ሰይጣን ተጽፎአል።
  መነኮሳቱ ወደ ማርያም ጮኹና ለ12 ዓመታት ባሪያ ሆኖ
  እንዲያገለግላቸው ምድጃቸውን ያፈረሰውን ያንኑ ሰይጣን ሸለመቻቸው።
  እነዚህ መነኮሳት ሰይጣንን ተቃወሙት የሚለውን ቃል አይታዘዙም
  ማለት ነው። ወይም ቃሉን ጨርሶውኑ አያውቁም ማለት ነው። ሳያውቁ
  ግን መነኩሴዎች ናቸው። ማዕድ ቤት አስገብተው እየፈጨ፥ እያቦካ፥
  እየጋገረ ዓሳ ነባሪ እያጠመደ ከመርከብ ጋር እየተሸከመ አምጥቶ መርከቡ
  ውስጥ የነበሩትን ሰዎች የሚያስመነኩስ ይህ አገልግሎት ከማዕድ ቤት
  ሥራ ያለፈ ነው!በምዕ. 98 ስለ ይሁዳ እግረ መንገድም ቢሆን የተነገረው ጌታን ሽጦ
  እናቱን አግብቶ አባቱን መግደሉ ተጽፎአል። ቅደም ተከተሉ እንደዚያ
  ከሆነ እናቱን አግብቶ አባቱን የገደለው ጌታን ከሸጠ በኋላ ነው ማለት
  ነው። በትክክል የሞተው መቼ እንደሆነ ባይታወቅም ተጸጽቶ ወዲያው
  ሄዶ ነው ታንቆ የሞተውና (ማቴ. 27፥1-10) ጋብቻውም ግድያውም
  በሰዓቶች ውስጥ ምናልባት በደቂቃዎች መሆን አለበት። ያለዚያ እናቱን
  አግብቶ አባቱን የገደለውንና የአይሁድ ሕግ ዝም ያለውን ሰው ነው ጌታ
  ከሐዋርያቱ ክልል ያስገባው።
  በምዕ. 121 ኢየሱስን በ8 ዓመቱ በጎች እንዲጠብቅ ላከችው ይልና ወደ
  ደብረ ዘይት መጥቶ በጎቹን አሰማራ ይላል። ለማያውቅ ሰው ልክ እሰፈር
  ዳርቻ በጎቹን ወስዶ የመሰገ ይመስላል። የሚኖሩት ናዝሬት በጎች
  የሚጠብቀው ደግሞ ደብረ ዘይት መሆኑን እንደገና እናስተውል። ደብረ
  ዘይት እኮ ከናዝሬት የ105 ኪሎ ሜትር ሩቅ አገር ነው። በኛ አገር ከአዲስ
  አበባ ናዝሬት ማለት ነው። መልክዓ ምድሩን ለማያውቁና ለማይጠይቁ ወይም የተባለውን ሁሉ እውነት ነው ብለው ለሚቀበሉ አድማጮች
  የተጻፈ በመሆኑ ደራሲዎቹ ይህን እና ይህን የመሰሉትን ግጭቶች
  ለመመርመር ሙከራ አላደረጉም።

  ReplyDelete
 8. ተአምረ ማርያምን ማሔስን ካላቆሙት በቀር መቆም አይችልም።
  ምክንያቱም እያንዳንዱ ምዕራፍ ከራሱ ከመጽሐፉ ሌላ ምዕራፍ፥
  ከታሪክና ከእውነት፥ ከአእምሮና ከተፈጥሮ፥ በተለይም ከመጽሐፍ ቅዱስ
  ጋር በምሬት የሚጣላ መጽሐፍ ነው።ዘላለም መንግሥቱ the above article taken ..............ቁጥር Ŧ Ɗ - ሰኔ ፪ሺህ ፬ ዓመተ ምሕረት JUNE 2012ዕዝራ ፥

  ReplyDelete
 9. http://good-amharic-books.com/images/PDFs/enoch.pdfተአምረ ማርያም ምንድርነው?
  ተአምረ ማርያም የተባለው መጽሐፍ እንደ ስያሜው ሁሉ ማርያም
  እንዳደረገቻቸው የሚነገሩ የብዙ ተአምራት መድብል ነው። ከተአምራቱ
  በጣም ጥቂቱን ሕጻኑ ኢየሱስ ያደረጋቸው ናቸው አንዳንዱ ምዕራፍ ምንም
  ተአምርነት የሌለበት የተደረጉ ነገሮች የተዘገቡበት ዘገባ ቢሆኑም
  በእያንዳንዱና በሁሉም ምዕራፎች መግቢያ ወይም አናት ላይ ማርያም
  ያደረገቻቸው ተአምራት እንደሆኑ በቀይ ቀለም እየተጻፈ በአንቀጽ
  ተቀምጦአል። ተአምር ባልሆኑት ላይ በአናቱ ላይ የማርያም ተአምር
  መሆኑን መጻፉ የግድ መሆን ስላለበት የተደረገ ይመስላል። ለምሳሌ፥
  ሁለተኛው ተአምር ወይም ምዕራፍ ማርያም ስለ መጸነሷና ስለ ልደቷ
  የተነገረ ሲሆን ያው የግዴታ ልማድ ሆኖ ክብርት እመቤታችን
  ያደረገችው ተአምር ተብሎ ተጽፎአል።የመጽሐፉ አሳታሚና ባለቤት ማን ነው?
  ይህኛውን (እኔ ያነበብኩትን) እትም ያተመው ተስፋ ገብረ ሥላሴ
  ማተሚያ ቤት ሲሆን አሳታሚው አልተጻፈም። ከመግቢያው
  እንደሚነበበው ግን አሳታሚው ተስፋ ገብረ ሥላሴ ዘብሔረ ቡልጋ
  ነው። ይህ መጽሐፍ በኢኦተቤክ ሰፊ ተቀባይነት ያለው የነገረ ማርያም
  ሰነድ መሆኑ አጠያያቂ ባይሆንም በማን ቡራኬ መታተሙ አልተጻፈም።
  በበርካታ የኢኦተቤክ መጽሐፎች እንደሚታየውም የሊቀ ጳጳስ ምስል እና
  መልእክትም የለበትም። ስለዚህም አይቶ፥ መርምሮ አጽድቆ ለአንባቢ
  የተገባ ነው ብሎ ያሳለፈ ተጠያቂ አካል የለውም ማለት ነው። በእውኑ
  የኢኦተቤክ ይህን መጽሐፍ እንደ ቅዱስ መጽሐፍ አድርጋ ትቀበለዋለች?
  መቼም ከተቀበለችው በቂ የሆነ ታሪካዊ ምንጭ ያለው ሆኖ መገኘት
  አለበት? ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋርም መጋጨት የለበትም። ምክንያቱም
  ማንም ክርስቲያናዊ መጽሐፍ አስተምህሮአዊ ተደርጎ ከተወሰደ ምንጩ
  መጽሐፍ ቅዱስ መሆን አለበት። ታሪካዊ ከሆነ ደግሞ ታሪካዊ ብቻ ነውና
  ሥልጣን ያለው መጽሐፍ መሆን የለበትም። ደግሞም ከዋናው
  ክርስቲያናዊ መጽሐፍ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ተያይቶ ሊቀበሉት ወይም
  ሊጥሉት የተፈቀደ መሆን የተገባው ነው። የኢኦተቤክ ይህን መጽሐፍ የኔ
  ብላ ትቀበለው ወይም አትቀበለው እንደሆነም ግልጽ አይደለም። በአንድ
  ድረ ገጽ ላይ በቅርብ ያነበብኩት ሁለቱ ሲኖዶሶች ከሚነጋገሩባቸው
  ነጥቦች አንዱ ይህ መጽሐፍ እንደሆነም ነው።
  1ለምሳሌ፥ ከ1924ቱ እትም) ተጽፎ ከኋለኞቹ እትሞች (ለምሳሌ፥
  ከ1989ኙ እትም) እንደቀረ በማውሳት ይህ የሆነው ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር
  በግልጽ በመጋጨቱ ምክንያት እንደሆነ ታትቶ ቀርቦአል። ለውጥ
  የሌለበት ለማስመሰል ግን ‘በድጋሚ የታተመ’ እየተባለ መቅረቡም
  ተወስቶአል።የተአምራቱ ቁጥራቸውም ከአንዱ እትም ወደ ሌላው ይለያያል ይባላል።
  እኔ ባነበብኩት መጽሐፍ (የŦ ŹƃƂƆ ዓመተ ምሕረት እትም) ተአምራቱ
  ወይም ምዕራፎቹ 123 ናቸው። አንዳንድ ተአምራት ወይም ምዕራፎች
  በአንዱ የመጽሐፉ እትም ይገኙና በሌላው እትም የማይገኙ ከሆኑ
  መጠኑና ይዘቱ ከእትም እትም ይለያያል ማለት ነው።በአንድ ድረ ገጽ ስለ ተአምረ ማርያም በተጻፈ
  አጭር መልእክት ላይ ምላሽ ከሰጡት ሰዎች አንዱ ተአምር 19 ላይ ስለ
  መሐመድ የተጻፈ ነገር እንዳለበት ጠቅሶአል።ማርያም ሙታንን እያስነሳች ለሰዎች ስታሳይ ነው የተጻፈው እንጂ ይህ
  ስለሌለ በድረ ገጹ የተጻፈው ትክክል ከሆነ ምዕራፎቹ ተሸጋሽገው፥
  ታጥፈው፥ ወይ ተሰርዘው ይሆናል? ምናልባት አንዳንዱ እትም ምዕራፎቹ
  እየተመረጡና የሚያጠያይቁት እየተነቀሱ የታተመ ሊሆን ይችላል፤ ግን
  ከላይ እንደተጠቀሰው ‘በድጋሚ የታተመ’ እየተባለ ከውስጡ እየተገመሰ
  ከቀረ ይህ ስነ ጽሑፋዊ እብለትና አንባቢን መደለል ነው።ወይስ ይሀኛው ክፍል የውጣው የሙስሊም ጂሃዲስቶችን ተፈርቶ ነው?ለፍርሃት ሲባል መጽሃፍ ይሰረዛል???

  ReplyDelete
  Replies
  1. አቤት እንዴት ማስረጃ አምጥተህ ሞተኅል? የጴንጤ ማስረጃ። ታዲያ ከተስማሙህ ለምን ጠቅልለህ እነሱው ጋር አትገባም?

   Delete
  2. taken from....http://wongelforall.files.wordpress.com/2011/11/the-fact-of-the-movement-in-the-church.pdf
   .. የሚያስተቹ የሚባሉ ነገሮችን መናፍቃኑ ደጋግመው ጽፈዋቸዋል መጻህፍት አውጥተውባቸዋል ተሳልቀውባቸዋል:: ሆኖም ግን መናፍቃኑ
   የጻፏቸው ጽሑፎች ሁሉ እውነተኞች ናቸው ማለት አይደለም:: እነርሱ የእምነት መጉደል ስላለባቸው እነርሱ በእምነታቸው መጉደል
   ምክነያት የሚጠራጠሩት ሁሉ እንደ ስህተት ቆጥረው ኦርቶዶክስ ውስጥ ይህ ስህተት አለ እያሉ ይጽፋሉ:: እነርሱ የሚተቹት
   የሚታመነውን ጭምር እንደሆነ ልብ ልንል ይገባል:: በተጨማሪም በቤተ ክርስቲያን ለትችት ይዳርጋሉ የሚባሉ ጉዳዮች የእምነት ነገሮች
   አለመሆናቸውን ልብ ልንል ይገባል::
   ቤተ ክርስቲያን እንደ እምነት ተቋም በእምነትዋና በቀኖናዋ በሃይማኖታዊ ትምህርቷ ነቀፌታ የለባትም:: የምታምነው የአበውን
   ሃይማኖት መመሪያዋ የአምላክ ቃል የምትኖረውም መንፈሳዊውን ህይወት ነው:: ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን ለብዙ ዘመናት ተቀናቃኝ
   ስላልነበራትና ቤተ ክርስቲያንን የሚተች ሰው ስላልነበር ሊቃውንቱ ሳያውቁ ወይም በመዘናጋታቸው ምክነያት ብዙ ሊያስተቹ የሚችሉ
   ነገሮች እና እውነታነት የሌላቸው ጽሑፎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዲፈጠሩ ሆነዋል:: እነዚህ እውነትነት የሌላቸው ነገሮች መሰረታዊ ዶግማውንና ቀኖናውን አይንኩት እንጂ በልዩ ልዩ ጉዳዮችና በእምነት ላይ የሚንጸባረቁ ሆነዋል::ኢትዮጵያ ውስጥ እስከ
   1950 ዎቹ ድረስ ሲኖዶስ አለመኖሩ ጠንከር ብሎ እነዚህን ጉዳዮች የሚያይ አካል እንዳይኖር አድርጓል::
   በዘመናዊ መልእክ ስለቤተ ክርስቲያን እምነትና ስርዓት ግልጽ መጽሓፍትን የጻፉ እንደ አቡነ ጎርጎሪዎስ ካልእ አይነት አባቶች የቤተ
   ክርስቲያን እምነት የሆነውንና ያልሆነውን ዶግማውንና ቀኖናውን ትውፊቱንና ልማዱን እንዲሁም ባህሉን አብራርተው
   አስቀምጠውልናል:: እኒህ አባት አሁን አስተያየት ለሚሰጡ ወገኖች መነሻ ናቸው:: የሃይማኖታችን ገደብና ድንበር ልንረዳው በምንችል
   ቋንቋ ጽፈውልናልና:: በዘመናች ያሉ ዲ/ን ዳንኤል ክብረትን የመሳሰሉ ወንድሞች ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን ሊያስተቹ የሚችሉ ጽሑፎች
   እንዴት ሊጻፉ እንደቻሉ በጥናት መልክ ጽሑፎችን አቅርበዋል::
   http://wongelforall.files.wordpress.com/2011/11/awalid_metsahift.pdf ገጽ 18 ቤተ ክርስቲያን በዘመንዋ ብዙ መጻህፍትን ጽፋ አሳልፋለች:: ምንም እንኳን አብዛኛው መጻህፍቱ ተዘርፈው ወደ አውሮፓ ቢሄዱም
   ሌሎችም ደግሞ በመቃጠል በእድሜ መርዘም ምክነያት በመበላሸት የጠፉ ቢሆንም በአንድ መረጃ እንደተመለከትሁት በኢትዮጵያ
   ውስጥ ወደ ሁለት መቶ ሺ /200 000/ የብራና መጻህፍት እንደተጻፉ /እንደተባዙ/ ይገመታል:: ከእነዚህ መጻህፍት ውስጥ ትልቁን
   ብዛት የሚይዙት አዋልድ መጻህፍቶቻችን ናቸው:: ብዙ መጻህፍት ከውጭ ሃገር ክርስቲያኖች ወደ ግእዝ ቋንቋ የተተረጎሙ ሲሆኑ
   ሌሎች ደግሞ በኢትዮጵያዊያን ሊቃውንት ተጽፈው የተባዙ ናቸው:: ታዲያ እነዚህ መጻህፍት ሲጻፉ የሚገለበጡት በእጅ ጽሁፍ ነው::
   ኮፒዎችም የሚጻፉት እና የሚባዙት በተለያዩ ግለሰቦች ነው:: ሁሉም ጸሓፊያን መንፈሳዊ መሆናቸውና የቤተ ክርስቲያን እውቀት
   እንደነበራቸው ማረጋገጥ አይቻልም:: ይህን ልንል የሚያስችለን ደግሞ አንዳንድ ቀላል ሊባሉ የሚችሉ ስህተቶችን ጭምር ስለምናገኝ
   ነው::
   እንደ ዲያቆን ዳንኤል ጥናት ከሆነ ግን አብዛኛዎቹ ለትችት የሚዳርጉ ነገሮችን መጻህፍቶቻችን ውስጥ ያስገቧቸው መናፍቃን ናቸው::
   ቤተ ክርስቲያን በልዩ ልዩ መልክ መጉዳት ቢፈልጉም እንደፈለጉት ስላልሆነላቸው በቤተ ክርስቲያን የማይታመኑ ጽሑፎችን በቤተ
   ክርስቲያን መጻህፍት ውስጥ ማስገባት መረጡ ይላል:: ቤተ ክርስቲያን የማታምናቸው እና የማትቀበላቸው ከታሪክ እና ከጊዜ ከቦታ ጋር
   የማይጣጣሙ ጽሑፎችን በማስቀመጥ ቤተ ክርስቲያን እንድትጠላ እንድትነቀፍና እንድትተች ምክነያት ሆኑ:: የዚህ ደግሞ ዓላማው
   ኦርቶዶክሳዊው ምእመን በጽሑፎቹ አማካኝነት ሃይማኖቱን እንዲጠላና እንዲንቅ ከእምነትም እንዲያፈነግጥ ነው:: አንዳንድ በስህተት
   ቤተ ክርስቲያን ገበተው ቤተ ክርስቲያንን ያስተቻሉ ከምንላቸው ጽሑፎች ውስጥ የሚከተሉትን ለምሳሌ እንመልከት::
   1. ሰዶምና ገሞራን የአቃጠሏት ሐዋርያት ናቸው /በሎጥ ዘመን ነበሩ
   2. የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ድንግል ማርያም የሙሴ እህት ናት
   3. ድንግል ማርያም የይስሓቅን ልጅ ያእቆብን በላባ ቤት ውስጥ እያለ ረዳችው
   ሌሎችንም ማቅረብ ቢቻልም ለጊዜው አስፈላጊ አይደለም:: አንድ ኦርቶዶክሳዊ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት የሚያውቅና የሚቀበል
   ጸሓፊ ከላይ የተገለጹትን ሊጽፍ አይችልም:: የዳንኤል ጥናት እንዳመለከተው መናፍቃን ያስገቧቸው ናቸው አለበለዚያ ደግሞ
   አላዋቂዎች የጨመሯቸው ናቸው:: ሆኖም ሊቃውንቱ እያወቁቸው እና የማያምኑባቸው ሆነው ሳለ ለምን ለማስተካከል አልደፈሩም?
   ይስተካከሉ የሚልንስ አካል እንደ ጥፋተኛ ማየት ይገባን ይሆን? የጎደለውን መሙላት የተጣመመውን ማቃናትን ቤተ ክርስቲያን
   ልታስብበት እንደሚገባ ሌሎች ጸሓፊያንም ጽፈዋል:: ብዙ ወጣቶች እንደ ምሳሌ የምናየው ዳንኤልም ይህንን
   አብራርቶታል:: http://www.danielkibret.com/2010/08/blog-post_11.html ....

   Delete
  3. .....ቅዱስ ሲኖዶስ መጻህፍቱንና ቀኖናዋን እያየ መስተካከል የሚገባውን ማስተካከል ስርዋጽ የገባውን ማስወጣት ያልጠነከረውን ማዳበር
   ሲኖርበት በአስተዳደሩ መዳከም ምክነያት ይህንን አይቶ ለማስተካከል ዓይን ያለው አይመስልም:: ኦርቶዶክሳዊያን ወጣቶች በነገረ
   ሃይማኖት ከበረታንና መጽሓፍትን ከመረመርን የቤተ ክርስቲያን የሆነውን እና ያልሆነውን መለየት እንችላለን:: መናፍቃን
   መጽሐፍቶቻችንን እየጠቀሱ ለማደናገር ሲሞክሩም አግባብ የሆነ መልስ ለመስጠት አቅሙና እውቀቱ ይኖረናል::
   ፕሮቴስታንታንቶች እንደመጠቀሚያነት የሚያደርጓቸው እነዚህን ድክመቶች ነው:: ድክመቶቹን የሃይማኖት ድክመት በማስመሰል
   ኦርቶዶክስ የተሳሳተች ናት በማለት ብዙ ሰው ለማስኮብለል አስችሏቸዋል:: ፕሮቴስታንቶች በእየቀኑ ብዙ ሰው የሚያጠምዱት በእነርሱ
   እምነት ትክክል ስለሆነ ሳይሆን በቤተ ክርስቲያን ላይ አንዳንድ ድክመቶች መኖራቸው እና ለምእመኖቻችን እነዚህን ድክመቶች
   ባለማሳወቃችን ወይንም ባለማሻሻላች ነው:: እንዲያውም አንዳንድ ካህናት ሳይቀር ሲጠይቋቸው መልስ መስጠት እስኪያቅታቸውና
   ሲደናገሩ ይታያሉ:: በመሆኑም ድክመቶችን በሚገባ አጥንቶ ማስተካከል ለቤተ ክርስቲያን ጥንካሬና መስፋፋት ለምእመናን መጽናት
   ለቀጣዩ ትውልድም መረጋጋት የሚፈጥር ነው::
   ሲኖዶስ ያላስተካከለውን እምነት መተቼት ይቻላልን?
   መምህራኖቻችን እነዚህን ስህተት የሆኑ ጽሑፎቻችንን እና አንዳንድ ጉዳዮችን እንዴት ሊያዩቸውና ሊያስተምሯቸው ይገባል?
   መምህራን ትክክለኛውም የእግዚአብሔር ቃል የመናገር ግዴታ ቢኖርባቸውም የቤተ ክርስቲያንን ባህል እና እምነት የሚጻረሩ
   ጽሑፎችን እና ትምህርቶችን ግን መስጠት የለባቸውም:: በአንጻሩ የዚህ ጽሑፍ ጸሐፊ እንደሚለው ስህተቶች እንዲስተካከሉ ለቤተ
   ክርስቲያን አባቶች ማስታወስ ተገቢ ነው:: በአደባባይ ግን ይህ ስህተት ነው እያሉ የሚታመነውን መናገሩ ምእመናንን ማደናገር ይሆናል::
   ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ ቃል ኪዳን በነገረ ድህነት በሚለው መጽሓፉ በመጨረሻው ምእራፍ በመጽሓፈ ጤፋትና በሌሎች ድርሳናት ላይ
   ተጽፎ የሚገኝ እና ምእመናን የምናምነውን ግሸንን የተሳለመ ሃጥያቱ ይሰረይለታል የሚለውን አስተምህሮ ትክክል አይደለም ብሎ
   ጽፏል:: ለዚህም ሃጥያት የሚሰረየው በንስሃ እንጂ በቃል ኪዳን አይደለም የሚለውን ለማሳየት ሞክሯል:: ጸሐፊው እውነትነት
   ሊኖረውም ላይኖረውም ይችላል:: ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን የምታምነው እስከሆነ ድረስ ተቃውሞ መጻፉ አግባብ አይደለም:: ድርሳናቱ
   ይህን በተመለከት የጻፉት ስህተትነት ካለው በመጀመሪያ በሲኖዶስ እንዲስተካከል መደረግ አለበት አለበለዚያ እርስ በእርሳቸው
   የሚቃረኑ መጻህፍት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዲኖሩ ማድረግ ምእመናኑን ለመከፋፈል እና ለትችት መዳረግን ያስከትላል::

   Delete
  4. "የጻፉት ስህተትነት ካለው በመጀመሪያ በሲኖዶስ እንዲስተካከል መደረግ አለበት" የሚሰማና የሚተገብረው ቢገኝ ፣ ይኸ መልዕክት በአምልኮና በእምነት ለሚከፋፍሉን ትምህርቶችና ልምምዶች ሁሉ ዋና መፍትሄ ነው ፡፡

   የቤተ ክርስቲያን የሆነውን ትምህርት ስህተት ነው ብሎ ህዝብ በሚያነበው አውድ ላይ ዘርግቶ እምነት ላለውና ለሌውም ፣ ለክርስቲያኑና ለአሕዛቡ ማስነበብ ፣ ለጸሐፊዎች ምን ጥቅም እንደሚያስገኝላቸው በግሌ ግልጽ አልሆነልኝም ፡፡ ጥርጣሬን በሰው ልብ መዝራትና ከእምነቱ እንዲሸሽ ማድረግ ካልሆነ በስተቀር ሰዎችን በእምነትና በምግባር ሊያንጻቸው ፈጽሞ አይችልም ፡፡ ይልቁንም ተማርን የሚሉት ሊቃውንቶቻችን ቢያዳምጡን ፣ የሚያምኑበትን መልዕክቶቻቸውን ለእኛ አስቀድመው ከማድረሳቸው በፊት ፣ ስህተት ነው ብለው የገመቱትን በሙሉ ፣ በየጊዜው ለአባቶች ጉባዔ (ሲኖዶስ) አቅርበው ቢከራከሩበትና አንድ መፍትሄ ላይ ቢደርሱ ፣ እርምት ለማድረግም እጅግ ቀና ፣ ለተቀባይነቱም ቀላል ይሆን ነበር ፡፡

   እስከ ዛሬ የጻፉትን ያነበበ ሁሉ እነርሱ እንደሚሉት ቢቀበላቸው ፣ ምን እርምጃ እንዲወስድ እንደሚያልሙ መገመት ከባድ አይሆንም ፡፡ ለምሳሌ አንድ የሚወዱትን ምሳሌ ላንሳ “የሚያማልደን ኢየሱስ ብቻ ነው ፤ ድንግል ማርያም አታማልደንም ፡፡” የሚለውን ትምህርት የተቀበላቸው ሰው ፣ የት ሄዶ ነው ይኸ እምነታቸውን የሚለማመደው ወይስ ቤተ ክርስቲያን መሄድ አቁም ማለታቸው ይሆን ? ይኸ ነው እንግዲህ ዕቅድና ዓላማቸውን ሊረዱት የማይቻል ስውር ደባ የሚያደርገው ወይንም ለቤተ ክርስቲያናችን ዕድገትና መሻሻል ሳይሆን መንጋውን አስደነብሮ ለማስወጣትና ወደ ሌላ ቤተ እምነት ለመንዳት ነው የሚለውን ሃሳብ እንድንቀበል የሚያስገድደን ፡፡ መቼም ከነጥርጣሬህ ሁነህ ቅድስት ድንግል ማርያም ፣ የአምላክ እናት ለእኛም በስጦታ እናታችን ፣ የፍጥረት የመዳን ምክንያት የሆነችልን ፣ አማላጃችን ከሚባልበት ቤተ ክርስቲያን ሄደህ ባታምንበትም አሜን ፣ አሜን በል ብለው እንደማይመክሩ እተማመናለሁ ፡፡

   በተረፈ ግን የሃይማኖትን መጽሐፍት በመንፈስ ሁነን መንፈሳዊ መልዕክቶቻቸውን ብቻ መከታተል ካልቻልን ማንኛውም የሃይማኖት መጽሐፍ በሰው ጥበብ ከትችት የሚያመልጥ አይደለም ፡፡ እንዲያውም ብዙ ከፈጣሪ የሚያጋጩንንም ሃሳቦች እናፈልቃለን ፡፡ ለጊዜው ማስረጃዎችን ከመዘርዘርና ሰድቦ ለሰዳቢ ከማድረግ በዚሁ ላብቃ ፡፡
   ሁላችንንም እግዚአብሔር ይርዳን

   Delete
 10. o man it is 100% true

  ReplyDelete
 11. ያስፈራል እግዚአብሔር እንዲህ ካለ የአምልኮ አመንዝራነት ይጠብቀን፡፡ በእውነት ይህን ሳይ ደንግጫለሁ

  ReplyDelete
 12. aba selamas if u want to change the church, ur approach & understanding of scriptures should be changed. This and other bla bla things are already said by protestants, nothing new & every body tired of that. As to me when I heard & read such kind of things I feel nausea & urge to vomit. I don't like to be protestant. Their origin is western. I don't want to loose my Ethiopian culture & character in my belief to God. Even orthodox followers believe that the church need some modifications but not totally as u stated.u couldn't get enough followers, specially from educated ones since u don't have any connection with orthodoxy rather u totally agree with protestants. Personally I appreciate the belief of Egypt. By the way I invite u to read POP shonoda III book of comparative theology. u will get what u missed to understand in being following orthodox christianity. I visit ur site by thinking that I can get some points. But now I am on the way to leave this page.

  Be mengedu hulu yemichekechikun pentewoch alu adel ende?

  ReplyDelete
  Replies
  1. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !December 18, 2012 at 8:16 AM

   Don't mix culture with religion.

   Delete
  2. Christianity is not a mater of culture of Ethiopia or Egypt or western protestant. These all are of this world. Our Christianity should be established on the Holy Bible and you should judge the article based on the truth of bible.

   Delete
  3. ትንሽ!!!!!!!!!!!!ትንሽ!!!!!!!!!!!!

   Delete
 13. lemin orthodoxawi post endaderegew amenk?...antem atamenzir!...lelelaw gize source.. lemd lebso ye KIRISTOS negn kemil KIRISTOS kalgebaw ytebiqen..

  ReplyDelete
  Replies
  1. lemin Yemimesil neger Atsefem. agul kerekere min yadergelehal?

   Delete
 14. በቃሉ አምኖ የኢየሱስ ከርስቶስ ተከታይ ሁሉ ማማለድ ይችላል። በእምነቱ መጠን ሰዉ ከሰው ይበልጣል። ለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ እንድህ ይለናል፦ ሉቃ 1፤28 መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ ፦ ደስ ይበልሽ ፤ ጸጋን የሞላብሽ ፤ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሰቶች መካክል የተባረክረሽ ነሽ አላት። እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች ለእያንዳንዳች የሚያስተምረን የራሱ የሆኑ ቁም ነገሮች አሉት። ሕልና ላለው ማስተዋል ልምችል አእምሮ ግልጽ ነው። አንቺ ከሰቶች መካከል የባረከሽ ነሽ ብሎ የጌታ መልአክ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሐይል ክብር ሰጥቶ ስጠራት እኛም ክብር ልንሰጣትና ልናከብራት ይገባል። ከሴቶች መካክል የተለየች ናትና ይህ ሕያዉ ቅዱስ ቃሉ ነው። ጌታ ከአንቺ ጋር ነው። ክብርም የሚነሰጣት ጌታ ከእርሷ ጋር ስለሆነ። የአዲስ ኪዳን የመጀመሪያ ሰው ጌታን ተቀብላ በማህጸንዋ ያኖረች ታላቅና ብቻ እናት ለሰው ልጅ ሁሉ ምሳሌ የሆነች ቅድስት ድንግል ማርያም ብቻ ነች። ጌታ ኢያሱስ ክርስቶስ በአካል በማህጸኑዋ ተቀብላ ያደረገችው ታላቅ ስጦታ ነው። እንድትከበር ያደረገው እራሱ የሰው ልጆች ፈጣሪ የሆነው ከሶስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ ኢያሱስ ከርስቶስ ነው።ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑሻል ተብሎ የተጻፈው ቅዱስ ቃሉ ላይ ነው ሉቃ 1፤47። ታድያ እሱዋ እግዚአብሔር ያከበራት ትውልድ ሁሉ ልያከብራት ይገባታል ተብሎ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከተጻፈ ያለ ምንም ጥያቄ ልናከብራነት መንፈሳዊ ግደታ ነው። ብትውዱኝ ቃሌን ጠብቁ ብሎ ጌታችን ተናግሮዋል። ዮሐ 14፤23። ቅድስት ድንግል ማርያን ልናከብራት የስፈለገበት ምክንያን የአለም ሁሉ መድሐንትን ስለ ወለደችልን ሉቃ 1፤49 ላይ አንድህ የምል የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ስራ አድሮጎዋል፡ ይህ ታላቅ ስራ የተባለው ከሥጋዋ ስጋ ከነፍሱዋ ነፍስ ነስቶ ፍጹም ሰዉ ሆኖዋልና። እርሱዋ አምላክ አይደለችም አትመለክም ነገር ግን እግዚአብሔር ክብር ሰጥቶዋታል እንደ ቃሉም እኛን ወደ ጌታ ታመልደናለች። ሮሜ 8፤30 ያጸደቃቸውን እነዚህን ደግሞ አከባራቸው ብሎ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለሮሜ ከርስቲያኖች በጻፈው ቃሉ ግልጽ አድርጎ አስቀምጦልናል። ዛሬ በሀገራችን ብዙ ጻሐፍዎች ሞልተዋል የፈለጉትን ልጽፉ ይችላል ያሉ መንፈሳዊ ነው ማለት አይደልም። ወደ ፊት ቅዱስ ስኖዶስ በቤተ ከርስቲያን ስም የምጻፉትን መጽሐፍት በትክክል አንደምቆጠር ተስፋ እናደርጋለ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቅድስት ድንግል ማርያም አምላክ አይደለችም አትመለክም ነገር ግን እግዚአብሔር ክብር ሰጥቶዋታል እንደ ቃሉም እኛን ወደ ጌታ ታመልደናለች 8፤30

   Tebarek.

   Delete
 15. አዎን አታመንዝሩ!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 16. ጽሑፋችሁን ስመለከተው ለረጅም ጊዜ በጣም በሳል በሳል ሊቃውንት ስብስብ ሀሳቦችን ለመመልከት ችያለሁ እና ምናለ አሁን በያዛችሁት የማስተማርና ቀስቅሶ የማንቃት መንፈሳዊ ጥበባችሁ በቅዱስ ያሬድ ስም የተ ጆበነውንና የጠላና የአረቄ ውጤት የሆነውን የደብተራ ስራ ( ዚቅ) በመባል የሚታወቀውን መጽሐፍ ጉድ ከመጽሐፍ ቅዱስ አኩዋያ ሌሊቱን ሙሉ ባለማወቅም ሆነ በማወቅ ስንጮህው ለምናድረው የምንዝር አገልጋዮች እንዲሁም ለምእመናኑ ብታስነብቡልኝ?። አረ ገና ብዙ ስራ አለባችሁ በጣም መበርታት ይጠበቅባችሁል፦ የሚስጥር ባለቤት እግዚአብሔር ብርታቱን ይስጣችሁ። እንወዳችሁአለን።

  ReplyDelete
 17. Every body have a right any kind of feeling to say and write. But need to under stand what is good or bad for our self spiritual practice. In our Orthodox Church lot of things need to change in positive way not keep wrong systems attach to the truth faith. The problems are our church leader they not doing there job how fix the iusse make folk confused . I so appreciate the person brought that kind wrong message to our indevidual mind. Lets us stop some where and ask our self. Our church right know it not on way moving. They are somany thing in questions to answer, who will answer kind of crucial points. Nobody. The church leaders are driving they people's on there stuped presonal interest . Lets us come together and discuss each others in truth Christians humble.

  ReplyDelete
 18. YIH BEKIDUSAN LAY YANETATERE ZEMECHACHIHU YET ENDEMIYADERSACHIHU GETA YWOKEW LAMANEGNAWM KIDUSANEN YAKEBERE KIDUS EGZIABHER SLEHONE MENEM BTLU ERSU YAKEBERACHEWN STKAWOMO ENDAT TEFU YAKEBERACHEWN ERSUNE FIRU LBONA YSTACHIHU ABA SELAMAWOCH GETAN YAKEBERNE EYEMESELACHIHU BIZU TEDAFERACHIHUNA ENGA LEMEHONU KIBER LEMIGEBAW KIBERNE STU YEMILEW KAL LENATE AYISERAM MALET NEW?

  ReplyDelete
 19. yihe yenanite yesim matifat sera new manim orthodoxawi yihen ayaderigim. lemehonu einanite gin lemin orthodox tewahidon lekek ataderiguwatim?

  ReplyDelete
 20. መጽሐፍ ቅዱስስ ቢሆን በሰዎችና በሰዎች ስም አይደለም እንዴ የተፃፈው ? ለምሳሌ 4ቱ ወንጌሎች በ4ቱ ወንጌላውያን ፣ በማቴዎስ፥ በማርቆስ ፥ በሉቃስ አና በዮሐንስ ነው የተፃፉት። የሐዋርያት ሥራ በሉቃስ፤ መልክታቱም በጳውሎስ ፥ በጴጥሮስ፥ በያዕቆብ፥ በዮሐንስ። ራእየ ዮሐንስ በዮሐንስ ነው የተፃፉት። ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረው እንጅ የፃፈው መጽሐፍ የት ነው የሚገኘው ? እነዚህን 27ቱን የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት የሐይማኖታችን መመሪያ እንዲሆኑ በ367 ዓ.ም እኮ ነው የእስክንድርያና የኢትዮጵያ ፓትርያርክ የነበረው ቅዱስ አትናቴዎስ (295-373) የወሰነው። ስለዚህ በዋናነት ሐልዎተ እግዚአብሔርን በመሰረቱ የማይክድ እስሆነ ድረስ የበለጠ እምነተ እግዚአብሔርን የሚያጠናክሩ የቤተ ክርስቲያናችን የጸሎትም ሆኑ የትውፊት መጻሕፍቶች ቢኖሩ ችግሩ ምን ላይ ነው ? የዜማ መጻሕፍቶቻችን ''አልቦ እግዜብሔር'' እያሉ እኮ አይደለም የሚያስተምሩን። ማኅሌታችንም የሚጀምረው ቅዱሳንን በማመስገን አይደለም። እንዲህ በማለት እራሱን እግዜብሔርን ነው እንጅ ፣ ''ስቡህ ወውዱስ ዘሣረረ ኩሎ ዓለመ ፥ በአሐቲ ቃል'' ስለዚህ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከሆነ የምንነጋገረው ባሏትና በነበሯት መጻሕፍቶች ዙሪያ እንነጋገር። እንደ ፕሮቴስታንት ትምህርት ከሆነ ግን ከነሱ ጋር መነጋገሩ ይሻላል። ቅዱሳን በሥጋ ሕይዎታቸው ዘመን እንጅ የሚማልዱን ከሞቱ በኋላ በአጸደ ነብስ ሁነው አይማልዱንም የሚለው ነገር ከሥጋ ሞት በኋላ ዘለዓለማዊ ሕይዎት አለ የሚለውን መሰረታዊ የሆነውን የሞኖተይስት እምነት የሚፃረር ሁኖ አግኝቸዋለሁ።

  ReplyDelete
 21. Wendimoch kelay post yetederegew tsihufim hone siel
  TWAHIDON aywekilim. Andim ken egna yetewahido lijoch endih
  yale kitfet wust gebten anawukim. Yeminamelkewun bendenb
  adirgachihu tawkalachihu. Le kidusan, tsadikan, semaitat yeminsetewun kibirm bedenb tawkalachihu.

  Tadia min lemalet new yih hulu atekara kidusan ye GETACHIN fitsum kirinchafoch nachew masayawochachin betsinatachew yeminasibachew felegachewn befikir bechalen lemeketel yeminimokir mehonachin minalbat kekerew alem yileyenal.

  Wendimoch mastewalin yistachihu gizew sayrefd.

  ReplyDelete
 22. ለቤተ ክርስቲያን ያለስሟ ስም መስጠት በአውነት አይገባም እግዚአብሔርም ይታዘባችዋል :: እስኪ የት ቤተ ክርስቲያን ነው ወይስ የትኛው ቅዱስ ነው የተመለከ ው ? አወ ክብር ይሰጣቸዋል የከበራሉ አወ በቤቱ መታሰቢያ ይደርግላቸዋል አወ በሰሩት ሥራ ይመስገናሉ የከበራሉ :: እግዚአብሔርን ከእናንተ በላይ በሃይማኖትና በሥራ አገልግለውጣልና ለእግዚአብሔር ቅርብ ናቸው :: እርሱማ ጸጋ ክብርን ሰጥቷቸዋል :: አሁን እናንተ የምትሉት ግን ከእውነቱ የራቀ ነው :: እና አኦርቶዶክሳውያን የምናመልከውን እናወቀዋለን አወቀንም እያመለክነው ነው :: ለቅዱሳን ክብርን ምስጋናን ስንሰጥም ከአምላካችን ታዘን ነው ::አንዳንድ ከእውቀት ማነስ የተነሳ ሰዎች ሊሳሳቱ ይችሉ ይሆናል ::ያንን ለማረም ለማስተማር ብትምክሩ መልካም ነው እናዳምጣለን ከዛ ውጭ ግን የቅዱሳንን ክብር ለመጋፋትና ለመናድ የምታደርጉት ክፉ ስራችሁ አሁን ግልጥ ሆኗል ::ከእግዚአብሔር እንዳልሆናችሁ አወቀናል ብትመለሱ መልካም ነው :: ባለቤቱ የጨለመውን የክህደት ልቦናችሁን ያብራላችሁ

  ReplyDelete
 23. ወዴት እየሄድን ነው? ለእልህ ተብሎ እግዚአብሔር ይካዳል ወይ? እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ለምድሪቱ ትልቅ ፍርድን እንዳናመጣባት እግዚአብሔር ያስበን፡፡ እንዲህ ያለ አስተሳሰብ የሚያራምዱት የማህበረ ቅዱሳን አባላት ናቸው፡፡ መማር እንደሚያደነቁር እያየን ነው፡፡ ዲግሪ ለመንፈሳዊነት ምንም ጥቅም እንደሌለው እነዚህ ሰዎች ምስክር ናቸው፡፡ በገጠሩ ብንሄድ ሰማይን ያለካስማ ምድርን ያለመሠረት የፈጠርህ ጌታ ተመስገን ይባላል፡፡ እነዚህ ሰዎች ግን የፍጻሜ ዘመን ማሳያ ናቸው። እግዚአብሔር ይቅር ይበለን

  ReplyDelete
 24. taken from....http://wongelforall.files.wordpress.com/2011/11/the-fact-of-the-movement-in-the-church.pdf ቤተክርስቲያንን ለትችትና ለነቀፋ የዳረጉ ጉዳዮች በሲኖዶስ አማካኝነት ይስተካከሉ!!!! ይህ ሐሳብ የአንዳንድ በሳል የማህበረ ቅዱሳን
  አባላትም ሓሳብ እንደሆነ አውቃለሁ:: ቤተ ክርስቲያን በእርግጥ ሊያስተች የሚችል ነገር አላትን ወይንስ ህዝቡን ለማወናበድ የሚቀርብ
  ክስ ነው? የሚለውን ሐሳብ መነሳቱ አይቀርም::
  የሚያስተቹ የሚባሉ ነገሮችን መናፍቃኑ ደጋግመው ጽፈዋቸዋል መጻህፍት አውጥተውባቸዋል ተሳልቀውባቸዋል:: ሆኖም ግን መናፍቃኑ
  የጻፏቸው ጽሑፎች ሁሉ እውነተኞች ናቸው ማለት አይደለም:: እነርሱ የእምነት መጉደል ስላለባቸው እነርሱ በእምነታቸው መጉደል
  ምክነያት የሚጠራጠሩት ሁሉ እንደ ስህተት ቆጥረው ኦርቶዶክስ ውስጥ ይህ ስህተት አለ እያሉ ይጽፋሉ:: እነርሱ የሚተቹት
  የሚታመነውን ጭምር እንደሆነ ልብ ልንል ይገባል:: በተጨማሪም በቤተ ክርስቲያን ለትችት ይዳርጋሉ የሚባሉ ጉዳዮች የእምነት ነገሮች
  አለመሆናቸውን ልብ ልንል ይገባል::
  ቤተ ክርስቲያን እንደ እምነት ተቋም በእምነትዋና በቀኖናዋ በሃይማኖታዊ ትምህርቷ ነቀፌታ የለባትም:: የምታምነው የአበውን
  ሃይማኖት መመሪያዋ የአምላክ ቃል የምትኖረውም መንፈሳዊውን ህይወት ነው:: ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን ለብዙ ዘመናት ተቀናቃኝ
  ስላልነበራትና ቤተ ክርስቲያንን የሚተች ሰው ስላልነበር ሊቃውንቱ ሳያውቁ ወይም በመዘናጋታቸው ምክነያት ብዙ ሊያስተቹ የሚችሉ
  ነገሮች እና እውነታነት የሌላቸው ጽሑፎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዲፈጠሩ ሆነዋል:: እነዚህ እውነትነት የሌላቸው ነገሮችመሰረታዊ ዶግማውንና ቀኖናውን አይንኩት እንጂ በልዩ ልዩ ጉዳዮችና በእምነት ላይ የሚንጸባረቁ ሆነዋል::ኢትዮጵያ ውስጥ እስከ
  1950 ዎቹ ድረስ ሲኖዶስ አለመኖሩ ጠንከር ብሎ እነዚህን ጉዳዮች የሚያይ አካል እንዳይኖር አድርጓል::
  በዘመናዊ መልእክ ስለቤተ ክርስቲያን እምነትና ስርዓት ግልጽ መጽሓፍትን የጻፉ እንደ አቡነ ጎርጎሪዎስ ካልእ አይነት አባቶች የቤተ
  ክርስቲያን እምነት የሆነውንና ያልሆነውን ዶግማውንና ቀኖናውን ትውፊቱንና ልማዱን እንዲሁም ባህሉን አብራርተው
  አስቀምጠውልናል:: እኒህ አባት አሁን አስተያየት ለሚሰጡ ወገኖች መነሻ ናቸው:: የሃይማኖታችን ገደብና ድንበር ልንረዳው በምንችል
  ቋንቋ ጽፈውልናልና:: በዘመናች ያሉ ዲ/ን ዳንኤል ክብረትን የመሳሰሉ ወንድሞች ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን ሊያስተቹ የሚችሉ ጽሑፎች
  እንዴት ሊጻፉ እንደቻሉ በጥናት መልክ ጽሑፎችን አቅርበዋል::
  http://wongelforall.files.wordpress.com/2011/11/awalid_metsahift.pdf ገጽ 18
  ቤተ ክርስቲያን በዘመንዋ ብዙ መጻህፍትን ጽፋ አሳልፋለች:: ምንም እንኳን አብዛኛው መጻህፍቱ ተዘርፈው ወደ አውሮፓ ቢሄዱም
  ሌሎችም ደግሞ በመቃጠል በእድሜ መርዘም ምክነያት በመበላሸት የጠፉ ቢሆንም በአንድ መረጃ እንደተመለከትሁት በኢትዮጵያ
  ውስጥ ወደ ሁለት መቶ ሺ /200 000/ የብራና መጻህፍት እንደተጻፉ /እንደተባዙ/ ይገመታል:: ከእነዚህ መጻህፍት ውስጥ ትልቁን
  ብዛት የሚይዙት አዋልድ መጻህፍቶቻችን ናቸው:: ብዙ መጻህፍት ከውጭ ሃገር ክርስቲያኖች ወደ ግእዝ ቋንቋ የተተረጎሙ ሲሆኑ
  ሌሎች ደግሞ በኢትዮጵያዊያን ሊቃውንት ተጽፈው የተባዙ ናቸው:: ታዲያ እነዚህ መጻህፍት ሲጻፉ የሚገለበጡት በእጅ ጽሁፍ ነው::
  ኮፒዎችም የሚጻፉት እና የሚባዙት በተለያዩ ግለሰቦች ነው:: ሁሉም ጸሓፊያን መንፈሳዊ መሆናቸውና የቤተ ክርስቲያን እውቀት
  እንደነበራቸው ማረጋገጥ አይቻልም:: ይህን ልንል የሚያስችለን ደግሞ አንዳንድ ቀላል ሊባሉ የሚችሉ ስህተቶችን ጭምር ስለምናገኝ
  ነው::
  እንደ ዲያቆን ዳንኤል ጥናት ከሆነ ግን አብዛኛዎቹ ለትችት የሚዳርጉ ነገሮችን መጻህፍቶቻችን ውስጥ ያስገቧቸው መናፍቃን ናቸው::
  ቤተ ክርስቲያን በልዩ ልዩ መልክ መጉዳት ቢፈልጉም እንደፈለጉት ስላልሆነላቸው በቤተ ክርስቲያን የማይታመኑ ጽሑፎችን በቤተ
  ክርስቲያን መጻህፍት ውስጥ ማስገባት መረጡ ይላል:: ቤተ ክርስቲያን የማታምናቸው እና የማትቀበላቸው ከታሪክ እና ከጊዜ ከቦታ ጋር
  የማይጣጣሙ ጽሑፎችን በማስቀመጥ ቤተ ክርስቲያን እንድትጠላ እንድትነቀፍና እንድትተች ምክነያት ሆኑ:: የዚህ ደግሞ ዓላማው
  ኦርቶዶክሳዊው ምእመን በጽሑፎቹ አማካኝነት ሃይማኖቱን እንዲጠላና እንዲንቅ ከእምነትም እንዲያፈነግጥ ነው:: አንዳንድ በስህተት
  ቤተ ክርስቲያን ገበተው ቤተ ክርስቲያንን ያስተቻሉ ከምንላቸው ጽሑፎች ውስጥ የሚከተሉትን ለምሳሌ እንመልከት::
  1. ሰዶምና ገሞራን የአቃጠሏት ሐዋርያት ናቸው /በሎጥ ዘመን ነበሩ
  2. የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ድንግል ማርያም የሙሴ እህት ናት
  3. ድንግል ማርያም የይስሓቅን ልጅ ያእቆብን በላባ ቤት ውስጥ እያለ ረዳችው
  ሌሎችንም ማቅረብ ቢቻልም ለጊዜው አስፈላጊ አይደለም:: አንድ ኦርቶዶክሳዊ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት የሚያውቅና የሚቀበል
  ጸሓፊ ከላይ የተገለጹትን ሊጽፍ አይችልም:: የዳንኤል ጥናት እንዳመለከተው መናፍቃን ያስገቧቸው ናቸው አለበለዚያ ደግሞ
  አላዋቂዎች የጨመሯቸው ናቸው:: ሆኖም ሊቃውንቱ እያወቁቸው እና የማያምኑባቸው ሆነው ሳለ ለምን ለማስተካከል አልደፈሩም?
  ይስተካከሉ የሚልንስ አካል እንደ ጥፋተኛ ማየት ይገባን ይሆን? የጎደለውን መሙላት የተጣመመውን ማቃናትን ቤተ ክርስቲያን
  ልታስብበት እንደሚገባ ሌሎች ጸሓፊያንም ጽፈዋል:: ብዙ ወጣቶች እንደ ምሳሌ የምናየው ዳንኤልም ይህንን
  አብራርቶታል:: http://www.danielkibret.com/2010/08/blog-post_11.html

  ReplyDelete
 25. taken from wongelforall.wordpress.com....ቤተ ክርስቲያን በዘመንዋ ብዙ መጻህፍትን ጽፋ አሳልፋለች:: ምንም እንኳን አብዛኛው መጻህፍቱ ተዘርፈው ወደ አውሮፓ ቢሄዱም
  ሌሎችም ደግሞ በመቃጠል በእድሜ መርዘም ምክነያት በመበላሸት የጠፉ ቢሆንም በአንድ መረጃ እንደተመለከትሁት በኢትዮጵያ
  ውስጥ ወደ ሁለት መቶ ሺ /200 000/ የብራና መጻህፍት እንደተጻፉ /እንደተባዙ/ ይገመታል:: ከእነዚህ መጻህፍት ውስጥ ትልቁን
  ብዛት የሚይዙት አዋልድ መጻህፍቶቻችን ናቸው:: ብዙ መጻህፍት ከውጭ ሃገር ክርስቲያኖች ወደ ግእዝ ቋንቋ የተተረጎሙ ሲሆኑ
  ሌሎች ደግሞ በኢትዮጵያዊያን ሊቃውንት ተጽፈው የተባዙ ናቸው:: ታዲያ እነዚህ መጻህፍት ሲጻፉ የሚገለበጡት በእጅ ጽሁፍ ነው::
  ኮፒዎችም የሚጻፉት እና የሚባዙት በተለያዩ ግለሰቦች ነው:: ሁሉም ጸሓፊያን መንፈሳዊ መሆናቸውና የቤተ ክርስቲያን እውቀት
  እንደነበራቸው ማረጋገጥ አይቻልም:: ይህን ልንል የሚያስችለን ደግሞ አንዳንድ ቀላል ሊባሉ የሚችሉ ስህተቶችን ጭምር ስለምናገኝ
  ነው::
  እንደ ዲያቆን ዳንኤል ጥናት ከሆነ ግን አብዛኛዎቹ ለትችት የሚዳርጉ ነገሮችን መጻህፍቶቻችን ውስጥ ያስገቧቸው መናፍቃን ናቸው::
  ቤተ ክርስቲያን በልዩ ልዩ መልክ መጉዳት ቢፈልጉም እንደፈለጉት ስላልሆነላቸው በቤተ ክርስቲያን የማይታመኑ ጽሑፎችን በቤተ
  ክርስቲያን መጻህፍት ውስጥ ማስገባት መረጡ ይላል:: ቤተ ክርስቲያን የማታምናቸው እና የማትቀበላቸው ከታሪክ እና ከጊዜ ከቦታ ጋር
  የማይጣጣሙ ጽሑፎችን በማስቀመጥ ቤተ ክርስቲያን እንድትጠላ እንድትነቀፍና እንድትተች ምክነያት ሆኑ:: የዚህ ደግሞ ዓላማው
  ኦርቶዶክሳዊው ምእመን በጽሑፎቹ አማካኝነት ሃይማኖቱን እንዲጠላና እንዲንቅ ከእምነትም እንዲያፈነግጥ ነው:: አንዳንድ በስህተት
  ቤተ ክርስቲያን ገበተው ቤተ ክርስቲያንን ያስተቻሉ ከምንላቸው ጽሑፎች ውስጥ የሚከተሉትን ለምሳሌ እንመልከት::
  1. ሰዶምና ገሞራን የአቃጠሏት ሐዋርያት ናቸው /በሎጥ ዘመን ነበሩ
  2. የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ድንግል ማርያም የሙሴ እህት ናት
  3. ድንግል ማርያም የይስሓቅን ልጅ ያእቆብን በላባ ቤት ውስጥ እያለ ረዳችው
  ሌሎችንም ማቅረብ ቢቻልም ለጊዜው አስፈላጊ አይደለም:: አንድ ኦርቶዶክሳዊ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት የሚያውቅና የሚቀበል
  ጸሓፊ ከላይ የተገለጹትን ሊጽፍ አይችልም:: የዳንኤል ጥናት እንዳመለከተው መናፍቃን ያስገቧቸው ናቸው አለበለዚያ ደግሞ
  አላዋቂዎች የጨመሯቸው ናቸው:: ሆኖም ሊቃውንቱ እያወቁቸው እና የማያምኑባቸው ሆነው ሳለ ለምን ለማስተካከል አልደፈሩም?
  ይስተካከሉ የሚልንስ አካል እንደ ጥፋተኛ ማየት ይገባን ይሆን? የጎደለውን መሙላት የተጣመመውን ማቃናትን ቤተ ክርስቲያን
  ልታስብበት እንደሚገባ ሌሎች ጸሓፊያንም ጽፈዋል:: ብዙ ወጣቶች እንደ ምሳሌ የምናየው ዳንኤልም ይህንን
  አብራርቶታል:: http://www.danielkibret.com/2010/08/blog-post_11.html
  ቅዱስ ሲኖዶስ መጻህፍቱንና ቀኖናዋን እያየ መስተካከል የሚገባውን ማስተካከል ስርዋጽ የገባውን ማስወጣት ያልጠነከረውን ማዳበር
  ሲኖርበት በአስተዳደሩ መዳከም ምክነያት ይህንን አይቶ ለማስተካከል ዓይን ያለው አይመስልም:: ኦርቶዶክሳዊያን ወጣቶች በነገረ
  ሃይማኖት ከበረታንና መጽሓፍትን ከመረመርን የቤተ ክርስቲያን የሆነውን እና ያልሆነውን መለየት እንችላለን:: መናፍቃን
  መጽሐፍቶቻችንን እየጠቀሱ ለማደናገር ሲሞክሩም አግባብ የሆነ መልስ ለመስጠት አቅሙና እውቀቱ ይኖረናል::
  ፕሮቴስታንታንቶች እንደመጠቀሚያነት የሚያደርጓቸው እነዚህን ድክመቶች ነው:: ድክመቶቹን የሃይማኖት ድክመት በማስመሰል
  ኦርቶዶክስ የተሳሳተች ናት በማለት ብዙ ሰው ለማስኮብለል አስችሏቸዋል:: ፕሮቴስታንቶች በእየቀኑ ብዙ ሰው የሚያጠምዱት በእነርሱ
  እምነት ትክክል ስለሆነ ሳይሆን በቤተ ክርስቲያን ላይ አንዳንድ ድክመቶች መኖራቸው እና ለምእመኖቻችን እነዚህን ድክመቶች
  ባለማሳወቃችን ወይንም ባለማሻሻላች ነው:: እንዲያውም አንዳንድ ካህናት ሳይቀር ሲጠይቋቸው መልስ መስጠት እስኪያቅታቸውና
  ሲደናገሩ ይታያሉ:: በመሆኑም ድክመቶችን በሚገባ አጥንቶ ማስተካከል ለቤተ ክርስቲያን ጥንካሬና መስፋፋት ለምእመናን መጽናት
  ለቀጣዩ ትውልድም መረጋጋት የሚፈጥር ነው::

  ReplyDelete
 26. Yemenamelkewen Egna ye Orthodox tewahido amagnoch enawkalen. Betekrstianachenem manen endemetamelk ena amleku endemetel tiret argen enawkalen. Yehe Orthodoxoch Dingel Mariamen yamelkalu yemilew mano yemasnekat ena yemastelat belom me'emenanochuan yemaskoblel serachu yetenekabet new. Yadanenen enawkalen. Yemenamelkewen enante atnegrunem. Kebalebetu yaweke... yemibal teret ale bagerachen.

  ReplyDelete
 27. የአርሲዋ እመቤት ጉዳይ.......................................http://www.eotc-patriarch.org/Saint%20Gebriel.pdf..ለዘመናት ከቤተ ክርስቲያን ትውፊት ሥርዓት ውጭ በሆነ መልኩ የአርሲዋ እመቤት የሚል መንፈስ የአምልኮ ባእድ ሲፈጸምበት በነበረው አካባቢ ለቤተ ክርስቲያን ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡
  በአርሲ ሀገረ ስብከት በመርቲ ወረዳ ልዩ ስሙ ፈረቀሳ በተባለ ሥፍራ የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ለመገንባት በብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ እና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ብፁዓን ሊቃ ጳጳሳት በተገኙበት የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡

  ኅዳር 1 ቀን 2005 ዓ.ም ለቤተ ክርስቲያን ግንባታ በተቀመጠው የመሠረት ድንጋይ ላይ ብፁዕ አቡነ ናትኤል እንደገለፁት የዛሬው ቀን ለክርስቲያኖች ልዩ ከመሆኑ አንጻር ብቻ የምንመከተው አይደለም የእግዚአብሔርንም ድንቅ ሥራ ያየንበትና የማዳኑም ሥራ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረ መጥቶ ዛሬም በግልጽ የሚታይ ሆኖ ይገኛል፡፡ይህ ቦታ ባዕድ አምልዕኮ የሚመለከትበት ቦታ የነበረ ሲሆን የዛሬው በዓል ለኛ በሕይወት ላለነው ብቻ ሳይሆን በሕይወት ለሌሉትም ጭምር ነው የእግዚአብሔር ሥራ ሁል ጊዜ ቢሆንም ለተለየ ሥራ ደግሞ የተለየና የተመረጠ ቀን አለ፡፡እናንተ ለእግዚአብሔር መመስገኛ አገልግሎት የሚውል ቤተ ክርስቲያን ለመገንባት እንዲህ ስትተጉ እርሱም ዋጋችሁን አያስቀርባችሁም፡፡ከዚህ በፊት ይህ ቦታ የአርሲዋ እመቤት በሚል የዲያቢሎስ መፈንጫና የበሽተኞች መዋያ የነበረ ሲሆን ከአሁን በኋላ የምህረትና ፈውስ አደባባይ እንዲሁም የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ የሚፈጸምበት ሆኗል አሁንም ለፈጣሪያችሁ በገባችሁት ቃል መሠረት የቤተ ክርስቲያኑ ግንባታ በጥራት በፍጥነት ተከናውኖ ቤተ ክርስቲያኗ ለምዕመናን የምትሰጠውን የተሟላ አገልግሎት እድታጠናክር የተለመደ ክርስቲያናዊ ትብብራችሁና መረዳዳታችሁ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በማለት ገልፀዋል፡፡

  ReplyDelete
 28. The above writer you are naive mk. God is neither black nor white, but she looks,pretty white girl. Now, this indicates she just represent only some group of race. Similarely, mk lead by gijam debtera, but the other elements ass kisser of gojam debtera. Mk mutu amen. Mehara wotesehala nefese gojam debtera mk ayref wo s er ol amen.

  ReplyDelete
 29. የአርሲዋ እመቤት የሚለው ስእል ቤተ ክርስቲያን በፍጹም አይወክልም!!! የድንግል ማርያም ስእል በፍጹም በጭራሽ አይደለም የዲያቢሎስ ማደናገሪያ ነው !!!!!!! እንደዚህ አይነት ነገር ካያችሁ ለቤትክርስትያን አመልክቱ ://www.eotc-mkidusan.org/site/index.php/-mainmenu-18/1137-2012-11-15-14-36-09ኅዳር 6 ቀን 2005 ዓ.ም.
  በእንዳለ ደምስስ

  “በአርሲ ሀገረ ስብከት በመርቲ ወረዳ ልዩ ስሙ ፈረቀሳ በተባለ ሥፍራ ከ120 አመታት በላይ የአርሲዋ እመቤት” በሚል የባዕድ አምልኮ ሥርዓት ሲፈጸምበት በነበረ ሥፍራ ላይ የባዕድ አምልኮ ሥርዓቱን በማጥፋት ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ገብርኤልን ቤተ ክርስቲያን ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ኅዳር 1 ቀን 2005 ዓ.ም. አኖሩ፡፡

  ብፁዕነታቸው በሥፍራው ለተገኙት ምእመናን በሰጡት ቃለ ምዕዳን “ከዚህ በፊት ይህ ቦታ የአርሲዋ እመቤት በሚል የዲያቢሎስ መፈንጫ፡ የሕሙማን መዋያ የነበረ ሲሆን ከአሁን በኋላ ግን የምሕረትና የፈውስ አደባባይ እንዲሁም የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ የሚፈጸምበት ሆኗል” ብለዋል፡፡ ለአካባቢው ምዕመናን ባስተላለፉት መልዕክትም የቤተ ክርስቲያኑን ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ የተጣለባቸውን ሓላፊነት ይወጡ ዘንድ አሳስበዋል፡፡

  ይህ የባዕድ አምልኮ ሥርዓት ከ1885 ዓ.ም. ጀምሮ ወ/ሮ ሻበሻ ወርቅ ይመር በምትባል ሴት በሥፍራው እንደተመሠረተና ምዕመናንን በማሳሳት ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እንዲያፈነግጡ በማድረግ እስካረፈችበት እሰከ ጥቅምት 19 ቀን 1912 ዓ.ም ድረስ ቆይታለች፡፡ ነገር ግን በወቅቱ ሲከተሏትና የመሠረተችውን የባዕድ አምልኮ ሥርዓት ሲያከናውኑ የነበሩ ተከታዮቿ “የአርሲዋ እመቤት”፤ የአካባቢው ሙስሊሞች ደግሞ “ሞሚናት” በሚል አጠራር ሥርዓቱን በማጠናከር በዚሁ ቦታ ላይ በቅዱስ ገብርኤል ስም በየዓመቱ ጥቅምት 19 እና ግንቦት 19 ቀን በከፍተኛ ሁኔታ የባዕድ አምልኮ ሥርዓቱን ለብዙ ዘመናት ሲያከናውኑት እንደቆዩ ይነገራል፡፡

  የብዙ ዘመናት ጸሎት ሰምሮ በብፁዕ አቡነ ናትናኤል መመሪያ ሰጪነትና ድጋፍ ሀገረ ስብከቱና የወረዳው ቤተ ክህነት እንዲሁም ምእመናን ባደረጉት ጥረት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነትና ሥርዓት መሠረት ባዕድ አምልኮ መፈጸም የተወገዘ መሆኑን በማስተማርና በማሳመን የመሠረት ድንጋዩ እንዲቀመጥና የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን እንዲሠራ ስምምነት ላይ ተደሷርል፡፡

  በአካባቢው የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮችም የእርሻ ማሳቸውን ለቤተ ክርስቲያን መሥሪያ በመፍቀድ ከ1200,00 ብር በላይ በማዋጣት መለገሳቸውን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፡፡

  ReplyDelete
 30. dimts albawn chuheten asemitachihu eyechohachihuling new God bless you all!!!

  ReplyDelete
 31. please read the following website ስለ አርሲዋ እመቤት እና ስለ ሌላም ነገር የሚገርም ነገር ታነባላችሁ.. http://ethiopia.ecadf.netdna-cdn.com/Amharic/wp-content/uploads/2011/09/ynegal1.pdf?84cd58

  ReplyDelete
 32. Please checkout the blog by Kesis Melaku. It is very Interesting. http://www.kesis.org

  ReplyDelete
 33. sile Zera Yakob Emebets (tsadkanie mariam) min tilalachihu?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ነገሩ ሁሉ አጋንንታዊ ነው

   Delete
 34. "ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል" የሚለው አባባል ለእናንተ ነው የተነገረው ልበል?

  መቼም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ "ድንግል ማርያም አምላክ ናት" ብላ አምናም አስተምራም እንደማታውቅ ልብህ ጠንቅቆ ይረዳል። እንዳንተና እንደ ግብር አባትህ ዲያብሎስ ያላችሁ ግን እምነቷን ያስተቻል ብላችሁ የምታምኑትን በየፌስቡክ ገጽና በየታክሲ መስታውቱ ላይ መለጠፋችሁን ሥራ አድርጋችሁታል።

  እኛ ግን የምናመልከውን እናውቃለንና ተውን። ይልቅ ሳይመሽባችሁ ባለቻችሁ አጭር ዕድሜ ለአገርና ለወገን የሚጠቅም ሥራ ፈልጉ። "አትማረኝ" ብሎ የጸለየን ዱዳ የማረ እግዚአብሔር እንጂ እናንተ አይደላችሁምና የዋህ ሰው ጽፎትም ከሆነ የልቡን እናንተ ሳትሆኑ የሚመረምረው እግዚአብሔር ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ተው እባክህ ጣኦት ናት ባንላትም ጣኦት ሆናብናለች፡፡ እርግጥ እርሷ ጣኦት አይደለችም፡፡ እኛ ግን ጣኦት አድርገናታል፡፡ ስለዚህ ወሬህና የሚታየው እውነታ ለየቅል ናቸው፡፡ ስለዚህ ከአምልኮተ ማርያም ፊትህን ወደአምልኮተ ኢየሱስ መልስ፡፡

   Delete
 35. መጽሐፍ ለሰነፍ መንገር ፣ ለአንቀላፋ ማውራት ነው ይለናል ፡፡ ቢሆንም የመጽሐፍ ቃልን ለማስነበብና ቀጣይ ርምጃ ምን ይደረግ ለማለት ያህል፡-
  ሮሜ 13፡7 - ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ
  ክብር ስጡ ሲባል ፡-
  - በተቀዳሚ ተነጻጻሪና ተወዳዳሪ ለሌው ለእግዚብሔር - የአምልኮ ምስጋና
  - በቀጣይ እግዚብሔር ላከበራቸው ለባረካቸው ቅዱሳን - የአክብሮት ምስጋና

  መዝ 33፡1 ጻድቃን ሆይ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ለቅኖች ምስጋና ይገባል።
  ሮሜ 2፡1ዐ በጎ ሥራ ለሚያደርጉ ሁሉ ምስጋናና ክብር ሰላምም ይሆንላቸዋል፥
  ከመጽሐፍ ቃሉ ይደምሰስ ወይስ እንደሚለው እንቀበል?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሰነፍ የሚለውን ስም ቀድሞ ለሌላው በመስጠት ጎበዝ መሆን አይቻልም፡፡ ሰነፉ ማን እንደሆነ ግብሩ ይለያል፡፡ ስለዚህ ከቅዱሳን አምልኮት ተላቀቅና ወደማስተዋል ና፣ ካልሆነ ግን ሰነፉ አንተ ነህ፡፡

   Delete
  2. መጽሀፉ እንደሚለው እንቀበላለን፡፡ ግን መጽኀፉ አምልኩዋቸው አላለም ብሎዋል እንዴ? ስለዚህ አናመልክሻለን የሚለው ቃል አጋንንታዊ ስለሆነ አጥብቀን እንቃወማለን!!!!!!!

   Delete
 36. አንት ጠማማ ክፉ እስኪ ቅዱሳንን ማክበር ለእነርሱ ምስጋና በማቅረብ ነው የሚገለጸው የሚል ትምህርት ከየት አመጣህ? የአምልኮ ምስጋናና የአክብሮት ምስጋና በሚል ለሁለት የከፈልከውስ በምን ማስረጃ ነው? ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን እኮ እንዲህ የሚል ትምህርት የላትም፡፡ ይህ ማቅ የዘራብህ ክፉ ዘር ነው፡፡ ስለዚህ የሳትከው ራስህ ነህና ተመለስ

  ReplyDelete
 37. ክብረ ቅዱሳንን በተመለከተ

  “ቅዱሳን እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ” በሚል ርዕስ ቀጥሎ በተመለከተው አድራሻ ከቀረበ ጽሁፍ ለንባብ እንዲያመች ፍሬ ሃሳቡ ብቻ ተመርጦ የተወሰደ ነው ፡፡ ጊዜ ላለው ሙሉ ንባቡ ሰፊ ትምህርት ይሰጣል ፡፡ በጸሐፊው ስም ጋብዣለሁ ፡፡
  http://wongelforall.wordpress.com//2010/03/31/


  እግዚአብሔር ለስጦታው ወደር ፣ ለቸርነቱም ቁጥር የለውምና በእርሱ የሚያምኑ እርሱን እንዲመስሉ ስልጣን ሰጥቷል። ይልቁን በስጋ የተገለጠው አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፥ /ዮሐ 14፤12/ ብሎ እንዳስተማረ በክርስቶስ እስከሞት ድረስ ያመኑ ቅዱሳን እርሱን እንዲመስሉ አድርጓል።

  ቅዱሳን ኢየሱስን እንዲመስሉ እግዚአብሔር መወሰኑን ሲያስረዳ ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤ አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው።ሮሜ 8፤28-30

  የልጁን መልክ ሲል እኛ የምናውቀውን ገጽ ማለት አይደለም ፡፡ የኢየሱስን ቅድስና ንጽሕና ክብር እንዲከተሉ ስራውን እንዲከተሉ እግዚአብሔር ወስኖላቸዋል። እንዲያውም እግዚአብሔር የልጁን መልክ የመሰሉ ቅዱሳንን ራሱ እንዳከበራቸው ሲገልጽ ያጸደቃቸውን ደግሞ አከበራቸው ይላል። ቅዱሳንን ያከበረ ራሱ እግዚአብሔር ነውና።

  ቅዱስ ማለትም የተለየ ማለት ሲሆን ቅዱሳን ሲሆን የተለዩ የሚለውን ያመለክታል። ቅዱሳን የተለዩ ናቸው ሲባልም ከዚህ አለም ርኩሰትና ሐጢያት የተለዩ ለእግዚአብሔር ክብር ራሳቸውን ያዘጋጁ ማለት ነው። ቅዱሳን ከራሳቸው ይልቅ ለእግዚአብሔር የኖሩ፤ አለምንና በእርሷ ያለውን የናቁ እነርሱም በአለም የተናቁ ፤ ስለወገኖቻቸው በኃጢያት መውደቅ የሚያዝኑ ስለክርስቶስ መንግስት የመሰከሩ ናቸው።

  ቤተ ክርስቲያናችን ቅዱሳን ብላ የምትጠራቸው ቅዱሳን ሰዎች የሚያጠቃልለው ፡-
  1. ቅዱሳን ሰማዕታት፡ ሰማዕት ማለት ምስክር ማለት ሲሆን ምስክርነታቸውን ለእግዚአብሔር ነው።እስከ ደም ጠብታ ድረስ ለእግዚአብሔር ሲሉ ራሳቸውን መስዋዕት ያደረጉና እውነትን የመሰከሩ ናቸው። የሰይፍ መሳል የእሳት መጋል አውነትን ከመመስከርና ስለእግዚአብሔር ሐያልነት ከመናገር ያላስቆማቸው ናቸው። ህይወታቸውን እስከመስጠትና እስከ መገደል ከቦታ ቦታ እስከመሰደድ ድረስ እግዚአብሔርን በህይወታቸው ያከበሩትን ቅዱሳንን ሰማዕታት እንላቸዋለን። እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የህይወትን አክሊክ አቀናጂሀለሁ ያለውን የክርስቶስን ቃል ይዘው የታመኑ ናቸው።/ ራዕ 2፤10/

  2. ቅዱሳን ጻድቃን፡ ጻድቃን ማለት እውነተኞች ማለት ነው። እነዚህም ሐዋርያው ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ። እንዳለው /ዕብ 11፤38/ ከዚህ ዓለም ራሳቸውን ለይተው በጾምና በጸሎት ራሳቸውን ጠምደው እግዚአብሔር ሲያገለግሉ የኖሩ አባቶችና እናቶች ጻድቃን ይባላሉ።

  3. ቅዱሳን ሊቃውንት፡ ቅዱሳን ሊቃውንት የምንላቸው በህይወታቸውና በኑሯቸው እየመሰከሩ የክርስቶስን የክብር ወንጌል ለዓለም ያስተዋወቁ ናቸው ፡፡ እኒሁም ከሐዋርያት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ የሚነሱ በእውነተኛው የክርስትና ትምህርት ላይ የታነጹ የሚያንጹም ናቸው። ተከራክረው መናፍቃንን የሚረቱ ከሐዲያንን የሚያሳምኑ ከእውቀታቸው ጋር ህይወታቸውን ለእግዚአብሔር ያስገዙትን ሊቃውንት እንላቸዋለን።

  ቅዱሳን እግዚአብሔር ራሱ ስላከበራቸው ከእግዚአብሔር የተነሳ የተከበሩ ናቸው። ስልጣናቸውን ክብራቸውን ጸጋቸውን ሁሉ ከእግዚአብሔር ያገኙት ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በራሱ በባህርይው የከበረ ነው። እርሱ ፈጣሪ ነው አርሱ አምላክም ነው እርሱ አክባሪ (ሌሎች እንዲከበሩ የሚያደርግ) ነው ፡፡ የሚያከብረው (እንዲከበር የሚያደርገው) አይፈልግም ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ሆኗልና።
  በዮሐ 8፤12 እኔ የአለም ብርሃን ነኝ ይላል፡፡ እንዲሁም ማቴ 5፡14 ላይ ቅዱሳኑን እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። ይላቸዋል።

  1. ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ ፈዋሽ ነው ቅዱሳንም የመፈወስ ጸጋ ሰጥቷቸዋል

  ከሞተ አራት ቀን የሆነውን አልአዛርን ከመቃብር አስነስቶታል (የሐ 11)፤ የሞተችዋን የኢያንሬዎስን ልጂ አስነስቷል፤ ሲወለድ ጀምሮ አይን ያልነበረውን ሰው አይን ሰርቶለታል /ዮሐ 9/፤ ሁለቱን እውሮችም አይናቸውን አብርቷል /ማቴ 9/ ። ኢየሱስ ክርስቶስ ከዚህም አልፎ ጨርቁ እንኳን ለሚያምኑበት ይፈውስ ነበር።
  አስራ ሁለቱንም ጠርቶ በእርኩሳን አጋንንት ላይ ስልጣን ሰጣቸው ፡፡

  ኢየሱስ ክርስቶስ በራሱ ሀይልና ስልጣን አጋንንትን እንዳስወጣ ሁሉ ቅዱሳን ደግሞ የእርሱን ስም መከታ አድርገው በስላሴ ስም፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፤ በእግዚአብሔር ስም ፤ በሐዋርያት ስልጣን አጋንንትን ያስወጣሉ።
  ሐዋ 3፡2 ፣ 3፡8 ፣ 9፡34 ፣ 9፡41 ፣ 20፡9 ፣ 19፡11 ፣ 5፡15

  ይቀጥላል

  ReplyDelete
 38. ክፍል ሁለት
  2. ኢየሱስ ክርስቶስ አለምን ከራሱ ጋር አስታርቋል ቅዱሳን ደግሞ ያማልዳሉ
  ምልጃ ማለት አንድን አካል ወክሎ በሌላ አካል ፊት ልመናን ማቅረብ ማለት ነው። በመንፈሳዊው አለም ምልጃ ለአንድ ሰው ወይም ሀገር ወደ እግዚአብሔር ልመናን ማቅረብ ነው። አንድ ሰው ስለሌላ ሰው ወደ እግዚአብሔር የሚያደርገው ልመናና ጸሎት ምልጃ ይባለል።

  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ይግባውና በስጋው ወራት በተመላለሰበት ጊዜ ለእኛ አርአያ ይሆነን ዘንድ ስለደቀ መዛሙርቱ እንዲሁም ስለጠላቶቹ ይጸልይ ነበር። የሐ 17፤1-26 ሉቃ 23፤34 ክርስቶስ ምንም እንኳን ራሱ እግዚአብሔር ቢሆንም እና ራሱ የመማርም ሆነ የመፍረድ ስልጣን ቢኖረውም ለእኛ አርአያ ይሆን ዘንድ ሲለምን እናየዋልን። ይህም እኛ እርስ በእርሳችን አንዱ ስለአንዱ እንዲለምንና እንዲማልድ ያስተምረን ዘንድ ነው።
  ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋው ወራት ቢጸልይም ቢለምንም እንኳን ከሞተና ከተነሳ በሗላ ልመናን ምልጃን የሚያደርጉ ቅዱሳን እንደሆኑ እንጂ ራሱ እንደማይለምን በአጭር ቃል አስቀምጧል።
  ዮሐ 16፤26 በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ፤ እኔም ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም፤ በዚህም እነርሱ እንደሚለምኑ እንጂ እርሱ አብን በስጋው ወራት እንደነበረው ሁኔታ እንደማይለምን ተናግሯል።

  2ኛ ቆሮ 5፤18 ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤ የማስታረቅ አገልግሎት የሰጠን ሲል ቅዱሳን አስታራቂዎች /አማላጆች/ መሆናቸውን ለመጥቀስ ነው። ቀጥሎም በእኛም የማስታረቅን ቃል አኖረ ብሎ ይናገራል። ቅዱሳን የማስታረቅን የማማለድን ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተቀብለዋልና።

  ራሳቸውም ስለ እናንተ ሲያማልዱ፥ በእናንተ ላይ ከሚሆነው ከሚበልጠው ከእግዚአብሔር ጸጋ የተነሣ ይናፍቁአችኋል። 1ኛ ቆሮ 9፤14 ለምዕመናኑ የተመረጡ ቅዱሳን እንደሚማልዱ ሲያመለክት ነው።

  2.1. የምልጃ መስራች ማን ነው?
  ቅዱሳን እንዲያማልዱ ፈቃድና ትዕዛዝ የሰጠ እርሱ ስለመሆኑ
  - ዘጽ 20፤7 አሁንም የሰውዬውን ሚስት መልስ፤ ነቢይ ነውና፥ ስለ አንተም ይጸልያል፥ ትድናለህም።
  - ኢዮ 42፡8 ወደ ባሪያዬ ወደ ኢዮብ ዘንድ ሂዱ፥ የሚቃጠልንም መሥዋዕት ስለ ራሳችሁ አሳርጉ፤ ባሪያዬም ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልያል፥ እኔም እንደ ስንፍናችሁ እንዳላደርግባችሁ ፊቱን እቀበላለሁ።

  ምልጃም ያስፈለገበት ዋናው ምክነያት እግዚአብሔር ከሐጢያተኞች ይልቅ የቅዱሳንን ስለሚሰማና የቅዱሳንን ልመና ለመፈጸም ደስ ስለሚለው ነው። 1ኛ ጰጥ 3፤12 የጌታ ዓይኖች ወደ ጻድቃን ናቸውና፥ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል፥ የጌታ ፊት ግን ክፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው።

  2.2. የቅዱሳን ምልጃ
  እግዚአብሔር በአብርሃም ምልጃ አቤሜሌክን እንደፈወሰው ዘፍ 20፡ 17፤
  አብርሃም ስለሰዶምና ገሞራ በእግዚአብሔር ፊት ማልዷል። ዘፍ 18፤20-33
  ነቢዩ ኤልያስ አማልዶ የህጻኑን ነፍስ አስመልሷል።1ኛ ነገ 17፤17-24 እንዲሁም ኤልያስ አማልዶ ለሶስት አመት አልዘንብ ያለው ዝናብ እንዲዘንብ አድርጓል። 1ኛ ነገ 18፤30 ኤልሳዕ በምልጃው የሞተውን ልጂ አስነስቷል። 2ኛ ነገ 4፤18-36።
  ኢዮብ እግዚአብሔር የልጆቹን ሐጢያት ይቅር ይል ዘንድ በእየእለቱ ሲማልድ እንመለከተዋለን /ኢዮ 1፤5/ ኢዮብ ለጓደኞቹ እንዲማልድ እግዚአብሔር እንዳዘዘና ኢዮብ እንደማለደም መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። ኢዮ 42፡8።
  ሙሴ የህዝብ መሪና ነቢይ ስለነበረ ጊዜውን በአጠቃላይ ያሳለፈው ለእስራኤል በመማለድ ነው። ሙሴ ለፈርኦን አማልዷል /ዘጸ 8፤8-15 ዘጸ 8፤25-31/
  ሙሴ እስራኤል ጣኦት በማምለካቸው ምክነያት እግዚእብሔር ሊያጠፋቸው ስለተቆጣ ሙሴ እንዳይጠፉ አማልዶ አስምሯቸዋል/ዘጸ 32፤1-15/ ሙሴ እህቱና ማርያምና ወንድሙ አሮን ኢትዮጲያዊቷን በማግባቱ በተቆጡ ጊዜ እህቱን እግዚአብሔር በለምጽ ስለመታት አማልዶ አድኗታል /ዘሁ 12፤1-7/
  ቀዳሚ ሰማዕት እስጢፋኖስ ስለገደሉት ሰዎች ተንበርክኮም። ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ እየጸለየ ብሎ ሲያማልድ እናየዋለን።/ሐዋ 7፤60/።
  ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ጢሞ 2፤1-2

  3. ኢየሱሰ ክርስቶስ የባህርይ አምላክ ነው ቅዱሳንም የጸጋ አማልክት ይባላሉ
  በመዝ 82፤1 እግዚአብሔር በአማልክት ማኅበር ቆመ፥ በአማልክትም መካከል ይፈርዳል። በአማልክት መካከል ሲል ሌሎች አምላኮች አሉ ማለት ሳይሆን ቅዱሳንን ነው አማልክት ያላቸው። እንዲሁም ቁጥር 6 ላይ 6 እኔ ግን። አማልክት ናችሁ፥ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ፤ በዚህም መሰረት አማልክት የሚለው ቅዱሳንን ነው።
  በዮሐ 10፤34-35 እነዚያን የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ካላቸው፥ በዚህም የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸው ከእግዚአብሔር ጋር የተነጋገሩ ቅዱሳን አማልክት እንደተባሉ ያስረዳል።
  እግዚአብሔር ነቢዩ ሙሴን በፈርኦን ላይ አምላክ አድርጎ እንደ ሾመው ሲናገር ዘጸ 7፤1

  4. ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉን አዋቂ ነው ቅዱሳንም እግዚአብሔር በሰጣቸው ጸጋ የተሰወረን ነገር ያውቃሉ
  ቅዱስ ጴጥሮስ ሐናኒያና ሰጲራ እቤታቸው ሆነው የተነጋገሩትን ሚስጢር ማንም ሳይነግረው አውቆታል። ሐዋ 5፤1-11 እንዲሁም ቅዱሱ የእግዚአብሔር ሰው ኤልሳ የሶሪያ ንጉስ የሚሰራውን ስራ እስራኤል ውስጥ በአንዲት ጎጆ ውስጥ ሆኖ ማወቅ ይችል ነበር።2ኛ ነገ 6፤12 ከባሪያዎቹም አንዱ። ጌታዬ ሆይ፥ እንዲህ እኮ አይደለም፤ ነገር ግን በእልፍኝህ ውስጥ ሆነህ የምትናገረውን በእስራኤል ዘንድ ያለ ነቢይ ኤልሳዕ ለእስራኤል ንጉሥ ይነግረዋል አለ።

  5. ኢየሱስ ክርስቶሰ ፈራጂ ነው ቅዱሳንም እርሱ በሰጣቸው ስልጣን ይፈርዳሉ
  ማቴ 19፤28 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው። እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተስ የተከተላችሁኝ፥ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ። ቅዱሳን ማማለድ አይደለም እንዲፈርዱ እርሱ እግዚአብሔር ሾሟቸዋል ፡፡
  እግዚአብሔር ምሥጢር የምንረዳበትን አእምሮ ይስጠን

  ReplyDelete
 39. 1. ሐተታውን የጀመረው ከየት መጣው ባልታወቀ ስዕልና መግለጫው ነው ፡፡ ራሱ ጸሐፊው ወይም ሌሎች አጽራረ ቤተ ክርስቲያን የሚባሉ ወገኖች ቴክኖሎጂን በመጠቀም ይሳሉት ፣ ትምህርታችንን ለመስደብ ይጠቀሙበት ማንም አያውቅም ፡፡ ነገር ግን በአገራችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስሟ የሚወደስበትና የሚመሰገንበት ቤተ ክርስቲያን ፣ የኢኦተቤ ስለ ሆነ ከጠጅ ቤትም ይሁን ከታክሲ ላይ ወይም ከሌላ ሥፍራ የተሳሳተ መልዕክት ነገርን ካገኙ ያንን ይዘው ኢኦተቤ ላይ መዝመት ሥራቸው አድርገውታል ፡፡

  ይህን ጽሁፍ ከፌስ ቡክ ላይ አወረድኩት በማለት ራሱ ጸሐፊው ከመሰከረልን ፣ ስለምን ከስዕሉ ባለቤት ጋር ውይይቱንና ትምህርቱን በዛው በኩል አይጨርስም ነበር ? የሚል ጥያቄ አቀርባለሁ ፡፡ ግለ ሰቦችና የሌላ እምነት ተከታዮች ሁሉ ለሚያስተላልፉት የሃይማኖት ትምህርት ተጠያቂው ማን ነው የሚሆነውስ ? ቤተ ክርስቲያንስ ይኸን ለማስቀረት ጽንፈኛነትን ማወጅ ይገባት ይሆን ወይንስ ምን ርምጃ እንድትውስድ ይመክራሉ ? እንደ ታዘብኩት ቤተ ክርስቲያን እንኳንስ የግለ ሰቦችን ፌስ ቡክና የታክሲ ጽሁፎችን ልትከታተል ፣ በአውደ ምሕረቷ ላይ የሚሰጡትንም ትምሕርቶች በአግባቡ ደንብ አውጥታ በመቆጣጠር ልትመራ አልቻለችም ፡፡ ያን ባለማድረጓም ነው ልጆቿ እርስ በርስ መግባባት ያልቻሉትና ዛሬ መንጋዎችን ሳይቀር በተለያየ ትምህርት የሚያምሱን ፡፡

  2. ወንድም ጸጋ ይህን ስዕል መነሻ በማድረግ ፣ ማስተላለፍ የፈለገውን የቅዱሳን ስዕላትን መጠቀም አግባብ እንዳልሆነና የተሳሳተ ትምህርት በማለት ከወንጌል ገላ 3፡1 ይተረጉምናል ፡፡ ጳውሎስ ይህን ትምህርት ያስተማረው ወንጌል ለተገረዙትና ላልተገረዙት ተብላ ስለተከፈለችና ፣ በእምነት መጽደቅን ያስተማራቸው የገላትያ ሰዎች ፣ ርሱ ካስተማራቸው ወንጌል ርቀው (ገላ 1፡6) የኦሪት ሕግን ወደሚሉት (ወደ መገረዝ) ስለተጓዙበት ነው ፡፡ ጠቅላላ ትምህርቱን ከምዕራፍ አንድ ጀምሮ ላነበበ ይኸን ትርጓሜ መረዳት ይችላል ፡፡ የአንደምታ መጽሐፍም ይኸንኑ ያስተምራል ፡፡

  ወንድም ጸጋ የሸሻቸው የኦሪት መጽሐፍት ግን ምስልን መሥራት ያስጀመረው እግዚአብሔር እንደ ሆነ ይመሰክራሉ ፡፡ ዘጸአት 2ዐ፡25-26 እግዚአብሔር የመላእክት ምስልን እንዲሰሩ ፣ የት ሥፍራ እንደሚያኖሩት እንዳዘዛቸው ይገልጻል ፡፡ ዘኁ 21፡8-9 የሚያትተውም ከናስ የተሰራ የእባብ ምስልን በማየት መፈወስ ፣ የጌታ መሰቀል ምሳሌ ተብሎ ቢተረጉሙትም ፣ በወቅቱ ግን ከናስ የተሰራ ምስልን ለፈውስነት ያዘዘ ራሱ ፈጣሪአችን እነደሆነ ቃሉ ይነበባል ፡፡ የጥጃ ምስልን የተቃወመ አምላክ የእባብ ምስልን ለድኀነት ሲፈቅድ በአግባቡ የምንገለገልበትና ልንገለገልበት የማይገባ መንገድ እንዳለ ያስረዳል ፡፡ በቤተ ክርስቲያናችንም የምንገለገልባቸው የቅዱሳትና የመላእክት ሰዕላት የጣዖት ተምሳሌት ሳይሆኑ እግዚአብሔር በምክንያትነት የሚወደስባቸውና የሚመሰገንባቸው ፤ እግዚአብሔርን በጽናት ላገለገሉ ሰዎችና መላእክት መታሰቢያነት የሚውሉ ቁሶች ናቸው እንጅ በዘዳግም 4፡15-19 እንዳስጠነቀቀውና እንደተመለከተው ዓይነት አምልኮ የሚደረግላቸው ጣዖቶች አይደሉም ፡፡

  በተጨማሪ ቤተ ክርስቲያናችን ቀደምት ሐዋርያት ስዕልን ለማስተማሪያነት እንደተጠቀሙበት ፣ ማንበብና መጻፍ የማይችሉትን መንጋዎቿን ፣ የቅዱሳት መጻሕፍትን ታሪክ በቀላሉ እንዲረዱና እንዲገነዘቡ ለማድረግ በየቤተ ክርስቲያን ግድግዳ ላይ መሳሏ ፣ የባዕድ አምልኮን ልታስተምርበት እንዳልሆነ በቀና ልቦና ሊረዱም ይገባል እላለሁ ፡፡

  3. “ብዙዎች ቅዱሳን የሚሏቸው በተጋድሎ ውስጥ ያለፉና ያንቀላፉ የቀደሙ ሰዎችን ብቻ ነው፡፡ ቅዱሳን የሚባሉት የቀደሙትና ዛሬ በሕይወት የሌሉት ብቻ ሳይሆኑ ዛሬ በሕይወት ያለነው ለወደፊቱም የሚነሡ ሁሉ ናቸው፡፡ ሩጫቸውን በድል ያጠናቀቁትን ብቻ ሳይሆኑ ዛሬ በትግል ውስጥ ያለነውም ነን፡፡” በማለት የራሱን ቡራኬ ለመውሰድ ትርጉም ይፈጥርልናል ፡፡ በርግጥ ቤተ ክርስቲያናችን የሚመሯትን ጳጳሳት ቅዱስ የሚል የስም ማዕረግ ትሰጣለች ፡፡ ነገር ግን በፈተና ውስጥ የሚጓዝ ሰውን በምን ዓይነት መመዘኛ ፈትሾ ነው ይህን የቅድስና ሹመት ላለነው ሁሉ ነው በማለት ራሱን የሚያክለው ? ይኸን በዚህ መልክስ ከተረዳው ለምን ጥቅም ሲባል በአባቶች ላይ የሆነና ያልሆነውን ሲወራባቸው ዝም ይላል ? ቅዱስን መቃወም በደል አይሆንምን ?

  ይቀጥላል

  ReplyDelete
 40. ክፍል ሁለት
  “ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በሕይወት ሳሉ በነበራቸው ስልጣንና ሀላፊነት አሁን ምንም ሊያደርጉ እንደማይችሉ” ይለናል ፤ ምሳሌ ተጠቅሶ ተሞቷል ፡፡ መጀመሪያ በምድር እንደ ሆኑት በሰማይም ፓትርያርክ ይሆናሉ ብሎ ያስተማረ ካህን ከየት መጣና ይኸ ተጠቀሰልን ? ፍርዳቸው እንኳን መጠናቀቁን ማረጋገጥ የማንችለውን አባታችንን ባልሆነ ቦታ ለምሳሌ እየጠራህ እባክህን አታንገላታቸው ፡፡ እንዲያውም በደላቸው እንዲቆጠር ፣ ይኸን ያንን እንዲባል የፈለግህ መስሎኛል ፤ እኔ ግን የራሴንም አልጨረስኩት እንኳንስ የሰውን ድክመት ልቆጥር ፡፡

  4. “ስለቅዱሳን ስናስብ ያለፉትን ቅዱሳን ከሌሎች ክርስቲያኖች የተለዩና ቅድስናን በራሳቸው ጥረት ያገኙ አድርገን ነው የምናስበው፡፡ «ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳችን እንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም፤» ብሏል፡፡ (2ቆሮ. 3፡5)፡፡”

  ወንድም ጸጋ ሰዎች የሆንን በሙሉ ነጻ ምርጫ አለን ፡፡ እግዚአብሔር ነጻ ምርጫችንን ተከትሎ መንገዳችን የቅድስና ቢሆን ፣ እንድንፈጽመው ይራዳናል ማለት ነው እንጅ ፤ እንደ እኔ ያለውን መንገደኛ ሁሉ ጭነቱን እየጫነ ጻድቅና ቅዱስ ሊያደርግ ይታገላል ማለት አይደለም ፡፡ ስለሆነም ቅዱሳን የሚባሉት ፣ ለቅድስና የሚያበቃ ትንሽ ፍሬ ሲያይባቸው ፣ ይባርካቸዋል ፣ ያግዛቸዋል ፣ ያከብራቸዋል ፣ ያጸድቃቸዋል ፡፡ አለበለዚያማ አምላክ ያዳላል ብለህ ልታስተምረን ፤ ለውድቀታችንና ለስንፍናችን ተጠያቂው ርሱ ነው ማለትህ ነው ፡፡

  5. “ቅዱስ ጳውሎስና በርናባስን የልስጥራን ሰዎች እንደ አምላክ ቆጥረው ሊሰዉላቸው ባፈለጉ ጊዜ” /ሥራ 14፡14-15/
  የጥንት የአይሁድ አምልኮን በሥርዓቱ ብትፈትሸው (አብርሃምና ሎጥን ዘፍ 18፡2-8 ፣ 19፡1-3) ፣ ሐዋርያው ጳውሎስም እንደ መሰከረው (ዕብ 13፡1-2) ፣ መላእክት በሰው አምሳል ይገለጣሉ የሚል እምነት አላቸው ፡፡ በመላእክት ዘንድ የሌለ ባህርይም በሉ ፣ ጠጡ የሚል መግለጫም አንብበናል ፡፡
  - በመጽሐፍ የተጠቀሱ ቅዱሳን ይኸንን የአምልኮ ወግና ልማድ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ሲሰግዱላቸው አምልኮ እንዳይሆን በማለት ተቃውመዋል
  - ቅዱሳን ለራሳቸው ክብርና ሙገሳ የሚሠሩና የሚታገሉ እንዳልሆኑም ለህዝብ ለማስተማር ሲሉ የሚሰግዱላቸውን ሁሉ አግደዋል
  - በመጽሐፍ ቃል መሠረት መላእክት እንኳን ሳይቀሩ የአምልኮ ስግደትን ተቃውመዋል ፤ ቅዱሳን ደግሞ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ፣ በኃጢአት እንዳሉ የሚቆጥሩ በመሆናቸው ፣ እንደ ዘመናችን ሰዎች ዝቅ ሲሉላቸው አንገታቸውን ማስረዘምም ስላለመዱ ስግደትን ሁሉ አታድርጉ ይሉናል ፡፡

  ቢሆንም ቅዱሳን አባቶችና መላእክት ይኸን ቢያስተምሩም አልተሰገደላቸውም ብሎ መደምደም ግን እጅግ ያስቸግረኛል ፡፡ ምክንያቱም ዛሬ በመሰልጠናችን በከተማዎቻችን ቀረ እንጅ ፣ በባህላችን አንዱ ወገን ዝቅ ብሎ ሰላምታውን ሲያቀርብ ፤ ተቀባዩ ወገን ኧረ ስለ እግዚአብሔር አይገባም በማለት ይከላከላል ፣ ሰላምታ አቅራቢው ግን የጀመረውን ከመፈጸም አይገታም ፡፡ ይኸን አይቻለሁ ፡፡ ዛሬም በገጠርና በየገዳማቱ ይተገበራል ፡፡

  6 “ዛሬ በስማቸው የምናደርገውን አምልኮት ዝማሬና ስግደት ሁሉ ቅዱሳን አያውቁትም፡፡” ፤ “ቅዱሳን ሕያዋን ቢሆኑም በዚህ ምድር ላይ የሚሠራውን እያንዳንዱን ነገር የማወቅ ችሎታ የላቸውም፡፡” ብለህ ለማስተማር ፣ እኛም እንድንቀበልህ የት ሥፍራ ሄደህ አየህና አረጋገጥህ ?

  7. “ቅዱሳን በዚህ ምድር ሳሉ ለአምላካቸው ባላቸው ፍቅርና ታማኝነት በሰሩት በጎ ሥራና በተጋደሉት መልካም ገድል ስማቸው ሲታወስ ኖራል፡፡” ይኸን ከተቀበልክም ትልቅ ነገር ነው ፡፡ ትናንት ያልነበረ መሻሻል ፡፡ ከሞቱ በኋላ አበቃላቸው ስትል ኖረህ ፣ ዛሬ አለማወቃቸውን ብቻ መከራከሪያ አድርገሃል ፤ ቀደም ለምን ሥራቸውን ፈጽመው ከሄዱ በኋላ ስለነርሱ ማውሳት የለብንም ስትል ዛሬ የስማቸውን መታወስ ተቀበልህ ? አሁንም እግዚአብሔር ይርዳህ ፡፡ ብዙውን እያወቅህ አጥፊ ብትሆንም ፤ ወደ ቤተ ክርስቲያናችን ትምህርተ ሃይማኖት እየመጣህ ነው ፡፡ ስለዚህም መለወጥ ጌታን ተመስገን አመሰግናለሁ ፡፡

  ምስጢርን የሚገልጹ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይርዱን

  ReplyDelete
 41. ምስጢርን የሚገልጹ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይርዱን ??????//
  Ab Wold M/Kidus 3 nachewu Ende? My Brother endet yerdun telaleh bayhon yerdan bel

  ReplyDelete