Wednesday, December 19, 2012

አባ ሳሙኤል ቀጣዩ ፓትርያርክ እኔ ነኝ በማለት እያወሩና እያስወሩ ነው

ቀጣዩ ፓትርያርክ ማን ይሆናል? የሚለው ጥያቄ በመላምትና በግምት ደረጃ አቡነ እከሌ ናቸው አይደለም አቡነ እከሌ ናቸው እየተባለ መወራት ከጀመረ ወራቶች ተቆጥረዋል፡፡ በዚህ መካከል ሁሉም የየራሱን ፓትርያርክ ለማስቀመጥ እየተንቀሳቀሰ መሆኑም ይወራል፡፡ የቤተክርስቲያኗን አስተዳደር የመቆጣጠር ህልም ያለውና ከአቡነ ጳውሎስ ሞት በኋላ ሰፊ እድል እንዳገኘ ቆጥሮ እንዳሻው እየሆነ ያለው ማህበረ ቅዱሳንም ይፋ ባያወጣም የራሱን ጳጳስ አቡነ እከሌ ካልሆኑ አቡነ እከሌ በሚል በአማራጭ ደረጃ ማስቀመጡም እንደዚሁ ከሚናፈሱት ወሬዎች መካከል ይገኛል፡፡ ማህበሩ ካጫቸው ጳጳሳት መካከል አባ ሳሙኤል አንዱ መሆናቸው አቡነ ጳውሎስ በሕይወት እያሉ በስፋት ሲወራ የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ለዚህ አንዱ ማሳያ ማህበሩም ይሁን አባ ሳሙኤል ራሳቸውን ተተኪው ፓትርያርክ አድርገው የመመልከት ነገር ነበራቸው፡፡ የማህበረ ቅዱሳን እጅ ያለባቸው የግል መጽሔቶችና ጋዜጦች ይህን በስፋት ሲያራግቡ ነበር፡፡ በአቡነ ጳውሎስ ጊዜ እንኳን የአቡነ ጳውሎስን ፎቶ ከአባ ሳሙኤል ፎቶ ጋር በማውጣት ሁለቱን ተገዳዳሪዎች አድርጎ የማቅረብ ነገር ነበር፡፡ ከዚህም ሲያልፍ አባ ሳሙኤልን «ብፁዕ» ከሚለው የሹመት ስም አልፎ ፓትርያርኩ በሚጠሩበት «ቅዱስ» የሚለውን ማእረግ ሰተው የጻፉ ጋዜጦችና መጽሔቶች ነበሩ፡፡
ቀጣዩን ፓትርያርክ ለመሰየም ከፊት ለፊት ትልቅ የቤት ስራ የሚጠብቀው ሲኖዶስ በምርጫ ህጉ ላይ እየተወዛገበ ባለበት በዚህ ወቅት እነማን ለፓትርያርክነት እንደሚታጩ ገና በውል ባልታወቀበት ሁኔታ አንዳንድ ሚዲያዎች ፓትርያርክነቱ ከእገሌና ከእገሌ ውጪ ሊሆን አይችልም እያሉ ነው፡፡ ማራኪ የተባለው መጽሄት በህዳር 2005 እትሙ «እርቀ ሰላሙና የአዲሱ ፓትርያርክ ጭላንጭል» በሚል ርእስ ባወጣው ጽሁፍ ውስጥ የብፁዕ አቡነ ማትያስንና የአባ ሳሙኤልን ፎቶግራፍ ጎን ለጎን አድርጎ በአባ ሳሙኤልና በብፁዕ አቡነ ማትያስ መካከል ውድድር እየተደረገ እንደሆነ ጽፏል፡፡ «አዲሱ ፓትርያርክ ሲኖዶስ በወሰነው መንገድ ሲከናወን ግን ስድስተኛው ፓትርያርክ ይሆናሉ ተብለው ሰፊ ግምት የተሰጣቸው አባቶች ከወዲሁ የድጋፍ ፊርማ ሳይቀር እየተሰበሰበላቸው ይመስላል፡፡ ቀደም ሲል የላቀ ግምት ከተሰጣቸው አቡነ ማትያስ በተጨማሪ በአንድ ወቅት ከአቡነ ጳውሎስ ጋር ውዝግብ ውስጥ የነበሩትና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ የነበሩት አቡነ ሳሙኤል ግምታቸው ከፍ እያለ ሄዷል፡፡» ብሏል፡፡ ማራኪ እንዲህ ብሎ የጻፈው ከምን ተንስቶ ይሆን? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ቢሆንም መልሱ ቀላል ነው፡፡ ከልምድ እንደሚታወቀው አባ ሳሙኤል ብር ከፍለው ነው እንዲህ ተብሎ እንዲጻፍ ያደረጉት ብሎ መደምደም ይቻላል፡፡ ይህ አቡነ ጳውሎስ በሕይወት እያሉ ሲያደርጉት የነበረው ስራቸው መሆኑን ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡
ይሁን እንጂ አባ ሳሙኤል ለፕትርክና ከሚታሰቡት መካከል ናቸው መባሉ ምክንያት አልተገኘለትም፡፡ ሰውዬው በአጭሯ የጵጵስና እድሜያቸው ፓትርያርክ ለመሆን እንደሚመኙና ለዚሁ ሲታገሉ እንደቆዩ አገር ያውቃል፡፡ ነገር ግን ያላቸው ፕሮፋይል ለዚህ እንደማያበቃቸው ብዙዎች እየተናገሩ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ሐገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በነበሩ ጊዜ የጥቅም ተጋሪዎቻቸው ካልሆኑ በቀር በብዙዎች ዘንድ ስማቸው በመልካም አይነሳም፡፡ ከጥቂት ኣመታት በፊት በርካታ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ካህናትን ሲያጉላሉና የተለያየ ግፍ ሲፈጽሙባቸው እንደነበርና ብዙዎች ጉዳያቸውን ወደ ኢትዮጵያ ሰባዊ መብት ኮምሽን ይዘው በመሄድ በተደጋጋሚ አቤት ማለታቸውና ኮምሽኑ መፍትሄ ለማፈላለግ መንቀሳቀሱ ይታወሳል፡፡ ከእርሳቸው አምባገነንነት የተነሳ ኮሚሽኑ በከፍተኛ ደረጃ እስከማማረርና ከቤተክህነት ፍትሕ በመጥፋቱና የሰብአዊ ምብት ጥሰት በመበራከቱ ቤተክህነትን እስከመውቀስ የደረሰበት ጊዜ ነበር፡፡ ብዙዎች መፍትሄ ሳያገኙ ለኣመታት በከፍተኛ ሁኔታ መጉላላት ደርሶባቸዋል፡፡ የስንቱ ቤት ከፍተኛ ችግር እንደደረሰበት የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ እስከ ፓርላማ ደርሶ ሲያነጋግር እንደነበር አይዘነጋም፡፡ አባ ሳሙኤል ግን መንግስት በሃይማኖት ሃይማኖትም በመንግስት ጣልቃ አይገባም የሚለውን ህገ መንግስታዊ ድንጋጌ አለቦታው በመጥቀስ ሰብአዊ መብትን ለማፈን ሲጠቀሙበት እንደነበር በወቅቱ በጊዜው በአንዳንድ ሚዲያ ጭምር ይፋ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡
ያኔ በአዲስ አበባ ካህናት ላይ ግፍ መፈጸም ያላቆሙትና በግፈኛ ሥራቸው ቀጥለው የነበሩት አባ ሳሙኤል የሾሟቸውንና ለትልቅ ደረጃ ያበቋቸውን አቡነ ጳውሎስን ለመገልበጥ ባሴሩት ሴራ ገመናቸው ወጣ፡፡ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተነሱ፡፡ ዘሪሁን ሙላቱ «የጳጳሱ ቅሌት» የሚል መፅሀፍ ጽፎ አባ ሳሙኤል ከቅድስናውም ከትምህርቱም የሌሉበት መሆናቸውን በተጨባጭ ማስረጃዎች ነገረን፡፡ በዚያ መፅሀፍ የተዘረዘረው የጳጳሱ ቅሌት በልቦለድ መልክ መቅረቡ እንጂ ታሪኩ በሙሉ እውነተኛ መሆኑን አባ ሳሙኤልን እንደ ዘሪሁን በቅርበት የሚያውቁ ሁሉ ሲናገሩ ይሰማል፡፡ እሳቸውም የቅድስናቸውን ጉድለት መሸፈን ሳይችሉ በዚያው መንገድ እየተጓዙ ናቸው፡፡ ባይማሩም የተማርሁኝ ነኝ ለማለት ግን ወደኋላ አላሉም፡፡ ለዚህም የተለያዩ ሰዎችን ጻፉልኝ እያሉና እያጻፉ በስማቸው መፃህፍትን ማሳተም አንዱ ስልታቸው አድርገውታል፡፡ በዚህም ብዙ መፅሀፍ ያላቸው ጳጳስ በመባል የሌላቸውን ገፅታ ለመገንባት ሲጥሩ ተስተውሏል፡፡ በሟቹ አባ ሚካኤል ቤተሰቦች ውስጥ ጣልቃ በመግባት ሌላ ገመና እንዳይወጣ በሚል የጀመሩት ተገቢ ያልሆነ ጥረትና ጉዳዩ ይበልጥ እንዲራገብና የቤተክርስቲያን ገመና አደባባይ ላይ እንዲወጣ በየፍርድ ቤቱም በመካሰስ ትልቁን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ታይቶ በማይታወቅና ከአባቶች በማይጠበቅ ሁኔታ ግለሰቦችን ፍርድቤት ከስሰው በመቅረብም የመጀመሪያው ጳጳስ ናቸው፡፡ ሌላው ቢቀር እንኳ እነዚህ ስራዎቻቸው ከጵጵስና የሚያሽሩ እንጂ ለፓትርያርክነት ምርጫ እጩ የሚያደርጉ አይሆኑም፡፡ ከዚህ ቀደም በመረጃዎች አስደግፈን ያቀረብናቸው ዘገባዎች እንደሚያሳዩት አባ ሳሙኤል እንኳን ለበለጠው ሹመት ለፓትርያርክነት አሁን ለሚገኙበት ለጵጵስናውም ብዙ ችግሮች ያሉባቸው ሰው መሆናቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ይህን የአደባባይ ሚስጢር የት አድርጎ ነው ማራኪ የተባለው መፅሄት ለፓትርያርክነት አባ ሳሙኤል ግምታቸው ከፍ እያለ ሄዷል የሚለው?
ከማራኪ ዘገባ በስተጀርባ ወይ ማህበረ ቅዱሳን ወይም አባ ሳሙኤል ራሳቸው አሉ፡፡ የአባ ሳሙኤልና የማህበረ ቅዱሳን ፍቅር የጲላጦስና የሄሮድስ አይነት ፍቅር ነው፡፡ ሁለቱን አንድ ያደረጋቸው እውነተኛ ፍቅር ሳይሆን በአቡነ ጳውሎስ ላይ ይዘው የነበረው አቋም ነው፡፡ ሁለቱም የየራሳቸው አጀንዳና ሚስጢር ስላላቸው ልብ ለልብ ባይገናኙም አቡነ ጳውሎስ በህይወት እያሉ ማህበረ ቅዱሳን አባ ሳሙኤልን ይዞ አቡነ ጳውሎስን ማበሳጨትና ያሻውን ማድረግ ስለቻለ ለዚህ አላማው አጥብቆ ያዛቸውና ተጠቀመባቸው፡፡ እርሳቸውም ዘሪሁን ከጻፈባቸው መጽሐፍ ጋር ተያይዞና ከዚያም በፊት ባለባቸው የቅድስና ጉድለት ሙስናና ብዙ ግፍና የአስተዳደር በደል ስማቸውን ሊያድስና ድጋፍ ሊሰጣቸው የሚችል ማህበረ ቅዱሳን ነው ብለው ስላሰቡ ከልብ ባያምኑትም ማህበሩም ባያምናቸውም የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው በሚለው ቀመር «ተዋደው» ለመሸጋገሪያነት በፍቅር ከነፉለት፡፡ ህገወጡን የግንቦቱን ውግዘት ህጋዊ ባልሆነ አሰራር በመምራትም ለማህበሩ ያላቸውን ታማኝነት አሳዩ፡፡ ይህ ፍቅር እስካሁን ድረስ ዘልቋል፡፡ ስለዚህ አሁን ብድር የመመለሱ ተራው የማህበረ ቅዱሳን ስለሆነ ቀጣዩ ፓትርያርክ አባ ሳሙኤል ይሆናሉ በማለት እያስወራ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ በቀር አሁን ባለው ሁኔታ አባ ሳሙኤል ፓትርያርክ ይሆናሉ ብሎ ማሰብ ከባድ ነው፡፡
ሌላው ቀርቶ ለፓትርያርክነት በወጣው መስፈርት ቢመዘኑ አባ ሳሙኤል ከትምህርቱም ከቅድስናውም የሉበትምና የሀሰት መረጃ ካላቀረቡ በቀር መስፈርቱን እንደማያሟሉ ብዙዎች እየተናገሩ ነው፡፡ ደግሞስ የሲኖዶስ አባላት የሆኑ ጳጳሳት አባ ሳሙኤል ፓትርያርክ ሊሆኑ ነው ቢባል ይቀበላሉ ወይ? የሚለው የብዙዎች ስጋት ሆኗል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ አዲስ አድማስ ጋዜጣ በታህሳስ 6 እትሙ ላይ «የጳጳሱ ቅሌት» መጽሐፍ ጸሀፊ በ«የጳጳሱ ስኬት» መጽሀፍ ይቅርታ ጠየቀ» የሚል ዘገባ አስነብቧል፡፡ የዚህ ሀገባ ዋና መልእክትም ቀጣዩ ፓትርያርክ አባ ሳሙኤል ይሆናሉ የሚል አንድምታ እንዲኖር ለማደረግ እንደሆነ ተንታኞች ይናገራሉ፡፡ ሃይማኖት የለሹና ህሊናውን ለገንዘብ ከሸጠ የሰነበተው ዘሪሁን ሙላቱ አስቀድሞ «የጳጳሱ ቅሌት» የሚል መጽሐፍ በአባ ሳሙኤል ላይ ከጻፈባቸው በኋላ በዚህ ወቅት «የጳጳሱ ስኬት» የሚል መጽሀፍ ጽፎ ይቅርታ ጠየቀ የተባለው አያድርገውና እንደተባለው አባ ሳሙኤል ቀጣዩ ፓትርያርክ ከሆኑ ዘሪሁን ዳግም የአባ ሳሙኤል ወዳጅ ሆኜ ተጠቃሚ እሆናለሁ ብሎ በማሰብ እንደሆነ ብዙዎች አልተጠራጠሩም፡፡ ዘሪሁን ከዚህ ቀደም መጋቤ ሐዲስ በጋሻው ደሳለኝ ለጻፈው «የመስቀሉ ስር ቁማርተኞች» መጽሐፍ «የስድብ አፍ» በሚል ርእስ አቡነ ጳውሎስን ደስ ለማሰኘት በያኔው አባ ተከስተ በዛሬ አባ ሳሙኤል ምክር ማዘጋጀቱና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በኩል በየቤተ ክርስቲያኑ በግዳጅ እንዲሸጥ መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡ አባ ሳሙኤል በአቡነ ጳውሎስ ላይ መፈንቅለ ፓትርያርክ ለማድረግ ከማህበረ ቅዱሳን ጋር እያሴሩ ባለበትና በሚሌኒየሙ ዝግጅት ላይ ሁለቱም በኮሚቴው ውስጥ እያሉ እርሳቸው ሳያውቁ ሀሰተኛ ደረሰኞችን በማቅረብ ዘሪሁን በብዙ ሺህ የሚቆጠር ገንዘብ ወደ ኪሱ በመክተቱ ምክንያት የዘሪሁንና የአባ ሳሙኤል ፍቅር ችግር ውስጥ በገባበት ወቅት ወደአቡነ ጳውሎስ ተጠግቶ «የጳጳሱ ቅሌት» የተሰኘውን መጽሐፍ እንደጻፈ ታውቋል፡፡ መጽሐፉን በብእር ስም ቢጻፍም አባ ሳሙኤል ከዘሪሁን ራስ አልወርድም ብለው ከሰውት እርሱ ቢክድም ጥፋተኛ ተብሎ ለእስር እንደተዳረገ የሚታወስ ነው፡፡ ያኔ በፍርድ ቤት የካደውን ሐቅ ዛሬ አምኖ ይቅርታ መጠየቁ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው፡፡ በአባ ሳሙኤል ላይ የጳጳሱ ቅሌትን ከጻፈ ከጥቂት ጊዜ በኋላም «የሐውልቱ ስር ቁማርተኞች» የሚል መጽሐፍ ጽፎ የሌሎችን ስም በማጥፋቱ ተከሶ ከታሰረ በኋላ በገደብ ተለቋል፡፡ አሁን ደግሞ ጥቅም የሚገኝበትን ሌላ እድል ለመሞከር ፊቱን በጨው ታጥቦ አባ ሳሙኤልን ይቅርታ ጠየቀ ተብሏል፡፡ ጥፋትን በማመን ይቅርታ መጠየቅ የታላቅነት ምልክት ቢሆንም የዘሪሁን ይቅርታ ግን ከታላቅነት የሚመነጭ አለመሆኑን ከግለሰቡ ማንነት መረዳት ይቻላል፡፡ እንደ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ዘገባ ዘሪሁን «በጳጳሱ ቅሌት መጽሐፍ ውስጥ የተገለጹት  «ሳሙኤል» ከሊቀጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ጋራ በምንም መልኩ ግንኙነት የሌላቸው ናቸው» በማለቱ ራሱን ትልቅ ትዝብት ላይ በመጣል ህሊናው አብሮት የሌለ መሆኑን በራሱ የመሰከረ ሲሆን፣ መጽሐፉን የጻፈው በአባ ሳሙኤል ላይ ጥላቻ ባላቸው ግለሰቦች ፍላጎት በመገዛቱ መሆኑን አምኗል፡፡ አባ ሳሙኤልን ይቅርታ ሲጠይቅ «ገዙኝ» ያላቸውን ሰዎች ደግሞ እያስቀየመ ነው፡፡ ለዚህ ነው ይቅርታው የታላቅነት ምልክት የሆነው ይቅርታ አይደለም የምንለው፡፡ ለሁሉም አሁን ይቅርታ የጠየቀው በማን ወይም በስንት ብር ተገዝቶ እንደሆነ ደግሞ ወደፊት እንደሚገልጽ በተስፋ እንጠብቃለን፡፡ 

22 comments:

 1. hulunim aynet sew hono menor yichalal mallet new. Ere Egziabiher yayal??

  ReplyDelete
 2. አስቀድመህ ከወንድምህ ጋር ታረቅ /ማቴ. 5፥24/
  ታኅሣሥ 10 ቀን 2005 ዓ.ም.
  ለቤተ ክርስቲያናችን አገልግሎት ስኬት የአባቶቻችን ስምምነት ወሳኝ ነው
  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በሥጋ ሕይወት በነበሩበት ባለፉት ዓመታት “ስደተኛ ሲኖዶስ” ተብሎ ከተጠራው በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ አባቶች ጋር ዕርቅ ለመፈጸም ጥረት ይደረግ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ተጨባጭ ለውጥ መመዝገብ ሳይችል በእንጥልጥል እንዳለ ቅዱስነታቸው ዐረፉ፡፡

  የእርሳቸው ዕረፍት ቀጣዩ የቤተ ክርስቲያኒቱ ፓትርያርክ ከመመረጣቸው በፊት በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ ተለይተው ከሚኖሩ አባቶች ጋር ውይይት ለመጀመር አስገዳጅ ሁኔታ አምጥቷል፡፡ ይህ እንዲታሰብ ግድ የሚያደርገውም ቀጣዩ ፓትርያርክ የሚሰየሙበት መንገድ ሁሉን የማያስማማ ከሆነ የነበረውን ልዩነት የሚያሰፋ ውዝግብ በዚህች ታሪካዊ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሊያስከትል እንደሚችል ከወዲሁ መገመት ስለሚቻል ነው፡፡ ይህንን ከግምት አስገብቶ የወቅቱን አንገብጋቢነት ተረድቶ ወደ ዕርቅ የሚያደርስ ውይይት ማድረግ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኒቱን ወሳኝ አገልግሎቶች በብቃትና በስፋት ለመስጠት፣ ጠንካራ መሠረትም ለመገንባት ስለሚያስችል ነው፡፡

  በመሠረቱ ሲኖዶስ ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ በጉልህ የተገለጠ ተግባሩ መለያየቶችን መፍታት ዘመኑን የዋጀ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት መትከል ነው፡፡ ስለዚህ ሲኖዶስ ሲታሰብ ሰላምና አንድነት ይታሰባሉ፡፡ ትሕትናና ፍቅር ይነግሣሉ፡፡ ይህ የሚሆንበት ዋናው ምክንያት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠውን የሐዋርያዊ አገልግሎት አደራ መንጋውን የመጠበቅ ሓላፊነት ከመወጣት ሌላ ለሚሰበሰበው መንጋ አርአያነት ያለው ሕይወት አባቶቻችን እንዲኖራቸው፣ ብርሃናቸውም በዓለም እንዲያበራ ስለታዘዙም ነው፡፡

  እነዚህ የክርስትና ዐበይት ተግባራት በአባቶቻችን ደግሞ ጎልተው እንዲገለጹ ይፈለጋል፡፡ አባቶች የክርስቶስን መልክ /እርሱን መምሰልን/ እንደያዙ በሚያስበው የእግዚአብሔር መንጋ፣ እንዲሁም የምድር ጨው ሆነን ሕይወታቸውን ለማጣፈጥ እንድንበቃ አደራ በተሰጡን የምድር አሕዛብ ሁሉ ላይ በጎ ተፅዕኖ ለማሳረፍ ብፁዓን አባቶች መልካሙን ጎዳና ሁሉ ሲከተሉ መገኘታቸው ታላቅ ሚና አለው፡፡

  ከዚህ ጎዳና ወጥተን ፍቅርን በማጣት፣ በጠብ በክርክር ጸንተን ብንገኝ ፍቅር ከሆነ እግዚአብሔር ጋር ለመኖር ባለመፍቀዳችን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ከእርሱ ጋር እንዳይኖሩ ማሰናከያ በመሆናችንም ጭምር ያዝናል፤ ይፈርዳል፡፡ ስለዚህ ለብፁዐን አባቶች ብቻ ሳይሆን በክርስቲያኖች ሕይወትም በፍቅር ጸንቶ መኖር፣ ከበደልንም በይቅርታና በዕርቅ ሕይወት ውስጥ ማለፍ ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው፡፡ የዚህ ሕይወት መሠረቱ ከሞት ወደ ሕይወት የተሸጋገርንበት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ያደረገው ዕርቅ ነው፡፡ ጠላቶቹ ከሆነው ከእኛ ጋር እግዚአብሔር ታረቀ መባሉ የሕይወታችን መሠረት ፍቅር መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡ ስለ ዕርቅ ሕይወት በብዙ ምሳሌና በብዙ ኃይለ ቃል ራሱ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረንም በመሆኑ በጉልሕ በሕይወታችን መንጸባረቅ የሚገባው የጽድቅ ሥራ ነው፡፡

  ለእግዚአብሔር ከምናቀርበው ከየትኛውም ዓይነት መባዕ አገልግሎታችን በፊት ከወንድሞቻችን መታረቅ እንደሚገባ ጌታችን አበክሮ ያስተማረው የሕይወት ቃል ነው፡፡ “አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ” ያለው የጌታ ቃል ይልቁንም በቤተ መቅደሱ ዕለት ዕለት መሥዋዕት ለሚያቀርቡ፣ ብዙዎችን በጸጋ እግዚአብሔር ባዕለ ጸጋ ለሚያደርጉ፣ ምስጢራትንም ሁሉ ለሚፈጽሙ፣ የሃይማኖትና የሥነ ምግባር ምልክት ለሆኑ ከሁለቱም ወገን ላሉ ብፁዐን አባቶች የሚያስተምሩት ብቻ ሳይሆን ዘወትር እንዲኖሩት የሚጠበቅ ክርስቲያናዊ ሕይወት ነው፡፡

  ይህ በመሆኑም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል “ክርክርና መለያየት አለ” መባሉ ሳይሆን ክርክሩን መፍታት፣ ልዩነትን ወደ አንድነት ስምምነት ማምጣት አለመቻል ከላይ የጠቀስነውን ወሳኝ የሕይወት ቃል የሚፈታተን ይሆናል ማለት ነው፡፡ ከዚያም አልፎ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመምራት ባለን አቅምና በጎ ፈቃድ ላይ ጥያቄ የሚያሥነሣ ይሆናል፡፡ በዚህ የማይደሰተው እግዚአብሔርም ብቻ አይደለም፡፡ ከሕፃን እስከ አዋቂ ያሉ የክርስቶስ ቤተሰቦችም ናቸው፡፡

  ስለዚህ ቤተ ክርስቲያናችንን ወደ አንድነት የሚያመጣ ዕርቀ ሰላም መፈጸም ከሃይማኖታዊ ሥነ ምግባር አንጻር፣ ለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ከማሰብ አንጻር፣ መንጋውን ከማነጽና ሐዋርያዊ አገልግሎትን ከማቅናት አንጻር ለአባቶቻችን ግዴታ ይሆንባቸዋል፡፡ የሚፈለገው ዕርቀ ሰላም እውን እንዲሆንም ለእግዚአብሔር ፈቃድ፣ ለእውነት፣ ለኅሊና ምስክርነት መገዛት አግባብ ይሆናል፡፡

  ከዚህ በፊትም ማኅበረ ቅዱሳን እንዳስገነዘበው አባቶች ሰላሙን ለማምጣት የሚያስችሉ ቀኖናዊ ጉዳዮችም ላይ ለመወሰን ለማጽናትም መንፈሳዊ ሥልጣንን የተጎናጸፉ በመሆናቸው ዕንቅፋትን ማራቅ ይችላሉ፡፡ የዕርቅ ሒደቱ ሲፈጸምም ሃይማኖታዊ መልክ ያጡ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትና ምእመናንን የማያሳምኑ ቅድመ ሁኔታዎችን ከመደርደር መታቀበ ከተቻለ በተስፋ የተሞላ ሒደት እንደሚሆን ይታመናል፡፡

  ከማንምና ከምንም በላይ የቤተ ክርስቲያናችንን ቤተሰብ ማሳመን የማያስችሉ እርምጃዎች ውስጥ መግባት ተአማኒነትን ሊያሳጡ ይችላሉ፡፡ ለዓመታት የዘለቀውን መለያየት /ውዝግብ/ ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ውስጥም የካህናቱ የሰንበት ትምህርት ቤቶች የአገልግሎት ማኅበራትና በአጠቃላይ የሕዝበ ክርስቲያኑ ሐሳብና አስተያየቶች ከግምት የሚገቡበት አካሔድ ሊኖር ይገባል፡፡ ሕዝበ ክርስቲያኑ ካልተሰማ በቀጣዩ ጊዜ በቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር አካላት ላይ የሚኖረው አመኔታ ይላላል፡፡ በመሆኑም በዚህ በዕርቁ ሒደት ክርስቲያኖች ያላቸው ሐሳብ ሊመረመር ይገባል፡፡ ስለዚህ ሁሉም የሃይማኖት ቤተሰብ ደስ የሚሰኝበት ምዕራፍ ላይ ለመድረስ መትጋት ከአባቶቻችን ይጠበቃል፡፡

  ስለዚህም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ለሰላሙ መስፈን አስፈላጊ የሆነ ዋጋ እንዲከፈል ግፊት በማድረግ ሊረባረቡ ይገባል፡፡ ምእመናንም ከካህናት አባቶች ጋር በጸሎት በመትጋት ለዚህ ችግር ዘላቂ መፍትሔ እግዚአብሔር እንዲሰጠን መማጸን ይገባናል፡፡ የተጀመሩትን ሒደቶች ሁሉ በእውነተኛነት በሚዛናዊነት እየተከታተሉ በጎ ተጽዕኖ ማሳደር ይገባናል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ያሳለፈችው ያለፉት ዓመታት ኣሳዘኝ ሁኔታዎች እንዳይቀጥሉ ዛሬ ላይ ማድረግ የሚገባንን ሁሉ ማድረግ እንደሚገባን ማኅበረ ቅዱሳን ያምናል፡፡ ለዚህም ይሠራል፡፡
  ወስብሐት ለእግዚአብሔር

  ምንጭ፡- ሐመር መጽሔት 20ኛ ዓመት ቁጥር 8 ታኅሣሥ 2005 ዓ.ም.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማቅ ለማያውቅህ ታጠን! ሀመርህ ላይ እንዲህ ብትጽፍም በተግባር እያደረክ ያለው ግን ሌላ ነው፡፡ በአሁኑ ሰኣት አባ ሳሙኤልን ብቻ ሳይሆን አባ ሉቃስን ፓትርያርክ ለማድረግ እየሰራህ እንደሆነ ግልጽ ሆኗል፡፡ እርሱ ሚስቱን ፈቶ ደቡብ ዲላ ላይ አንዱን ጎረምሳ ግብረሰዶም ካልፈጸምኩብህ ብሎ ሲታገል የነበረና አዲስ አባ ሲመጣ አራት ኪሎ ላይ አልቤርጎ ሴት ይዞ የሚያድር የነበረ ነው፡፡ ሰሞኑን የቤተክርስታኗን የቅርስ መምሪያ ስራ ነጥቃችሁ በቱሪዝም ዙሪያ ባዘጋጃችሁት አውደጥናት ላይ ይህን ጉደኛ አቶ ሉቃስ ዋና ተናጋሪ በማድረግና ፖለቲካና ሃይማኖትን እያጣቀሰ እንዲናገር በማድረግ አንዱ እጩአችሁ እሱ መሆኑን ነግራችሁናል፡፡ ውስጥ ለውስጥ እንዲህ ያለ መሰሪ ስራ እየሰራችሁ ላይ ላዩን እርቅ ብትሉ ማንም አይሰማችሁም፡፡ ከማንም ይልቅ እርቁን የምትቃወሙት እናንተ ናችሁ፡፡ ስለዚህ ስለእርቅ ለማውራት ምንም ሞራል የላችሁምና ዝም በሉ፡፡

   Delete
  2. የሰዎን ግላዊ ጉዳይ የሆውን ስህተትና ሃጢዓት ትተህ ስለ ሐይማኖት ስህተት ብትጽፍልን ይሻል ነበር

   Delete
  3. ይቅር ይበላችሁ!!!

   Delete
 3. Egziabher lemishomew aba selamawoch tikatelalach, Gena tinedalachu!!!
  Everybody know u r woyane ,with no relgion.u r main point is also clear it is about the tigray ethnic.
  I wonder how devil fights with the word of God inside of u. go to hell with aba pawulos blood suckers!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Gena wongel endalgebah anegagerih yastawiqibihal. Tolo nisha gebana keamlakih gar tareq. Firdun leEgziabeher tewow. Yesidib qal minchu gilits new.

   Delete
 4. ዘሪሁን እኮ ከሀዲ ነው፡፡ እግዚአብሔር የለም ስብከት አገልግሎቴ ሳይሆን እንጀራዬ ነው ይል የነበረ ደፋር ነው፡፡ ከሱ ምን ይጠበቃል? አምላኩን ገንዘቡን አድርጎ የለ!!!!!!!

  ReplyDelete
 5. ዘሪሁንና ማህበረ ቅዱሳን በጳጳሱ ስኬት መጽሀፍ ጠቡ ውስጥ ናቸው፡፡ የተጣሉትም ይህን መጽሀፍ ለምን ታወጣለህ በሚል ነው፡፡ የመጽሀፉ መውጣት የአባ ሳሙኤልን ገጽታ የሚያስተካክል መስሎ ስለተሰማቸው ነው፡፡ በእነ አሉላ የተመራው የማቅ ቡድንም አባ ሳሙኤል ቤት ሄዶ ያነጋገራቸው ሲሆን፣ ይህ መጽሀፍ መውጣቱ የቀድሞውን መጽሐፍ ይቀሰቅስቦታልና ቢቀር ጥሩ ነው ያሏቸው ሲሆን አባ ሳሙኤል ምንም ሳያናግሯቸው ውጡልኝ ብለው አስወጥተዋቸዋል፡፡ ይህም የሚያሳየው ማህበሩ አባ ሳሙኤልን እንደማይፈልጋቸውና ለአላማው ማስፈጸሚያነት መጠቀም እንዳሰበ ነው፡፡ እንዲህ ባይሆንማ ኖሮ በመጽሀፉ መወጣት ደስ ባለው ነበረ፡፡ ለነገሩ የቤተ ክህነት ፍቅር እንዲሁ ነው

  ReplyDelete
 6. ዘሪሁንና ማህበረ ቅዱሳን በጳጳሱ ስኬት መጽሀፍ ጠቡ ውስጥ ናቸው፡፡ የተጣሉትም ይህን መጽሀፍ ለምን ታወጣለህ በሚል ነው፡፡ የመጽሀፉ መውጣት የአባ ሳሙኤልን ገጽታ የሚያስተካክል መስሎ ስለተሰማቸው ነው፡፡ በእነ አሉላ የተመራው የማቅ ቡድንም አባ ሳሙኤል ቤት ሄዶ ያነጋገራቸው ሲሆን፣ ይህ መጽሀፍ መውጣቱ የቀድሞውን መጽሐፍ ይቀሰቅስቦታልና ቢቀር ጥሩ ነው ያሏቸው ሲሆን አባ ሳሙኤል ምንም ሳያናግሯቸው ውጡልኝ ብለው አስወጥተዋቸዋል፡፡ ይህም የሚያሳየው ማህበሩ አባ ሳሙኤልን እንደማይፈልጋቸውና ለአላማው ማስፈጸሚያነት መጠቀም እንዳሰበ ነው፡፡ እንዲህ ባይሆንማ ኖሮ በመጽሀፉ መወጣት ደስ ባለው ነበረ፡፡ ለነገሩ የቤተ ክህነት ፍቅር እንዲሁ ነው

  ReplyDelete
 7. Power strugle was exploded in the head office of eotc. Some fake bishop that suported by terrerist mk using strategy to pay money for gov. Official. Aba Abrham (Ibrahim) on the close door of serial killers,mk fight is hugely exploded power strugle between aba samuel and Aba, abrham. In the,near distance people who have close to betkehinet said both the dream runners are ethicaly bullsheet which are gay and adultory. It is shame in eotc tradition. Mk have planed to get the position for his suporter and qudeta for current gov. $70, 000, 0000.00 birr. Death to gay bishop abrham and death to mk.

  ReplyDelete
 8. ሳሙኤል ቀጣዩ ፓትርያርክ khone ene hymanoten bgza faqade elqalhu

  ReplyDelete
  Replies
  1. wegnie haymanotn melkek chewata arekew endie benfsh tewrardeh eko new yemtlkew new haymanot poletica mesleh

   Delete
 9. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !December 20, 2012 at 8:19 AM

  What am going to say about our church? please our fathers at Synods read John 10:11 it said: " I am the good shepherd. The good shepherd lays down his life for the sheep." Lord Jesus please bring your kingdom!!!!!!!

  ReplyDelete
 10. ገላግሌ ከደብረ ማርቆስDecember 20, 2012 at 12:33 PM

  ይህች ቤተክርስቲያን የሚያስፈልጋት እንደ ሳሙኤልና ሉቃስ ያለ ወሮበላ ሳይሆን እንደአቡነ ማርቆስ ያለ የወንጌል ሰው ነው፡፡ ማቅማ ቀድሞ ስማቸውን በወንጌል ምክንያት አጥፍቶታል፡፡ ይህ ለእርሳቸው ታላቅ ክብር ነው፡፡ እንዲህ ያደረገው እርሳቸው እንዳይተቆሙ ነው፡፡ ስለዚህ እርሳቸው እንዲጠቆሙ ሁላችንም የተቻለንን እናድርግ፡፡ ስለዚህ ለወንጌል ማሰፋፋትና ለቤተክርስቲያን መንፈሳዊ እድገት ካሰብን እርሳቸው የተሻሉ አባት ናቸው፡፡ እነ ሳሙኤል ግን ቤተክርስቲያኗን ይዘው ገደል ነው የሚገቡት፡፡ ስለዚህ ሁላችን እናስብበት

  ReplyDelete
  Replies
  1. ግልገሌ ደህና ብለሃል ፡፡ አቅሙ ካለህ በርታ ፡፡

   Delete
 11. Do not call them fathers! They are high paying employers in head of the church. Most of them sexual partener and ground plus one house in center of Addis. Shame on you , stop calling fathers. May be good name is our fuckers.

  ReplyDelete
  Replies
  1. it sounds you are just talking about your pastors! im i right?

   Delete
 12. yetekeberachu wendmoche mechewunm gize lintekachewu yemantekachew abat nachewuna abune markosn lekek adrgachew yeabune teweflos yibekanal

  ReplyDelete
 13. lemehonu dejeselam mahibere kidusan beyetignaw gazeta new kidus bilo yawotaw masreja aleh asayegn

  ReplyDelete