Friday, December 21, 2012

ቤተ ክርስቲያኒቱ የወንበዴዎች ዋሻ፣ ንስሐ የማይገቡ ሌቦች መሸሺያ ሆናለች!!

Read in PDF  (ምንጭ፦ ደጀ ብርሃን http://dejebirhan.blogspot.com)
 
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሰይጣን እንደ ስንዴ  ሊያበጥራት እግዚአብሔርን የለመነ ይመስላል። ልክ የክርስቶስን ደቀ መዛሙርት በጭንቅ ይፈትናቸው ዘንድ እንደለመነው ማለት ነው።

 “ጌታም፦ ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ” ሉቃ 22  እንዳለው።

ከዚህ ፈተና ቤተ ክርስቲያኒቱ ትወጣ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር አጥብቆ የሚጸልይ ኤልያሳዊ ማንነት  ያለው አንድም ሰው ጠፍቷል። ገዳማቱን የዐመጻ ሰዎች ሞልተውበታል። ዋልድባን በመሳሰሉ ትላልቅ ገዳማት ሳይቀር ቀጣፊዎች እርስ በእርስ በመነቃቀፍና  የሀሰት ስም በመለጣጠፍ፣ ስለሃይማኖት ልዩነት በማውራትና በማስወራት የሰይጣንን አገልግሎት በተገቢው እየፈጸሙ መገኘታቸው  በጸሎታቸው እንኳን ለዓለሙ ሊተርፉ የራሳቸውን ይዞታ ከስኳር ልማት ለማስጠበቅ የማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ የተቃውሞ ሰልፍ አስፈልጓቸዋል። አብዛኛዎቹ ገዳማትም የመርበብተ ሰሎሞን፣ የመድፍነ ጸር፣ የዐቃቤ ርእስና የገድላ ገድል መፈልፈያዎች ከመሆን አልፈው የሀገሪቱን ችግር ማቃለል የሚችል የጸሎት መልስ የሚገኝባቸው ናቸው ብሎ መጠበቁ ከቀረ ዓመታት አልፈዋል። ደብረ ሊባኖስን ያየ ዓለም እንዴት ሰነበትሽ? ማለቱ እንደማይቀር  ጥርጥር የለንም።  ያላየም ሄዶ በማየት እውነታውን ሊያረጋግጥ ይችላል።

አዲስ አበባ ላይ ማጅራት መቺዎችና ኪስ አውላቂዎች ንስሐ ሳይገቡ አስተዳዳሪዎች፣ጸሐፊዎችና ገንዘብ ያዥዎች ሆነው አብያተ ክርስቲያናቱ የደም እንባ እያለቀሱ ይገኛሉ። ሰሞኑን በልደታ ቤተ ክርስቲያን በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ብር ሲዘርፉ የተደረሰባቸው የቢሮ ሠራተኞች ተጠቃሾች ናቸው። ቤሳ ቤስቲን የሌላቸው ሹመኞች ሚሊየነሮች ሆነዋል። ኑሮ በከበደበት ሀገር የቤተ ክህነቱ ሰዎች ቱጃሮች ለመሆን መቻላቸው ያስገርማል። ለሌቦቹ ካህናት ቤት መገንባትና መኪና መግዛት ቀላል ነገር ነው። እንደ እነ ቄስ ኃይሌ ዓይነቶቹ ዓይን አውጣዎች ደግሞ የሕዝብ ማመላለሻ መኪና ወደ መግዛት ተሸጋግረዋል። በብሔረ ጽጌ ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን የራያ ሰዎች መፈልፈያ ያደረገ ዘረኛ መሆኑም አንዱ የአሳዛኝ  ግብሩ ማሳያ ነው። እነ ኃይለ መለኮት በጎፋ ገብርኤል የኪስ ማደለቢያ ኢንቨስትመንት ከፍተው ያጋብሳሉ። የሰዋስወ ብርሃኑ ቤተ ክርስቲያን  አስተዳዳሪ ደግሞ ከእነ መሐመድ ጋር በድለላ ሥራ ተሰማርቶ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ጊዜ የለሽ ሆኗል።

እነ ተክለማርያም፣ ነአኩቶ ለአብ፣እነ እዝራ  ኧረ  ስንቱ ተቆጥሮ!!!  አብዱልቃድርና አሕመድም በስመ ገ/ማርያም  ተሸሽጎ የማይጠፋ የሚመስለው ጭካኔ የተሞላበቱ ዘረፋና ዘረኝቱ ሲታይ ነው። ግራኝ አህመድስ ከዚህ ወዲያ ምን  አደረገ?  የአብያተ ክርስቲያኒቱ ዘረፋና ዘረኝነቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ  መግነኑ ያንን ያሳያል።  ቤተ ክርስቲያኒቱ መሪና ተመሪ የሌላት የባለጊዜዎች መፈንጫ ሆናለች። በግብራቸው  እነ አቡነ ኢብራሂም፣ እነ አቡነ ኢሊያስ፣እነ አቡነ ጅብሪል፣እነ አቡነ ጊርጊስ  የሚመሯት፣ እነ የሃዘን ልብሱ (ማቅ) የሚያሾሯት ቤተ ክርስቲያን የወንበዴዎች ዋሻ፣ ንስሐ የማይገቡ ሌቦች መሸሸጊያ መሆኗ እውነት ነው። ጳጳሳቱ ሚሊየነሮችና የ G+ ባለህንጻዎች፣ ማኅበራቱ የሚሸጡባትና የሚሸቅጡባት የእርግብ ለዋጮች ሜዳ ካደረጓት ውሎ አድሯል።  በዚህም መሃከል ግን ብዙዎች ምስኪናን ቀሳውስትና  ዲያቆናት የበይ ተመልካች ሆነው በኑሮ እሳት ይጠበሳሉ።

የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዘመናትን አቋርጣ እዚህ የደረሰችው እንዲህ በቀላሉ አልነበረም። ብዙ ጦርና ሰይፍ አልፎባታል። ብዙ ልጆቿን በባእድ እጅ ለሞት ከፍላለች። ቅርስ፣ ታሪክና ሀገር ያቆየችው ዛሬ ከሜዳ ተነስተው እንደሚፈነጩባት የዘመኑ ዲስኩረኞች ወሬ ሳይሆን በመከራ ውስጥ አልፋ ነው። አዎ! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እስከነ ድክመትዋ ኢትዮጵያ ለምትባለው ሀገር መኖር ዋጋ የማይተምነው ባለውለታዋ ነች። የሚሳዝነው ነገር አመድ አፋሽ ሆና መቅረትዋ ነው እንጂ!!  የወላድ መካን ሆና ሥነ ምግባራቸው የቆሸሸ ጳጳሳት፣ መነኮሳትና ቀሳውስት ተፈልፍለውባት ለሥልጣን ሲሉ የሚገዳደሉባት፡የሚወጋገዙባት፣ ራሳቸውን የሚያጩባት፣ ሀብቷን፡ንብረቷን የሚዘርፉባት፣ ዘረኝነቱን የሚያስፋፉባት፣ ሁሉም ጥርሱን የነከሰባት ሆና መገኘትዋ ያሳዝናል፣ ያስለቅሳልም።  ቤተ ክርስቲያኒቷ ከውስጥም ከውጭም የስንግ ተይዛለች። ድክመትዋን፣ ጉድፏንና ተግዳሮቶችዋን ከወዲሁ አርማ ካልተነሳችና ንስሃ ካልገባች መጪው ጊዜ አስፈሪ ነው።  መጽሐፉ እንደሚለው ዘመንን የሚሰጠው ለንስሐና ለበጎ ፍሬ ነውና።

“እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ ንስሐም ግባ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፤ አለዚያ እመጣብሃለሁ ንስሐም ባትገባ መቅረዝህን ከስፍራው እወስዳለሁ” ራዕይ 2፡5

ከመቼውም ጊዜ በላይ ቤተ ክርስቲያኒቱ በመከራ ወጀብ እየተናጠች ትገኛለች። ልብ ብሎ ያስተዋለው ካልሆነ በስተቀር ቀኑ መሽቶ በመንጋቱ ብቻ ነገሮች ሁሉ እንደ ወትሮ እየሄዱ ያለ የሚመስለው ጥቂት አይደለም። በምድር ላይ ያለው እውነታ ግን ያንን የሚያሳይ አይደለም።  በነነዌ ዘመን ውስጥ እያለፍን እንዳለን ይሰማኛል። አምላክ ሆይ አንዱን ዮናስ ላክና ከዚህ ዐመጻ እንድን ዘንድ የንስሐን እድል ስጠን! የርግብ ሻጮቹንና የገንዘብ ለዋጮቹን ጠረጴዛ ገልብጠህ እውነተኛ ቃልህ በደጅህ የሚታወጅበትን ቀን አምጣልን!!

ቤተ ክርስቲያኒቱ በሰይጣን ፈተና እንደ ስንዴ እየተበጠረች ነውና ስለእምነታችን አንተ ማልድ! አንተው ይቅር በል!! አሜን!
 

7 comments:

 1. nektenbachihual atidkemu. Merzamoch, tesfa maskoret mehonu new! Menafik hulu. Lenegeru post atadergutm.

  ReplyDelete
 2. christian nen tilu yele leminn wore kemitaworu lemin tselotun enante atjemirum.endenante sirama lemafres new ymitiserut egziabher degmo sle hzibu sil yitadegatal.

  Tifafua amiruachihu amiruachihu Yiwotalachihual

  ReplyDelete
 3. አባት እና ልጅ
  =========

  ልጅ አባቱን ቢክደው እንቢ አሻፈረኝ ቢለው ፤
  አባት ነው ልጅ ? እኮ ማነው የሚጐዳው ።
  አባት በልጅ ቢያዝን ፣ ልጅም ቢያዝን ባባት፤
  ከቶ በማን ፣ ለማን ይደርሳል ጉዳት ።
  እንዲያው ፣ መለኪያ ቢኖረው ለሃዘን ፤
  የየትኛ ትካዜ ይበልጥ ይሆን ቢመዘን ።
  ልጅ አባቱን ባይሰማ ፣ አባት ልጁን ቢቆጣ ፤
  ልጅም ባባቱ ቢያዝንና ቤቱን ለቆ ቢወጣ ።
  ልጅ ስብርብር ቢል ቢሆን ቆማጣ ፤
  ማን ነው ጥፋተኛ ለሚመጣው ጣጣ ።
  የአባት ፍቅሩ አይሎ ፣ ና በእኔ ዳን ልጄ ብሎ ፤
  ይኸው ስጋየን ብላ ደሜን ጠጣ ብሎ አባብሎ ።
  ልጅ እንቢ መዳን አልፈልግም ካለው ፤
  አባት ወይስ ልጅ ? ለዚህ ቂመኛ ማነው ።
  አባት ደግሶ ሊድር ልጁን ፤
  እልፍኝ አስጥሎ አጽድቶ ደጁን ።
  ካልታረቀው ልጅ አባቱን ፤
  ማን ሊመርቅ ነው ዘሩን ፤
  በምድር የዘራውን ።

  ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

  ከብርሃኑ መልአኩ

  ReplyDelete
 4. ennante ketefiwoch ahun endew le tewahedo yazenachehu atemeslum endih ye azo enba setanebu ...

  ReplyDelete
 5. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዘመናትን አቋርጣ እዚህ የደረሰችው እንዲህ በቀላሉ አልነበረም። ብዙ ጦርና ሰይፍ አልፎባታል። ብዙ ልጆቿን በባእድ እጅ ለሞት ከፍላለች። ቅርስ፣ ታሪክና ሀገር ያቆየችው ዛሬ ከሜዳ ተነስተው እንደሚፈነጩባት የዘመኑ ዲስኩረኞች ወሬ ሳይሆን በመከራ ውስጥ አልፋ ነው። አዎ! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እስከነ ድክመትዋ ኢትዮጵያ ለምትባለው ሀገር መኖር ዋጋ የማይተምነው ባለውለታዋ ነች። የሚሳዝነው ነገር አመድ አፋሽ ሆና መቅረትዋ ነው እንጂ!! የወላድ መካን ሆና ሥነ ምግባራቸው የቆሸሸ ጳጳሳት፣ መነኮሳትና ቀሳውስት ተፈልፍለውባት ለሥልጣን ሲሉ የሚገዳደሉባት፡የሚወጋገዙባት፣ ራሳቸውን የሚያጩባት፣ ሀብቷን፡ንብረቷን የሚዘርፉባት፣ ዘረኝነቱን የሚያስፋፉባት፣ ሁሉም ጥርሱን የነከሰባት ሆና መገኘትዋ ያሳዝናል፣ ያስለቅሳልም። ቤተ ክርስቲያኒቷ ከውስጥም ከውጭም የስንግ ተይዛለች። ድክመትዋን፣ ጉድፏንና ተግዳሮቶችዋን ከወዲሁ አርማ ካልተነሳችና ንስሃ ካልገባች መጪው ጊዜ አስፈሪ ነው። መጽሐፉ እንደሚለው ዘመንን የሚሰጠው ለንስሐና ለበጎ ፍሬ ነውና።

  ReplyDelete
 6. እውነት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ችግር የዮናስ መጥፋት ነው? ወይስ የነነዌ ሰዎች መታጣት? እውነት እንደዮናስ የሚጮኹ፣ እንደኤርምያስ የሚያለቅሱ፣ እንደ ዕንባቆም ዕንባ ይቁም የሚሉ ሰዎች ጠፍተዋልን?

  በእኔ ዕይታ የጠፋው የነነዌ ሰዎች ልብ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ልባችንን በእብሪት ደፍነነው እንደነነዌ ሰዎች ኃጢኣት መሥራት እንጂ እንደነነዌ ሰዎች ንስሐ መግባት አቅቶናል፡፡ ንስሐ እኮ ወደ ልብ የመመለስ ፍሬ ነው፡፡ በልቡናችን ውስጥ ኾኖ “ወደ እኔ ወደ አባታችኹ ዕቅፍ ተመለሱ!” እያለ የሚጣራውን እግዚአብሔርን መስማት አቅቶናል፡፡ ኹላችንም በውስጣችን ከጌታ ይልቅ የምናስበልጠው፣ የምንመርጠው ጣዖት አስቀምጠናል፡፡ ባህላችን፣ ክልላችን፣ ገንዘባችን፣ ኩራታችን ወዘተ. ንስሐ እንዳንገባ ዕንቅፋት ኾነውብናል፡፡ እግዚአብሔርንም ኾነ ቤተክርስቲያንን የምንፈልጋቸው እነዚህን ጣዖቶቻችንን እንዲጠብቁልን ነው፡፡ ቤተክርስቲያንን የወንጌልን ሥራ ትታ እኛ “ብሔራዊ ኩራት” ብለን የምንጠራውን እውነቱ ሲታይ ግን “እኛ ከእነዚያ እበልጣለን! እንሻላለን!” የምትል የሀገራዊ ትዕቢታችንን ባንዲራ ሸክም እንድትሸከም ስናደርጋት ፍጻሜው እንዲህ መባላት ይኾናል፡፡
  የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ችግር ከውጪ የመጣ ማዕበል አይደለም- በእያንዳንዳችን ቤተክርስቲያን አገለግላለኹ ብለን በተሰበሰብን ሰዎች ውስጣዊ ዕብሪትና ራስ ወዳድነት እንጂ፡፡ ውጫዊ ማዕበል ቢኾንማ እሰየው ነበር፡፡ ውጫዊ ማዕበል በአንድነት፣ በአንድ ልብ ታንኳዋን ይዘን “ጌታ ሆይ! ጠፋን አድነን!” ያሰኘናል እንጂ እርስ በርስ አያባላንም፡፡ ውጫዊው ማዕበል ይበልጥ ያስተቃቅፈናል እንጂ አያራርቀንም፡፡ ውጫዊ ማዕበል ቤተክርስቲያንን የሚገድል ቢኾን ኖሮ የግብጽ ክርስቲያኖች በእስማኤላውያኑ ሰይፍ ሲቀሉ ቤተክርስቲያን ፈጽማ ከዚያ ምድር በጠፋች ነበር፡፡ ወይም ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በኢአማንያንና በእስማኤላውያን ተከብባ፣ የቀድሞ ምእመናን ልጆች ፍጹም ከሐዲዎች ኾነው በንቀት በሚሳደቡበት በዚህ ዘመን በብርታት ስታንሠራራ አናያትም ነበር፡፡ እንዲያውም ይህን የያዝነውን ዓመት “የእምነት ዓመት” ብላ ሴኪዩላሪዝም የበላውን የአውሮጳ ማሣዋን ዳግም በወንጌል ለማረስ ስትነሣ አናያትም ነበር፡፡

  የአውሮጳን ቤተክርስቲያን ታሪክ ያጤነ ሰው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እየኼደችበት ያለው የጥፋት መንገድ ግልጥ ብሎ ይታየዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ክርስትና በአውሮጳ እንዲህ እንዲመነምን ያደረገው የእስማኤላውያን ጡጫ ወይም የኢአማንያን ፈላስፎች ክሕደት አይደለም፡፡ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ቅድስና በማጣታቸው ምክንያት የእግዚአብሔርን ስም ስላስናቁት እንጂ፡፡ እነርሱ በዕብሪት ተሞልተው ለሀብትና ንብረት ሲሻኮቱ ቅዱስ ጳውሎስ አንገቱን ለሰይፍ እጁን ለእስራት ሰጥቶ ወንጌል የሰበከበትን ምድር በኢአማንያን አስወረሩት፡፡ ኢአማንያኑ የእግዚአብሔርን አለመኖር ለማስረዳት ብዙ ከመፈላሰፍ ይልቅ ወደ ቤተክርስቲያን አገልጋዮች መጠቆም በቂያቸው ነበር፡፡ የዋኁ ምእመንም እግዚአብሔርን በአገልጋዮቹ አምሣል እያሰበው ህልውናውን ተጠራጠረ፡፡ “ክርስቲያን ነኝ፡፡” ማለት “የምናገረውና የምሠራው የማይጣጣም፣ መልካም ተናግሬ ክፉ የምሠራ ግብዝ ነኝ!” ብሎ የመናገር ያኽል የሚያሳፍር ነገር ኾነ፡፡ “ኑ! ወደ እግዚአብሔር እንመለስ!” የሚል ጥሪ ያቀረቡ ሰዎች ሳይኖሩ ቀርተው አልነበረም- የሚሰማቸው አጥተው እንጂ፡፡

  የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ዛሬ ችግሯ ማዕበል አይደለም፡፡ በአገልጋዮቿ ውስጥ የተቀበረው እብሪትና ራስ ወዳድነት እንጂ፡፡ ራስ ወዳድ ሰው ደግሞ ራስ ተኮር ነው፡፡ በሱ ቤት ዓለም ተጀምራ የምታልቀው እሱ ላይ ነው፡፡ እርሱ ያለው ካልኾነ ሰማዩ ይቆረሳል፤ ምድሩ ይገመሳል፤ ታሪክ ይፋለሳል፤ ባህል ይበረዛል፡፡ የሌሎችን ሐሳብ ለማድመጥ ጊዜ የለውም፡፡ የአውሮጳን ቤተክርስቲያን ሰፋፊ የመሬት ርስቷን በጨካኝ ሴኪዩላር መንግሥታት አስነጥቆ ከምድራዊ ግሣንግሥ ያላቀቀና ወደ ወንጌል በግድ እንድታተኩር ያደረገ ጌታ የኢትዮጵያንም ቤተክርስቲያን ከተጫኑባት የባህልና የቅርስ ሙዚየምነት ቀንበር ያላቅቃት፡፡ የምድራዊ ሥልጣን፣ ምቾትና ክብር ሐሳቦች የሞሉት ማኅበረሰብ እንኳን ዮናስ ቀርቶ “ከሴቶች ከተወለዱት የሚበልጠው የለም” የተባለለት መጥምቁ ዮሐንስም ቢነሣ ወይ አውግዞ ያሳድደዋል፤ ወይ ገዝግዞ ይገድለዋል እንጂ፡፡ አይመለስም፡፡

  “የምትጠፋ ከተማ ነጋሪት ቢጎሥሙባት አትሰማ!” አይደል አባባሉስ?

  ጌታ ሆይ! ማስተዋልን ስጠን፤
  ጊዜ እንዳያመልጠን፡፡

  ReplyDelete
 7. ታዲያ የኦርቶዶክስ ቤ/ክ እንፈለጋት ብትሆን .. እናንተ ተሃድሶዎችን ምን አገባችሁ ?

  ReplyDelete