Saturday, December 22, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን የፓትርያርክ ምርጫ ህጉ እንዲጸድቅ ሲገፋ ከርሞ እንደሚፈልገው ሳይሆን በመቅረቱ አገር ይያዝልኝ እያለ ነው

የማህበረ ቅዱሳንና የአባ ሳሙኤል ፍቅር አደጋ ላይ ወድቋል
የራሱን ፓትርያርክ ለማስቀመጥ ላይ ታች ሲል፣ የነበረውና የምርጫ ህጉ የእርሱን ምራጮች እንዲያስቀምጥልት በሚያስችለው አኳኋን ከጀርባ ሆኖ በቀረጻው ዋና ተዋናይ የነበረውና 5 ገጽ አስተያየት ለጳጳሳት ሲበትን የሰነበተው ማህበረ ቅዱሳን፣ የምርጫ ህጉ እርሱ ባሰበው መንገድ ስላልሄደለትና ብዙ ማሻሻያዎች በመደረጋቸው ምክንያት እቅዱ ሁሉ መክሸፉን ተከትሎ ከልቡ የማይፈልገውን «እርቅ» አጀንዳው አድርጎ እየተንቀሳቀሰና ህዝቡንም ለጦርነት ተነስ እያለ በመቀስቀስ ላይ መሆኑ ተሰማ፡፡ ይህ የታወቀው  በደጀሰላም እና አንድ አድርገን ድረገጾቹ ላይ በተከታታይ ባወጣቸው ዘገባዎቹ ላይ ነው፡፡ እነዚህ ድረገጾች የምርጫ ህጉ ሲረቀቅና ውይይትም እየተደረገበት ሳለ ስለ6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ ሲጽፉና ሲያበረታቱ እንዳልነበር አሁን ያን ሁሉ ወደጎን ብለው በመጀመሪያ እርቅ ይውረድ አሊያ አመፅ እናስነሳለን እያሉ ህዝቡን እየቀሰቀሱ ነው፡፡ ድረገጾቹ  ካስተላለፉት ቅስቀሳ መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
§  መረጃውን ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን እናድርስ፣ (በስልክ የኤስ.ኤም.ኤስ መልእክቶች፣ በፌስቡክ፣ በትዊተር)
§  ዜናውን ለመገናኛ ብዙኃን እናድርስ፣
§  ብፁዓን አባቶችን በስልክም በአካልም በመቅረብ ስለ ጉዳዩ ማነጋገር፣ በውሳኔው እንደማንስማማ እናሳውቅ፣
§  ጉዳያችን እና ዓላማችንድብቅ የፖለቲካ አጀንዳሳይሆን የቤተ ክርስቲያናችን አባት የመምረጥ ጉዳይ መሆኑን ለሚመለከታቸው አካላት አለ ፍርሃትና ያለ ሥጋት እንግለጽ፣
§  ከመንግሥት አካላት የተደበቀ የመሥራት ፍላጎት እንደሌለን ከወዲሁ በተደጋጋሚ እንግለጽ፣
§  በአገር ውስጥ ያሉ ጋዜጦችና መጽሔቶች ለጉዳዩ ሽፋን እንዲሰጡት እናበረታታ፣
§  የውጪ አገር ኢትዮጵያውያን ሚዲያዎችም በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ በሚል በዚሁ ሰበብ ኢሕአዴግን ለመተቸት ሳይሆን ጉዳዩን ለክርስቲያኑ ሕዝብ በማይጎረብት መልክ እንዲያቀርቡት እናግዝ፣
§  ኦርቶዶክሳውያን ጡመራ መድረኮችም ዜናዎችን በትብብርና በኅብረት ለምእመኑ እናድርስ፣
§  እሑድን ለቤተ ክርስቲያን ጥያቄ ማቅረብ የምንጀምርበት የመጀመሪያው ቀን እናድርገው። ብሏል፡፡
ማቅ እነዚህን ነጥቦች በማንሳት የተቃውሞ ድምፁን አሁን ለማሰማት ምን አነሳሳው? እውን ማቅ እርቁን ይፈልገዋልን? እንዲህ ከሆነ የምርጫ ህግ ሲረቀቅ የት ነበረ? በመጀመሪያው ቀን የሲኖዶስ ስብሰባ ውሎ እነአባ ሳሙኤል ሲፈነጩና በእድሜና በዜግነት ላይ ገደብ ጥለው ለራሳቸው ሲያደላድሉስ በርቱ ግፉ እያለ ሲያበረታታ እንዳልነበረ አሁን ባለቀ ሰዓት እርቅ ይቅደም ያለው ለምን ይሆን? ይህ ሁሉ ሲደረግ ስለስድስተኛው ፓትርያርክ እየታሰበ አልነበረም ወይ? የሚሉ ጥያቄዎችን አስነስቷል፡፡ ነገር ግን የምርጫ ህጉ የማቅን ፍላጎት የማያሳካ ሆነ ስለተገኘ ብቻ በእርቅ ሽፋን አብዮት ለማስነሳት ልዩ ልዩ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ አሁን ስለእርቅ የሚያወራው ጊዜ ለመገዛትና አሁን በቤተክህነት ውስጥ አዛዥና ናዛዥ የሆነበትን ስርአት በማራዘም ስብከተ ወንጌልን ለማሽመድመድና ሊበቀላቸው የሚፈልጋቸውን ሠራተኞች በእድገትና በዝውውር ስም እያነሳ ቁልፍ ቦታዎችን በእርሱ ደጋፊዎች ለመሙላት እንደ ሆነ እስካሁን በተስፋዬ ውብሸት የተደረጉት ዝውውሮች ፍንትው አድርገው ያሳያሉ፡፡
በትናንትናው የደጀሰላም ዘገባ መሰረት የምርጫ ህጉ ማቅ በሚፈልገው መንገድ ሳይጸድቅና የማይፈልገው ማሻሻያ ተደርጎበት አሁን ባለው ሁኔታ ስድስተኛ ፓትርያርክ የሚመረጥ ከሆነ «ልዩነቱ በውጪ አገር ብቻ ሳይሆን በአገር ውስጥም ከባድ የመለያየት ቀውስ እንደሚፈጥር አያጠራጥርም። ቤተ ክርስቲያን ለስብከተ ወንጌል አገልግሎቷ፣ ለዕድገቷ፣ ለልማቷ ልታውል የምትችለውን ኃይል በመለያየት ሰበብ እየበታተነች መሔዷ ለወደፊቱ ህልውና አስቸጋሪ እንደሚሆን የታወቀ ነው።» ሲል አስጠንቅቋል፡፡ ይህ የማቅ ህልም ቤተክርስቲያንን መቆጣጠር ነው ካልሆነም ተገንጥሎ የራሱን ቤተክርስቲያን መክፈት ነው የሚለውን የብዙዎችን ግምት ያረጋገጠ ምስክርነት ሆኗል፡፡ የሁሉም ናፍቆት የሆነው ግን ማቅ ከኦርቶዶክስ ተገንጥሎ የራሱን «ቤተክርስቲያን» ሲመሰርትና የራሱን ጠቅላይ ቤተክህነት፣ የራሱን ፓትርያርክ… ሲመሰረት ማየት
ድረገጹ አክሎ እንዳለው «ይህንን ፍፁም ሃይማኖታዊ ጥያቄ ሌላ መልክ ለመስጠት፣ ኢሕአዴግ ላይ የተነሣ ሰላማዊ ሰልፍ ለማስመሰል የሚሞክሩትን በግልጽ ከወዲሁ መልስ ልንሰጣቸው ያስፈልጋል። በሃይማኖት ስም ፖለቲካ አንነግደም። ፖለቲካውን በራሱ በፖለቲካነቱ የማራመድ ሙሉ ኢትዮጵያዊ መብት አለን። በዜግነታችን እርሱን በቦታው ማድረግ እንችላለን። አሁን የምንጠይቀው ጥያቄ ሃይማኖታዊ ነው፤ ማቅረብም የምንፈልገው ለቅ/ሲኖዶስ ነው ማለት ይገባናል።» ማቅ በዚህ አነጋገሩ ግልጽ ያደረገው በሃይማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀስ የፖለቲካ ድርጅት መሆኑን ነው፡፡ እርሱ በሃይማኖት ስም ፖለቲካን አንነግድም ቢልም፣ ፖለቲካን በቦታው ነው የምናደርገው ቢልም፣ የአሁኑ ጥያቄው የሃይማኖት ነው የሚለው አጠራጣሪ ሆኗል፡፡ ምክንያቱም በምርጫ ህጉ ተስማምቶ ህጉን አስቀርጿል፡፡ ባለ 5 ገጽ አስተያየትም ለጳጳሳቱ በትኖ ህጉ ላይ ማሻሻያ እንዲያደርጉለት ጠይቋል፡፡ ያቀረባቸው ማሻሻያዎችም ሁለት ሲሆኑ ምርጫው በዕጣ እንዲሆንና በመራጮች ማንነት ላይ ያተኮረ ነው፡፡
ይህ ሁሉ ሆኖ ህጉን የሚያጸድቀው ሲኖዶስ ነው፡፡ የማቅ ደጋፊ ከሆኑት አንዱና ሰሞኑን ማቅ ባዘጋጀው ቱሪዝምን የተመለከተው አውደ ጥናት ላይ ዋና ተናጋሪ ሆነው መንግስትንም እየካቡ እንዲናገሩ ተደርገው በቴሌቪዥን መስኮት ለእይታ የቀረቡት አባ ሉቃስ በማቅ በኩል እጩ ፓትርያርክ እንዲሆኑ ቃል ስለተገባላቸው ከአባ ሳሙኤል ጋር በመሆን ሽንጣቸውን ገትረው ቢከራከሩለትም የእድሜውን ጣሪያ በማንሳት፣ ዜግነትን የተመለከተውን አንቀጽ በማውጣት፣ የገዳም መነኩሴ ሊሆን ይችላል የሚለው በማስቀረት የማቅንና የአባ ሳሙኤልን ዕቅድ ማክሸፉ፣ ጉዳዩ እኔ መመረጥ አለብኝ የሚል የፖለቲካ እንጂ የሃይማኖት ሊሆን አይችልም፡፡ እኛ ያልነው ለምን አልሆነም ነው ጠቡ፡፡  ማቅ በከፍተኛ ሁኔታ ጣላቃ ገብነቱን ባሳየበት በረቂቅ የምርጫ ህጉ ላይ ወሳኙ አካል ያሳለፈውን ውሳኔ መቀበል እንጂ እኔ ያልኩት ካልሆነ «ሃይማኖት ፈረሰ» በቅደሚያ እርቅ መውረድ አለበት ብሎ አቧራ ማስነሳት ፖለቲካ እንጂ ሃይማኖት ሊሆን በፍጹም አይችልም፡፡ ማቅ ሃይማኖተኛ ቢሆን ኖሮማ ስለእርቅ ማንሳት የነበረበት ቀድሞ እንጂ ዛሬ አልነበረም፡፡ ይህን ያህል ጊዜ የራሱን ፓትርያርክ ለማስቀመጥ በተለያዩ አማራጮቹ ሲንቀሳቀስና ስለእርቁ አልተናገረም ላለመባል ያህል ጥቂት ነገሮችን ከአንገት በላይ ሲጽፍ ቆይቶ አሁን እድል የከዳችው ሲመስለው እርቅ ማለቱ ብዙዎችን አስገርሟል፡፡   
አንድ አድርገን በበኩሉ «ባለፉት 16 መቶ ክፍለ ዘመናት ከግብጽ በመቶ አስራ አንድ አባቶች አንድነቷ አደጋ ላይ ሳይወድቅ መመራት ችላለች ባለፉት 40 እና 50 ዓመታት በንጉሰ ነገስቱ እና በወቅቱ በነበሩ አባቶቻችን  የጳጳስነት እና የፓትርያርክነት ስልጣን ወደ ኢትዮጵያውያን ከተመለሰ በኋላ በአንድነት የማያስቀጥላት ደረጃ ላይ ደርሳለች፡፡» በማለት በቤተክርስቲያኗ ታሪክ ትልቅ የውርደትና የባርነት ዘመናት የሆኑትን እነዚያን 1600 ዓመታት ማድነቃቸው ከዚህ ቀደም እንዳልነው ማቅ ልቡ አሁንም ግብጽ መሆኑን አስመስክሯል፡፡  ቤተክርስቲያኗ በችግሮች ውስጥ መሆኗ ግን እውነት ነው፡፡ ከግበጻውያኑ የጭቆና ዘመን ጋር የሚነጻጸር ግን አይደለም፡፡ 
ይህ በእንዲህ እንዳለ ብዙ ገንዘብ አፍስሰው ፓትርያርክነቱን የራሳቸው ለማድረግ ከማህበሩ ጋር በጋራ በግልም ሲንቀሳቀሱ የነበሩት አባ ሳሙኤል በልካቸው አሰፍተውት የነበረው የምርጫ ህግ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ከማህበረ ቅዱሳን ጋር የነበራቸው ፍቅር መቀዝቀዙና ግጭት ውስጥ መግባታቸው ተሰምቷል፡፡ ማቅ አባ ሳሙኤልን የተጣላቸው ከመንግስት ጋር ወግነዋል በሚል ነው፡፡ አባ ሳሙኤል ግን ከራሳቸው ጋር እንጂ ከማንም ጋር አልነበሩም ነው የተባለው፡፡ አንድ አድርገን «በየአህጉረ ስብከታቸው ከቤተክርስቲያኒቱ አንድነት በፊት ራሳቸውን ለወንበር ለማብቃት ውስጥ ውስጡን ብዙ ገንዘብ አፍስሰው እና ሰዎችን ቀጥረው እግዚአብሔር እንደሚመርጥ ፍጹም ዘንግተው የቅስቀሳ ስራ እየሰሩ ያሉ አባቶችም ቢሆኑ ከዚህ ስራቸው ወደ ኋላ ካላሉ ስራቸውን አደባባይ ከማውጣት ወደ ኋላ አንልም፡፡» በማለት ያስጠነቀቀውም አባ ሳሙኤልን ነው ተብሏል፡፡ የሰውዬውን በገንዘብ ሀይል ፓትርያርክ ለመሆን የያዙትን ህልም ማጋለጡ መልካም ሲሆን፣ «የቅስቀሳ ስራ እየሰሩ ያሉ አባቶችም ቢሆኑ ከዚህ ስራቸው ወደ ኋላ ካላሉ ስራቸውን አደባባይ ከማውጣት ወደ ኋላ አንልም» ማለቱ ግን አንድአድርገንን ተቀድመሃል አሰኝቶታል፡፡ ያው እንደተለመደው አባቶችን ዋ እያለ የሚያስፈራራበትን መረጃ አወጣዋለሁ ማለቱ እንደሆነ ተገምቷል፡፡ ማቅ ስለአባ ሳሙኤል ምን አዲስ ነገር ሊነግረን ይችላል? ከሚጡና ከምሥራቅ ጋር ስለነበራቸው የፍቅር ግንኙነት ነው? ሚጡና ምስራቅ ተቀናንተው አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ መደባደባቸውን ነው? ወይስ ከምስራቅ ወንድም ጋር ስለነበራቸውና ዘሪሁን በጳጳሱ ቅሌት ስለገለጸው ግብረሰዶማዊነታቸው? ወይስ ደግሞ የምስል መረጃዎችን ይፋ ያደርግ ይሆን? የሚለው እየተጠበቀ ነው፡፡

15 comments:

 1. This article contradicts itself every where. If M K is pushing for the final election to be made by the Holy Spirit through the age old "lot casting" system, how can they impose their will on us? In fact they deserve praises for suggesting that option. Also, suggesting criteria does not necessarily mean they are against the recociliation process. Once enshrined into laws, the election criteria can serve the generations to come, not just immediate elections.

  ReplyDelete
 2. ማህበረ ቅዱሳን ፊት ለፊት በምርጫው እሳተፋለሁ እያለ ከበስተጀርባ ደግሞ ህዝቡን ለአመጽ ስራ ማነሳሳቱ የሚገርም ነው፡፡ ማህበረ ቅዱሳን መዘጋት ያለበት ጊዜው አሁን ይመስለኛል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. yanete anedebete yezegal

   Delete
 3. may God forgive you

  ReplyDelete
 4. "አንድ አድርገን «በየአህጉረ ስብከታቸው ከቤተክርስቲያኒቱ አንድነት በፊት ራሳቸውን ለወንበር ለማብቃት ውስጥ ውስጡን ብዙ ገንዘብ አፍስሰው እና ሰዎችን ቀጥረው እግዚአብሔር እንደሚመርጥ ፍጹም ዘንግተው የቅስቀሳ ስራ እየሰሩ ያሉ አባቶችም ቢሆኑ ከዚህ ስራቸው ወደ ኋላ ካላሉ ስራቸውን አደባባይ ከማውጣት ወደ ኋላ አንልም፡፡» በማለት ያስጠነቀቀውም አባ ሳሙኤልን ነው ተብሏል፡፡" የ አቡነ ሳሙዔ ሀገረ ስብከት የት ነው?

  ReplyDelete
  Replies
  1. መች አጣኸው? ምንም የልማት ኮምሽን ጳጳስ ቢሆንም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ካህናትን በባለፈው የሰበካ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ውሎአበል ከፍሎ አልነበረምን? ሰውዬው እኮ እጁ ሰፊ ነው እንኳን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሌላውም ጋር ሊዘረጋው ይችላል፡፡ ለጋዜጦች እየከፈለ ቀጣዩ ፓትርያርክ እርሱ ነው እያስባለ መሆኑን እናውቃለን፡፡ መጽሔቶቹ ይህን በነጻ ይሰራሉ ማለት ዘበት ነው፡፡ ስለዚህ ከአባ ሳሙኤል ራስ መውረድ አይቻልም፡፡ በተረፈ አንተ ሌላ አለ ካልክ ንገረን፡፡

   Delete
 5. OO EGZIOO MIN GUD NEW METASEMUN ABASELAMAWOCH MK (MAQ) Yemiserut sira betamm yasazinal YEWAHE KERSTYAN WEGENOCHACHENN siyaweku Mejemerya yet nebru seleerku ahun yasebut sayehon siker erk belew mawenabedachew manim ayekebelachewem bekentu yidekimalu degimoss poletikegna yetaweku ayedelu endeee lemin medbabek asfelge Yebtekersetyann abatoch wendimoch diyakonat zemareyan sebakiyan atekalay memenan enzhi mk yemeyawenabidutin letnekubachew yasfeligalll egna betkiresetyan yemtelenin mesmat alebin abaselamawoch enanetm bertu merjam azegajuuu egna ye mk werena weshet selchetonal ye amerkawen sinodos sisadebu siyawegizu neber zaresss min ayetew erkin felegu ene abaa samuael fitachewen selazoru neww ??? ayeee mk awekeneshal egnam gudguadd mesnelshal ayetoch ye egziabeher bett ayengedibetim hulachenim lenenka zor belu linelachew yigebal ke addis abeba tekilhayemanot senbet temhert bet andualem bertu yebtekerseteyan lijoch

  ReplyDelete
 6. አስቀድመህ ከወንድምህ ጋር ታረቅ /ማቴ. 5፥24/
  ታኅሣሥ 10 ቀን 2005 ዓ.ም.
  ለቤተ ክርስቲያናችን አገልግሎት ስኬት የአባቶቻችን ስምምነት ወሳኝ ነው
  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በሥጋ ሕይወት በነበሩበት ባለፉት ዓመታት “ስደተኛ ሲኖዶስ” ተብሎ ከተጠራው በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ አባቶች ጋር ዕርቅ ለመፈጸም ጥረት ይደረግ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ተጨባጭ ለውጥ መመዝገብ ሳይችል በእንጥልጥል እንዳለ ቅዱስነታቸው ዐረፉ፡፡

  የእርሳቸው ዕረፍት ቀጣዩ የቤተ ክርስቲያኒቱ ፓትርያርክ ከመመረጣቸው በፊት በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ ተለይተው ከሚኖሩ አባቶች ጋር ውይይት ለመጀመር አስገዳጅ ሁኔታ አምጥቷል፡፡ ይህ እንዲታሰብ ግድ የሚያደርገውም ቀጣዩ ፓትርያርክ የሚሰየሙበት መንገድ ሁሉን የማያስማማ ከሆነ የነበረውን ልዩነት የሚያሰፋ ውዝግብ በዚህች ታሪካዊ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሊያስከትል እንደሚችል ከወዲሁ መገመት ስለሚቻል ነው፡፡ ይህንን ከግምት አስገብቶ የወቅቱን አንገብጋቢነት ተረድቶ ወደ ዕርቅ የሚያደርስ ውይይት ማድረግ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኒቱን ወሳኝ አገልግሎቶች በብቃትና በስፋት ለመስጠት፣ ጠንካራ መሠረትም ለመገንባት ስለሚያስችል ነው፡፡

  በመሠረቱ ሲኖዶስ ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ በጉልህ የተገለጠ ተግባሩ መለያየቶችን መፍታት ዘመኑን የዋጀ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት መትከል ነው፡፡ ስለዚህ ሲኖዶስ ሲታሰብ ሰላምና አንድነት ይታሰባሉ፡፡ ትሕትናና ፍቅር ይነግሣሉ፡፡ ይህ የሚሆንበት ዋናው ምክንያት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠውን የሐዋርያዊ አገልግሎት አደራ መንጋውን የመጠበቅ ሓላፊነት ከመወጣት ሌላ ለሚሰበሰበው መንጋ አርአያነት ያለው ሕይወት አባቶቻችን እንዲኖራቸው፣ ብርሃናቸውም በዓለም እንዲያበራ ስለታዘዙም ነው፡፡

  እነዚህ የክርስትና ዐበይት ተግባራት በአባቶቻችን ደግሞ ጎልተው እንዲገለጹ ይፈለጋል፡፡ አባቶች የክርስቶስን መልክ /እርሱን መምሰልን/ እንደያዙ በሚያስበው የእግዚአብሔር መንጋ፣ እንዲሁም የምድር ጨው ሆነን ሕይወታቸውን ለማጣፈጥ እንድንበቃ አደራ በተሰጡን የምድር አሕዛብ ሁሉ ላይ በጎ ተፅዕኖ ለማሳረፍ ብፁዓን አባቶች መልካሙን ጎዳና ሁሉ ሲከተሉ መገኘታቸው ታላቅ ሚና አለው፡፡

  ከዚህ ጎዳና ወጥተን ፍቅርን በማጣት፣ በጠብ በክርክር ጸንተን ብንገኝ ፍቅር ከሆነ እግዚአብሔር ጋር ለመኖር ባለመፍቀዳችን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ከእርሱ ጋር እንዳይኖሩ ማሰናከያ በመሆናችንም ጭምር ያዝናል፤ ይፈርዳል፡፡ ስለዚህ ለብፁዐን አባቶች ብቻ ሳይሆን በክርስቲያኖች ሕይወትም በፍቅር ጸንቶ መኖር፣ ከበደልንም በይቅርታና በዕርቅ ሕይወት ውስጥ ማለፍ ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው፡፡ የዚህ ሕይወት መሠረቱ ከሞት ወደ ሕይወት የተሸጋገርንበት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ያደረገው ዕርቅ ነው፡፡ ጠላቶቹ ከሆነው ከእኛ ጋር እግዚአብሔር ታረቀ መባሉ የሕይወታችን መሠረት ፍቅር መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡ ስለ ዕርቅ ሕይወት በብዙ ምሳሌና በብዙ ኃይለ ቃል ራሱ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረንም በመሆኑ በጉልሕ በሕይወታችን መንጸባረቅ የሚገባው የጽድቅ ሥራ ነው፡፡

  ለእግዚአብሔር ከምናቀርበው ከየትኛውም ዓይነት መባዕ አገልግሎታችን በፊት ከወንድሞቻችን መታረቅ እንደሚገባ ጌታችን አበክሮ ያስተማረው የሕይወት ቃል ነው፡፡ “አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ” ያለው የጌታ ቃል ይልቁንም በቤተ መቅደሱ ዕለት ዕለት መሥዋዕት ለሚያቀርቡ፣ ብዙዎችን በጸጋ እግዚአብሔር ባዕለ ጸጋ ለሚያደርጉ፣ ምስጢራትንም ሁሉ ለሚፈጽሙ፣ የሃይማኖትና የሥነ ምግባር ምልክት ለሆኑ ከሁለቱም ወገን ላሉ ብፁዐን አባቶች የሚያስተምሩት ብቻ ሳይሆን ዘወትር እንዲኖሩት የሚጠበቅ ክርስቲያናዊ ሕይወት ነው፡፡

  ይህ በመሆኑም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል “ክርክርና መለያየት አለ” መባሉ ሳይሆን ክርክሩን መፍታት፣ ልዩነትን ወደ አንድነት ስምምነት ማምጣት አለመቻል ከላይ የጠቀስነውን ወሳኝ የሕይወት ቃል የሚፈታተን ይሆናል ማለት ነው፡፡ ከዚያም አልፎ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመምራት ባለን አቅምና በጎ ፈቃድ ላይ ጥያቄ የሚያሥነሣ ይሆናል፡፡ በዚህ የማይደሰተው እግዚአብሔርም ብቻ አይደለም፡፡ ከሕፃን እስከ አዋቂ ያሉ የክርስቶስ ቤተሰቦችም ናቸው፡፡

  ስለዚህ ቤተ ክርስቲያናችንን ወደ አንድነት የሚያመጣ ዕርቀ ሰላም መፈጸም ከሃይማኖታዊ ሥነ ምግባር አንጻር፣ ለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ከማሰብ አንጻር፣ መንጋውን ከማነጽና ሐዋርያዊ አገልግሎትን ከማቅናት አንጻር ለአባቶቻችን ግዴታ ይሆንባቸዋል፡፡ የሚፈለገው ዕርቀ ሰላም እውን እንዲሆንም ለእግዚአብሔር ፈቃድ፣ ለእውነት፣ ለኅሊና ምስክርነት መገዛት አግባብ ይሆናል፡፡

  ከዚህ በፊትም ማኅበረ ቅዱሳን እንዳስገነዘበው አባቶች ሰላሙን ለማምጣት የሚያስችሉ ቀኖናዊ ጉዳዮችም ላይ ለመወሰን ለማጽናትም መንፈሳዊ ሥልጣንን የተጎናጸፉ በመሆናቸው ዕንቅፋትን ማራቅ ይችላሉ፡፡ የዕርቅ ሒደቱ ሲፈጸምም ሃይማኖታዊ መልክ ያጡ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትና ምእመናንን የማያሳምኑ ቅድመ ሁኔታዎችን ከመደርደር መታቀበ ከተቻለ በተስፋ የተሞላ ሒደት እንደሚሆን ይታመናል፡፡

  ከማንምና ከምንም በላይ የቤተ ክርስቲያናችንን ቤተሰብ ማሳመን የማያስችሉ እርምጃዎች ውስጥ መግባት ተአማኒነትን ሊያሳጡ ይችላሉ፡፡ ለዓመታት የዘለቀውን መለያየት /ውዝግብ/ ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ውስጥም የካህናቱ የሰንበት ትምህርት ቤቶች የአገልግሎት ማኅበራትና በአጠቃላይ የሕዝበ ክርስቲያኑ ሐሳብና አስተያየቶች ከግምት የሚገቡበት አካሔድ ሊኖር ይገባል፡፡ ሕዝበ ክርስቲያኑ ካልተሰማ በቀጣዩ ጊዜ በቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር አካላት ላይ የሚኖረው አመኔታ ይላላል፡፡ በመሆኑም በዚህ በዕርቁ ሒደት ክርስቲያኖች ያላቸው ሐሳብ ሊመረመር ይገባል፡፡ ስለዚህ ሁሉም የሃይማኖት ቤተሰብ ደስ የሚሰኝበት ምዕራፍ ላይ ለመድረስ መትጋት ከአባቶቻችን ይጠበቃል፡፡

  ስለዚህም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ለሰላሙ መስፈን አስፈላጊ የሆነ ዋጋ እንዲከፈል ግፊት በማድረግ ሊረባረቡ ይገባል፡፡ ምእመናንም ከካህናት አባቶች ጋር በጸሎት በመትጋት ለዚህ ችግር ዘላቂ መፍትሔ እግዚአብሔር እንዲሰጠን መማጸን ይገባናል፡፡ የተጀመሩትን ሒደቶች ሁሉ በእውነተኛነት በሚዛናዊነት እየተከታተሉ በጎ ተጽዕኖ ማሳደር ይገባናል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ያሳለፈችው ያለፉት ዓመታት ኣሳዘኝ ሁኔታዎች እንዳይቀጥሉ ዛሬ ላይ ማድረግ የሚገባንን ሁሉ ማድረግ እንደሚገባን ማኅበረ ቅዱሳን ያምናል፡፡ ለዚህም ይሠራል፡፡
  ወስብሐት ለእግዚአብሔር

  ምንጭ፡- ሐመር መጽሔት 20ኛ ዓመት ቁጥር 8 ታኅሣሥ 2005 ዓ.ም.

  ReplyDelete
 7. አንድ አድርገን «በየአህጉረ ስብከታቸው ከቤተክርስቲያኒቱ አንድነት በፊት ራሳቸውን ለወንበር ለማብቃት ውስጥ ውስጡን ብዙ ገንዘብ አፍስሰው እና ሰዎችን ቀጥረው እግዚአብሔር እንደሚመርጥ ፍጹም ዘንግተው የቅስቀሳ ስራ እየሰሩ ያሉ አባቶችም ቢሆኑ ከዚህ ስራቸው ወደ ኋላ ካላሉ ስራቸውን አደባባይ ከማውጣት ወደ ኋላ አንልም፡፡» በማለት ያስጠነቀቀውም አባ ሳሙኤልን ነው ተብሏል፡፡" የ አቡነ ሳሙዔ ሀገረ ስብከት የት ነው? አቤት ውሸት ‹‹አባቶች›› ተብሎ በብዙ አንቀት የተጠራውን ለአንድ አባት ለአቡነ ሳሙኤል ብቻ አድርጋችሁ የምትወስዱት ለምንድን ነው!!!!?

  ReplyDelete
 8. "ከሚካኤል በቀር የሚያጽናናኝ የለም" ትንቢተ ዳንኤል ፲፥፳፩

  ReplyDelete
 9. Aba selama kibr leabatachin neger gin yihin sim wosidewu yeseyitan ageligay lehonut le aba selama bilog enante ye selam woren mechi newu yemitasinebibut bihons des yemilachihu mindin newu?betekirsteyan bitkefafel andinetwa bitefa wondim be wondimu bekuta binesa andu lelawun bikes ye mot fird biferdibet ....betekirsteyan lay lela ye haymanot dirjitoch komewu mayet ...

  ReplyDelete
 10. የእናንተ ዓላማ አልገባኝም? ዕርቅ ሳይፈፀም ምርጫው ይካሄድ ነው? ወይስ እንዲሁ ከማህበረ ቅዱሳን ተቃራኒ መሆን ልማዳችሁ ስለሆነ ነው?

  ReplyDelete
 11. ማቅ የራሱ ቤተክርስትያን የሚኖረው ከናንተ ልምድ ወስዶ ይሆን?

  ReplyDelete
 12. ማቅ እውነትም የፖለቲካ ድርጅት ነው። believe or not, the end of mahibere kidusan is coming soon; in no more than 6 months.

  ReplyDelete
 13. ከሁሉም የሚያሳዝነኝ ማቅ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጃንጥላ ስር ሆኖ የፖለቲካ አላማው እና የቢዝነስ ድርጅቱ አላማን እያካሄደ ይገኛል። የእግዚአብሄር ቤት የፖለቲካ እና የቢዝነስ ድርጅት አይደለም።

  ከማቅ አባላት የሚወጣ ወርሃዊ የገንዘብ ስብስብ በምንም ተአምር ለቤተክርስቲያን ጥቅም አይውልም። እንዲያውም ማቅ ከቤተክርስቲያን አፍ ነጥቆ ይወስዳል እንጂ። እስከ ትላንትናው ድረስ የማቅ ደጋፊዎች እና የማቅ ህቡእ አላማን ይደግፋሉ ለሚባሉ ለአባቶች ገጸ በረከት እያለ ሙስናን ሲሰጥ ቆይቶአል። አሁን ደግሞ ለተወሰኑ ለኢሃዴግ መንግስት አባላት በህቡእ እና በምስጢር ሙስና መስጠት ጀምረዋል።

  የማቅ ህቡእ አላማ መጀመርያ በተክርስቲያን መቆጣጣር። ለምን ቢባል ሰዎች የሚገኙ በቤተክርስቲያን ናቸው። ወደ ጎንደር፡ጎጃም፡ወሎ፡ ትግራይ፡ኦሮሞ እና ሌሎች ኮሚኒቲዎች የፖለቲካ እና የዘር ችግር ስላለባቸው ሰዎች ወደ ቤተክርስቲያን ብቻ መሄድ መርጦዋል እና ወደነዚሂ ኮሚኒቲዎች መሄድ አይፈልግም። ቤተክርስቲያን ከተቆጣጠር ቡሃላ ሰዎችን የቤተክርስቲያንን ማህበር በመምሰል የማህበሩን አባላት ማብዛት እና ውስጥ ለውስጥ ህዝብ ራሱ በመንግስት ላይ አመጽ እንዲያነሳ በህቡእ ህዝብን ማነሳሳት። የመጨረሻው አላማ የኢትዮጵያን መንግስትን መቆጣጠር። ይህንን የተደበቀ አላማ የሚያውቁ የማቅ አባላት ከመቶ ፐርሰንት አምስት ፐርሰንት ብቻ ናቸው።

  Mahibere Kidusan is following the footsteps of Egypt's Muslim Brotherhood. Unfortunately, this will not happen in Ethiopia because everything is in place and the downfall of Mahibere Kidusan is in the near future.

  ReplyDelete