Sunday, December 23, 2012

የትንቢት መፈጸሚያ ወይስ መጠቀሚያ?

በቅርቡ የይሁዳ ወንጌል መገኘቱን ሰምተው ይሆን? የመልዕከቱን ሐሰተኝነት እንዲያውም ከቅዱሳት መጻፍት ተራ ሊታሰብ የሚችል ቁምነገር እንደሌለው በመመልከት ከቀኖና መጻሕፍት ውጭ ሆነው ከተወገዱት መሓል እንዲሆን በቅዱሳን አባቶች የተወሰነበት የይሁዳ ወንጌል አርቀው ቢቀብሩትም ቀን ጠብቆ ለመገኘት በመብቃቱ የብዙዎችን ቀልብ እየሳበ ይገኛል። የመጽሐፉን ብዙ ዘመን ማስቆጠርና ቀዳሚ ከነበሩት ወንጌላት ተርታ እንደነበረ በማየት ሃሳቡ ምንም ከቀኖና መጻሀፍት መልዕክት ጋር የሚጋጭ ቢሆንም የሚንከባከቡትና የሚያሽሞነሙኑት ኣላጣም። በዚህ ረገድ በጥንታዊ ጽሁፎች ላይ ምርምር በማድረግ ረገድ ስም የወጣላቸው አንጋፋ ምሁራን ሳይንቲስቶች ሳይቀሩ ይህንን ወንጌል እሹሩሩ ሲሉት ይስተዋላሉ፡፡ ይሁዳን አንደ ጀግና ደግሞም የአምላኩን ሃሳብ በሚገባ አንደፈጸመ ብሎም የተጣለበትን ጌታውን አሳልፎ የመስጠት ተልዕኮውን በሚገባ እንደተወጣ ሃቀኛ አገልጋይ አድርጎ የሚያወሳው ይህ የሐሰት ወንጌል፤ ብዙዎችን “ነገሩ እውነት ይሆንን” ብለው እንዲጠይቁ ምክንያት እየፈጠረላቸው ነው። በጥቅማ ጥቅም ተደልሎ ጌታውን አሳልፎ የሰጠ ከሃዲ መሆኑ ቀርቶ የሚያወድሰውና እንደ ጀግና የሚቆጥረው ወንጌል በስሙ     ተጽፎ መገኘቱ እውን የይሁዳን ሀጢአት ያቀልለት ይሆን?
          አንድ ነገር ግልጽ ሊደረግ ይገባል። ይሁዳ አገልጋይ ነበር። ሁለት ሁለት አድርጎ በፊቱ ሲልካቸው ጮቤ እየዘለሉ መናፍስት ስንኳ በስምህ ታዘዙልን ካሉትና ልዩ ልዩ መመሪያዎችን ከጌታ በመቀበል ረገድ ከቀዳሚ አገልገዮች መሀል ሊመደብ ይችል እንደሆን እንጃ። (ማቴ 10፡1-4፤ ሉቃስ 10፡17) ጌታም ተላልፎ መሰጠቱና መሞቱ ግድ ነው; ነገር ግን ይሁዳ ትንቢቱ ተፈጸመበት እንጂ ትንቢቱን በታማኝነት እንደ ሀቀኛ አገልጋይ ሲፈጽም አናየውም። ብዙም ርቀን ሳንሄድ ጌታ ራሱ ”የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደተጻፈ ይሄዳል። ነገር ግን የስው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት። ያ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር።” ብሎታል።(ማር 14፡21) ደግሞም አሳልፎ መስጠቱን ነቅፎታል።(ሉቃስ 22፡48) ታዲያ ይሁዳ ትንቢት መፈጸሚያ ነበር ወይስ ፈጻሚና ተጠቃሚ?
          እኔ ስለ ይሁዳ መጻፍ ምን ገዶኝ። ስለ እርሱ ለመናገር ፈልጌ ሳይሆን ምናልባት ዛሬም ሳናውቀው የእርሱን አገልግሎት እያደረግን ያለን ብንኖር የትንቢት መፈጸሚያ እንጅ ፈጻሚ እንዳልሀን ልብ ልንል ይገባል ልል ፈልጌ ነው። ሁለቱንም የሚፈጽሙ ሊኖሩ ግድ ነው; እንደ ይሁዳ የትንቢቱ መፈጸሚያ አልያም እንደ አውነተኞቹ አማንያን ተጠቃሚ መሆን የግድ ነው። ጌታ መሰቀል ነበረበት፤ የመጣበት ዓላማ ነበራ። የሚሰቅለው መኖሩ ግድ ነው ምንም እንኳ እርሱ በግድ ስቀሉኝ ባይልም?
          እንደ ማኅበረ ቅዱሳን (ማቅ) ያሉ ማህበራት  የይሁዳን አገልግሎት ሳያውቁት ያነሱ ይመስላሉ። በነርሱ ፀረ ወንጌል አቋም ምክንያት ብዙዎች አይናቸው ሲበራና ወደ እውነተኛው ወንጌል ሲመጡ ይስተዋላሉ። አንግዲህ ይህን የአደፍራሽነት ስራ መስራታቸው ግድ ሆኗል። ያን ባያደርጉ ኖሮ የጠራውን ማየት አዳጋች ነበር,። ንጹሁን ወንጌል ለመስማት የግድ አደፍራሽ ሆነው መገለጥ ነበረባቸው፡፡ ለዚህም ነው ሰውን የሚያክል ክቡር ፍጡር እየገደሉ እንኳን  እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ የሚመስላቸው ይኖራሉ ብሎ ጌታ ራሱ የተናገረው።(ዮሐ፡16፡2) በአንድ በኩል ለአገልግሎታቸው ምስጋና ሊቸሩ ይገባል ምክንያቱም በእነርሱ ግፊያ ምክንያት ወደ ወንጌል የቀረበው ሰው ቁጥሩ ቀላል አይደለም።
          በሌላው በኩል እነማቅ የቆሙለት ኣላማ የኢየሱስ እላማ አይደለም። ወደ እግዚአብሔር መቅረቢያ መንገዱ ለእነርሱ ብዙ ነው። እንደ ይሁዳ የሰው ደጋፊ አሏቸው። ለተገኘው የይሁዳ ወንጌል አጫፋሪዎቹ ብዙ እንደሆኑ ሁሉ! እግዚአብሔር ግን ከሃሳቡ ጋር ስለማይጣላ ከአጀንዳቸው ጋር የለም ነገር ግን የትንቢት መፈጸሚያ አድርጎ እየተገለገለባቸው ይሆን?
          ሰይጣንን ማን ይወደዋል? ቢቻልስ ከዚህ ምድር ቢወገድ እንወድ ነበር። ለእግዚአብሔርስ ምን ተስኖት ነው ሊያስወግደው ቢወድስ? ነገር ግን ማንስ ይፈትነን? ማን መከራውን ያብዛልን?  እርሱ ከተወገደ ”በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ”(ዮሐ 16፡33) የሚለው ቃል እንዴት ይፈጸም? እርሱም የዚህ ዓለም አምላክ ተብሎ የለ?(2 ቆሮ 4፡4) መቸም እርሱ እጅ እግር የለው የክፋት መንፈሳዊ አሰራር ነው እንጂ? ደግሞም ለዓለማው ራሳቸውን የሰጡትን ይጠቀማል እንጂ እግዚአብሔር እጃቸውን ጠምዝዞ በግድ የርሱ አያደርገንም። ያልኩት ሃሳብ ልብ እንዲባል እወዳለሁ።
እኔ ማቅ የሰይጣን ማህበር ነው አላልኩም (እንዲያ የሚሉ ቢኖሩም)፤ ያልኩት ግን ሰዎች በውዴታ የሚያነሱትን የአፍራሽነት ተልዕኮ ይህ ማህበር እያነሳ ይሆን ወይ? አልያም ሳያውቀው ለዚህ እኩይ የአደፍራሽነት ራዕይ የተደራጀ ማህበር ይሆንን ነው ያልኩት። መቸም እግዚአብሔር ይጠቀምበት እንጂ በመጨረሻው ሰይጣን ለአገልግሎቱ ዋንጫ አይጠብቅም፤ የይሁዳ ወንጌል ጸሐፊ እንደነገረን ሁሉ።
          ከሁሉ የሚገርመው ማንበብ መጻፍ የሚያውቀው የዚህ ማህበር የማቅ ጀሌ ሁሉ አይኑ መያዙ ነው። መጻፍ እንደሚለው በክርስቶስ ብቻ እንድናምን ሳይሆን በስሙ መከራም እንድንቀበልም ተጠርተናል። (ፊልጵ 1፡ 29) ታደያ የማይገባ ቅናት ሞልቶት ከአሸባሪ ወገን ሲሆን ሲያዩ ለምን ዝም አሉ ይሆን? የትንቢት ተጠቃሚ ሳይሆን መፈጸሚያ መሆኑ ገብቷቸው? ማህበሩ አሳዳጅ፣ አባራሪ፣ ገዳይ፣ሳያውቀው በአሉታዊ መልኩ ጌታውን እያገለገለ መሆኑን ተረድተውት?
ይህ ጥሪ የአሰላለፍ ለውጥ ለማድረግ ለወሰኑ ለማቅ አባላት ሁሉ ነው። አውቀውም ሳያውቁት ከገቡበት ክርስቶስን የማሳደድ ስራ ተመልሰው የትንቢቱ   ተጠቃሚ ይሁኑ ነው የምለው። ወንዝ የማያሻግር ደንብ አውጥተን ዋጋ ለማይከፈልበት ዋጋ አንስጥ። እርሱ ጌታችን እንደሆነ በዚህም ይሁን በዚያ ሊጠቀምብን ይችላል። ግን እንደ ባለአዕምሮ ሰው ልናስብ ግድ ነው፤ ትንቢቱ የሚፈጸምብን ወይስ ከሚፈጸምልን ወገን እንሆን?
          መልካም የልደት በዓል ለሁላችን በተለይ በመምጣቱ ተጠቃሚ ለሆንን ሁሉ።ጌታ የመጣው ለሰው ሁሉ አንጂ ለኢትዮጵያውን ብቻ አይዶለም። እንደእርሱ የመሰለን ያለን እንደ ሆነ ይህን የሚያወራውን ጓሮ በቀል የማቅ ወሬ ትተን በብቸኛው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንመን ደግሞም አንታመን። እርሱ ለሁላችንም ይበቃል። የሰው ባዶ ቅናት የሰውን እንጅ የእግዚአብሔርን ልብ አይሞላም። አሻፈረን የምንል ከሆነ ተጠቅሞብን እንደ ይሁዳ መጣል የማየቀር ነው። ጌታ ለማቅ ብሎ በቃሉ የገለጠውን ሀሳቡን እንደሁ አይተው!
 Kebede
15 comments:

 1. ጋሽ ከቤ

  ስሞትን ብቻ በእንግሊፍጣ ለመጻፍ ለምን አስፈለጎት? የተማርኩ ነኝ ለማለት ነው? ለነገ ደግሞ ሌላ ስም አዘጋጁ። "አባ ሰላማ" እኮ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የጥላቻ ነጠላ ዜማ ከለቀቀ ሰንብቷል። የተበላ ቁብ? እንዲያው በከንቱ ስትዳክሩ ታሳዝናላችሁ። ማኅበረ ቅዱሳን የጽድቅ ሥራ ላይ ነው፤ ለመማር ካልፈለጋችሁ በስተቀር ከእናንተ ዓይነቱ ሥራ ፈቶች ጋር አተካሮ ለመግጠም ጊዜ የለውም። ይልቁንስ ጊዜው ሳይረፍድ ትክክለኛዋን መንገድ ፈልጉና ከጥፋት መንገድ ተመለሱ።

  ReplyDelete
 2. መጽሐፍ ቅዱስን በሚገባ ካልተረዳ የጌታን ክብር ዝቅ ከሚያደርግ የቅዱሳንን ክብር ከሚያቃልል ወገን ተሰልፎ ለቤተ ክርስቲያን ክብር ቆሜያለሁ ማለትና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ከነ ሙሉ ክብሩ ተቀብሎ በማገልገል ላይ የሚገኘዉን ማኅበረ ቅዱሳንን መንቀፍ ስህተቱ ካንተ መሆኑን በግልጽ ያሳያል፡፡ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ ማለት የእውነተኛነት መገለጫ ሊሆን አይችልም፡፡ ማሳደድም ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ አንተዉ እራስህ የጌታን ክብር ዝቅ እያደረግህ ቅዱሳንን እያቃለልክ አላሳደድኩም ብትል የመዉጊያዉ ብረት ሲያገኝህ ይገባሃል፡፡

  ReplyDelete
 3. Ay....kebede....serafet Yale MK werena sibket yelachihum.

  MK lemastewawek new weyis wongel lemesbek yihinin bilog yekefetachihut gerami fiturich.....

  ReplyDelete
 4. መልካም የልደት በዓል ለሁላችን በተለይ በመምጣቱ ተጠቃሚ ለሆንን ሁሉ።ጌታ የመጣው ለሰው ሁሉ አንጂ ለኢትዮጵያውን ብቻ አይዶለም።

  ReplyDelete
 5. የያዛችሁት ሃይማኖትን ማስተማር ሳይሆን የቡድንተኝነት ፕሮፖጋንዳን ማስፋፋት መሆኑ በጣም ግልጽ እየሆነ መምጣቱን የዛሬው ፍሬ አልባ ጽሑፋችሁ ምስክር ነው። የእናንተና የማህበረ ቅዱሳን መሠረታዊ ልዩነት ለወንጌል አገልግሎት የመቆምና ያለመቆም ጉዳይ መሆኑም ግልጽሆኗል። ለዚህ የሁለታችሁም ድረ ገጾች በየዕለቱ የሚጽፉትን ማየት በቂ ነው። ማንም መመስከር እንደሚችለው ከሁለታችሁ ፈጠራንና የአሉሽ አሉሽ ወሬን ሲፈተፍት የሚውለው ይህ የእናንተ ብሎግ እንጂ የማህበረ ቅዱሳን ብሎግ አይደለም።

  ዛሬ ደግሞ ማህበረ ቅዱሳን ጌታ የመጣው ለኢትዮጵያውያን ብቻ መሆኑን እንደሚያስተምር መፃፋችሁ ምን ያክል በተራ ሰዎች እየተመራችሁ እንደሆነ ነው።

  አሁን ያናደደኝ ነገር ቢኖር ግን የእናንተን ውሸትና የፈጠራ ወሬ እያነበብኩ መልስ ለመስጠት ጊዜዬን ማጥፋቴ ነው። ለማንኛውም ወደማንነታችሁ ፍለጋ ሳይመሽ በጊዜ ዝለቁ።

  ReplyDelete
 6. yihuda eko yetesetewn tewnet lemechawot bicha edil yetesetew sew neber. andie tinbit tenegroletal beka bezia menged bicha mehed neber mirchaw. Hawariyatm eko siletemeretu enji astesasebachew ena emnetachew kenga yanesu nachew. Leziam new menfes kidus yasfelegachew.

  ReplyDelete
 7. 'Ke Egziabher gar yemitala yifechal".Meles ke Geta gar yemiserawun mahber tesadebe. Be Geta tefeche minm saykoy. don't tell us the word of Meles repeatedly, he got what he deserves.

  ReplyDelete
 8. MECHEM YIH EWINET NEW. YEMIYASAZINEW GIN AWQEWIT AYDELEM. BIYAWQUTMA NORO YEKIBIRIN GETA BALSEQELUT NEBER TEBLO TETSFUAL. MQ GETA YELIBACHEWIN AYIN ABRTO WONGELUN SAYSHEFAFINUNA SAYQELAQILU YEMISEBKUBET ZEMEN YIMTA, MEKERA KEMIYAMETU MEKERA TEQEBAYOCH LEMEHON ENDIYAGELEGILU. MQ KEMIYASERAW HINTSA YIBELT YEEYESUS DEM YIKBRAL.

  ReplyDelete
 9. be bechengawu geta Eyesus kerestos enmen? degmom enetamen. Excellent.

  ReplyDelete
 10. Please use your website for the right thing. Why you finish your time by talking about one group, MK. Just use the website to teach good things. If you keep doing like this, I advice you to change your name from Aba Selama to Luther.

  ReplyDelete
 11. mr kebede, you yourself are devil. you should go to memhir Girma. yours is the fake Jesus.

  ReplyDelete
 12. የኸ የግል የመጽሐፍ ግንዛቤ ፣ ሊቃውንቶቻችን (ጸጋ ፣ ተስፋ ፣ Kebede ) ሃሳብ እንዲሰጡበትና እንድንማርበት ያህል በማለት እንጅ ፣ የቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት ነው በማለት የቀረበ ጽሁፍ እንዳልሆነ ከወዲሁ እገልጻለሁ ፡፡

  ጠቃሚ ቃል ፡-
  ንስሓ ፡- ጸጸት ፣ ሐዘን ፣ ቁጭት ፣ በተሠራ ኀጢአት ምክንያት የሚደረግ ፤ ቅጣት ቀኖና ፣ የኀጢአት ካሳ
  ንስሓ ገባ ፡- በክፉ ሥራው ዐዘነ ፣ ተጸጸተ ፣ በደሉን ገለጠ ፤ ኀጢአቱን ተናገረ ወይም አመነ

  ይሁዳ በጌታ ከተመረጡት 12 ሐዋርያት መሐከል አንዱ ነው (ዮሐ 6፡7ዐ ፤ 13፡18)፡፡ አባቱ ስምዖን ይባላል (ዮሐ 6፡71) ፡፡ ከሌሎች ይሁዳዎች ለመለየት በመጽሐፍ የአስቆሮቱ ይሁዳ በመባል ይታወቃል ፡፡ ይኸ ሐዋርያ ፣ ጌታን በመክዳቱና ለሠላሳ ዲናር አሳልፎ በመለወጡ ፣ አባቶች ከሃዲው ፣ የጥፋት ልጅ እያሉ የሚያስተምሩን ነው ፡፡ እንዲያውም አባቱን እናቱን የሚል ተጨማሪ በደል እንዳለውም በትውፊት ይነገራል ፡፡

  ይሁዳ ፡ በርግጥ በስተ መጨረሻው ጌታን አሳልፎ የሰጠ ፣ ዮሐንስም የገንዘብ ሌባ እንደ ነበረ ቢገልጽም ፣ ለሞት ያበቃውን ወንጀል ከመፈጸሙ በፊት ፣ የነበረ የወንጌል ሕይወቱን አስቃኛለሁ ፡፡

  ማሳሳቢያ ፡- የኸ የግል ግንዛቤ እንጅ ፣ የቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት እንዳልሆነ በድጋሚ እገልጻለሁ ፡፡ ይኸን ተከትላችሁ ብዕር እንዳትመዙ ፡፡

  ይሁዳ ፤
  - እንደ ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት አብሮ ከጌታ ጋር እየተዟዟረ የጌታን ትምህርት ተከታትሏል ፤ ጌታ ያሳያቸውን ተአምራት ፣ መፈውሶች በሙሉ (ጴጥሮስ ፣ ዮሐንስና ያዕቆብ በግል ካዩትና ከትንሣዔው በኋላ ከታዩት በስተቀር ) በመመልከት እውነት መሆናቸውን ፤ ጌታም የእግዚአብሔር ልጅ ፣ የሚጠበቀው መሲህ (ክርስቶስ) እንደሆነም አምኗል (ዮሐ 6፡69)
  - እንደ ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት ወንጌልን የማስተማር ፣ ድውያንን የመፈወስና አጋንንትን የማውጣት ሥልጣን ተሰጥቶት እየተዘዋወረ አገልግሏል ፡፡ ማቴ 1ዐ፡1-4 ፤ ሉቃ 9፡1-2
  - ጌታም ተልዕኮአቸውን ፈጽመው ወደርሱ ሲመለሱ ፣ ስማቸው በሰማያት ባለው መዝገብ መጻፉን አብስሯቸዋልና በዚህም የይሁዳ ስምም ተመዝግቧል ማለት ይቻላል
  - በሰው ፊት ለሚመሰክሩልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርላችኋለሁ ፡፡ ማቴ 1ዐ፡32 (ይሁዳ በተሠማራባቸው አካባቢዎች ስለ መንግሥተ ሰማያት መቅረብ እየመሰከረ አስተምሯል)
  - ጌታ በተራራ ስብከቱ እናንተ የዓለም ጨው ናችሁ ፤ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ በመባል ከብጤዎቹ ጋር ሳይነጥል መስክሮለታል ፡፡ ማቴ 5፡13-14
  - እንደ ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት በመጨረሻው ምሽት ሥጋወ ደሙን ከጌታ እጅ ተቀብሏል ማቴ 26፡26-29 (ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የሚለውን ዘር እንመልከት ፡፡ ዮሐ 6፡55-59 )
  - “አባቴ እኔን እንደ ሾመኝ እኔ ደግሞ በመንግሥቴ ከማዕዴ ትበሉና ትጠጡ ዘንድ፥ በአሥራ ሁለቱ በእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በዙፋኖች ትቀመጡ ዘንድ ለመንግሥት እሾማችኋለሁ” በመባል የጋራ ቃል ተገብቶለታል ። ሉቃ 29-30 ፡፡
  - ከጌታ ጋር ዕድል እንዲኖረው ዘንድ በሚያስችል መልኩ በፋሲካ በዓል ዋዜማ ፣ ጌታ እግሩን አጥቦታል ዮሐ 13፡5-8

  ይቀጥላል

  ReplyDelete
 13. ክፍል ሁለት
  - የምስመው እርሱ ነው፤ ያዙት ተጠንቅቃችሁም ውሰዱት ብሎ ምልክት ሰጥቶአቸው ነበር። ማር 14፡44 (ተጠንቅቃችሁ ውሰዱት ሲል በመንገድ እንዳይበደል ፣ ክብሩም እንዳይጓደል ፣ ወይም እንዳይገደል ማለቱም ይሆናል ፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ ላይ ተመሰካክረው እንዲገደል በወሰኑበት ሰዓት ፤ ይሁዳ ወደዚያው የወሰደው ርምጃ የሰጡትን ገንዘብ ለካህናቱ መመለስና ፣ በሠራው በደል ተጸጽቶ ራሱን ማጥፋቱ ነው (ማቴ 27፡1-5)፡፡ ይኸም ማለት ካህናቱ ከስምምነታቸው ወይም ይሁዳ ከገመተው ውጭ ፈጽመዋል ያሰኝ እንደሁ እንጅ ኢየሱስን ማስገደል ፍላጐቱ ነው አያስብልም ፡፡ ይህንኑ አባባል የሚያጠናክረውን የሚከተለውንም ንባብ እንመልከት )

  - የካህናት አለቆችም ሸንጎውም ሁሉ እንዲገድሉት በኢየሱስ ላይ ምስክር ይፈልጉ ነበር፥ አላገኙምም ፤ ብዙዎች በሐሰት ይመሰክሩበት ነበርና ፥ ምስክርነታቸው ግን አልተሰማማም ። ማር 14፡55-56 (የካህናት አለቆች ኢየሱስን ለመወንጀልና ለመግደል በቂ ምስክር ቢፈልጉም ፣ ይሁዳ የጌታን ትምህርት ሁሉን እያወቀ ሳለ ፣ ከመጀመሪያው የጌታ የስብከት እንቅስቃሴ ጀምሮ የነበረ ደቀ መዝሙር ቢሆንም እንዲፈርዱበት በምሥክርነት ሥፍራ አልቆመም ፤ ይኸም የሚያስረዳን ኢየሱስን እንዲገድሉ ማድረግ ዓላማው አልነበረም ማለት ነው )

  - ይሁዳ በደል ስለፈጸመ ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ጋር በፍርድ ቀን ለዳኝነት የማይሰየም ለሚመስላቸው ፣ በደልን ከፈጸማት በኋላ ንስሐን በመፈጸሙ ፣ ወንጌል ደግሞ ንስሐ የሚገቡ ሊፈርዱ ዕድል እንዳላቸው ስለሚናገር የተገባለት ቃል አይነፈገውም ፡፡ ማቴ 12፡41 ፣ ሉቃ 11፡32 ፡፡ (የመጥምቁ ዮሐንስና የጌታችንና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጀመሪያዋ ቀዳሚ ትምህርት ንስሐ ግቡ የምትል ናት ፡፡ ይሁዳም በሠራው ኀጢአት በመጸጸት በቃላት ከሚለፈለፈው በላይ የተቀበለውን ገንዘብ በመመለስና ራሱን በመግደል ፣ የበደል ካሳ አድርጎ ሕይወቱን አቅርቧል ማቴ 27፡4-5 ፤ ሥራ 1፡18 ፡፡ ይኸን ድርጊቱን እንደ ንስሓ ለምን እንደምቆጥርለት ማቴ 5፡29-3ዐ የሚለውን ተመልከት)

  - በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። ማቴ 7፡21 (የአብ ፈቃድ መላው ዓለም እንዲድን ነው ፣ ይኸ ድኀነት የሚገኘው ደግሞ በልጁ መስዋዕትነት ብቻ ነው ፡፡ ስለዚህም ይኸ ዕቅድና ፈቃድ እንዲፈጸም ይሁዳ በአጉል መንገድ ተሰማርቶ ቢሆንም የሚፈለገውን አስተዋጽኦ አድርጓል ፡፡ የማን ፈቃድ እንደፈጸመ ደግሞ ከሚከተለው ኃይለ ቃል እንመልከት)

   ኢየሱስ ፣ ቁራሽም አጥቅሶ ለአስቆሮቱ ለስምዖን ልጅ ለይሁዳ ሰጠው ፡፡ ቁራሽም ከተቀበለ በኋላ ፣ ያን ጊዜ ሰይጣን ገባበት ፡፡ እንግዲህ ኢየሱስ የምታደርገውን ቶሎ ብለህ አድርግ አለው (ዮሐ 13፡26-27) ፡፡ ይሁዳም ቁራሹን ከተቀበለ በኋላ ወዲያው ወጣ ፤ ሌሊትም ነበረ ፡፡ ርሱም ከወጣ በኋላ ፣ ኢየሱስ የሰው ልጅ ከበረ ፤ እግዚአብሔርም ስለ እርሱ ከበረ ፤ እግዚአብሔር ስለ እርሱ የከበረ ከሆነ ፤ እግዚአብሔር ደግሞ እርሱን ራሱን ያከብረዋል ፤ ወዲያውም ያከብረዋል (ከቁጥር 3ዐ-32)

  - የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል፥ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት፤ ያ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር አለ። ማቴ 26፡24 (ለዚያ ሰው ወዮለት ማለቱ ፤ ከወንጌል ትምህርት አኳያ በፈጣሪነቱ የይሁዳን አሟሟት ተረድቶ ማዘኑ ነው እንጅ ፣ የቂም በቀል በትር እንደሚያሳርፍበት መዛቱና ለኛም እንዲያ ልባችንን በቁርሾ እንድናጨቀይ ማስተማሩ ሊሆን አይችልም)

  - በተመሳሳይም በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና። ማቴ 5፡44 (ይኸን ያስተማረ ጌታችን ፣ ርሱን የበደለውን ይሁዳን ይቅር አይለውም ማለትም የክርስትና ትምህርታችንን መልዕክት ይጻረራል)

  - ማቴ 26፡31 በዚች ሌሊት ሁላችሁ በእኔ ትሰናከላላችሁ፤ እረኛውን እመታለሁ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ የሚል ተጽፎአልና፤ (የጌታ ቃል እንደተነገረው ሁሎችም ጌታን ለብቻው (ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ በስተቀር) ትተውት ተበትነዋል ፤ በቅርብ የሚከታተሉትም እነ ጴጥሮስ እንኳን የማያውቁት መሆናቸውን ደጋግመው አስረድተዋል ፡፡ ይኸም ማለት ኢየሱስን በዛች ምሽት ያልካደ አንድም ደቀ መዝሙር አልነበረም ማለት ነው ፡፡ ታድያ ይሁዳ ብቻ ስለምን ?)

  ሰላማዊ የወንጌል መግለጫችሁን ለማንበብ በመጠበቅ

  ReplyDelete