Monday, December 24, 2012

የማህበረ ቅዱሳን ግራ ማጋባትና የእርቁ ጉዳይ እያነጋገረ ነው

አቡነ ህዝቅኤል  «በውጪ የሚገኙ አባቶቻችን እዚህ መጥተው የመምረጥም ሆነ የመመረጥ እድል ይኖራቸዋል» አሉ። ምን ማለት ነው?
የሰሞኑ የማኅበረ ቅዱሳን «እርቁ ይቅደም» የሚለው ጩኸት ብዙዎችን ግራ እያጋባ ነው፡፡  እስካሁን የእርቁን ሂደት ከልቡ ሳይደግፍና ተገቢውን ጥረት ሳያደርግ ቆይቶአል፡፡ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ ከዚህ ቀደምም እንዳልነው በውጭ አገር በሚገኘው ሲኖዶስ ውስጥ ያሉትን ብዙዎቹን አባቶችና መምህራን ተሐድሶ ናቸው ብሎ ስለፈረጃቸው ነው፡፡ እንደታሰበው እርቁ ቢሳካና በውጭ ያሉ አባቶች በአገር ቤት ካሉ አባቶች ጋር በአንድ ሲኖዶስ ስር ከቆሙ ጳጳሳቱ ሀገረ ስብከት ይኖራቸዋል፡፡ መምህራኑም በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ስፍራ ይሰጣቸዋል ብለን እናስባለን፡፡ ይህ ግን ለማህበረ ቅዱሳን ትልቅ ራስ ምታት ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ተሐድሶ ብሎ የፈረጃቸውና በየልሳኖቹ ስማቸውን ያጠፋቸው አባቶችና መምህራን በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ስፍራ ካገኙና አገልግሎታቸውን ከቀጠሉ ከማህበሩ ጋር ግጭት መፈጠሩ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ምናልባትም እንደ ግንቦቱ ያለ ውግዘት እንዲተላለፍ ሌላ የክስ ፋይል ከፍቶ ውግዘት የሚጠይቅባቸው አባቶችና መምህራን ይኖራሉ፡፡ ስለዚህ ከዚህ ሁኔታ አንጻር ማቅ እርቁን አይደግፍም፡፡ ስለእርቁ ከልቡ ያልተንቀሳቀሰው ለዚህ ነው፡፡
አሁን «እርቅ ይቅደም» እያለ ያለው ለእርቁ ካለው ፍላጎት ሳይሆን የምርጫ ህጉ ማህበሩ ያልጠበቃቸውን ማሻሻያዎች ስላደረገና የማኅበሩን ጥቅምና ፍላጎት የማያሟላ ስለሆነ ተቃውሞውን በተቃውሞነቱ ማቅረብ ሲገባው «እርቁ ይቅደም» በሚል ሽፋን እያቀረበ ነውና ያለው ህዝበ ክርስቲያኑ ይህን ሐቅ መገንዘብ አለበት፡፡ ማቅ ግራ እያጋባ ያለው ለቅስቀሳ የተጠቀመባቸው ቃላትና አርአያዎቹ ናቸው፡፡ የአክራሪ ሙስሊሞችን ምሳሌ ጠቅሶ እንደዚያ አይነት ተቃውሞ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንዲደረግ ማወጁ በራሱ ጤናማ አይደለም፡፡ በዚህ ትልቅ ጉዳይ ላይ ጾም ጸሎትን ዝቅ አድርጎ መመልከቱና ከዚያ ይልቅ ተቃውሞን ማበረታታቱ ያወጀው ሥጋዊና አለማዊ ተቃውሞ መሆኑን አሳይቷል፡፡ ስለጾም ጸሎት የሚሰብኩትን ትምህርታቸው የተጣመመ ነው ማለቱ ደግሞ ማቅ ሃይማኖት እንደሌለው አስመስክሯል፡፡
ማህበረ ቅዱሳን ከእርቅ ይቅደም በስተጀርባ እያስተላለፈ ያለው መልእክት ቤተክርስቲያኒቱን መቆጣጠር ያለብኝ እኔ ነኝ የሚል ነው፡፡ ከምንም በላይ የሚያሳስበው የእርቁ ጉዳይ ሳይሆን የቀጣዩ ፓትርያርክ ማንነት ነው፡፡ ቀጣዩ ፓትርያርክ ጥቅሜን ላያስጠብቅልኝ ይችላል ብሎ ስለሰጋ ተቃውሞ መነሳት አለበት ብሎ አምኗል፡፡ ህዝቡን ለተቃውሞ የሚያነሳሳው ደግሞ ይህን ጉዳይ ጠቅሶ ሳይሆን «እርቅ ይቅደም» የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው በሚል በዚህ አጀንዳ ተከልሎ ነው፡፡ ስለዚህ የማቅ አጀንዳ አስፈጻሚ መሆን የለብንም፡፡ ለእርቁ መሳካት ግን ሁሉም ወገን ተገቢውን ሁሉ በአክራሪ ሙስሊሞች መንገድ ሳይሆን በክርስቲያናዊ ጨዋነት ማቅረብ ለማቅ ባይዋጥለትም ከምንም በላይ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር መጸለይ አለበት፡፡  
ከዚህ ቀደም እንዳልነው እርቁ እንዲሰምር ከምንም በላይ የሁለቱ ሲኖዶሶች አባላት ከልባቸው መስራት አለባቸው፡፡ «እርቅ መደረግ አለበት» የሚል ግፊት እንደማቅ ባሉ ግድ የለሾች ስላየለ ብቻ ሳይሆን በእርቁ አስፈላጊነት ላይ ማመንና ያስቀመጧቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ደግመው በሚገባ ማጤን አለባቸው፡፡ እኔ ያልኩት ብቻ ነው ተፈጻሚ መሆን ያለበት የሚለው የማይለወጥ አቋም መሰል የድርድር ሀሳብ ውጤቱ ከወዲሁ የታወቀ ነው፡፡ የአገር ቤቱ ሲኖዶስ ዋና ጸሀፊ ብፁእ አቡነ ህዝቅኤል ሰሞኑን በታህሳስ 2005 እትም እንቁ መጽሄት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዲህ ብለዋል፡፡ «ብፁእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ ሀገር ቤት መጥተው እዚህ ጠቅላይ ቤተክህነትም ሆነ በሚፈልጉት ገዳም አስፈላጊው ነገር እየተደረገላቸው እንዲቀመጡ ነበር እኛ ለእርቁ ሰው የላክነው፡፡» ይህ ቃል ከዚህ ቀደምም የተናገሩት ነው፡፡ የተሻሻለ ነገር የለም፡፡ ከዚህ ቃል የምንገነዘበው ጉዳዩ እኛ ያልነውን መቀበል አለባቸው አይነት ከሆነ እርቁ ትርጉም የለውም፡፡
አባ ህዝቅኤል አክለው አቡነ መርቆሬዎስ ይመለሱ ቢባል ታሪክና ቀኖና ይፋለሳል የሚል ምክንያት ነው ያቀረቡት፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የተፈጸመው ታሪክ በቤተክርስቲያኗ ላይ ያስከተለው ችግር እስካሁን ቀጥሏል፡፡ አሁን እየተባለ ያለው የእርቅ ሂደትና ውጤቱም የታሪኩ አካል ነው፡፡ መቀየር አይችልም፡፡ ከዚህ አንጻር ቤተክርስቲያኗን ለሁለት የከፈለው ታሪክ በእርቁ ሂደት ቢስተካከል ለቤተክርስቲያን ሰላምን የሚያመጣ እንጂ እንዴት ታሪክንና ቀኖናን የሚያፈርስ ይሆናል?
በቅርቡ ይፋ ባደረግነው የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ደብዳቤዎች ላይ ቅዱስነታቸው የዚያን ጊዜ ተጨባጭ ሁኔታዎች ለቅዱስ ሲኖዶስ አብራርተዋል፡፡ ቅዱስነታቸው በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ በመመልከት ነሐሴ 28/1983 በተደረገው የሲኖዶስ ስብሰባ በተሰጠው ውሳኔ መሰረትና ውሳኔውን ተከትሎ መስከረም 28/1984 በተደረገው የሲኖዶስ ስበሰባ መንበረ ፓትርያርኩን እንዲለቁ መደረጉንና ይህም የሆነው በቁጥር 69/298/84 በተጻፈ ደብዳቤ «በወቅቱ የነበረው ያልሆነ ውዥንብር እስኪስተዋል፣ መላው የኢትዮጵያ ምዕመናንና ካህናት ሁኔታውን በእርጋታ እስኪመለከቱትና ለቅዱስ ሲኖዶስ ከታሪክና ከቀኖና ቤተክርስቲያን አንጻር ትክክለኛውን ፍትህ ለመስጠት የሚያስችል ግንዛቤ እስኪያገኝ ድረስ» እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ፓትርያርክነቱን ለቀቁ የተባለበት የጤና ችግርም እንዳልነበረባቸውና ይህንንም በወቅቱ የነበሩ የሲኖዶስ አባላት እንደሚያውቁ ተናግረዋል፡፡ አንድ ፓትርያርክ ከሥልጣኑ ሊወርድ ከሚችልባቸው ህጎች መካከል አንዱ ሥራውን መሥራት የማያስችለው የጤና እክል ካጋጠመው የሚል ነው፡፡ እርሳቸውም በዚህ አንቀጽ መሰረት ከስልጣናቸው እንደወረዱ ነው ያኔ የተነገረው፡፡ እርሳቸው ግን እስካሁንም ጤናማ ናቸው፡፡ በውጪ ያለውን ሲኖዶስም ፓትርያርክ ሆነው እየመሩ ነው፡፡ ከዚህ ሁኔታ አንጻር በእርቁ ሂደት ውስጥ ወደመንበራቸው ይመለሱ በሚለው ሐሳብ መስማማት ቢቻል የሚጣስ ታሪክም ሆነ ቀኖና እንደማይኖር የብዙዎች እምነት ነው፡፡
እንደ አባህዝቅኤል ቃለ ምልልስ ከሆነ «አቡነ መርቆሬዎስ ወደ አገር መጥተው መቀመጥ ይችላሉ፡፡ ሰላሙ ተመስርቶ በውጪ የሚገኙ አባቶቻችን እዚህ መጥተው የመምረጥም ሆነ የመመረጥ እድል ይኖራቸዋል» ብለዋል፡፡ ይህ አቡነ መርቆሬዎስን ይጨምራል አይጨምርም የሚለው ግልጽ አይደለም፡፡ የሚጨምር ከሆነ ግን በምን ቀኖና መሰረት ነው ይህ ሊከናወን የሚችለው? ሌላ ታሪክ እና ቀኖና መፍጠር አይሆንም ወይ? የሚል ጥያቄን ያስነሳል፡፡ ስለዚህ ቀኖና እኛ እንዳደረግነው የሚሆን ነገር ነው ማለት ይቻል ይሆን?
በአንድ በኩል ስለፓትርያርክ ምርጫ እየታሰበ በሌላ በኩል ስለእርቅ ማሰብ እንዴት አብሮ ሊሄድ እንደሚችል ባናውቅም የምርጫው ጉዳይ እርቁን እንዳያደናቅፈው ግን ያሰጋል፡፡ እርቁ ቢሳካ እጅግ መልካም ነገር ነው፡፡ የማይሳካ ከሆነ ግን አቡነ መርቆሬዎስ ሰጡ እንደተባለው አስተያየት እርሳቸው በሕይወት እስካሉ ድረስ የአገር ቤቱ መንበር በዐቃቤ መንበር ሲመራ ቢቆይ ተመራጭ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ይሁን እንጂ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በማህበረ ቅዱሳን ከፍተኛ ጣልቃ ገብነት ቤተክህነቱ በሹምሽር እየታመሰ ነው፡፡ የቤተክህነቱ አስተዳደር ትልቅ ዝቅጠት ውስጥ ገብቷል፡፡ ከፍተኛ የሀብት ምዝበራም እየተፈጸመ ነው፡፡ አቶ ተስፋዬ ውብሸት በምክትል ስራ አስኪያጅነቱ ሊቃውንቱን እያነሳ ቁልፍ ቦታዎችን እንደእርሱ ባሉ ከልማት ኮምሽን እንዲዛወሩ በተደረጉ «አቶዎች» እየሞላና በሚደረገው የፓትርያርክ ምርጫ ላይ ለአባ ሳሙኤል እድሉን ለማስፋት እየሰራ ነው፡፡ አቃቤ መንበሩም ስልጣናቸው ተገድቦ ስላለና ጥቂት አምባገነኖች አልታዘዝ ስላሏቸው ክፍተቱ ለህገወጦች አመቺ ሆኗል፡፡ ስልጣኑን የሚፈልጉ ጳጳሳትም እርስ በርስ እየተራኮቱ እንዳለ ካሉት ሁኔታዎች መገንዘብ ቀላል ነው፡፡ ሆኖም የፓትርያርኩ ወደመንበራቸው መመለስም ሆነ በአቃቤ መንበር መቀጠሉ ግን የሚታሰብ አይመስልም፡፡
ለሁሉም የሰላም አምላክ ሰላምን ለቤተክርስቲያናችን ፍቅር አንድነትን ለአባቶቻችን ይስጥልን፡፡

9 comments:

 1. This comment has been removed by a blog administrator.

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተ እርግጥ የማቅ ውጤት ስለሆንክ አልፈርድብህም ከአንተ ይልቅ አባሰላማ ብሎግ ያሳዝናል እንዲህ ያለ የብልግናና ቃል ማስነበቡ

   Delete
 2. kkkk yemogn zefenu hulgizie.... alu. Lela zefen yelachihum. Lezare gin altesakalachihum.

  ReplyDelete
 3. why MK members drive crazy this church? why our church leaders not come to conclusion for Abune Morkros to his position (Patriarch)? every buddy need to answer those questions to become a part of unity the church.All orthodox church members really leave a side our difference and discuss each others regarding the MK roll in church body. every one got bad opinion about MK doing stupid thing or play game in church for MK advantage. Guys must have to stop Mk interface from Orthodox church interest, otherwise church members never come united.

  ReplyDelete
 4. የቤተ ክርስቲያናችን ወደ አንድነት የመምጣቱ ነገር እጅግ አስቸጋር ነው። ምክንያቱም ማቅ መንፈሳዊያኑን አባቶች በጥቅማ ጥቅም እያደናገራቸው በመሆኑ ቀዉሱ ሰቆቃው እያየለ መጥቶዋል። ቀድሞ እርቅ አያስፍልግም 6ኛ ፓትርያርክ ይመረጥ እያለ ሊቃነ ጳጳሳቱን በነዋይ አደዝዞዋቸው ህግ ተረቆ እንደፈለገው ለማድረግ ሞክሮ ነበር ነገር ግን እግዚአብሔር በክነ ጥበቡ ነገሮች ሁሉ እንድቀየሩ በማድረጉ መንገዱ እንደ መለወት ተገዶዋል። በድህረ ገጾቹ ላይ ሁላችንን ያገባናል ተነሱ በማለት ሌላ አዋጅ በማወጅ ላይ ነው። ምነው ድሮ ሁሉንም ያገበዋል አላልም? በፊት እናንተን አያገባችሁም ፈላጭ ቆራጭ እኔ ነኝ እያለ ይፎክር አልነበረም እንደ ?። ጨለማው አይሎበታል መሰልኝ ትላንትና ይቃወመው የነበረውን መንገድ መከተል ጀምሮዋል። ይህች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማቅ አባለት እስካሉባት ድረስ ከቶ ወደ አንድነት አትመጣም። ማቅ ዳር ዳር ከምል ምነው አቡነ መርቆርዮስ ወደ መንበራቸው ይመለሱ ብሎ መናገር አቃተው? አልዋጥለት ስለምለው፤ ድሮ በቅጥፈት ይቃወማቸው ስለ ነበር ነው። ይልቁን መንግስት እጅ አለበት እያለ ከምዋሽ ንስሀ ብገባ ይሻለዋል። የማቅ ቅጥረኛ ጳጳሳት ለምርጫው እየሮጡ ናቸው እግዚአብሔር ደግሞ መንገዱን ዘግቶባቸውል።እሳቱም አይሎባቸዋል። የማቅ እሳት ማጥፋት የሚቻለው እያንዳንዱ ምዕመንና ምዕመናት ስለ ቅድሰት ቤተ ክርሰቲያኑ መነጋገር አላበት እጅ የማቅን ተንኮል በዝምታ ማለፍ የለበትም። እርሱ መርዘኛ ኮብራ እባብ ነው። ሰው እግዚአብሔርን ማምለክ ትቶ እንደት ማህበርን (ማቅ) ያመልካል? የሰንበት ት/ቤት መዘምራንም አምልኮት የምገባው ለእግዚአብሔር ነው እንጅ ማህበርን አይደለም ማለት አለባቸው ደግሞም አስራታቸውን ለቅድሰት ቤተ ክርሰቲያን መሰጠት አለባቸው እንጅ እንደ ጣኦት ለማህበር መገበር የለባቸውም። ሐይማኖትና ማቅ ለይተው ልያዉቁ ይገባል እንላለን።

  ReplyDelete
 5. here bakachehu 1 aseteyayete seche heweane orthodox nawe

  ReplyDelete
 6. ያለ ድንግል ማርያም አማላጅነት አለም አይድንም!!!

  ReplyDelete
 7. Egizbher Yiker yebeleh !! yesedib menfes yarkelih , bewinu Orthdoxawinethen bemesadeb new yemtgeltew ?? endezih eyehonachihu new Bet Emnetachinin yemtasedibut . yebzuwochachin chiger yehe new , Sile wengel yeteleke ewiket saynoren derso asteyayet lemestet enrotalen , kezam sinalef degmo ensadebalen . Egziabher sideben atbiko yetelal
  ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ 1 peter 2 :23
  የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር። ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም። Yehuda 1:9

  ReplyDelete
 8. ለሁሉም የሰላም አምላክ ሰላምን ለቤተክርስቲያናችን ፍቅር አንድነትን ለአባቶቻችን ይስጥልን፡፡

  ReplyDelete