Wednesday, December 26, 2012

እርቅ ከእግዚአብሔር ጋር

·        ከአምስተኛ ወደ አራተኛ ፓትርያርክ አንመለስም የሚለው አቋም ክርስቲያናዊ አቋም አይደለም። ስለ ክርስቶስ መመለስ ይቻላል።
 ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ሰላምን ካላደረገ ከወንድሙ ጋር ሰላም አይኖረውም። ሰላም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፤ እግዚአብሔርን ትተን ሰላምን ስንፈልግ ከንቱ ድካም እንጂ ሌላ ትርፍ አናገኝም። ነቢዩ ኢሳይያስ ለክፉዎች ሰላም የላቸውም ይላል። ክፉዎች እግዚአብሔርን አይፈሩም ሰላምን በጉልበታቸው፤ ወይም በገንዘባቸው ለማምጣት ይሞክራሉ። ሌሎች ደግሞ በጠረጴዛ ዙሪያ ስለሰላም ይፈራረማሉ። ነገር ግን ክፉዎች ስለሆኑ እራሳቸው የመሠረቱትን ሰላም እራሳቸው ያፈርሱታል። ለዚህ ነው ነቢዩ ለክፉዎች ሰላም የላቸውም ያለው።57፥21።
    ሰው ከአምላኩ ከተጣላ በኋላ እግዚአብሔር የሰውን ልብ ጎብኝቶ ነበር። የሰው ልብ እግዚአብሔር እንዳየው ይህን ይመስላል «እግዚአብሔርም የሰው ክፋት በምድር ላይ እንደበዛ የልቡ ሐሳብ ምኞቱም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደሆነ አየ» ይላል ዘፍ 6፥5። ነቢዩ ኤርምያስም የሰው ልብ እጅግ ክፉ ነው ማንስ ያውቀዋል? ብሏል። ጠቢቡ ሰሎሞን «የሰው ልጆች ልብ ክፋትን ትሞላለች በሕይወታቸውም ሳሉ እብደት በልባቸው ነው ከዚያ በኋላ ወደ ሙታን ይወርዳሉ» ይላል መክ 9፥5። ይህ የሰው የልብ ክፋት ሊወገድ የሚችለው ከእግዚአብሔር ጋር ሲታረቅ ብቻ ነው። እግዚአብሔር ክፋትን ከሰው ያስወግድ ዘንድ አንድያ ልጁን ልኳል። ክፋት ለሚባለው የልብ በሽታ መድኃኒቱ የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ቃሉ «ለእናንተ አስቀድሞ እግዚአብሔር ብላቴናውን አስነሥቶ እያንዳዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ ሰደደ» ይላል የሐዋ 3፥26።
    የዛሬዋ ቤተ ክህነት ከክፋት እየመለሰ የሚባርከውን ወልደ እግዚአብሔርን ትታ ከሱ ውጭ ዓለም የሚሰጠውን ሰላምን ስትፈልግ ትታያለች። በንጹሕ ልብ ወንጌል የሚሰብኩ ለቤተ ክርስቲያን እና ለሀገራቸው ቀና ሐሳብ ያለቸው በርካታ ደቀ መዛሙርት ነበሯት፤ ከልጅነት እስከ እውቀት ድረስ ከፊደል እስከ ትርጓሜ መጻሕፍት ቤተ ክርስቲያን ያስተማረቻቸው በርካታ ዓይናማ ሊቃውንት ነበሯት። በጸሎታቸው የሚማልዱ ከክፉዉ ጋር የሚዋጉ ታጋዮች መንፈሳውያን ቅዱሳን በውስጧ ነበሩ። እነዚህን ሁሉ የቤተ ክርስቲያን ኃይላት ጊዜ ከሰጠው ገፊ ማህበር ጋር በመተባበር አሳደደች። ቤተ ክህነት የሚጠቅማትን እና የሚጎዳትን አላወቀችም፤ ጊዜ ካመጣው ባለ ጠብመንጃ ጋር እያመነዘረች የመጀመሪያ ትዳሯን ፈታች።
    ለቤተ ክርስቲያናቸውና ለሀገራቸው ቀና ሐሳብ የነበረቻውን በብሩህ አእምሮ እየተንቀሳቀሱ ብዙ ለውጥ ያመጡትን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን ለነፍሰ በላው ለደርግ በጣቷ ፈርማ እንዲገደሉ አሳልፋ የሰጠች ቤተ ክህነት ናት። ጳጳሳቱ የቴዎፍሎስን መንበር ለመውረስ በነበራቸው ክፉ የሚመኝ ልብ ደርግ በፓትርያርኩ ላይ የወሰደውን እርምጃ እንደግፋለን ብለው በፊርማቸው አረጋግጠዋል። በዚያ ወቅት በየቤታቸው በር እያንኳኳ ጳጳሳቱን ያስፈርም የነበረው ሰው ዛሬ የማህበረ ቅዱሳን ስውር አመራር አባል ነው። በክርስቶስ ያልተፈወሰ ክፉ ልብ ክፋትን እየሠራ ወደ ሞት ይገሰግሳል።
    ኢሕዴግ ደርግን አስወግዶ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ታመዋል እያለች ታስወራ የነበረችው ገለሞታዋ ቤተ ክህነት ናት። ፓትርያርኩን ይህ ውዥንብር እስኪያልፍ ድረስ ታመምሁ ይበሉ ካልሆነ ኢሓዴግ ሊገልዎት ይችላል እያሉ ይመክሩ እና ያስወሩ የነበሩት  ጳጳሳቱና ባለቤታቸው ቤተ ክህነት ናት። ኢሕዴግ አቡነ ጳውሎስን ከጓሮ ደብቆ ጳጳሳቱን እያናጠለ ፕትርክናው መሆን ያለበት ለናንተ ነው ይላቸው ነበር። ይህ መርቆርዮስን ከሥልጣን ለማስወገድ የተጠቀመበት ዘዴ ነው። ጳጳሳቱ አቡነ መርቆርዮስን በደብዳቤ ሳይሆን በቃል አሞኛል ብለዋል በማለት በጸበልና በህክምና እንዲቆዩ ብሎ ወሰነባቸው። አቡነ መርቆርዮስ ግን አልታመምሁም መሥራት እችላለሁ እኔ ጤነኛ መሆኔን ልባችሁ ያወቀዋል፤ አሁን የምታደርጉት ነገር ነገ ለኔም ለናንተም ለሚመጣው ትውልድም አስቸጋሪ ፈተና ያመጣልና ብታስተውሉ ይሻላል ብለው በደብዳቤ አመልክተዋል። ደብዳቤውን ካባ ሰላማ ላይ ስለሚገኝ ያንቡ።
    ዛሬ ላይ ያሉ ጳጳሳትም እውነቱን ሕሊናቸው ያውቀዋል፤ ነገሩ የልብ ጉዳይ ነው። በሥጋዊ መንገድ ከመደራደር ይልቅ በሕይወት ያሉ ፓትርያርክን በፍቅርና በክርስቶስ መንፈስ ተቀብሎ ስላምን ማወጅ ይቻል ነበር። ግና ክፉ ልብ እያለ ሕሊና የሚያውቀውን አያሠራም። መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም እዳ አይኑርባችሁ ይላል ሮሜ 13፥8። ጳጳሳቱ የማን እዳ እንዳለባቸው እራሳቸው ያውቁታል። እነ አባይ ጸሐዬን እንጂ ክርስቶስን ለመስማት ፈቃደኛ አይመስሉኝም። የክርስቶስ ዕዳ ቢኖርባቸው የተሰደዱትን ወንድማቸውን በባዕድ አገር ለ20 ዓመት በሰላምና በጸጥታ የኖሩትን አባት አይጠሉም ነበር።
    እኔ በዚህ ሁሉ የሚታየኝ አባቶቻችን ከእግዚአብሔር ጋር አለመታረቃቸው ነው። በነጻ የሰጠኋችሁን በነጻ ስጡ ይላል መጽሐፍ፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ይቅር እንዳለን እዳችንን ከፍሎ ጸጋውን እንዳደለን ቢያውቁ ይቅር ለማለት ይህን ያህል ባልተለመኑ ነበር። ፍቅርን የሚሽር ሕግ የለም፤ ቢኖር እንኳ አስፈላጊ አይደለም። ፍቅር የሕግ ሁሉ ፍጻሜ ነውና ከአምስተኛ ወደ አራተኛ ፓትርያርክ አንመለስም የሚለው አቋም ክርስቲያናዊ አቋም አይደለም። ስለ ክርስቶስ መመለስ ይቻላል። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስም ስለ ፍቅር ሁሉን መተው ይችላሉ። ጳጳሳቱ የውሸት ምስክርነት እየሰጡ አስቆጧቸው እንጂ እውነቱን ተቀብለው እባክዎት ይቅር ይበሉን አጥፍተናል ቢሉ አቡነ መርቆርዮስ ከፍቅር የሚበልጥ ስልጣን እንደሌለ የሚያውቁ ይመስለኛል።
    ብቻ እግዚአብሔር ከክፉ ልብ ያድነን። በመጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጋር እንታረቅ አለባለዚያ በቤተ ክርስቲያን ለፈሰሰው የቅዱሳን ደም ሁሉ ዋጋ እንከፍላለን። በገፋናቸው የወንጌል ሰዎችም ዋጋ እንከፍላለን። ለማንኛውም ለሁላችንም እግዚአብሔር የሚያስተውል ልብ ይስጠን።
    ይቆዬን!!!!!
   ተስፋ ነኝ

8 comments:

 1. Sile mahber kidusan yesetehew haset bihonim, melkam timihiret new. Aba Selamawochim kemahiberu gar tareqachihu bandi lay lebetekrestiyan siru

  ReplyDelete
 2. I like it Tesfa. Most of your articles are useless but today you write well.

  ReplyDelete
 3. Sijemr ante maneh b/krstiyan ena abatochin emtawardew drows kemenafkan mn ytebekal sdb ena mnfkna enji lemangnawm ezaw adarash tekrayth abune merkoryoshn yzeh menfk b/krstiyanachinn lkekln ykesarn lekesar new

  ReplyDelete
 4. መልካም ነው!!

  ReplyDelete
 5. Wow what's going on with MK leaders? Becaus they are not built on the truth rock. Now the time is coming to shaking like a earth quick on MK . Be honest to Lord God!!!

  ReplyDelete
 6. አቡነ መርቆሬዎስ እና ሌሎቹም አገራችን ቤተ ክርስቲያናችን
  ያባረሩን አሁን የሉም ሞተዋል ስለዚህ ተመልሰን መጥተናል ብለው አገር ቢገቡ
  ያዲስ አባው ጳጳሳት ኢሀደግን እሰሩልን ሊሉ ነው
  ያን ጊዜ ክርስቲያኑ በነቂስ ወጥቶ
  እነሱኑ እናንተ ውጡል ከናንተ መሃል የመንፈስ ቅዱስ ተገዢዎች ለሆኑ
  እንታዘዛለን ቢል ወዴት ያሄዳሉ

  ReplyDelete
 7. God bless you brothers for your wonderful spiritual message. it very crucial to get the right word of God at this crazy time. thank your so much. If everybody understand how to reconciliation with Lord God, I believe everything was very simple to make peace in church, no one the right way word of God in orthodox church leaders. yes if we make peace with God, easy to make peace each-other.Please lets us stop to proud our flesh.The truth peace come from Lord Jesus Chris only.

  ReplyDelete
 8. Aba selamawech, U wrote wonderful articles today.but most of your Previous articles were not meaning full. But today wow wow thank u million times and God bless u

  ReplyDelete