Sunday, December 30, 2012

ፍካሬ መጻሕፍት

(በጮራ ድረ ገጽ ላይ የቀረበ፦ http://www.chorra.net/)

                             “ወትቀውም ንግሥት በየማንከ
በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት
ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአፅምኢ እዝነኪ”
“በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።
ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ” (መዝ. 44/45፥9-10)

ይህን የመዝሙረ ዳዊት ጥቅስ በሚያነብብ በአብዛኛው ሰው አእምሮ ውስጥ በቶሎ የምትከሠተው ድንግል ማርያም ናት። ይህ የሆነው ጥቅሱ ስለ እርሷ የተነገረ ስለ ሆነ ግን አይደለም። ስለ እርሷ የተነገረ ነው ተብሎ ስለ ተወሰደ፥ በተደጋጋሚ ከእርሷ ጋር ተያይዞ ስለ ተነገረ፥ በየወሩ በ21 ለበዓለ ማርያም የሚዜም ምስባክ ስለ ሆነ ነው ስለ እርሷ የተነገረ ያህል እየተሰማን የመጣው። ቅድስት ድንግል ማርያምን ንግሥተ ሰማይ ወምድር ብለው የሚያምኑ ክፍሎች፥ ሐሳባቸውን በዚህ ጥቅስ ለማስደገፍ ይሞክራሉ። እርሷን በንጉሥ እግዚአብሔር ቀኝ እንደ ተቀመጠች ንግሥትም ይቈጥሯታል።

ቃሉ ስለ ማን እንደ ተነገረ ከመጽሐፉ ተነሥተን እንመልክት። ጥቅሱ ለሚገኝበት ለዚህ የመዝሙረ ዳዊት ክፍል የዐማርኛው የ1953ቱ ዕትም መጽሐፍ ቅዱስ “ለመዘምራን አለቃ፤ በመለከቶች፤ የቆሬ ልጆች ትምህርት፤ የፍቅር መዝሙር” የሚል ርእስ ተሰጥቶታል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለራሷ ባሳተመችው የ2 ሺሁ ዕትም መጽሐፍ ቅዱስም “ለመዘምራን አለቃ በመለከቶች የቆሬ ልጆች ትምህርት የፍቅር መዝሙር” በማለት ይህንኑ ርእስ ነው ያስቀመጠው።
ይህ የቆሬ ልጆች መዝሙር በቊጥር 1 ላይ “ልቤ መልካም ነገርን አፈለቀ፥ እኔ ሥራዬን ለንጉሥ እነግራለሁ፤ አንደበቴ እንደ ፈጣን ጸሓፊ ብርዕ ነው።” ተብሎ እንደ ተመለከተው፥ የዚህ መዝሙር ዐላማ ስለ ንጉሡ መልካም ቅኔን መቀኘት ነው። ከቊጥር 2 አንሥቶም እስከ ቊጥር 9 ድረስ ስለ ንጉሡ ይቀኛል። ቀጥሎም ከቊጥር 10 እስከ 15 ድረስ ንግሥቲቱን ያመጣታል።

የንጉሡ ማንነት በግልጽ የተቀመጠ ስለ ሆነ ጥያቄ አያስነሣም። ጥያቄው ያለው ንግሥቲቱ ማናት? በሚለው ሐሳብ ላይ ነው። ከላይ እንደ ጠቀስነው ብዙዎች “ንግሥቲቱ” የሚለውን ለቅድስት ድንግል ማርያም ሰጥተው ይተረጒማሉ፤ እውን በዚህ ዐውድም ይሁን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የጌታ እናት በመሆኗ “ንግሥት” የሚለውን ለእርሷ መቀጸል ተገቢ ነው ወይ? የንጉሥ እናትስ ንግሥት ተብላ ትጠራለች ወይ?

ንግሥት የንጉሥ ሚስት እንጂ እናት አይደለችም። መዛግብተ ቃላትም ይህንኑ ነው የሚያረጋግጡት።
·        የአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ንግሥት የሚለውን ቃል፥ “በቁሙ፤ በአባቷ ፈንታ የነገሠች፤ እንደ ማክዳና እንደ ህንደኬ እንደ ዘውዲቱና እንደ ቢክቶሪያ ያለች ባለሙሉ ሥልጣን። … የንጉሥ ሚስት እተጌ፥ ባሏ ከርሱ ጋር ያነገሣት” ብሎ ነው የሚፈታው (1948፣ ገጽ 624)።
·        የደስታ ተክለ ወልድ “ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት”ም በተመሳሳይ "ዐልጋው [ዙፋኑ] ያባቷ ኹኖ ባሏ ሳይነግሥ ብቻዋን የነገሠች እንደ ማክዳ ያለች፤ ወይም ዐልጋው የባሏ ኹኖ ከባሏ ጋር የነገሠች ይተጌ።” በማለት ይተረጒማል (1962፣ ገጽ 840)።
·        በአዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማእከል ያሳተመው ዐማርኛ መዝገበ ቃላትም ንግሥት የሚለውን ስም “በዘውዳዊ አስተዳደር ዙፋን ላይ የተቀመጠች የሀገር መሪ። የንጉሥ ሚስት” ሲል ይፈታዋል (1993፣ ገጽ 286)። ቃሉ የንጉሥ ሚስትን እንጂ እናትን አያመለክትም ማለት ነው። ሌሎችም መዛግብተ ቃላት ቢኖሩ ከዚህ ውጪ ሊናገሩ አይችሉም።

በዚህ የመዝሙር ክፍል ከቊጥር 9-17 ስለ ንግሥቲቱ የተነገሩት ሐሳቦች ንግሥቲቱ የንጉሡ ሚስት እንጂ እናት መሆኗን አያሳዩም። ንግሥት የተባለችው ለጊዜው የሐሴቦን ንጉሥ ልጅ መሆኗን እንረዳለን (ቊ. 13)። ንጉሡ ውበቷን ወድዷል። የእርሱ ሚስት ስላደረጋትም እርሱን በመከተል ትታቸው የወጣችውን ወገኖቿንና የአባቷን ቤት እንድትረሳ ይነግራታል። እርሷ የንጉሡ ሚስት በመሆን የምታገኘው ልዩ ልዩ ክብርም በዚህ ክፍል ውስጥ ተዘርዝሯል፤ - የምድር ባለጠጎች አሕዛብ በፊቷ ይማለላሉ፤ ልብሷ ለንግሥትነቷ የሚመጥን የወርቅ መጐናጸፊያ ነው፤ ሚዜዎቿ የሚሆኑ ደናግልም በእርሷ መሪነት ወደ ንጉሡ ይቀርባሉ፤ በአባቶቿ ፈንታ ስሟን ለልጅ ልጅ የሚያሳስቡ ልጆች ተወልደዉላታል፤ ንግሥት እንደ መሆኗም በአባቶቿ ፈንታ የተወለዱላትን ልጆች በምድር ላይ ገዥዎች አድርጋ ትሾማቸዋለች። እነዚህ ሁሉ በክፍሉ የተዘረዘሩት የንግሥቷ መገለጫዎች፥ ንግሥቲቱ የንጉሡ ሚስት እንጂ እናት አለመሆኗን ያሳያሉ።

ወደ መዝሙሩ ፍጻሜ ስንሄድ የዕብራውያኑ ጸሓፊ ከመዝሙር 44/45 ውስጥ ጠቅሶ ስለ ክርስቶስ የተናገረውን ቃል እናገኛለን። “ስለ ልጁ ግን፥ አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው ይላል” የሚለው ከተጠቀሰው መዝሙር ቊጥር 6-7 ላይ የተወሰደ ነው። ስለዚህ የቆሬ ልጆች በዚህ ክፍል የዘመሩት ስለ ክርስቶስ ነው ማለት ነው። ንጉሥ የተባለው ክርስቶስ ከሆነ፥ ንግሥቲቱ ታዲያ ማናት? ክፍሉ የተነገረው ስለ መሲሑ (ክርስቶስ) ነውና፥ “በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።” ተብሎ የተነገረላት ንግሥት ቤተ ክርስቲያን እንጂ ሌላ ልትሆን አትችልም።

በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ እግዚአብሔር የሕዝቡ የእስራኤል ባል እንደ ሆነ፥ እስራኤልም ሚስቱ እንደ ሆነች ተጽፏል (ኢሳ. 54፥5-6፤ ኤር. 3፥14፤ ሆሴ. 2፥4)። የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ደግሞ፥ ክርስቶስን በሙሽራ ቤተ ክርስቲያንን በሙሽሪት ገልጸዋቸዋል (ዮሐ. 3፥29፤ 2ቆሮ. 11፥2፤ ራእ. 19፥7-8፤ 21፥9፤ 22፥17)።

“ወትቀውም ንግሥት በየማንከ - ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች” ለሚለው ንባብ በግእዙ መዝሙረ ዳዊት አንድምታ ላይ ከተሰጡት ትርጉሞች መካከል የመጀመሪያው ምእመንን (ቤተ ክርስቲያንን) የተመለከተ ነው። አንድም ብሎ ግን ለቤተ ክርስቲያን ሰጥቶት የነበረውን ትርጒም ለማርያም በግል በመስጠት ጥቅሱን አለንባቡ አለምስጢሩም ይፈታዋል (1982፣ ገጽ 240)።

በግብረ ሐዋርያት ተጽፎ እንደምናነበው ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት በኋላ፥ በኢየሩሳሌም ተሰብስበው የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ በመጠባበቅ በጸሎት ይተጉ ከነበሩት 120 ሰዎች መካከል አንዷ ቅድስት ድንግል ማርያም ነበረች (ሐ.ሥ. 1፥12-15)። ይህች ጉባኤ፥ ቤተ ክርስቲያን እንደ ሆነችና የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችውም በእነርሱ አማካይነት እንደ ሆነ ግልጽ ነው። በዚህ ውስጥ የጌታ እናት ቅድስት ድንግል ማርያም የቤተ ክርስቲያን የአካል ክፍል ወይም ከምእመናን አንዷ በመሆኗ፥ ንግሥት ከተባሉት የቤተ ክርስቲያን አባላት መካከል ናት እንጂ፥ ከዚህች አንዲት የክርስቶስ አካል ውጪ በተለየ ሁኔታ ልትቈጠርና ንግሥት ልትባል የምትችልበት አግባብ ግን የለም። እንዲህ ስንል ግን መጽሐፍ ቅዱስ የሚመሰክረውን እውነት ሳንሸራርፍና ሳንጨምርበት ማስቀመጣችን ነው እንጂ እርሷን ዝቅ ማድረጋችን እንዳልሆነ በትሕትና እንገልጻለን።  

ጥቅሱን ለማርያም መስጠት ለምን አስፈለገ?
በአገራችን “የእናት አማላጅ ፊት አያስመልስ አንገት አያስቀልስ” የሚል ብሂል አለ። ብዙ ጊዜ ብሂሉ የሚነገረው ከቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ ጋር ተያይዞ ነው። ብሂሉን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ትረካዎችም በአዋልድ መጻሕፍት ውስጥ በብዛት ይገኛሉ። “ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች” የሚለው ጥቅስ አለንባቡና አለምሥጢሩ ለቅድስት ድንግል ማርያም የተሰጠውም ለብሂሉ ማጠናከሪያ ይሆን ዘንድ ይመስላል። እርሷ በንጉሥ ክርስቶስ ቀኝ የቆመች ንግሥት ተደርጋ ተወስዳለች፤ በቀኙ የቆመችውም ለምልጃ ነው ተብሎ ታምኗል። ይሁን እንጂ በዚህ ምድር ያሉ ቅዱሳን ካንቀላፉ ቅዱሳን ጋር የማይታይ መንፈሳዊ ኅብረት እንጂ በቀጥታ የሚገናኙበት መሥመር የላቸውም። በዚህ ዓለም ያሉትም ከጥቂቶችና በአካል ከሚተዋወቁት በቀር በዐይን የማይታይ መንፈሳዊ ኅብረት እንጂ ቀጥተኛ ግንኙነትም ሆነ ኅብረት የላቸውም። ስለዚህ ወዳንቀላፉ ቅዱሳን የአማልዱን ጥያቄ የምናቀርብበት እድል የለም። አዋልድ መጻሕፍት ግን ይህ ይቻላል ነው የሚሉት። እነርሱ በሚሉት መንገድ ቢታሰብ እንኳ፥ ተገቢነት የሌለውና ምልጃ ሊጠየቅበት የማይገባ ጒዳይ ሁሉ፥ የእናት ምልጃም ቢሆን እንኳ፥ በተማላጁ በኩል ተቀባይነት ያገኛል፥ ምላሽም ያሰጣል ማለት አይደለም።

የዳዊት ልጅ  ሰሎሞን ከነገሠ በኋላ፥ አጊት ከተባለች ሴት የተወለደው ሌላው የዳዊት ልጅ አዶንያስ መንገሥ ባይሆንለትና ዙፋኑ ለሰሎሞን ቢሰጥበት፥ ዳዊትን በእርጅናው ታገለግለውና ታሞቀው የነበረችውን ቆንጆዪቱን ሱነማዪቱን አቢሳን እንዲድርለት የሰሎሞንን እናት ቤርሳቤህን አማላጅ አድርጎ ወደ ሰሎሞን ልኳት ነበር። ቤርሳቤሕን የላከው “የእናት አማላጅ ፊት አያስመልስ አንገት አያስቀልስ” ብሎ ይሆናል። “አያሳፍርሽምና ሱነማዪቱን አቢሳን ይድርልኝ ዘንድ ለንጉሡ ለሰሎሞን እንድትነግሪው እለምንሻለሁ” ሲልም ተማጽኗት ነበር (1ነገ. 2፥17)። “ቤርሳቤሕም፥ መልካም ነው፥ ስለ አንተ ለንጉሡ እነግረዋለሁ አለች። ቤርሳቤሕም የአዶንያስን ነገር ትነግረው ዘንድ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን ገባች። ንጉሡም ሊቀበላት ተነሣ፤ ሳማትም፤ በዙፋኑም ተቀመጠ። ለንጉሡም እናት ወንበር አስመጣላት፥ በቀኙም ተቀመጠች። እርስዋም፦ አንዲት ታናሽ ልመና እለምንሃለሁ አታሳፍረኝ አለች። ንጉሡም። እናቴ ሆይ፥ አላሳፍርሽምና ለምኚ አላት። እርስዋም፦ ሱነማዪቱ አቢሳ ለወንድምህ ለአዶንያስ ትዳርለት አለች። ንጉሡም ሰሎሞን ለእናቱ መልሶ፦ ሱነማዪቱን አቢሳን ለአዶንያስ ለምን ትለምኝለታለሽ? ታላቅ ወንድሜ ነውና መንግሥትን ደግሞ ለምኚለት። ካህኑም አብያታርና የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ ደግሞ ከእርሱ ጋር ናቸው አላት። ንጉሡም ሰሎሞን፦ አዶንያስ ይህን ቃል በሕይወቱ ላይ አለመናገሩ እንደ ሆነ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፥ ይህንም ይጨምርብኝ። አሁንም ያጸናኝ፥ በአባቴም በዳዊት ዙፋን ላይ ያስቀመጠኝ፥ እንደ ተናገረውም ቤትን የሠራልኝ ሕያው እግዚአብሔርን! ዛሬ አዶንያስ ፈጽሞ ይገደላል ብሎ በእግዚአብሔር ማለ። ንጉሡም ሰሎሞን የዮዳሄን ልጅ በናያስን ላከ፤ እርሱም ወደቀበት፥ ሞተም።” (ቊ. 18-25)።

ንጉሡ እናቱን ወንበር አስመጥቶ በቀኙ አስቀምጧት ነበር። “እናቴ ሆይ፥ አላሳፍርሽምና ለምኚ” ብሏትም ነበር። ይሁን እንጂ ልመናዋ በንጉሡ በልጇ ዘንድ ተገቢ ሆኖ ባለመገኘቱ፥ ምንም እናቱ ብትሆን የገባላትን ቃል ሊጠብቅ አልቻለም። አዶንያስ አቢሳን ሚስቱ ሊያደርጋት ካለመቻሉም በላይ ሕይወቱንም ዐጣ። እናትም ብትሆን እንኳ ልመናዋ ሁሉ ይሰማል ማለት እንዳይደለ ከዚህ ታሪክ እንማራለን። ከዚህ አንጻር “የእናት አማላጅ ፊት አያስመልስ ዐንገት አያስቀልስ” የሚለው ብሂልም በጥያቄ ውስጥ ይወድቃል። 

በአዋልድ መጻሕፍት ውስጥ ድንግል ማርያም ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን ምልጃ ጠየቀችባቸው የተባሉቱ አንዳንዶቹ ጒዳዮች የጌታን እናት ቅድስት ድንግል ማርያምን ጨምሮ የእግዚአብሔር ሰዎች ምልጃ ሊጠይቁባቸው የማይገቡና በእግዚአብሔር ቃል ከተገለጠው የእግዚአብሔር ፈቃድና ሐሳብ ጋር ፈጽሞ የማይስማሙ ናቸው። በተኣምረ ማርያም ውስጥ ስለ በላኤ ሰብእ በተጻፈው ትረካ ውስጥ፥ ደኻው ሰው በውሃ ጥም እጅግ ተቃጥሎ “ስለ እግዚአብሔር ብለህ ውሃ አጠጣኝ” ሲለው በላኤ ሰብእ እጅግ እንደ ተቈጣውና በማርያም ስም ሲለምነው ግን እንደ ሰጠው ተጽፏል። በዚሁ መነሻነት በላኤ ሰብእ ሲሞት ማርያም ተከራክራ ነፍሱን እንዳስማረች ተጽፏል (ተኣምረ ማርያም 1985፣ ገጽ 70)።

በቅዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ ላይ የምናገኘው የአንድ ባለጠጋ ታሪክም ተመሳሳይ ይዘት አለው። ባለጸጋው የነበረውን ሀብት “ላዝማሪ ለዘዋሪ እየሰጠ ዐለቀበት።” ከዚያም ሀገሩን ጥሎ ወደ ሌላ ወደማይታወቅበት ስፍራ ሲሄድ፥ ሰይጣን የጨዋ ልጅ መስሎ ወዴት ትሄዳለህ ይለዋል። ባለጠጋውም የደረሰበትን ይነግረዋል። ሰይጣንም ድንጋዩን በምትሐት ወርቅ አድርጎ በማሳየት ይህን ብሰጥህ አትመለስም ወይ? ሲለው እመለሳለሁ ይላል። እርሱም የምሰጥህ የምፈልገውን ስትፈጽምልኝ ነው በማለት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስን እንዲክድ ይጠይቀዋል። እርሱም ይክዳል። መላእክት ጻድቃን ሰማዕታት አያማልዱም በል ይለዋል። እርሱም ይላል። በመጨረሻም የማርያምን ወላዲተ አምላክነት ካድ ይለዋል። ይሁን እንጂ ባለጠጋው እርሷንስ አልክድም በማለት ይመልሳል፤ በዚህ ጊዜ ሰይጣን ወርቅ አስመስሎ የሰጠውን ደንጊያ ተቀብሎ በእርሱ ይመታውና ይገድለዋል።

በምድር ላይ በኖሩት ሕይወት መሠረት የበላኤ ሰብእም ሆነ የባለጠጋው ነፍስ ዘላለማዊ መኖሪያ ሊሆን የሚችለው ሲኦልና ገሃነመ እሳት ነው። እግዚአብሔርን የካዱትን በላኤ ሰብእንና ባለጠጋውን ቅድስት ድንግል ማርያም በምልጃዋ አስታረቀች የሚለው ሐሳብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። በስሟ የተደረሰ ድርሰት ካልሆነ በቀርም የጌታ እናት ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔርን የካደውን ከእግዚአብሔር ጋር ልታስታርቅ አትችልም። እንኳ እንዲህ ያለው የከፋ በደል ቀርቶ የእግዚአብሔርን ቃል ላልሰማውና እግዚአብሔር ለናቀው ለሳኦል በሕይወተ ሥጋ ሳለ ሲያለቅስ የነበረውን ሳሙኤልን፥ “በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው?” ብሎ ዳዊትን እንዲቀባው ነገረው። በዚህም የሳሙኤል ልቅሶ ለሳኦል እንዳልጠቀመው እናስተውላለን (1ሳሙ. 16፥1፡12-13)። በሕይወተ ሥጋ አንዱ ስለ ሌላው እንዲማልድ ሞገስን የሰጠ እግዚአብሔር፥ በአንዳንድ ሁኔታዎች ከዚህ ቀደም በፊቱ ለመቆም ሞገስ ያገኙና ያንቀላፉ ቅዱሳን መማለድ ቢችሉ እንኳ ልመናቸው ተቀባይ እንደማይኖረው እግዚአብሔር የተናገረበት ሁኔታ አለ። ነቢዩ ኤርምያስ “እግዚአብሔርም እንደዚህ አለኝ። ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም፥ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አይዘነብልም ከፊቴ ጣላቸው ይውጡ” ሲል መስክሯል (ኤር. 15፥1)።
ቅድስት ድንግል ማርያምን ጨምሮ የእግዚአብሔር ሰዎች ሁሉ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈጽሙ እንጂ ከእግዚአብሔር ፈቃድ በተቃራኒ የሚቆሙ አይደሉም። ሐዋርያው ዮሐንስ በመልእክቱ፥ “ማንም ወንድሙን ሞት የማይገባውን ኀጢአት ሲያደርግ ቢያየው ይለምን፥ ሞትም የማይገባውን ኀጢአት ላደረጉት ሕይወት ይሰጥለታል። ሞት የሚገባው ኀጢአት አለ፤ ስለዚያ እንዲጠይቅ አልልም” (1ዮሐ. 5፥16) በማለት፥ በሕይወተ ሥጋ ያለን ክርስቲያኖች ስለ ሌሎች ምልጃ የምናቀርብባቸው ኀጢአቶች እንዳሉ ሁሉ፥ ምልጃን ልናቀርብባቸው የማይገቡ ኀጢአቶች መኖራቸውንም ያስረዳል።

“ሞት የሚገባው ኀጢአት” በሚለው ሐሳብ ዙሪያ ሊቃውንት የተለያየ አመለካከት ያንጸባርቃሉ። በመልእክተ ዮሐንስ ውስጥ ሐዋርያው ያነሣውና ምልጃ እንዳይቀርብበት የከለከለው ኀጢአት ምን ይሆን? በመልእክቱ ውስጥ የተገለጸው አንዱና ዋናው ኀጢአት የክርስቶስ ተቃዋሚ መሆን ነው። “ክርስቶስ አይደለም ብሎ ኢየሱስን ከሚክድ በቀር ውሸተኛው ማን ነው? አብንና ወልድን የሚክድ ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው” እንዲል (1ዮሐ. 2፥18፡22)። መቼም አግዚአብሔርን ከመካድ የበለጠና የሚከፋ ኀጢአት አይኖርም። “ሰውስ ሰውን ቢበድል እግዚአብሔር ይፈርድበታል፤ ሰው ግን እግዚአብሔርን ቢበድል ስለ እርሱ የሚለምን ማን ነው?” የሚለውም ቃል እግዚአብሔርን በቀጥታ የበደለን ሰው የሚያስታርቀው አማላጅ እንደማይኖር ያብራራል (1ሳሙ. 2፥25)። ይልቁንም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለራሷ ያሳተመችው የ2ሺሁ ዓ.ም. መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ጥቅስ፥ “ሰውስ ሰውን ቢበድል ወደ እግዚአብሔር ይጸልዩለታል፤ ሰው ግን እግዚአብሔርን ቢበድል ወደ ማን ይጸልዩለታል?” ነው የሚለው።


ከላይ እንደ ተመለከትነው “ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች” የሚለው ጥቅስ፥ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። በጥቅሱ ሽፋንነት እየተሠራጩ የሚገኙት ልዩ ልዩ ኢመጽሐፍ ቅዱሳውያን ትምህርቶች ሁሉ ግን ከእግዚአብሔር ሐሳብ ውጪ ስለ ሆኑና የድንግል ማርያምን “ርኅራኄ” በመግለጽ ስም ሰው እግዚአብሔርን እስከ መካድ ቢደርስ እንኳ በእርሷ ምልጃ ይድናል ወደሚል የክሕደት ትምህርት የሚወስዱና ኀጢአትን የሚያበረታቱ ናቸውና በክርስትና ትምህርት ውስጥ ተቀባይ የላቸውም።

26 comments:

 1. ክርስቶስ ራሱ ከሴቶች ሁሉ መርጦ ፥ ከሥጋዋ ሥጋውን ከነብሷ ነብስን ነስቶ ፥ ወላዲተ መለኮት የሆነችውን ቅድስት ድንልግል ማርያምን ከአምልኮት በስተቀር የተፈለገውን ሁሉ ምሳሌ በመስጠት ብናከብራት ምንድነው ችግሩ ? ሊቃውንት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ለእውነተኛዋ ንግሥት ይህን ጥቅስ አዎ ለርሷ ሠጥተዋታል ! እኛም እናንተም ብትቃወሙ አንተወውም! ቅዳሴዋን የደረሰው አባ ሕርያቆስ በብዙ ምሳሌ ቀድሷታል። ይህንስ ምን ልትሉ ነው ? ..''የንጉሥ ሚስቱ እንጅ እናቱ ንግሥት አትባልም'' ብላችኋል። የታላቁ ንጉሥ የቆስጠንጢኖስ እናት በታሪክ መጻሕፍት ''ንግሥተ እሌኒ '' አትባልም እንዴ ? እስቲ ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ ስጡኝ። ከአክብሮት ጋር ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድም Kebede Bogale መልካም ብለሃል ፡፡ እንዲያው ግን ስትመልስ ጠንቀቅ በል ፤ ለነዚህ ሰዎች እንደ ልብ የሚሯሯጡበት ቀዳዳ አትክፈትላቸው ፡፡ በተለምዶ አባባል ያልለመድነውን አገላለጽ “ወላዲተ መለኮት” የተባለው “ወላዲተ አምላክ” ብትለው ቀና ይሆናል ፡፡ መለኮት የሦስቱም የጋራ ንብረት ነው ብለው የሚሞግቱ አይታጡም ፤ የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥጋና ነፍስ የተዋሃደው ወልድ ኋላም በምድራዊ ስሙ ኢየሱስ የተባለው በተለየ አካሉ ነው ፡፡ ይኸ ልዩ አካል የተዋሃደው በርግጥም መለኮት የተለየው አካል እንዳልሆነ እረዳለሁ ፡፡ ምክንያቱም የመለኮትን ሥራ ሥጋ ፣ የሥጋን ተግባራት ደግሞ መለኮትም እንደተጋራው መጽሐፍ ስለሚያስረዳን ፡፡ ነገር ግን እንዲህ በጥቅሉ ሲቀመጥ ብዕራቸውን የሚስሉ ሰዎች አይታጡም በማለት ስለፈራሁ ለመጠቆም ያህል ነው እንጅ የጽንሰ ሃሳብ ስህተት አለው በማለት አይደለም ፡፡

   በተረፈ ለቅድስት ድንግል ማርያም ንግሥት ብንላት እንዲያውም ያንስባታል እላለሁ ፡፡ ምክንያቱም የዓለም መድኃኒት የሆነውን ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ወልደዋለችና ፡፡ እመ አምላክ መባል ወይስ ንግሥተ ሰማይ ወምድር ማለት ሊከብደን የሚገባው ? እስቲ መግባባት ብንችል ለማንኛውም መዝሙሩ ምን እንደሚል እንመልከት ፡፡

   1/ መጀመሪያ እንዳመቸን የመጽሐፍን ቃል እየበጣጠስን ወደ ምንፈልገው አቅጣጫ ባንጓዝበት እጅግ መልካም ይሆናል የሚል ምክርን አስቀድማለሁ ፡፡
   ከጠቀሳችሁት የመዝሙር ቁጥር ቀደም ብሎ በመዝሙር 44 የሚገልጸውን ብንመለከት አምላካቸውን ንጉሥ እንደሚሉት እንገነዘባለን ፡፡ ሙሉ የምዕራፉ ንባብ ሃሳብ ወይም መልዕክት አምላክ ቀደም እንደረዳቸው በማስረዳት ይጀምራል ፡፡ ኋላ ላይ ግን እንደተዋቸውና ለአሕዛብ አሳልፎ እንደሰጣቸው ፤ እንዲያ ሆኖም እንኳን እነርሱ ግን የሚመኩት በርሱ እንደሆነ ይገልጻል ፡፡ ጊዜ ያለው ሙሉ ምዕራፉን ይመረምረው ዘንድ እንዲያነብ ተጋብዟል ፡፡ ለዓይነት ያህል ከቃሉ እነዚህን መርጫለሁ ፡፡
   ቁ 1 አቤቱ፥ በጆሮአችን ሰማን፥ አባቶቻችንም በዘመናቸው በቀድሞ ዘመን የሠራኸውን ሥራ ነገሩን።
   ቁ 4 አምላኬና ንጉሤ አንተ ነህ፤ ለያዕቆብ መድኃኒትንህ እዘዝ።
   ቁ 8 ሁልጊዜ በእግዚአብሔር እንከብራለን፥ ስምህንም ለዘላለም እናመሰግናለን።

   እናስተውል !!! ስለ ምድራዊ የሰው ንጉሥ ቢሆን የሚተርከው አምላኬ እያለ ፣ ስለ አምላክ ችሎታና ችሮታ ፣ የአባቶችን ርዳታና ስሙ ለዘላለም እንደሚመሰገን አይተርክም ፡፡

   2/ እናንተ መንደርደሪያ ያደረጋችሁት ኃይለ ቃል የሚገኝበትን መዝሙር 45ን ደግሞ ስንመለከተው ፣ አሁንም ንጉሥ ብሎ የሚጠራው አምላካችንን እንደሆነ ቅንነት ያለው ሁሉ መረዳት ይችላል ፡፡ እናንተ ጎርዳችሁ ካለፋችሁት ከፍ ብዬ ጥቂት ኃይለ ቃሎችን እጠቅሳለሁ ፡፡
   - ስለ ቅንነትና ስለ የዋህነት ስለ ጽድቅም አቅና ተከናወን ንገሥም ፤ ቀኝህም በክብር ይመራሃል።
   - ኃያል ሆይ፥ ፍላጻዎችህ የተሳሉ ናቸው፥ እነርሱም በንጉሥ ጠላቶች ልብ ውስጥ ይገባሉ፥ አሕዛብም በበታችህ ይወድቃሉ።
   - አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ ለዘላለም ነው፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው።
   - ጽድቅን ወደድህ ዓመፃንም ጠላህ፤ ስለዚህ ከባልንጀሮችህ ይልቅ እግዚአብሔር አምላክ የደስታ ዘይትን ቀባህ። መዝ 45 ቁ 4- 7

   ዘላለማዊ ዙፋንን (ቁ 6) ሊወርስ የተገባው የዚህ ዓለም መድኃኒት የሆነው ፣ አንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው ፡፡ በቁጥር ስድስትና ሰባትም የተጠቀሰው ኃይለ ቃል የተነገረው ስለኢየሱስ መሆኑን የምንረዳው “ስለ ልጁ ግን። አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው። ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ” በማለት በዕብራውያን መልዕክት 1:8-9 ላይ ተጠቅሶ እናገኘዋለን ፡፡ ታድያ የሔሶብ ልጅ ትሁን ወይም ሚስት ፣ ከኢየሱስ ጋር ምን ግንኙነት ይኖራታልና ምንም ሳናፍር ንግሥቲቱ ርሷ ናት ብለን እንከራከራለን ፡፡ ይልቁንም በማሕፀኗ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ሙሉ የተሸከመች ብፅዕት እናታችን በቀኙ ብትቆም ይገባታልና ፣ እንዲህ ቢተረጎም አግባብ ይሆናል ፡፡

   3/ በሌላ ምድራዊ ትርጉም ብንመለከትም “ንግሥት የተባለችው ለጊዜው የሐሴቦን ንጉሥ ልጅ መሆኗን እንረዳለን (ቊ. 13)።”
   እንደ ደንቡ መሠረት የንጉሥ ልጅ የሚሰጣት የስም ማዕረግ ንግሥት ሳይሆን ልዕልት ነው ፡፡ ስለዚህም ደግሞ ትርጉማችሁ ስህተት ይሆናል ፡፡

   እግዚአብሔር ይርዳን

   Delete
  2. god bless you ምእመን

   Delete
  3. እግዚኣብሔር ይስጥልኝ ወገኔ። ግን በመለኮትና በአምላክ መካከል ያለውን የትርጉም ልዩነት ልረዳው አልቻልኩም። መለከ=ገዛ፥ መለኮት ገዢ ሲሆን። አምላክ =ገዥ፥ ፈጣሪ ፥ በፍጡራን ላይ ሁሉ ክብርና ኃይል ሥልጣንም ያለው ማለት ነው። ''ወመለኮትሰ አብ፥ ወልድ፥ ወመንፈስ ቅዱስ=መለኮት ግን አብ፥ ወልድ፥ መንፈስ ቅዱስም ነው። '' አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም ድርሰቱ። አዎ ሠለስቱ ስም አሐቲ ምኩናን ብለን ነው የምናምነው።

   Delete
  4. ወንድም Kebede Bogale በቅድሚያ ስለቃልህና ማብራሪያህ አመሰግናለሁ ፡፡ የእኔ መልዕክት ምላሳችን የለመደውን ቃል ብንጠቀም ለማለት ፈልጌ ነው እንጅ መልዕክትህን አልተረዳሁም በማለት አይደለም ፡፡

   ከዚህ ቀደም በዚሁ ርዕስ ላይ ምልልስ ስናደርግ ፤ ለአብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ አንድ መለኮት ብቻ ስለአላቸው በማለት ፣ ወንድም ጸጋ አባባላችንን እንድናርም አስተምረውናል ፡፡ እስከ አሁንም ድረስ በግሌ መለኮት የሌለው ልዩ አካል የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥጋና ነፍስ ተዋሃደ ለማለት በእጅጉ ያስቸግረኛል ፡፡ ምክንያቱም የመለኮትን ሥራ ወልድ በምድራዊ ሥጋና በተለየ ከመለኮት በተለየ አካሉ እንደምንና በምን ምክንያት ሊሠራው ቻለ ብዬም ራሴን ሁልጊዜ እጠይቃለሁ ? በባህር ላይ መራመድ ፤ አራት ቀን ሞቶ መሽተት የጀመረን ሬሳ ማስነሳት ፤ ከጭቃ በደረቅ ግንባር ላይ ዓይንን መፍጠር ፤ ድውያንን በቃል ትእዛዝ ብቻ መፈወስ … ብዙ ድንቅ የሆኑ ሥጋ በባህርዩ የማይሠራቸውን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈጽሟቸዋልና ፡፡ ማስረጃ ስላቀረቡ ግን ተቀብያለሁ ፡፡

   ጉዳዩን ጊዜ ካለህ በጥሞና እንድትመለከተውና ምናልባት የበለጠ ብታስተምረን በማለት ፡
   - ጉዳዩ January 2ዐ12 ፡- “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እውነትና እውነተኞች የሚገፉባት፤ ሐሰትና ሐሰተኞች የሚነግሱባት እስከ መቼ ይሆን? - - ክፍል 2” በሚል ርዕስ ነው የቀረበው ፡፡

   - የሚገኝበት አድራሻ ፡- http://www.abaselama.org/2012/01/2-pdf.html

   - ጉዳዩ በዋናነት የሚያጠነጥነው ፡- መምህር ዘሪሁን ያስተማረውን ነገረ ድኀነት ኑፋቄ ነው ለማለት ነው ፡፡ ምክንያታቸውም ድንግል ማርያም “ሥላሴን ጸነሰች” ብሏል በማለት ፡፡ እኔ በግሌ እንዲህ ያለበትን ምክንያት ወይም ትንታኔ ከዋና ምንጭ ለማጣራት አልቻልኩም ፡፡

   በጽሁፍ ከቀረበው ትምህርታቸው ጥቂት የተቆራረጡ መልዕክቶችን እዚሁ አስነብባለሁ ፡፡
   ኑፋቄ አንድ ይልና መቁጠር ይጀምራል
   ኑፋቄ መዝራት የጀመረው፣ በማዳን ሥራ ውስጥ አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ አሉ በማለት ተንደርድሮ ነው፡፡ ነገሩ ትክክል ነው ፡፡

   የሰዎች መዳን በአብ የታቀደ፣ በወልድ የተከናወነ እና በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት ለሰዎች የሚገለጥና ሰዎች አምነው የሚድኑበት ምስጢር ነው ማለት ነው፡፡ ጴጥሮስም በመልእክቱ በአብ አስቀድሞ እንደታወቅን፣ በወልድ ደም እንደ ተረጨን፣ በመንፈስ ቅዱስ እንደ ተቀደስን የሚናገረው ክፍል የሚያስረዳው ይህንኑ እውነት ነው፤ (1ጴጥ. 1፡1-2)፡፡

   ሊቃውንት ተጠንቅቀው ሲገልጹ ወልድ በድንግል ማሕጸን ያደረው በተለየ አካሉ ነው ይላሉ፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስት ናቸው፤ ወልድ ሥጋ የለበሰውም ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ልዩ በሆነው አካሉ ነው እንጂ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ በሆነበት ባሕርዩ ወይም በመለኮቱ አይደለም፡፡

   ዮሐንስ ዘእስክንድርያ፡- “በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ህልውና እንዳለ የምናውቀው መለኮት ሁለንተናው ሰው እንደሆነ፤ ሰው የሆነው ከሶስቱ አካላት አንዱ አካል እንዳይደለ በመናገራቸው ሶስቱ አካላት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሰው እንደሆኑ የሚያስቡትን … እናወግዛለን፡፡” (ሃይማኖተ አበው ገጽ 392)

   (ይበልጥ እንዲገባን ደግሞ) “ሌላውም አባት “ይቤ ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር ኢይቤ ወልድየ ዘከመ ትስብእት አላ ዘከመ መለኮት፡፡ አኮ ወልደ ማርያም በመለኮት፤ አላ ዘከመ ሥርዐተ ትስብእት፡፡”

   ትርጓሜ፡- “ይህ የምወደው ልጄ ነው አለ፤ ልጄ ያለው የትስብእት በሆነው ስርአት ሳይሆን የመለኮት በሆነው ስርአት ነው፡፡ እርሱ የማርያም ልጅ የተሰኘው የትስብእት በሆነው ስርአት ነው እንጂ በመለኮት የማርያም ልጅ አይደለም፡፡” (ሃይማኖተ አበው)

   ዮሐንስ አፈወርቅም የዕብራውያንን መልእክት በተረጎመበት ድርሳን ባሕርየ መለኮቱ ሥጋ አልሆነም ወይም መለኮት ሥጋ አለበሰም ብሏል (ድርሳን 1 ቁጥር 185)፡፡ ብንያሚ ዘእስክንድርያም “ቃል ዘኮነ ሥጋ በአካሉ ባሕቲቱ” ማለትም ቃል ሥጋ የሆነው በአካሉ ብቻ ነው (በመለኮቱ አይደለም) (ሃይማኖተ አበው ገጽ 382) ብሏል፡፡ እነዚህ የአበው ምስክርነቶች የሚያሳዩት ወልድ በተለየ አካሉ ሰው መሆኑንና መለኮት ስጋ አለመልበሱን ነው፡፡ መለኮት ነው ስጋ የለበሰው ከተባለ ግን ሥላሴ ሥጋ ለብሰዋል ወደሚል የስህተት ትምህርት ውስጥ እንገባለን፡፡ መለኮት ግን አይከፈልም፤ ሶስቱ አካላተ ሥላሴ፣ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የተወሐዱበትና በመገናዘብ አንድ አምላክ የሆኑበት ነውና፡፡ “ይሤለሱ በአካላት ወይትወሐዱ በመለኮት” (በአካል ሶስት በመለኮት አንድ ናቸው) እንዲል፡፡

   ስላሴ በማርያም ላይ ማደራቸውን “አበው ሊቃውንት ይህንን ብሥራት አስተርእዮ ማርያም ይሉታል በድንግል ማርያም ላይ የተገለጸ የሥላሴ ሦስትነት ለማለት፡፡ የመለኮት ማደሪያም እንላታለን፡፡” ሲል በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከዚህ ቀደም ተሰምቶ የማያውቅ ትምህርት አምጥቷል፡፡

   “የመለኮት ማደሪያ ማለት እንዴት ይቻላል?” የሚለውን ጥያቄ ዘሪሁን ሲመልስ
   “መለኮት አንድ ነው እግዚአብሔርነት አይከፈልም፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ድንግል ማርያም የአብ፣ የወልድ፣ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ናት ማለት ነው፡፡ በዚህን ጊዜ ታዲያ አብ መረጣት፣ ወልድ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሳ መንፈስ ቅዱስ አጸናት ማለት መሆኑን ልብ ማለት ይገባል፡፡” ብሏል፡፡

   እዚህም ላይ ቃል ሥጋ የሆነው በተለየ አካሉ ነው የሚለውን የሊቃውንት ማብራሪያ መሰረት ያላደረገና ሥላሴ ስጋ ለብሰዋል የሚያሰኝ ገለጻ ነው ያደረገው፡፡ በማለት ተንትነዋል ፡፡

   የምትለን ካለ እጠብቃለሁ ፡፡ ምን ጊዜም ለመማር ዝግጁ ነኝ ፡፡

   Delete
  5. BE LOYAL TO THE SCRIPTURE NOT TO YOUR TRADITION AND OLD STORIES. WE ARE IN THE NT ERA. THE HOLY SPIRIT TEACHES. JESUS DID NOT DIE ONLY FOR ETHIOPIANS OR EOTC BUT TO ALL IN THE WORLD. DO NOT DIE TO THE ORTHODOX TEACHINGS WHICH ARE FULL OF LIES ABOUT MARY . DO NOT TRY TO MAGNIFY HER WONGLY BUT HER SON THE ONLY REEDEMER SHOULD BE GLORIFIED. DO NOT USE HUMAN ELEMENTS TO SUPPORT YOUR CASE. DO NOT TRY TO BE SMART BY TALKING TOO MANY FANCY WORDS. WHEN IT COMES TO OUR SALVATION THERE IS ONLY JESUS WHO SAVES. I AM AN EOTC BELEIVER. I CANNOT GO BACK TO THE OLD STORY FULL OF FABRICATED LIES THAT THIS CHURCH IS TEACHING. MANY GOOD LOOKING WORDS LIKE YOURS CANNOT TAKE ME OR OTHERS WHO HAVE COME TO JESUS CHRST THE ONLY SAVIOUR. YOUR UNSAVING KNOWLEDGE REMAINS WITH YOU. BETTER BELIEVE IN JESUS AND COME TO LIFE.

   Delete
  6. ወንድም Demissew ፤ ወንድም Kebede Bogale የሚያስተምረኝን እየጠበቅሁ ሳለ መሃከላችን ገባህ ፡፡
   ወደ ቃልህ ስመለስ፡-
   - ‘BE LOYAL TO THE SCRIPTURE NOT TO YOUR TRADITION AND OLD STORIES.’
   መዝሙር 44 እስከ 45 አንብቤ መልዕክቱን እንደተረዳሁት አስተያየት እንዲሰጡበት አስቀመጥኩት እንጅ ወግና ጥንታዊ ታሪካችንን አልዘበዘብኩም ፡፡ ከጻፍኩት ውስጥ አስረጅ ጥቀስ ወይንም በተጻፈው ልክ ፣ አስተያየትና ትምህርት እንዲሆን የመጽሐፍ ኃይለ ቃል እየጠቀስክ አስነብበኝ ፡፡

   - ‘JESUS DID NOT DIE ONLY FOR ETHIOPIANS OR EOTC BUT TO ALL IN THE WORLD.’
   አሁን ደግሞ ፣ አማርኛችንን በሥርዓቱ የምትረዳ አልመሰለኝም ፡፡ ኢየሱስ ለኢትዮጵያውያኖች ብቻ ወይም ለኤኦተቤ ሞተላት የሚል ቃል አልጻፍንም ፡፡ የሌለ ነገር ያነበብክ መሰለኝ ፡፡

   - ‘DO NOT DIE TO THE ORTHODOX TEACHINGS WHICH ARE FULL OF LIES ABOUT MARY .’
   እዚህ ጋር የመስመር ልዩነታችንን በግልጽ አወጣኸው ፡፡ በበኩሌ ሃይማኖቴን እስከ መጨረሻው ድረስ እቆምላታለሁ ፡፡ በምንም መጤ ዘመናዊ ትምህርት አልቀይራትም ፡፡ ሃይማኖት የሳይንስ ግኝት አይደለችም ፡፡ ከመጀመሪያው አንስታ አንድ ናትና አንለውጣትም ፤ አታረጅምም ፡፡

   - ‘TO MAGNIFY HER WONGLY BUT HER SON THE ONLY REEDEMER SHOULD BE GLORIFIED.’
   የሚገባትንም ያህል እንኳን አላከበርኳትም ፤ እንኳንስ ስለ እኛ ሲል በመስቀል ላይ ከሞተልን ፣ ከልጅዋ ላስበልጣት ወይም ላስተካክላት ፡፡ አሁንም ጽሁፉን የመገንዘብ ችግር ያለ መስሎኛል ፡፡

   እንዲያውም “ቅድስት ድንግል ማርያም ፣ አምላኳንና አምላካችንን ፣ የዚህን ዓለም ፈጣሪ የሆነውን ጌታዋንና ጌታችንን ወልዳዋለች” በማለት ደጋግመህ በልና ምን እንደሚሰማህ ጻፍልኝ ፡፡

   - ‘DO NOT TRY TO BE SMART BY TALKING TOO MANY FANCY WORDS.’
   እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አሳምሮት ቢሆን እንጅ ፣ የምጽፈውን ላሳምር ብዬ ተነስቼም ፣ ተጨንቄም አላውቅ ፡፡ በመጣልኝ ነው የምደናበረው ፡፡ መንፈስ ቅዱስ የምትመልሱትን ይሰጣችኋል ብሏልና ፣ አልፈልግም አትስጠኝ ለማለትና ለማመጽ ግን እፈራለሁ ፡፡

   - ‘WHEN IT COMES TO OUR SALVATION THERE IS ONLY JESUS WHO SAVES.’
   ለዚህ መግለጫህ ጌታ ይባርክህ ፡፡ ከዚህ ቃል ውጭ እኔም አልልም ፡፡

   - ‘I AM AN EOTC BELEIVER.’
   ትንሽ አብራራው እንጅ ፤ ይህች ከላይኛዋ አዋጅህ ተጣላችብኝ “ DO NOT DIE TO THE ORTHODOX TEACHINGS WHICH ARE FULL OF LIES ABOUT MARY .” ፡፡ ውሽትን ከምታስተምር ቤተ ክርስቲያን እንደምን አባል ሆንክ ወይንስ ዋሸኸኝ ?

   - ‘I CANNOT GO BACK TO THE OLD STORY FULL OF FABRICATED LIES THAT THIS CHURCH IS TEACHING.’
   አየህ ጽናት የሌለህ ሰው መሆንህን ፡፡ ሥንዝር ሳትራመድ ያዋጅ ቃልህን አፈረስከው ፡፡ ይኸን ሲያዩት ዋሽተህ ነበር ያሰኛል ፡፡

   - ‘MANY GOOD LOOKING WORDS LIKE YOURS CANNOT TAKE ME OR OTHERS WHO HAVE COME TO JESUS CHRST THE ONLY SAVIOUR.’
   እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ፈቃዱ ከሆነ ፣ በሚያደርገው ሁሉ አትጠራጠር ፡፡ እንኳንስ አንተን እንዲህ የወንጌል ቃልን ማንበብ የጀመርከውን ፣ ጫካ ውስጥ በሌላ ባዕድ አምልኮ ያለውን እንኳን ይለውጠዋል ፡፡ ቅንጣት ያህል አልጠራጠርም ፡፡

   - ‘YOUR UNSAVING KNOWLEDGE REMAINS WITH YOU.’
   የምናመልከውን ባትነቅፉ ቃል አይወጣኝም ነበር ፡፡ በኢትዮጵያውያኖች መሃከል ያለው ትልቅ ችግር ፣ ወንጌልን ለይቶ ከማስተማር ይልቅ የሌላውን ትምህርት በመተቸት ለማንቋሸሽ ስለምንሰማራ ተጠላልፈን ሁላችንም ከጉድባ እናርፋለን ፡፡ ይኸ በተለይ በተለይ የአገራችን ሊቃውንት መሰል መምህሮች ድክመት ነው ፡፡

   በጎደለው አሁንም እግዚአብሔር ይሙላበት !!! አሜን

   Delete
 2. የሙሽራዉ ሚስት የተባለችዉ ሙሽራዋ ቤተክርስቲያንማ በዪሃንስ እራዕይ ላይ አጊጣና ደምቃ ከሰማይ ስትወርድ አየሁ እያለና ስፋቷን የተገነባችበትን የማእድን አይነት እየዘረዘረ የተናገረላትና በመጨረሻም ከንግዲህ ወዲህ በዉስጧ ጨለማ አይኖርም በጉ በመካከሏ ስላለ እርሱ ያበራላታል የተባለላት ናት ስለዚህ ንጉስ ክርስቶስ ሙሽራ በተባለት ቤተክርስቲያን አድሮ መኖሩን እንጂ በወርቅ ልብስ ተከናንባና ተሸፋፍና በቀኝ እንደምትቆም አልተነገረንም፡፡ መቸም ጥንተ ጠላት ዲያቢሎስ የአዳም ተስፋ ስለሆነትና ድህነታችንም ከእርሷ ማህጸን ስለጀመረ በድንግል ማሪያም ላይ የማይከፍተዉ ጦርነት ስለሌለ እንዲሁ በዉስጣችሁ አድሮ ይቃወማል እንጂ ማርያምስ በቀኝ የቆመች ንግስት ናት የጌታ እናት ንግስት ያልተባለት ማን ሊባል ነዉ? ፡፡ልብ ይስጥህ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይህማ ሲባል የኖረ ነው ድንግል ማርያም በቀኝ የቆመች ንግሥት መሆኗን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ ግን አትችልም፡፡ ስለዚህ የቀረበውን ሐሳብ በተሻለ ሐሳብ ማፍረስ ሲገባህ ቀጥታ ወደ ስድብ ነው የዞርከው፡፡ ይህ የብዙዎች ችግር ነው ሐሳብን በሐሳብ ማፍረስ ሲያቅት ወደስድብ ለምን እንሄዳለን? አሁን ማስረዳት ያለብን ድንግል ማርያም ንግስት መሆኗን ነው እንጂ ሌላ ጉዳይ መሆን የለበትም፡፡

   Delete
  2. አዳምም ለሚስቱ ሔዋን ብሎ ስም አወጣ፥ የሕያዋን ሁሉ እናት ናትና።
   ኦሪት ዘፍትረት ምዕራፍ 3፡20
   የሕያዋን ሁሉ እናት እንደሆነች ማርያምን ትክዳለህ አሁን;;;;; እግዚአብሔር አባትበና እናትህን አክብር ላል አንተ ግን የሔያዋን እናት የሆነችውን ሄዋንን ብሎም የአምላክ እናት የሆነችውን ማርምን የዘንዶው አፍ ተከፈተ እንደተባለ ትሳደባለህ፡፡ የምታደርገውን አታውቅምና መድህነዓለም ይቕር በልሕ፡፡ እናትህንና አባትክን የምታከብርበት ቀን ይስጥህን፡፡ሉቃስ 1፤46 ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል ብላ እራሱዋ መዝ 44ን ደግማለች፡፡ ለትውልድሁሉ ስሜን ያሳስባሉ ይሐው ነው፡፡

   Delete
  3. EGZIABHER yibarkh

   Delete
  4. ebakachihu tiqsun yalebotaw atitiqesut. Begimitim atinageru yekristian amlak yiferdal. Kalgebachihu zim belu beminalbat atawru. Maninim begulbet masamen ayichalim. Mesqel lay yewotawin bicha sibekut.

   Delete
 3. ክርስቶስ ራሱ ከሴቶች ሁሉ መርጦ ፥ ከሥጋዋ ሥጋውን ከነብሷ ነብስን ነስቶ ፥ ወላዲተ መለኮት የሆነችውን ቅድስት ድንልግል ማርያምን ከአምልኮት በስተቀር የተፈለገውን ሁሉ ምሳሌ በመስጠት ብናከብራት ምንድነው ችግሩ ? ሊቃውንት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ለእውነተኛዋ ንግሥት ይህን ጥቅስ አዎ ለርሷ ሠጥተዋታል ! እኛም እናንተም ብትቃወሙ አንተወውም! ቅዳሴዋን የደረሰው አባ ሕርያቆስ በብዙ ምሳሌ ቀድሷታል። ይህንስ ምን ልትሉ ነው ? ..''የንጉሥ ሚስቱ እንጅ እናቱ ንግሥት አትባልም'' ብላችኋል። የታላቁ ንጉሥ የቆስጠንጢኖስ እናት በታሪክ መጻሕፍት ''ንግሥተ እሌኒ '' አትባልም እንዴ ? እስቲ ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ ስጡኝ። ከአክብሮት ጋር ።

  ReplyDelete
 4. ጌታ ይባርካችሁ! አሁን ገና ትክክለኛ ማንነታችሁን ወደ ሚያሳየው ትምህርት ተመለሳችሁ። የእናንተ ነገር ግራ አጋብቶኝ ነበር። አሁን የቀራችሁ ከላይ ያሉትን ፎቶዎች ማንሳት ብቻ ነው፤ ምናልባት ከአንዱ በስተቀር። ክርስቶስ ጌታ ነው! አ..ሜ..ን!!!

  ReplyDelete
 5. የዮሐንስ ራእይ
  13፥6 እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ።
  የመለኮትን ማደሪያ ለመሳደብ አፋችሁ ተከፈተ ለምን ይሆን?? በእውነት እናንተ እንደምትሉት ቅድስት ድንግል ማርያም ከምድራዊ ንጉስ ሚስት ታንስ ይሆን?? ወርቅ ለበሰች ስለተባለ ለምን ነደዳችሁ? መለኮት እኮ ይህንን ያህላላ ይመስላል ሊባል አይቻልም። እርሱ በሷ ማህጸን አደረ። በቀኝ መቀመጥ እኮ ምንም አይደለም ፣ ማደሪያ መሆን ይበልጣል ማስተዋል ለተሰጠው። ወገኞቼ ማስተዋልን ይስጣችሁ፣ በናንተ ያደረው መንፈስ ለምን እርሷን እንድትጠሉ አደረጋችሁ? ለሚለው ጥያቄ
  መልሱ የዮሐንስ ራእይ ግልጽ አድርጎ አስቀምጦታል። መለኮት የተዋሃደው ስጋ እኮ የማርያምን ነው፡ ከሰማይ ይዞት አልወረደም ዛሬ እኛ በልተን ጠጥተን ህይወትን የምናገኝበት፡ ቤተክርስትያንን በደሙ የመሰረተበት። በዚህ ደግሞ ልንደሰት ልንኮራባት ይገባል እንጂ ጭራሽ ልንሳደብ አይገባም።
  ልቦና ይስጣችሁ።

  ReplyDelete
 6. I completely disagree, I do not belive the wrong interpretation of Pslam 44/45 9-10 , becuase even if you siad it means" the church" the church itself has three main parts the main part of the church is called Mekedes accoding our EOTC, that Mekedes is an example of vergine Mary the mother of jesus. there is no dout we are calling her the queen and we will call her the queen even more than that. please do not misleading the our forfathers interpretation.

  Mengesha
  from london

  ReplyDelete
  Replies
  1. አናኒመስ በጣም ተሳስተሃል ቤተክርስቲያን የክርስቲያኖች ኅብረት እንጂ ሕንጻ አይደለም፡፡ ህንጻው በልማድ ቤተክርስቲያን ይባላል እንጂ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት የለውም፡፡ ህንጻው ጸሎት ቤት ነው፡፡ ስለዚህ ንግስት መባል የሚገባው የክርስቶስ ሙሽራ የሆነች ለቤተክርስታን እንጂ ለድንግል ማርያም በተናጠል ወይም የጌታ እናት በመሆኗ አይደለም፡፡ ስለዚህ በመጀመሪያ በዚህ ጉዳይ ላይ ከመከራከርህ በፊት ቤተክርስቲያን የምእመናን ኅብረት ወይም ጉቤ እንጂ ህንጻ አለመሆኑን ተረዳ፡፡

   Delete
 7. heloo Abaselamawyan minew yehan yakil silemebetachin memesker asaferachihu kesetoch hulu teleyetesh yetebareksh nesh, tebelalech getam eko esuan meretoat beswa laye adere mine tihonalachihu enkuan getan yewoledechinlen kerto midrawy enatim eku tikeberalech. Silemebetachin dingel maryam sinesa yemikefaw yediyabelos wodaje bech new amlak libona setote kibruan lememesker yabkaw AMEN.

  ReplyDelete
 8. አሜን ልቦና ይስጣችሁ!!

  ReplyDelete
 9. የተጻፈውን ዋና ነገር ትታችሁ ማርያምን በተጻፈላትና በተነገረላት ቃል ሳይሆን ባልተጻፈላትና ባልተነገረላት ቃል በአክብሮት ስም እናምልካት የምትሉ ሁሉ ምናለ ከሁሉ በፊት የተጻፈውን ጽሁፍ በጥሞና ብታዩት? በእኔ እምነት በዚህ ጽሑፍ የድንግል ማርያም ትክክለኛ ማንነት ተገለጠ እንጂ ክብሯ አልተቀነሰም፡፡ ምናልባት የተቀነሰው አለአግባብ ተጥቷት እስከ መመለክ ያደረሳት ሐሰተኛ ክብር ነው፡፡ ለድንግል ማርያም ያልተነገሩና ለእርሷ አለአግባብ የተሰጡ ብዙ ጥቅሶች አሉን፡፡ እነዚያን ማረምና ለተነገረበት ዐውድ መጠቀም እንጂ ኣ ለምንፈልገው ዐላማ ስንል ብቻ የእግዚአብሔርን ቃል ማጣመም የመጽሐፍ ቅዱስ ደራሲ የሆነውን መንፈስ ቅዱስን ያሳዝናል፡፡ ጽሑፉ አሳማኝ በመሆኑ ልንቀበው ይገባል እንጂ በጽሑፉ ፈጽሞ ያልተነሡ ሌሎች ጉዳዮችን በማንሣት ነገሩን ወደ ሌላ አቅጣጫ መምራት ተገቢ አይደለም፡፡ ብዙዎቻችን የሰጠናቸው ኮሜንቶች ከጽሑፉ ጋር ምንም የማይገናኙና ድንግል ማርያምን በተመለከተ በሌላ ርእስ ልንነጋገርባቸው የሚገቡ ናቸው፡፡ ስለዚህ እባካችሁ ከመቃወማችን ወይም ከመደገፋችን በፊት ቆም ብለን እናስብ፡፡

  ReplyDelete
 10. @anonymos jan 1,2012 11:10 PM Esu yante emnet new yegna aydelem. yante tikikil yemihonew lante bicha new yegna ewunet endangeshegesheh hulu yante wushet degmo yangeshegshal. geta ewunetun yigletselih.

  ReplyDelete
 11. ጠረ ማርያም! እመቤቴ ልብ ትስጥህ! ልጇ ይቅር ይበልህ!

  ReplyDelete