Tuesday, December 4, 2012

ይድረስ ለጾመኛው ዳንኤል ክብረት

«ስትጦሙም፥ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን ስትጦም፥ በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ ፊትህንም ታጠብ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።» (ማቴ. 6፥16-18)

ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነኝ ዳንኤል ክብረት በድረገጹ ላይ “ወርቅ የማይገዛው አገልግሎት” በሚል ርእስ Monday, November 26, 2012 በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የጻፈው ትችት ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ ዝናን ያተረፈ አየር መንገድ መሆኑ ለማንኛችንም ግልጽ ነው። ከፍተኛ ዝናን ማትረፍ የቻለውም በሚሰጠው አገልግሎት ነው እንጂ በሌላ አይደለም። እንዲህ ሲባል አየር መንገዱ ፍጹም ነው አንዳችም እንከን የለበትም ለማለት ፈልጌ አይደለም። ፍጹም ሊሆን አይችልምና፡፡ ከችግሮቹ ይልቅ ስኬቶቹ ስለበለጡ ግን አየር መንገዱ በብዙዎች ዘንድ ተመራጭ፣ ዝነኛ፣ አትራፊ፣ ስኬታማና ተሸላሚ ሆኖ ቀጥሏል። የዚህ ጽሑፍ ዋና ትኩረት በቀጥታ አየር መንገዱ አይደለም። ዳንኤል ክብረት በአየር መንገዱ ላይ ያቀረበውና “ጾመኛ ነኝ እወቁልኝ” አይነት በእኔ እምነት በግብዝነት የተሞላ አስተያየቱ ነው።

ዳንኤል ወደ ውጭ ለመሄድ ቲኬት ሲቆርጥ ጀምሮ የጾም ምግብ አዝዞ እንደነበር፣ ከባለቤቱ ጋር ወደኤርፖርት ከገባና ተፈትሸው ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ መስኮት ከደረሱና ትኬታቸውን በማሳየት ሻንጣዎቻቸውን ካስረከቡ በኋላም በመስኮቱ ጀርባ ለምታገለግለው የአየር መንገዱ ባለሞያ ወቅቱ የገና ጾም ወቅት ስለሆነ የጾም ምግብ ማስመዝገባቸውን ገልጸውላት እንደነበር፣ አውሮፕላኑ ከተነሳ በኋላም የበረራ አስተናጋጆቹ ምግብ እያደሉ ወደእነርሱ ሲደርሱም ‹የጾም ምግብ አዝዘን ነበር› ማለቱን ሳያፍር በኩራት ጽፎአል፡፡ በመጨረሻም ያዘዘው የጾም ምግብ ሳይመጣለት እንደቀረና ለባለቤቱ እንደምንም ተፈልጎ እንደተገኘላት እርሱ ግን እየሞረሞረው መጓዙን ጽፎአል፡፡

ጥፋተኛው ወይም ተጠያቂው ማነው? የሚለውን ለመመለስ በተለይ ከአየር መንገዱ ማረጋገጫ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን ዳንኤል በሰጠን መረጃ መሰረት አስተናጋጆቹ በእነዳንኤል ቁጥርና ስም የተመዘገበ የጾም ምግብ እንደሌለ ገልጠውለታል፡፡ መቼም ባያስመዘግብ ነው እንጂ የተከበረውና ዝነኛው አየር መንገዳችን ደንበኛውን ሆነ ብሎ ሊጎዳ ይህን እንደማያደርግ ግልጽ ይመስለኛል፡፡ በመልሱ ጉዞ ላይ አየር መንገዱ ይቅርታ ጠይቆኛል ቢልም፣ በሁሉም በኩል ጥፋቱ የዳንኤል ነው ብሎ መደምደም ሳይቻል አይቀርም፡፡

በመጀመሪያ የጾም ምግብ ይዘጋጅልን ማለቱ ከሃይማኖቱ አንጻር መብቱ ቢሆንም እንኳን ከዚያ በኋላ ስለጾም ምግብ ከአንዴም ሁለቴ በየደረሰበት ሁሉ “የጾም ምግቤ እንዳይረሳ” የሚል ተደጋጋሚ መለከት መንፋቱና ማስነፋቱ ሰውዬው ጿሚ ነው ወይስ ጾመኛ ነኝ እወቁልኝ በሚል ሰበብ ለሆዱ የቆመ በላተኛ ነው? እንድል አስገድዶኛል፡፡ ዳንኤልን ማንም እንደሚያውቀው ማኅበረ ቅዱሳን ነው፡፡ ማህበሩ ደግሞ በዚህ አይነቱ የግብዝነት ስራ የተጨበጨበለት የፈሪሳውያን ጥርቅም ነው፡፡ የጾምን ምንነት ያልተረዳ፣ በምግብ አይነት ላይ እንጂ ጾም በሚጠይቀው ግዳጅ ላይ የማያተኩር፣ መጾሙን ትቶ ሰዎች በሉ አልበሉም ብሎ የሚጠባበቅ፣ የልማድ ጾም ሰለባ የሆነ የልማድ ጿሚዎች ጥርቅም ነው፡፡ ከእነዚህ መካከልም አንጋፋው ዳንኤል ይጠቀሳል፡፡

የዚሁ ማህበር ስርዓት ውጤት የሆነው ዳንኤል ጾመኛ ነኝ እያለ ስለጾም ሳይሆን ስለመብል እንዲህ መወትወቱ በማህበረ ቅዱሳን መንደር ጾም ምን ማለት እንደሆነ ፍንትው አድርጎ አሳይቶናል፡፡ ዳንኤል ሌላው ቢቀር እንኳ «አድልዉ ለጾም» የሚለውን አስታራቂ ቃል ወዴት ጥለህ ነው «አድልዉ ለሆድን» የያዝከው?

ከአንተ ጽሁፍ እንደተረዳሁት ጾም የምግብ ለውጥ ከመሆን ያላለፈ ልማድ ሆኗል፡፡ ምክንያቱም ሰው የሚጾመው ሁሉን ነገር ትቶ ወደፈጣሪው በልዩ ሁኔታ ለመቅረብና ለመጸለይ ነው፡፡ አንተ ግን በጾምህ ወቅት ምግብ ተከለከልሁ ብለህ አየር መንገዳችንን ከሰስክ፡፡ «እነሆ፥ ለጥልና ለክርክር ትጾማላችሁ ድምፃችሁንም ወደ ላይ ታሰሙ ዘንድ … አትጾሙም።» የሚለው ቃል አልተፈጸመብህም? (ኢሳ. 58፥4)፡፡ አንተ ጾም ስትል የጠራኸው ጾምህ እኮ የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል የጾምን መስፈርት አላሟላም፡፡ እንዲያውም ጾምን የሚጻረር ተግባር ሆኖ ነው ያገኘሁት፡፡ ሲጀመር አላማህ መጾም ከሆነ ዝም ብለህ መጾም እንጂ ስለምግብ ማሰብ ከቶ አልነበረብህም፡፡ አላማህ ግን ልማዴን እወቁልኝ ከማለት የዘለለ አልነበረም፡፡ ስለዚህ ድርጊትህ «በሳምንት ሁለት ቀን እጾማለሁ» ካለው ግብዝ ፈሪሳዊ ድርጊት በምን ተለየ? ደግሞስ ጠይቀህ እንኳን ባያዘጋጁልህ እንደእውነተኛ ጿሚ አንድ ቀን ብትቆይ ምን ትሆናለህ? አንተ ግን ጾሜን ዋልኩ ብለህ «ገድልህን» አወራህ፡፡ ዳኒ መብል ለሆድ ነው ሆድም ለመብል ነው ሁለቱንም ጌታ ያጠፋቸዋል፡፡

ከሁሉ የሚገርመው ደግሞ ከአቡነ ቴዎፍሎስ ጊዜ ጀምሮ መታሰቢያነቱ እንዳይጠፋ የመጨረሻው ሳምንት ብቻ ይጾም እንጂ የገናና የሰኔ ጾም ሙሉ በሙሉ እንዳይጾምና በተለይም እንዳንተ ያለ መንገደኛ ለመጾም እንደማይገደድ ተጠቅሶ እያለ፣ ሐሳብ ቀርቦበትም ለእስራ ምእት በተዘጋጀው መጽሐፍ ላይ ያ የቀድሞው የውሳኔ ሐሳብ ታትሞ እያለ በገና ጾም ላይ «ማካበድህ» አላማህ ቤተክርስቲያኗ ያቀረበችውን ማሻሻያ ለመቀበል አለመፍቀድህን ያሳያል፡፡ ለነገሩ የአንተ ማህበር ሰዎች ጎጃም ውስጥ አንድ ስፍራ ላይ ቤተክርስቲያኗ ያሳተመችውን ይህን የእስራ ምእቱን መጽሐፍ የተሐድሶዎች ነውና እንዳትገዙት እንዳታነቡት እያሉ ሲያከላክሉ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡   
    
ይህን አየር መንገድ በግድ አወጀብን ያልከውን በጾም መዋል አንተና ወዳጆችህ (ያው የማህበርህ ሰዎች ናቸው) «ስምንተኛው ጾም» ብላችሁታል፡፡ ዳኒ ስምነተኛውማ ሁሉን አውቃለሁ ባዩ የአንተ ማህበር ያለቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ያወጀው የጽጌ ጾም ነው እኮ? እኔና ወዳጆቼ ደግሞ «የጽጌ ጾምን ልዩ የሚያደርገው ጠዋት እየተቀደሰ የሚጾም ጾም መሆኑ ነው፡፡» ብለን «ሙድ ይዘንበታል»፡፡ ስለዚህ ረስተኸው ይሆናልና ይህን አንተና ጓደኞችህ «ከአዲስ አበባ እስከ ቀጣዩ የበረራ መዳረሻ የሚጾም ጾም» ብላችሁ «ስምንተኛ» የሚል የሰጣችሁትን ስያሜ ብታስተካክለውና «ዘጠነኛው ጾም» ብትለው ሳይሻል አይቀርም፡፡

ዳኒ ሐሳቤን ላጠቃል። መቼም ጾም በመጽሐፍ ቅዱስ የታዘዘና ልንፈጽመው የሚገባ ምግባር ነው፡፡ በልማድ የምንፈጽመው ባለመሆኑም ጌታችን ስለጾም የሰጠንን መመሪያ ተከትለን መጾም ይገባናል፡፡ እርሱ የሚልህ «አንተ ግን ስትጦም፥ በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ ፊትህንም ታጠብ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።» ነው፡፡ ይህማ ስለግል ጾም የተነገረ ነው ብለህ እንደማትሞግተኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ስራህን በዚህ ጥቅስ ስትመዝነው ራስህን እንዴት ታየዋለህ? በእኔ እምነት ግብዝ ሆነሃል፡፡ ከጌታ አንዳች አታገኝም፤ ዋጋህን ከሰው እንኳን እንዳታገኝ በሰው ፊትም ስለመብልህ እንጂ ስለጾም አላወራህምና ከሁለት የወደቀ ሆነሃል፡፡ ዳኒ በእውነት ምስኪን ነህ፡፡ ምንም መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ሐሳብ ለመቀበል ዝግጁ ባትሆንም እግዚአብሔር እውነተኛውን የጾም መንገድ እንዲያሳይህ ግን እመኛለሁ፡፡

                                                          አየለ
ከአዲስ አበባ

53 comments:

 1. lol, I think you don't have something that is important to write...

  I just lough because I also read the article and see how you are hateful and try to spread false accusation.

  Hey guys, watch out your values in life. You are just wasting your time with unnecessary things.

  ReplyDelete
  Replies
  1. You lough because, you don't have value for what the bible said and teach us. can you tell us what kind of value you have? who is wasting time? you or us? we are gaining in this website not wasting.

   Delete
  2. At the time when they post, it says Tesfa, when I see in other days it is changed to Ayele. Ayyyyy aba selama. This Tesfa & Ayele are lib woleds.


   Eski diferu, like Daniel create a blog by ur own name if u r working on truth.

   Delete
 2. Dear Ayele do you really belive in what you write or it is just for the sake of MEKAWEM.

  Are you orthodox tewahedo or protestant follower of Luther?????If you are Orthodox what you wrote should not even come to your mined because it is our church teaches us about all those 7 yeawaje tsome.
  Medhamialem Eyesus christos ayenehen yaberaleh

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ayele has the right to criticize, any article special related to his religion, our religion didn't tell has to blame others for not getting the right food.

   Delete
 3. ባለፈው ሳምንት ከአዲስ አበባ ወደ ጆሃንስበርግ በሚሄደው ኢትዮጵያ አየር መንገድ የደረሰብኝን መጉላላት ዘርዝሬ በዚህ ጦማር ላይ ጽፌ ነበር፡፡ ያንን ሳደርግ ዋናው ዓላማዬ የኢትዮጵያ አንዱ መለያ የሆነው አየር መንገዳችን እንዲሻሻል በማሰብ ነው፡፡ ‹ጠላት ያማል ወዳጅ ይወቅሳል› እንዲሉ፡፡ ታላቁን መርከብ የአንዲት ብሎን መውለቅ ለአደጋ እንደሚ ዳርገው ሁሉ እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ያሉ ታላላቅ ተቋማትንም በየአካባቢው የሚፈጠሩ ትናንሽ የሚመስሉ ስሕተቶች ዋጋ ያስከፍሏቸዋል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. I don't get you, you mean ETA made a mistake not giving yes some megebe for this person paid a price? I don't think you have a sense of mind. look, how many hours he traveled may be less than 5 hours, he could fast for more than that by not eating he could eat different kind of non fatty foods, like bread and drink water or soda. I eat what ever , God give it to me to but I still Orthodox. the bible didn't told me to that I should eat certain food to go to the kingdom, I already have a visa to go to the kingdom by the blood of Jesus.

   Delete
  2. "tininish negeroch le tininish sewoch tililik nachew"
   (Ayele)

   Delete
 4. ጣፊው አቶ ? አየለ የተቆረቆሩት የመንግሥትዎ ንብረት ለሆነው አየር መንገድ እንጅ ለክርስትናው አይመስለኝም። አዎ በሰማያዊው መንግሥት ስም ለምድራዊው መንግሥታችሁ ተቋማት ጥብቅና ለመቆም በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ተሰግስጋችሁ ኢትዮጵያውያንን እንደምታጠቁ ካወቅን ዓመታት አለፉ እኮ ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Kebede: close your big mouth. what are you doing in this web site go to Dejeselam and read tert tert--

   Delete
 5. LMIGEBAWE Dneqe TEHUFE NEW

  ReplyDelete
 6. ምነው ወንድማችን ዳንኤል ትችቱ በሆድ የተነሳ ሆነ። መጾምህ መልካም ነው ግን ለታይታ አደረከው። ከንቱ ውዳስን በገዛ የሀገርህ አየር መንገድ ላይ አደረከው አያምርም። ምክንያቱም የጾም ምግብ እንኳን ባይኖራቸው ብያንስ ሰላጣና ትማትም ቃርያ አያጡም እርግጠኛ ነኝ። አንተ የፈለከው የጾም ምግብ ግን ለየት ያለ ብዙ በየአይነቱ ሆኖ ከሆነ አልገባኝም። ወንድማችን ዳንኤል ብያንስ እንደማውቅህ የሆድ ህመምተኛ እንደሆነክ ትንሽ ግንዛበ አለኝ ስለማውቅህ። ነገር ግን የጾም ምግብ ኦሮደር አድርገ ከለከሉኝ ማለት እውነት አይመስለኝም ከአንድም መምህር ተብሎ ከሚጠራው ሰው የምጠበቅ አይመስለኝም። ወንድማችን የጻፈውም የምንጽመፈውና የምንናገረውን ነገር ማስተዋል እዳለብን ፈልጎ ስለሆነ አመስግነዋለሁ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንድታረም ብታስብ ኖሮ በድህረ ገጽህ ላይ ባለወጣህ ነብር። ገበያ ያጣል ብለህ ከፖለትካ ጋር ለማያያዝ ሞክረ ከሆነ እራስን በቃሌ እግዚአብሔር መርምሪ። አየር መንገዳችን አገልግሎቱ ከጀመረ ከአንተ እድሜ በላይ ሆኖታል። በጾም ምግብ የተነሳ አየር መንገዱን መተቸትህ ስህተት ነው። ብያንስ vegetarian የሆኑ መንገደኞች እንዳሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጠንቆቆ ያውቃል ስለዚህ ምግቡ order ባይደረግም ሁሉ ግዜ አላቸው። ስለዚህ የጾም ምግብ አንተም ባታዛቸው እነርሱ አላቸው።ያቀረብከው ወቀሳ ከእውነት ያራቀ ስለሆነ አንጋፋውን የኢትዮጵያን አየር መንገድ ይቅርታ ብትጠይቃቸው ያስመሰግንሃል እንጅ አላዋቅ አያደርግህም።አንድ ሰው ሁለት ሰው መሆን አይችልም። መንፈሳዊም አለማዊም መሆን አይቻልምና እራስህን መርምር:::::::::::::::ኢትዮ አየር መንገድ የከበረ ነው.........

  ReplyDelete
  Replies
  1. @Anon 10:12
   አንተ እንኳን በአውሮፕላን ወደ ውጪ በሎንቺንም ወደ ከተማ አልገባህም። እውነትም አየለ። ጥሩ የጴንጤ ድፍረት አለህ፦ ስለማታውቀው ነገር ማውራት እንደደራሲው። ይህ ደሞ በሽታ ነው።

   Delete
  2. I agree with u, he is not fasting from his daily bad conducts. I don't think, this person know God.

   Delete
  3. You just missed the point of the blog post of Daniel. Any organization (including Ethiopian Airlines and/or Lufthansa) should respect their customers' needs. Mistakes as small as this, may cost the company seriously in the long run. This is a very constructive criticism which the Airliner took positively. Nothing religious about the post. It is just his opinion as a human being.

   Delete
 7. orthodox church has its own set fastings. If u are a follower u r expected to do that like Dani the great

  ReplyDelete
 8. what do u say with the fastings of Nenewe people, who fast all?

  ReplyDelete
 9. ለመሆኑ አንተ ክርስቲያን ነኝ ነዉ የምትለዉ እሽ ጾምን ማወጅ ቅዱስ ቃሉ ይከለክላል እንዴት ሰዉ ጾመኛ ነኝ ይላል አልክ፤ ልክ አንተ እንዳደረከዉስ ቅዱስ ቃሉ በሰዉ ላይ ፍረዱ ይላል? አንተን ማን ፈራጅ አደረገህ የዳንኤል ጾም ጌታ የማይቀበለዉ እንደሆነ ስትናገር ያንተ ትክክል እንደሆነስ ስታወራ አንተ እራስህ ግብዝ የሆንክ አልመሰለህም? ለመሆኑ እራስህን ጻድቅ አድርገህ ነዉ የምትቆጥረዉ? ከሆነም ጻድቃን አለምን ካሸነፉበት መሳሪያ አንዱ ጾም ነዉ አንተ ደግሞ አብዝቶ መጾምን ትቃወማለህ ታዲያ እራስህን ማን ትላለህ? ፡፡ ደግሞም ሃዋርያዉ ጳዉሎስ አብዝቶ እንደሚጾምና ወንጌልን ለመስበክ እንዴት እንደተንገላታ ጽፏል ታዲያ ባንተ መስፈርት(እራስህብ ፈራጅ ስላደረክ) ይህ ሃዋሪያ ግብዝ ነዉ እና አይጸድቅም ትል ይሆን? እስኪ መልስልኝ ፈራጁ!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. TEBAREK !!!!! Biruk hun !!!!!

   Delete
 10. hi dani, you are 100% Sega nehe.

  ReplyDelete
 11. To tell you the truth you are not protesting MK or Dn Dani, you are protesting the church. I have seen what daniel has written. Your view and interpretation is so much far from what he wanted to say. I can say you have evil mind. Please try to cleanse such a mind.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thank you very much Ayele, They dont understand what they believe. Any way your article is wonderful and teching Christianity.
   God Bless you More......

   Delete
 12. እጅግ፣ እጅግ በጣም መሳጭ እና አስተማሪ ገንቢም ጽሑፍ ነው፡፡ እጅ ይባረክ ያሰኛል፡፡ ወንድሜ አየለ ተዛማጅ ጽሑፎችን ሌላም ጊዜ እንዲህ አድርገህ ብትጽፍ ለሁሉም ወገን የሚጠቅም ይሆናል፡፡ አንተ ያተትከውን የዳንኤል እይታዎች ከሚለው ከራሱ ከዳንኤል ብሎግ አይቼዋለሁ፡፡ አንተ ግን በይበልጥ ተረድተኸዋል፡፡ ምሥጋናዬ ይድረስህ፡፡ ቃለ ሕይወትን ያሰማልን፡፡
  ያንተው አናኒመስ!!

  ReplyDelete
 13. Dear Abaselama, This is really great articulate that to inform the nature of Fersawiyan in the public. Daniel kissret in the first place not preach in Jesus except tert such like Gojam debtera. He is extermely hypacrite fersawe. Ethiopian air lines has the back bone of Ethiopian economy that providing a lot amount of money to reduce povierty in the land of Ethiopia. Daniel Feresawi kibret he just againest this bussiness similar to fundementalist opposition. Daniel never been fastinig. He has living with cheating, killing and eating and fuck..... .Death to mk . Long live for true writer aba selama.

  ReplyDelete
 14. ወይስ ጾመኛ ነኝ እወቁልኝ በሚል ሰበብ ለሆዱ የቆመ በላተኛ ነው? yes, he is hodame. Hodachew amelakachew yemelew le MK new. we only close to God by broken heart not by changing the types of food to eat. The bible told us about "fersawyne" the current fersawyne in our church is MK.

  ReplyDelete
 15. Aba Selamawech menalebet Egziabher Tsegama Bereket Yesetachewn astemarewochena Himanotachennen Behone Balholne neger Batanesut. Menew Lela Sera Betefelegu Endiaw YeEthiopian Hizbe Yemtawnabedu Ebed Yemeselacheh.(Ygele Ena Yemahber Tselote Enkuan atartachehu Yematweku Brain washers).

  ReplyDelete
 16. አቶ አየለ ከመጻፋቸው በፊት የዲያቆን ዳንኤል ክብረትን ጽሁፍ አንብቤው ስለነበር ፤ ጸሃፊው አንድን ነገር ባቀደለትና በሚፈልገው ዓላማ ሳይሆን በተለያየና አንባቢ በፈቀደው መልክ እንደሚረዳው ተገንዝቤአለሁ ፡፡ ዲያቆን ዳንኤል ስለ ምግብ ቢያወራንም ፣ የተረዳሁት ዋናው መልዕክቱ ስለ አየር መንገዳችን ፣ ስለ አየር መንገዳችን የሚል ቁም ነገር እንዳነገበ ነው ፡፡ የጾሙ ምግብም ታሪክም በዋናነት የተያያዘው ከአየር መንገዳችን መስተንግዶ መበላሸትና አገልግሎት ማሽቆልቆል ጋር ስለሆነ ፤ በሂደት ከቀጠለ በአየር መንገዳችን ላይ ጉዳትና ኪሣራ ይዳረጋል ፣ አገርም ትጎዳለች ለማለት በመፈለግ የዜግነት ግዴታውን ለመወጣት የሞከረ ይመስለኛል ፡፡

  ይህች ጽሁፍ በቀጣይ ያወጣት ግልባጭ ስለሆነች ዓላማውን ልብ ይበሉለት ፡፡ "ባለፈው ሳምንት ከአዲስ አበባ ወደ ጆሃንስበርግ በሚሄደው ኢትዮጵያ አየር መንገድ የደረሰብኝን መጉላላት ዘርዝሬ በዚህ ጦማር ላይ ጽፌ ነበር፡፡ ያንን ሳደርግ ዋናው ዓላማዬ የኢትዮጵያ አንዱ መለያ የሆነው አየር መንገዳችን እንዲሻሻል በማሰብ ነው፡፡ ‹ጠላት ያማል ወዳጅ ይወቅሳል› እንዲሉ፡፡ ታላቁን መርከብ የአንዲት ብሎን መውለቅ ለአደጋ እንደሚ ዳርገው ሁሉ እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ያሉ ታላላቅ ተቋማትንም በየአካባቢው የሚፈጠሩ ትናንሽ የሚመስሉ ስሕተቶች ዋጋ ያስከፍሏቸዋል፡፡"

  አየር መንገዳችን ደረጃው ሊወርድ የቻለበት ምክንያት ዳንኤል ያነሳው ጉዳይ ቁም ነገር በመሆኑ ይኸው ከአፍሪካ ሰባተኛ የተባለበት ሰነድም ይለፍፋል ፡፡ አየር መንገዳችን በዘመናዊ ጀት ቁጥር ከአፍሪካ አንደኛ ቢሆንም የመስተንግዶ ደረጃውና የደረሰበትንም እንድትመዝኑት ይኸው ለንባብ ያህል ተቀንጭቧል ፡፡

  The Best Airline in Africa
  1 South African Airways
  2 Kulula
  3 Air Mauritius
  4 Kenya Airways
  5 Egyptair
  6 Mango
  7 Ethiopian Airlines
  8 1time
  9 Air Austral
  10 Air Seychelles

  ምንጭ ፡ http://www.worldairlineawards.com/Awards_2012/africa.htm

  አቶ አየለ በነገር ሸፋፋ በዳንኤል በኩል ማኀበረ ቅዱሳንን አፍ ማሟሻ ለማድረግ የቀየሱት ዘዴ ነው እንጅ ከዲያቆኑ መንደርደሪያ አጀንዳ ጋር የተያያዘ እውነታ የለውም ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thanks for the link.

   If we want growth for our airline, it should be us who are supposed to go extra miles to advise the airline managment team to improve everything. At large if we want for change in Ethiopia, customer compliant has to be heard. We all has to go and say it for the sake of improvment.

   In a developed world, when you buy something new, you have 100% right to say I don't like what I bought and return it back (sometimes with in up to 2 weeks).

   እኛ የአባባሎች ባለቤት ብቻ ሆነን ነው እንጂ ሁሉንም አባባሎች በተግባር የምንፈጽም ቢሆን ኖሮ "ደንበኛ ንጉስ ነው" የሚለውን በተግባር ባሳየን::

   Delete
  2. wuuuuuuuuuuuuuuuuuuu, endante ayinet astewayun yabzaln abooooooooooooooo

   Delete
 17. Any one hate Ethiopian air lines hater of Ethiopia. Daniel stop go Gojam to ride Mule. That is you orginally ride for. First of all you are talking about hod or eating, do you know how many true preachers you killed in past decades???? Daniel Feresawi go to hill to burn through out of your life. Other wise come back to truth. It is way and life called Jesus. You never ride bike, on your life goje, please do not waste our poor church money. I recomaned you to back to Gojam to ride Horse. Bekelo yegchehina mut. Nefegeday Daniel. We suspect you the death of aba paulos, investigation is on the, way.

  ReplyDelete
  Replies
  1. @anon 4:47
   አንተ ይሄን እንግሊዝኛ ተጫወትክበት ነው የሚባለው! አቤት እንዴት ፅፈህ ሞተሃል። የሚያሳፍረው ውጪ መኖርህ ብቻ ሳይሆን ዘመናዊ ለመሆን ጴንጤ መሆንህ ግን መሰረታዊ ነገሩን በፃፍክበት ቋንቋ እንኳን አለመማርህ ከፈረሱ ጋሪው አረገብህ። ለመፃፍ መጀመሪያ ተማር።

   Go to hill አልክ ቂቂቂ ማፈሪያ በቅሎ።

   Delete
  2. ki ki ki , I haven't seen such kind of English ha ha ha

   Delete
 18. look at this link too:
  http://www.diretube.com/articles/read-ethiopian-airlines-finishes-a-disappointing-7th-best-airline-in-africa_1632.html

  ReplyDelete
 19. Dear Ayele, this simply tells me the hate you have for the Church rules and regulations. All the Bible verses you used here are totally irrelevant. The Bible says, anyone who misleads his brother will be punished. The truth is that our Church has no restriction on declaring fasting during those 7 official fasting seasons of the Church (which seem are too many for you, my brother). The other point you want to mislead readers about EOTC Holy Synod's decision on the official number of Fasting is also untrue. The following have been the Official fasting seasons of the EOT Church since ever - Tsome Nenewe, Abiy Tsome, Tsome Hawariat, Tsome Dehnet (Arb and Rob), Tsome Filseta, Tsome Nebiyat, Tsome Gehad. There is also one more optional fasting a Christian can add on the list- Tsome Tsige. A Christian who wants to have a Private fasting (other than the Church’s official fastings) should NEVER tell/discuss with anyone about his/her fasting. That is what the Church teaches. So I don’t see anything wrong with a Christian talk/write/ discuss about official fastings of the Church.
  Aba selamawoch, we are glad to know more and more about your motives from day to day. God willing, rest assured our Church's teaching and traditions will be passed to the coming generations intact. EOTC children no more be fooled with your pro-protestant teachings.

  ReplyDelete
 20. qeduseyard@yahoo.comDecember 5, 2012 at 10:59 AM

  dani betam hodam nhe yasazenal::

  ReplyDelete
 21. ዲ/ንዳንኤል እና መንገደኞቹ ከኢትዮጵያ አየረ መንገድ ጋር ይቅርታ ከተባባሉ ታድያ እናንተን ምን ይሏችኋል?

  ባለፈው ሳምንት ከአዲስ አበባ ወደ ጆሃንስበርግ በሚሄደው ኢትዮጵያ አየር መንገድ የደረሰብኝን መጉላላት ዘርዝሬ በዚህ ጦማር ላይ ጽፌ ነበር፡፡ ያንን ሳደርግ ዋናው ዓላማዬ የኢትዮጵያ አንዱ መለያ የሆነው አየር መንገዳችን እንዲሻሻል በማሰብ ነው፡፡ ‹ጠላት ያማል ወዳጅ ይወቅሳል› እንዲሉ፡፡ ታላቁን መርከብ የአንዲት ብሎን መውለቅ ለአደጋ እንደሚ ዳርገው ሁሉ እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ያሉ ታላላቅ ተቋማትንም በየአካባቢው የሚፈጠሩ ትናንሽ የሚመስሉ ስሕተቶች ዋጋ ያስከፍሏቸዋል፡፡

  ዛሬ ከጆሃንስበርግ ወደ አዲስ አበባ ስመለስ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአካባቢ ሥራ አስኪያጅ በተፈጠረው ጉዳይ ላይ አነጋግረውን ነበር፡፡ ባለፈው ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታ ጠይቀው፣ በቀጣይ ተመሳሳይ ስሕተቶች እንዳይፈጠሩ አሠራራቸውን ማረማቸውን ገልጠውልናል፡፡ ያለፈውንምንም ለመካስ በቢዝነስ ክላስ ወደ አዲስ አበባ እንድንመለስ አድርገዋል፡፡

  በመጀመርያ ቅሬታችንን በመስማታቸው፤ ቆይቶም ቢሆን ይቅርታ በመጠየቃቸውና ስሕተቱን ለማረም አሠራር መዘርጋታቸው ያስመሰግናቸዋል፡፡ ችግሮች መቼምና የትም ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡ ሁለት ነገሮችን ግን ይፈልጋሉ፡፤ አንድ ሲፈጠሩ በቅርብ ተገኝቶ ሳይብሱ የሚፈታ አመራርና፣ ችግሮቹ ዘላቂ ሆነው እንዳይቀጥሉ የሚያደርግ አሠራር ናቸው፡፡ ያኔ ያጣነው ይሄንን ነበር፡፡

  ደንበኞች ቅሬታቸውን የሚሰማና የሚፈታ ካገኙ ከአየር መንገዱ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ይቀጥላሉ፡፡ ቅሬታቸውን እንደያዙ እንዲቀጥሉ ከተደረገ ግን በዚህ የውድድር ዘመን ፊታቸውን ወደ ሌሎች ያዞራሉ፡፡

  በመሆኑም አየር መንገዳችን ቅሬታውን ተቀብሎ ለማረምና ይቅርታ ለመጠየቅ ያደረገው አሠራር አስደስቶኛል፡፡ ወርቅ እንዲህ ሲገዛ ያምርበታል፡፡ ነገም እንዲሁ እየተሰማማን እንደምንቀጥልም ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ጥበቡን በልቡናችሁ፣ መልካሙን መስተንግዶ በአውሮፕላናችን ላይ ያሳድርብን፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 22. አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች አስተሳሰብን ሳይሆን ግለሰብን በጭፍን መደገፍና መቃወም አስተውዬባችሀለሁ፡፡ አሁን ጉዳዩ የተረት አባታችን ዳንኤል ክብረት ለምን ተነካ ነው እንጂ ለሃይማኖት መቅናት አይመስለኝም፡፡ በአየለ የቀረበው ጽሁፍ የዳንኤልን ጽሑፍ መሰረት ያደረገና መታየት የሚገባውን ሌላ ጎን ያሳየ ነው፡፡ ከሃይማኖት አንጻር የተሟገታችሁ አንዳንዶች የሳታችሁት ዋና ነገር ያለ ይመስለኛል፡፡ ጾም አየለ ባቀረበው መንገድ ነው መታየት ያለበት ወይስ ዳንኤል ባቀረበው መንገድ? ስለዚህ እባካችሁ አትሳቱ ዳንኤል ሰው ነው በብዙ ይስታል፡፡ ስለዚህ እርሱን ተዉትና በሐሳቡ ላይ አተኩሩ፡፡ አየለ ያቀረበውንም ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር ብታዩት ይበልጥ ተቀባይነት አለው፡፡ ስለዚህ እባካችሁ ሚዛናዊ ህሊና ይኑረን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. አቶ አየለ ፣ ዲያቆን ዳንኤል የጻፈበትን ዓላማ ስለሳተና በራሱ መነጽር ወደሚፈልገው አቅጣጫ ጐትቶ የሃይማኖትና የድርጅት አተካሮ እንዲሆንለት ፈልጓል ፡፡ ዲያቆኑ የጻፈው ግን ስለ አገራችን ጉዳይ ያገባኛል በማለት የዜግነት ግዴታውን ለመወጣት የተሰማውን ፣ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል በመጠቆም አሥፍሯል ፡፡

   የሌላ አገር ዜጋ ቢሆን እኮ እንዲህ ለመውቀስም ሆነ እንዲያርሙት ተከታትሎ አይጽፍም ፡፡ ፈረንጅ በሰዓቱ የተበደለበትን ጉዳይ እስከመጨረሻ ሄዶ ለማስተካከል ይሞክራል ፤ ከዛ ካለፈ ግን አያመውም ፤ ስለማይመለከተውም ብታሻሽሉ ብሎ አስተያየት አይሰጥም ፡፡ ምክንያቱም እድገቱም ሆነ ውድቀቱ አይነካውምና ነው ፡፡ ኢትዮጵያዊው ዳንኤል ግን የመስተንግዶ ችግሮችን በማጋለጥ ለወደፊት እርምት እንዲያደርጉና የገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ጋብዟል ፡፡ እነርሱም ስህተታቸውን ተቀብለው እናርማለን ብለዋል ፡፡ ከዚህ ውጭ የሃይማኖት አጣብቂኝ ፈጥራችሁ ከመጽሐፍ ቅዱስ ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ እንመዝን የሚለው የተለመደ የታወቁት የሉተር ተከታዮች ጥያቄ ነውና በየምክንያቱ ነገር አትጎትቱ ፡፡

   Delete
  2. Ayu endet gebitoshal ebakish. Beka endih new ante sititsif. Gebez mehaym neh wodaje. Huletunim sileminaneb enquan endante yale tsehafi lelam ayshewiden. Please try to be human being leave alone religious person. Aba selama blog is much non ethical, non-sense and stupied than even poltical blogs. I think the reason is the bloggers are with serously compromized IQ status.

   Delete
 23. Yibel!!! Ato Ayele!!!! Egzibaher Edme Ystih!!!
  I agree with you a 1000 times. I am ashamed to call Daniel a Diakon!

  ReplyDelete
 24. I know you will not post my comment as you have reaptdly done it but my objective is you have to now how we are feeling your post. So let me say someting on your blid post. I have read Dn. Daniel's post and it is really useful for the aireline and for our church in that the airline will correct its mistake and we the EOTC members will get our right in our flights. But as the narrow minded (dedebu) Ayele said it is "wudasie kentu" where did you learn this. We could ask our rights so that we can do our religoius obligations. You the tehadiso menafikans need to distroy everything of the EOTC. This is confirmed by your usual post. Lenegeru dani yetsafewn Ayele endet liredaw yichilan, tehadiso mender lemender mawudelidelina meziref bicha new siraw (Diros bene Begie eyetemera min lihon yichilal)

  ReplyDelete
 25. You are block head, how can you come in this web to curse truth writer. Daniel fersawie asemesay, he does not represent our church. Moraly, he has no wright to blame our air lines. We all Ethioian never respect the enemy of development. Daniel Goje, tell for your ferse gary. Daniel ebede wosha new lekafe lekeft. Bekelo yirgetehna,mut.

  ReplyDelete
 26. hodam here after dont talk aboutHod ayele is educated and gentle man tahank you

  ReplyDelete
 27. Ato Ayele I think you are a very person.

  ReplyDelete
 28. Ato Ayele whatever your name is, you don't understand the point, DANIEL is absolutely right and if you are ORTHODOX you will understand it but you are not you are traying to divide our church nice tray it's impossible because " AND I SAY ALSO UNTO THEE,THAT THOU ART PETER,AND UP ON THIS ROCK I WILL BUILD MY CHURCH ;AND THE GATES OF HELL SHALL NOT PREVAIL AGAINST IT."matthew 16-:-18. DON'T LET THE DEVIL USE YOUR MIND ! GOD HAVE MERCY ON YOU !

  ReplyDelete
  Replies
  1. አቶ አየለ ክርስትና እንዴት ነው የምናየው? በትችት በመነቃቀፍ? አንዳችን ስናጠፋ ቀስ ብሎ ወንድምን ማረም ይቻላል ደግሞስ ማን ፈራጅ አደረገን?

   Delete
 29. aye mk. manenetachu endeh behodachu yetawek ewnetun mekebel ye enanete deresha behonem wendemea keber yeseteh

  ReplyDelete
 30. Ayele, who are you? Bik bey keguada neh adel? Daniel is a known precious son of Ethiopia & EOC.

  ReplyDelete
 31. ante kelb hod amlaku enji ante someh tawkaleh

  ReplyDelete
 32. ድፍረትህ አየለ፤እውቀት አልባነትህ አየለ፤ባዶነትህ አየለ፤የርጎ ዝንብነትህ አየለ፤አየለ በቀረህ ነበር፡፡

  ReplyDelete
 33. I listened some of Daniel's preachings, and like them. But I watched his political presentation I was not impressed.
  I read Ayele's writing, and helped me a lot to like Daniel.
  No matter what Daniel wrote about that airlines, the customer and the airline have to resolve their own problem, because they were doing business.
  If Daniel is not fasting in a proper way, he has his God or his own mind to judge him, because he doing it for his own purpose. Where come from this guy called "Ayele" ?? what is his Concern?

  ReplyDelete