Saturday, December 29, 2012

በውጭ የሚገኙ ገለልተኛ እንዲሁም በሀገር ቤቱ ሲኖዶስ የሚመሩ አብያተ ክርስቲያናት በውጭው ሲኖዶስ ስር ለመጠቃለል ጥያቄ እያቀረቡ ነው።

የእርቁ ተስፋ እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ እየተሟጠጠ ነው። የሰላም እና አንድነት ጉባኤ አባላት የሆኑት ሊቀ ካህናት ኃይለ ሥላሴና ዲያቆን አንዱአለም የእርቁን ጉዳይ ለመወያየትና ለመጭው የጥር ስብሰባ የማግባባት ስራ ለመስራት በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ ሄደው እንደነበር ይታወቃል። ሆኖም ግን እነዚህ ግለሰቦች የሄዱበትን ጉዳይ በአግባቡ ሊፈጽሙ አልቻሉም። ወደ ቤተ ክህነት መግባት አልቻሉም። ሊቀ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ማን እንደቆረጠው ባልታወቀ ቲኬት በአስቸኳይ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርገው ዛሬ አሜሪካ ገብተዋል። በትዕዛዝ ከአገር እንዲወጡ እንደተደረጉም በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ተናግረዋል። ዲያቆን አንዱአለምም እዚያው አዲስ አበባ ባልታወቁ ሰዎች ተወስዶ ወዴት እንደደረሰ የታወቀ ነገር የለም። ይህ ሁኔታ መንግስት ጣልቃ አልገባም ብሎ የሰጠውን መግለጫ ከፍተኛ ጥያቄ ውስጥ ይጥለዋል ወይንም በተግባር ሊታይ አልቻለም ማለት ነው። ይህ ደግሞ እጅግ አሳፋሪ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በውጭው ዓለም የሚገኙ በርካታ የገለልተኛ አብያተ ክርስቲያናት በውጭው ሲኖዶስ ለመጠቃለል እየተነጋገሩ ነው። በሀገር ቤቱ ሲኖዶስ ስር በሚመሩ አብያተ ክርስቲያናት ያሉ  በርካታ ምዕመናንን ጨምሮ በስደት ወዳለው ሲኖዶስ ለመጠቃለል ጥያቄ እያነሱ ነው። በውጭው ሲኖዶስ የተገኙ ምንጮች እንደሚጠቁሙት  በውጭ በገልልተኛነት ያሉ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ወደውጭው ሲኖዶስ ለመቀላቀል ጥያቄ እያቀረቡና ውይይት እያካሄዱ ነው። በነዚሁ አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙ ካህናትና የቦርድ (ሰበካ ጉባኤ) አባላት የአባሎቻቸውን ድምጽ በመስማት በጉዳዩ ውይይት እያደረጉ ነው። በኢትዮጵያ ሲኖዶስ ስር የነበሩ የተወሰኑ አብያተ ክርስቲያናትም ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ውጭው ሲኖዶስ የመቀላቀል ጥያቄ እያንሸራሸሩ ነው። ይህ የሚያመለክተው የቤተ ክርስቲያንን አንድነት በጉጉት ሲጠብቅ የነበረው ምዕመን ትዕግስቱ እያለቀበት መሆኑን ነው።

በውጭው ሲኖዶስ ስር የሚያገለግሉ አባቶችና ሰባክያነ ወንጌል በውጭው ዓለም የሚገኘውን የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድነት ለመሰብሰብና ወደፊት የሚሄዱበትን አቅጣጫ ለመገምገም በሎስ አንጀለስ በጥር ወር ይሰበሰባሉ።
ወደውጭው ሲኖዶስ እንቀላቀል የሚሉ ምዕመናን ከሚያነሷቸው ዋና ዋና ጥያቄዎች/ምክንያቶች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል።
1)     በቅርቡ ይፋ የተደረገው የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ደብዳቤ ሳይታመሙ ያለፍቃዳቸው በግፍ የተባረሩ መሆኑን ስላሳየ
2)    የአዲስ አበባው ሲኖዶስ መንግስት ጣልቃ ስለገባበት ለቤተ ክርስቲያን በትክክል መስራት አይችልም
3)    ገለልተኛ የሆኑት ደግሞ እስከ መቼ ገለልተኛ እንሆናለን?  የሚሉት ይገኙበታል።
ለቤተ ክርስቲያን ጸልዩ!

8 comments:

 1. WE IN DALLAS ST.MICHAEL , ST.MARY AND NEW CHURCH EYESUS CHURCH ON THE WAY TO ENTER ABUNE MERKORIOUS HOLY SYNOD .

  ReplyDelete
  Replies
  1. Good Job Dallas Orthodox Christians.That Is The Only Way To Get Out Of This Messy Situation.May God Bless You All

   Delete
 2. Is there Eyesus church in Dallas?
  Where is the address?

  ReplyDelete
 3. We from Ethiopia also follow. If the fathers are not right there is no way to accept the patriarch that will be appointed by the government. We can accept it only once, not twice.

  ReplyDelete
 4. በሙስናና በዘረኝነት ከተጨማለቁትና ከሚጨማለቁት ጋር አንጨማለቅም፡፡ ያለን አማራጭ በውጭው ሲኖዶስ ሥር መተዳደር ብቻ ሊሆን ይችላል፡፡

  ReplyDelete
 5. Please somebody explain to me if this teaching of our lord Christ has any implication to the holly father's or it’s meant only for the rest of us.
  Matthew 5:3-13
  Blessed are the poor in spirit: for theirs is the kingdom or heaven.Blessed are they that mourn:for they shall be comforted.Blessed are the meek:for they shall inherit the earth.Blessed are they which do hunger and thirst after righteousness:for they shall be filled.Blessed are the merciful:for they shall obtain mercy.Blessed are the pure in heart:for they shall see God.Blessed are the peacemakers:for they shall be called the children of God.Blessed are they which are persecuted for righteousness sake:for theirs is the kingdom of heaven.Blessed are ye,when men shall revile you,and persecute you and shall say all manner of evil against you falsely,for my sake.Rejoice,and be exceeding glad:for great is your reward in heaven:for so persecuted they the prophets which were before you.
  ye are the salt of the earth:but if the salt have lost his savour, wherewith shall it be salted? it is thenceforth good for nothing, but to be cast out,and to be trodden under foot of men.

  ReplyDelete
 6. selam lehulachihu yihun!
  bewich sinodosi (sedetegnaw,Higawiw yemibalew) sir lemehoni yemitifeligu eina kezihi befiti be midere ethiopia bemiyasitedadire sinodos sir yeneberachu be ahunu seat lewit lemadireg yemitifeligu beselam gibu betam zegeyacschu lemin duro atigebum neber mani asigededachihu? eigna gin be ethiopia yemnimera gin aininawetim mingizem bihoni ethiopia wisit be menori sinodosin patiriyarik einemeralen beteleyaye menigedi keheger wist yewetuti abatachin bigebu einimeraleni gin eindenanit eidimiliki betekawimo yemitnoru yikirita yematawiku tinisch koyitachih Fetarin satikawemu atikerum belu menigedu yimechachihu,eigna gin Eigizi abiheri mefitehe yamita eiyalin bemeseleyi einiketilalen

  ReplyDelete