Wednesday, December 5, 2012

አስደናቂ ሰበር ዜና፦ የኢትዮጵያ መንግስት የቤተ ክርስቲያናችንን የእርቅ ሂደት እንደሚደግፍ በደብዳቤ አረጋገጠ

በቀጥታ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በተላከ ደብዳቤ የኢትዮጵያ መንግስት የቅዱስነታችውን ወደ መንበራቸው መመለስ ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፍ አስታወቀ።  ደብዳቤው እንደሚገልጸው ቤተ ክርስቲያንን ወደ አድነት ለማምጣት የአገር ውስጥ ሽማግሌዎችን ሃሳብ ተቀብሎ ይህንን እንደወሰነ ይናገራል። ይህ መልካም ዜና አሁን በዳላስ እየተካሄደ ያለውን የእርቅ ውይይት መሰረታዊ በሆነ መልኩ ይቀይረዋል ተብሎ ይገመታል። 

ሙሉውን ደብዳቤ  ከዚህ በታች ማንበብ ይችላሉ (ደብዳቤው ላይ ቢጫኑ ለማንበብ ይቀልዎታል)

እግዚአብሔር ሀገራችንንም ቤተ ክርስቲያናችንንም ይጠብቅልን።  ለመሪዎቻችንም አስተዋይ ልቦና ስለሰጠልን እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን።  ለቤተ ክርስቲያን መሪዎቻችንም እንዲሁ ያድርግልን።


10 comments:

 1. Thanks God! No more mekefafle.

  ReplyDelete
 2. ሠጠው መርቆDecember 5, 2012 at 3:41 PM

  እግዚአብሔር መልካሙን እንዲያደርግልን ሁላችንም እንጸልይ ፡፡ ይኸ መልካም ጅምር ነው፤ ከኘሬዘዳንቱ ይበልጥ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በራሳቸው ፣ በያዙት ሥልጣንና መንግሥት ስም ትንሽ እራፊ የድጋፍ ደብዳቤ ቢጽፉ መንግሥት ለቤተ ክርስቲያን አንድነትና ሰላም ሙሉ ድጋፍ ሰጥቷል ማለት እንችላለን ፡፡ ይኸን ያስባለኝ በህገ መንግሥታችን ከኘሬዘዳንቱ ይልቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይበልጥ ተደማጭነትና ከበድ ያለ ኃላፊነት ስላላቸው ነው ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ነሳው መርቆDecember 5, 2012 at 10:58 PM

   የጻፍኩት አስተያየት ቀለሙ ሳይደርቅ ፣ ድጋፋቸውን የሰጡት ኘሬዘዳንት መልሰው አነሱት ፡፡
   መርዶ ቢመስልም ለማዳመጥ ለሚፈልግ ለትምህርት
   http://amharic.voanews.com/content/president-girma-to-abune-merkorios/1559340.html

   አቡነ መርቆርዮስ ወደ አገር ተመልሰው መምራት ባይችሉም ፣ ተስማምተው ቤተ ክርስቲያኗን ወደ አንድነት ከመለሷት በስደትም ቢሆን ቡራኬ በስልክ እያስተላለፉ ማስተዳደር ይችላሉ ፡፡

   Delete
 3. Ewnetm Asidenak Seber zena Mengisit Behayimanot Tsalka Ayigebam Malet Ahun Ayichalim Yigermal pirezdent Girma Welde Giyorgis Behasabachew Metsenker Alebachew Negeru Gin Ewnet ayimesilim Argitewal Malet New Negerochin Alakatetum Mawki Lalebachew Hulu Masawek Neberebachew Yasasatachew sew yale Yimesilal Asibewbet Aminewbet Ayimesilim Selam Mefelegachew gin yasdesital Ahun Mengist Abune Merkorewos endigebu fekede Malet Yichalal ?Yeselam Dirdiru Hulu Abeka Malet New ? Temesigen

  ReplyDelete
 4. http://amharic.voanews.com/content/president-girma-to-abune-merkorios/1559340.html

  ReplyDelete
 5. የኢትዮጵያን መንግስት ለእርቁና አራተኛው ፓትርያርክ በቦታቸው እንድመሉስ የሰጠው መግለጫ እጅግ የሚያስደስት ነው። የሀገራችን መንግስት እንድህ አይነቱ የእርቀ ሰላም በሀይማኖቱ ውስጥ እንድፈጠር ያረገው ጥሪና ውሳኔ የቤተ ክርስቲያናችን ታላቅ ዋግ የምሰጠው ነው።ነገር ግን እንደነ ማቅ የመሳሰሉት ሰላም አንድነት የማይወዱ ክፉ መንፈስ ግን ደስ አይለውም። አንድነቱ እንዳይፈጠር ሌላ ጉድጓን እየቆፈረ ነው። ነገር ግን የእረሱ መቀበርያ ስለሆነ ችግር የለውም። ትላትና እነ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስን እና አቡነ መልኬ ጼድቅ ስያሳድ የነበረ መርዘኛዉ ማህበረ ቅዱሳን በጣም ቅር ይለዋል። ግን እግዚአብሔር የሰላም አምላክ እርሱ ድል ያደርገዋል። ሰላም ለቤተ ክርስቲያናችን ልመጣ ነው በርትተን ወደ እግዚአብሔር እንጸልይ ተስፋ አንቁረጥ እረሱ አምላችን ከቶ አይተወንም። የማቅ ሊቃነ ጳጳስ አሁንም ደስተኞች አይደሉም። ምክንያቱም የራሳቸው የሆነ የማቅ አባት ለመሾም መንገዱ ይዘጋባቸዋልና። እግዚአብሔር ያለው ሁሉ በግዜውና በሰዓቱ ይፈጸማል። ትግስት ብቻ ይኑረን ።

  ReplyDelete
 6. Thank you guys. we have to appreciate Ethiopian Government regarding supported reconciliation between Orthodox Tewahedo church leaders.Really I am so happy to hear and read those written letter from our country leaders. Let leave our difference a side and stand together for our church unity.we all Orthodox Tewahedo church members are brothers and sisters through our God, who died on the cross for our sins. we didn't pay any thing for him. But he paid his life for our sins. lets us love each others as a bible said to us not by hating each others. we are not obeying the word of God to day.It doesn't matter which side you came from, north south east and west. Christianity means not by each others,just think about Lord God suffered for our sins on the cross. Do you feel some thing regarding how he suffered for you.If do you feel something inside your heart,yes you know Lord Jesus Christ crucified.O Lord we need your help and guide us and protect our peoples and country.Amen.........

  ReplyDelete
 7. አባስላማዎች ግና ዛሬ ወደድኳሁ መልካም የምስራች ስለነግራችሁን
  ለኔ ፕሬዘዳንቱ ጥሩ የሽምግልና ስራ ሰሩ እግዚያብሄር እድሜ ሰጠዎት ይህችን ሐገርና ሐይማኖት እንዲታደጉ ነውና አስታራቂ አባት አያሳጣን፣ መከፋፈል፣ አድመኝነት እንዲስፋፋ፣ በጸሎት እንዳንተጋና ያደርጋልና እግዚያብሄር ጅምርዎን ያሳምረው አሜን

  ReplyDelete
  Replies
  1. AMENENENENENE

   Delete
  2. ENGEDIH MENGEST TARIK SERA BEEWENETEM KE WOGENEU GAR MEHONUN ENDIHUM LEEREQE ZEGEJU ENEDEHONE ASAYENE ENANETES BE KERESETOS EYESU TESHUMACHU YE FIKER AMABASADEROCH YEMEHONACHU LIQANE PAPASAT ESTI FIKRACHUN ASAUN EGNAME LE HAYEMANOTACHENE LEMEMEOT QALE ENEGEBA

   Delete