Thursday, December 6, 2012

ከፕሬዚዳንት ግርማ ደብዳቤ ምን እንማራለን?

በትላንትናው ዕለት (Dec 5,2012) እንደዘገብንላችሁ ፕሬዝዳንት ግርማ ተስፋ ሰጭ የሆነና የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የማይፈልጉ ግለሰቦችን ወይንም ቡድኖችን ምክንያት የሚያሳጣ ደብዳቤ ጽፈው ነበር። በአሜሪካን ድምጽ ራዲዮ እንደተደመጠው ፕሬዝዳንት ግርማ አዲስ አበባ ካለው ቤተ ክህነት በደረሰባቸው ተቃውሞ የጻፉት ደብዳቤ ችግር እንደፈጠረ በማብራራት እንዲስተባበልላቸው አሳስበዋል። ከፕሬዝዳንቱ ደብዳቤ እንዲሁም በ VOAከሰጡት ማስተካከያ ማብራርያ ልናስብባቸው የሚገቡና የምንማራቸው 2 ነገሮች፦

1ኛ) በዳላስ የሚካሄደው ድርድር ውጤት የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ መንበራቸው መመለስ ቢሆን መንግስት ሙሉ ድጋፍ እንደሚሰጥ፦
ፕሬዝዳንት ግርማ የጻፉት ደብዳቤ መንፈሱ መንግስት በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ጣልቃ የገባ ስለሚያስመስለው ተቃውሞ የደረሰበት ይመስላል። ፕሬዝዳንቱም ከቤተ ክህነት የመጣውን ወቀሳ ስላመኑበት በቅንነት የጻፉትን ደብዳቤ እንዲነሳ ጠይቀዋል። ይህ ማለት ግን የኢትዮጵያ መንግስት አቡነ መርቆሬዎስ ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ አይፈቅድም የሚል አንድምታ አይሰጥም። የሲኖዶሶቹ ውሳኔ የአቡነ መርቆሬዎስ ወደ መንበራቸው መመለስ ከሆነ በስደት ያሉትን የሲኖዶሱን ዋና ጸሐፊ አቡነ መልከጼዴቅን ጨምሮ የሲኖዶስ አባላትና ካህናት ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ ወይንም መንበርነቱ አዲስ አበባ ከሚሆነው የአንድነት ሲኖዶስ ጋር ያለ ተጽዕኖ እንዲሰሩ መንግስት ሊፈቅድ ይገባል። በዚህም ውስጥ መንግስት ጣልቃ ገብቶ ችግር ይሆናል ብለን አናምንም የፕሬዚዳንቱም ደብዳቤ የሚጠቁመውም ይህንኑ ነው። 

2ኛ) አዲስ አበባ ያለው ሲኖዶስ የአቡነ መርቆሬዎስን ወደ መንበራቸው መመለስ ብዙም እንደማይደግፍ፦ 
 በፕሬዝዳንት ግርማ ደብዳቤ ከቤተ ክህነት የደረሰው ፈጣንና ጠንካራ ተቃውሞ  የሚያመለክተው ቤተ ክህነት የመንግስትን ጣልቃ ገብነት አለመፈለግ ብቻ ሳይሆን የአቡነ መርቆሬዎስን ወደ መንበራቸው መመለስን ያለመፈለግም ጨምሮ ይመስላል። የአዲስ አበባው ሲኖዶስ ባለፈው የግንቦቱ ስብሰባ እንደወሰነው 6ኛ ፓትርያርክ ለመሾም ቅድመ ሁኔታዎችን ማስተካከል እንደሚጀምር ለህዝብ ይፋ አድርጎ ነበር።  እንደሚታወቀው ይህ ለኦርቶዶክሳዊው ምዕመን እንቆቅልሽ ነው። ቤተ ክርስቲያናችን ለ 20ዓመታት በ ሁለት ሲኖዶስ ስተመራ የቆየችው እኮ የቀድሞው ፓትርያርክ በህይወት እያሉ ለምን ሌላ ፓትርያርክ ተሾመ በሚል የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥያቄ ነበር። እግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ አንደኛው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ቤተ ክርስቲያንን ወደ አንድነት ለመመለስ ግልጽና ትክክል የሆነው እርምጃ (most logical approach) በይህወት ያሉትን ፓትርያርክ ለመላዋ ቤተ ክርስቲያን መሪ ማድረግ ነው። ይሄ ለምን ድርድር እንደሚያስፈልገውና ከባድ እንደሆነ ለህዝብ ግልጽ አይደለም።

የዚህች ቤተ ክርስቲያን አንድ መሆን ለቤተ ክርስቲያንም ሆነ ለሀገራችንም ከፍተኛ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ስለሚኖረው መንግስትም ሆነ ማንኛውም ወገን የራስን ጥቅም፣ ስልጣን  ወይንም ሌላ ነገር ወደ ጎን አድርጎ የአንድነቱን ሂደት መደገፍ ይኖርበታል።

8 comments:

 1. I am surprised to learn that yesterday was April 5, 2012? Is it?

  ReplyDelete
 2. ኘሬዘዳንት ግርማ የሰጡትን ድጋፍ ከማንሳት ይልቅ እንደነበረ ቢተውትና ለሚጠይቃቸው አካል በሬዲዮ እንዳሰሙት ፣ እንደ ዜጋ ፣ እንደ አማኝነቴም የሚሰማኝ የግል ስሜቴን መግለጽ መብቴ ነው በማለት ሊያስረዱና ሊከራከሩ ይችሉ ነበር ፡፡ ያን በዚህ መልክ ሊጓዙበት አልፈለጉም ፤ ከቤተ ክርስቲያን አባት ቅሬታ ሲሰማ ፣ መልዕክታቸው እንዲነሳ ማድረጋቸውም ክርስቲያንነታቸውን የበለጠ ያጐላዋል ፤ የቤተ ክርስቲያን አባት መመሪያን ማክበራቸውን ያመለክተናልና ፡፡

  በሌላ በኩል ግን በፖለቲካ ቋንቋ ከመነዘርነው መንግሥት ይኸን ድጋፍ ቢሰጥ ፣ ለሰላም ድጋፍ መስጠትና በሃይማኖት ጣልቃ መግባት በትርጉም አይገጣጠሙልኝም ፡፡ በሃይማኖት ጣልቃ መግባት ከአባቶች ፈቃድ ውጭ ሃይማኖቱንም ልምራ በማለት ያለማዕረጉ ነገር ቢያቦካ ነው ፡፡ ያን ሲያደርግ እስካልተገኘ ድረስ ግን ፣ ለቤተ ክርስቲያን አንድነትና ለክርስቲያን ህዝብ መስማማት መሥራት ለአገር መረጋጋትና ሰላም እንደሚተጋው ግዴታውን ተወጣ ማለት ነበር እንጅ እንደተፈራው ዓይነት ድምዳሜ ላይ አያደርስም ነበር እላለሁ ፡፡

  ያም ሆነ ይህ አሁን ኳሷ ያለችው ለድርድር በቀረቡት አባቶች መሃከል ነው ፡፡ ተስማምተው አቡነ መርቆርዮስን ወደ መንበራቸው እንመልስ ወይም አንመልስምም ቢሉ ውጤቱን መንግሥት ይቀበላል እንጅ ምንም አያደርግም ፡፡ ምክንያቱም በሃይማኖት ጣልቃ ገባህ ተብሎ እንዳይወቀስ ስለሚፈራ ውጤቱን እንዲቀለበስ አይሞክርም ፡፡ ስለዚህ በቅርብ ያላችሁ ወገኖች ፣ አባቶችን አትጉልን ፤ እንደ መጽሃፍ ቃል ይቅር በመባባል ቤተ ክርስቲያናችንን ወደ አንድነት መልሰው ለአንድ መንጋ መሪ ይሁኑ እላለሁ ፡፡

  ReplyDelete
 3. እግዚአብሔር ይባርካችሁ ወንድሞች፣ ትልቁ ችግር ያለው በማህበረ ቅዱሳን የሚመራው የአድስ አበባው ስኖዶስ ክፉኛ ስላስቆጣቸው ይህን የከቡር ፕሬዝዳንቱ ሀሳብ በአቡነ ናትናኤል በኩል እንደ ግሳጸ ዓይነት አስቆጥቶአቸዉ ተቃዉሞ አቅርበዋል። እዉነት ለመሆኑ ማረጋገጫው በማቅ ድህረ ገጽ በሆነው በአንድአድረገን አቡነ ናትናኤል አያገባችሁም ብሎ የተናገሩት ትክክል ነው በማለት አዉጥዋል። ይገርማል እኝህ የተከበሩ ፕሬዝዳን እንደ አንድ የኦቶዶክስ አማኝነታቸው በየዋህነት ለአንድት ቤተ ክርስቲያን አባት አልባ ሆና በአልችበት አሁኑ ወቅት ነበር ስመታቸውን ለሰላምና ለአንድነት ስባል ይግቡ ብሎው ከሽማግለዎች ጋር የተስማሙት። ወገኖቸ ምንዉ ቅንነት ከሃማኖታችን አባቶች ራቀ ? የአድስ አበባው የዓቃቤ መንበሩ የማህበረ ቅዱሳን አባለት ቁጣው ለሰላም ወይንስ የተለያያች ቤተ ክርስቲያን በዚህ ሁኔታ መቀጥል ይኖርበታል ብለው ነው። የማቅ አባላት ትላትና የብፁዕ አቡነ መርቆርዮስ ጠላት የነበሩ አቡነ መልኬ ጼድቅን ስያሳዱ የኑሩ ለሌችንም መምህራን እንደ እነ ልዑለ ቃል ያሉት በአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን አውደ ምህረት ላይ በግልጥ ስሰድቡአቸውና ስያዋርዱአቸው እንደነበር በvideo በተለያዩ ግዝያት ያሳዩን አልነበር? የወጋ ብረሳ የተወጋ አይረሳም ይሉ የለም ጥንታዊያኑ አባቶቻችን። በአለፈው ሰሞን በማቅ ድህረ ገጽ ደጄ ሰላም ላይ ፓትርያርኩ የት ነው ያሉት ለምን አይናገሩም እያሉ ያወሩና ያሾፉ አልነበር? ዛሬ ግን የህዝቡን ስነ ልቦና ለመስለብ እንደ ለመዱት በሰንበት ት/ቤቶች በኩል የውስጥ ቅስቀሳ ያካሄዳሉ። ጨካኞች ናቸው የመስቀሉ ዋጋ የማይገባቸው የከፋት ጠንቅ የሆኑት በገንዘብ አባቶችን አንደበቶቻቸውን ሸብበው አሰሩአቸው። ማቅ በኦቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ነግሶ እያለ በዚህ እድሜያችን ዉስጥ ሰላምና አንድነት ለቤተ ክርስቲንቱ ይመጣል ብለን ማስብና ማለም ከቶ አይቻልም። እዉነትቱ ይህ ነው። የሰላምና የአንድነት ነገር የሰማይ ደመና ሆኖ እንደ ነፈቀን ዘመናችን ያልፋል እጅ አንድ አንሆንም። ነብይ አይደለሁም ግን ........በዳላሱም ጉባኤ ብሆንም እነዚህ አባቶች መልዕክተኞች ናቸው እንጅ መሳኔ ስጪ ክፍሎች አይደሉም ስለዚህ ምንም እጅግ መፍቴህ ልያመጣ አይችልም። ነገሮቹን ለግዜ ማለዘብያ ወይንም ማቆያ ነዉ። መፍተው ያለው በአድስ አበባው ዓቃቤ መንበር አባላት እጅ ነው። ብፁዕነታቸው ይግቡ አይግቡ ብሎ የመወሰኑ ሀይልና ስልጣን ማለተ ነው።ማቅ አባለት ከላፈቁዱ ከቶ አንድ አንሆንም!!! የእግዚአብሔር መንፈስ ከእኛ ተሰውሮአል ሰውንና ገንዘብን ስለ ምናመልክ። የቅዱሳኖቹ አምላክ ሀገራችንና ህዝባችንን ይጠብቅል።

  ReplyDelete
 4. TEKULAWECH HASABACHU GEBTONAL WOYANE BE HAYMANOT TALKA ENDEMAYGEBA EYENEGERACHUN NEW.
  The fact is woyane was more than the senodis who fired the former patriac and appoint his patriaric at the beginning. and continue to rule the the religion for 21 years.
  U cannt foolish us idiot racists. We can read u who u r the so called aba selama. We know also u r not protestant.
  but u r mission is attackin only on mahber kidusan due to fear of Amhara concentration . I m not Mk for that matter I don't care about them.I care only to my religion.

  ReplyDelete
 5. I like to say something for our church leaders and government leaders. Please work out for good not by ignoring one thing in your life time. That is the Orthodox church members separated in two place for so many years for personal issues.who will bring this our church leaders ugly difference? is this church of Lord Jesus Christ? I don't know something wrong with me not to understand or our church leaders? nobody obey word of God in this church? I'm pretty sure we gonna loose lots of peoples from our church. Because is not true faith according what I am seeing on website and in the church every Sunday.Nobody love each others.why? No answer. If no one stop this kind of crucial difference, what will happen in the next step? what is the church future fate? know I'm so confused...not only me a lots of church members too. every day peoples talking regarding only this issue. what do you feel about this crazy difference in the church? ....

  ReplyDelete
 6. The core problems of our church are:
  1. MK
  2. MK's strategic approach to blackmail all others if
  they are not working/supporting MK agendas
  3. Lack of spirituality from Bishops down to individual
  church members
  4. Lack of dependable information
  5. MK's political approaches to reach the members of the
  church and the public by dissemination of wrong/huge
  information which are difficult to cross-check and
  accept as it is.
  6. MK's devilish approach to present positively who are
  his supporters even though they are against church
  principles
  7. The protestant type of reformationists
  8. Assignment of non-qualified individuals in to the
  positions like PRs in the church.
  9. Corruptions at all levels
  10. Lack of proper christian understanding and knowledge
  at all levels etc

  Can anyone deny these?

  ReplyDelete
 7. ke dejeselam yebasachu nachu ende? minew asteyayetochen be yegizew afinachu taskerutalachu????? yibarkachu

  ReplyDelete