Saturday, December 8, 2012

ላለመታረቅ የተያዘ የእርቅ ስብሰባ

በሁለት ሲኖዶሶች አየተመራች ያለችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ወደአንድነት ለማምጣት የዕርቁ ስብሰባ በዳላስ ተካሂዷል፡፡ ከአቡነ ጳውሎስ ሞት በኋላ በሁለቱም በኩል የወጡት መግለጫዎች የሚያሳዩት የእርቁ ሂደት አጣብቂኝ ውስጥ መግባታቸውን እያሳዩ ነው፡፡ ለእርቁ መሳካት አንደኛው ወገን ለቤተክርስቲያን አንድነት ሲል የግድ መሸነፍ እንዳለበት ይታመናል፡፡ ለመሸነፍ ፈቃደኛ የሆነ ወገን ግን አለ ማለት አስቸጋሪ ነው፡፡ በዚህ ረገድ በአገር ቤት ያለው ሲኖዶስ ከፍተኛ ሀላፊነት ያለበት ይመስለናል፡፡ በውጪ ያለው ሲኖዶስም የራሱን አስተዋጽኦ ማበርከት አለበት፡፡

ሰሞኑን በፕሬዝዳንት ግርማ የተጻፈውና ወዲያው የተሻረው ደብዳቤ በመንግስት በኩል መልካም የሚያሰኝ ነገር እንዳለ አመላክቷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ዋናው ችግር በማን በኩል እንዳለ የፕሬዝዳንቱን ደብዳቤ ተከትሎ የተወሰዱ እርምጃዎች ትልቅ ማሳያ ሆነዋል፡፡ ቤተክህነቱ በፕሬዝዳንቱ ደብዳቤ ስላልተደሰተ መንግስትን በሃይማኖት ጣልቃ እንደገባ በመቁጠር ፕሬዝዳንቱን መውቀሱና ፕሬዝዳንቱም የጸፉትን ደብዳቤ ለማጠፍ እንደተገደዱ መረዳት ተችሏል፡፡ ቤተክህነቱ የፕሬዝዳንት ግርማን ደብዳቤ ተቃውሞ ሲነሳ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ገቡ በሚል ቢሆንም በዋናነት ግን አቡነ መርቆሬዎስን ላለመቀበል ትልቅ ሽፋን የነበረውና «እኛ ይመለሱ ብንልም መንግስት አይደግፋቸውም» የሚለው ሰበብ በፕሬዝዳንት ግርማ ደብዳቤ በጥቂቱም ቢሆን መሸርሸሩ ደስ ስላላሰኛቸውና ከዚህ ውጪ የሚያቀርቡት ምክንያት ብዙ የሚያራምዳቸው ሆኖ ባለመገኘቱ እንደሆነ ተገምቷል፡፡

አቡነ ጳውሎስ በሕይወት እያሉ በውጭ ካለው ሲኖዶስ ጋር ለሚካሄደው የእርቁ ሂደት ትልቅ እንቅፋት እንደሆኑ ተደርጎ አብረዋቸው ባሉትና ያኔ ሲቃወሟቸው በነበሩትና ዛሬ ላለመታረቅ ወስነው እርቁ ይደረግ የሚሉት ጳጳሳት ጭምር ብዙ ሲባል እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ ከእርሳቸው ዕረፍት በኋላ ነገሮች ይለወጣሉ ተብሎ ቢጠበቅም እንዲያውም ብሰው ነው የተገኙት፡፡ ቀድሞስ አቡነ ጳውሎስ ናቸው እንቢ ያሉት እንበል፤ አሁን ግን አቡነ መርቆሬዎስ ወደመንበራቸው ሊመለሱ አይገባም የሚሉት ጳጳሳት አላማቸው ምንድነው? የሚለው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ በተለይም «5ኛ ብለን ወደ4ኛ አንመለስም፤ 6ኛ ነው የምንለው» የሚለው ምላሽ ለአቡነ ጳውሎስ ክብር ከመጨነቅ የሚመነጭ እንዳልሆነ ታውቋል፡፡ ይህን መግለጫ የሰጡት አቡነ ህዝቅኤልን ጨምሮ ሲኖዶሱን እያናወጡ ያሉት ጥቂት አስቸጋሪ ጳጳሳት አቡነ ጳውሎስ የሾሟቸውና የአቡነ ጳውሎስ ተቃዋሚ ሆነው የዘለቁ ናቸው፡፡ ታዲያ ከእርሳቸው ህልፈት በኋላ ለምን እንዲህ አሉ? ይህን አቋምስ ለምን ያዙ ቢባል አንዱ ምክንያት ቀጣዩ ፓትርያርክ ለመሆን እየተሻኮቱ ስለሆነና የአቡነ መርቆሬዎስ ወደመንበራቸው መመለስ ነገሮችን ሊቀይርባቸው ስለሚችል ነው። እነዚህ ጳጳሳት የግል ጥቅማቸው እንጂ የቤተክርስቲያን አንድነት እንደማያሳስባቸው ግልጽ እያደረጉ ነው፡፡ በዝግ እየተከናወነ ባለው የእርቅ ስብሰባ ላይ በዚህ ልብ  ሲነጋገሩ ሰንብተዋል፡፡

እርቁን ለማውረድና የአገር ውስጥና የውጭ አገር ተብላ ለሁለት የተከፈለችውን ቤተክርስቲያን አንድ ለማድረግ ከጳጳሳቱ በተጨማሪ የራሳቸውን ጥቅምና ጉዳት አይተው እርቁ እንዳይደረግ የሚፈልጉ ወገኖች መኖራቸውም ግልጽ ነው፡፡ ከእነዚህ ክፍሎች መካከል አንዱ ማህበረ ቅዱሳን ነው፡፡ ማህበሩ ከሁለት የተከፈለችው ቤተክርስቲያን አንድ እንድትሆን ሳይሆን እንዲያውም መከፋፈሉ ወደሶስት እንዲያድግ በውጪው ዓለም እየሰራ ይገኛል፡፡ በውጭ የሚገኙትን አብያተ ክርስቲያናትን ለሁለት እየከፈለ ከውጭው ስኖዶስ ወደ ገለልተኝነት እየመራ ያለው ማቅ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ስለዚህ ከላይ የጠቀስናቸው ጳጳሳት እርቁን ሳይፈልጉ ለእርቅ እንደተቀመጡ ሁሉ፣ ማህበረ ቅዱሳንም በውስጡ የሁለቱን ሲኖዶሶች መታረቅ ሳይፈለግ በውጫዊ እንቅስቃሴው ግን እርቃቸውን የሚፈልግ መስሎ በተለይም በውጪው ዓለም የድጋፍ ፊርማ እስከማሰባሰብ የደረሰ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን በየድረገጾቹ ሰሞኑን ካወጣው ዘገባ መረዳት ተችሏል፡፡

በዚህ የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብ ሂደት ምክንያት ማቅ በግርግር በውጪው ዓለም የጀመረውን የውጪውን ሲኖዶስ የመከፋፈል ስትራቴጂ ወደፊት ለማራመድ ሊጠቀምበት ይችላል የሚለው ግምት አይሏል፡፡ በኢትዮጵያ ባለው ስኖዶስ ውስጥ  ያሉት አንዳንድ ሊቃነ ጳጳሳት የማቅ አጀንዳ አስፈጻሚዎች ናቸው፡፡ ማቅ በአገር ቤት ወደ ኋላ መመለስ የለብንም ወደ ስድተኛው ፓትርያርክ ነው መሄድ ያለብን የሚለውን እንደሚደግፍና ስድስተኛው እርሱ የሚፈልገውና አጀንዳውን የሚያስፈጽምለትን ፓትርያርክ ለማስቀመጥ በርካታ ሥራ እየሠራ ነው፡፡ ታዲያ በውጪው አለም ስለእርቅ እያወራና የድጋፍ ፊርማ እያሰባሰበ ያለው ለምን ይሆን የሚለው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ በአንዳንድ ቦታዎችም ተቃውሞ እየገጠመው መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ለምሳሌ Dec 2/2012 በካሊፎርኒያ ሳንሆዜ ደብረ ይባቤ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ከርስቲያን በማቅ ቀንደኛ አባል በሆነውና መቅደሱን እንደ ምሽግ ይዞ ሚገኘው በዲያቆን ተስፋዬ በኩል የድጋፍ ፊርማ ፎርሙ ላይ ፈርሙ እያለ ህዝበ ክርስቲያኑን በአውደ ምህረቱ ላይ ያውክ ውሏል። ህዝቡ እኛ በአገር ውስጥ ስኖዶስ የምንመራ ስለሆነ በተዋረድ የሚመጣውን መመሪያ በመቀበልና የእራሳችንንም ጥያቄ ወደ በላይ አካላት ማቅረብ አለብን እንጂ ማንም እየተነሳ ወረቀት እየጻፈ በመምጣት ፈርሙልን እያለ ለራሱ ጥቅምና አጃንዳ ህዝቡን ማወክ የለበትም በማለት አብዛኛው ህዝብ ቅሬታውን አሰምቷል፡፡ «እግዚአብሔር እርሱ ሰላሙን ያምጣልን» በማለትም ፈጣሪውን እየተማጸነ ጥሎዋቸው ወጥቷል ይህም የተቀነባበረው ቀድሞ የቤይ ኤርያ የቅንጅት አባል በነበረው በአቶ ዳምጠው በኩል  መሆኑ ሲታይ ማህበሩ አሁንም ሃይማኖትንና ፖለቲካን እያጣቀሰ የሚጓዝና በሃይማኖት በኩል ክፍተት ሲያገኝ ፖለቲካውን ለማራመድ እድሉን ከመጠቀም ወደኋላ እንደማይል ከዚህ ቀደም ባደረጋቸው እንቅስቃሴዎች ስራው ታውቋል፡፡

ማቅ እንዲህ ማድረጉ ባልከፋም ነበር፡፡ ትልቁ ጥያቄ የሁለቱን ሲኖዶሶች መታረቅና የቤተክርስቲያንን አንድነት በእርግጥ ይፈልገዋል ወይ? ነው፡፡ ማቅ ትናንትና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅን፣ ታላቁን ወንጌል ሰባኪ አባ ወልደትንሳኤን መምህር ልኡለቃልንና ሌሎችንም ታዋቂ መምህራን በስምአ ሐሰት ጋዜጣውና በሀመር መጽሔቱ በየድረገጾቹ ሁሉ መናፍቃን ናቸው እያለ ስማቸውን ሲያጠፋ ነበር፡፡ ከዚህ አንጻርም ማቅ እርቁን እንደማይፈልግ ይታወቃል፡፡ ምክንያቱም እርቁ ተሳክቶ ቤተክርስቲያን አንድ ከሆነች ስማቸውን አለአግባብ ያጠፋባቸው ታላላቅ አባቶችና መምህራንም እንደአስፈላጊቱ ወደአገር ቤት ሊመለሱ በውጭም ሆነው በአንዲቱ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሊያገለግሉ ነውና ይህ ለማቅ ትልቅ ፈተና ነው የሚሆንበት፡፡ ምክንያቱም እነዚህ አባቶችና መምህራን የማቅን የተሳሳተ አካሄድ በወንጌል ብርሃን እርቃኑን አስቀርተዋልና አብረው ሊሰሩ የሚችሉበት እድል የጠበበ ነው ሊሆን የሚችለው፡፡ ስለዚህ ማቅ እርቁ ሳይካሄድ ልዩነቱ ቢቀጥል ለእርሱ ጥሩ እድል ይፈጠርለታል፡፡
   

11 comments:

 1. «5ኛ ብለን ወደ 4ኛ አንመለስም፤ 6ኛ ነው የምንለው» ከታመነበት ይኸ ቃል የቤተ ክርስቲያን ዶግማ ነው ወይስ ቀኖና መሻር የሚያስቸግርበት ? ለምን ዘጠኝ ብለን ሁለት ወይም ሦስት ብለን ሰባት አንልም ካስፈለገ ? ይኸ የቁጥር ቅደም ተከተል መጠበቅ ከእምነትና ከቤተ ክርስቲያን ደኀንነትና ሰላም ጋር ምን አቆላለፈው ? አፈርኩ ክርስቲያን ነን ብለው መስቀሉን በደረታቸው ተሸክመው ለሚታወቁበት መሪዎቻችን ፡፡ ይቅር ሳትባባል መባህን አታቅርብ ብሎ ራሱ ጌታ ተናግሮና አስተምሮ ፣ ይህችን የመንደር አተካራ እንኳን ደፍነው ማለፍ ተሳናቸው ፡፡

  የክርስትናችን መደምደሚያ ሁለቱም ታላላቅ ትእዛዛት፣ የፍቅር ትእዛዛት ናቸው
  1.ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ። 2.ባልንጀራህን እንደ ራስህ/እንደ ነፍስህ ውደድ አለው። ማቴ 22፡37-39 ፣ ሉቃ 1ዐ፡27

  የራሳችንንና የነፍሳችንን ያህል የምንወድበት ፍቅር በልባችን ውስጥ ካለን እንደምን መሸናነፍ ያስቸግረናል ? መውደድ ማለት የጥላቻ መንፈስን ከህሊናችን ፈጽሞ ማስወገድ ማለት ነው ፡፡ ሰውን ከነድክመቱና ከነጥፋቱ ፣ ከነጽቁና ከነኃጢአቱ እንዳለ ምንም ሳይመዝኑና ሳይመረምሩ በሙሉ ልብ መቀበል ፤ መውደድ ፤ በደልን አለመተሳሰብ ፤ ኃጢአትን አለማስተዋል ...

  አሁንም ቀኑ አልመሸምና እግዚአብሔር ለእኛ ለደንቆሮዎቹ የገለጠውን ፣ ለእናንተም ልቦናችሁን እንዲከፍትላችሁ እጸልያለሁ ፡፡

  ReplyDelete
 2. mechem mehabrekidusan letshufacheh hulu matafecha chewna kemem eyadergachut new. enante gin men eyeserachihu new?????????????????

  ReplyDelete
 3. bretu mlekam new zegebachu

  ReplyDelete
 4. endeat yehun ye egnam tesefa mk, kebeatekeresteyan guazzun yezo yemelekebeten ken new men ale abatoche beshenefu moten bayersu yeselam amkak selamun yametalen....

  ReplyDelete
 5. ye aba selama blog focal point mk new yasekal lenegeroch hulu mk mekniat adergachehu eskemech endemtnoru aygebagnem eskemech blogu ye alublta belog hono endemiketel aygebagnem lemanegnawem gena bezu asekign neger endemtasnebebun enamnalen yebuna were be internet liawem be aba selama blog lay

  ReplyDelete
 6. በእውነት እግዚአብሔር ይስጣችሁ ሐቁን በማጣታችሁ እጅግ ደስ አሰኛችሁን።እባካችሁ አሁንም የማቅን ጥፋትና ተንኮሉን ከማውጣት ወደ ሗላ እንዳትሉ። የቀደመው እባብ አሁን በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ መሽጎዋል። በድንግል ማርያም ልጅ በአማኑኤል ደም በመቅደስ ውስጥ እየነገደበት ስለሆን እዉነቱ መውጣት አለበት። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መቼ ነው አንድነቱዋን የሚታሳየው? አዎ መልሱ የማቅ ጳጳሳት ከስኖዶስ ዉስጥ ስነቀሉ ብቻ ነው። የተዋህዶ ትንሳኤዋን ልናይ የሚንችለው። ሰላም እንድሁ በከንቱ አይመጣም። በስብሰባም ብዛት ሰላም ለተዋህዶ ልጆች አይገኝም። ማቅ ስነቅል ብቻ ሰላም ፍቅር አንድነት የምናገኘው።

  ReplyDelete
 7. ስለ አቡነ መርቆርዮስ መመለስ ግልጽ ደብዳቤ የጻፉትን የፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስን ሐሳብ አስመልክተው ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጣቢያ ቃለ ምልልስ የሰጡት ዐቃቤ መንበረ ሐላፍ አቡነ ናትናኤል ከትናንት በስቲያ አርብ “ፓትርያርኩ በተወሰነላቸው ቦታ እንዲቀመጡና ለአገራቸው አፈር እንዲበቁ” እንጂ በመንበራቸው ሙሉ ስልጣናቸው አያገኙም በማለት የማህበረ ቅዱሳን አጀንዳ ተናግረዋል። የአዲስ አበባው ስኖዶስ እንድህ አይነት አቋም ካላቸው ስብሰባው ለምን ማድረግ አስፈለጋቸው? ይህ እኮ የማቅ አጀንዳ ነው። ለምን ሕዝበ ከርስቲያኑን ያታልላሉ? እጅግ በጣም ያሳዝናል የማቅ ሊቃነ ጳጳሳቱ እየፈጸመ ያሉት። የሰላም አምላክ እግዚአብሔር እርሱ በፈቀደው ሰዓት ሰለሙን ያምጣልን።

  ReplyDelete
 8. Hulun yemiyawk geta amlak esu begizew hulun yastekakilewalna yegna dirsha lebalebetu metew newu. Hulunim Egziabher begizew yastekakilew. Amen.

  ReplyDelete
 9. it is very tragic to hear the failure of the long term expected negotiation to bring about unification among the two synods of the Ethiopian Orthodox church. In my opinion the clergy fathers particularly here in Ethiopia seem to stand for running for power just like the secular leaders do so.They are not totally governed by the spiritual will of God and are not abide by the Gospel. What will their being a model to the followers. They are not worrying for the unity of their church, they are completely influenced with political affiliations existing in the country that is a system driven by ethnic based attitude. But you should also be very careful for yourselves from on wards your representation to the church as well as the respection from God and the followers will be in question because you intentionally contribute the division to continue for unlimmitted period of time and this in turn may put the followers to be driven towards either the synod in abroad or other religious groups that may leave you assigned for nothing.This will in turn may put you accountable for losing being a shepherd for the crowds according to the Gospel.Before you become a bishop you need to have the fear of God in your heart and be obedient to God rather than for secular or earthly leaders.
  May God give us the unity we deserve for long to our church.

  ReplyDelete