Thursday, December 27, 2012

አናንያ አዛርያ ሚሳኤልን ከእሳት ያወጣው ማነው? ገብርኤል ወይስ ሚካኤል? ወይስ እግዚአብሔር?

“የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።” መዝ. 33፡7፡፡ ይህ ጥቅስ የእግዚአብሔር መልአክ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ሰዎች ከእግዚአብሔር ተልኮ በዙሪያቸው ሆኖ ከመከራ እንደሚያድናቸው ያስተምራል፡፡ የመላእክት አንዱ ተግባር መዳንን ይወርሱ ዘንድ ያላቸውን ሰዎች መጠበቅ መሆኑ ተጽፏል፡፡ “ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?” ዕብ. 1፡14፡፡
የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ስለሚል እግዚአብሔር ገብርኤልን ልኮ አናንያ አዛርያ ሚሳኤልን ከእሳቱ ሊያድን እንደሚችል አምናለሁ፡፡ ነገር ግን በሶስቱ ወጣቶች ታሪክ ውስጥ እንደምናነበው ወጣቶቹን ለጣኦት አንሰግድም በማለታቸው ከተጣሉበት እሳት ውስጥ ያዳናቸው ገብርኤል መሆኑ አልተጻፈም። ያዳናቸው እግዚአብሔር ነው፡፡ ገብርኤልንም ልኮ እንኳን ቢሆን አዳነ የሚባለው እግዚአብሔር ነው፡፡ እኛ በግድ ገብርኤል ነው ያዳናችሁ ብንላቸውም አናንያ አዛርያ ሚሳኤል ግን “የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል ከእጅህም ያድነናል፥ ንጉሥ ሆይ! ነገር ግን፥ ንጉሥ ሆይ፥ እርሱ ባያድነን፥ አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ አሉት።” ነው የሚለው፡፡ ዳን. 3፡18-19፡፡ ይህም የሚያስተምረን መልአኩንም ልኮ ሆነ ሳይልክ የሚያድን እግዚአብሔር መሆኑን ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን “የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ አማካሪዎቹንም። ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን? ብሎ ተናገራቸው። እርሱም፦ ንጉሥ ሆይ፥ እውነት ነው ብለው ለንጉሡ መለሱለት። እርሱም፦ እነሆ፥ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ ምንም አላቈሰላቸውም የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል ብሎ መለሰ።” ዳን. 3፡24-25፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ገብርኤል ተልኮ የፈጸመውን ተልእኮ ገብርኤል ነው ብሎ ይናገራል፡፡ ሚካኤልም ከሆነ ሚካኤል ነው ይላል፡፡ ለምሳሌ ድንግል ማርያምን ያበሰራት ገብርኤል መሆኑ ተጽፏል፡፡ ስለ ሙሴ ስጋ ከዲያብሎስ ጋር የተከራከረው ሚካኤል መሆኑ ተጽፏል፡፡ ከዚህ ውጪ ገብርኤል ያልሰራውን ገብርኤል ነው፤ ሚካኤል ያልሰራውን ሚካኤል ነው ማለት ለምን እንዳስፈለገ አይገባኝም፡፡ ለምሳሌ እስራኤልን የመራቸው ራሱ እግዚአብሔር ሆኖ እያለ፣ መና እያወረደ የመገባቸውም ራሱ እግዚአብሔር ሆኖ እያለ ሚካኤል ነው እየተባለ ሲነገረን ኖሯል፡፡ እንዲህ የሚለው ድርሳነ ሚካኤል ነው እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ግን ሚካኤል ነው ብሎ በአንድም ስፍራ አይናገርም፡፡ ስለዚህ ያልተጻፈውን በማንበብ የእግዚአብሔርን ሥራ ለሚካኤል ሰጥተናል ማለት ነው፡፡ ይህም ሚካኤልን ወደማምለክ ነው የመራን፡፡ በነገራችን ላይ የታህሳስ ድርሳነ ሚካኤል ሶስቱን ወጣቶች ከሚነደው እሳት ያዳናቸው ሚካኤል ነው ይላል፡፡ ድርሳነ ገብርኤል ደግሞ ገብርኤል ነው ይላል፡፡ ታዲያ የቱ ነው ልክ? መጽሐፍ ቅዱስ ግን “የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል” እንጂ ሚካኤል ወይም ገብርኤል ነው አይልም፡፡ ታዲያ ለምን ይዋሻል?
እንደዚህ አይነቶቹ ትምህርቶች በመላእክት ስም ለመነገድና በበኣላቸው ቀን ብዙ ገንዘብ ለማግኘት እነ ሆድአምላኩ የፈጠሩት ትምህርት ነው፡፡ ታህሳስ 19 ቁሉቢ የሚሄደው ሰው ስፍር ቁጥር የለውም፡፡ ለዚያውም በስለት ስም ተስያለሁ በሚል ለጭፈራ፣ ለማመንዘር የሚሄዱና “ስለ ስለት” የሚሉ በርካቶች እንደሆኑ ይነገራል፡፡ ይህም ከአህዛብ የተወረሰ ልማድ ነው፡፡ በአሕዛብ የጣኦት አምልኮ ውስጥ ከሚፈጸሙ ተግባራት አንዱ ዝሙት ነው፡፡ ቁሉቢ ገብርኤልም ተመሳሳይ ነገር ይፈጸማል ነው የሚባለው፡፡ በአንጻሩ በጥር ሥላሴ በዓል ላይ የሚገኘው ሰው ጥቂት ነው፡፡ እንኳን ሊገኝ የሥላሴ በዓል መሆኑን የሚያውቁ ከነመኖራቸውም ያጠራጥራል፡፡ አዋልድ የተረት መጻህፍቶች ህዝቡን ምን ያህል እያሳቱትና ከፈጣሪው እየለዩት እንደሆነ ከዚህ መገመት ይቻላል፡፡  እስከ መቼ ይሆን ፈጣሪን ትተን ፍጡርን የምናመልከው? ኧረ እባካችሁ እንመለስ? በመላእክት ስም አምልኮትን ለሰይጣን መስጠቱ፣ ራስን ማርከሱ፣ መነገዱም ይብቃ፡፡
ከጸጋ ታደለ

35 comments:

 1. 1- “የእግዚአብሔር መልአክ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ሰዎች ከእግዚአብሔር ተልኮ በዙሪያቸው ሆኖ ከመከራ እንደሚያድናቸው ያስተምራል፡፡ መዝ 33፡7” … “የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ስለሚል እግዚአብሔር ገብርኤልን ልኮ አናንያ አዛርያ ሚሳኤልን ከእሳቱ ሊያድን እንደሚችል አምናለሁ፡፡”

  ወንድም ጸጋ እናንተ ሲመስላችሁና ሲመቻችሁ የፈለጋችሁትን ልትጽፉና ልታጣቅሱ ፤ እኛ ደግሞ ይራዱናል ፣ ጸሎታችንን ያሳርጉልናል ፣ እግዚአብሔር በነርሱ በኩል ይሰማናል ፣ ያግዘናል ፣ ያድነናል ስንል “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለም።” /ሥራ 4:12/ ይላል እያላችሁ ልታሳክሩን ፤ እንዴት ያለ በወንጌል ትምህርት መቀለድ ነው የተያዘው ? እንዲህ የምታመን ከሆነ እስከ ዛሬ ስለምን ሲባል ብዙውን ሰው አንተና ብጤዎችህ ለማሳሳት ታገላችሁ ? በል አሁኑኑ ንስሐ ግባ ፡፡

  2- እነሆ፥ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ ምንም አላቈሰላቸውም የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል ብሎ መለሰ።” ዳን. 3፡25፡፡

  ወንጌል “ከሙታንስ ሲነሡ በሰማያት እንዳሉ መላእክት ይሆናሉ እንጂ አያገቡም፥ አይጋቡምም።” ማር 12፡25 ፤ ማቴ 22፡3ዐ ፤ ሉቃ 2ዐ፡35 ይላልና ፣ ታድያ አማልክት ከየት የመጣ ልጅ ይኖራቸዋል ብለህ ታስባለህ ? እምነቱ የፈቀደው ዓይነት ቢሆንም ፣ ንጉሥ በመሆኑ የተናገረው ቃል በሙሉ ትክክል ነው ወይንስ ከመላእክት አንዱ መባል ይገባዋል ፡፡ ስለዚህም እንደ ወንጌል ቃል አማልክት ልጅ አይኖራቸውምና ስህተትን አምጥተህ የቤተ ክርስቲያን ትምህርትን ለማረቅ አትድከም ፡፡

  3- “እስራኤልን የመራቸው ራሱ እግዚአብሔር ሆኖ እያለ፣ መና እያወረደ የመገባቸውም ራሱ እግዚአብሔር ሆኖ እያለ ሚካኤል ነው እየተባለ ሲነገረን ኖሯል፡፡”

  እግዚብሔር እስራኤላውያንን ነጻ ለማውጣትና ወደ ቃል ኪዳኗ አገር ለማስገባት የተጠቀመው ሙሉ በሙሉ መልአኩን ነው ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር እየመራ እንዲያ እንዲህ አይልም ፡፡ ቃሉን በቀጥታ እንደ ተጻፈ እናንብበው ፡-
  - “በእስራኤልም ሠራዊት ፊት ይሄድ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ ፈቀቅ ብሎ በኋላቸው ሄደ፤ የደመናውም ዓምድ ከፊታቸው ፈቀቅ ብሎ በኋላቸው ቆመ፥ በግብፃውያን ሰፈርና በእስራኤል ሰፈር መካከልም ገባ፤ በዚያም ደመናና ጨለማ ነበረ፥ በዚህ በኩል ግን ሌሊቱን አበራ፤ ሌሊቱንም ሁሉ እርስ በእርሳቸው አልተቃረቡም።” ዘጸ 14፡19-2ዐ

  - በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ። በፊቱ ተጠንቀቁ፥ ቃሉንም አድምጡ፤ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት። ዘጸ 23፡2ዐ-21

  - አንገተ ደንዳና ሕዝብ ስለ ሆንህ በመንገድ ላይ እንዳላጠፋህ እኔ በአንተ መካከል አልወጣምና በፊትህ መልአክ እሰድዳለሁ ዘጸ 33፡2

  - ወደ እግዚአብሔርም በጮኽን ጊዜ ድምፃችንን ሰማ፥ መልአክንም ሰድዶ ከግብፅ አወጣን፤ ዘኁ 2ዐ፡16

  ስለዚህ ያልተጻፈውን ሳይሆን የተጻፈውን በሥርዓቱ ለማንበብ ፈቃዱ የለህም ፤ ወይንም ለመንቀፍ ብለህ ስለምታነበንበው የተጻፈው አይታይህም ፡፡ የደረደርኩልህ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሠፈረውን ቃል ነው ፡፡
  እግዚአብሔር ይርዳን

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምእመን አስተያየትህ በምእመን ደረጃ የተሰጠ ስለሆነ ብዙም አይገድም፡፡ ጸጋ እኮ አንተ ያልከውን አላለም፡፡ እርሱ ያለው ዳንኤል 3 ላይ ገብርኤል አልተጠቀሰም፡፡ ከየት አምጥተን ነው ገብርኤል የምንለው እያለ ነው፡፡ ለዚህ መልስ ካለህ በቀጥታ መልስ፡፡ ደግሞም ድርሳነ ሚካኤል ይህንኑ ታሪክ ለሚካኤል ሰጥቶት ይገኛልና ይህንስ እንዴት ማስታረቅ ይቻላል? ስለዚህ ምእመን ይህን ጥያቄ ለመመለስ ደረጃህ ባይፈቅድልህም አንዴ ግብተህበታልና እንደምንም ብለህ ተወጣው፡፡ ካልሆነ ሊቃውንትን ጠይቅ፡፡

   Delete
  2. ለ AnonymousDecember 28, 2012 10:26 AM
   ጸጋ ያለውን ለማለቴ እንዳይጨናበር በማለት ለቃሉ ወይም አባባሉ ቁጥር እየሰጠሁ ደግሜአለሁ ፡፡ ጸጋ ከሆንክ አይ እኔ አላልኩም ወይም እንዲህ ለማለት ፈልጌና አስቤ አይደለም በልና ይቅርታ በል ፡፡ ድሮ ሲያዞርብኝ የነበረውን ዛሬ አምናለሁ ብሎ ሲጽፍ አንተ ምንም በማታውቀው ምስክር አትሁን ፡፡

   በተረፈ በደረጃ ዝቅ ማለቴም ይሁን መግባትና መውጣቴ ባልከፋኝም ነበር ፡፡ እኔን እየመከርክ ግን ስለምን መጀመሪያ ነገር የገባህ ሊቅ ሰው ፣ አንተው አታደርገውምና መልሱን አታስነብበኝም ? ስለምንስ እንቆቅልሽ እያመጣችሁ በተራ አማኝ ላይ ጥርጣሬንና እንክርዳድን ትዘራላችሁ ? እንደ ቃልህ ስለምን ሊቃውንትንና አባቶችን እየጠየቃችሁ የተሰጣችሁትን መልስ የስም አስረጅ እየጠቀሳችሁ ለንባብ አታቀርቡትም ? አሁን ከእሳት ማውጣት የገብርኤል ሆነ የሚካኤል ሥራ ለይቶ ማውቁ በእኔ መዳን ላይ ምን ለውጥ ያመጣልና ይሄንን የቤት ሥራ አደረግህልኝ ?

   እንዲያው በመሃይምነቴ ካልተበሳጨህብኝና አወጣጡ ላንተም ካላስቸገረህ ትንሽ የመጽሐፍ ቃል ላስነብብህ ፡፡ የመላእክት እገዛ የሚያስፈልገው ባይሆንም እንኳን ምን ያህል እንደሆነ እንድትረዳው ለማለት ፡-

   1. ኢየሱስ በጾም በቆየበትና በሰይጣን በተፈተነበት ወቅት ፡፡
   - "በምድረ በዳም ከሰይጣን እየተፈተነ አርባ ቀን ሰነበተ ከአራዊትም ጋር ነበረ፥ መላእክቱም አገለገሉት።" ማር 1፡13
   - "ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው። ያን ጊዜ ኢየሱስ። ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና አለው። ያን ጊዜ ዲያቢሎስ ተወው፥ እነሆም፥ መላእክት ቀርበው ያገለግሉት ነበር።" ማቴ 4፡9-11 (ተርቦና ተጠምቶ በደከመበት ሰዓት ሊረዱት መሆኑን ልብ በል ፤ መግባባት እንድንችል በማለት ነውና ስለ ቃላት አጠቃቀሜ ለደንቡ ያህል ይቅርታ ፤ ደሞም ስለ እኛ ሲል ያልሆነው የለምና ብዙ አትጨነቅ)

   2. ኢየሱስን መከራ ባጋጠመውና በጸሎት በተጋበት ሰዓት
   - "ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር። ከሰማይም መጥቶ የሚያበረታ መልአክ ታየው።" ሉቃ 22፡42-43 (ጌታችን በባሕርዩ ሰንፎና ደክሞ ባይሆንም ፣ ጌታ በተጨነቀበት ሰዓት መልአክ ሊያበረታው ታይቶታል)
   - "ወይስ አባቴን እንድለምን እርሱም አሁን ከአሥራ ሁለት ጭፍሮች የሚበዙ መላእክት እንዲሰድልኝ የማይቻል ይመስልሃልን?" ማቴ 26፡53 (በራሱ ከነርሱ በላይ የፈቀደውን ማድረግ እየቻለ ፣ የመላእክትን ተራዳኢነትና ችሎታቸው እስከ ምን ድረስ እንደሆነ መግለጹን እናስተውል )

   አቤቱ ጌታዬ እነ ጰውሎስ አንተን እግር በእግር ተከትለው ሳይማሩ ፣ በመገለጽጥ ሊቅ አድርገሃቸዋልና ለእኔም ለደካማው ምስጢርህን እደርስበት ዘንድ እርዳኝ ፡፡ አሜን!!!

   Delete
 2. "የምታመሌኩትን ዛሬ ምረጡ እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመሌካሇን እርሱ ቅደስ ነውና"
  It's ok,...let us go in the path we chose as a belief. If u don't believe it,...u don't have 2 worry about it. አንተ በእግዚአብሔር ካመንክ: በድንቅ ስራውም ጥርጥር ሊገባህ ባልተገባ ነበር:: ምክንያቱም መላእክቶቹ ሚሰሩት ሁሉ ስለስማቸውና ስለክብራቸው ሳይሆን ስለ አምላካቸው ክብር ነው:: እርሱም በነሱ አድሮ ድንቅ ይሰራል:: ለዛ ነው እያንዳንዱ ስራቸው አምላካቸውን ስለሚገልጽ ገብርኤል አዳናቸው ስንል እግዚአብሔር አዳናቸው እያልን ጭምር ነው!! ፈጣሪን ትተን ፍጡር አናመልክም አምልከንም አናውቅም:: አምልኮት ምስጋና እና የአምልኮት ስግደት ለእግዚአብሔር ብቻ የጸጋ ስግደትና ምስጋና ደሞ እርሱ ለወደዳቸው: ለጠራችው: ላከበራቸውና ላጸደቃቸው የምንሰጠው!
  በእውነቱ ከሆነ እኛ እጻድቃንና ለጌታ መላእክቶ በምንሰጠው ክብር ደስ የማይለውና ሁሌ ይህን ሚቃወመው ማን እንደሆን ታውቃለህ? አዳምን በቅናት ያሳሳተው ጥንተ ጠላታችን ሰይጣን ነው:: አንተ ከማ ወገን ትሆን ወንድሜ???እኔው እብድ ነኝ ከወፍ የገበየሁ....አለ ያገሬ ሰው! የኔው ስህተት ነው ከመናፍቅ አገር መምጣቴ::ከዝንብ ማር እንደማይገኝ ሁሉ ከዚህም website ህይወት የሚሰጥ የህይወት ቃል አይገኝበትም: ከምንፍቅና እና ከሃሰት ቃል በስተቀር::

  ReplyDelete
 3. whta are you talking TSEGA,,,, R U menafik? or real kiristiyan?

  ReplyDelete
 4. ፕሮቴስታንቱ እኮ ገብርዔል መሆኑን ተቀብለዋል:: ጽፈውታልም:: እባክህ ከመጻፍህ በፊት በደንብ አንብብ::እንግሊዝኛ የማትችል ከሆነ ደግሞ እንተረጉምልሀለን::

  ReplyDelete
  Replies
  1. ፕሮቴስታንት የክርስትና ማረጋገጫ አይደለም፡፡ ቁምነገሩ መጽሐፍ ቅዱስ ዳንኤል 3 ላይ ገብርኤልን ጠቅሷል ወይ ነው? ካልተጠቀሰ አልጠቀሰም፡፡ ድርሳነ ሚካኤል ደግሞ ሚካኤል ነው ያለውንስ ምነው አለፍነው? ድርሳናት ተሳስተዋል ማለት መቻል እኮ አለብን?

   Delete
  2. ለ AnonymousDecember 28, 2012 10:22 AM
   አባቶች ተቀባብለው ያደረሱንን የሃይማኖት መጽሐፍት ፣ ምሥጢሩን ሳናውቅና ሳንረዳ ፣ ቃል ስላልተጣጣመልን ብቻ ገድላትና ድርሳናት ተሳስተዋል የሚል መግለጫ አናወጣም ፡፡ ያንን ማለትና ማድረግ የሚችሉት ፣ ሆነም ቀረ ቤተ ክርስቲያንን የሚመሩ አባቶች ብቻ ናቸው ፡፡ እንዲያ እንንቀስ ካልን መጽሐፍ ቅዱስም ላይ ብዙ የማይገጣጠም እጅግ ቃል እናገኛለን ፡፡

   - በማቴዎስ (1፡16) የዮሴፍ አባት ያዕቆብ በሉቃስ (3፡23) ግን የዮሴፍ አባት ዔሊ ነው (ሁለቱም የሚገልጹት አንዱን ዮሴፍን ነው ታድያ እንዴት ታስማማው)

   - መከረኛው በመጥፎ የሚመሰለው ይሁዳን ማቴዎስ (27፡5) ታንቆ ሞተ ሲለን ፣ በሐዋርያት ሥራ (1፡18) በግንባሩም ተደፍቶ ከመካከሉ ተሰነጠቀ አንጀቱም ሁሉ ተዘረገፈ፤ ይለናል (እንዴት አስማምተህ ትገልጸዋለህ)

   - ከሐዋርያው ጳውሎስ ጋር አብረው የነበሩ ሰዎችን ማስረጃ አድርጎ ሲተርክ ሥራ (1፡7) “ከእርሱም ጋር በመንገድ የሄዱ ሰዎች ድምፁን እየሰሙ ማንን ግን ሳያዩ እንደ ዲዳዎች ቁሙ።” በ(22፡9) ላይ ደግሞ “ከእኔ ጋር የነበሩትም ብርሃኑን አይተው ፈሩ፥ የሚናገረኝን የእርሱን ድምፅ ግን አልሰሙም።” በማለት ይገልጻል ፡፡ በሥራ (26፡13-14) ደግሞ እንደ አዲስ ታሪክ “እኔ በዙሪያችን ብርሃን ሲበራ አየሁ ፤ ሁላችን በወደቅን ጊዜ ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል የሚል ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ሲናገረኝ ሰማሁ።”

   አንዱ ጸሐፊ ቀደም ሰሙ ግን አላዩም ብሎ ሲያበቃ ፤ እልፍ ብሎ ደግሞ አዩ ግን አልሰሙም ወይም በሦስተኛውም ሌላ ታሪክ የሚመስል ስላስነበበን ብቻ መጽሐፉ ተሳስቷል ልንል አይገባም ፡፡ ይኸን አይነቱን እንቆቅልሽ እኔ ራሴ ስላልገባኝ ነው ብዬ ነው በአጭር ቋንቋ የምዘጋው ፡፡ ከሁለት ሺህ ዓመት በፊት የጻፈው ሰው ተሳስቷል ለማለት ቀድሞ እሱንና በእርሱ ደረጃ መሆን ያስፈልጋል ፡፡

   እንዲሁ ብንቀጥል ብዙ ማለት እንችላለን ፡፡ ግን ለማንኛችንም ደካማ አማኞች አይረባንም ፡፡ የሃይማኖት ትምህርት ፣ እያንዳንዱን ቃል እየመረመርን ፣ ትክክል ነው አይደለም እያልንና እያጣራን ፣ የምናምነው ወይም የምንክደው ሳይሆን ፣ በየዋኀነት አባቶች ያስተማሩን ሁሉ እውነት ነው ብለን የምንቀበለው የመዳን ትምህርት ነው ፡፡

   እግዚብሔር በጐደለ ይሙላበት
   Delete
 5. የተኛዉንም የ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይን ብትጠይቅ አናንያ አዛርያ ሚሳኤልን ያዳናቸዉ እግዚአብሔር እንደሚል እርግጠኛ ነኝ፡፡ እግዚአብሔር ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ ከእሳት አዳናቸዉ እንጂ ቅዱስ ገብርኤል አዳናቸዉ የሚል ኦርቶዶክስ የለም ልጅ ጸጋ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምነው ታዲያ እግዚአብሔርን ሲያከብር አይታይ? እያከበረ ያለው እኮ የታምራት ባለቤት የሆነውን እግዚአብሔርን ሳይሆን ገብርኤልን ነው፡፡

   Delete
  2. ለ AnonymousDecember 28, 2012 10:16 AM

   አንተ እግዚአብሔርን ስታከብር ፣ ምን ምንድር ነው የምታደርገው ? ስሙን መጥራትና መቀደስ ፣ መባረክ ፣ ማወደስ ብቻ ከሆነ በየቤተ ክርስቲያኑ እየተከናወነ ነው ፡፡ ከርሱ በዘለለ ለመላእክቱም ምስጋና ይቀርባል ፡፡ ብዙ አዋቂ ስትሆን መላእክት ሲከበሩ እግዚአብሔርን ማክበር መሆኑ ስለምን ይጠፋሃል ?

   እስቲ ይህችን ዘር መርምራትና ተመለስ ፡፡ “በፊቱ ተጠንቀቁ፥ ቃሉንም አድምጡ፤ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት።” ዘጸ 23፡21
   ስሜ በእርሱ ስለ ሆነ ማለቱ ገብርኤል ብንል ወይንም ሚካኤል ...፣ በነርሱ ስም ጥሪና ምስጋና ውስጥ እግዚአብሔር አለ ፡፡ “ኤል” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን የሚያመለክት ነው ፡፡ ለመሆኑ መንጋ ማስደንበር ነው ወይንስ እንዲያው ሳይገለጥልህ ቀርቶ እንዲህ በየቦታው

   እግዚአብሔር ይርዳን

   Delete
  3. ቃለህይወት ያሰማልን ምእመን፡፡ ለተጋረደባቸዉም እግዚአብሔር ይግለጥላቸዉ፡፡ አሜን፡፡

   Delete
 6. you are right i Agree

  ReplyDelete
 7. ክፍል 2
  በአንጻሩ ደግሞ ሥልጣኑ የፈጣሪ ነው ማለት መላእክት ‹‹ይህን ሠሩ›› አይባልም ማለት አይደለም፡፡ ፈጣሪ በመላእክት ሲሠራ መላእክትን እንደ ቁስ ቆጥሮ ይሠራባቸዋል ማለት አይደለም፡፡ መላእክት ሕያዋን ናቸው፡፡ የማዘንና የመደሰት ስሜት አላቸው፡፡ ያ ባይሆን ኖሮ ንስሐ በሚገባ ኃጢአተኛ ደስ እንደሚላቸው አይጻፍም

   

  በቅዱሳን መላእክት ማዳንና ተራዳኢነት ውስጥ የእግዚአብሔር ሥልጣንና አዛዥነት በረቂቅ አለበት፡፡ እግዚአብሔር ሰዎችን ለማዳን በምንም መንገድ ቢሠራ በዛ ውስጥ የእርሱ ሥልጣንና ሥራ የማይጠረጠር ነው፡፡ መላእክት ያለ ፈጣሪ ትእዛዝና ፈቃድ አንዳች ሊሠሩ አይችሉም፡፡ ፈጣሪ ግን ያለ መላእክት አጋዥነት የፈለገውን የሚሠራ ሁሉን ቻይ አምላክ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ፈጣሪ ይህን ሠራ ስንል መላእክትን ላይጨምር ይችላል፡፡ መላእክት ይህን አደረጉ ስንል ግን በምንም ተአምር ከፈጣሪ ውጭ ሊሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ መናፍቃን ‹‹ጌታ፣ እግዚአብሔር ይህን አደረገ›› ብቻ እንድንል የሚፈልጉት ቅዱሳንን ላለማስገባት ነው፡፡ እኛ ኦርቶዶክሳዊያን ቅዱሳን መላእክትንና ቅዱሳን ሰዎችን ይህን አደረጉ የምንለው እግዚአብሔርን ከማመን ጋር ስለ ቅዱሳን ክብር ለመመስከር ነው፡፡

   

  እሳት በባሕርይው የሚፋጅ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እንጨትና ብረት ግን ብቻቸውን ሳሉ ቢነኳቸው አያቃጥሉም፡፡ ነገር ግን ከእሳት ጋር ከተዋሐዱ /ከጋሉ/ በኋላ ቢነኳቸው ይፋጃሉ፡፡  እሳት የተዋሐደው ብረት የማያቃጥልበት ምንም ሁኔታ የለም፡፡ ካላቃጠለ ወይ እሳት አልተዋሐደውም ወይም ደግሞ እሳቱ ራሱ አያቃጥልም ማለት ነው፡፡ እንደዚሁም እግዚአብሔር በባሕርይው አዳኝ ነው፡፡ መላእክት አያድኑም ካልን ወይ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር አይደለም ማለት ነው ወይም ደግሞ እግዚአብሔር ራሱ አያድንም እንደማለት ይቆጠርብናል፡፡ ስለዚህ ‹‹መላእክት ያድናሉ›› ስንል የሚያድን እግዚአብሔር ከእነርሱ እንደማይለይ እየመሰከርን መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡

   

   

  የእግዚአብሔር ቸርነት

  የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት አይለየን!

  Ben

   

  ዲያቆን ኅብረት የሺጥላ

  ሌሎቹን ጽሑፎች ለማንበብ ከፈለጉ በዚህ ሊንክ http://www.facebook.com/hibrety?sk=notes ይፈልጓቸው!

  ReplyDelete
 8. match the foolowing(tehadso,selefis,protestants,mkidusan, bete-khnet,liberal) with below characters. you can choose more than one choice from above groups for one below character) ........ 1.ወጨጌ
  ቃሉ ብዙ ትርጓሜና ተርጓሚ ቢኖረውም (ከርዐሰ ጉዳያችን ስለሚወጣ ዘልዬዋለው፡፡) ለዘመናችን አንድ ጎጥ መጠሪያነት ውሏል፡፡ ጥንተ ምዕላዱ ሆዳም ደብተራዎች ከዳዊት ድጋም አልቀው ከሚቀጽሉትና አንድ ወፍራም አንቀጽ ከሚወጣው የአቡነ ጳዉሎስ የማዕረግ ስም የተወሰደ ነው፡፡ነጠላ በመልበስና ረዘም ያለ መግቢያም መውጫም ያለው የማዕድ ጸሎት በማድረግ ይታወቃሉ፡፡ሀገራዊ እምቅ ዕውቀት እና ፍልስፍና እንዳለ በደመ ነፍስ ይከራከራሉ፡፡ አብዛኞቹ ግን ለሀገርኛው ዕውቀት (ለነገረ መለኮትም ሆነ ለቱባው ትውፊታዊ ትምህርት)ባዕድ ናቸው፡፡ከቅብጥ የሀይማኖት ምሁራን በቀር ሌሎችን ለመስማት ፍቃደኛ አይደሉም ፤ እዚህም የሚደርሱት የበረቱት ናቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቷ ያለችበት ዘርፈ ብዙ ችግር ግራ መጋባት ውስጥ ከቷቸዋል፡፡ደብተራውን ፈንግለው ወይም በትውፊት፣ በህግ እና በስርዓት ጠፍረው የኔ የሚሏትን ቤተ ክርስቲያን በባለቤትነት ከመርዳት ይልቅ በቤተ ክህነቱ በሚታየው ምግባረ ብልሹነት ሙድ ይይዛሉ፡፡ የኢትዮጵያን አማኝ ማኀበረሰብ ያልተረዱት ኢአማኒያን የፈጠሩት ወከባ በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ እንዲሉ ለሀገር ሆነ ለቤተ ክርስተያኒቷ የደማ አገልግሎት እንዳይፈጽሙ አግዷቸዋል፡፡ ከሌላ አካል የሚሰጣቸውን ጠባቂ በመሆናቸው ፣ ሁሉንም ነገር ጠርጣሪ መሆናቸውና ያመኑበትን ጉዳይ በላቂያ(with excellence ) አለመፈጸማቸው ለድቀታችን ምስክር ለልዩነቱ ግንብ ደግሞ ድንጋይ አቀባይ አድርጓቸዋል፡፡
  2.አረብ አስተኔ
  ወንዶቹ ጺም በማሳድግ፣ ሱሪ በማሳጠር፤ ሴቶቹ ደግሞ ወደ አልታዬ ባጋደለ አለባበሳቸው በቀላሉ ይታወቃሉ፡፡ የሌላ ሰው አእምሯዊ ንብረትን እንደራስ አድርጎ በመጠቀም እና ሃይማታዊ ኪራይ ሰብሳቢነት በሚታሙት ( Plagiarism and smartly marketed religious celebrity) ዶክተር ዛኪር ‘መነጥር’ ኢትዮጵያን ለመመልከት ይሞክራሉ፡፡ታሪክን ወደኃላ ተመልክተው እኩይ አና ክፉ ቀኖችን መርጠው ለማጮኽ ይሞክራሉ፡፡ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትም በካድሬነት መታማቱ የኪራይ ሰብሳቢዎች ጎሬ መሆኑ ደግሞ እነዚህን ወጣት ሐሳሲያን ይይዙት ይጨብጡት አሳጥቶ ከሁለት ያጣ… አድርጓቸዋል፡፡ከሌላው የትውልድ አቻቸው ጋር ተባብረው በታሪክ አጋጣሚ እነርሱ ባልመረጡት ባላነጹት ሀገር አንዴት መኖር እንዳለባቸው ከመወያየት ይልቅ መቆራቆስ ይዘዋል፡፡ስለእስልመናም ሆነ አለማችን ያላቸው ዕውቀት ጥራዝ ነጥቅ በመሆኑ ለዘላቂ ሰላም እና የሰው ልጆች በመልካም ሁኔታ መኖር(well being of mankind) የጠራ ኃልዮት የላቸውም፡፡በአ ይፎን ስልካቸው ሙሉ ቅዱስ ቁርዓናቸውን ጭነው ገልጠው እያነበቡ ምዕራባዉያን የደረሱበትን የዕውቀት ከፍታ ይክዳሉ፡፡ በቀላሉ ምዕራብ ርኩስ አረብ ሰናይ የሚሉ ናቸው፡፡ይህ ሁኔታ ሌላዉን በጥርጣሬ እንዲመለከቱ እነርሱ ደግሞ በጥርጣሬ እንዲታዩ አደርጓቸዋል፡፡
  3.ምዕራብ አስተኔ

  ይህ የትውልዳችን ክፍል ምዕራባውያን ሆን ብለው ለፍላጎታቸው ማስፈጸሚያ፣ ለቅራቅንቧቸው(የንዋይም ሆነ ኃልዮት) ማራገፊያ ይሆን ዘንድ የፈጠሩት፣ ያደራጁት አሁንም የሚዶግሙት ነው፡፡ ሀገርኛ ቋንቋ ፣ እውቀት ፤ የሞራል ህግ እና ማኀበራዊ ተቋማት የተጠየፈ የወደብ መብራቶቹ የሆሊውድ የፊልም አክተሮች ያደረገ ፣ በጣልያን መገዛትን የሚመኝ ፣ ትሻልን ሰድጄ ትብስን አመጣው አይነት ነገር ነው፡፡ ቢያንስ ለ ሶስት ሺህ አመታት በአንድ አከባቢ ሰፍረን እርስ በርስ መታኮሳችንን የረሳ ነው፡፡ከዚህ ከእናት ሀገር ስሩ የተነቀለ ነገር ግን የሚያመልካቸው ምዕራባውያን ከተራ ማሰመሰል በቀር ምናቸውም የሌለው ነው፡፡ግማሹን የትውልዳችን ለሱሶች ተገዢነት እና ስደት የዳረገ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እምነትን ሽፋን ባደረገ የምዕራባውያን የተቀነባበረ ሴራ የተሸነፈ ቅዱስ ለመሆን አውሮጳዊ አመለካከት እና ይትበሐል አንደሚያስፈልግ የሚያትት ነው፡፡ please read carfully befor answering the question!

  ReplyDelete
 9. Dejeselam- Is this your business. If you are not of the member and follower of Orthodox church why not you promote your own doctrine without following the church and attacking here beliefs and practices? Amlake Kirus genriel wagachihun Yistachihu!!

  ReplyDelete
 10. Durom bihon betekrstianachin sitastemir
  Mela , ekt adanun eyalech say hon amaledun
  Bemalet new mez33:1 enaa ebra1:14 ante yetelakew
  Masreja new . Lela Lelawn staf enji yemaytekim
  Tarik atawru.

  ReplyDelete
 11. 1 wengel lay geta andi bota lay be ahiyayitu lay tekemete yilail lela bota degimo be ahiyayitu wirinichila lay tekemete yalal. enidi tebilo bemetsfu wenigelu tikikil ayidelelem maalet yihon?2ga yakob ye yosefi lijochin sibarik egiziaabeher, kelijinete jemro yetebekegn melak enezihen lijoch yibark biluwal tesasito yihon.lib yisitih

  ReplyDelete
 12. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !December 28, 2012 at 9:04 AM

  This is my testimony, when I was kid I used to go to protestant church as well as Orthodox Church; during my childhood there was not bible study or preaching at the Orthodox Church, but I studied bible at the protestant church when I was ten years old at the Ureal Mekna yesuse. Coming to my point, my both eyes almost went to blind, I used to pray Jesus to heal my eyes and got my vision, remember! I mentioned that I visit both churches (protestant and orthodox) during my visit at Gebe Gabriel I asked saint Gabriel to took my prayer to lord Jesus, Saint Gabriel one blessing night came in to me and told me that lord Jesus sent him and said: "JESUS CHRIST heal your eyes from now on." Saint Gabriel touched my eyes and left.

  Saint Gabriel or others Angles can only come to us if they send from GOD, they can't do by themselves, they are a servant and we are the children of God. Please give appropriate respect for all the Angels and saints, don't worship them they don't want that! All the angles still guarding me because I love their lord and my savior LORD JESUS!

  Thanks,

  ReplyDelete
 13. enaneta tekawamiwathe lamen tewahedon tetathu protastanet atehonum yamayegabathu bate weset naw yalathehut ebakathu neku eza betehadu aberahu bezu teseralathu waye yemethareshaw zeman kehedate kabate weset EGEZIABEHARE YEGASETHATHUN

  ReplyDelete
 14. Misgana yihun le ersu lefetari mela'ektun
  Eyelake silemimren.

  ReplyDelete
 15. 1.

  መልአኩን ልኮ አዳናቸው
  በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታህሣሥ 19 ከከበሩት መላእክት አንዱ የሆነው የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክበረ በዓል በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት በመዝሙር በጸሎት በምስጋና በቅዳሴ በዝክር ይከበራል ይታሰባል። የሚከበርበት ምክንያት ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ሠለሥቱ ደቁቅን ከዕቶነ እሳት(ከነደደ እሳት) ያዳነበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡
  ቅዱስ ገብርኤል ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው ብሏል ሉቃ 1፥20
  ታላቁ ነብይ ሄኖክ ስለ ነገረ መላእክት በተናገረበት አንቀጽ እንዲህ ሲል መሰክሯል << በባቦች ላይ በገነትም በጸድቃን ላይ በኪሩቤልም ላይ የተሾሙ ከከበሩ መላእክት አንዱ ገብርኤል ነው ፡፡>> ሄኖክ 6-7<< በሦስተኛውም በመላእክት ሁሉ ላይ የተሾመ ቅዱስ ገብርኤል ነው >>10፥14 እያለ የመልአኩን ክብር ተናግሯል
  ገብርኤል የሚለው ቃል የሁለት ቃለትውህድ ነው እነዚህም ገብር እና ኤል ትርጉምም የአምላክ አገልጋይ /የእግዚአብሔርን ልጅ የሚመስል የአምላክ አገልጋይ ማለት ነው። ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳን መላእክትን ”ንቁም በበእላዌነ እስከ ንረክቦ ላምላክነ ” አምላካችንን ፈጣሪያችንን እስከምናውቅ ድረስ ባለንበት በተረዳንበት ነገር ጸንትን እንቁም በማለት ያጽናና ያረጋጋበተወዳጁመልአክበቅዱስ ሚካኤል መሪነትየሰው ልጆች ጠላት የሆነውን ዲያብሎስን ተዋግተው ድል እንዲያደርጉ ወደ ጥልቁ እንዲጣል አድርጓል (አክሲማሮስ ገጽ.35) ራእ12፥7 ነቢዩ ኢሳይያስ በሰማያት የሳጥናኤል ትዕቢትና ውድቀት ምን እንደሚመስል ሲጽፍልን “አንተ በንጋት የሚወጣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! ወደ አሕዛብ መልእክትን የላክ አንተ ሆይ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀጠቀጥህ! አንተም በልብህ፡ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደረጋለሁ፤… በልዑልም እመሰላለሁ አልህ፡፡ ዛሬ ግን ወደ ሲኦል ትወድቃለህ፤ ወደ ምደር ጥልቅም ትወርዳለህ”(ኢሳ.1416)በማለት ገለጠልን፡፡ ወደ ምድር የጣሉት በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል መሪነት እነ ቅዱስ ገብርኤል ነበሩ፡፡

  ቅዱስ ገብርኤል በብሉይ ኪዳን በቅድስና ሕይወት ለተጋውና በገዢዎች ዘንድ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ያደረበት ሰው(ዳን.5፡11)ተብሎ ለተመሰገነው ለነቢዩ ዳንኤል ማስተዋልንና ጥበብን የሰጠ መልአክ ነበር፡፡ ለዚህ ነቢይ እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጆችን ከሰይጣንና ከሞት ባርነት ነጻ ሊያወጣቸው ሰው እንደሚሆንና ሰማይንና ምድርን አሳልፎ በቅዱሳን ላይ ነግሦ እንደሚኖር በምሳሌ ገልጾ ያስተማረው መልአክ ነው፡፡(ዳን.9፡21-22) አሁንም ነቢዩ ዳዊት “አቤቱ እርዳታው ከአንተ ዘንድ የሆነለት በልቡም የላይኛውን መንገድ የሚያስብሰውብፁዕነው፡፡በልቅሶሸለቆ በወሰንኸቸውስፍራየሕግመምህርበረከትንይሰጣልና፡፡”(መዝ.83፡5-6)እንዳለውናቸው፡፡

  ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳን ይሆኑ ዘንድ ለተጠሩት መንፈሳዊ እውቀቱን የሚያካፍላቸው መልአክ ብቻ አይደለም፤ ለእግዚአብሔር በመገዛታቸው ምክንያት ከአላውያን ገዢዎች ከሚደርስባቸው መከራም የሚታደጋቸው መልአክም ነው፡፡ የፋርስ ንጉሥ የነበረው ናብከደነፆር እግዚአብሔር አምላክ ምድሪቱን ሁሉ ሲያስገዛለት በትዕቢት ተሞልቶ “በኃይሌ አደርጋለሁ፣ በማስተዋል ጥበቤም የአሕዛብን ድንበሮች አርቃለሁ፣ ሀብታቸውንም እዘርፋለሁ፣ የሚቀመጡባቸውንም ከተሞች አናውጣለሁ፣ በእጄም ዓለምን ሁሉ እንደ ወፍ ቤት እሰበስባለሁ፣ እንደ ተተወ እንቁላልም አወስዳቸዋለሁ፤ከእኔም የሚያመልጥ የለም የሚቃወመኝም የለም፡፡”(ኢሳ.10፡13-14) ብሎ በመታበይ የወርቅ ጣዖትን አሠርቶ ዱራ(አዱራን) በሚባል ስፍራ ላይ አቆመው፡፡ በግዛቱ በልዩ ልዩ የሥልጣን እርከን ላይ ያሉትን ሹማምንቱንና ገዢዎችን ሰበሰባቸው፤ “የመለከትና የእንቢልታ የመሰንቆና የክራር የበገናና የዋሽንትን የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ወድቃችሁ ንጉሥ ናብከደነፆር ላቆመው ለወርቁ ምስል ስገዱ፡፡ ወድቆም ለማይሰግድ በዚያን ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣል” ብሎ አዋጅ አስነገረ፡፡ ይህን አዋጅ የሰሙ የንጉሥ ሹማምንት ሁሉ የመለከቱና የእንቢልታው እንዲህም የዘፈን ድምፅ በተሰማ ጊዜ ተደፍተው ለወርቁ ምስል ሰገዱ፡፡

  ReplyDelete
 16. 2.
  በባቢሎን አውራጃዎች ላይ የተሾሙ አዛርያ(ሲድራቅ)፣ አናንያና(ሚሳቅ) ሚሳኤል(አብደናጎ) ግን ንጉሥ ላቆመው ምስል አልሰገዱም፡፡ ነገር ሠሪዎችም ይህንን ወሬ ለንጉሥ ነገሩት፤ ንጉሥም እጅግ ተቆጥቶ ወደ እርሱ አስጠራቸው፡፡ እርሱ ላቆመው ለወርቅ ምስል ያልሰገዱ እንደሆነ እጅና እግራቸውን ታስረው ወደ እቶን እሳቱ እንደሚጣሉ አስጠነቀቃቸው፡፡ ሠልስቱ ደቂቅ ግን “ናብከደነፆር ሆይ! በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አንፈልግም፡፡ ንጉሥ ሆይ! እኛ የምናመልከው አምላክ በሰማይ አለ፣ ከሚነደውም ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፤ ንጉሥ ሆይ! ይህም ባይሆን አማልክትህን አንዳናመልክ፣ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ” ብለው መለሱለት፡፡ የንጉሥ ናብከደነፆር ቁጣ ከፊት ይልቅ እጅግ ነደደ እሳቱንም ሰባት እጥፍ እንዲያቀጣጥሉና እነዚህን ሦስት ብላቴኖች እጅና እግራቸውን አስረው ከእነ ማዕረግ ልብሳቸው ከእቶን እሳት ውስጥ እንዲጨምሩአቸው ትእዛዝን አስተላለፈ፡፡ ትእዛዙ አስቸኳይ ነበርና እነርሱን ወደ እሳቱ የጣሏቸውም ኃያላን በእሳቱ ወላፈን ተገርፈው ሞቱ፡፡ እንዲህ ሲሆን ሳለ ግን ሠልስቱ ደቂቅ ወደ አምላካቸው “በፍጹም ልባችን እናምንሃለን፣ እንፈራሃለን፣ አታሳፍረን እንጂ ገጸ ረድኤትህንም እንፈልጋለን፡፡” እያሉ ይጸልዩ ነበር፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ጸሎታቸውን ተቀበለ፤ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልንም ከመጣባቸው መከራ ይታደጋቸው ዘንድ ላከው፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም እስራታቸውን ፈታ፤ እሳቱን እንደ ውኃ አቀዘቀዘው፡፡ ሠልስቱ ደቂቅም መልአኩን ልኮ ከዚህ እቶን እሳት ያዳናቸውን አምላክ “የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይክበር ስምህም ለዘለዓለም የተመሰገነና የከበረ ነው” በማለት አመሰገኑት፡፡
  ንጉሥ ናብከደነፆርም ሠልስቱ ደቂቅ እሳቱ አንዳች ጉዳት ሳያደርስባቸው በእሳት ውስጥ ሲመላለሱ ከእነርሱ ጋር የሰው መልክ ያለው ነገር ግን አምላክን የሚመስል መልአክ ተመለከተ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሊቀ ካህናቱን ቀያፋን ፊቱን ጸፍቶ አፉን ከፍቶ “ሕዝቡ ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ስለሕዝቡ ይሞት ዘንድ እንዲሻለን አታስቡምን”(ዮሐ.11፡49) ብሎ እንዳናገረው እንዲሁ ናብከደነፆርንም “እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎችን በዚያ አያለሁ ምንም የነካቸው የለም፤የአራተኛውም መልክ የእግዚአብሔርን ልጅ ይመስላል” ብሎ እንዲናገር አደረገው፡፡ የእግዚአብሔር ልጅን መልክ ያለው ያለው በኋላም መልአክ ብሎ የተናገረለት ቅዱስ ገብርኤልን ነበር፡፡ እርሱ ስለመሆኑ ለነቢዩ ዳንኤል በተገለጠበት ግርማ ማረጋገጥ እንችላለን፡፡

  ናብከደነፆርም ወደ እሳቱ እቶን በመቅረብ እነዚህ ብላቴኖችን “እናንተ የልዑል አምላክ ባሮች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ኑ ውጡ ብሎ ተናገራቸው፡፡” እነርሱም ከእሳቱ ወጡ ሹማምንቱና መኳንንቱ፣ አማካሪዎችና የአገር ገዢዎች ሁሉ እሳቱ በእነዚህ ብላቴኖች ላይ አንዳች አቅም እንዳልነበረው፣ ከጠጉራቸው ቅንጣት አንዱን እንኳ እንዳላቃጠለው፣ ሰናፊናቸውም እንዳልተለወጠ፣ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው ተመለከቱ፡፡ ንጉሥ ናብከደነፆርም መልአኩን ልኮ ያዳናቸውን የእነዚህን ቅዱሳንን አምላክ አመሰገነ፡፡ በእነርሱ አምላክ ላይም የስድብን ቃል የሚናገር ሰው እንደሚገደልና ቤቱም የጉድፍ መጣያ እንዲሆን አዋጅ አስነገረ፡፡ አዛርያ አናንያ ሚሳኤልም በንጉሡና በሹማምነቱ ዘንድ ሞገስ አገኙ በክብርም ከፍ ከፍ አሉ፡፡(ዳን.3 በሙሉ) ሊቀ ነቢያት ሙሴ<< እኝን እንዲረዱን እንዲጠብቁን እንዲያጽናኑን እና እንዲያማልዱን መላእክቱን በፊታችን ይልካል።በመላአክ ፊት ተጠንቀቁ ስሜ ከእነርሱ ስም ጋርአለ >> እና ብሎ የሰራዊት ጌታ ቅዱሳን መአእክትን እንዳከበራቸው አስተምሮናል
  ቅዱስ ገብርኤል በአማላጅነቱ በጸሎቱ ለታመኑበት ፈጥኖ የሚደርስ በብለይ እና በሐዲስ ኪዳን በልዪልዩ ተልኮዎቹ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ፈቃድ በመፈጸም የጸና ሰለሆነ ጥበብ በመግለጽ በማጽናት በማብሰር ከመከራ በማዳን ከእሳት ወላፈን በመታደግ ከአንበሳ መንጋጋ በማትረፍ እና ትዕቢተኞችን በመቅጣት በመገሰጽ እውነተኛ ታዳጊ መልአክ መሆኑን አስመስክሯል ።ሰለስቱ ደቂቅን በሚያሰደንቀው ትንብልናው እንደታደጋቸው እንደተራዳቸው ዛሬም በጸሎቱ ለሚታመኑ ዝክሩን ለሚያደርጉ ድረሳኑን የሚደግሙትን በጸሎት በመዝሙር በቅዳሴ በልዮ ልዮ መንፈሳዊ ክብረ በዓሉን ብናናክበር አማላጅነቱን የጸጠውን ጸጋ ብንመሰክር በበደላችን ምክንያት ከተግባረ ጽድቅ ለተሰደድን ስደተኞች ከባሕረ እሳት ለሰጠምን ኃጥያተኞች የምናመልከው ያባቶቻችን አምላክ ለመልአኩን ልኮ የእሳቱን ባሕር እንዲያሻግረን የሊቀ መላእክትየቅዱስ ገብርኤል አማላጅነቱ የሰለሰቱ ደቂቅ በረከታቸው ይደርብን
  ምንጭ ደርሳነ ገብርኤል
  ሐመር መጽሔት
  ስምዓጽድቅ
  ነገረ መላእክት ትምህርት

  ReplyDelete
 17. ከሠለስቱ ደቂቅ ሦስት ነገር እንማራለን

  ማመን፣ መቁረጥ እና ማድረግን፡፡ ሃይማኖት እነዚህን 3 ነገሮች ይፈልጋል፡፡ ሦስቱ ሕፃናት በእግዚአብሔር ፍጹም አመኑ፣ ይህንንም እምነታቸውን ሲገልጡ “የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል” በማለት ተናግረዋል፡፡ የመጣባቸውን ሁሉ ለመቀበል ወሰኑ ቆረጡ “አምላካችን እኛን ማዳን ይችላል ነገር ግን ፈቃዱ ከዚህ እሳት ገብተን ሠማዕትነትን እንድንቀበል ቢሆን ከእሳት እንገባለን” በማለት አንድ ልብ፣ አንድ ቃል ሆነው አቋማቸውን ገለጡ፡፡ የቆረጡትን ነገር አደረጉት፤ ወደ እሳት ውስጥ ተወረወሩ ሦስቱም ነገሮች ስለተፈጸሙ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ እሳቱን አብርዶ አዳናቸው፡፡ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል” በማለት የተናገረው ቃልም ተፈጽሞላቸዋል፡፡ /መዝ.33፥7/ ጠባቂ መልአካቸው ቅዱስ ገብርኤል በእሳት ውስጥ ገብቶ ከመከራ ሥጋ አድኖአቸዋል፡፡ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራና መልአኩል ልኮ የፈጸመውን ትድግና ያየው ናቡከደነጾር “ናቡከደነፆርም መልሶ፡- መልአኩን የላከ ከአምላካቸውም በቀር ማንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ፥ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብድናጎም አምላክ ይባረክ፡፡ እኔም እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና በሲድራቅና በሚሳቅ በአብድናጎም አምላክ ላይ የስድብን ነገር የሚናገር ወገንና ሕዝብ በልዩ ልዩም ቋንቋ የሚናገሩ ይቆረጣሉ ቤቶቻቸውም የጉድፍ መጣያ ያደረጋሉ ብዬ አዝዣለሁ አለ፡፡ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብድናጎንም በባቢሎን አውራጃ ውስጥ ከፍ ከፍ አደረጋቸው፡፡” ዳን.3፥28-30

  http://eotc-mkidusan.org/site/index.php/-mainmenu-24/--mainmenu-26/1177--317

  ReplyDelete
 18. እግዚአብሔር ስራውን የሚሰራው በቅዱሳን መላእክት፤ በቅዱሳን ሰዎችና እርሱ በፈቀዳቸው ነገሮች አድሮ ታምራዊና ድንቅ ስራውን ይሰራል። እግዚአብሔር አምላክ ለመላእክቱ ሀይል ስለሰጣቸው በእርሱ ፈቃድ ብዙ ታላላቅ ስራዊችን የሰሩት እንጅ ከራሳቸው የሆነ ሀይል የላቸው።በትክክል የማንክደው ነገር አለ በቤተ ክርስቲያናችን ብዙ መጽሐፍትም ሆኑ ገድላት በቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት ተመርምረው የተጻፉ አይደለም።በየመንደሩ እንዳሻቸው በተለያዩ ሰዎች ተጽፈው በየገበያ ላይ አሉ። መናፍቃን ይጻፉ ደብተራው ይጻፍ ማንም አያውቀውም። ስህተቱ እዚህ ላይ ነው። ቤተ ክርስቲያናችን ዉስጥ ማንም እንዳሻው የፈቀደው የምሸቅጥበታ ቦታ ሆኖዋል። ይህ አይነቱ ስህተት በቅዱስ ስኖዶስ ልታረም ይገባቸዋል እላለሁ። ብዙ ከእውነት የራቁ የሐሰት ጽሁፎችና ገድላት እናት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችንን እያሰደቡ ናቸው። ልክ ያልሆነውን ነገር እውነት ነው ብሎ መቀበል አይቻልም። እንድታረም መደረግ አለበት ። አምልኮት የምገባው ሁሉን ቻይ ለሆነው እግዝአብሔር ብቻ ነው። አንዳንድ የቅዱሳን በዓላት ስንመለት ከእግዚአብሔር ስም በላይ የማይገባ ስራዎች ስደረጉ እያየን ነው። ገናናውን የሰውን ልጆች በደሙ ዋጅቶ ያዳነን አምላክ ቦታ ሳንሰጥ እርሱ ላከበራቸው ቅዱሳን የበለጠ ክብር የሚንሰጥ ከሆነ ስህተት ነው። ወንገሉን የግድ ማወቅ ይገባናል ። እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተናገረችው ቃል ትልቅ ትምህርት ነው ማስተዋል ለቻለው ሰው ዮሐ ም 2፤5 እናቱም ለአግልጋዮቹ እርሱ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉት በማለት ለሰርጉ ቤት አገልጋዮች ተናገረች ። ዛሬ እግዚአብሔር አደርጉ ያለንን ነው ወይንስ ሌላ ነገር እያደረግን ነው? ። ከእኔ በቀር ለሌላ አማልክት አታምልክ የሚለው ህያዉና ዘላለማዊ ቃሉ በትክክል ማመን መፈጸም ያስፈልጋል። እግዚአብሔርንና ቅዱሳን መላእክትን ለይተን አምልኮት ያስፈልጋል፤ አምልኮት የምገባው ለማነው ብለን ቅዱስ ቃሉን መጠየቅ እጅግ ለነፍሳችን ጠቃም ነው። ቅዱሳን መላእክት ወደ እግዚአብሄር ይጸልዩልናል ምንም ክርክር አያስፈልግም። ልዩ አምልኮት እና ዉዳሴ ለህያው እግዝአብሔር ብቻ እንጅ ለቅዱሳን መላእት አይደልም። ነገሮችን እንደ ቅዱስ ቃሉ ለያይትን መረዳት አለብን።አዳኝ ስንል ወገኖቼ ለእግዚአብሔር ብቻ የተሰጠ ነዉ ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ በመስቀል ላይ ደሙን አፍሶ ስጋውን ቆርሶ ስለ እኛ በመሞት ሞትን ድል አድሮ ከሙታን መሐከል በመነሳት በክብርና በምስጋና ወደ ቀደመው ዙፋኑ በመመለስ ነው። የቅዱሳን የጸጋ ማዳን ግን ከሐጥአት መንገድ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ምስክርነትና ተአምዕታቱን በመናገር ነው። ብዙዎችን ከእሳት ውስጥ ነጥቃችሁ አድኑአቸው ይላል። የይሁዳ መልዕት ቁጥር 23። ይህ ማለት ሰዎችን ከሐጢአት ከክፉ ስራ ከጨለማ ሕይወት ወደ እግዚአብሔር መንገድ በመመለስ (የማዳን) አገልግሎት መፈጽም ማለት ነው።ሀሉቱ ልዩት አላቸው። የእግዚአብሔር ማዳንና የቅዱሳን መላእክት ማዳን የተለያየ ነው።መከባበር መልካም ነው።የእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር የቀሳርን ለቀሳር የሚገባውን ማድረግና መፈጸም አለብን ።

  ReplyDelete
 19. ለእዚህም እዚያም ረጋጮች፣
  1/ ከ3ቱ ደቂቅ ጋር እሳት ውስጥ የታየው

  ሀ/ የአማልክትን ልጅ የሚመስል ነው?
  ለ/ ገብርኤል ነው?
  ሐ/ ሚካኤል ነው?
  መ/ ወይስ ገብርኤልና ሚካኤል በጋራ ናቸው? (የሁለቱም ድርሳን እኔ ነኝ ይላሉ)

  2/ ከሰዎች ይልቅ መጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛ ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ያልጠቀሰውን ስም እንመን ወይስ ሰዎችን የሚናገሩትን ያልተጻፈ ስም እንቀበል?

  ReplyDelete
 20. I have some thing to advice Aba selama, do you know that MK are assigned a person to all look and responses for the article posting in this web site, all the comments disapproved the articles ( most of them biblical) in your web site are by one MK follower. please! don't post copy of ሐመር መጽሔት and other MK articles. we don't need them they kill our church and religion. MK are the son of devil, who are diverting us from Wonegle to tert tert and devil books.

  ReplyDelete
 21. ስለ ሙሴ ስጋ ከዲያብሎስ ጋር የተከራከረው ሚካኤል መሆኑ ተጽፏል ያልከውን በብሉይ ኪዳን አናገኘውም ሐዋርያው ይሁዳ ከየት አመጣውና ተናገረው ያልን እንደሆነ ትውፊትን እንድንቀበል ያስገድደናል ያልከውን በብሉይ ኪዳን አናገኘውም ሐዋርያው ይሁዳ ከየት አመጣውና ተናገረው ያልን እንደሆነ ትውፊትን እንድንቀበል ያስገድደናል

  ReplyDelete
 22. አስርቱ ተእዛዛት የእግዚአብሔር ሆኖ ሳለ የሙሴ ተእዛዛት ይላል፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ብንል የመላእክት አለቃ ነውና በመልእክት ደረጃ ቅዱስ ሚካኤል ይነሳል ግን በድርጊት ቅዱስ ገብርኤል አድረጎታል ስለዚህ አይጣላም ፡፡በምድራዊ ስራ እንኩዋን ብንመለከት ወታደሩ በሚያደርገው ድል የበላዮቹ አዛዦችም ይነሳሉ፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን ያከናውናል ነገር ግን በቅዱሳኑ ማድረግና መፈጸም ፈቃዱ ነው፡፡ አማልክት ስለሚያደርጋቸው እኮ ነው የአማልክት አምላክ መባሉ እናም አይጣላም፡፡አስርቱ ተእዛዛት የእግዚአብሔር ሆኖ ሳለ የሙሴ ተእዛዛት ይላል፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ብንል የመላእክት አለቃ ነውና በመልእክት ደረጃ ቅዱስ ሚካኤል ይነሳል ግን በድርጊት ቅዱስ ገብርኤል አድረጎታል ስለዚህ አይጣላም ፡፡በምድራዊ ስራ እንኩዋን ብንመለከት ወታደሩ በሚያደርገው ድል የበላዮቹ አዛዦችም ይነሳሉ፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን ያከናውናል ነገር ግን በቅዱሳኑ ማድረግና መፈጸም ፈቃዱ ነው፡፡ አማልክት ስለሚያደርጋቸው እኮ ነው የአማልክት አምላክ መባሉ እናም አይጣላም፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. እጅግ ታላቃ ማብራሪያ ፡፡ ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ

   Delete
 23. Enanta yamtrbu sewoch ke egna wogen endaydalachihu eko tsehufachihu yinageral yane Ato begashaw zemadoch kegna wogen bithonu egna haymanote likayir yamatwun sew sintala enantam malet nabarbachihu gin min yidaragal kand gudguad tagegnachihu .ahun asteyayetan kawotachihu tiru eski woda hilinachihu temalesu genzeb naw endih yamiyadergachihu enantenm ena begashawunim egna yaminfalgaw minim satinaka Kabatochiachin yatakabalnatin haymannot.Bekadamechiuwa menged bithadu Lanfsachihu Eraft tagegnalachihu.....

  ReplyDelete
 24. bebetecrstian abatoch ende minagerut kehone ananya azaria misaln kesat yawetachew melaku kdus gebral new yemilun.ante gn melamnt new yaderghw.

  ReplyDelete
 25. endanebew slanesahgn bcha god bluss you.

  ReplyDelete