Tuesday, December 11, 2012

አባ ሳሙኤልና መሰሎቻቸው እንዲሁም ማህበረ ቅዱሳን «በልካቸው ያሰፉት» የፓትርያርክ ምርጫ ህገ ደንብ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው፤ ጳጳሳት እርስበርስ እንዳይከፋፈሉ አስግቷል

Read in PDF

በዘንድሮው የጥቅምት ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ እስከ ህዳር 30 የፓትርያርክ ምርጫ ህገ ደንብ ረቂቁ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ በተወሰነው መሰረት ሲኖዶሱ በረቂቅ ህገ ደንቡ ላይ እየተወያየ ይገኛል፡፡  በውይይቱ ላይ በውጪ ሀገር የሚገኙ የሲኖዶሱ አባላት ጳጳሳትን «መምጣት አያስፈልጋችሁም፤ ያለውን ነገር እናሳውቃችኋለን» በሚል እንዳይገኙ በአባ ህዝቅኤል የተነገራቸው መሆኑ ታውቋል፡፡ ይህም የሆነው በነአባ ሳሙኤል ልክ የተሰፋው ህገ ደንብ ሊገጥመው የሚችለውን ተቃውሞ ለመቀነስ ታስቦ ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል፡፡ ይሁን እንጂ አገር ውስጥ ባሉት ጳጳሳትም ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ ቀድሞ አቡነ ጳውሎስን ለመጣል አንድ የሆኑ የመሰሉት ጳጳሳት ጭምር በአቋም ተለያይተው ታይተዋል ተብሏል፡፡

15 አንቀጾች ባሉት 9 ገጽ ህገ ደንብ ላይ በአንቀጽ 5 የሰፈሩት አንዳንድ ነጥቦች ለአለመግባባቱ መንስኤ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡ አንቀጽ 5 እንዲህ ይላል፦
«ለፓትርያርክነት የሚመረጡ ዕጩዎች መመዘኛ
ለፓትርያርክነት የሚቀርብ እጩ ተወዳዳሪ የሚከተሉትን መስፈርት ማሟላት አለበት፡፡
1.     ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ የሆነ
2.    ሊቀጳጳስ ወይም ጳጳስ ወይም ኤጲስ ቆጶስ ወይም የገዳም መነኩሴ የሆነ፣
3.    ለፓትርያርክነት እጩ ሆኖ የቀረበ የገዳም መነኩሴ ከሆነ በመነኮሳት ገዳም ከ7 ዓመታት በላይ ያገለገለና ፈጽሞ ያላገባ ድንግል፣
4.    እድሜው ከ45 ዓመት ያላነሰ፣ ከ70 ዓመት ያልበለጠ፣
5.    ትምህርተ ሃይማኖትንና ቀኖና ቤተክርስቲያናንን ጠንቅቆ ያወቀ፣ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ጽኑዕ የሆነና በቅድስና ህይወቱና በግብረ ገብነቱ የተመሰገነ፣
6.    ከቤተክርስቲያኒቱ የአብነት ትምህርት ቤቶች በአንድ ትምህርት የተመረቀ ወይም ሁለገብ የቤተክርስቲያን ትምህርት ያለው ሆኖ ከከፍተኛ የመንፈሳዊ ትምህርት ተቋማት ወይም በዘመናዊ ትምህርት ቢያንስ ዲፕሎማ ያለው፣
7.    ሙሉ አካል ያለውና ጤንነቱ የተሟላ፣
8.    ለሌሎች መልካም አርአያ መሆን የሚችል፣ ታማኝና ቃሉን የማይለውጥ ንጹህ ሰው፣
9.    የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጠባቂና ጠበቃ መሆኑን በተጨባጭ ያስመሰከረ፣
10.  የቤተክርስቲያኗ ቋንቋ የሆነውን ግእዝ ጠንቅቆ ያወቀ እንደዚሁም ከአገር ውስጥ ቋንቋዎች አማርኛና ቢቻል ከሌሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አንዱን ወይም ከዚያ በላይ የሚያውቅ ሆኖ በተጨማሪ ከዓለም አቀፍ ቋንቋዎች ቢያንስ አንዱን በሚገባ የሚያውቅ፣
11.    መንፈሳዊና ማህበራዊ አገልግሎት በመፈጸም በቂ የአስተዳደር ችሎታና ልምድ ያለው፣
12.  በዚህ ህገ ደንብ አንቀጽ 11(2) (ሀ) ላይ የተገለጸውን ስምምነት ሰነድ የፈረመ፣»
 ይላል፡፡ በተራ ቁጥር 11(2) (ሀ) ላይ የሰፈረው እንዲህ የሚል ነው «እኔ አባ ………………………………………………………….. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ሆኜ ብመረጥ ከተመረጥኩበት ዕለት ጀምሮ በፓትርያርክነት ዘመኔ ሁሉ በተጣለብኝ የስራ ሀላፊነት የተነሳ በደመወዝ፣ በስጦታ፣ በሽልማትም ሆነ በሌላ ማናቸውም መንገድ በእጄ የሚገባና በስሜ ያለ ማንኛውም ገንዘብም ሆነ ሌላ ንብረት በሙሉ ሀብትነቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እንጂ የግሌ አይደለም፡፡ ከዚሀ ዓለም በሞት ስለይም ያለኝን ማንኛውም ሀብትና ንብረት በሙሉ ወራሿ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብቻ ናት፡፡ ይህንንም በፊርማዬ አረጋግጣለሁ፡፡» የሚል ነው፡፡

በዚህ አንቀጽ ውስጥ ብዙ ያነጋገረው የዜግነትና የእድሜ ጉዳይ ሲሆን፣ ህገ ደንቡ ዜግነትንና እድሜን በዚህ መልክ ያስቀመጠው ፓትርያርክ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ በስፋት የተወራላቸውን አባ ማትያስን ከውድድር ውጪ ለማድረግ ነው ተብሏል፡፡ በአንጻሩ ፓትርያርክነትን ለሚመኙት ለአባ ሳሙኤል፣ ለአባ አብርሃምና ለአባ ሉቃስ፣ እንዲሁም ከገዳም መነኮሳት መካከል ለፕትርክና እጩዎች እንዲካተቱለት ለሚፈልገው ማቅ እንዲመች ተደርጎ የቀረበ መሆኑም ታውቋል፡፡

 በህጉ ላይ የከረረ ተቃውሞ ካሰሙት መካከል አቡነ ጢሞቴዎስ፣ አቡነ ማርቆስና አቡነ ሳዊሮስ የሚገኙ ሲሆን የራሱን ፓትርያርክ ለማስቀመጥ በቡድን ተደራጅቶ ይንቀሳቀሳል የሚባለው የወሎ ተወላጅ ቡድንም ተቃውሞታል፡፡ በዚህ ቡድን በኩል አቡነ አትናቴዎስን ፓትርያርክ ለማድረግ ታስቧል ነው የተባለው፡፡ እድሜን በሚመለከት ከ45 እስከ 70 ተብሎ የተገደበው መነሻው 50 እንዲሆንና 70 የተባለው ጣሪያ እንዲነሳ ሐሳብ ቀርቧል፡፡ ዜግነትን በተመለከተም የዜግነት ጉዳይ በሌሎችም ህጎች የተካተተው በትውልድ ኢትዮጵያዊ ያልሆነ የውጪ ዜጋ እንዳይሾም እንጂ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑና የውጪ ዜግነት ያላቸውን ጳጳሳት ለመከልከል አይደለም ተብሏል፡፡ የዜግነትን ነገር አስመልክቶ የጉድ ሙዳዩ አባ አብርሃም «የዜግነትን ጉዳይ በሚመለከት ደንቡ መሻሻል የለበትም» ሲሉ ብፁእ አቡነ ማርቆስ አባ አብርሃምን «አጭበርባሪ .. አንተም ባይሳካልህ ነው እንጂ የአሜሪካን ዜግነት ፈልገህ ነበር እኮ ግን ሳታሰካ ተቀየርክ» ብለው እንደገሰጿቸው ተሰምቷል፡፡ በዚህ የተናደዱት አባ አብርሃም በማቅ ድረገጾች ብፁእነታቸውን ማሰደብ ይዘዋል፡፡ ሰሞኑን አንድአድርገን የተባለው የማቅ ብሎግ ብፁእ አቡነ ማርቆስን በወንጌል ላይ ባላቸው አቋም እየዘለፋቸው ይገኛል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ በ2/4/2005 አመሻሹ ላይ ጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ የማቅ አባል የሆነው ባያብል ብፁእነታቸውን ከጉድ ሙዳዩ ከአባ አብርሃም ጋር ሲያነጋግራቸው ታይቷል፡፡ በደንቡ ላይ የቀረቡት ክርክሮች ጠንካራ ስለነበሩ አንዳንድ ማሻሻያዎች ካልተደረገ በቀር ጳጳሳቱ እንዳይከፋፈሉ ተሰግቷል፡፡ ይህን ስጋት የገለጹ ጳጳሳት መኖራቸውም ተሰምቷል፡፡

ሌሎቹም ነጥቦች ሁሉ አነጋጋሪ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በተራ ቁጥር 3 ላይ የተቀመጠውና «ለፓትርያርክነት እጩ ሆኖ የቀረበ የገዳም መነኩሴ ከሆነ በመነኮሳት ገዳም ከ7 ዓመታት በላይ ያገለገለና ፈጽሞ ያላገባ ድንግል፣» የሚለው በማቅ ልክ የተሰፋ ነው የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ ማቅ ካሉት ጳጳሳት የእኔ የሚላቸውን ማሳተፍ ካልቻለ በየገዳሙ ለአላማው ያስቀመጣቸውን በዋልድባው ጉዳይ እንደተጠቀመባቸው ለቀጣይ ዋና አላማው ፓትርያርክ አድርጎ ለመጠቀም ያሰባቸው መነኮሳት እንዳሉት ማወቅ ተችሏል፡፡ በዚሁ አንቀጽ ላይ መነኩሴ ፈጽሞ ያላገባ ድንግል እንዲሆን የወጣው መስፈርት ለጳጳሳትስ መስፈርት ተደርጎ ለምን አልቀረበም? የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡ መቼም እነርሱ ድንግል ስለሆኑ ነው እንዳይባል አንዳንዶቹ የቅድስና ጥያቄ የሚነሳባቸው መሆናቸው በተለያየ ጊዜ ተገልጧል፡፡ ለምሳሌ የሚጡ ባል አባ ሳሙኤል ቢያንስ ይህን ነጥብ ጨምሮ በተራ ቁጥር 5 ላይ «… በቅድስና ህይወቱና በግብረ ገብነቱ የተመሰገነ፣» የሚለው መስፈርት ከእጩነት ውጪ ያደርጋቸዋል፡፡

ሌላው አነጋጋሪ ፓትርያርክ የሚሆነው አባት ፓትርያርክ ከሆነ በኋላ የሚያፈራው ሀብትና ንብረት የቤተክርስቲያን ይሆናል የሚለው ነጥብ ነው፡፡ ይህም አያድርገውና ለምሳሌ አባ ሳሙኤል በተጭበረበረ መንገድም ቢሆን ፓትርያርክ ቢሆኑ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ አሁን ደግሞ የልማት ኮምሽን ጳጳስ በሆኑበት ዘመን ያካበቱት ከፍተኛ ሀብት ለቤተሰቦቻቸው እንዲሆን በዘመነ ፕትርክና የሚያፈሩት ብቻ ደግሞ ለቤተክርስቲያን እንዲሆን ተብሎ የተሰራ ሴራ ነው፡፡ ለምን የፓትርያርክ ሀብት ብቻ? ሁሉም ጳጳሳት ከቤተክርስቲያን አለአግባብ የሰበሰቡትን ሀብት ለቤተሰቦቻቸው ለማውረስ እንዲመቻቸው በ1991 ያወጡትን ህግ ሽረው የሁሉም ጳጳስ ሀብት በየፍርድ ቤቱ የወራሽነት ጥያቄ እያስነሳ ከሚያጓትትና ቤተክርስቲያንን ከሚያዋርድ ይልቅ ቤተክርስቲያን እንድትወርሰው ለምን አይደረግም?  ሌሎችን የህገ ደንቡን አንቀጾች እንደአስፈላጊነቱ ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡           

10 comments:

 1. I could not understand where ur standing is? Is it bad to Select an Ethiopian Citizen for Ethiopian Church? If a Monk is to be the one in the patriarch selection is it started to be him a 'Dingle' now? Or does the church have the same requirement even to make a Bishop? Is that mean asking the materials of a patriarch is the resource of the church the same not applied to bishop. Pls before u write smting see it from different direction

  ReplyDelete
 2. ለመሆኑ ማህበረ ቅዱሳን ወይንም ሰልፍያ የተባለው ይህ እርቃኑን በየመንገዱ እንደ አበደች ውሻ እየተንከራተተ ያለው ማህበር በሐሰት ስራው እየገፋበት ነው። እናንተ አባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ እርሱ ከመጀመሪያው ነፍሰ ገዳይ ነበር እዉነትም በእርሱ ውስጥ የለም ዮሐ 8፤44 ተብሎ በጌታችህን በኢየሱስ ክርስቶስ የተገሰጸው ይህ ማህበር ነው። እነሆ ብጹዕ አቡነ ማርቆስ ላይ ያንን ክፉ አፉን መክፈት ጀምሮዋል። ለመሆኑ በማቅ ድህረ ገጽ በአንድአድረገን ላይ ብጸዕነታቸውን መናፍቅ ናቸው ብሎ መስደቡ ምን ያክል ሰጣናዊ መንፈስ እንደ ተጠናወተው ነው። ብጹዕ አቡነ ማርቆስ የታወቁ ለእውነት የቆሙ በመሆናቸው እነሆ በማቅ እንድህ ያለ ዘመቻ ተጅምሮባቸውል። ማቅን የማይቀበል ሁሉ መናፍቅ ተሐድሶ እየባለ መነደፍ ሆኖዋል ።አሁን ወደ ሊቃነ ጳጳስ ዞሮዋል መንፍቅናው። ይገርማል ያሳዝናል። አንድ ተራ ማህበር በትምክትና በትዕብት ተነፍቶ ሊቀ ጳጳሱን ሐይማኖት እናስተምርህ ብሎ መነሳት ምን ያህል ክፉ ዘመን ላይ እንዳለን ያሳየናል። ተዋህዶ ገና ወንጌል ያልተሰበከልን ሆነናል። ገና ነን ማለት ነው በማቅ አመለካከት; ይህ ከማቅ ድህረ ገጽ ከአንድአድርገን ስለ በጹነታቸው የተጻፈው የተወሰደ ነው። ፍርዱን ለተዋህዶ እውነተኛ አማኞች ትቸዋለሁ "ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ለቅዱሳን ያላቸውን አመለካከት “ቅዱሳንን የቀደሰ ክርስቶስ ነው ስለሆነም ወንጌል ክርስቶስ ነው እንጂ መነኩሴ አይደለም፤ አቡሀይ እሙሀይ አትበሉ ክርስቶስን ስበኩ” በማለት በግልጽ በሕዝብ መሀል ተናግረዋል፡፡ በ2004 ዓ.ም ጾመ እግዚእ/ዐብይ ጾም/ ወቅት በደብረ ማርቆስ ጽርሐ ጽዮን አብማ ማርያም ቤተክርስቲያን በተደረገ ጉባኤ ላይ ከበሮ እያስመቱ ያስጨበጨቡ ሲሆን፤ በተደጋጋሚ ለቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ያላቸው ዝቅተኛ ግምት እህቶቻችንና እናቶቻችን በወር አበባ ወቅት እንዲገቡ መፍቀዳቸውና ማስገደዳቸው፤ ጸሎተ ቅዳሴውን አቋርጦ መውጣት እንጂ መግባት እንደሚቻል በተደጋጋሚ መናገራቸው የብፁዕነታቸው አካሄድ አባታዊ ምክርና ማስተካከያ ሳይሆን መሠረታዊ የሃይማኖት ችግር መሆኑን ምእመናን እንደተረዱ ገልጸዋል፡፡" እንድህ ብለዋል ብሎ የሐሰት ዘመቻ ጅምሮዋል። እርሳቸውን ጠንቅቀን እናውቃቸዋለን በእዉነት ለብዙ ዘመናት በዉጪ ሀገር ኖረው አሁን ደግሞ ሀይማኖተንና ሀገራችን በማገልገል ላይ ያሉ አባት ናቸው። እንወዳቸዋለን እናከብራቸዋለን። አንተ ክፉ መንፈስ ያለብህ የማቅ አባለት ከሐጢአታችሁ ወደ ንስሐ ሕይወት ተመለሱ። ቤተ ክርስቲያናችንን አትከፋፉሉዋት። ክፉ መንፈስ በክርስቶስ መስቀል ድል ይሆናል። አሜን

  ReplyDelete
 3. አበኑ ማርቆስ ላይ ማቅ ለምን አነጣጥሮ መተኮስ ጀመረ ? ወንጌልንና ኢያሱስ ክርስቶስን ሰበኩ ብለው ታናገሩ ተብለው በማቅ ድህረ ገጽ ተከሰሱ (አንድአድርገን}። ታዲያ ሰባኪያን ስለ ጌታቸን ኢየሱስ ክርስቶስና ስለ ወንጌል ካል ሰበኩ ማንን ልሰብኩ ነው? ስለ ማቅ ቅድስና ወይንስ ስለ እግዚአብሔር መንግስት ? ብጹነታች ትክክል ተናግረዋል መሰበክ ያለበት ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ነው። የጎጃም ሕዝበ ክርስቲያን ወንጌል የጠማው አንጅ ስለ ማህበረ ቅዱሳን ተንኮል አይደለም።ገና ጳጳሳቱ የባሰውን ይከፋፈላሉ። ጦርነቱ ተጀመረ እንጅ አልተፈጸመም። ማቅን አንቀበልም ያሉ ብጹዓን አባቶች መከራ መቀበል ጀምረዋል። ሁል ግዜ ስለ ወንጌል የምናገሩና ወንጌልን ስበኩ የምሉ አባቶችና ወንድሞች መከራ ከመቀበል አልተቆጠቡም።ሐወርያት የተቀበሉት መከራ ስለሆነ አድስ አይደለም። እኛ የሚንሰብከው በቀራንዮ የተሰቀለዉን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው እንዳለው ሐዋርያው እዉነቱ መነገር አለበት።ለእግዚአብሔር ክብር መሰደብ አባቶችን ያጠነክራቸውል እንጅ አያደክማቸውም። የማቅ ገንዘብ ይቀራል እንጅ የክርስቶስ ፍቅር አይቀርባቸውም። ማቅ እኮ ትላትና ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳዉሎስ ተሐድሶ ያለቸው ክፉ ማህበረ ስለሆነ አቡነ ማርቆስ መናፍቅ ብላቸው አደንቅም። ከዚህ የተዋህዶ ልጆች ምን እንማር ይሆን?

  ReplyDelete
 4. Wey Tata Yechi betekerestiyan min Yesalatal?

  ReplyDelete
 5. ቤተክርስቲያን “እንተ ላዕለ ኵሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት” (ካቶሊካዊት/ ኵላዊት) መኾኗ ከታመነ ሰውየው ክርስቲያን መኾኑ እንጂ ተወልዶ ያደገበት ሀገር ለምን ይጠየቃል? ይህ ትምህርት ከየት የመጣ ነው? በእርሱ ብንዘራበት መበስበስን እናጭድ ዘንድ ካለን ከምድራዊው የዘር ሐረግ ይልቅ ሰማያዊው፣ የማይጠፋው ዘር አይበልጥም ነበር ወይ? ከዚህ በላይ ዘረኝነት ከየት ይመጣል? በካሪቢያን ያሉት አማኞቻችኹ፣ በደቡብ አፍሪካ ያሉት የቤተክርስቲያናችኹ አባላት፣ በአሜሪካ የሚገኙት አሜሪካውያን የቤተክርስቲያኒቱ ልጆች፣ በደቡብ ሱዳን ወደፊት ሊኖሩ የሚችሉ ደቡብ ሱዳናውያን በፍጹም ፓትርያርክ የመኾን ኃላፊነት መቀበል አይችሉም ማለታችኹ ነው ወይ? ወንጌል ይህንን ያስተምረናልን?

  ኢትዮጵያውያን ሀገራችኹን እንደብቸኛዋ የመንፈሳዊነት ማማ እየቆጠራችኹ ስትታጀሩ ሌላው የክርስቲያን ዓለም ጥሏችኹ ነጎደ! ክርስትና ሕይወት ሳይኾን ተራ ባህል ኾነባችኹ፡፡ ቃሉን ከማድመጥና ከማስተንተን ይልቅ እርስበርሳችኹ ጎራ ለይታችኹ ስትታኮሱ ቤተክርስቲያናችኹን የፖለቲከኞች መጫወቻ አደረጋችኋት፡፡ ቤተክርስቲያኗ ክርስቶስ አልባ ኾነች፡፡ ወንጌልን ለባህላችኹ ሰጋጅ አደረጋችኹት፡፡ ፈጣሪን በአምሣላችኹ ለመፍጠርና በሞኖፖል ለመያዝ ትታትራላችኹ፡፡

  ተነግሮ የማያልቀውን በኢየሱስ የተገለጠው የእግዚአብሔርን ፍቅር ከመነጋገር ይልቅ ስለአንድ ገድል በመጨቃጨቅ ጊዜያችኹን ታባክናላችኹ፡፡ ይህ ኹሉ የኾነው ቤተክርስቲያኗ ለወንጌል ትኩረት የሚሰጥባት ስላልኾነች ነው፡፡ ያለ አንዳች በቂ ትምህርት ቄስና ዲያቆን የሚኮንባት ቤተክርስቲያናችኹ ወንጌል ሰባኪ ሳትኾን ባህል ጠባቂ ሙዚየም፣ ፖለቲከኞችን ስትሞዳሞድ የምትኖር የፖለቲከኞች መሣሪያ ኾነች፡፡ ለዚህ ከአፄ ዘርዐ ያዕቆብ ጀምሮ፣ ደርግን አጢኖ፣ 1997ን ማስታወስ በቂ ነው፡፡ ያ ኹሉ ደም ሲፈስ ቤተክርስቲያናችኹ ከፖለቲከኞቹ ጋር ተሞዳሞደች እንጂ እንደክርስቲያን ጽኑ አቋም አልያዘችም፡፡ በእኔ ዕይታ የዚህ መነሻው የካህናታችኹ የትምህርት እጥረት ነው፡፡ ከሲኖዶሳችኹ ስብሰባዎች ዘገባዎች እንደታዘብኹት ጳጳሳታችኹ የተጠሩበትን የእረኝነት ተግባር ምንነትና የጠሪያቸውን ማንነት ፈጽመው የተረዱ አይመስሉም፡፡ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ካህናታችኹ ክህነትን እንደ ማኅበራዊ ከፍታ (Social status) እንጂ እንደምሥጢር የሚመለከቱም አይመስሉም፡፡ “ሆዴ ይሙላ! ደረቴ ይቅላ!” የኑሮ ፍልስፍናቸው ይመስላል፡፡
  ወንጌል የማያውቁ ቀዳሾች፣ የክርስትና ስብከት ማዕከሉ ኢየሱስ መኾኑን ዘንግተው ገድል ሲተርኩ የሚውሉ ሰባኪዎች፣ በንግሥ በዓላት ላይ የሕዝቡን ኪስ በማራቆት የአስተዳዳሪዎችን ጉርሻና እንክብካቤ የሚያሳድዱ “መምህራን”፣ ሥራ ፈት መነኮሳት፣ ቆብ ጭነው ድራፍት ቤት የሚገኙ፣ ጥምጥም ጠምጥመው ጠጅቤት የሚሠየሙ፣ የንስሐ ልጆቻቸውን በዝሙት ቀንበር የሚጠምዱ፣ ጥንቆላን ልማድ ያደረጉ፣ ስለ ንስሐ ልጆቻቸው መንፈሳዊ ሕይወት ሳይኾን እኪሳቸው ስለሚጨመረው የጉርሻ ገንዘብ የሚዋትቱ ካህናት ይህችን የስንት ክርስቶሳዊ ሀብት ባለቤት የነበረች ቤተክርስቲያን ሞልተው አፍነዋታል፡፡ የካህናቱ የጌታን ቃል አለማወቅና ችላ ማለት ቤተክርስቲያናችኹ ጥቂት መጻሕፍት ባነበቡ ነገር ግን እዚህ ግባ የሚባል የቤተክርስቲያን ዕውቀት (ecclesiastical knowledge) በሌላቸው ፊዚክሰኞችና ኬሚስትሪኞች እጅ ላይ እንድትወድቅ አደረገ፡፡ ግብጾች ከዓለም ክርስትና ገንጥለው ሲጫወቱባት የከረሙትን ያህል አሁን ደግሞ ፊዚክሰኞቹና ኬሚስትሪኞቹ ከወንጌል ይልቅ ባህልን ማዕከል ባደረገ የኹለንተናዊ ዕድገት መርሐ ግብራቸው ግራ ሲያጋቡ እንዳይኖሩ ያሠጋኛል፡፡

  የሚገርመው ነገር አለኝ ከምትለው ከአርባ ሚሊየን ምእመን መካከል 10 በመቶው እንኳ ቅዱስ ቁርባን የማይቀበልባት፣ ምእመኑ የጌታን እራት እንደ ጦር የሚሸሽባት፣ መጽሐፍ ቅዱስን ፈጽሞ የማያነቡ ምእመናን የሞሉባት ቤተክርስቲያን ራሷን ተሐድሶ አያስፈልገኝም ብላ ስትናገር ነው፡፡ ተሐድሶ አያስፈልገኝም ማለት ንስሐ አያስፈልገኝም፤ ድርጊቶቼ ኹሉ ንጹሐን ናቸው ብሎ መታጀር ነው፡፡ ነገር ግን “ለእመ ንቤ አልብነ ኃጢኣት ንሔሱ ወኢንገብራ ለጽድቅ፡፡” ተብሎ ተጽፏል፡፡ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ስለኾነች ንጽሕት የመኾኗን ያኽል የእኛ ኃጢኣት እየተመላለሰ የሚያረክሰን የምእመናን ጉባኤ ስለኾነች ኹልጊዜም በንስሐ መታደስ ያስፈልጋታል፡፡ በየጊዜው ቤተክርስቲያን ውስጥ ሲጎሰጎሱ የኖሩት የሐሰት፣ የጭካኔ፣ የዘረኝነት፣ የዕውቀት ማጣት ግብስብሶች ወንጌልን መንሽ ባደረገ ንስሐና ዕውቀትንና ጸሎትን (ድጋምን አላልኩም፡፡ መድገምና መጸለይ ለየቅል ናቸውና፡፡) ሊጠሩ ይገባቸዋል፡፡

  እርግጥ ነው ኪዳኑ፣ ቅዳሴው፣ ድጓው ምንጫቸው ወንጌልና ወንጌልን “የበሉ” ቅዱሳን አበው ነበሩ፡፡ ዛሬ ያለው ትውልድ ግን ዐወቀ ከተባለ ያንን ከመሸምደድና ከመድገም ውጪ የራሱን መንፈሳዊነት በወንጌል መሠረት ላይ ሲጥል አይታይም፡፡ ቅዳሴን ያኽል ንዑሰ ክርስቲያን እንኳ ሙሉውን እንዲካፈሉ ያልተፈቀደላቸው ልዩ ጸሎት ለከት በሌለው ድምጽ ማጉያ በየገበያውና በየመጸዳጃ ቤቱ እንዲሰማ የተደረገው ይህ የተሸመደደው ወይም በቃል የተጠናው ዜማ ሕይወት ስላልኾነን ነው፡፡ የሚያዜመውን የሚያስተውል ስንት ይኾን?

  በቤተክርስቲያኒቱ ዘንድ ዕውቀትና ወንጌል ትኩረት እንደተነፈገው ለማየት ካስፈለገ በአሜሪካ ሀገር ያለው ሲኖዶስ በሀያ ዓመት ክራሞቱ አንድ እንኳ ካህናት ማሠልጠኛ የነገረ መለኮት ኮሌጅ አለመክፈቱ፣ ኢትዮጵያ ያለው ሲኖዶስ ደግሞ ካሉት ጳጳሳት መካከል ዶክተሮቹ እንኳ በመንፈሳዊ ኮሌጆች ተገኝተው ሲያስተምሩ አለመታየታቸው፣ ካሉት ሦስት ኮሌጆች ያልተመረቁ ሰዎችን ክህነት እንዳይሰጣቸው ማድረግ አለመቻሉን ማንሳት እንደሚቻል አምናለኹ፡፡

  ቤተክርስቲያኗ ከተጫነባት የብሔራዊነት የፖለቲካ ቀንበር እንድትላቀቅ የተማሩ ካህናት ያስፈልጓታል፡፡ ለዚህ ደግሞ መንፈሳዊ ኮሌጆቿን በጥብቅ መጠበቅና ከጥቃት መከላከል አለባት፡፡ አልያ በብሔራዊነት ስም ወደ ሙዚየምነት መለወጧ አይቀርም፡፡ ሙዚየም ደግሞ ወንጌል ጉዳይዋ አይደለም፡፡

  ReplyDelete
 6. please let us humble our self for the Lord God words. How many peoples daily read Holy Bible at home in our church followers? That is the lack of church leaders not doing or practicing there spiritual obligation. why our church sticky in political issue instead of share word of God.? why in this church members hate each other? the answer is lack of a bible in our daily life. every body are hungry for word of Lord. that why we need change in the systems and biblical preach.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Do u think in families live in Protestant countries read Holy bible daily? Please don't be ignorant.

   Delete
  2. The question is about deeds, be meshemded adelem mengste semayat yemigebaw. If it were I will be the first. "Terbe abiltachihugnal?, tarizhe albisachihugnal, tasire..." u don't deny it this is the direct word of Jesus christ. My mother doesn't read & write. She knows about God what is told to her.But practically she is a real christian whom Jesus loves by her act. She is a better person than me who acquire MSC with 20s. I read bible from the first page to the end several times & other books but...

   Delete
  3. Getaw what about protestants who quarell each other daily in the church but know bible as knowledge but not in practice. Reading is not a guarantee it is ur willingness to give ur life to God.

   Delete
 7. Hi abba selamawoch,
  why don't u post some of the excellent comments as main post for further dialogue? I think, it will be so useful for the development of the church. For example, the comment by christian sounds very touching but it may also need further theological development. This will invite the theologians of the church to participate further in your blog. So, please think about widening the space to theologians to express their thoughts.

  ReplyDelete