Sunday, December 9, 2012

የአንድነት ጉዟችንን ጀምረን ከግማሽ በላይ ተጉዘናል - ብጹዕ አቡነ መልከጼዴቅ

ዛሬ በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከሁለቱም ሲኖዶሶች የመጡ አባቶች በአንድነት  ተገኝተው የቅዳሴ ስነ ስርዓት አካሂደዋል። ቅዳሴውን በዋናነት የቀደሱት በስደት ያለው ሲኖዶስ አባል የሆኑት ብጹዕ አቡነ ኤልያስ ሲሆኑ በቅዱስ ቁርባን ሰዓት ላይ ደግሞ በአዲስ አበባው ሲኖዶስ ስር ያሉት ብጹዕ አቡነ ቀውስጦስ ትምህርት አስተምረዋል።  ከዚያም በስደት ያለው ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብጹዕ አቡነ መልከጼዴቅ ትምህርትና ቃለ ምዕዳን ሰጥተዋል። ዘማሪ ትዝታው ሊነጋ ሲል ይጨልማል የሚለውን መዝሙር በምዕመናን  ግብዣ የዘመረ ሲሆን ከራሱ ደግሞ የፈራ ይመለስ ከልዓድ ተራራ የሚለውን መዝሙር ዘምሯል። የእርቁን ውጤት በጉጉት ሲጠብቅ የነበረው የዳላስ ህዝብ ከምን ጊዜውም በበለጠ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያኑን አጨናንቆ ነበር።

የዕለቱ ፕሮግራም የተመራው በዲያቆን አንዱዓለም ሲሆን ዛሬ ከሰዓት በሁዋላ ( በማታው ጉባኤ)  የመላው ዳላስ ምዕመናን በሚገኙበት የእርቅ ድርድሩ ውጤት በመግለጫ መልክ በዳላስ ሚካኤል ይቀርባል።

የብጹዕ አቡነ መልከጼዴቅ የትምህርት ርዕስ «አባት ሆይ እኔ እና አንተ አንድ እንደሆንን እነርሱም በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምንሃለው» የሚለው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸሎት ነበር። በዚህ ርዕስ ስለ አንድነት ሰፋ ያለና ህዝቡን ያስደሰተ ትምህርት ሰጥተዋል። የብጹዕነታቸው ትምህርት የሚከተሉት የሰላምና የአንድነት ሃሳቦች ነበሩት፦

አንድነትን የማይፈልግ ሰይጣን ስለሆነ ሰይጣን ሊለያየን ይፈልጋል እግዚአብሔር ግን አንድነትን ይወዳል፤ ጌታም በመካከላችሁ እገኛለሁ ብሎ ቃል የገባው ሁለት ወይንም ሶስት ሆነን በአንድነት በምንሰባሰብበት ነው። አንድነት ኃይል ነው፤ ድር ቢያብር አንበሳ ያስር ፤አንድ ከሆንን ለጠላት አንጋለጥም፤ አንድ ከሆንን እግዚአብሔር ከኛ ጋር ይሆናል። እግዚአብሔር ከኛ ጋር ከሆነ ደግሞ ማንም አይችለንም። ብጹዕነታቸው  ስለ አንድነት በምሳሌ ሲናገሩ፦ አንድ ሰው 12 ልጆች ነበሩት 12ቱም በትር እንዲያመጡ አደረገና 12ቱን በትር በአንድነት እንዲያስሩ አደረገ። ከዚያ 12ቱንም በየተራ እየጠራ በሉ ይህንን ስበሩ አላቸው። 12ቱም ልጆች ሲሞክሩት መስበር አልቻሉም። ነገር ግን በትሮችን ለየብቻ እንዲይዙ አድርጎ ስበሩ አላቸው፤ ልጆቹም ለየብቻ ያሉትን በትሮች በቀላሉ ሰባብረው ጣሉት። ስለዚህ ኃይል ሲበተን ይሰባበራል፤ አንድ ላይ ሲሆን ግን አይሰበርም። በዘመነ መሳፍንት ጎጃም፤ ትግሬ፤ ሸዋ የራሱ መስፍን ነበረው፤ በመካከላቸውም ከፍተኛ ልዩነት ነበረ። በዚህ ጊዜ ግን ቤተክርስቲያን አንድ ነበረች። በሁዋላም ጣሊያን አገራችንን ሲወር የቤተ ክርስቲያን አንድነት ህዝቡን ስላስተባበረ በትግል አገራችንን ነጻ ልናወጣ ችለናል። አሁንም እኛ አንድ ብንሆን ብዙ ጥቅም ለሃገራችንም ሆነ ለቤተክርስቲያናችን እንሰራለን። በተለይም እናንተ ምዕመናን የዚያኛው የዚህኛው እያላችሁ አትከፋፈሉ። ገለልተኛ ነን ለሚሉ አብያተ ክርስቲያናትም መልዕክት ነበራቸው፤ ከምኑ ነው ራሳችሁን ያገለላችሁ ሲሉ ጠይቀዋል። Independent (ገለልተኛ) ማለት ነጻነት ማለት ነው። እናንተ ከምን ነው ነጻ የወጣችሁት ብለው ህዝቡን አስቀውታል።    በመጨረሻም የዚህ ሁሉ ችግር ፈጣሪዎች እኛ ጳጳሳቱ ነን ብለዋል። ነገር ግን አሁን ከኛ ታናናሽ በሆኑ ወንድሞች የሰላም ኮሚቴ አባላት አማካኝነት የሰላም ጉዞው ተጀምሮአል።  በተለይም በዚህ በዳላስ የታየው የሰላም ጅማሬ ከድሮው ጊዜ የተለየ ነው። አብረን በልተናል፤ አብረን ጸልየናል፤ አብረን ውለናል፤ አብረን ስጋ ወደሙ ተቀብለናል። ዛሬ እንዲህ እንዳደረግነው ሁሉ እኛም አዲስ አበባ ሂደን እንደዚህ ልናደርግ እንችል ይሆናል በማለት ለአንድነት ያላቸውን ጉጉት ገልጸዋል። ይህ ጅማሬ የፍጻሜውን መልካምነት ያሳያል። የአንድነት ጉዞ ጀምረናል ከግማሽ ጉዞም በላይ ተጉዘናል።  ወደፍጻሜው እየገሰገስን ነው ፤ ለዚያ ፍጻሜ ሁላችንንም ያድርሰን በማለት የአንድነት መንፈስ የሚንጸባረቅበት መልዕክት ለተሰበሰበው ህዝብ አሰምተዋል። 

በመጨረሻም በአቡነ ኤልያስ አሳራጊነት ሰርሆተ ህዝብ ተደርጎአል። በማታው ፕሮግራም የሚነበበውን መግለጫ እንደወጣ ተከታትለን እናቀርብላችሃልን


12 comments:

 1. እንደማይሆን እኮ ዐቃቤ ቤቱ አቡነ ናትናኤል ነግረውናል። የልጆቻቸውን የነ ዐባይ ፀሐየን ፈቃድ ይፈጸሙ ወይስ የቤተ ከርስቲያንን? ፕረዚደንት ግርማ የጻፉትን መልካም ደብዳቤ እንዲሰርዝ ያደረጉ 'አባት' እኮ ናቸው። ነገሩን ሁሉ ለታሪክ እና ለእግዜብሔር ብቻ ሰጥቶ የፍርድን ቀን እየተጠባበቅን መቆየት ብቻ ነው።

  ReplyDelete
 2. አይቴ ሐለው ቀደምት ጳጳሳት እለይትቀነዩ ለመለኮት ፥ ወልሳነ ንባቦሙ ርትዕት፥ ወፍትሖሞ ፍትሕ ወርዕት፥ ኢፈርህዎ ለሞት ፈርሕዎ ለኃጢእት። =ለአምላክ ብቻ የሚገዙት ፥ ከአንደበታቸው የሚወጣው ቃል ቀጥተኛ የነበረ ፥ ፍርዳቸውም ፍትሐዊ የነበረው ፥ ኃጢአትን እንጅ ሞትን ያልፈሩት እኒያ የጥንቶቹ ሊቃነ ጳጳሳት ዛሬ የት አሉ ?

  ReplyDelete
 3. Ask yourself first. saying that where am I? Do not judge you will be judged. If you can and have a pure heart just pray to the Almighty God. Cut off you flesh and put on your spirit. Then you can live Godly life.

  ReplyDelete
 4. Abune Natinaeil Tikikil Nachew Pirezident Girma patiryarik Meshomna Meshar Yichilalun ? Yemisimamanin Tikikil Yemanfelgewin sihiitet malet yelebinim Abune Merkorewos Ketemelesum Memelesi Yemichilut sinodos Tesimamito siwesin Bicha New
  Lehayimanotachin Sibal bete Kiersityann Anid Lemadireg tebolo New enj Abune Merkorewos Derg Mehonachewna Egiziabher Yelem sibal yetesimamu Key Kard Yeneberachew Papas Mehonachewn Aliresanewim

  ReplyDelete
 5. ይድረስ በአገር ውስጥና በውጭ አገር ለምትገኙ ለውድ አባቶቻችን ብጹአን ሊቀ ጳጳሳት።
  ከሁሉ አስቀድሜ የማክበር ትትና የተሞላበት የልጅነት ሰላምታየን ዝቅ ብየ ከጫማችሁ ስር ተደፍቸ አቀርባለሁ። ቡራኬአችሁ ለእኔና ለመላው የአለም ሕዝብ ይድረሰን እያልሁ በመልመን ከዚህ በታች የማቀርበውን አቤቱታየን ትሰሙልኝ ዘንድ በማክበርና በትትና እለምናለሁ።
  ስሜ ዳንኤል እባላለሁ፤ እድሜየ 20 ነው፤ የትውልድ ቦታ ሰሜን አሜሪካ ነው፤ ስራየ ተማሪ ነው፤ እምነቴ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነው።
  በጉጉት መልካም ውጤቱን እየተጠባበቅን ያለው የአባቶች ዕርቀ ሰላም ውይይት በአሜሪካዋ የቴክሳስ ግዛት ዳላስ ከተማ እየተካሄደ መሆኑን ይታወቃል። ይህ በእንዲህ እያለ ኣባታችን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ናትናኤል ለ VOA እንደተናገሩት ፓትርያርኩ (አቡነ መርቆሬዎስ) ወደ ሀገራቸው ገብተው በመረጡት ቦታ መቀመጥ እንደሚችሉ እንጅ ከዚያ የተለየ ምንም ሌላ ነገር እንደሌ ገልጸዋል።፣ በውጭም ሆነ በዉስጥ ያለነው ብዙዎቻችን የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች እንደጠበቅነው፥ የተጣሰው ቀኖና ተስተካክሎ በአንድ ቅዱስ ሲኖዶስና በአንድ ቅዱስ ፓትርያርክ የምትመራ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ትኖረናለች ብለን አስበን በጸሎትና በስግደት አምላካችንን ፈጣሪያችንን ያስጨነቅነውን ተስፋ ያጨለመብን ይመስላል። ምንም እንኳን የእግዚአብሔር ሃሳብና የሰው ልጅ ሀሳብ አንድ ባይሆንም የነበረው እንዳልሆነ ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት።
  ቤተ ክርስትያኗ የምትመራው በአንድ ፓትርያርክ ነው፤ በፓትርያርክ ላይ ፓትርያርክ አይሾምም፤ ቀኖና ተጥሷል፤ ውግዘት ይንሳ፤ እርቅና ሰላም ይውረድ እንዲሁም የመሳሰሉትን መንፈሳዊ ጥያቅይዎች መልስ ልማግኘት እውነት ከዚህ የሻለ ጊዜ አለን?
  አቡነ መርቆሬዎስ በህይዎት አሉ፤ ስልጣናቸው መንፈስ ቅዱስ የሰጣቸው ስልጣን ነው፤ ከሃገር የወጡት ተገፍተው ነው፤ ሕዝባቸውን በሙያቸው እያገለገሉ ናቸው። ምእመናን የምናውቀው፥ የምናየውና የምንሰማው ሀቅ ይህ ሆኖ እያል፤ ታድያ ለምን ሌላ ፓትርያርክ መምረጥ አስፈለገ? ውድ አባቶቻችን ከኰሚዩኒዝም ጀምሮ እስከ ቅርብ ጊዜ እግዚአብሔር በሀገራችን ላይ ያደረገው ለእናንተ ግልጽ ሳይሆንላችሁ ቀርቶ አይደለም፤ እግዚአብሔር ያረመውን እኛ ፍጡሮቹ እንዳናበላሽ እናስተውል እንጂ፤ በማቴ ፮፥፲፬ -፲፭ ያዘዘው እናንተን አይመለከታችሁም?
  ሁሉም ለማለት ብቸገርም፤ አብዛኛው ምእመናን ዛሬ ይቅር ለእግዚአብሔር እያል ይገኛል። ከአባቶቻችንም ይህንኑ ይጠብቃል። በጐች ተቅበዘበዙ፥ በጐች ጥሩ እረኛ ፈለጉ፥ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች ሰግስገው ገብተው በጐችን እያመሱ ናቸው፤ የተኩላው መንጋ ራቅ ብሎ በጐች እስኪበተኑ ይጠብቃል። ልጆቻችሁ ተኩላውን እናሸንፍ፤ አባቶቻችን እርዱን? ይህን አድርጉልን?

  አቡነ መርቆሬዎስ ፈቃደኛ ከሆኑና በቀራቸው የእድሜ ዘመን መንጋውን ለመጠበቅ ፈቃደኛ ከሆኑ:-
  ፩ ወደ ኢትዮጵያ ይግቡ፣
  ፪ ማእረጋቸው ፬ኛው ፓትርያርክ እንደሆነ ይጠበቅ፣
  ፫ አሜሪካ ከ፬ ባላነሰ አህጉረ ስብከት ትከለል፣
  ፬ ቃለ አዋዲ በመላው የውጭ አገር ላሉ የኢኦተቤክ ባስቸኳይ ይሰራጭ፣
  ፭ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ከሙስናና ከዘረኝነት ባስቸኳይ ትንጻ፣
  ፮ ስራችን ሁሉ ክርስቶስን ይምሰል፤ ቅድስትና ብጽእት ማርያምን እናስብ፥ የመላይክትን አገልጋይነት እንይ፥ ጻድቃንና ሰማእታት ትተውልን እንዳለፉ ጠብቀን እናስተላልፍ።
  የቅዱሳን አምላክ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን፤ አሜን።

  ReplyDelete
 6. Abba Selama Atissatu Bizu Neger Tawikalachihu Abune Melketsedik & Abune Gerima Yalubet Neger Selam Yihonal Malet zebet new Mekeled new yeteyazew Ahun Leyekatit ( febrewary )Ketsero yizewal Abune Merkorewos Megibat yemichilut Bemin yihun Bemilew Malet New

  ReplyDelete
 7. His Excellency Abbuna Mekiesdike Arcbishop the great journy and remarkable work,with grea prsonality and top biography his lif in the Ethiopian Orthdox Tewahido church. still menataly alret and fanctioning effectively at the age of 90 the witeness of the truth and the guidance of the right way. Execellent.

  ReplyDelete
 8. It is really very sad not only to witness the" peace and reconciliation" miserably failed but also watching those "big religious leaders " trying to make the innocent followers of the Church believe that their getting together (meeting), and praying together ( I do not know if we can call it prayer in the real sense of the term) is a great step forwad. Is this the character of teaching and living by example as Jesus himself and his desciples did or ....? I think the innocent followers of the Church are sick and tired of talks just for the sake of talks (most of the time misleading and deceiving) which has become very serious illnessses not only in arena of politics but also in the world of faith or religion. I do not know why the negotiators did not tell us how "their great hope" for success they are going to make it next month (in LA)and the very categrical statements from Addis Ababa can make common sense.

  ReplyDelete
 9. This is the truth, whether we like it or not:

  1. The negotiation for peace and unity that took place in Dallas during Dec. 4-8, 2012 has FAILED!
  2. Although the Papasat wined, dined, and prayed together, they were in contravention of their respective condemnation i.e. "Wugzet"! It is extremely sad that they failed to at least lift the "Wugzet".
  3. The basic problem which the Papasat have been unable to resolve is the competition for leadership. It's shameful to note that monks who are supposed to care less for worldly honour are creating huge problems for the church because of their interest in such privileges.
  4. Only the Almighty God will rid us of such irresponsible people.

  ReplyDelete
 10. Begbstaweyan papsat betmera yeshalen neber oh akatayoch hulum seltan felage ahun papasatu patryark lemeshom tefozo eyasebasebu nachew tadya yeymsel erke weshetamoche begzeabhar bet yemitachberebru zemawoche

  ReplyDelete
 11. His Excellency Abbuna Mekesedik, the man with great spritual journy all his life in the Ethiopian Orthodx Tewahido Church With remakeble work,top in biography, still doing such great job to save the ordinal constitution of this Historic church the Identity of Ethiopia.His actively working had to preserve Church as it is for the generation to come. He is mentaly alert, moraly strong, fanctioning effectively,playing majore role to restor the unity of the Ethiopian Orthodx Tewahido Church at age of 90 by the help and grace of almight God. Mengesha

  ReplyDelete