Tuesday, January 29, 2013

ጌታ በወንጌል ስለ እናቱ የተናገራቸው ንግግሮች ለምን ቀጥተኛ አልሆኑም?

በትውፊት እንደሚነገረው ጥር 21 የእመቤታችን የእረፍቷ መታሰቢያ ቀን ነው፡፡ ሆኖም የእረፍቷን መታሰቢያ ማድረግ ካስፈለገም በዚያው ባረፈችበት ቀን ብቻ መሆን ሲገባው ወርሃዊ ተደርጎ በቤተ ክርስቲያናችን ያሉትን የበዓላት ቁጥር ከፍ እንዲል አድርጎታል፡፡ ይህ በእርሷ ብቻ ሳይሆን በሌሎቹም ቅዱሳን ስም የተሰሩት በዓላት ላይ ሁሉ የሚስተዋል ነው፡፡ ነገር ግን መስተካከል አለበት፡፡
በዚህ ጽሑፍ ስለዕረፍቷ የምለው ነገር የለም፡፡ ጌታ ከእናቱ ጋር በተያያዘ ለተጠየቃቸው ጥያቄዎች የሰጣቸው መልሶች፣ በእርሷ ዙሪያ የሰጣቸው አስተያየቶች ቀጥተኛ አልነበሩምና ለምን ቀጥተኛ አልነበሩም? የሚል ጥያቄ ለማንሳትና በዚያ ላይ ሐሳቤን ለማካፈል ነው፡፡ እውነት ነው፤ እናት አባትህን አክብር ብሎ ያዘዘን ጌታ የሰጣቸው ምላሾች ቀጥተኛ አለመሆናቸው እናቱን ለማቃለል ፈልጎ እንዳልሆነ በእርግጥኝነት መናገር ይቻላል፡፡ ታዲያ ምክንያቱ ምን ይሆን? እስኪ በመጀመሪያ ጥቅሶቹን እንመርምራቸው፡፡

Sunday, January 27, 2013

የዳንኤል ክብረት ክሽፈት ጥር 2005
አቶ ዳንኤል ለመናገርና ለመጻፍ ያለው ፍጥነት በሚናገርባቸው ጉዳዮች ላይ ካለው እውቀት ጋር አይመጣጠንም፤ እንዲያውም ያውቃል እንዲባል የሚጽፍ አንጂ አውቆ የሚጽፍ አይመስልም፤ አቶ ዳንኤል ሳላውቀው በጻፈው ላይ አስተያየት ስሰጥ ይህ ሁለተኛዬ ነው፤ ከዚህ በፊት በአንድ ጋዜጣ ላይ በጣም የታወቀውን የአየርላንድ ችጋር 150 ዓመታት ያህል አቅርቦት በማየቴ አስተያየት ሰጥቼበት ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ስለመክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ በጻፈው ላይ አጭር አስተያየት ልስጥ፤ እንዲያው እንትንን እንትን ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታል የሚባለውን በመከተል እንጂ ትርፍ ይኖረዋል ብዬ አልገምትም፤ ከደርግ ዘመን ጀምሮ የተለያዩ ካድሬዎች ደብተራዎችም ጭምር ማነብነብን እንደተናጋሪነት ሠልጥነውበታል፤ ስለዚህም ሰውም ማነብነባቸውን እንደእውቀት እየወሰደው ይወናበዳልና በጊዜው መልስ መስጠት ግዴታ ይመስለኛል፤ የሰው ልጅ በምን ይታፈራል? በወንበር፤ በወንበር አይደለም በከንፈር፤ ይባላል፡፡
ነገር ሳላበዛ ጥቂት ነጥቦችን በማንሣት የአቶ ዳንኤልን የማንበብ ችሎታና የተንኮል ክህነት ብቻ ለአንባቢዎች ላሳይ፤ ስለአስተያየቱ አስተያየት መስጠት አስፈላጊ አይደለም፡፡

Saturday, January 26, 2013

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የጥምቀት መልዕክት በጽሑፍ

ጥር 11 ቀን (January 19, 2013)  በስደት የሚገኙት 4ኛው ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ በወቅታዊው የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ዙሪያ የሰጡትን መግለጫ በቪዲዮ አቅርበንላችሁ ነበር።  አንባቢያን በጽሑፍ እንዲደርሳችሁ በጠየቃችሁት መሰረት የቅዱስነታቸውን መልዕክት ከዚህ በታች አስቀምጠናል።ለአቶ ማንያዘዋል የተጻፈው ደብዳቤና አንድምታው

ስለማንያዘዋል ከዚህ ቀደም ስንዘግብ ነበር፡፡ አንዳንዶች የምንዘግበውን ሐሰት ነው ሲሉ የቆዩ ቢሆንም ከአቃቤ መንበር ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የተጻፈው ደብዳቤ ግን እስካሁን ስንዘግብ የነበረው ሁሉ እውነት መሆኑን ያረጋገጠ ነው፡፡ ማንያዘዋል በፎርጂድ የትምህርት ማስረጃ ስላሴ ኮሌጅ ገብቶ በሰዎች ድጋፍ እንደምንም «ተመርቆ» ቢወጣም ቤተክርስቲያኗ በአቶነቱ ነው የምታውቀው፡፡ «ፊደል ዳገቱ» ማን ያዘዋል ለማቅ «መምህር» ቢሆንም እኛ ግን በትክክለኛ ማእረጉ አቶ ማንያዘዋል እያልን ነበር የምንጠራው፡፡ የአቃቤ መንበሩ ደብዳቤም አቶ ሲል ነው የጠራው፡፡
በዘንድሮው የጥምቀት በዓል በተሰራ አንድ ፕሮግራም ላይ ማን ያዘዋል በኢቴቪ መስኮት ብቅ ብሎ ስለ ቤተክርሰቲያን ለማስረዳት ሲውተረተር ታይቷል፡፡ ይህን አቶ በመምህር ደንብ ጋብዘው እንዲደሰኩር እድሉ ተመቻችቶለታል፡፡ ይህም አንዳንድ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ውስጥ ያሉ የማቅ ሰዎች ያደረጉት እንደ ሆነ ይታወቃል፡፡ ቤተክርስቲያን «አቶ» ያለችውን ማንያዘዋልን ደብዳቤ ከተጻፈበት በኋላ ከቤተክህነት ግቢ ቢታገድም አለ ለማለት ያህል ይህ እንደተደረገ ተገምቷል፡፡ ኢቴቪ ላይ ስሙ ተጽፎ የተነበበውም አቶ ማንያዘዋል አበበ ተብሎ ነው፡፡

Friday, January 25, 2013

ጥንቆላ - በሀገራችን ፣ በቤተ ክርስቲያናቸን እንዲሁም በእያንዳንዳችን ላይ ሊኖረው የሚችለው ተጽዕኖ

ራሳችንን ከጥንቆላ ስራዎች ለመጠበቅ ወይንም ሳናውቅ የጥንቆላ ስራዎች ተባባሪ ከመሆን ለመዳን ስለ ሀገራችን የጥንቆላ ዘዴዎች መጠነኛ ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል። ጠንቋይ ማለት ጠንቅ ዋይ ወይም ጠንቀኛ ማለት ነው። በሀገራችን ሁለት ዓይነት የጠንቋይ አይነቶች አሉ። አንደኛው ወገን ባለ ዛር፣ ባለ አውሌ (ውቃቤ) የሆኑትን ሲያካትት ሁለተኛው ወገን ደግሞ ደብተራ የሚባሉትን ያካትታል።  
ባለ ዛር ወይንም ባለ ውቃቤዎች
አውሌ ወይም ዛር የሚባሉት በሰው ላይ ሰፍረው አምልኮን ለራሳቸው የሚወስዱ የአጋንንት ወገን ናቸው። ባለ አውሌዎች በመላው ኢትዮጵያ ይገኛሉ። በኦሮሞው፣ በአማራው፣ በጉራጌው ወዘተ በየትኛውም ብሔር ብሔረ ሰብእ ዘንድ በብዛት አሉ። ብዙዎቹ ሃይማኖታቸው እስልምና ወይም ኦርቶዶክስ ክርስቲያን እንደሆኑ ይናገራሉ።  ብዙውን ጊዜ አማኞች ለመምሰል የአላህን ወይም የእግዚአብሔርን ስም ያነሳሉ። እንዲህ የሚያደርጉት ብዙዎች ደንበኞቻቸው ከእስልምና ወይም ከክርስትና የመጡ ስለሆኑ ይመስላል። ኢየሱስ የሚለውን ስም ግን ተሳስተውም እንኳ አይጠሩትም።

Wednesday, January 23, 2013

የጸረ ተሀድሶ ሰባክያን ጥምረት ቡድን ተበተነ

ጥምረቱን ከመበተን ለማዳን አሉላ እየሰራ ነው
ማቅ በመለመላቸው ሰዎች ያደራጀውና በገንዘቡ የሚደግፈው የጸረ ተሀድሶ ሰባኪዎች ጥምረት እያለ ራሱን የሚጠራው ጸረ ወንጌል ቡድን መበተኑ ተሰማ፡፡ ባለፈው የቱሪስት ሆቴል መዘጋትን ተከትሎ በውስጡ ይሰበሰቡ የነበሩ ሰባኪዎች መሰብሰቢያ ማጣታቸውን ገልጸን ነበር። ባወጣነው ዘገባ መነሻነት መረጃው እንዴት ሾልኮ ሊወጣ ቻለ በሚል የቡድኑ አባላት እርስ በርስ ሲካሰሱና ሲጣሉ መሰንበታቸው ታውቋል፡፡ ለመረጃው ሾልኮ መውጣት የቡድኑን አባል ዘሪሁን ሙላቱን ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን ይህን ተከትሎ በ5/5/2005 ወደ ሐረር እንዲጓዙ የተመደቡት ተስፋዬ ሞሲሳና ዘሪሁን የነበሩ ሲሆን ጥምረቱ ተስፋዬን ልኮ ዘሪሁን እንዲቀር አድርጓል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ለተስፋዬ ሞሲሳ ጋብቻ የጥምረቱ አባላት 100 ብር በነፍስ ወከፍ በህሩይ ባዬ (ወቅታዊ ስሙ ማጠልሸት ነው የማቅን ስም ለማጥፋት ሆነ ብሎ የገባ ነው ይሉታል) እጅ እየሰበሰቡ የነበረ ሲሆን ዘሪሁን ከሀረር ጉዞው መታገዱን ተከትሎ ብሩ ይመለስልኝ ሲል ጠይቋል ተብሏል፡፡ ሌላው የቡድኑ አባል ጳውሎስ ዱከሌ ከ3ኛ የሴት ጓደኛው የተበረከተለት አይፎን ሞባይል በመጥፋቱ እጅግ በጣም ከማዘኑም በላይ ክፉኛ መደንገጡን ቅርብ ጓደኞቹ ተናግረዋል፡፡ የደነገጠውም ጸያፍ ምስሎችን ስለጫነበት ነው ተብሏል፡፡ አሁን  የጥምረት ተብዬው ትልቁ ስጋትና ፍራቻ ዘሪሁን በለመደ እጁ መጽሀፍ እንዳያወጣብን የሚል ሲሆን እርሱም በእርግጠኝነት እንደሚያወራው በቅርብ ቀን ጉድ ጠብቁ ብሏል ተብሏል፡፡

Tuesday, January 22, 2013

ከእሾህ በለስ አይለቅሙም፥ ከአጣጥ ቍጥቋጦም ወይን አይቈርጡም!

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
(እርማችሁን አውጡ! ክፍል 3)
ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል።
የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።
ወይስ ከእናንተ፥ ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው?
ዓሣስ ቢለምነው እባብን ይሰጠዋልን?
እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥
በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው? ማቴዎስ ወንጌል 7፣ 7- 12
እንዲህ ባለ ሁኔታ ሁለቱም እውነት ሊሆኑ አይችሉም። ወይ "ሊቃነ ጳጳሶቻችን" አልያም ደግሞ ላይሰጥ ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ላይገኝ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ ላይከፍት መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል ያለ የቃሉ ባለቤት እግዚአብሔር ሐሰተኞች ነው። ታድያ ማን ይሁን እውነተኛ? እግዚአብሔር ወይስ እነ አቡኑ? መልሱ ቀላል ነው ቀጥለው እንደሚከተለው የሚቀርቡትን ሦስት መጠነኛ ትንተናዎች ልብ ብለን እንከታተል።

Monday, January 21, 2013

በቤተ ክህነት ፖለቲካው ማቅ ኪሳራ እየደረሰበት ነው

የማቅና የአቡነ ቀሌምንጦስ ፍቅር አልቋል  
ከአቡነ ጳውሎስ ሞት በኋላ ማቅ አለቅጥ ጣልቃ በገባበት የቤተክህነት ጉዳይ በረጃጅም እጆቹ በርካታ ግብታዊ እርምጃዎችን እያስወሰደ፣ የሚቃወሙትን እያስነሣ የሚደገፉትን እያስቀመጠ ሲንቧችበት የነበረው ቤተ ክህነት በተወሰነ መልኩም ቢሆን በማቅ ላይ ፊቱን እያዞረበት መሆኑ እየታየ ነው፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆኑት ማቅ በአንድ ጊዜ እላይ ወርውሮ መምሪያ ሃላፊ ያደረገውና በምርጫው ሥራዬን ይሰራልኛል ብሎ ተስፋ የጣለበት ሀይለ ጊዮርጊስ ተሽቀንጥሮ እታች መውረዱና በአሁኑ ጊዜ በወንጀል ተከሶ ሸዋሮቢት ማረሚያ ቤት መገኘቱ፣ የማቅ ዋና ወሬ አቀባባይ የሆነው ማንያዘዋል ቤተክህነት ግቢ እንዳይገባ በአቃቤ መንበር ናትናኤል መታገዱ፣ ይጠቀሳል።

Sunday, January 20, 2013

ቃና ዘገሊላ የማን ክብር የተገለጠበት በዓል ነው?


ትናንት በጥምቀት በዓል አንዳንድ ወጣቶች በለበሷቸው ቲሸርቶች ላይ ጥምቀትን የተመለከቱ ጥቅሶች አንብቤአለሁ፡፡ የወንጌልን ቃል በሚታይ ቲሸርት ላይ ሳነብ እጅግ ደስ ብሎኛል፡፡ አንዱ ወንጌልን የምንሰብክበት መንገድ ይህ ነውና፡፡ አንዳንዶቹን ጥቅሶች ሳይ ግን በጣም «ሾክድ» አድርገውኛል፡፡ በተለይ የአምላክ ክብር ለማርያም ተሰጥቶ ስመለከት በጣም ነው የደነገጥኩት፡፡ ይህች ቤተ ክርስቲያን በቃ ሰው የላትም ማለት ነው? ስልም ቆዝሜያለሁ፡፡

አምላክ፣ ጌታ፣ ፈጣሪና የሕይወት ውሃ ምንጭ እርሱ እግዚአብሔር እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ ያለ እውቀት በሆነ ባዶ ሃይማኖታዊ ቅናት የተነሳሱ አንዳንድ ወጣቶች በዘንድሮው የጥምቀት በዓል በለበሱት ቲሸርት ላይ «ማርያም የሕይወት ውሃ ምንጭ ናት» የሚል ጽፈዋል፡፡ በድጋሚ በጣም «ሾክድ» የሚያደርግ ነው። እነዚህን መንፈሳዊ እውቀት የሌላቸው ባዶ ቀናተኞችና ከእግዚአብሔር ይልቅ ማርያምን የሚያመልኩ ወጣቶች «አቤቱ፥ የእስራኤል ተስፋ ሆይ፥ የሚተዉህ ሁሉ ያፍራሉ፤ ከአንተም የሚለዩ የሕይወትን ውኃ ምንጭ እግዚአብሔርን ትተዋልና በምድር ላይ ይጻፋሉ።» ኤር. 17፡13 ከማለት በቀር ምን ይባላል?

Friday, January 18, 2013

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ

የጥምቀት በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ ጽድቅን ለመፈጸም ሲል በባሕረ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ መጠመቁን የምናስብበት በዓል ነው፡፡ በዚህ እለትም የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሲሕነትና የእግዚአብሔር ልጅነት በአብና በመንፈስ ቅዱስ ተመስክሯል። የምወደው ልጄ እርሱ ነው እርሱን ስሙት ሲል አብ በደመና ሆኖ ተናግሯል፡፡ ስለዚህ ኢየሱስን ልንሰማ እንደሚገባን ከመቼውም ጊዜ ይልቅ በዓለ ጥምቀት ያሳስበናል፡፡ እርሱ ደግሞ እናንተ ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችሀለሁ ብሏል፡፡ ይሁን እንጂ እርሱን እንዳንሰማ የዚህን በዓል መንፈስ የሚለውጡ በርካታ ነገሮች አሉ፡፡

የዚህ በዓል ማእከል የተጠመቀው ኢየሱስ መሆን ሲገባው ከቤተ ክርስቲያን እቃዎች (ንዋያተ ቅድሳት) አንዱ የሆነው ታቦት አምልኮት ይቀርብለታል፡፡ ይህም የበዓሉን መንፈስ የሚያደፈርስና አላማውን የሚያስት ነው፡፡ ለማንኛውም በዓሉ ጌታ የሚታሰብበት እንጂ ታቦት የሚመለክበት ሊሆን አይገባውም፡፡ ታቦት መቼ ተመለከ የሚል ምላሽ በሰፊው ሊሰጠን እንደሚችል ከወዲሁ እንገምታለን፡፡ ታዲያ እየቀረበ ያለው እልልታ ጭፈራና ስግደት ለማን የሚቀርብ ነው? ብንል ምላሹ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያስቸግርም፡፡ ለማንኛውም በታቦት ዙሪያ «አልተሳሳትንም» በሚል ርእስ ስለታቦት ለሰበከው ምህረተአብ «ፍልፍሉ» ወይም አንዳሻው ከተሰጠው «አልተሳሳትንምን?» ከተሰኘው መጽሐፍ ገጽ 34 ላይ የሚከተለውን ለዛሬ እንድታነቡ ጋብዘናል፡፡

ታቦታት በኢትዮጵያ

ሰበር ዜና፦ በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ የወቅቱን የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ አስመልክቶ ሰፋ ያለ መግለጫ አወጣ

በ4ኛው ፓትርያርክ በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሚመራውና በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ ከጥር 7-9 ቀን 2005 ዓ/ም በሎስ አንጀለስ ከተማ አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ አካሂዶ  ሰፋ ያለ መግለጫ አወጣ። መግለጫው አዲስ አበባ የሚገኘው ሲኖዶስ በቅርቡ ላወጣው መግለጫና የ 6ኛ ፓትርያርክ ሹመት መልስ ይሰጣል፤ የተወሰነውም የ 6ኛ ፓትርያርክ ሹመት ተገትቶ ለሰላምና ለአንድነት ቅድሚያ እንዲሰጥ ጥሪም ያስተላልፋል።

ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፦ መግለጫThursday, January 17, 2013

ቤተ ክርስቲያን እንደ ተከፈለች ልትቀጥል ነው? ወይስ ሌላ እድል ይኖራት ይሆን?

  • በስደት ያለውና በ 4ኛው ፓትርያርክ የሚመራው ሲኖዶስ በዚህ ሳምንት በሎስ አንጀለስ ከተማ ስብሰባ እያካሄደ ነው። መግለጫም ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ብዙዎች የተጀመረው እርቅ ሰምሮ ቤተ ክርስቲያን እንድ ትሆናለች ብለው ተመኝተው ነበር፡፡ እርቁ እንደማይሰምር ግን ከአያያዙ ያስታውቅ ነበር፡፡ የአገር ቤቱ ሲኖዶስ እርቁ በሂደት ላይ እያለ አስመራጭ ኮሚቴ መሰየሙ እርቁን እንዳልፈለገው ገና ከማለዳው ግልጽ አድርጓል፡፡ ጉዳዩ ነገሩን ይበልጥ አጋግሎት ሰንብቷል፡፡ በትናንቱ መግለጫ ላይ እንደተተቀሰው እስካሁን ለተፈጠረው ችግር አቡነ መርቆሬዎስንና አብረዋቸው ያሉትን ጳጳሳት ብቻ ተጠያቂ ማድረግም እርቁ ወደፊት እንዳይቀጥል እንቅፋት ሊሆን ይችላል የሚለው የብዙዎች ግምት ነው፡፡

የጉድ ሙዳዮች ሲኖዶስ የኢትዮጵያን ሕዝብ በሙሉ አሳዝኗል

የሁለቱ ሲኖዶሶች እርቅ የኢትዮጵያን ሁኔታ ይለውጣል ሰላም እና ልማት፤ መልካም አስተዳደር እርቅና ፍቅር ያመጣል የሚል ተስፋ ተጥሎበት ነበር። ቤተ ክርስቲያን አሁን ካለችበት ውስብስብ ችግር የመፈታት ተስፋ ይኖራታል ተብሎም ታስቦ ነበር። በተለይም ምዕመናን የዚህና የዚያኛው ከሚለው ክፍፍል የምናርፍበት ጊዜ መጣልን ብለው በተስፋ አድርገውት ነበር። ነገር ግን ተስፋው ባዶ፤ ብርሃኑም ጨለማ ሆኖ ተጠናቋል።
ድሮም የጉድ ሙዳዮች በሥጋ መንገድ ሲጓዙ ስናያቸው ከወዲሁ ውጤቱን አውቀነው ነበር። የእግዚአብሔርን ሥራ ይሠራሉ ብለን መጠበቅ ከተውን ረጅም ጊዜ ሆነን።  በመካከላቸው ያሉ ጤነኞች ብፁዓን አባቶች ከክፉው ጋር ተዋግተው ያሸንፉ እንደሆነ ብለን ትንሽ ተስፋ ነበረችን እንጂ ውጤቱን እናውቀው ነበር።
ጌታ በወንጌል "የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውስጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኩላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን? እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፣ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል፤ መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፤ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም‚ እንዳለ ማቴ 7፥15-18
ከመንፈሳዊ ሰው ፍቅር፣ ሰላም፣ ደስታ፣ ይቅርታ፣ የዋህነት፣ ደግነት፣ እራስን መግዛት የሚባሉ ፍሬዎች ይለቀማሉ፤ ከሥጋዊ ሰው ግን መልካም ሐሳብ ፈጽሞ አይገኝም። እንግዲህ ሕዝባችን ወደ ጌታ ቃል ዘወር ብሎ እግዚአብሔርን ከማዳመጥ ይልቅ በልዩነቱ ሲረጋገም እንዲኖር ዛሬ ተፈርዶበታል። እጅግ ያሳዝናል። ብፁእ አቡነ መርሐ ክርስቶስ ነቢይ ነበሩ ማለት ይቻላል፤ አቡነ ሳሙኤልና አቡነ አብርሃም ጵጵስና ሲሾሙ ጨርቃቸውን መቅደድ ነበር የቀራቸው ።ለረጅም ጊዜ ለቤተ ክርስቲያን ተሟግተው አረፉ። ይህ ያሁኑ ጊዜ ታይቷቸው ይሆን? ሲኖዶሱ በወሰነው መጥፎ ውሳኔ ኀዘናችን መራራ ነው።

Wednesday, January 16, 2013

በውዝግብ የተሞላው አስቸካዩ የሲኖዶስ ስበሰባ ልዩ ልዩ ክስተቶችን በማስተናገድ ተጠናቀቀ ወደ 6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ ለመግባትም ወስነዋል

ከጥር 6 ጀምሮ ሲካሄድ የቆየውና ትኩረቱን በፓትርያርክ ምርጫና ከምርጫው ጋር በተያያዘ  በተከሰቱ ልዩነቶች ሲወያይ የሰነበተው የጳጳሳት ጉባኤ ዛሬ መጠናቀቁ ተሰማ፡፡ ሲኖዶሱ በሰጠው መግለጫ የእርቁ ሂደት በውጪ የሚገኙት ጳጳሳት ወደ እርቅ ሊያመጣ የሚችል ሐሳብ ባለማቅረባቸውና ለእርቁ ፈቃደኝነታቸውን ባለማሳየታቸው መንበሩ ተተኪ ፓትርያርክ ሳይኖረው መቀጠል ቤተክርስቲያንን የሚጎዳ በመሆኑ ወደ 6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ ለመግባት መወሰናቸው ተሰምቷል። ከፍተኛ ክፍፍልና ንትርክ ባስተናገደው በዚህ ስብሰባ ላይ ለእርቅ ተልኮ የነበረው ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት ላይ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ ኮሚቴው እርቁ እንዲቀድም ቢወተውትም እንዲሁም አቡነ መርቆሬዎስ የሚመጡበትን መንገድ ብንፈልግ ይሻላል የሚል ሐሳብ ቢያቀርቡም፣ ወደ 6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ መግባት የፈለጉት ጳጳሳት «የተላካችሁት አቡነ መርቆሬዎስ ይምጡልን ለማለት አልነበረም አላማችሁን ስታችኋልና ለቀጣዩ ውይይት ሌላ ኮሚቴ ይላካል» የሚል ውሳኔ ማሳለፋቸውን ምንጮች ተናግረዋል፡፡ 4ኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ስልጣናቸውን በመልቀቃቸውም ተጠያቂው ራሳቸው መሆናቸውን የሲኖዶሱ መግለጫ በዝርዝር ያስረዳል፡፡ አቡነ መርቆሬዎስ ግን በመንግስት ተጽዕኖና ጫና ሥልጣናቸውን እንደ ለቀቁ በእርሳቸው በኩል የሚቀርቡ መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ የሲኖዶሱ ውሳኔ አክሎም በውጭ የሚገኙት አባቶች ለእርቁ ፈቃደኞች ከሆኑ የእርቁ ሂደት እንደሚቀጥል ገልጿል፡፡

ሰበር ዜና፦ የአዲስ አበባው ሲኖዶስ 6ኛ ፓትርያርክ ለመሾም ወሰነ፤ የሰላሙንም በር በ አምስት ገጽ መግለጫ ጥርቅም አድርጎ ዘጋ

የአዲስ አበባው ሲኖዶስ ጥር 6 ቀን 2005 ዓ/ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ 6ኛ ፓትርያርክ ለመሾም ወሰነ።  በወጣውም ረዘም ያለ መገለጫ የ 4ኛውን ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስን ወደ ስልጣናቸው መመለስ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ለምንም አይነት ድርድር ቦታ አይሰጥም። ይህም ተጀምሮ የነበረውን የሰላም ጥረት ማመንመን ብቻ ሳይሆን ሙሉ ለሙሉ ዋጋ ቢስ ያደርገዋል። 

ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፦  ሙሉ መግለጫ

የአባ ሚካኤል ልጅ የዮሐንስ እና የእነ አባ ሳሙኤል ሙግት የጥር 2 የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሎ

ለጥር 2/2005 ተቀጥሮ የነበረው በአባ ሚካኤል ወራሽ ልጅ በዮሐንስ ሚካኤል እና “እርሳቸው ድንግል እና ጳጳስ ስለሆኑ ሊወልዱ አይችሉም” በሚል ሀብታቸውና ገንዘባቸውን ልጃቸው እንዳይወርስና እግረ መንገዳቸውን የራሳቸውን የቆብ ውስጥ ገበና ለመደበቅ በሚል በስር ፍርድ ቤቱ ሲረቱ ይግባኝ በማለትና በሲኖዶስ አባልነታቸው መሰሎቻቸውን በማሳመንና በሲኖዶስ ስም ደብዳቤ በማጻፍና ጉዳዩ የሃይማኖት ነው በሚል እንዲቋረጥ ለማድረግ ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ በመቅረቱ ጉዳዩ መታየቱን ቀጥሎ ለጥር ተቀጥሮ የነበረ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡ እንደ ምንጮቻችን ከሆነ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ክርክሩን በቃል ከመስማት ይልቅ በጽሑፍ እንዲያቀርቡ ከጥር 2 በፊት ለሁለቱም ወገኖች ትእዛዝ ማስተላለፉ ታውቋል፡፡ ጉዳዩ በጽሑፍ እንዲቀርብ የታዘዘው በክርክሩ ላይ ጳጳስ ይወልዳል አይወልድም በሚለው ነገር በችሎት መሰማቱ መልካም መስሎ ስላልታየ ነው የሚል ጥርጣሬ አሳድሯል፡፡

በእለቱ ሁለቱም ወገኖች መከራከሪያቸውን በጽሑፍ ያቀረቡ መሆናቸውን የሚናገሩት ምንጮች በጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚታዩ ጉዳዮች የሚሰጣቸው ቀጠሮዎች ረጅም ጊዜ 3 ወይም 4 የሚወስዱ መሆናቸውን መሰረት በማድረግ ዮሐንስ ለፍርድ ቤቱ በቀጠሮው መርዘም ላይ ቅሬታውን አቅርቧል፡፡ በቅሬታው እንደተገለጸው የቀጠሮው መርዘም ለባላንጣዎቹ የአባቱን ሀብትና ገንዘብ ለማሸሽ እድል የሚሰጥ በመሆኑ ብይኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱም አቤቱታውን ተቀብሎ ብይን ለመስጠት ለጥር 29 ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Tuesday, January 15, 2013

መንግሥትና ቤተ ክህነቱ፣ የሁለቱ ሲኖዶሶች ሰላማዊ ድርድር፣ የአቡነ መርቆዮስ ጉዳይ፣ የፓትርያሪክ ምርጫና ውዝግቡስ ወዴየት እያመራ ይሆን!?

ክፍል ሁለት፣ ምንጭ - ሪፖርተር ጋዜጣ የእሁድ እትም
በፍቅር ለይኩን
befikir12@yahoo.com/fikirbefikir@gmail.com
ባለፈው አስራ አምስት ቀን ጽሑፌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ አጠር ባለ መልኩ አጠቃላይ የሆነ የቤተ ክርስቲያኒቱን የረጅም ዘመን ታሪክን ተንተርሼ አንድ መጣጥፍ ለማቅረብ ሞክሬ ነበር፡፡ አንዳንድ አንባቢዎቼ የጽሑፌን ጭብጥ ካለመረዳት ይሁን ወይም በሃይማኖት ካባ ሥር ተሸሽገው ፖለቲካዊ አጀንዳቸውን ለማራመድ ከሚፈልጉና አሊያም ስሜታዊነት ካየለበት የሃይማኖት አርበኝነት መንፈስ ተነሳስተው ነው መሰል ‹‹አንተ ከማን ወገን ነህ፣ ሚናህን ለይ…›› የሚል ሰም ለበስ ጥያቄያቸውን በማስቀደም ‹‹ለመሆኑ በአባቶችና በቤተ ክርስቲያኒቱን ታሪክ ዙሪያ እንዲህ ዓይነቱን ጽሑፍ ለማቅረብ ማን መብት ሰጠህ?!›› ዓይነት አስተያየታቸውን ለግሰውኛል፡፡

Monday, January 14, 2013

ሰበር ዜና፦ ማንያዘዋል ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ እንዳይገባ በዐቃቤ መንበሩ ደብዳቤ መታገዱ ተሰማ

ጉዳዩ ወደ ተስፋዬ ውብሸትና እስክንድር ገ/ክርስቶስ ሳይዞር እንደማይቀር እየተነገረ ነው

የማቅ ቀኝ እጅ የሆነውና ማቅ በቤተ ክህነት ውስጥ የማይገባውን ከፍተኛ ቦታ እንዲያገኝ ትልቅ ሚና ሲጫወት የነበረው ማንያዘዋል ቤተክህነት ውስጥ እየፈጠረ ካለው ውስብስብ ችግር የተነሳ ወደዚያ እንዳይገባ መታገዱ ተሰማ፡፡ የታገደበት ምክንያት ለጊዜው ባይታወቅም ማቅ በፓትርያርክ ምርጫ ዙሪያ እያደረገ ባለው መጠነ ሰፊ ጣልቃ ገብነት ጋር ሳይያያዝ እንዳልቀረ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ማንያዘዋል የማቅ ድረገጾች ዋና የወሬ ምንጭ መሆኑ ሲታወቅ ባለፈው ግብጽ ሄዶ ሳለ ደጀሰላም የወሬ እጥረት አጋጥሟት አንደነበረ መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡ ማቅ ማን ያዘዋል ሙሉ ጊዜውን በምርጫው ላይ እንዲያደርግና የማቅን እጩ ጳጳስ ፓትርያርክ ለማድረግ እንዲሰራ በማሰብ ከቴዎሎጂ ምሩቃን ማህበር ገለል እንዲል ማድረጉን ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በማንያዘዋል የተጀመረው ይህ የደብዳቤ መጻፍ እርምጃ በአሁኑ ሰዓት ከማቅ ጎን በመቆም የማቅን አላማ ለማስፈጸም የሰራተኛ ህገ ወጥ ዝውውር በማድረግ ለማቅ ያልተመቹትን ሰዎች ከሞያቸውና ከትምህርታቸው ጋር ወደማይገናኝ ክፍል በማዛወርና በቦታቸው ለማቅና እርሱ ላጫቸው ጳጳሳት መመረጥ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ አቶዎችን በጠቅላይ ቤተ ክህነት ቁልፍ ቦታዎች ውስጥ በመሰግሰግ ለማቅ ያለውን ታማኝነት እያሳየ የሚገኘው ተስፋዬ ውብሸትና ባልደረባው እስክንድር ቀጣይ ደብዳቤ የሚጻፍባቸው እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡ ማንኛውም አይነት ዝውውር እንዳይደረግ መታገዱም ታውቋል፡፡ በዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር መረጃዎችን እየተከታተልን ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡   

የግንቦት 15ቱ ውግዘት መነሻ፣ ሂደት፣ ፍጻሜና ቀጣዩ ሲገመገም - ክፍል 8

ክፍል 8

የግንቦት 15ቱን “ውግዘት” የተመለከተ ዘገባችንን ካቆምንበት እንቀጥላለን፣ ከሳቴ ብርሃን በተሰኘው ማህበር ላይ የቀረቡትን የመጨረሻዎቹን ሁለት “ኑፋቄዎች” ለዛሬው እናቀርባለን፡፡ የግንቦቱ ቅዱስ ሶኖዶስ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ ላይ በከሳቴ ብርሃን ማህበር ላይ የቀረቡት “ኑፋቄዎች” “መሰረታዊ የክርስትና እምነት መግቢያ” ከሚለው ጽሁፋቸው ላይ የተወሰደ መሆኑን ቃለ ጉባኤው ያመለክታል፡፡ የከሳቴ ብርሃን ጽሁፍ እጃችን ላይ ስለሌለ ጥቅሱ በትክክል ይጠቀስ ወይም ለክስ በሚመች መልኩ ይቅረብ ለማረጋገጥ ባንችልም፣ ቃለ ጉባኤው ያሰፈረውን መሰረት አድርገን ግን ኑፋቄ የተባሉት ነጥቦብ ኑፋቄ መሆን አለመሆናቸውን እንፈትሻለን።

“6ኛ መሠረታዊ የክርስትና እምነት መግቢያ” በተሰኘው ጽሑፋቸው፦

“ሀ. “ጥምቀት የኀጢአት ስርየትን አያሰጥም” በማለት ጽፈዋል፡፡ መሰረታዊ የክርስትና እምነት መግቢያ -
2000 ዓ.ም ገጽ 1”
ጥምቀት ከክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ጋር መተባበራችንን የምንገልጥበት ሥርአት ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።” ማቴ. 28፥19-20 ብሎ ባዘዘው መሠረት ሐዋርያት ወንጌል እየሰበኩ ያመኑትን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በማጥመቅ ወደ ቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዲጨመሩ በማድረግ ደቀ መዛሙርት ለማድረግ ይፈጽሙት የነበረና ዛሬም ቤተክርስቲያን የምትፈጽመው የተቀደሰ ምስጢር ነው። ጥምቀት አላማው ከክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ጋር መተባበርን በሚታይ ስርአት ማለትም ውሃ ውስጥ በመግባት ከሞቱ ጋር ከውሃ በመውጣት ደግሞ ከትንሳኤው ጋር መተባበርን ማሳያ ነው።

Sunday, January 13, 2013

እርማችሁን አውጡ! ክፍል ሁለት

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
ከባለፈው የቀጠለ
ባለፈው ክፍል አንድ ሰፊ ንባባችን ርእሱ ጠብቀው የሚነሱ በርከት ያሉ የተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች እንስተን መወያየታችን የሚታወስ ነው። በዛሬ ለትም እንዲሁ ከባለፈው በመቀጠል ዋና ዋና ነጥቦች በማንሳት ጥቂቶቹን የምንዳስስ ሲሆን ከሁለትና ከሦስት ገጽ በላይ ጽሑፍ የማንበብ ነገር የማይሆንላቸው አምስትና ስድስት  ገጽ ረዘመ/በዛ በማለት የሚያማርሩ ወገኖቻችን ግምት ውስጥ በማስገባት ተጨማሪ  ሦስተኛ ክፍል ማዘጋጀቱ ግድ ስላለ ከተጨማሪ ሃሳቦች ጋር ጸሐፊው ክፍል ሦስት በቀጣይነት መኖሩንም  ሲያሳውቁ በአክብሮት ነው::

Saturday, January 12, 2013

አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል - ክፍል 2

“ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም።” ማቴ 12፡39፤ 16፡4
ክፍል ሁለት
ፈዋሽ ነኝ ባዩን ግርማን በቅርበት የሚያውቁ ስለሰውዬው አጋንንታዊ አሰራር ልዩ ልዩ መረጃዎችን እያስነበቡ ነው፡፡ ባለፈው ሎሚ መጽሔት በህዳር ወር 2004 ዓ.ም. እትም ላይ ዲ/ን ዓለማየሁ ነጋሽ ሀይሉ ዘተክለ ሃይማኖት ካቀረበው ጽሁፍ ላይ ስለ አጥማቂው ግርማ ያሰፈረውን እናስነብባችሁ ነበር፡፡ ለዛሬ ደግሞ የ”ማሳቀል” መጽሐፍ ደራሲ መሪጌታ ሠረቀ ብርሃን ከገጽ 74-79 ላይ “መምህር ግርማና ሥራው” በሚል ርእስ ስለ ግርማ ካሰፈሩት እናስነብባችሁ፡፡

መምህር ግርማና ሥራው
መምህር ግርማ በአሁኑ ጊዜ በመቊጠርና አልፎ አልፎም በውሃ እየገረፉ በሽተኞችን እፈውሳለሁ፣ አጋንንትንም አወጣለሁ እያለ በአዲስ አበባና በሌሎችም ክልሎች እየተዘዋወረ በመሥራት ላይ ያለ ሰው ነው፡፡ መምህር ያሉት ምእመናን ናቸው እንጂ የመምህርነት ሙያ ኖሮት አይደለም፡፡

Friday, January 11, 2013

እውነቱ የቱ ነው?

(ምንጭ፦ ደጀ ብርሃን ብሎግ) ለውይይት የሚጋብዙ ብዙ ግሩም ሃሳቦችን የያዘች ጽሑፍ ስለሆነች እዚህም አቅርበናታል 
መነሻ ሃሳብ «ገመና 81» መጽሐፍ
   ሀተታ፤
በኦርቶዶክሳውያን  ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከታች ጀምሮ እስከላይኛው እርከን ድረስ ያለው ሰው ስህተት ይኖርብናል ወይም ልንሳሳት እንችላለን ብሎ የሚያስብ ማግኘት አዳጋች ነው። በክርስቶስ ደም የተመሰረተችው ቤተክርስቲያን ፍጽምትና ንጽሕት መሆኗን በመቀበል እንዳለ መሪውና ተመሪው ራሱንም በዚያው ዓይን እያየ እኛ ፍጹማንና ንጹሐን ነን በሚል ከለላ ስር ራሱን በማስጠለል፤ ስህተትን አምኖ ለመቀበል አይፈልግም። የስህተት አስተምህሮ አለ፤ በእግዚአብሔር ቃል ሲመረመር አደጋው የከፋ ነው፤ የክፉ መንፈስ አሰራር ወደማወቅ እንዳንደርስ ቃሉን በክሏል ሲባል የሚሰጠው ምላሽ፤ 2000 ሺህ ዘመን የኖረችን ቤተክርስቲያን ዛሬ የተነሱ አፍቃሬ ተሐድሶ መናፍቃን ሊያርሟትና ሊበርዟት ይፈልጋሉ በማለት ታፔላ መለጠፍ ይቀናቸዋል። የስም ታፔላ መለጠፍ ብቻ ሳይሆን ሽልማት የሚያሰጥ ቢሆን ኖሮ የተመረጡና ለመስማት የሚዘገንኑ ስድቦችና ዛቻዎች ይዥጎደጎዳሉ።