Wednesday, January 2, 2013

የአባ ሰላማ ድረ ገጽ ከባለ ራእዩ አዕምሮ ተጸንሳ ከተወለደች ዛሬ 2 ዓመት ሆናት!

 
ውድ የአባሰላማ ድረ ገጽ አንባቢዎች፦ በታላቁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባት አቡነ ሰላማ ስም የተቋቋመችው ይህች ድረ ገጽ የሚከተሉትን ሦስት አበይት ጉዳዮችን ለማከናወን የዛሬ 2 ዓመት ለኢትዮጵያውያን እንድትደርስ ተደርጋለች።
 1. ቤተ ክርስቲያናችንን እየበደሉ ያሉ ክፉ ስራዎችን፣ ክህደቶችንና የስህተት ትምህርቶችን ማጋለጥ
 2. በድርጅት መልክ ተደራጅተው የህዝብ ግንኙነቶች ሁሉ ባለቤትና ብቸኛ ተሰሚ ሆነው የስህተት ትምህርቶችንና ስርዓቶችን በማራመድ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ያሉ ድርጅቶችን ህዝቡ እንዲያውቃቸውና እንዲመረምራቸው መጠቆም
 3.  ወቅታዊ የሆኑ የቤተ ክርስቲያን ዜናዎችን ለምዕመናን ማድረስ።
 በዚህች አጭር ሁለት ዓመት ውስጥ  ከላይ በጠቀስናቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከጠበቅነውና ካሰብነው በላይ ማከናወን ችለናል። ለዚህም በመጀመሪያ እግዚአብሔርን ስናመሰግን ቀጥሎ ደግሞ በመላው ዓለም ተበትናችሁ የምትገኙ ጸሐፊዎችን፤ አስተያየት ሰጭዎችንና አንባብያንን እናመሰግናለን። በድረ ገጻችን ላይ አወያይ የሆኑ ጉዳዮችን በማቅረብ ህዝባችን ሁሉንም እንዲመረምር፣ ከሀሳቡ ጋር የማይስማማውን እንደጠላት ከማየት ይልቅ በጨዋነትና በመቻቻል ሐሳብን በአግባቡ የመግለጽን ባህል ለማዳበር እንዲችል መጠነኛ አስተዋጽኦ እንዳበረከትን ይሰማናል።

ከላይ በምስሉ ላይ እንደጠቆምነው በዚች ሁለት ዓመት ውስጥ ድረ ገጻችን  1 ሚሊዮን ሰማንያ ሺ ጊዜ በላይ የተጎበኘ ሲሆን  ወደ 1 ሚሊዮን የሚሆነው የድረገጽ ጉብኝት አሁን በጨረስነው 2012 የፈረንጆች ዓመት የተቆጠረ ነው። ይህ የሚያሳየው ድረ ገጻችን እጅግ ከፍተኛ በሆነ ፍጥነት እያደገ መሆኑን ነው። በአሁኑ ሰዓት ድረ ገጻችን በወር115,000 በሚሆኑ በኢትዮጵያና በመላው ዓለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ይነበባል።  ከዚህ በታች ያለው ሰንጠረዥ ከፍተኛ አንባቢያን ካላቸው 10 አገሮች በአንድ ወር ውስጥ የተደረጉ ጉብኝቶችን (pageviews) ያሳያል።   

 በጎብኝዎች ብዛት ኢትዮጵያ የ 1ኛነቱን ደረጃ የያዘች ሲሆን በአሜሪካ ያሉ አንባብያን ቁጥር ከኢትዮጵያው ጋር ይቀራረባል። በአገራችን ኢትዮጵያ ይህን ያህል የኢንተርኔት አንባቢ መኖሩ እጅግ ቢያስደስተንም ከህዝባችን ቁጥር አንጻር ግን አገራችን በኢንተርኔት ተጠቃሚነት (Internet access) ብዙ እንደሚቀራት ይጠቁማል።
 
ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በአገልግሎታችን ብዙዎቻችሁ የተደሰታችሁ  ቢሆንም  ቅር የተሰኛችሁም እንዳላችሁ  እናውቃለን። የአባ ሰላማ ድረ ገጽ  ዓላማ ከላይ የጠቀስናቸውን ሶስት ዋና ዋና ስራዎችን ለማከናወን ስለሆነ ሁሉንም ማስደሰት የማይቻል ነገር ነው።   የተከበራችሁ አንባቢያን፦ ባለፉት ሁለት አመታት አብራችሁን ስለቆያችሁ፣ ስለተሳተፋችሁና አስተያየታችሁን ስለለገሳችሁን በእግዚአብሔር ስም እናመሰግናለን። አሁንም ምክራችሁ አይለየን እንላለን።

8 comments:

 1. እንኳን ለሁለተኛው ዓመት የአባ ሰላማ ብሎግ ልደት በሠላም አደረሳችሁ፡፡ ብሎጋችሁን ቢያንስ በቀን ሁለት ጊዜ ሳልጎበኘው አላድርም፡፡ እጅግ በሳልና የተመረጠ አቀራረብ አላችሁ፡፡ ጥሩውን ጥሩ፣ መጥፎውን ደግሞ በመጥፎነቱ በመረጃ አስደግፋችሁ ዘገባዎችን ማስተላለፋችሁ ከሁሉም ብሎግ በላይ ተመራጭ ያደርጋችኋል፡፡ ምን ጊዜም እውነትን ብቻ ዘግቡ፡፡ ማን ያውቃል የዛሬ ዓመት ደግሞ ይኸው ቁጥር በዕጥፍ ያድግ ይሆናል፡፡ በርቱ ተበራቱ ለዓመቱ ደግሞ ሰው ይበለን፡፡

  የእናንተው አናኒመስ
  እንኳን ለሁለተኛው ዓመት የአባ ሰላማ ብሎግ ልደት በሠላም አደረሳችሁ፡፡ ብሎጋችሁን ቢያንስ በቀን ሁለት ጊዜ ሳልጎበኘው አላድርም፡፡ እጅግ በሳልና የተመረጠ አቀራረብ አላችሁ፡፡ ጥሩውን ጥሩ፣ መጥፎውን ደግሞ በመጥፎነቱ በመረጃ አስደግፋችሁ ዘገባዎችን ማስተላለፋችሁ ከሁሉም ብሎግ በላይ ተመራጭ ያደርጋችኋል፡፡ ምን ጊዜም እውነትን ብቻ ዘግቡ፡፡ ማን ያውቃል የዛሬ ዓመት ደግሞ ይኸው ቁጥር በዕጥፍ ያድግ ይሆናል፡፡ በርቱ ተበራቱ ለዓመቱ ደግሞ ሰው ይበለን፡፡

  የእናንተው አናኒመስ

  ReplyDelete
 2. መልካም አባ ሰላማ በተረፈ ግን ከሃይማኖት ጋር በቀጥታም ባይሆን በትዘዋዋሪ ስለሚገናኙ አንገብጋቢ የሃገራችን ጉዳዮች...ማለትም ዘረኝነት፣ ጥላቻ እና ጸብ የግብረ ሰዶማዊነት በከትማችን መስፋፋት፣ የአደንዛዥ እፅ መስፋፋት፣የፖርኖግራፊ ቤቶች መብዛት ፣ የውጣነት ፈተናዎች በተለይ በዩንቨርሲቲዎች...ወዘተ ጉዳዮች ላይ አውያይ ምሁራዊ ደረጃን የጠበቁ ትንተና ጥናቶችንም ሆነ መርጃዎችን ብታቀርቡ ደስ ይለኛል!የቤተ ክርስቲያኒቷ የምር ልጆች (mkidusanm hone tehadso honachu mehal sefariwoch)ቤተ ክርስቲያኒቷን ከጥፋት ለመታደግ ከችግሩ ምንጭ በመነሳት ማሰብ ተገቢ እንደመሆኑ መጠን ህዝቡን ማህበራዊ ፖለቲካዊ እና ግብረ ገባዊ እይታ ማስተካከል (ሃይማኖታዊ ወጉን በጠበቀ መንገድ) ሰውን ለወንጌል ቀና አመልካከት እንዲይዝ ኮረብታው እንዲለሰልስ ጎባጣው እንዲቃና ያደርጋል ባይ ነኝ:አንድ ሰው(abel) እንዳለው..ስብከታችን ሁልጊዜ ኢየሱስ ከናዝሬት ወደ ገሊላ ሄደ ብቻ ከሆነ ምዕመኑን ምን ጠቀምነው? ድሐ ሲበደል፣ እያየን ዝም ከተባባልን፤ ወንድሞቻቸን ወይም እኅቶቻቸን ራቁታቸውን ሲሆኑ የዕለት ምግብንም ሲያጡ፥ በደኅና ሂዱ፥ እሳት ሙቁ፥ ጥገቡም ካልናቸው ለሰውነት ግን የሚያስፈልጉትን ባንሰጣአቸው ምን ይጠቅማቸዋል?

  ReplyDelete
 3. መልካም አባ ሰላማ በተረፈ ግን ከሃይማኖት ጋር በቀጥታም ባይሆን በትዘዋዋሪ ስለሚገናኙ አንገብጋቢ የሃገራችን ጉዳዮች...ማለትም ዘረኝነት፣ ጥላቻ እና ጸብ የግብረ ሰዶማዊነት በከትማችን መስፋፋት፣ የአደንዛዥ እፅ መስፋፋት፣የፖርኖግራፊ ቤቶች መብዛት ፣ ስለድህነት ፣ ጠኔ ፣ ስለስደተኛ ወገኖቻችን ፣ ስለሴተኛ አዳሪ እህቶቻችን ፣ ጎዳና ተዳዳሪ ወንድሞቻችን የውጣነት ፈተናዎች በተለይ በዩንቨርሲቲዎች...ወዘተ ጉዳዮች ላይ አውያይ ምሁራዊ ደረጃን የጠበቁ ትንተና ጥናቶችንም ሆነ መርጃዎችን ብታቀርቡ ደስ ይለኛል!የቤተ ክርስቲያኒቷ የምር ልጆች (mkidusanm hone tehadso honachu mehal sefariwoch)ቤተ ክርስቲያኒቷን ከጥፋት ለመታደግ ከችግሩ ምንጭ በመነሳት ማሰብ ተገቢ እንደመሆኑ መጠን ህዝቡን ማህበራዊ ፖለቲካዊ እና ግብረ ገባዊ እይታ ማስተካከል (ሃይማኖታዊ ወጉን በጠበቀ መንገድ) ሰውን ለወንጌል ቀና አመልካከት እንዲይዝ ኮረብታው እንዲለሰልስ ጎባጣው እንዲቃና ያደርጋል ባይ ነኝ:አንድ ሰው(abel) እንዳለው..ስብከታችን ሁልጊዜ ኢየሱስ ከናዝሬት ወደ ገሊላ ሄደ ብቻ ከሆነ ምዕመኑን ምን ጠቀምነው? ድሐ ሲበደል፣ እያየን ዝም ከተባባልን፤ ወንድሞቻቸን ወይም እኅቶቻቸን ራቁታቸውን ሲሆኑ የዕለት ምግብንም ሲያጡ፥ በደኅና ሂዱ፥ እሳት ሙቁ፥ ጥገቡም ካልናቸው ለሰውነት ግን የሚያስፈልጉትን ባንሰጣአቸው ምን ይጠቅማቸዋል?

  ReplyDelete
 4. አባ ሰላማ ብሎግ እውነትቱን በመግለጥ፤ ቃለ እግዚአብሔርን በማካፈል፤ የስህተት አስተምህሮን በማጋለጥ፤ የቤተክርሰቲያንን ተግዳሮቶች በማሳየትና ወቅታዊ መረጃን በመስጠት ለፈጸመችው አገልግሎት ምስጋናችን ወሰን የለውም።። የአባ ሰላማ ብሎግና የሌሎች ተመሳሳይ ብሎጎች በመረጃ መረብ ላይ ብቅ ብቅ ማለት፤ እውነትም ይሁን ሀሰት ከአንድ አቅጣጫ ብቻ ይፈስ የነበረውንና በተደራጁ ማኅበራት የሚሰራጨውን መረጃ በሚገርም ሁኔታ የገደበው ሲሆን አንዳንዶቹን ክጫወታው ሜዳ አድርጓል። ያሉትም ቢሆን እየተንገዳገዱ ናቸው።
  አባ ሰላማ ብሎግ በፈር ቀዳጅነቱ የተለየ ሃሳብና መረጃ በማቀበል ፍርዱን ኅሊና ላለው አንባቢ በመተው እየሰራ የቆየበትን ብርታት በመቀጠል፤ በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ የሰው ኃይል በመጠቀም እንዲሁም በተጨባጭ የመረጃ ምንጭ ላይ የተመሰረተ ዘገባና መረጃ በማቅረብ ቢሰራ መጻኢው የሥራ ዘመን በበለጠ መልኩ የተሻለ ይሆናል።
  ለዚህም የሁላችን ርብርብና ትብብር አስፈላጊ እንደሆነ ሳይዘነጋ ነው።
  በተረፈ መልካም የአገልግሎት ዘመን እንዲሆንላችሁ «ደጀ ብርሃን» ብሎግ ትመኝላችኋለች!!

  ReplyDelete
 5. yegobegne hulu yamene aydelem.

  ReplyDelete
 6. አባ ሰላማዎች እንኳን አደረሳችሁ
  እኔ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ነኝ፤ የእናንተን ብሎግ በየዕለቱ እከታተላለሁ፤ በሀይማኖታችን ውስጥ ያለውን የስህተት ትምህርት (በተለይ አዋልድ መጽሐፍትን የተመለከተ) በማጋለጣችሁና በጽናት በማስተማራችሁ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡ሀይማኖቴን ይበልጥ እንዳውቀው ስለረዳችሁኝ አመሰግናለሁ፡፡ በእርግጥ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የክርስትና ሀይማኖት ድርጅቶች ውስጥ የስህተት ትምህርቶች ይሰተዋላሉ፤ የሚያሳዝነው ግን በተለይ የኛዎቹ ለመታረም ዝግጁዎች አለመሆናቸው ነው፡፡
  ለማንኛውም በርቱ ጠንቅራችሁ ስሩ/አስተምሩ/ እላለሁ
  በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ

  ReplyDelete
 7. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 3, 2013 at 9:58 AM

  Happy two years anniversary! I personally expect a lot from Abaselam to reach all the "Orthodox Christians" by preaching the gospel with out adding strange lessons. You may face a lot of opposition from the other side, but be strong! at least you are safe from the physical attack.Some true Orthodox preachers like Begashawe are facing a physical attack,like their fathers Saint Paul and peter.

  Good to have you Abaselam!

  ReplyDelete
 8. ደቂቀ ሉተር ብላችሁ ትቆጡ ይሆን ? እኔም ብሆን እንደ አንድ አማኝ አዋልድ መጻሕፍትን በነገረ መለኮት ላይ ለሚነሳ ጥያቄ እንደ ማስረጃ ማቅረብ አልችልም ፥ የሚያቀርቡትንም አልቀበልም። ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ግን ከአምልኮት ሌላ ሁሉም ነገር ይገባታል ብየ ነው የማምነው። ''ላቲ ይደሉ ክብር ወስብሐት ፥ ወለወልዳ አምልኮ ወስግደት '' የሚለውን አገላለጽ እቀበላለሁ። እናንተ ግን ''ላቲ ይደሉ ክብር ወስብሐት ምስለ ወልዳ አምልኮ ወስግደት'' ብለን እንደምናምን አድርጋችሁ ነው ለሉተራውያኑ እያቀረባችሁን ያላችሁት። ታድያ የሥጋ ወገኖቸ ሆይ ! ደቂቀ ሉተር ብላችሁ ትቆጡ ይሆን ?

  ReplyDelete