Saturday, January 12, 2013

አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል - ክፍል 2

“ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም።” ማቴ 12፡39፤ 16፡4
ክፍል ሁለት
ፈዋሽ ነኝ ባዩን ግርማን በቅርበት የሚያውቁ ስለሰውዬው አጋንንታዊ አሰራር ልዩ ልዩ መረጃዎችን እያስነበቡ ነው፡፡ ባለፈው ሎሚ መጽሔት በህዳር ወር 2004 ዓ.ም. እትም ላይ ዲ/ን ዓለማየሁ ነጋሽ ሀይሉ ዘተክለ ሃይማኖት ካቀረበው ጽሁፍ ላይ ስለ አጥማቂው ግርማ ያሰፈረውን እናስነብባችሁ ነበር፡፡ ለዛሬ ደግሞ የ”ማሳቀል” መጽሐፍ ደራሲ መሪጌታ ሠረቀ ብርሃን ከገጽ 74-79 ላይ “መምህር ግርማና ሥራው” በሚል ርእስ ስለ ግርማ ካሰፈሩት እናስነብባችሁ፡፡

መምህር ግርማና ሥራው
መምህር ግርማ በአሁኑ ጊዜ በመቊጠርና አልፎ አልፎም በውሃ እየገረፉ በሽተኞችን እፈውሳለሁ፣ አጋንንትንም አወጣለሁ እያለ በአዲስ አበባና በሌሎችም ክልሎች እየተዘዋወረ በመሥራት ላይ ያለ ሰው ነው፡፡ መምህር ያሉት ምእመናን ናቸው እንጂ የመምህርነት ሙያ ኖሮት አይደለም፡፡
 
መምህር ግርማ በደርግ ጊዜ በውትድርና ሲያገለግል ከቆየ በኋላ ከውትድርና ኮብልሎ ሱዳን ሄዶ የሱዳንን የጥንቆላ አሠራር ተምሮ የመጣ ነው፡፡ ከዚያ ከመጣ በኋላ በዝዋይና በቡታጅራ ከተሞች ለጥቂት ዓመታት መንፈሳዊ የሚመስል አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቶ ከሱዳን ባመጣውና በመቊጠሪያ ላይ ባስደገመው አስማት ዛሬ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ ሲያጠምቅና ሲያስጮኽ እንመለክታለን፡፡

መምህር ግርማ ቅስና ቀርቶ ዲቁና እንኳን የለውም፡፡ ምክንያቱም የደርግ ወታደር የነበረ ሰው እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት በንስሐ ሊታደስና ሊለወጥ ሌላ አገልግሎት ማለትም ጸናጽልና ማቋሚያ ማቀበል፣ ከበሮ መምታት፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከተአምረ ማርያም በቀር ስንክሳርና ሃይማኖተ አበውን ሌሎችንም ገድላትና ድርሳናትን እንዲሁም የጸሎት መጻሕፍትን ማንበብ ይችላል፡፡ ከዚህ ውጭ በምንም መንገድ እንዲያጠምቅና ሥልጣነ ክህነት እንዲኖረው ሕጉ አይፈቅድለትም፡፡ በእርግጥ አሁን ባለው የተበላሸ አሠራር *ሙስና( እንኳንስ ሚሊየነሩ መምህር ግርማ ይቅርና ማንም ሰው በገንዘብ ኃይል የዲቁና ወይም የቅስና ካርድ ሊቀበል እንደሚችል ጥርጥር የለውም፡፡ መምህር ግርማ ደግሞ የሰባት ብር መቁጠሪያ በሃያ ብር እየሸጠ ከሚድኑ ሰዎችም በልዩ ልዩ የሰላቢ አሠራር በርካታ ገንዘብ የሚበዘብዝ ነጋዴ ነው፡፡

ይህ ሰው ምንም እንኳን በሰውነቱ ያስቀበረውና ያስደገመው አስማት እንዳለው ቢታመንም በዋናነት ግን ድግምቱ በመቊጠሪያው ላይ ነው፡፡ ይህንን የሚያውቁ ዲያቆናት አንድ ቀን መቊጠሪያውን ወስደውበት ሳያጠምቅ ውሎአል፡፡ ያለ መቊጠሪያው ማጥመቅ ስለማይችልም ሦስት ሺህ /3,ዐዐዐ/ ብር ከፍሎ አስመልሶአል፡፡ ድግምት የሌለው ተራ መቊጠሪያ ቢሆን ኖሮ ሦስት ሺህ /3,ዐዐዐ/ ብር ከፍሎ ከሚያስመልስ መርካቶ ራጉኤል ሄዶ በሰባት ብር ገዝቶ በተጠቀመ ነበር፡፡

ይኸው አጥማቂ ነኝ ባይ መምህር ግርማ መቊጠሪያ በሰባት ብር እየገዛ ተጠቃሚዎችንና አስጠማቂዎችን በሃያ ብር እንዲገዙና መንፈሱን በመቊጠሪያ ላይ አስደግሞ በመላክ እያንዳንዱ ሰው መቊጠሪያውን ገዝቶ በቤቱ ግድግዳ ላይ እንዲያንጠለጥል እያስገደደ ይገኛል፡፡ መቊጠሪያውን ገዝቶ በቤቱ ግድግዳ ላይ ያደረገ ሰው በሽታ አይነካውም፤ አጋንንትም አይቀርቡትም እያለም ያስተምራል፡፡ ይህም መናፍስቶቹ በድግምቱ አማካይነት ከሰዎቹ ጋር ኪዳን ስለሚገቡ ነው፡፡ የድሮ ባሕታዊ ገብረ መስቀል የዛሬው አቶ ገብረ መስቀልም እጣንና ነጭ ሽንኩርት በመያዝ ከማንኛውም አጋንንታዊ በሽታ መዳን ይቻላል ብለው ያስተምሩ ነበር፡፡  አሁን ግን በመጠኑም ቢሆን እውነት እየገባቸው እንዳለ ሰምቻለሁ፡፡

መምህር ግርማ በሚያጠምቅበት ጊዜ ቪሲዲውን ካያችሁ የጴንጤ መንፈስ ሲል ይሰማል፡፡ ጴንጤ ነን የሚሉ ሰዎችም ሲጮኹ ይታያል፡፡ እንደተለመደው ምስህ ምንድ ነው ተብለው ሲጠየቁም መዝሙር ይላሉ፡፡ መምህሩም ዘምርና ውጣ ይላቸዋል፡፡ የመስፍን ጉቱን፣ የተከስተን፣ የሊሊን፣ የኤፍሬምንና የሌሎችንም መዝሙሮች ይዘምራሉ፡፡ ለመሆኑ ይህ መዝሙር የማን ነው@ ብሎ ሲጠይቃቸውም ለዘማሪ እገሌ ከጥልቁ የሰጠነው ነው ይላሉ፡፡ ዘማሪው በጌታ አይደለም እንዴ@ ሲባሉ ደግሞ ታዲያ በእኛው ጌታ ነው እንጂ በእናንተው በኦርቶዶክሱ ጌታ እኮ አይደለም ይላሉ፡፡ ሌላ ጌታና ሌላ ኢየሱስ አለ እንዴ@ ተብለው ሲጠየቁም የእኛ ጴንጤዎቹ ኢየሱስ ከድንግል ማርያም የተወለደው ኢየሱስ ሳይሆን የጥልቁ ኢየሱስ ነው ብለው ይመልሳሉ፡፡ ሎቱ ስብሐት፡፡ ዘማሪዎቹን ጠጪዎች፣ ጫት ቃሚዎች፣ መዝሙሩን የሚቀበሉትም ከጥልቁ መሆኑን መናገራቸው ሊሆንም ላይሆንም ስለሚችል መከራከር አልፈልግም፡፡ ይህንን የሚያውቅ እግዚአብሔር ብቻ ነውና፡፡ ደግሞም መዝሙር የመዳን ምልክት ስላልሆነ ዘማሪ የተባለ ሁሉ ድኖአል ብሎ መከራከር አይቻልም፡፡ *ዘማሪዎችንም ሆነ ሌሎችንም አገልጋዮች በተመለከተ ተሐድሶ ለፕሮቴስታንት በሚል ርእስ እያዘጋጀሁ ስለሆነ በዚያው እናየዋለንና ይቆየን(፡፡ እኔን ያበሳጨኝ ግን የእኛ ኢየሱስ የጥልቁ ኢየሱስ ነው ማለታቸው ነው፡፡ ይህንን የሚሉበት ምክንያትም መናፍስቶቹ ሁለት ዓይነት ኢየሱሶች አሉ በማለት ሰዎች እየተሰበከ ያለውን ጌታን እንዳያምኑ ለማድረግ መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡

ይህ ሰው በመቊጠሪያና በጠበል በሚሠራው አሠራር የጴንጤ መንፈስ ወይም የመናፍቅ መንፈስ ሲል ብዙ ሰዎች ስለሚጮኹ በእርግጥ የጴንጤ መንፈስ የሚባል አለ ማለት ነው@ የጴንጤ መንፈስ የሚባል ካለ የኦርቶዶክስ መንፈስ፣ የካቶሊክ መንፈስ ወዘተ. የሚባል መንፈስ አለ ማለት ነው ብዬ ስላሰብኩ ለማንኛውም የጴንጤ መንፈስ የሚባል መኖሩን ለማረጋገጥ የማውቃቸውን ጴንጤዎችን ይዤ እርሱ ወደሚያጠምቅበት ስፍራ በተደጋጋሚ ሄጃለሁ፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ ከወሰድኳቸው ሰዎች መካከል አንድ ሰው እንኳ የጮኸ ግን የለም፡፡ በመሆኑም የሚሠራው ሥራ በፍጹም ሊታመን የማይችል አጋንንት የሚሠሩት ድራማ መሆኑን አረጋግጫለሁ፡፡ በጣት የሚቆጠሩ ከቅድስና የራቁ ወላዋዮች እንደማይታጡ ግን ማስተዋሉ ተገቢ ነው፡፡ በትክክል የጌታ ሞትና ትንሣኤ ገብቶአቸው ጌታን ተቀብለው በንጽሕናና በቅድስና ለጠራቸው ጌታ ታማኝ ሆነው እንደ እግዚአብሔር ቃል የሚኖሩ ክርስቲያኖችን ማለቴ ነው፡፡ እናም ጴንጤ ሆነው እንደ እግዚአብሔር ቃል ካልኖሩ በሰይጣን አሠራር ሊወድቁ ይችላሉ፡፡ ማስተዋል ያለብን በጌታ የመሆን እንጂ በአንድ የአምልኮ ስፍራ መገኘት ወይም አባል ሆኖ መኖር አይደለም፡፡ ይህማ ቢሆን ኖሮ በሌሎች አብያተ ክርስቲያኖች *በፕሮቴስታንት( የአምልኮ ስፍራ በልዩ ልዩ የአጋንንት አሠራር ተይዘው የሚጮኹ ጴንጤዎችን አናይም ነበር፡፡

እነ መምህር ግርማ ወደሚሠሩት ድራማ ስንመለስ ሰይጣኑ ኢየሱስ” በል ሲባል “ኢየሱስ” እያለ “ተዋሕዶ” በል ሲባል ግን ይህንን ስም መጥራት አልችልም፤ ያቃጥለኛል ሲል እንሰማዋለን፡፡ እግዚአብሔር ይገሥፀው! እንደዚህ ያለውን ምስክርነት አሜን ብሎ የሚቀበል ሰው እንዴት ምስኪን ነው@
“ተዋሕዶ ሃይማኖት እንከን የሌላት፣
 “ተዋሕዶ ንጽሕት እንከን የሌላት፣
“እንመናት በውነት የአምላክ ናት” ሲባል አብሮ የሚዘምረው ሰይጣን አይደል? ለመሆኑ ሴት አዳሪውና ዘፋኙ፣ አመንዝራዉና ሰካራሙ፣ ጠንቃዩና መተታሙ፣ አስማተኛው፣ ጥላ ወጊ፣ አጋንንት ጎታች *የአንደርቢ ደጋሚ( ደብተራው ሁሉ የተሰገሰገው የት ሆኖ ነው “ተዋሕዶ ንጽሕት እንከን የሌላት” የሚባለው@ ቅድስና በቤተ ክርስቲያችን ስፍራ እንደሌለው እየታወቀ@

የኢየሱስን ማንነት የተረዳ ሰው ኢየሱስን “ተዋሕዶ” ከሚለው የእምነት ድርጅት ጋር አያነጻጽርም፡፡ ኢየሱስ የሚለው ስም ከአንድ የእምነት ድርጅት ብቻ ሳይሆን ከስሞች ሁሉ ከያሕዌ፣ ከኤልሻዳይ፣ ከአዶናይ፣ ከኤሎሂም፣ ከአኑኤል ወዘተ እና ከሌሎች ፍጥረታት ሁሉ ስም በላይ ነውና (ዕብ. 1፥4፤ ፊል. 2፥9-11፤ ኤፌ. 1፥2ዐ-21)፡፡ በመሆኑ ሰይጣን የኢየሱስን ስም ለማስጣልና ለማስካድ ከመምህር ግርማ ጋር ተስማምቶ ወይም መምህር ግርማን ተጠቅሞ ይህን ይበል እንጂ እውነተኞች ግን አይቀበሉትም፡፡ ሰይጣን ሐሰተኛና የሐሰት አባት መሆኑን ያውቃሉና፡፡ በእርግጥ ሰይጣንን እውነተኛ አድርገው የተቀበሉት ሰዎች ኢየሱስን መቃወማቸው አይገርምም፡፡ የሚገርመው ከሰይጣን ጋር ተስማምተው እየኖሩ አልፎ አልፎ የኢየሱስን ስም መጥራታቸው ነው፡፡

በመሠረቱ ድንቆችና ምልክቶች እውነተኛነትን ብቻ አያረጋግጡም ወይም አይመሰክሩም፡፡ እውነት የተረጋገጠና የፀና ነው፡፡ እውነተኞቹ ምልክቶች ስለ እውነት ሲመሰክሩ ሐሰተኞች ምልክቶች ደግሞ ሐሰትን ይደግፋሉ፡፡ ሰይጣን ልዕለ ተፈጥሮአዊ ድንቆችና ታምራትን የማድረግ አቅሙም ችሎታውም አለው፡፡ ይህም የሚያደርገው የሐሰት አሠራርን ለማስፋፋት ወይም እውነትን ለመደበቅ ነው፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጀመሪያም የመጨረሻም መካከለኛነቱ የእግዚአብሔር ክብር የጎደለበትን የሰው ዘርን ከእግዚአብሔር ጋር በሞቱ ማስታረቅ እንጂ ድንቅና ተአምራት ማድረግ አልነበረም (2ቆሮ. 5፥18)፡፡

መምህር ግርማ የተባለውን አጥማቂ ሰው ስትመለከቱት በእርግጠኝነት የሚሠራው በአጋንንት ኀይል ነው፡፡ አንድ ነገር ግን አስረግጬ ልንገራችሁ፡፡ ቊጥር ዘጠኝ ቪሲዲውን ተመልክታችሁ ከሆነ ከፓስተሮች ጋር ሲከራከር ይታያል፡፡ ፓስተሮች የተባሉ ፓስተር ስለመሆናቸው ማረጋገጫ የለኝም፡፡ ጥያቄዬ እነዚህ ሰዎች በተሰጣቸው ስፍራ ቁጭ ብለው እየታዩ መምህር ግርማ የመናፍቅ መንፈስ ብሎ ለአጋንንቶቹ ጥሪ ሲያቀርብ ምስኪን የሆኑ ሕፃናትና ወጣቶች እየዘለሉ ወደእርሱ ሲመጡ እንመለከታለን፡፡ ታዲያ እነዚህ ፓስተሮች የተባሉ ሰዎች ለምን አልወጡም@ ለምንስ አልጮኹም መምህር ግርማ በእነዚህፓስተሮች ላይ እንዴት ኃይል አጣ፡፡ መቼም እነዚህን ቢያስር ወይም ቢያስጮህ ኖሮ እንዴት ያለ ትልቅ ተአምር ይነገር ነበር፡፡ ጭፍሮችን ከሚያሰቃይ ይልቅ አለቆች ወይም አገልጋዮች የተባሉትን ማስጮህ አይሻልም ነበር? ከነዚህስ በላይስ ማን ይጩህ? እውነታው ግን መምህር ግርማ ጋ ካለው መንፈስ ይልቅ እነርሱ ጋ ያለው መንፈስ እንደበለጠ ያሳየናል፡፡ በሥጋ ተገልጦ አስደበደባቸው እንጂ በጥንቈላው ወይም በአስማቱ ሊያንበረክካቸው አልቻለም፡፡ ቆሞ ማስደብደቡም መንፈሳዊ ሰው አለመሆኑን ያሳያል፡፡ እነዚያ ሰዎች ወይም ፓስተሮች ይህንን ከጥልቁ የሆነውን ክፉ መንፈስ በአደባባይ ለማጋለጥ መሞከራቸውና በነፍሳቸው ተወራርደው በዚያ ሕዝብ ሁሉ ፊት መታገላቸው መልካምና ይበል የሚያሰኝ ቢሆንም እንዲህ ያለውን ክፉ መንፈስ በጾምና በጸሎት ካልሆነ በቀር በቀላሉ ሊወጣ እንደማይችል መገንዘብ ነበረባቸው፡፡ ማቴ. 17፥14-21 ያለውን ስናነብ ሐዋርያትን አልወጣም ያላቸው ክፉ ጋኔን እንዳለ የለባቸውም፡፡ በጾምና በጸሎት ጭምር ሊወጡ የሚችሉ እንዳሉና ይህም ጸጋችንን ብቻ በጸሎት ጭምር ሊወጡ የሚችሉ እንዳሉና ይህም ጸጋችንን ብቻ እየተመካን እንዳንኖር ወደ ጸጋው ባለቤት መጮህ እንድንችል የሚረዳን ነው፡፡

መምህር ግርማ ብዙ ጊዜ እንደ ቤተ ክርስቲያኒቱ ሥርዓት አጋንንት የሚጮኹበት ጠበል የሚባል ነገር እንኳ አይጠቀምም፡፡ ይህ አሠራር በቀጥታ በመናፍስት ትእዛዝ በመቊጠሪያው ላይ ባስደገመው የድግምት ኃይል የሚሠራ የጥልቁ አሠራር ነው፡፡ እንደ ቤተ ክርስቲያኒቱ የቀኖና መጻሕፍት ትእዛዝ ማጥመቅ የሚችል ሰው ሥልጣነ ክህነት ቅስና ያለው ብቻ ነው፡፡

ክርስቲያኖች የአጋንንትን ምስክርነት መቀበል የለባቸውም፡፡ በፊልጵስዩስ ከተማ የሙአርት መንፈስ የነበረባት ሴት እነ ጳውሎስ ወንጌልን ሲያስተምሩ ብዙ ጊዜ እየተከታተለች “የመዳንን መንገድ የሚነግሩአችሁ እነዚህ ሰዎች የልዑል አምላክ ባራዎች ናቸው” እያለች ትመሰክር ነበር፡፡ እነ ጳውሎስ ግን ምሰክርነቱ ከክፉ የሙአርት መንፈስ ስለነበረ አልተቀበሉአትም፡፡ የዛሬ አጥማቂዎች ነን ባዮችም ሆኑ ሌሎች መሰል ክብርና ዘና ፊላጊዎች ግን ለምስክርነት ይጠቀሙባት ነበር፡፡

ስለዚህ እውነተኛ አገልጋዮች ተአምራትን የስብከታቸው ማጽኛ እንጂ ቋሚ ስብከት ማድረግ የለባቸውም፡፡ ይህም ማለት በሚሰብኩበት ጊዜ ሁሉ የግደ ተአምራት መደረግ የለበትም፡፡ ቢደረግ እንኳ ተአምራቶቹ ለትምህርትና ሕዝብን ለንስሐ የሚያዘጋጁ መሆን አለባቸው (ሉቃ. 1ዐ፥13)፡፡ ሁልጊዜ ተአምራት ካላደረግሁ የሚል አገልጋይ ቢኖር ተሳስቶአል፡፡

45 comments:

 1. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 12, 2013 at 2:07 PM

  እኔን ያበሳጨኝ ግን የእኛ ኢየሱስ የጥልቁ ኢየሱስ ነው ማለታቸው ነው፡፡ ይህንን የሚሉበት ምክንያትም መናፍስቶቹ ሁለት ዓይነት ኢየሱሶች አሉ በማለት ሰዎች እየተሰበከ ያለውን ጌታን እንዳያምኑ ለማድረግ መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ yes, you are right! that is the main strategic of devil.

  ለምንስ አልጮኹም መምህር ግርማ በእነዚህፓስተሮች ላይ እንዴት ኃይል አጣ፡፡ መቼም እነዚህን ቢያስር ወይም ቢያስጮህ ኖሮ እንዴት ያለ ትልቅ ተአምር ይነገር ነበር፡፡ ጭፍሮችን ከሚያሰቃይ ይልቅ አለቆች ወይም አገልጋዮች የተባሉትን ማስጮህ አይሻልም ነበር? ከነዚህስ በላይስ ማን ይጩህ? እውነታው ግን መምህር ግርማ ጋ ካለው መንፈስ ይልቅ እነርሱ ጋ ያለው መንፈስ እንደበለጠ ያሳየናል፡፡ በሥጋ ተገልጦ አስደበደባቸው እንጂ በጥንቈላው ወይም በአስማቱ ሊያንበረክካቸው አልቻለም፡፡ I feel sad when I read this story, I never seen his vcd and will never too. What I want say any one who are believing on Lord Jesus is my brother , I don't care about denomination.

  Good news, Girma will be fallen pretty soon.Bad news Orthodox Church will lose many of her followers to protestant, unless the church taking
  an appropriate actions on this evil person.

  God help us to see him and his son.

  ReplyDelete
  Replies
  1. እኔ ጊዜ የለኝም እንጂ የስንቱን ፓስተር ማታለል እና የ አጋንንት ስራ እዘረዝርልህ ነበረ በተጨባጭ ራሳችሁ ከጻፋችሁት ወስጄ መጽሐፍ ቅዱስም “በዓለም ላይ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ስለ ተነሱ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፣ ይልቅስ መንፈሶች የእግዚአብሔር መሆናቸውንና አለመሆናቸውን መርምሩ” [1ኛ ዮሐንስ 4፡1] ይለናል። በኢየሱስ ስም አይመጡም ልትለኝ ነው?አዎ ልድገምልህ የኛ የድንግል ልጅ(የሴቲቱ ዘር) ክርስቶስ እና የናንተ ከሴት ዘርን ያልውሰደው ክርስቶስ(ፓስተር ዳዊት ካለው የተወሰደ)አይገናኙም ቅዱስ ጳዉሎስም “የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸዉን እየለወጡ ዉሸተኞች ሐዋርያትና ተንኮለኞ ሠራተኞች ናቸዉ። ይህም ድንቅ አይደለም ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለዉጣልና።” 2ቆሮ. 11፡13-15 ብሏል። ሐዋርያት ሁሉ በየመልእክቶቻቸዉ ከሐሰተኞች ክርስቶስ ነቢያት አስተማሪዎች እንድንጠበቅ ደጋግመዉ አሳስበዋል።

   Delete
  2. ወንጌላዊነት(aba sereke ke 12 amet befit ketwegezu behula wengielawi hunew 3 books leprotestantoc aberktewal) ዱሮ ስናውቀው የአጋንንት መንፈስ ለማውጣት ከሰፈር ሰፈር በሽተኛ አላችሁን እያለ ይዞር ነበረ አሁን ምን ነካችሁ? ብዙ ሰው አሳቱ ብላችሁ ካሰባችሁ ለምን ፊት ለፊት አትጋፈጡዋቸውም?አሁን ምን አስፈራችሁ? በ አዳኛችን ስም የሚፈውሱትን ግርማ ምን አስፈራችሁ? እውን አስማት ከኢየሱስ በላይ ነውን ወይስ የናንተ እየሱስ ሌላ ነው?

   Delete
  3. ante pente

   Jesus healed only those who believe and demanded to get his blessing. thousands of people were following him but only few were healed. these pastors could be healed if they were in a position to get the exorcism. but they were there to oppose him and show their jesus is powerful to crash his magic.

   you can come and see....your false jesus that led the europeans and americans to atheism, Judaism and sodomy will be casted out of you.....ahunima nektenal tiru memhirna abat agignitenal!!!!!!

   tebabrachuh yemitserut yebetekristian tenkuyawochina pentewoch aferachuh.....yenante geta hayil kalew nuna memhir girman fewusut...leba bicha.....nisiha bitgeba yishalihal......legeta yakena yemimesilew menfes leferenjim alitekeme...nika you dull...

   Delete
 2. ከመሪጌታ ሠረቀ ብርሃን መጽሐፍ የቀረበልን ሐተታ በግለሰብ የህይወት ታሪክ (የትምህርተ ክህነት ፣ የውትድርና ፣ የስደተኛ ፣ የመንፈሳዊ አገልግሎት) ላይ ያተኮረ ስለሆነ ፤ ባለ ጉዳዩ ወይም በቅርብ የሚያውቋቸው ግለ ሰዎች ትክክለኛውን አስተያየት ቢሰጡ መልካም ይመስለኛል ፡፡ ጽሁፉን ጠቅለል አድርጌ ስረዳው ግን የገበያ ሽኩቻ በመፈጠሩ የተጻፈ መስሎኛል ፡፡

  ይኸንን ለማለት ምክንያቶቼም በዝዋይና በቡታጅራ ከተሞች ለጥቂት ዓመታት መንፈሳዊ የሚመስል አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቶ በማለት የመምህር ግርማን መንፈሳዊ አገልግሎቱን ካንኳሰሱ በኋላ
  1. አስቀድመው ክህሎቱን ለማጣጣል የመምህርነቱን ህጋዊነት ይሞግታሉ

  2. መምህር ግርማን እንኳንስ ባለ ሚሊየነሩ እያሉ ሃብታምነታቸውን ይገልጻሉ (የሃይማኖት ግድፈትን ከማሳየት ይልቅ ሃብት ንብረትን አይቷል)

  3. በሰባት ብር የሚገዛን መቁጠሪያ በሃያ ብር ይሸጣል ፤ በሰላቢ አሠራር በርካታ ገንዘብ የሚበዘብዝ ነጋዴ ነው ይሏቸዋል (ትርፍና ኪሣራን ጠቁሟል)

  4. የተሰረቀ መቁጠሪያውን ሦስት ሺህ ብር ከፍሎ አስመለሰ (ሳላገኛት የምትል የቁጭት ገለጻ እንዳትሆን ጠርጥሬአለሁ ) ፤ እዚህ ጋ እምም ያሰኘኝ ዜናም ቀርቧል ፤ መቁጠሪያውን ወስደውበት ተብሎ ቢጻፍልንም ዲያቆናት ሌቦች ናቸው የሚልና በገንዘብ የሚደለሉ ወይም የሚቸነፉ የሚያስብል መልዕክት አስነብበውናል ፡፡ አገልጋዮቻችን ሃይማኖት የሚገዳቸው ከሆኑና ፣ ጉዳዩን እያወቁ ፣ ስለምን ለንዋይ ተንበረከኩ ወይንስ እዛ አካባቢ ያልተባበረ ፣ በአሉባልታ ድርሰት የሚመታ ዝርያ ይኖራቸው ይሆን ? ችግር እንዳለ ያመለክታል ፡፡

  5. “የማውቃቸውን ጴንጤዎችን ይዤ (ንክኪው ላይ ትኩረት ይደረግበት) እርሱ ወደሚያጠምቅበት ስፍራ በተደጋጋሚ ሄጃለሁ፡፡” በማለት የምስክርነት ቃል መስጠታቸው ፡፡ መንፈሱን ለመስረቅ ወይም አሠራሩን ለመቅዳት ፣ ወይ መቁጠሪያ ፍለጋ ካልሆነ በስተቀር ፣ ያለጉዳይ ፣ ለዛውም አንድን ትልቅ የተማረ ሰው አስማት አደባባይ ምን ያመላልሰዋል ?


  ይኸን ጉዳይ በዚህ መልኩ እንድመለከተው ያደረገኝ ፣ ከዚህ ቀደም በዚሁ ድረ ገጽ መሪጌታ ሙሴ የህይወት ታሪኩን ሲናዘዝልን ፣ ከጥቂቶች በስተቀር መሪጌቶች ሁሉ በዚሁ የጥንቆላና የአስማት ጥበብ የተካኑ ናቸው ብሎን ነበር ፡፡ ቀጠል አድርጎም አንዳንዱ ሰነፍ ሆኖ … እያለ ይቆጭላቸዋል ፡፡ ሙሴ የተናገረውን ቃል እውነት ነው ብለን ብንቀበለው ፣ እኚህን ሰው ከገበያው የወጡ አኩራፊ ፣ በሌላ ግንባር ዞረው ፣ በአዲስ ስልት ለማጥቃት የሚሞክሩ ብልህ ሰው ያሰኛል ፡፡

  ከጽሁፋቸው መሃል ሌላ እምም ያሰኘኝ ደግሞ ፣ መሪጌታ በመንፈስ ማጣራት ሰበብ ስለ ጴንጤዎችና ፓስተሮች ክርስቲያንነትም ሊያስተምሩን ፣ ያለ ከበሮ መሃል መሃሉን እያሉልን መሰለኝ ፡፡ ጴንጤን ሲገልጹት “በትክክል የጌታ ሞትና ትንሣኤ ገብቶአቸው ጌታን ተቀብለው በንጽሕናና በቅድስና ለጠራቸው ጌታ ታማኝ ሆነው እንደ እግዚአብሔር ቃል የሚኖሩ ክርስቲያኖችን ማለቴ ነው፡፡” ይሏቸዋል ፡፡

  ስለ ፓስተሮችም ደግሞ “መምህር ግርማ ጋ ካለው መንፈስ ይልቅ እነርሱ ጋ ያለው መንፈስ እንደበለጠ ያሳየናል፡፡ በማለት በመጠኑ ይክቧቸዋል ፡፡ ይህን እንደሚገባኝ ስተረጉመው በኀብረተሰቡ አመለካከትና ግንዛቤ ላይ ለውጥ ለማምጣት ቅስቀሳ እያደረጉ መስሎኛል ፡፡

  ፍቅርና አንድነት መፈጠሩን ባልጠላውም የሚያገለግሉባትንና ምናልባትም የሚተዳደሩባትን (ገቢያቸው እሷ ብቻ ከሆነች ማለት) የተዋሕዶ እምነትን ሲተነትኑ ደግሞ ““እንመናት በውነት የአምላክ ናት” ሲባል አብሮ የሚዘምረው ሰይጣን አይደል? ለመሆኑ ሴት አዳሪውና ዘፋኙ፣ አመንዝራዉና ሰካራሙ፣ ጠንቃዩና መተታሙ፣ አስማተኛው፣ ጥላ ወጊ፣ አጋንንት ጎታች የአንደርቢ ደጋሚ ደብተራው ሁሉ የተሰገሰገው የት ሆኖ ነው “ተዋሕዶ ንጽሕት እንከን የሌላት” የሚባለው? ቅድስና በቤተ ክርስቲያችን ስፍራ እንደሌለው እየታወቀ? በማለት ይቀብሩናል ወይስ አንገት ያስደፉናል ልበል ፡፡ እኔ ደግሞ ይኸን ሁሉ ድክመት እየተመለከቱ ርስዎ ደሞዝ ከመቀበልና ከመሄድ በስተቀር የትኛው ዓውደ ምሕረት ላይ ቆመው ጉሮሮትዎ እስከሚደርቅ አስተማሩን እላለሁ? እንዲህ ለገበያ በመጽሐፍ ስለጻፉ ብቻ ከኃላፊነተና ከተጠያቂነት ወይም ከተወቃሽነት ማምለጥ አይቻልም ፡፡
  ይቀጥላል

  ReplyDelete
  Replies
  1. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 13, 2013 at 7:55 AM

   ምእመን
   አምላከ ቅዱሳን ዓይንህን ይክፈትልህ ከማለት በቀር ምን ይባላል?

   Delete
  2. እግዚአብሔር የሁላችንንም ይከፍትልን ዘንድ እኔም እየለመንኩ ነው ፡፡ በርታና ጸልይልኝ ፡፡

   Delete
 3. ክፍል ሁለት
  አንዳንዴ ሳስበው ደግሞ መሪጌታ መምህር ግርማን ይፈሯቸዋልም ልበል መሰለኝ ፡፡ ምክንያቴን ደግሞ እዩት
  1. “በሰውነቱ ያስቀበረውና ያስደገመው አስማት እንዳለው ቢታመንም በዋነነት ድግምቱ መቁጠሪያው ላይ ነው” በማለት ጥንቃቄ የሚደረግበትን ሥፍራ ለይተው ይጠቁሙናል

  2. ራሳቸውን የወንጌል አርበኛ አድርገው ፣ በግንባር ቀርበው ከመሞገት ይልቅ የመንፈሱን ጥንካሬና ኃይለኛነት ለመመዘን የሚያውቋቸውን ጴንጤዎች በተደጋጋሚ እየወሰዱ ማጋፈጣቸው

  3. ስለ መቁጠሪያው በዚህ መጽሐፍ ሲጽፉ እንኳን በቀጥታ ከማውገዝ ይልቅ አሁንም ሪፖርት የማድረግ ያህል “መቊጠሪያውን ገዝቶ በቤቱ ግድግዳ ላይ ያደረገ ሰው በሽታ አይነካውም፤ አጋንንትም አይቀርቡትም እያለ ያስተምራል ፡፡” አቤቱታ ያሰሙናል ፡፡ ከመዘገብ ውጭ የውግዘት ቃል አልተጨመረበትም

  ***** ኢየሱስ የሚለው ስም ከአንድ የእምነት ድርጅት ብቻ ሳይሆን ከስሞች ሁሉ ከያሕዌ፣ ከኤልሻዳይ፣ ከአዶናይ፣ ከኤሎሂም፣ ከአኑኤል ወዘተ እና ከሌሎች ፍጥረታት ሁሉ ስም በላይ ነውና (ዕብ. 1፥4፤ ፊል. 2፥9-11፤ ኤፌ. 1፥2ዐ-21)፡፡

  እዚህ መግለጫቸው ላይ በማበላለጥ የደረደሩልን ስሞች ደግሞ በሙሉ የእግዚአብሔር (የፈጣሪ ፤ የአምላክ ፤ የገዥ ወይም የጌታ) መጠሪያዎች ናቸው ፡፡ እንዲያ ሲሆን ደግሞ አባባላቸው አግዚአብሔርን ከእግዚአብሔር ማበላለጥ ይሆንና የዶግማን ተፋልሶ ያመጣል ፡፡ ሌላም የምለው ነበረኝ እኔ ግን ማለቱ ከበደኝ ፡፡ የዘረዘሯቸው ስሞች ትርጉም በአማርኛ መዝገበ ቃላት አተረጓጐም ቀርቧል ፡፡ የአይሁድን ቋንቋ የሚረዳ ሰው ወይም አይሁድ ወዳጅ ያለው ወገን በትርጓሜው ቢረዳን ትልቅ ትምህርት ይሆነናልና ዕድሉ ያላችሁ አንድ በሉን ፡፡

  ይሆዋ ፡- ስመ አምላክ ፤ ከፈጣሪ በቀር ለማንም የማይሰጥ (ጥብቅ ሰ)
  ያሕዌ (ያህ) ፡- ስመ አምላክ ፤ የይሆዋ ክፋይ ፡፡ ዘይቤው እግዚእ ምስጢሩ ምላትና ስፋት
  አዶን ፡- ጌታ ፣ ፈጣሪ
  አዶናይ ፡- የአምላክ ስም ሲሆን ትርጉሙ ጌታዬና ወይም ጌቶቼ ማለት ነው ፡፡
  እግዚአዊ ፤ ወልደ እግዚእ ፣ ዘቦቱ እግዚአና
  አዶናይ - እግዚአብሔር ተብሎ ለአምላክ ሲቀጠልና የአምላክ ስም ሲሆን ፣ ምስጢሩ ምስጢረ ሥላሴ ነውና ፤ አንድነትን መደብ አድርጎ ሦስትነትን ያሳያል ፡፡ ዘይቤውም ጌቶቼ እግዚብሔር እንዲህ አለ ያሰኛል ፡፡ (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት)
  ኤሎሄ ፡- አምላኬ ወይም አምላክ
  ኤሎሂም ፡- አማልክት ፣ አምላኮች ፣ ዳኞች ፣ ፈራጆች ፡፡ ለፈጣሪ ሲቀጠልና የፈጣሪ ስም ሲሆን በቋንቋ ሁሉ አምላክ ይባላል እንጂ እንደ ዘይቤው ቃል በቃል አማልክት አይባልም ፡፡
  ኤልሻዳይ ፡- የአምላክ ስም

  ከጽሁፉ መልካም ቃሎች የምላቸው ፡-
  - መቁጠሪያ በየቤታችሁ አንጠልጥሉ የሚል ትምህርትን በቀጥታ ባይቃወሙትም ፤ በተዘዋዋሪ ከቅናት በመነጨ ስሜትም ቢሆን መጻፋቸው መልካም ነው ፡፡ ይኸ ልማድ መወገድ ይገባዋል ፡፡

  - “…ክፉ መንፈስ በጾምና በጸሎት ካልሆነ በቀር በቀላሉ ሊወጣ እንደማይችል መገንዘብ ነበረባቸው፡፡” በማለት የጾምና የጸሎትን ጥቅምን ክብደት ሰጥተውታል

  - የማትወዱትን ተአምረ ማርያም በቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ማዕረግ ያለው መጽሐፍ እንደሆነ ለማያውቁ መስክረዋል ፡፡ ቃላቸውም “ከተአምረ ማርያም በቀር …” ብሏልና

  ካነበብኩ በኋላ ማለት ያለብኝን ብያለሁ ፡፡ እናንተም የመሰላችሁን ማለት ትችላለችሁ
  ሰላም ሁኑልኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምእመን ይህንን መጽሃፍ አንብበው አደራህን አንብበው ብዙ ነገር ታውቅበታለህ በተርፈ የምትጽፋቸው ጽሁፎች ይምቹኛል በርታ http://www.ethiopianorthodox.org/amharic/holybooks/seweruadega.pdf

   Delete
  2. ምእመን ይሄን አንብበው ሁለተኝ አደራ http://good-amharic-books.com/images/PDFs/shirts.pdf

   Delete
  3. ለ AnonymousJanuary 13, 2013 5:19 AM
   AnonymousJanuary 13, 2013 5:54 AM

   ስለሰጠኸኝ አድራሻ እግዚአብሔር ይስጥልኝ ፡፡ ትልቅ እገዛ ነው ፡፡ በተለይ መለሰ ወጉ የሚባለው ብዙ የሚጽፍ ሰው ቢሆንም መንፈሳችን የተለያየ ስለሆነ ነው መሰለኝ መጽሐፍቱን አንብቤ አላውቅም ፡፡ በቀሲስ መላኩ አወቀ የተጻፈውን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ የቀረበውን ከዚህ ቀደም የተወሰነውን አንብቤዋለሁ ፡፡ ዛሬ ግን ሁለቱንም መጽሐፎች በኮምፒዩተሬ ስለጫንኩአቸው በአንተ ግብዣ መሠረት እስከ መጨረሻ አነባቸዋለሁ ፡፡

   መደጋገፍ እንዲህ ነው ፡፡ እኛ እንዲህ እንደየአቅማችን በሃሳብ ከተደጋገፍን አጥሩ ግንብ ይሆንባቸዋል ፡፡ የቤተ ክርስቲያናችንን ትምህርት የተማሩ ሊቃውንት ካገኘህም እየጋበዝክ አስተያየት እንዲሰጡ ብታደርግ ብዙውን ሰው ከመጠለፍ ታድናለህ ፡፡ አንተም በተረዳኸው መጠን ፣ ሰዎችን ሊያስተምር የሚችል ገንቢ አስተያየት ጻፍ ፡፡ ስህተት ቢሆን እንኳን እየተራረምን እንማራለን ፤ ለመጻፍ አትፍራ ፡፡ ብትሳሳት ማርክ አይቆረጥ ጭንህ አይቆነጠጥ ፡፡ ከነርሱም መሃልም ደግሞ ብዙ የአዋቂ አጥፊዎች ስላሉ አንዳንዴ ከሚያቀርቡት በየአጋጣሚው እንማራለን ፡፡

   ሰላም ሁንልኝ

   Delete
 4. መሪጌታ እንኳን ደህና መጡ በአለም የተላኩ ወንጌላውያንን የምትገድል ብቸኛዋ ቤተክርስትያን ባዩ ሰረቀ = ለመሆኑ ፓስተሮች ዘማሪዎች አልተፈወሱምን?ልጠቁምዎት መሰለኝ http://www.youtube.com/watch?v=HF2oMuhCels http://www.youtube.com/watch?v=pdKipHmovnQ http://www.youtube.com/watch?v=EaIEOBGy8W0 http://www.youtube.com/watch?v=L6c7dTAObfw http://www.youtube.com/watch?v=1zTEQTn29xU http://www.youtube.com/watch?v=wdbKrJ0a5PU http://www.youtube.com/watch?v=6G7TKuy-FxY http://www.youtube.com/watch?v=p0u8gLQnAxQ http://www.youtube.com/watch?v=xaTBGFhHclg http://www.youtube.com/watch?v=PDXFE0Z2tjg http://www.youtube.com/watch?v=Z1DYlfyALjohttp://www.youtube.com/watch?v=0-id1Kd9DS4 http://www.youtube.com/watch?v=2ytFL91CmD0 http://www.youtube.com/watch?v=wiM_YE_mIJ0 ነገሩ ግርማ ርስዎእንደጻፉት መጽሃፍ የዘመናት እንቆቅልሽ@ ቢሆንብዎት አይገርመኝም? ለመሆኑ ግርማ ከአውደነገስት ገላጮች አጋንንቱን ሲያስወጡ አልተመልከቱምን

  ReplyDelete
  Replies
  1. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 13, 2013 at 7:42 AM

   ምእመን

   How much is you are paid by Girma? you know what go watch your crappy video of false devil healing. We are not serfet to see ye setane agelgelote. Shame for you!

   Also, why don't limit your post only by your name ምእመን? you have send several comments by anonymous.Let me ask you, when are you going to be Christian?

   Delete
  2. JESUS IS THE LORD. THIS IS ENOUGH.

   Delete
  3. I THINK THE ARGUMENT IS BASED UPON A QUARREL THAT WHO THE BEST IS. LEAVE THAT AND PREACH JESUS. HE WINS!!!

   Delete
  4. THE DEVIL IS THE FATHER OF LIES. DO NOT LISTEN TO WHAT HE SAYS AND ARGUE ON THAT, THE BIBLE SAYS HE CAN EVEN CHANGE HIMSELF OR HIS SEREVANTS AS GODLY MINISTERS (2 COR 11:15). STOP THE ARGUMENT AND PREACH ABOUT THE SON OF GOD, WHO IS THE ONLY WAY INTO HEAVEN. LEAVE THE JUDGMENT TO GOD

   Delete
  5. ለየተሰቀለው
   አስተያየትህን የሰጠኸው የኔ መግለጫ ባልሆነ ቦታ ነው ፡፡ ተደናግጠሃል ወይንም ተናደሃል ማለት ነው ፡፡ ንዴት ከሆነ ደግሞ ከክፉው ነውና ራስክን ተቆጣጠረው ፡፡
   እኔ እውነትን ተከትዬ ስለምሠራ መምህር ግርማን ምንም አላስከፈልኩትም ፡፡ ይህችን ቤተ ክርስቲያን ለመናድና ለማፍረስ አንተን የሚያስተምሩና የሚያስታጥቁህ ስንት እየከፈሉህ ነው ?

   አሁን ከግርማ ጋር ጦርነት የጀመራችሁት ፣ ያስኰበለላችሁትን ሁሉ እያናዘዘ ወደ ቤቱ ስለመለሰባችሁ መስሎኛል ፡፡ እስኪ ውሸት ነው በለኝ ፡፡

   በተረፈ ልታስተምረኝና ልታስተካክለኝ ከፈለግህ ከምጽፈው ቃል እያመጣህ ስህተትነቱን አስረዳኝ ፡፡ ዝም ብለው ቢሉኝ ደደብ ስለሆንኩ የምትሉት አይገባኝም ፡፡

   Delete
 5. WHO ARE YOU?? DO YOU STILL SAY THAT YOU ARE AN ORTHODOX... PLEASE YOU CAN'T CHEAT EVEN A SIMPLE MAN...EVEIDENCE

  ነ መምህር ግርማ ወደሚሠሩት ድራማ ስንመለስ ሰይጣኑ “ኢየሱስ” በል ሲባል “ኢየሱስ” እያለ “ተዋሕዶ” በል ሲባል ግን ይህንን ስም መጥራት አልችልም፤ ያቃጥለኛል ሲል እንሰማዋለን፡፡ እግዚአብሔር ይገሥፀው! እንደዚህ ያለውን ምስክርነት አሜን ብሎ የሚቀበል ሰው እንዴት ምስኪን ነው@
  “ተዋሕዶ ሃይማኖት እንከን የሌላት፣
  “ተዋሕዶ ንጽሕት እንከን የሌላት፣
  “እንመናት በውነት የአምላክ ናት” ሲባል አብሮ የሚዘምረው ሰይጣን አይደል? ለመሆኑ ሴት አዳሪውና ዘፋኙ፣ አመንዝራዉና ሰካራሙ፣ ጠንቃዩና መተታሙ፣ አስማተኛው፣ ጥላ ወጊ፣ አጋንንት ጎታች *የአንደርቢ ደጋሚ( ደብተራው ሁሉ የተሰገሰገው የት ሆኖ ነው “ተዋሕዶ ንጽሕት እንከን የሌላት” የሚባለው@ ቅድስና በቤተ ክርስቲያችን ስፍራ እንደሌለው እየታወቀ@

  የኢየሱስን ማንነት የተረዳ ሰው ኢየሱስን “ተዋሕዶ” ከሚለው የእምነት ድርጅት ጋር አያነጻጽርም፡፡ ኢየሱስ የሚለው ስም ከአንድ የእምነት ድርጅት ብቻ ሳይሆን ከስሞች ሁሉ ከያሕዌ፣ ከኤልሻዳይ፣ ከአዶናይ፣ ከኤሎሂም፣ ከአኑኤል ወዘተ እና ከሌሎች ፍጥረታት ሁሉ ስም በላይ ነውና (ዕብ. 1፥4፤ ፊል. 2፥9-11፤ ኤፌ. 1፥2ዐ-21)፡፡ በመሆኑ ሰይጣን የኢየሱስን ስም ለማስጣልና ለማስካድ ከመምህር ግርማ ጋር ተስማምቶ ወይም መምህር ግርማን ተጠቅሞ ይህን ይበል እንጂ እውነተኞች ግን አይቀበሉትም፡፡ ሰይጣን ሐሰተኛና የሐሰት አባት መሆኑን ያውቃሉና፡፡ በእርግጥ ሰይጣንን እውነተኛ አድርገው የተቀበሉት ሰዎች ኢየሱስን መቃወማቸው አይገርምም፡፡ የሚገርመው ከሰይጣን ጋር ተስማምተው እየኖሩ አልፎ አልፎ የኢየሱስን ስም መጥራታቸው ነው፡፡

  ReplyDelete
 6. Dear Christians,

  (2 Theselonke 2:3- 10), teaching us about deceptive teachers. Please read it! Be Krsotse laye anamenzer ebakachew. Satan himself transforms himself into an angel of light, don't be surprised! Stick with the bible and take Jesus your only why to go to the Kingdom of God.

  Thanks

  ReplyDelete
 7. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 13, 2013 at 8:28 AM

  The Following is a true story, after I shared Abaslema at face book. I got a chance to chat with her about Girma. Read the following true story:


  HI , I am sorry earlier when we communicant I was having hard time with the connection I was using my cell phone and b/c I was at work by the time and us I told I don’t have amharic software so I am not be able to read it but I have a feeling that this man doesn't have blessing from God. When I was in Ethiopia my friends all they are his followers so they told me his story but heart didn't let me trust him so one day one of my close friend she call me and she said there is tselot program in her house the Guest for the program is Memhra Girma so I ask why she told me we all tsebel metemek alebn and I said to her I am busy and I heard they all scream he told them they have yesytsn menfes or somebody did bad thing to them I said to them how what he did to heal you guys they told me mekuterya alachew ena when he hit you with that you will get heal so it's caution in my mind but my friends they been telling me if I go I will scream one day I call Memhra Girma in his cell phone I make appointment with him and we have coffee to gather and I ask him my husband and I tsebel metemek metemek Enfelgalen and he said com to gorgoryos church I said no and I ask him in his house and he offer me if he can do it in our house and I said no and said to him hulum sew sytan alebet ybalal ena ebatwo yatmkug ena lyew alkuwachew and me and my husband we went to his home and I pray to my god be for I get in so I didn't say anything but my husband after he hit him with his mekuterya he start saying something and I told him besmeab bel and he stop and I ask him what is the mekuterya why he hit with that he didn't answer my causation but he told me that I don’t have seytan and I told him I know I don’t have anything and I ask my husband why he did that and he told me that he was ok but after he hit him with his mekuterya he start talking and when I said besmeab bel to him everything goon so after that time I know he is not from God but me I am not the person trust easily those kind things I did it b/c my friends they been telling me if I go that I am going to scream so I want to show them. But by the time if you said he is not from God or he don't have power this poor people no body listen to you I hope you will understand what I have rout sorry I mix English and amharic.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድሜ ለማስተባበል የሞከርክበት ድርሰት ጥሩ ነበር ፡፡ ግን ሙሉ ለሙሉ አልተዋጣልህም ፡፡ ቀደም በዋናው ሰው ከተሰጠው መግለጫ ተጣርሷል ፡፡

   ማነው የመጀመሪያውን የመምህር ግርማን ታሪክ የጀመረልን ዲያቆን ነው ምን ? ብቻ አዎ እሱ ሲጽፍ እኮ ከሰዎች በግል አለመገናኝቱን አስነብቦን ነበር ፡፡ መለስ ብለህ አንብበው

   ማረጋገጫ በማለት በቁጥር ከደረደራቸው ውስጥ በቁጥር ስድስት ላይ የሚከተለውን ጽፏል ፡፡
   6 “ብዙ ጊዜ አኗኗሩ ለሰዎች ድብቅ ነው፡፡ ተማሪ ተ/ማርያም ያለኝ ትዝ ይለኛል፡፡ ይህንን ሥራ ለመሥራት አንዱ መስፈርት /ሕግ/ ከሰዎች መገለል ነው፡፡ ምክንያቱም ከሰዎች በተቀላቀለ ቁጥር የአንዳንድ ሰዎች የተፈጥሮ ሃይል /ፓወር/ የሚታዘዙትን የመናፍስት አለቆች ስለሚፈታተናቸው ነው፡፡”

   ታድያ የማንን እንመን ? የአንተን ልብ ወለድ ወይስ የጸሐፊውን ፡፡
   ከጻፍከው ሁሉ መልካም መልዕክት የምልልህ በአብ በወልድ በመንፈሰ ቅዱስ ስም ክፉውን መንፈስ መገሰጽ እንደሚቻል ማስተማርህን ነው ፡፡ “በስመ አብ” በል እያለች ባሏን የመከረችው ሃይማኖት ያስተምራል ፡፡ የተቀረው ግን እኔ እንጃ ፣ ሚዛን አልደፋልኝም ፡፡

   ይኸን የጻፍኩት ወንድሜን ለማናደድ አይደለም ፡፡ ብትችል ስትጽፍ ጥንቃቄ እንድታደርግ ለማሳየትና ነገሮችን ለማያያዝ ትንሽ ረጋ እንድትል ነው ፡፡

   Delete
  2. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 14, 2013 at 10:22 AM

   ምእመን
   Stop right here!

   ታድያ የማንን እንመን ? የአንተን ልብ ወለድ ወይስ የጸሐፊውን ፡፡

   My Family never thought me deception, I am from the respected family, living and obeying principles. The only reason, I am sending you a comment for you is I don't like to see lie ( woshet), I can't pass it. In addition, I don't want any one to oppose the power of Holy Trinity and Our savior Jesus. That is the only reason I stay in Orthodox church.

   Your church is based on Grima's መቊጠሪያ, mine is based on Lord Jesus blood. Maferia!

   Delete
 8. Dear Aba Selama:- This article is great! I think you should better reorient yourself towards such bigger enemies of our people and church rather than fighting with your own brothers and sisters who are working for the church. Thanks!

  ReplyDelete
  Replies
  1. እየተቆጫችሁ በመሄዳችሁ መምህር ግርማን ሳልወድ በግድ ደም መላሽ አሰኛችሁኝ ፡፡ አንዱ ግርማ የኰበለሉትንና የጠፉትን ሁሉ እያስጓራ ወደቤታቸው በገፍ መመለስ ስለጀመረ ማነጣጠራችሁ ትክክል ነው ፡፡ ግን ጉዳዩ ከርሱ ሳይሆን ፣ ከላይ ከፈጣሪ ስለሆነ አሠራሩ ከሰው አቅም በላይ ነው ፡፡ ለዚህች ቤተ ክርስቲያን ማንሰራራት የተላከ የንጋት አርበኛ ነውና ፤ እርሱን ብታገሉት እንኳን እግዚአብሔር ሌላ ማስነሳቱን አይተውም ፤ ጦርነታችሁ አቁሙት ፡፡ መጽሐፍም ከሰው ጥበብ ከሆነ ይጠፋል ከአምላክ ከሆነ ይስፋፋልና ርሱን መከታተሉን ተወት አድርጋችሁ እንዲሆን የምትፈልጉትን በጾም በጸሎት ጠይቁ ፡፡

   Delete
  2. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 14, 2013 at 10:10 AM

   ምእመን ዘግርማ አገልጋይ

   You said:እርሱን ብታገሉት እንኳን እግዚአብሔር ሌላ ማስነሳቱን አይተውም ፤ ጦርነታችሁ አቁሙት ፡፡

   Make sure or to give you መቊጠሪያ to replace him. I am sure you have one. please read the bible--The Apostle Peter when healed a man,a crippled one from since his birth did not use መቊጠሪያ in order to heal that crippled just said only words " I don't have gold or silver, but I have Jesus Christ, Walk"

   I am worried about your soul, please come to your mind. I pray God to return you to the truth.

   Delete
  3. ለየተሰቀለው

   መቁጠሪያ በግድግዳ አንጠልጥሉ የሚለውን ትምህርትማ ፣ ከመሪጌታና ከአንተም ይልቅ መጥፎ ልምምድ ስለሆነ መወገድ አለበት ብዬ ያስነበብኩህ በኢየሱስ መሞትና መነሳት የማምነው ፣ እኔው ክርስቲያኑ ነኝ ፡፡ አሁንም የጻፍኩትን ከመተቸት ይልቅ ሌላ ርዕስ ቀይረሃል ፡፡

   Delete
 9. Here is what the holy Bible said about Galatians . . . And “Menafiqan aka Pente”
  “O foolish Galatians, by what strange powers have you been tricked, to whom it was made clear that Jesus Christ was put to death on the cross?” . . . Let me say this. . . O senseless ‘’menafiqan”, who has bewitched you that to not believe, the work of memher Girma is not from the God. Thank you God for giving us memher Girma we learn a lot about you (menafiqan). Instead of pouring false accusation on memher Girma, I will advise you to abandon your Protestantism and come back to Orthodox Tewahedo before the sunset on you. “IF YOU ARE WISE”

  ReplyDelete
  Replies
  1. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 14, 2013 at 7:55 PM

   Instead of pouring false accusation on memher Girma, I will advise you to abandon your Protestantism and come back to Orthodox Tewahedo before the sunset on you. “IF YOU ARE WISE”

   Let me give you the "wise man" the follower of Devil Girma, be wise to get መቊጠሪያ to replace him.we follow Our father the Almighty of God living at the heaven, our faith is based on by looking Jesus wound, his suffering at Gologota, his cursification at Kernayo.

   we are not looking for miracle to be a christian, our faith is beyond that. you may ask, who is this guy said we? I tell you We the true orthodox Christina who listen Saint Mary,What she told us at kana zegelela, she said: she said do what ever my son told you to do (in simple language). we listen our Mother Saint Marry, she can only be our Mother if we worship her son.

   you and your friends, who forgot what Lord Jesus did for you and worshiping human and now a person guided and powered by devil Girma. you have not place at either on the earth or at heaven. Mafriawoch!

   We will save Orthodox by preaching Lord Jesus! Amen!

   Delete
 10. ለየተሰቀለው
  "I am from the respected family."
  ውሸትን ከቤተሰብ ወረስክ አላልኩም ፡፡ እነርሱ እንዲህ ሲሆኑ አንተ ግን ከምን አመጣኸው ታድያ ? እኔም እንደ አንተ ክርስትናን የሰበኩልኝንና ያስተማሩኝን አባቴንና አጐቴን ተከትዬ ነው መጽሐፍንና ሃይማኖቴን የመመርመር ነገር የተማርኩና በፈለጋቸው የተከተልኩት ፡፡ እነርሱ እንዲያ ባይተጉልኝ ፣ እኔም እንደ አንዳንዶች ፈረንጅ ተከታይ ሆኜ እነጉድ ነበር ፡፡

  I stay in Orthodox church.
  አመሰግንሃለሁ ፡፡ አንድ ጥያቄ ጠይቄህ ግን አልመለስክልኝም ፡፡ ዛሬም ሳትዋሽ ፣ ሳትተነትን ቁጥር በመጻፍ ብቻ የምትመልስልኝ ከሆነ እደግመዋለሁ ፡፡

  ****** ቅድስት ድንግል ማርያም ስንት ልጅ አላት ?

  “Your church is based….”

  ይኸን ስትለኝ አንተ በእኛ ማኀበር የለህበትም ማለት ነው ፡፡ በል እንግዲህ ያንተ ቤተ ክርስቲያን የሆነችው ማን እንደምትባል ንገረኝ ፡፡ እኔ እውነትን ከማወቅ ውጭ ምንም ለማለት ፈልጌ አይደለም ፡፡ አትንኩኝ የምል እንጅ ፣ የእኔ እምነት ብቻ የሚል አቋም የለኝም ፡፡

  ሰላም ሁንልኝ ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 15, 2013 at 7:53 AM

   ****** ቅድስት ድንግል ማርያም ስንት ልጅ አላት ?

   Be Geta be Eyesus yalen holeu Ye esua legochenen.

   ይኸን ስትለኝ አንተ በእኛ ማኀበር የለህበትም ማለት ነው ፡፡ በል እንግዲህ ያንተ ቤተ ክርስቲያን የሆነችው ማን እንደምትባል ንገረኝ ፡፡ እኔ እውነትን ከማወቅ ውጭ ምንም ለማለት ፈልጌ አይደለም ፡፡ አትንኩኝ የምል እንጅ ፣ የእኔ እምነት ብቻ የሚል አቋም የለኝም ፡፡
   Yene betekirstain ye temersertechew be lego deme nowe (my church is based on by the blood of my Lord Jesus Christ)and by faith,
   About you: There is no doubt you have knowledge (even devil has) the problem is you don't have faith to believe the existence of God you are looking for Miracles. finally, the devil powered Girma's miracles leading you to wrong place.at this time your faith and believes as well as your hope is evil Grima.

   I said earlier in other comment, I have not read and have a bible knowledge as you have but I can confidently said that I have faith and I am not looking for miracles to believe in on Lord Jesus, Keranewo and Gologota are enough to trust Lord Jesus.

   Delete
  2. ለየተሰቀለው
   አሁንም ጥያቄዬን ሸፈን አድርገህ አለፍከው ፡፡ እኔ የጸጋ ልጆችን ቁጥር አይደለም የጠየኩህ ፡፡

   ጥያቄዬን አሁንም በግልጽ ላስቀምጥልህ ፡-
   *** ቅድስት ድንግል ማርያም ከአብራኳ የተወለደ ስንት ልጅ አላት ? እንደ ቋንቋችንና ባህላችን አነጋገር የሥጋ ልጅዋን ማለቴ ነው ወይም ዲኤንኤ ብንሠራ ፣ አዎ የርሷ ነው የምንለውን የልጅ ቁጥር እንድትመልስልኝ ነው የጠየኩህ ፡፡ የምታምነውን የልጅ ብዛት (ቁጥር) ብቻ እንድትገልጸው ነው የፈለግሁት ፡፡

   እባክህ አአሁንም ሳትዋሽኝ መልስልኝ ፡፡

   Delete
  3. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 15, 2013 at 11:45 AM

   Oh! I got you. She is a step mother for Yackob. My mother Saint Mariam is ድንግል (virgin) before and after the birth of son of God.

   Does your question is to know about my religion? Today is the Day of the Holy Trinity ( ጥር 7 ), I just finished my prayer about you guys, who worshiping wrong spirit in stated of the true one that is Lord Jesus.For your information: My kids were baptized At the Holy Trinity Cathedral at addis. If I am protestant I would not have to traveled 20 hours three time to Addis.

   Delete
  4. ወንድሜን በእውነትም ጌታ ይባርክህ ፡፡ የጥያቄዬ መነሻ ምክንያት የነበረው አሁን በቀደም ለአንድ ወንድም አስተያየት ስትሰጥ ፣ ባስቀመጥከው አድራሻ ውስጥ ገብቼ ሳደምጥ ሰባት ስድስት አምስት እያሉ ያላዋለዱትን የልጆች ጋጋታ ሲቆጥሩ ስለሰማሁ ነው ፡፡

   ከአዳመጥኳቸው አምስት አስተማሪዎች ውስጥ አራቱ "...half brother of Jesus" ብለው ሲገልጹ አንደኛው ብቻ "...are step brothers" እያለ ያስተምራል ፡፡ ኋላም ይሄ ሰው ኦርቶዶክሰ ነኝ እያለን ፣ እዛ ደግሞ ምን ይሠራል? እየዋሸኝ ነው ማለት ነው ብዬ ስለተጠራጠርኩ ለመጠየቅ ደፈርኩህ ፡፡ ሁለተኛውንም ንስሓዬን ዋጋ ሰጥተህ ይቅርታ ታደርግልኛለህ ብዬ አስባለሁ ፡፡

   ግና አሜሪካ ክርስትና አያነሱም እንዴ ? ለምን ይኸን ያህል ድካም ? አገርና ቤተሰብ ናፍቆህ የተመላለስከውን ሁሉ በክርስትና አሳበብከው ወይስ አረብ አገር ነው ልበል የምትኖረው ፡፡

   ከእዚሀ ወዲያ ከበድ ያለ ቋንቋ ብትጠቀም እንኳን አልከፋም ፡፡ ሰላም ሁንልኝ ፡፡

   Delete
  5. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 15, 2013 at 2:35 PM

   ምእመን
   Let me answer try to answer your question:

   ጥያቄዬን አሁንም በግልጽ ላስቀምጥልህ ፡-
   *** ቅድስት ድንግል ማርያም ከአብራኳ የተወለደ ስንት ልጅ አላት ? እንደ ቋንቋችንና ባህላችን አነጋገር የሥጋ ልጅዋን ማለቴ ነው ወይም ዲኤንኤ ብንሠራ ፣ አዎ የርሷ ነው የምንለውን የልጅ ቁጥር እንድትመልስልኝ ነው የጠየኩህ ፡፡ የምታምነውን የልጅ ብዛት (ቁጥር) ብቻ እንድትገልጸው ነው የፈለግሁት ፡፡

   Which one of the following statements are true about ቅድስት ድንግል ማርያም
   A. She is the mother of Lord Jesus
   B. she is a step mother of Yakobe
   C. She is virgin before and after birth of infant Jesus
   D. Yosefe was her guard, not a husband
   E. ድንግል ማርያም did tell us to listen her Son Jesus at kan zegelela.
   F. All of the above statements are correct

   The answer is F

   Delete
  6. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 15, 2013 at 3:31 PM

   ምእመን

   No problem, trust me I will never leave the church.But I want to see change in my church,if I suppose to leave the Orthodox, I would have to leave it when I was 10 years old. I need the church to be free of tenqulena,metete, tert tert and ETC.
   ምእመን, I will tell you that I listen tesfay gabisso and other old pent mezemure. Ask me why?

   Delete
  7. አየህ አሁን መስመሩን እያየኸው ነው ፡፡ እኔም እንደዚህ የተበላሸ ነገር ካላት መስተካከሉን አልቃወምም ፡፡ ይኸንን ካየህ ማሻሻል ለሚችለው ክፍል መጠቆም ፣ አቤት ማለት ያስፈልጋል እንጅ ፣ ከደጅ ሆኖ ማውራት ፣ ለሃሜተኛ ማጋለጥ ነው የሚሆነው ፡፡ ከባለቤትህ ጋር ችግር ቢኖርብህ ፣ ከቤትህ ገብተህ ትወያያለህ እንጅ ፣ አውራ ጎዳና መንገድ ላይ ቆመህ አንቺ አንተ አትባባሉም ፡፡

   Delete
 11. If the information is correct Please tell to all Orthodox Tewahedo Christian follower

  ReplyDelete
 12. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 15, 2013 at 4:11 PM

  ምእመን
  When I was nearly Six years old, I was traveling to Lalibla with Airplane my mother and two of my siblings. I saw the Holy-trinity in the cloud, I was shouting and told my mom, look! Slesewech, Look! passengers said kids can see. I also feel like God is at that particular church. I have a lot to share you but that is enough for now. There are many churches in the place I am living (north america), but I have enough reason plus I promised him when I was in Ethiopia for Holy Trinity.

  Peace for you

  ReplyDelete
  Replies
  1. ተአምር ልትነግረኝ ፈልገህ ወይንስ እውነተኛ ገጠመኝህን እየመሰከርክልኝ ነው ፡፡ እንዲህ እንደምትለው በእውነት አጋጥሞህ ከሆነ ደግሞ በእውነትም ዕድለኛ ነህ ፤ ስለዚህም አንተ በእምነት ልትበልጠኝ ይገባሃል ፡፡ ምክንያቱም በገሃዱ ዓለም ምልክት አይተሃልና ፡፡ እኔ ደግሞ በጽድቅ እቀድምሃለሁ ፣ ምክንያቱም ሳላይ አምኛለሁና ፡፡ ደግሞ ብለህ ብለህ መቀልድ ጀመርክ አይደል ፤ አንዳንዴ ህይወትን እንዲህ ካላዋዟት አትጥምምና ፤ በርታ ፡፡

   እኔም ደግሞ ከጐረመስኩ በኋላ በአውሮኘላን ስጓዝ ፣ በመስኰት ቀዳዳ ደመና እንደ ጥጥ ተነጥፎ ስላየሁ ምናልባት ከመልአክ አንዱ ወይም ቅድስት ድንግል ማርያም ቢትታየኝ በማለት ስፈልግ ብዙ ሰዓት ቆየሁ ፤ ኋላም እንጽብራቄው በዛብኝና ዓይኔን በማስቸገሩ አቋረጥኩ ፡፡ እግዚአብሔርን ማየት ያልፈለግሁበት ምክንያት ፤ ፊቴን አይቶ ሰው መኖር አይችልም ብሎ ስላስጠነቀቀ ፈርቼው ነው ፡፡ ያን ጊዜ የሆነ ነገር ቢያጋጥመኝ እኔም ዛሬ እተርክልህ ነበር ፡፡

   ገጠመኝህን ስላካፈልከኝ አመሰግናለሁ ፡፡ ሰላም ሁንልኝ

   Delete
  2. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 16, 2013 at 10:59 AM

   ምእመን

   I never expect any positive comments from you, I am busy now! I get you some other time, to response for your negative comments.

   Delete
 13. medhaniyalem huletachihunm yastemirachihu. eme birihan libona tisitachihu.

  ReplyDelete
 14. aba girma is the right,,,,,,,amlakachin Eyesus christosim,,,,yesachewun ababal yidegifal,,,,,,,be mat24;15" bemechereshaw zemen,,,,,,bizu christosoch yimetalu,"",,,,bilual,,be sime Eyesus yetenagere hulu,,,,christian aydelem,,,,,,,protestantism, forgid christos amlaki new,,,,lezih new aba yetenagerut.

  ReplyDelete
 15. ምእመንJanuary 13, 2013 at 10:43 PM
  የኔ ምክር!

  "መደጋገፍ እንዲህ ነው ፡፡ እኛ እንዲህ እንደየአቅማችን በሃሳብ ከተደጋገፍን አጥሩ ግንብ ይሆንባቸዋል ፡፡"

  ጥያቄ: ለድጋፋም ደርስዋል ማለት ነው አጥሩ? ደሞም ለዛወም “የሃሳብ ድጋፋ” የሚገርም ነው በጣም ::

  “የቤተ ክርስቲያናችንን ትምህርት የተማሩ ሊቃውንት ካገኘህም እየጋበዝክ አስተያየት እንዲሰጡ ብታደርግ ብዙውን ሰው ከመጠለፍ ታድናለህ ፡፡”

  ጥያቄ: የአስትያየት አይነትህ ያውም ለ "የሃሳብ ድጋፋ" ብቻ ተብሎ, ከመጠለፍ ካዳነ ጥሩ:: ግን ቃሉ ላይ እግዚአብሄር እረኛዬ ነው የሚለው ጠባቂ ስላስፈለገን ነው:: በበኩሌ የሃሳብ ድጋፍ ውስን ይመስለኛል; "የሚጠብቀን አይተኛም አያንቀላፋም" የሚለው ቃል ኣይሻልም?

  “አንተም በተረዳኸው መጠን ፣ ሰዎችን ሊያስተምር የሚችል ገንቢ አስተያየት ጻፍ ፡፡ “

  እንግዲህ እኔ የጻፍክለት ሰው ባልሆንም, "Think outside of a box" እንደሚለው አስተያየት አይምሮህን ያድሰዋል የሃሳብ ድጋፍም ይሆንሃል ብዬ እመክርሃለው::"

  "ብትሳሳት ማርክ አይቆረጥ ጭንህ አይቆነጠጥ ፡፡ "

  ተጠንቀቅ ጠፍቶ ማጥፋት አክሊልን ይሰርቃል, የደግፍከውንም ቤት ሳትወርስ ትቀር ይሆናል ስለዚህ የማይሳሳተውን የእግዚአብሄርን ጥበብ ክርስቶስን ልበስ::

  “ከነርሱም መሃልም ደግሞ ብዙ የአዋቂ አጥፊዎች ስላሉ አንዳንዴ ከሚያቀርቡት በየአጋጣሚው እንማራለን ፡፡“

  መችም ይቺ ትንሽ ምክር ወደ "አዋቂ አጥፊዎች" አሳልፎ ይሰጥሃል ብዬ አላስብም ልብ ብለህ ስማት,

  የማቴዎስ ወንጌል
  7፥24 ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል። ፥25 ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት ገፋው፥ በዓለት ላይም ስለ ተመሠረተ አልወደቀም። 26 ይህንም ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሰው ሁሉ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራ ሰነፍ ሰውን ይመስላል።

  በ ሃሳብ መደጋገፍ ሳይሆን አጥሩን ግንብ የሚያደርገው, ሳያወላውሉ በ አለቱ በ ክርስቶስ ላይ ብቻ መመስረት ነው:: ይህንን ብቻ ነው "አዋቂ አጥፊ ማይሽረው" ::

  በተጨማሪ የ ደጋፊን ሃሳብ ሳይሆን ያንተን እንድታሰማ አበረታታሃለው::

  ReplyDelete
 16. "የማውቃቸውን ጴንጤዎችን ይዤ እርሱ ወደሚያጠምቅበት ስፍራ በተደጋጋሚ ሄጃለሁ፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ ከወሰድኳቸው ሰዎች መካከል አንድ ሰው እንኳ የጮኸ ግን የለም፡፡"
  ትገርማለህ የእግዚአብሔር የማዳን እጅ ላመኑት ብቻ መሆኑን ረሳሃው፡፡ ለመሆኑ ክርሰቲያን ነህ;

  የክርስቶስ የማዳን ሃይል አንተ ከምትለው እንቶፈነንቶ/ የሱዳን መተት/ እጅግ የበለጠ ነው፡፡ አንተግን የእግዚአብሄርን የማዳን ሥራ ከመግለጥ ይልቅ የሰይጣንን ጉልበት ለመስበክ አፍህ ተገለጠ፡፡ ለማንኛውም ሜዳውም ፈረሱም ነውና መናፍቅ እያመጣህ አልጮህም ከምትለኝ እሱጋና አንተጋር ያለው “ቅዱሱ መንፈስ ” መምህር ግርማ ውስጥ አለ የምትለውን መትትና እርኩስ መነፈስ ለምን አባሮ ህዝቡን አይታደግም፡፡ ብሎግ ከፍቶ መጮህ ለማንም አይጠቀቅምም፡፡
  ትገርማለህ የእግዚአብሔር የማዳን እጅ ላመኑት ብቻ መሆኑን ረሳሃው፡፡ ለመሆኑ ክርሰቲያን ነህ;

  የክርስቶስ የማዳን ሃይል አንተ ከምትለው እንቶፈነንቶ/ የሱዳን መተት/ እጅግ የበለጠ ነው፡፡ አንተግን የእግዚአብሄርን የማዳን ሥራ ከመግለጥ ይልቅ የሰይጣንን ጉልበት ለመስበክ አፍህ ተገለጠ፡፡ ለማንኛውም ሜዳውም ፈረሱም ነውና መናፍቅ እያመጣህ አልጮህም ከምትለኝ እሱጋና አንተጋር ያለው “ቅዱሱ መንፈስ ” መምህር ግርማ ውስጥ አለ የምትለውን መትትና እርኩስ መነፈስ ለምን አባሮ ህዝቡን አይታደግም፡፡ ብሎግ ከፍቶ መጮህ ለማንም አይጠቀቅምም፡፡

  ReplyDelete
 17. የምትከራከሩት የምትወያዩት ከሞት ቡኋላ ለሚገኘው ህይወት ለማግኘት አይደለም እንዴ ለዛውም በሰው ሳይሆን በእግዚያብሄር ሁሉን በሚያውቀው ስራችሁ ታይቶ ወዴ ገነትና ወደ ሲዖል ልትሄዱ .ታድያ እንደዛ ከሆነ ህሊናችሁ እያወቀ ሆን ብላችሁ የውሸት ታሪክ በመጻፍ በማስመሰል በቅናት ሰውን መወንጀላችሁ ማስከዳታችሁ ትርፉ ለናንተ ምንድን ነው ዋጋችሁስ ምንድነው ?
  ጌታ ይቅር ይበላችሁ ፡፡ ለቡድናችሁ ብላችሁ መሸነፍን መቀበል አቅቷችሁ አትዋሹ ስራችሁ ከሰው እንጂ ከ እግዚያበሄር አይደበቅም በከንቱ አትድከሙ ፡፡

  ReplyDelete