Wednesday, January 16, 2013

በውዝግብ የተሞላው አስቸካዩ የሲኖዶስ ስበሰባ ልዩ ልዩ ክስተቶችን በማስተናገድ ተጠናቀቀ ወደ 6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ ለመግባትም ወስነዋል

ከጥር 6 ጀምሮ ሲካሄድ የቆየውና ትኩረቱን በፓትርያርክ ምርጫና ከምርጫው ጋር በተያያዘ  በተከሰቱ ልዩነቶች ሲወያይ የሰነበተው የጳጳሳት ጉባኤ ዛሬ መጠናቀቁ ተሰማ፡፡ ሲኖዶሱ በሰጠው መግለጫ የእርቁ ሂደት በውጪ የሚገኙት ጳጳሳት ወደ እርቅ ሊያመጣ የሚችል ሐሳብ ባለማቅረባቸውና ለእርቁ ፈቃደኝነታቸውን ባለማሳየታቸው መንበሩ ተተኪ ፓትርያርክ ሳይኖረው መቀጠል ቤተክርስቲያንን የሚጎዳ በመሆኑ ወደ 6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ ለመግባት መወሰናቸው ተሰምቷል። ከፍተኛ ክፍፍልና ንትርክ ባስተናገደው በዚህ ስብሰባ ላይ ለእርቅ ተልኮ የነበረው ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት ላይ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ ኮሚቴው እርቁ እንዲቀድም ቢወተውትም እንዲሁም አቡነ መርቆሬዎስ የሚመጡበትን መንገድ ብንፈልግ ይሻላል የሚል ሐሳብ ቢያቀርቡም፣ ወደ 6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ መግባት የፈለጉት ጳጳሳት «የተላካችሁት አቡነ መርቆሬዎስ ይምጡልን ለማለት አልነበረም አላማችሁን ስታችኋልና ለቀጣዩ ውይይት ሌላ ኮሚቴ ይላካል» የሚል ውሳኔ ማሳለፋቸውን ምንጮች ተናግረዋል፡፡ 4ኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ስልጣናቸውን በመልቀቃቸውም ተጠያቂው ራሳቸው መሆናቸውን የሲኖዶሱ መግለጫ በዝርዝር ያስረዳል፡፡ አቡነ መርቆሬዎስ ግን በመንግስት ተጽዕኖና ጫና ሥልጣናቸውን እንደ ለቀቁ በእርሳቸው በኩል የሚቀርቡ መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ የሲኖዶሱ ውሳኔ አክሎም በውጭ የሚገኙት አባቶች ለእርቁ ፈቃደኞች ከሆኑ የእርቁ ሂደት እንደሚቀጥል ገልጿል፡፡
ከስብሰባው ቀደም ብሎ አቃቤ መንበር ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሲያሰሙ እንደነበረው  መሥራት አልቻልኩም፤ በጳጳሳቱ መካከል የማይታዘዘኝ ቡድን አለ ስራዬን ሊያሰራኝ ስላልቻለና ዐቃቤ መንበርነቴ ትችት ላይ እንዲወድቅ ስለማልፈልግ ጉዳዩን መንግስት ይወቅልኝ ብለው ደብዳቤ መጻፋቸውን ተከትሎ፣ ለምን ደብዳቤ ተጻፈ በሚል አባ ህዝቅኤል ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል፡፡ በሲኖዶስ ጸሀፊነታቸው የአቡነ መርቆሬዎስን ወደ ፕትርክና መመለስ ሲቃወሙ ከነበሩትና ፕትርክናው ለእኛ ይገባል ከሚለው የወሎ ጳጳሳት ቡድን መካከል የሆኑት አባ ህዝቅኤል ስብሰባ ረግጠው የወጡት አቡነ ናትናኤል «የሚቃወመኝ ቡድን አለ» ያሉት እኛን ነው በሚል እንደ ሆነ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ተናግረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የጠቅላይ ቤተክህነቱ አስተዳደር የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በርካታ የደብር አለቆች ጡረታ እንዲወጡ እንቅስቃሴ ማድረጉን ተከትሎ የደብር አለቆቹ ተቃውሟቸውንና በምን ምክንያት ጡረታ ይውጡ እንደተባለ የሚጠይቅ ደብዳቤ ጽፈውና ተፈራርመው ለጠቅላይ ቤተክህነትና ለመንግሥት አቤት ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደተናገሩት ከሆነ ይህን ጉዳይ ወደ ፊት እያስኬደ ያለው ተስፋዬ ውብሸት ሲሆን፣ አላማው አቡነ ጳውሎስ የሾሟቸውን የደብር አለቆች በማንሳት ማቅ በሚፈልጋቸው አለቆች መተካት መሆኑ ታውቋል፡፡ ማቅ በአሁኑ ጊዜ የራሱን ፓትርያርክ ለማስቀመጥ የሚያደርገው ጥረት ውጤታማ እንዳልሆነ ስለተገነዘበ እንደ ግብር ወንድሙ «የግብጹ ሙስሊም ብራዘር ሁድ» ከታች ወደ ላይ ለመምጣት ሲል ይህን አጀንዳ በታዛዥ አገልጋዩ በተስፋዬ ውብሸት በኩል እያስፈጸመ ይገኛል ብለዋል፡፡ በተያያዘም ባለፉት ሁለት ቀናት ማን ያዘዋል ቤተክህነት ግቢ ውስጥ አለመታየቱን ምንጮቻችን ገልጸዋል።       

7 comments:

 1. «የግብጹ ሙስሊም ብራዘር ሁድ»

  አይ ፅጊቱ ታዲያ ለምን ይህን የሚገልፅ መፅሐፍ ፅፈሽ አትቸበችቢም?


  ReplyDelete
 2. Expected news from TPLF. Most racist, stubborn, narrow minded and short sighted organization.

  Expected - because we know their inablity and unwillingness to learn from mistakes

  http://www.ethiotube.net/video/24269/ETV-News--Ethiopian-Orthodox-Synod-says-could-not-come-to-in-agreement-with-the-ETOC-Synod-in-America--January-16-201

  Lie after lie ....huhhhhh

  ReplyDelete
 3. Please watch this too.

  http://www.ethiovid.com/tplf-rejects-the-return-of-abune-merkorios-as-patriarch-of-ethiopia-video_438921ce6.html

  ReplyDelete
 4. ቅዱስ ሴኖዶስ እውነቱ ይህ ስለሆነ አሁን ወደ ፮ኛው ፓትርያርክ ምርጫ ነው የምንሄደው አለ። ታዲያ አቡነ መርቆሬወስ ለምንድን ነው ለሕዝብ እውነቱን መናገር ያቃታቸው ምናልባት እውነቱ ይዅው የሀገር ቤቱ ሴኖዶስ ያለው ስለሆነ ይሆናል።
  ታዲያ ሌላ ምን ይሆናል፣ ማንን ይፈራሉ፣ የሚኖሩት የመናገር ነጻነት በሚከበርበት ሀገር ነው፤ ከእግዚአብሔር ሌላ አለቃ አላቸው ብየ አላምንም። መንግሥት ገልብጦ ወደ ሀገር ቤት ለመግባት መሞከር በመንፈሳዊ ስልጣን መታሰብ የለበትም፤ ለሀገርና ለሕዝብ አይጠቅምም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. አቡነ መርቆርዮስን በቅርብ ከሚያውቋቸው ልጆች አንደበት እንደሰማሁት ፣ አባታችን ሁሉን ትተው በሱባዔ የሚኖሩ ሰው እንደሆኑ ነው ፡፡ እጅግ ካልባሰ በስተቀር ይኸን ያንን የሚሉና የሚናገሩ ሰው አይደሉም ይለቸዋል፡፡ ዕድሜ ራሱ ተጭኗቸው ቅዳሴ እንኳን ለመቀደስ ብዙ እንደሚታገሉ ሰምቻለሁ ፡፡ በጾምና በጸሎት ሰውነታቸውን ስላደከሙት ደግሞ በየአደባባዩ መገለጫ ለመስጠት የሚያስችል ትርፍ አቅምም የላቸውም ፡፡ ፍላጎታቸውን ራሱ ማንም ሰው እንዲህ ነው እንዲያ ሊልም አይችልም ፡፡ ምክንያቱም ዘወትር ወደ አምላክ ከመጸለይ በስተቀር ፣ ከአንደበታቸው ከፉም ሆነ ደግ ቃል ስለማይወጣ ነው ይላሉ ፡፡ ሌላ ቀርቶ ርሳቸውን ወክለው የሚደራደሩና እንዲህ መሆን አለበት ብለው ስለ አንድነት የሚከራከሩት ተከታይ አባቶች ናቸው ፡፡ ከኢትዮጵያ የሚመጡት ተደራዳሪዎች እንኳን ፣ እስከ አሁን አንድም ጊዜ ወደ ርሳቸው ቀርበው አልተወያዩም ፤ ሃሳባቸውን አልተረዱም ፡፡ ይኸ ግርዶሽ ለምን ተፈጠረ ? የእግዚአብሔር ፈቃድ ወይንስ የሰዎች ብልሃት ? መልስ የለኝም ፡፡ ነገሩ ግን እጅግ ግራ ያጋባኛል ፡፡ ስለዚህም ነው በዚህች አገርና በዚህች ቤተ ክርስቲያን ላይ እግዚአብሔር ምን ሊሠራና ምን ሊያመጣ እንደፈለገ አናውቅም ማለት የሚያስችለን ፡፡

   እንዲያው ስናስበው በርግጥ ርሳቸውን የሚጠይቅ አንድ ጋዜጠኛ ከምድራችን ጠፍቶ ነው ? አይደለም ፡፡ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሊያሳየን የፈለገው ገና ብዙ መከራና ፈተና ይቀረን መስሎኛል ፡፡ ሰዎች ይህን ያን ስለወሰኑ አይሆንም ፡፡ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያቸንፈው ማንም አይኖርምና ፣ ርሱ ያላለው አይፈጸምም ፡፡ መሄድ ያለብን መንገድ ሩቅ ሊሆን ይችላል ፡፡ ልንገፋ (ቀላል ገ) የሚገባን ብዙ ሃዘን ይኖር ይሆናልና በሁኔታው ተስፋ አንቁረጥ ፡፡ አሁንም በእምነትና በጸሎት ሆነን በጽናት ወደፊት መጓዝ አማራጭ የማይገኝለት መንገዳችን ነው ፡፡ አሁንም እግዚአብሔር ይህችን ቤተ ክርስቲያንና ልጆቿን ይጠብቅ ፡፡

   ዘገባዬ አሉባልታ ነው ፡፡ እውነትም ውሸትም ሊሆን ይችላል ፡፡ ከሁኔታው ግን እውነትነቱ ያመዝንብኛል ፡፡ ተስፋችንን በእግዚአብሔር ላይ እንጣለው ፡፡ ርሱ የማይፈታው አንዳች የለም ፡፡ ክርስቲያን ደግሞ ተስፋ አይቆርጥም ፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገም ቀናችን ነው ፡፡

   Delete
 5. በእውነት ያሰዝናል፡፡ እግዚአብሔር ጊዜ ሰጥቶን አላወቅንበትም፡፡ ለእርቅ ምን ቅድመ ሁኔታ ይቀመጣል? የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ እርቅን ማወጅ አይደለም ወይ? ከዚህ በኋላ ታረቁ ብለው መናገር እንደምን ይችላሉ? አቡነ መርቆርዮስ በምን ምክንያት እንደወረዱ ይታወቃል፡፡ የእርሳቸውን መምጣት ባይፈልጉ እንኳን እውነቱን ለምን አያምኑም? አቡነ መርቆርዮስ በወረዱ ጊዜ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ "ይህ ሲኖዶስ የዱርዬዎች ጥርቅም ነው" ብለው በአደባባይ መግለጫ ሰጥተው ነበር፡፡ ያለፉትን ዘመናት ታሪካችንን በንስሐ ብንቀብረው መልካም ነበር፡፡ ነገር ግን እየመጣ ያለ መዓት ስላለ እግዚአብሔር እያመቻቸን ነው፡፡ ብዙ ግፍና ዕንባን የተሞላ ሲኖዶስ ነውና፡፡ በስደት የሚገኘውም ሲኖዶስ ከፖለቲካ መስመር ሙሉ በሙሉ ጸድቶ አገር ውስጥ ቅርንጫፉን ሊከፍት ይገባዋል፡፡ ብዙ ምእመናን ይጠብቃሉና፡፡ ይህንን እንናፍቃለን፡፡

  ReplyDelete
 6. ya itis rally muslim brotherhood style. shame on mk.

  ReplyDelete