Tuesday, January 1, 2013

በፓትርያርክ ምርጫ ህግ ዙሪያ ሁለት ጊዜ ጋዜጠኞች ተጠርተው መግለጫ ሳይሰጥ መቅረቱ ተሰማ

Read in PDF
አዲስ በተረቀቀውና እነአባ ሳሙኤል በልካቸው አሰፍተውታል በተባለው፣ በጳጳሳት መካከልና በሌሎችም ዘንድ ከፍተኛ ውዝግብ ባስነሣው የምርጫ ህግ ዙሪያ የተደረገው ስብሰባ ከተጠናቀቀ በርካታ ቀናት ያለፉ ቢሆንም እስካሁን ይፋዊ መግለጫ አለመሰጠቱና ጋዜጠኞች ሁለት ጊዜ ተጠርተው እንዲሁ መበተናቸው ታውቋል፡፡ G8 የተባለው የእነአባ ሳሙኤል ቡድን አባላት መግለጫውን አባ ህዝቅኤል እንዲሰጡ ቢጠይቁም መግለጫውን ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸው ታውቋል፡፡ የሲኖዶሱ ስብሰባ ሁሉም ለእርቅ ተወክለው የሄዱት አባቶችና ሌሎችም አባቶች ባልተገኙበት የተደረገ በመሆኑና በእርቁ ሂደት ላይ አሉታዊ ጫና ያሳድራል በተባለው ውሳኔ ላይ አለመግባባት በመፈጠሩ ሳቢያ ይፋዊ መግለጫው አለመሰጠቱን ምንጮች እየተናገሩ ነው፡፡ የተሰየመው አስመራጭ ኮሚቴ እስከ ጥር 30/2005 ዓ.ም ድረስ እጩዎችን እንዲያቀርብ የተወሰነ ቢሆንም ከአስመራጭ ኮሚቴው መካከል ብፁእ አቡነ ቄርሎስ አልፈርምም በማለታቸው፣ ብፁእ አቡነ አትናቴዎስና ብፁእ አቡነ ፋኑኤልም እርቁ መስመር ሳይዝ በአገር ቤቱ ሲኖዶስ በሚወሰዱ እርምጃዎች ላይ የተቃውም ድምጻቸውን በማሰማታቸው እርቁን ከቁብ ሳይቆጥሩ ምርጫው ላይ ሲጣደፉ የነበሩ ራስ ወዳዶች መግለጫውን ለመስጠት ድፍረት እንዳጡ ተገምቷል፡፡ የብፁእ አቡነ አትናቴዎስን የተቃውሞ ድምፅ ተከትሎ አቡነ ቄርሎስ አልፈርምም ማለታቸውና አባ ህዝቅኤል መግለጫውን እንዲሰጡ ቢጠየቁም ከመስጠት ማፈግፈጋቸው፣ በአንዳንዶች ዘንድ በእነአቡነ ፊልጶስ ቡድን በኩል አንድ ነገር እየተደረገ ይሆናል የሚል ግምት አሳድሯል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ እስከ ህጉ መሻሻል ድረስ ጉዳዩን ሲገፋና አስተያየት ጽፎ ለጳጳሳቱ እስከ መበተን የደረሰው ማቅ፣ በእርቁ ዙሪያ ዝም አለ ላለመባልና ከአንገት በላይ ሲንቀሳቀስ እንዳልነበር የህጉ መንፈስ እርሱ እንደሚፈልገው ባለመሆኑና የሰጣቸውን አስተያየቶች በተለይም በእጣ ይሁን የሚለውን ጉባኤው ውድቅ በማድረጉ ስለተበሳጨ በየድረገጾቹ ሙስሊሞችን ምሳሌ በመጥቀስ ጭምር ተነሱ የሚል ጦርነት መሰል ቅስቀሳ በማድረጉ ምክንያት የመንግስት አካላት የማቅን 3 አመራሮች ጠርተው ማናገራቸውና ማስጠንቀቃቸው ተሰምቷል፡፡ ከቀናት በፊት የሃይማኖትን ጉዳይ የሚመለከተው የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር  ዋና ጸሀፊውን ሙሉጌታ ሃ/ማርያምን ጨምሮ ሌሎች ሶስት የማቅ አመራሮችን ያነጋገረ መሆኑን ምንጮቻችን ገልጸው በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ እየተፈጠረ ባለው ችግር የእነርሱ እጅ ያለበት መሆኑን በመግለጽ ከአድራጎታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቅቋቸዋል ተብሏል፡፡

በተያያዘም ከሳምንት በፊት በጅማ ዩኒቨርሲቲ የማቅ ተከታይ የሆኑ ተማሪዎች በጾም ቁርስ ስለማንበላ የቁርስ ገንዘብ ይሰጠን የሚል ጥያቄ በማንሳታቸው ምክንያት በተፈጠረ ውዝግብ ምክንያት ትምህርት የተስተጓጎለ ሲሆን፣ ማህበረ ቅዱሳኑ ባያብል ሄዶ ተማሪዎቹን እንዳረጋጋቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ተማሪዎቹ የቁርሳቸውን ሂሳብ ይሰጠን ያሉት ከዚህ ቀደም እንደዘገብነው ማቅ ከዩኒቨርሲቲዎች በጾም ወቅት ለሚሰበስበው ገቢ የሚውል ነው ተብሏል፡፡ 4 comments:

 1. Isn't that the bible tell us to do by Eita
  "ማቅ በእጣ ይሁን የሚለውን ጉባኤው ውድቅ በማድረጉ ስለተበሳጨ"
  Dear Aba Selama you r trying to tell us MK r doing wrong.Fortunately you r showing us they do things based on our bible.Thank you so much.Be enante bete MKn meksesachehu newe gene ewnetegnetachewen asayachehun.Thank you again

  ReplyDelete
 2. Ene eko yemigermegn, beka hulem hulunim zena keMahibere Kidusan gar kalagenagnachihut titamemalachihu ende? weyy gudd, beka endeminim bilachihu Makk bilachihu kaltesadebachihu libachihu ayiregam ayidel? Kentu.

  ReplyDelete
 3. Mk eko new abatochen yemibetebetew erk endayemeta yemifelegew EGZIABHER degimo selemeyawek yakeshfebachewal bedejeselam ena and adregen blogu torenet seyawej alenber ende mk ejehen anesa ke abatoch layee

  ReplyDelete