Friday, January 11, 2013

እውነቱ የቱ ነው?

(ምንጭ፦ ደጀ ብርሃን ብሎግ) ለውይይት የሚጋብዙ ብዙ ግሩም ሃሳቦችን የያዘች ጽሑፍ ስለሆነች እዚህም አቅርበናታል 
መነሻ ሃሳብ «ገመና 81» መጽሐፍ
   ሀተታ፤
በኦርቶዶክሳውያን  ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከታች ጀምሮ እስከላይኛው እርከን ድረስ ያለው ሰው ስህተት ይኖርብናል ወይም ልንሳሳት እንችላለን ብሎ የሚያስብ ማግኘት አዳጋች ነው። በክርስቶስ ደም የተመሰረተችው ቤተክርስቲያን ፍጽምትና ንጽሕት መሆኗን በመቀበል እንዳለ መሪውና ተመሪው ራሱንም በዚያው ዓይን እያየ እኛ ፍጹማንና ንጹሐን ነን በሚል ከለላ ስር ራሱን በማስጠለል፤ ስህተትን አምኖ ለመቀበል አይፈልግም። የስህተት አስተምህሮ አለ፤ በእግዚአብሔር ቃል ሲመረመር አደጋው የከፋ ነው፤ የክፉ መንፈስ አሰራር ወደማወቅ እንዳንደርስ ቃሉን በክሏል ሲባል የሚሰጠው ምላሽ፤ 2000 ሺህ ዘመን የኖረችን ቤተክርስቲያን ዛሬ የተነሱ አፍቃሬ ተሐድሶ መናፍቃን ሊያርሟትና ሊበርዟት ይፈልጋሉ በማለት ታፔላ መለጠፍ ይቀናቸዋል። የስም ታፔላ መለጠፍ ብቻ ሳይሆን ሽልማት የሚያሰጥ ቢሆን ኖሮ የተመረጡና ለመስማት የሚዘገንኑ ስድቦችና ዛቻዎች ይዥጎደጎዳሉ።
በእርግጥ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ፍጽምትና ንጽሕት መሆኗ አያጠራጥርም። ምክንያቱም የመሠረታት በዓለቱ ላይ በፈሰሰው ደሙ ነውና። ይህ እውነት ቢሆንም በክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ አባል ሆነው የሚኖሩት የአዳም ልጆች መሆናቸውንም በመዘንጋት የቤተክርስቲያኗን መንፈስና ባህርይ እንዳለ ወደሰዋዊ ማንነት በመውሰድ እኛ ፍጹማንና ንጹሐን ነን በማለት ከስህተት አልባነት የቤተክርስቲያን ማንነት ጋር ራስን መቁጠር ትኩረት የሚያሻው መሆኑን ልናሰምርበት ይገባል። በእርግጥም የተጠራነው ፍጽምት በሆነች ቤተክርስቲያን ውስጥ ፍጹማን እንድንሆን ነው። ነገር ግን ሰው ከተፈጠረበት ማንነት የተነሳ በፍጽምቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ ፍጹም ሆኖ መኖር የሚችል ማንነት የለውም።
ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ሊሆኑን የሚችሉት የገላትያ ሰዎች ማንነት ነው። የገላትያ ሰዎች በክርስቶስ አዳኝነት አምነው ወደ ሕይወት መንገድ የተመለሱ ሕዝቦች ነበሩ። ፍጽምትና ንጽሕት በሆነች የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ተጨምረው የቆዩ ሆነው ሳለ ሰብአዊ ማንነታቸው አሸንፎአቸው ወደስህተት መንገድ በመግባታቸው በሐዋርያው ጳውሎስ እጅግ የተወቀሱ ሕዝቦች ሆነዋል።
«የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነውገላ 31
ክርስቶስ ኢየሱስ በፊታቸው የተሰቀለ ሆኖ በእምነት ይታያቸው የነበሩት ሕዝቦች ከዚያ የቅድስና ማንነት ወርደውና እውነትን በመተው፤ የጠላት አዚም የወረደባቸው  ሕዝቦች እስከመሆን መድረሳቸውን ሲናገር እናያለን። ሥራቸውን ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የጀመሩ ሆነው ሳለ ቁልቁል ተመልሰው የሥጋን ሃሳብና እውቀት ወደማመን መመለሳቸው በእርግጥም አሳዛኝ የሰው ልጆች ማንነት ማሳያዎች እንደሆኑ የሚያስገነዝበን  ነገር ነው።
«እንዲህን የማታስተውሉ ናችሁ? በመንፈስ ጀምራችሁ አሁን በሥጋ ትፈጽማላችሁንገላ 33 ይላል።
እንግዲህ ክርስቲያኖች ፍጽምትና ንጽሕት በሆነች ቤተክርስቲያን ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እምነታቸውን ሊጀምሩ ይችላሉ። ይሁን እንጂ ይህንን ፍጽምና ወደአለማወቅ መመለስም ሊታይባቸው ይችላል። ምን ጊዜም ቢሆን የስህተት መንፈስ አገልግሎቱ፤ የእውነቱን መንፈስ ከሰው ልቡና ላይ በመውሰድ ወደስህተት መንገድ መምራት ስለሆነ በቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ ባሉ ሰዎች ውስጥ የስህተት አስተምህሮ እንደሚገባ እናረጋግጣለን።
ብዙዎች የአብያተ ክርስቲያናት አባላት በክርስቶስ ፍቅር ላይ ጸንተው ከመቆም ይልቅ ወደ ምድራውያንና ሰማያውያን ፍጥረቶች ፍቅራቸውን ስለለወጡ የሕይወት መንገድን ስተው መገኘታቸው እውነት ነው።
ጳውሎስ ጢሞቴዎስ ልጁን ወደ ተሰሎንቄ የላከበት ዋናው ምክንያትም ተሰሎንቄዎች  ከእምነት ጽናታቸው ወደኋላ እንዳይመለሱ በመንፈስ ያበረታታቸው ዘንድ ነበር። ምክንያቱም ፈታኝ የምንጊዜም አዚሙን የሚያፈሰው  የአማኞችን ልቡና በማደንዘዝ ወደ አልሆነ አቅጣጫ መመለስ  ሥራው ስለሆነ ከዚህ ፈታኝ ይጠበቁ ዘንድ እንደላከላቸው ቅዱሱ ወንጌል ይነግረናል።
«ስለዚህ እኔ ደግሞ ወደ ፊት እታገሥ ዘንድ ባልተቻለኝ ጊዜ። ፈታኝ ምናልባት ፈትኖአቸዋል ድካማችንም ከንቱ ሆኖአል ብዬ እምነታችሁን ለማወቅ ላክሁ» 1 ተሰ 35
ከከሳቴ ብርሃን አባ ሰላማ ወዲህ ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል ተብለው የሚጠሩ መነኮሳት በዋሻና በፍርክታ ገዳም መስርተው ሰው ሁሉ ወደዚያው እንዲከትም ከማድረግ ውጪ ሀገር ላገር ዞረው፤ እንደሐዋርያቱ ወንጌል ላልበራለት ሕዝብ ወንጌልን ስለማስተማራቸው የሚታወቅ ነገር የለም። ወንጌል ለሕዝቡ የበራ ቢሆንማ ኖሮ እስከዛሬ በዛፍ ስር ቡና የሚደፉ፤ ደም የሚያፈሱ፤ቅቤ የሚቀቡ፤በጨሌ፤ ቆሌና የቤት ጣጣ አምልኮ ሰርጾባቸው የሚኖሩ ባልኖሩ ነበር።  እምነት አለን፤ አውቀናል የሚሉት እንኳን እስከፕሮቴስታንት መምጣት ድረስ መጽሐፍ ቅዱስን አያውቁትም። ደረትን ነፍቶ ኦርቶዶክሳዊ ስለመሆን አረጋጋጭ ከሆኑት ከድርሳናት ውጪ መጽሐፍ ቅዱስን ይዞ መገኘት በራሱ ኮትልኳል ወይም ጰንጥጧል የሚያሰኝ በመሆኑ ይዞ መገኘት ያሳፍር ነበር። ይህ በእድሜአችን ያየነው እውነት ነው። አንዳንዶች «ሳያዩ የሚያምኑ ብጹአን ናቸው» የሚለውን ቃል ጠምዝዘው ራሳቸው ለመሸንገያነት በመጠቀም አንድም ሐዋርያ ሳይመጣ ያመንን ስለሆንን ቃሉ እኛን ኢትዮጵያውያንን ያመለከታል ለማለት ቢፈልጉም የሐዋርያ ወይም የሰባኪ አለመምጣት እንደ ጉዳት እንጂ እንደጠቃሚ ነገር መቁጠር አለማወቃችንን የሚያሳይ ነው። መጽሐፍ የሚለን እውነት ይህንን ነው።
«እንግዲህ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል? ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ? ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉሮሜ 1014
እንደዚሁ ሁሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እውነተኛ ወንጌል በማስተማርና ሕዝቡን ከክርስቶስ ወንጌል ጋር በማስማማት እንዲኖር ለማድረግ እስከሞት ድረስ ከታገለው ከአባ እስጢፋኖስ በቀር ግብጻውያንም ጳጳሳት የሰሩት የወንጌል አገልግሎት አልነበረም። ወንጌል ሥራው በግጻዌ ምድቡ በጥቅስ ደረጃ በየሥርዓተ ቅዳሴው ላይ ተመርጦ ከሚነበብ ውጪ ከተአምረ ማርያምና ከድርሳናት እኩል መድረክ አልነበረውም። አቡነ ቴዎፍሎስ የወንጌልን አስፈላጊነት በማመን አዳሪ /ቤቶችን በማጠናከር፤ ሰንበት /ቤቶች በማቋቋምና በቃለ ዓዋዲ እንዲደነገግ እስኪያደርጉ ድረስ አብያተ ክርስቲያናት በግእዝ ቀድሰው፤ በግእዝ አንብበው፤ ለዓለመ ዓለም ካሉ በኋላ እግዚኦ መኀረነ ክርስቶስ እንበል 12 ጊዜ ብለው ጣት ከማስቆጠር ባለፈ ህዝቡ ወንጌልን እንደማያውቅ ጠንቅቀን እናውቃለን።
 እንዲያውም ወንጌል እቃ ግምጃ ቤት ገብቶ የሸረሪት፤ የአቧራና የአይጥ ቀለብ ሲሆን በአንጻሩ ልፋፈ ጽድቅ በየአንገት ላይ የሚንጠለጠል ክቡር መጽሐፍ ሆኖ ለዘመናት ኖሯል። ዛሬም እስከመቃብር ድረስ አብሮ የሚወርድ፤ ክቡር አዳኝ መጽሐፍ ሆኖ መቆጠሩን አላቋረጠም። የዲቁናም ይሁን የቅስና ማእርግ የሚሰጠው ሥርዓተ ቅዳሴውንና ኩሳኩሱን ከመልክዓ መልክዑ ጋር መሸምደዱ እንጂ ወንጌልን ተንትኖ ሕይወት የሚገኝበትን ቃል ማስተማር ስለሚችል አይደለም። 
ከዚህ በታች የምናቀርባቸው መጽሐፍ ቅዱሳችን በምንለው መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙ ስህተቶች፤ ነገር ግን እውነት እንደሆኑ ቆጥረን የምንከራከርላቸው ሲሆኑ ችግሩን እንደችግር ያለመቁጠራችን ዋና ምክንያት ከላይ በሀተታ እንደዘረዘርነው አንድም እኛ ፍጽምትና ንጽሕት በሆነች ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለን ስህተት አልባዎች ነን ከማለት የመነጨ ሰውኛ ማንነትን ካለመቀበል ችግር፤ አንድም- ክርስቶስ ከፊታቸው ተስሎ የነበሩት ገላትያውያን እንደሆኑት የሆነ አዚም አደንዝዞን እውነትን ለመቀበል ባለመፈለግ፤ አለያም ሳያዩ የሚያምኑ……በሚለው የሽንገላ ቃላት ተሸውደን እውነተኛውን የክርስቶስ ወንጌል የሚሰብክ እንዲኖረን ባለመፈለግ ራሳችንን ስናሞኝ በመኖራችን ይሆናል።
 የስህተት ትምህርት አስረጂዎች፤
ብዙውን ጊዜ «ከእውነተኛ የወንጌል አስተማሪዎች እጦት የተነሳ» /ከአስተማሪዎች እጦት የተነሳ አላልኩም/ ሕዝቡ እስካሁን ለወንጌል ቃል አዲስ በመሆኑ አሳማኝ መልስ መስጠት ስለማይችል እንደችግር መፍቻ መፍትሄ የሚጠቀምበት መንገድ በመሳደብ፤በማሳደድ፤በማሽሟጧጥ፤ በመደባደብ ብሎም በመግደል  ልዩ ለሆነ ሃሳብ ሁሉ ምላሽ ሲሰጥ ቆይቷል። አሁንም ይህ አድራጎት አላቋረጠም። ከዚህ በታች ለሚቀርቡ አስረጂዎች ምላሽ መስጠት የሚችል አንድም ሰው እንደሌለ እርግጠኞች ስንሆን የሚሳደብ ወይም የሚያንቋሽሽ ክርስቲያኖችን ግን በሺህዎች እንጠብቃለን።
 
   1/ ስለታቦተ ጽዮን ትረካ፤
1,1  ስለታቦተ ጽዮን አመጣጥ ታሪክ የሚናገረውን  «ክብረ ነገሥት» የተባለውን መጽሐፍ ማኅበረ ቅዱሳን ውሸታም ብሎታል።

ማኅበረ ቅዱሳን ትውፊትንና ባህልን፤ ልምድንና አምልኰትን ለይቶ የማያውቅ የጅምላ እምነት አራማጅ መሆኑ ሲታወቅ፤ ራሱ እገዛበታለሁ የሚለውን ትውፊት ሲሽር እንጂ ሌሎች ሲሽሩ ዓይኑ ደም የሚለብስ አስቸጋሪ ድርጅት ነው። እንደሚታወቀው ግራሃም ሐንኰክ የተባለ እንግሊዛዊ ምሁር /The sign of the seal/ በሚል ርእስ // 1992 / ያሳተመውን መጽሐፍ ይህ የትውፊት ጠበቃ ነኝ የሚለው የጅምላ እምነት አራማጅ ማኅበር፤ /ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ/ በሚል ርእስ በጌታቸው ተስፋዬ አስተርጉሞ ያሳተመው መጽሐፍ  እንደሚተርከው ታቦተ ጽዮን በንጉሥ ሰሎሞን ዘመን በልጁ ኢትዮጵያዊ ንጉሥ በቀዳማዊ ምኒልክ እጅ ሳይሆን ወደኢትዮጵያ የመጣው በግብጽ ኤሌፋንታይን አቋርጦ ከዓመታት ቆይታ በኋላ የዓባይን ሸለቆ ተከትሎ ቀስ በቀስ በጣና አድርጎ ነው የገባው በማለት ይናገራል። ስለዚህ «ክብረ ነገሥት» ስለታቦተ ጽዮን አመጣጥ የሚተርከው የእነ ቀዳማዊ ምኒልክ ታሪክ በውሸታምነቱ ተመዝግቧል ማለት ነው። ማኅበረ ቅዱሳን የታቦተ ጽዮንን አመጣጥ በግራሃም ሃንኰክ አተራረክ መሰረት የሚያምን ከሆነ ክብረ ነገሥትን ትረካ ዋጋ ቢስ ያደርገዋል። የሚገርመው አንድም የሊቃውንት ጉባዔ ይሁን የጳጳሳቱ ዓለም የክብረ ነገሥትን ትረካ የሚቃወመውን የማኅበረ ቅዱሳን እትም መጽሐፍ ሲያወግዝ ወይም ታሪካችንን አፋልሷል ሲል አልተሰማም። ስለዚህ የክብረ ነገሥትን ውሸታምነት አጽድቆታል ወይም የማኅበረ ቅዱሳንን የትርጉም አተራረክ ለመከላከል አቅም አጥቷል። ከዚህ አንጻር ስለታቦተ ጽዮን አመጣጥ የሚናገር የተለያየ ሃሳብ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ስላለ እውነተኛው የትኛው እንደሆነ ለጊዜው አይታወቅም ማለት ነው።
  1,2/ ታቦተ ጽዮን ወደኢትዮጵያ አልመጣችም በማለት መጽሐፈ እዝራ ካልዕ ይናገራል።

ከላይ እንዳስቀመጥነው ማኅበረ ቅዱሳን ክብረ ነገሥትን ውሸታም በማለት በግብጽ በረሃ አድርጋ ነው ታቦተ ጽዮን የመጣችው የሚለውን የግራሃም ሃንኰክን መጽሐፍ ለተከታዮቹ ሲያከፋፍል የምንረዳው ሁለት የተለያየ የአመጣጥ ትረካ መኖሩን ነበር። ይሁን እንጂ ሰማንያ አሀዱ በተባለው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በመጽሐፈ እዝራ ካልዕ ምዕራፍ 1 ቁጥር 54 ላይ እንዲህ በማለት ከላይ የቀረቡትን ሃሳቦች ሁሉ ውድቅ በማድረግ ታቦተ ጽዮን ወደኢትዮጵያ እንደመጣች ሳይሆን ወደባቢሎን መሄዷን በግልጽ ይናገራል።
«እግዚአብሔርን የሚያገለግሉበትን ንዋየ ቅድሳቱንና ጥቃቅኑንና ታላላቁን ዕቃ ሁሉ የእግዚአብሔር ማደሪያ ታቦትንም፤ ከቤተመንግሥት ዕቃ ቤት ያለውን ሣጥኑንም ሁሉ ማርከው ወደ ባቢሎን ወሰዱ» እዝራ ካልዕ 154
ናቡከደነጾር 634-562 / የነበረ የባቢሎን ንጉሥ ሲሆን እርስ በእርሳቸው ያልተስማሙት የክብረ ነገሥትና የታቦተ ጽዮንን ፍለጋ መጻሕፍት ትረካ ውድቅ በማድረግ ወደ ባቢሎን ማርኰ ስለመውሰዱ ሰማንያ ወአሀዱ የተባለው መጽሐፍ ቅዱስ አፖክሪፋ መናገሩ ነገሩን ሁሉ መያዣ መጨበጪያ የሌለው አድርጎታል። አሁን እንግዲህ ሊነሳ የተገባው ጥያቄ፤

·         ክብረ ነገሥት የተባለው መጽሐፍ ነው ትክክል?
·         ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ የተባለው መጽሐፍ ትረካ ነው ትክክል? ወይስ
·        የለም! ሁለቱም የሚሉት ትክክል አይደለም፤ ታቦቱ ወደባቢሎን በምርኰ ተወስዷል የሚለው የመጽሐፈ እዝራ ካልዕ ቃል ነው ትክክል?
 1,3/ መጽሐፈ ነገሥትም እስከ ባቢሎን ምርኰ ድረስ ታቦቲቱ ኢየሩሳሌም እንደነበረች ይናገራል።
 ሌላው ስለ ታቦተ ጽዮን በንጉሥ ሰሎሞን  ዘመን ወደኢትዮጵያ መጣች የሚለውን አባባል ውድቅ የሚያደርገው አስረጂ 300 ዓመት ቆይታ በኋላም በኢዮስያስ ዘመን/ 649-609 // ኢየሩሳሌም  እንደነበረች መጽሐፍ ቅዱስ መናገሩ ነው። የሕጉ መጽሐፍ መነበቡን/ 2 ነገ 228/ ንጉሡ የሕጉን መጽሐፍ ሲሰማ ልብሱን መቅደዱን /2 ነገ 2211/ የእግዚአብሔር ቤት ይጠገን ዘንድ ማዘዙን /2 ዜና 3410/ ከዚያም የእግዚአብሔርን ታቦት በመቅደሱ እንዲያኖሩት ማድረጉን መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
«እስራኤልንም ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩት፥ ለእግዚአብሔርም ለተቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አለ፦ ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ አኑሩት ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ ሸክም አይሆንባችሁም አሁንም አምላካችሁን እግዚአብሔርንና ሕዝቡን እስራኤልን አገልግሉ» 2 ዜና 353
እንደእኛ እምነት የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ስለማይሳሳት መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃወሙ መጻሕፍት ሁሉ ስሁታን ናቸው።
    2/ ዲያብሎስ  የወደቀው በትዕቢቱ  አምላክ  ለመሆን ስለፈለገ ነው ወይስ  ለአዳም ስገድ ተብሎ  እምቢ በማለቱ ነው?
 እንደቤተክርስቲያን አስተምህሮ ሰይጣን እስከነሠራዊቱ የወደቀው በመታበዩ ምክንያት እንደሆ ነው። ትንቢተ ኢሳይያስ 1412
«አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ፥ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቈረጥህይለዋል።
ራሱን የሁሉ ገዢ ለማድረግ ልቡናው ስለተነሳሳ በስሁት መንፈሱ ለውድቀት ተዳርጓል የምትል ቤተክርስቲያን፤ «የለም! ሰይጣን የወደቀው ለአዳም አልሰግድም ስላለ ነው» የሚል አስተምህሮ ይዛ መገኘቷ ነገሩን ሁሉ አስገራሚ ያደርገዋል።
2,1 መጽሐፈ መቃብያን ለአዳም ስላልሰገደ ዲያብሎስ ወደቀ ይለናል።
 እንደዚህ የሚል ትምህርት በቤተክርስቲያናችን የለም የሚል ሰው ቢኖር ቁጥሩ ከአፖክሪፋ የሆነውንና እንደመጽሐፍ ቅዱስ አንድ ክፍል እንዲቆጠር በግድ የተበየነበትን መጽሐፈ መቃብያንን አያነብም ወይም ስለተሸከመው ብቻ የገባው ይመስለዋል ከማለት ውጪ ምን ልንል እንችላለን።
«የሚጠፉ በኔም የሚስቱ ሰዎች ፈጽመው ይበዙ ዘንድ፤ የአዳምም ልጆች ይጠፉ ዘንድ፤ ይህንን በተናገሩ ጊዜ እኔ ደስ ይለኛል፤ ለሚዋረድልኝ ለአዳም አልሰግድም በማለቴ እግዚአብሔር ስለአባታቸው ስለአዳም ከማዕረጌ አዋርዶኛልና፣ 3 መቃ 115
«ክሳደ ልቡናውን በማጽናትና ራሱን በማኩራት ፈጣሪው ለፈጠረው ለአዳም መስገድን እንቢ እንዳለ» 2 መቃ 91-3
ዲያብሎስ የወደቀው ለአዳም አልሰግድም ብሎ እምቢ በማለቱ ነው የሚል ይህ እንግዳ ትምህርት ከእውነተኛው የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ጋር በፍጹም ተቃራኒ ነው። በባለፈው ጽሁፋችን ከግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጋር በመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት ቁጥርና ዓይነት የምንለያይበትን መንገድ ለመጠቆም መሞከራችን አይዘነጋም። ግብጾች ወርቁንና ብሩን ከጫንላቸው የቱንም የስህተት መንገድ ብንከተል ጉዳያቸው እንዳልነበር የሚያሳይ ነገር ነው። እነሱ ይህንን የመቃብያን መጽሐፍ ከቅዱስ መጽሐፍ አካል ያልቆጠሩት ይህንን የመሰለ ስህተት እንዳለበት ስለሚያውቁ ይሆናል።
ዲያብሎስ የወደቀው ለአዳም አልሰግድም በማለቱ ነው የሚለው የመቃብያን መጽሐፍ የሚመሳሰለው ከቁርዓን ጋር ነው። ቁርዓን እንዲህ ይላል።
 
2,2 ቁርዓንም  እንደመቃብያን ይናገራል።
ሱረቱል አልበቀራህ ወይም የላም ምዕራፍ 2 34
وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ أَبَى وَاسْتَكْبَرَ وَكَانَ مِنَ الْكَافِرِينَ ንባቡም ይህንን ይመስላል።
Waith qulna lilmalaikati osjudoo liadama fasajadoo illa ibleesa aba waistakbara wakana mina alkafireena
ወደአማርኛ ሲመለስ፤
«ለመላእክትም ለአዳም ስገዱ ባልን ጊዜ (አስታውስ) ሁሉም ወዲያው ሰገዱ። ኢብሊስ (ዲያብሎስ) ብቻ ሲቀር እምቢ አለ፤ኮራም ከከሀዲዎቹ ሆነ» ማለቱ ነው።
እንግዲህ ቁርዓንና መጽሐፈ መቃብያን ዲያብሎስ እንዴት እንደወደቀ አንድ ዓይነት ቃል ይዘዋል። እሱም  ለአዳም ስገድ በተባለ ጊዜ እምቢ በማለቱ  ነው ይሉናል።  ሊቃውንቱ ስለመቃብያን መጽሐፍ  ከቁርዓን ጋር መመሳሰል ምን ይላሉ? ግብጻውያን እነሱ  ያልተቀበሉትንና  ያልፈለጉትን  መጽሐፍ  ጭነውብን  ነው ወይስ  ለእኛ ለኢትዮጵያኖች ለብቻችን መቃብያን መጽሐፍ ከሰማይ የወረደልን ሆኖ ይሆን?
ዲያብሎስ  ለአዳም  እንዲሰግድ  የታዘዘውስ  መቼ ነው? ይህስ  ከየት የተገኘስ  አስተምህሮ  ነው?
    3/ ለሰዎች በጥቁርና ቀይ ቀለም መጻፍ ያስተማረው አጋንንት ነው?
ለዚህ ጥያቄ  መቼም አዎን! የሚል ምላሽ ቢሰጥበት ሰዎች መቃወማቸው እርግጥ ነው። ምክንያቱም  ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ በጥቁር ወይም  በጥቁርና  ቀይ መጻሕፍት  እያዛነቁ  መጻፍ የተለመደ ስለሆነ የጥቁርና  ቀይ ቀለማትን ምንጭ  ከአጋንንት ጋር ማያያዝ ትክክል ነው  ማንም  ሊል እንደማይችል ይታሰባል። ይሁን እንጂ የግብጽ ኦርቶዶስክ ቤተክርስቲያን ከቅዱሳት መጻሕፍት ዝርዝር ውስጥ የማትቆጥረው መጽሐፈ  ሄኖክ  የተባለው  አፖክሪፋ / */በቀይና በጥቁር ቀለም መጻፍ ለሰው ልጆች ያስተማረው አጋንንት ነው ይለናል። መጽሐፈ ሄኖክ 1922-24 ይመልከቱ። እንግዲህ ለመልካም ይሁን ለጥፋት በዚህ ዘመን የሰው ልጅ የሚጠቀምበት የመጻፊያ ጥቁርና ቀይ ቀለም ተጠቃሚዎች ሁሉ የአጋንንት ተማሪዎች ናቸው ማለት ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ተስፋ /ሥላሴ ዘብሔረ ቡልጋና ትንሣዔ ዘጉባዔ ማተሚያ  ቤቶች ይበልጥ ተጠያቂ ናቸው ማለት ነው።
ይሁን እንጂ የጽሕፈት፤ የፊደላትና የእውቀት ባለቤት የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንጂ  አጋንንቶች ሊሆኑ በፍጹም አይችሉም። ሰዎች የተሰጣቸውን እውቀት ላልተፈለገ  ዓላማ ሊገለገሉበት  ይችላሉ እንጂ አጋንንት የአዳምን ልጆች የጽሕፈት እውቀት አስተማሩ ማለት ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለውና ሰውን የአጋንንቶች ወዳጅ አድርጎ የሚያቀርብ  የክህደት አስተምህሮ ነው። ቋንቋን ለሰጠ እግዚአብሔር፤ የቋንቋ መጻፊያ ቀለማትን ሰይጣን በመፍጠር በምንም መልኩ አጋዥ ሊሆን አይችልም።  ቤልሆር ከክርስቶስ ጋር ምንም ኅብረት የለውምና።
መጽሐፍ ቅዱስ ግን እግዚአብሔር  ለነቢያቱ ይህን  ጻፉ፤ እንዲህም ጻፉበት እያለ የጽሕፈት ባለቤትነቱን  ይመሰክርለታል።
     «ሙሴም  የእግዚአብሔርን ቃሎች ጻፈ ማለዳም ተነሣ» ዘጸ 244
    «ሙሴም በዚያ ቀን ይህችን መዝሙር ጻፈ፥ ለእስራኤልም  ልጆች አስተማራት» ዘዳ 3122
    «አንድ  የመጽሐፍ  ክርታስ ውሰድ፥ ለአንተም  ከተናገርሁበት  ቀን ከኢዮስያስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ  በእስራኤልና በይሁዳ ላይ በአሕዛብም  ሁሉ ላይ የተናገርሁህን ቃል ሁሉ ጻፍበት» ኤር 362
    «ዳግመኛም  ሌላ  ክርታስ ውሰድ፥ የይሁዳም  ንጉሥ ኢዮአቄም  ባቃጠለው  ክርታስ  ላይ የነበረውን  የቀድሞውን ቃል ሁሉ ጻፍበት» ኤር 3628

እጅግ ብዙ አስረጂዎችን  ማቅረብ ይቻላል።  እውነትን  ለመግለጥ በቂ ነውና በሄኖክ ስም ራሱን በእግዚአብሔር ቦታ አስቀምጦ እኔ ለሰው ልጆች እውቀትን የሰጠሁ ነኝ የሚለው ክፉ መንፈስ ግን በእግዚአብሔር ቃል የተሳሳተ አስተምህሮ ነው። አጋንንት ጽሕፈትን እንዴትና መቼ  እንዳስተማሩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ  የሚያቀቡ አስረጂ ወዳጆች ካሉት  ለመስማት ዝግጁ ነን። ይሁን እንጂ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  እጅግ  የምታደንቀው  የሃይማኖት አባት አትናቴዎስ የማያውቀውንና የኮፕት ቤተክርስቲያንም  እንደቅዱሳት መጻሕፍት የማትቀበለውን መጽሐፈ ሄኖክ   የመምህርነቱን ስፍራ  ለአጋንንት ሰጥቶት ይገኛል። የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንስ ያልተቀበለችው ለምን ይሆን?
 3/ ዲያቆናት ጥርስ  ማፋጨትና እሳቱ ወደማይጠፋ ቅጣት ይወርዳሉ የሚል ትምህርት ዉሸት ነው።

 በማቴዎስ ወንጌል ላይ የተሰጣቸውን መክሊት አራብተው ለባለቤቱ ዋናውን የመለሱ ሠራተኖችን ማንነት የሚገልጽ ቃል አለ።
(የማቴዎስ ወንጌል 2514-30 ያለውን ይመለከቷል)
በቁጥር 15 ላይ «ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ፥ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ» ይላል። እነዚህ ሰዎች በተሰጣቸው መክሊት አትርፈው ዋናውን ለባለዋናው መመለስ በሚገባቸው ወቅት የተገኘባቸው ትጋት እንዲህ ተቀምጧል።
« አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክቦ። ጌታ ሆይ፥ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት አለ። ጌታውም። መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው። ሁለት መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት አለ። ጌታውም። መልካም፥ አንተ በጎ፥ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፥ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው። አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ፈራሁም ሄጄም  መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ አለ»
በዚህ ውስጥ ያተረፉት ሲሾሙና ሲሸለሙ፤ ያላተረፈውን ባለአንድ መክሊት ባሪያ  ግን ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት እሳት መጣሉን ቃሉ ይናገራል። ይህንን ቃል አንድምታ በተባለው ትርጉም  ውስጥ እንዲህ የሚል ቃል ተቀምጧል።
ባለአምስት መክሊቱ  ሊቀጳጳስ ነው፤ ባለሁለቱ መክሊት በቄስ  ይመሰላል፤ ባለአንድ መክሊቱ ደግሞ በዲያቆን ይመሰላል በማለት እጣ ፋንታውን በቤተክህነቱ የስልጣን  እርከን መሠረት ይደለድላል። በዚህ ድልደላ መሠረት ዲያቆናት « ወለገብርሰ ዘእኩይ» ተብለው እድል ፈንታቸውም  የዘላለም እሳት እንደሆነ የተቀመጡበት የሥልጣን እርከን ድልድል በፍጹም ትክክል አይደለም። (ወንጌል ቅዱስ ንባቡና ትርጓሜው 1916 /)
 በዚህ ዘመን ያለውን ግብር  ተመልከተን ብንመዝን በያዙት ሥልጣንና ኃላፊነት ደረጃ ተጠያቂ በመሆን የሚወዳደራቸው የማይኖረው ለራሳቸው የባለአንድ  መክሊቱን ሥፍራ  ቆርሰው የያዙት በሆኑ ነበር። ለተልእኰ  በመፋጠንና ከሙጋድ ጭስ  ጋር ሲታገል የሚኖረውን ዲያቆን ገብር ሀካይን ደረጃ ሰጥተውታል።  ለምን?
ስናጠቃልል እስካሁን ለዘረዘርናቸው መጠይቅ  መላሾች እውነቱ የቱ ነው? በማለት እንጠይቃለን።  ስህተት ካለብን ያለ እውቀት  ስለሃይማኖት በማክረር  ከማሽሟጠጥ ይልቅ ምራቅ ዋጥ እንዳደረገ ሰው እውነቱን ይገልጥ ዘንድ ይፈለጋል። መሆን ካልቻለ እውነቱን ለመቀበል ባንፈልገውም  እውነት ምን ጊዜም  እውነት  እንደሆነ ሲኖር ውሸትም ለእውነት ጊዜውን ጠብቆ ሥፍራውን መልቀቁ አይቀርም።
«ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልምና» 2 ቆሮ 138

41 comments:

 1. Wanaw neger eko, yemigermegn, enante kedimo neger beMetshafe Mekabiyan ena beMetsehafe Ezra ataminum eko. Lemin titeksutalachihu. Tiliku wishet demo, Orthodox tewahedo mechem bihon Seyitan yewedekew leAdam silalsegede new bila atastemirim, adirgam atawikim. Yihe Ewnet mesayy yeMenafik wishet new. Asmesay atihunu.
  Mejemeriya neger Adam rasu yetefeterew keSeytan widket behuala new. Seytan wediko sitall, beElete arbb demo bewedekew neged mitik Adam tefetere. Endegena Metto neged hone.

  Atwashu, enante hulem menafikinetin endemitisebiku kalachihu yaweral, tsihufachihum yimesekiral. Minale esi Emebetachinin, MelaEktinina Kidusanin le'egna bititewulun. Egna eko techegerin alalnachihu, Nulin alalnim eko, lemin tibetebitunalachihu. Esti lebichachin tewun, egna ahunim keEmebirhan gar, kemelaEktina kekidusan gar menor enifeligalen. Fetari demo becherinetu yimirenal. Esu Geta new, yawim yeAmalkt hulu amlak. Silezih endecherinetu yikir yilenal.

  Demo yihenininm tsihuf delete arigut eshi? Sew Ewnet sinegerew silemayiwed, ayletifewim. Esti lelelawim yihenin hasaben akafiluna, Ewnetun enisma.

  ReplyDelete
  Replies
  1. meshafu yemilewn new yesafut hidna 81un bible temelket

   Delete
 2. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 11, 2013 at 10:46 AM

  እስከፕሮቴስታንት መምጣት ድረስ መጽሐፍ ቅዱስን አያውቁትም። ደረትን ነፍቶ ኦርቶዶክሳዊ ስለመሆን አረጋጋጭ ከሆኑት ከድርሳናት ውጪ መጽሐፍ ቅዱስን ይዞ መገኘት በራሱ ኮትልኳል ወይም ጰንጥጧል የሚያሰኝ በመሆኑ ይዞ መገኘት ያሳፍር ነበር።

  Yes, you are right. God Bless you!

  ReplyDelete
  Replies
  1. 1. ወንድሜ መጽሐፍ ማዘጋጀት እንደ አሁኑ ዘመን የተቀላጠፈና ቀላል ስላልነበረ ፣ በእጅ የሚጻፉት መጽሐፍት ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንዲውሉ ይበረከታሉ እንጅ ፣ እንደዚህ ነጋዴና አትሪፊ ትውልድ ለገበያ አያቀርቡትም ነበር ፡፡ ሸጠው ሃብት ንብረት ከማፍራት ይልቅ የቤተ ክርስቲያንን በረከት ማግኘት ስለበለጠባቸው ያንን አደረጉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያህል መጽሐፍ ቁጭ ብለው የግዕዝን ፊደል እየለቀሙ ሲገለብጡ ትንሽ እንኳን የእምነታቸው ጥንካሬ አይታይህም ?

   2. የህትመት ሥራ ሲጀመር ደግሞ ሚሽነሪዎች (ሚሲዮኖች) መግባት ስለጀመሩ የመጽሐፍ ወደ ህዝብ መበተን ፣ ከነርሱ መምጣት ጋር በመገጣጠሙ ፤ ትርጉምም ተሰጠው

   3. ሌላውም ችግር ወንጌል መታተም በጀመረበት ዘመን ከአገራችን ህዝብ ከዘጠና አምስት በመቶ በላይ ማንበብና መጻፍ የማይችል መሆኑ ነው ፡፡ ታድያ አንብቦ መረዳት የማይችለውን መጽሐፍ የውጋት መድኃኒት እንዲሆነው ወይስ ሰውነቱን እንዲያሻሽበት መሸከምና መዞር የሚያስፈልገው ?

   4. ሌላውም አስተያየትህን ዋጋ የሚያሳጣብህ ምክንያት ፣ ክርስቲያን የሚያሰኘው መጽሐፉን ተሸክሞ መዞሩ ሳይሆን ፣ በውስጡ የሰፈረውን ቃል፣ በተነገሩትም ሆነ በአነበቡት ልክ አምነውበት በተግባር እየተረጐሙ በሃይማኖትና በቅድስና መኖር መሆኑ ነው ፡፡ መሸከምንማ ቁም ነገር ካደረግኸው አህያም ከጫኑዋት ተሸክማው ትዞራለች ፡፡

   5. ህዝባችን ቅዱስ የሆነውን የሃይማኖት መጽሐፍ ፣ በማይጠበቅበት ሥፍራ ሁሉ (አልዘረዝረውም) ማየቱ ግራ ቢያጋባው መናገሩ ፣ የእምነቱን ጥንካሬና ጥልቀት ያመለክታል እንጅ መጽሐፉን በመጥላቱ ወይም ጥቅሙን ስላላስተማሩትና ባለማወቁ ነው ማለት አይቻልም ፡፡


   Delete
 3. መፅሐፍ ቅዱስ 66 ሆነ 70 ወይም 81፥ 89 ምን ልዮነት ያመጣል? ዛሬ ጳውሎስ የፃፈው ፅሁፍ ተቆፍሮ ቢወጣ አይገባም 66 ብቻ ነው መሆን ያለበት ብለህ ልታለቅስ ነው? አባትህ ሉተር የያዕቆብን መልዕክት አውጥቶት ነበር እኮ። ለመሆኑ የትኛው ወንጌል ላይ ነው 66 ነኝ የሚለው?

  ReplyDelete
  Replies
  1. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 11, 2013 at 1:43 PM

   your comments words are full of non-substance and out of touch. "አባትህ ሉተር" you use this word several times. I prefer ሉተር to your father Grima.

   Delete
  2. @ ኢየሱስ ጌታ ነው
   Every time when you responded to others comment, your comment is always immature and confused. You always talk about scripture but don't know what that means.
   The above comment just asked you, is there a verse in the bible which says bible is only 66?
   And about luter he took out one of the book (James) from bible because it wasn't support his belief.
   Now just answer the Q.
   Is there a verse which says bible is only 66?

   Delete
  3. ok two can play at that game; is there a verse that says Bible must be 81? No babbling just give chapter & verse please

   Delete
 4. To the web master:

  I want to say this: I like most of the articles posted on your blog and I disagree with some of them. It didn't take me that much time to have a sense of who you are. I am apologist and a firm beliver that dialog is the best way to grow in one's faith. I like confronting any body who has a diffrent view of what I believe is true using the example of our Lord when he confronted the pharasis and the lawyers on different ocassions when they try to accuse him of false teachings. As I grow every day in my faith I have learned that the problem in our church now a days is to identify people to those false teachers (menafikan) when they question our faith or their faith.

  Now a days I have convinced my self that I have to be the first person to defend the true Ethiopian Orthodox Church Teachings of the Holy virgin Mary, the Angeles, and the Saints that I learned in my school and from the doctors of the church(1st - 8th century)if there is any one open to debate, place where we can get audience, and moderator to make civil arguments. I am more than willing to confront either a protestant scholar or some brothers in the church who belive that we are in the wrong track regarding the above teachings. I have to confess that we have several false teachers in our church now a days who don't have the background of early church fathers teachings on Theotokos(Mother of God) and the saints. But that doesn't mean that the EOTC is the wrong church.

  But I like us to be tolerant when people express what they believe freely and they have the right to do so. We can't just attack people because they have a different view of what we believe. As an Ethiopian Orthodox Tewhedo Church members each and every one of us should know what we believe, why we belive, and how we believe. We need to learn how to do appologetics(Defending our faith) rather than anathema and attacking people.

  I don't know the intention of the writer of this article whether it is intended to tell our church has the wrong evidence regarding the Arc or the writer is trying to tell us that we have the wrong belief regarding the arc of the covenant. I will leave all of that for the writer but I believe that the content of the article has some substance. Therefore, our role is not to condemn the writer rather than defending what we believe with evidence or search for the truth. As Orthodox christians we can't continue to be defiant(this is a character defect) every time either a protestant church member or someone with a different view of what we believe pushes our button. I say this with confidnce to those of you reading this comment that we have more than enough resource to defend our orthodox christian faith with love for those who inquire about the church's teaching. We need to learn doing this with the grace of God. The only way we can win the heart and mind of people for the Lord Jesus Christ is when we witness what we believe and why we believe with love and care.

  After I read some of the comments to the writer of the article in question and the writer's reply to his critique I wanted to say this to both of them that leave alone Luther and memher Girma for which neither of them has nothing to do with the article in discussion.

  When I get time I will have my say in response to the article posted on your blog regarding memher Girma's exorcism.

  May God graciously bless you all

  ReplyDelete
  Replies
  1. ተሳትፎህን በጉጉት እንጠብቃለን!እንደዚህ አይነት እውቀት ያለው ሰው ካለ እኮ ሰዎችም ለስድብ አይቸኩሉም

   Delete
  2. Hi I read your comment. Can you just tell me about the use of
   Crosses and pictures. are they acceptable in Christianity?
   are they teaching of christ?

   Delete
  3. ጐረቤቴ በሆንክ እላለሁ ፤ ውብ ይሆንልኝ ነበር ለመማር ፡፡

   Delete
  4. Brother, you wasted 3 mins of my life because of your extremely foolish essay. You didn't even bother to discuses or at least give a response to the article. why mefoker? Bro, This is not adwa. Give a logical rebuttal or don't say anything at all. Do you actually believe the writer of this article to debate with some amateur anonymous, emotionally driven self proclaimed "apologist"? You must've your mind

   Delete
  5. Hey, is that comment or feedback? are taking English 101 during this Semester?


   Ethiopian Orthodox Church Teachings of the Holy virgin Mary, the Angeles, and the Saints that I learned in my school and from the doctors of the church(1st - 8th century)

   Where did you get the above statement? I read one comment written about your comment it is full of copy and paste plus you did not proof the statements you copy. Be careful! I lot of people are visiting this website even foreigner. The webmaster should have to hide your comment from reading.

   Thanks!

   Delete
 5. ፀሐፊው የሚለን "ኦርቶዶክስ እምነት ጣኦት አምላኪ ነው" ነው። የ3000 ዓመት አገልግሎቷ ጣኦት ማምለክ ብቻ ነበር ግን "ፕሮቴስታንት መጥቶ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ አስተማረን" ነው የሚለን ያለው። ጉድ ነው ዘንድሮ
  "... ወንጌል ለሕዝቡ የበራ ቢሆንማ ኖሮ እስከዛሬ በዛፍ ስር ቡና የሚደፉ፤ ደም የሚያፈሱ፤ቅቤ የሚቀቡ፤በጨሌ፤ ቆሌና የቤት ጣጣ አምልኮ ሰርጾባቸው የሚኖሩ ባልኖሩ ነበር። እምነት አለን፤ አውቀናል የሚሉት እንኳን እስከፕሮቴስታንት መምጣት ድረስ መጽሐፍ ቅዱስን አያውቁትም። ደረትን ነፍቶ ኦርቶዶክሳዊ ስለመሆን አረጋጋጭ ከሆኑት ከድርሳናት ውጪ መጽሐፍ ቅዱስን ይዞ መገኘት በራሱ ኮትልኳል ወይም ጰንጥጧል የሚያሰኝ በመሆኑ ይዞ መገኘት ያሳፍር ነበር። ይህ በእድሜአችን ያየነው እውነት ነው። አንዳንዶች «ሳያዩ የሚያምኑ ብጹአን ናቸው» የሚለውን ቃል ጠምዝዘው ራሳቸው ለመሸንገያነት በመጠቀም አንድም ሐዋርያ ሳይመጣ ያመንን ስለሆንን ቃሉ እኛን ኢትዮጵያውያንን ያመለከታል ለማለት ቢፈልጉም የሐዋርያ ወይም የሰባኪ አለመምጣት እንደ ጉዳት እንጂ እንደጠቃሚ ነገር መቁጠር አለማወቃችንን የሚያሳይ ነው። መጽሐፍ የሚለን እውነት ይህንን ነው።"

  ReplyDelete
  Replies
  1. እዉነት ብለሃል ሁል ጊዜ እነዚህን ሰዎች ሳስብ የሚገርመኝ ድፍረታቸዉ ነዉ::
   "... የሰማ እለት ያብዳል ነዉ ነገሩ" በቤተ ክርስቲያናችን ዉስጥ እነማን እንዳሉ ለማወቅና ተግቶ ቤትን ለመጠበቅ ካልሆነ በቀር ከእንክርዳድ መልካም የስንዴ ፍሬ ይገኛል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነዉ ::
   ለማንኛዉም
   አምላከ ቅዱሳን ዓይናቸዉን ይክፈትላቸዉ ከማለት በቀር ምን ይባላል????

   Delete
 6. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 11, 2013 at 8:14 PM

  You use good and fancy vocabularies for in your comment with out citation.Any ways, what do you mean defending the EOTC? As I understand from the article, the writer of the article clearly telling us the truth with the evidences. I haven't found any thing with that is a treat to our church.

  Also, what do you want to say about this statement: "The only way we can win the heart and mind of people for the Lord Jesus Christ is when we witness what we believe and why we believe with love and care." you are copy and paste or rewrite from the following website:http://www.blueletterbible.org/commentaries/comm_view.cfm?AuthorID=13&contentID=4087&commInfo=18&topic=Growing%20in%20the%20Grace%20of%20God

  When I get time I will have my say in response to the article posted on your blog regarding memher Girma's exorcism.

  When are you getting time to defend your father Girma instead of your Church.
  Next time, use your own words or put the citation,Plagiarism is a civil crime.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሰውየው በሰበቡ ቤቱን አስመረቀን ፡፡

   Delete
 7. ስለ አጻጻፌ ፡- በቁጥር የተመለከተው ከቀረበልን ጽሁፍ እንዳለ የተወሰደ ወይንም መልዕክቱ ብቻ የተቀነጨበ ነው ፡፡ የኔ መልስና አስተያየት በሰረዝ የተከፈተው ነውና ጥሩ ውይይት ለማድረግ ወደ ንባቡ ፡፡

  1.ከከሳቴ ብርሃን አባ ሰላማ በኋላ የመጡ መነኮሳት በዋሻና በፍርክታ ገዳም መስርተው …. በመቀጠል ደግሞ እንደ ሐዋርያቱ ወንጌልን ማስተማራቸው አይታወቅም
  - ወንድም መነኮሳቱ በዋሻና በፍርክታ ሆነው ምንድር ነው እየሠሩ የሚውሉት ? ኧረ እባካችሁ ታሪኩን እያወቃችሁ በተቀኛችሁበት ብቻ አትዘምሩ ፡፡
  - ለመሆኑ የቤተ ክርስቲያን መጽሐፍትና መምህራን እስከ ዛሬ ድረስ ከየት ነው ምንጫቸው ?
  - እነርሱ እንዲያ ባይጽፉና ባያስተምሩ ክርስቲያን ነኝ የሚል ዜጋ ዛሬ በምድሪቱ ይገኝ ነበር ? ገዳማቱ የአሁኖቹ የዘመናችን ኰሌጆችን ይመስል ቅዱሳት መጻሕፍትን ያስተምሩ ነበር ፡፡ የምትወዷቸው ወንጌል አዋቂ ፣ አባ እስጢፋኖስ እኮ ገዳም ነው ለረጅም ጊዜ የኖሩት ፡፡

  2.መጽሐፍ ቅዱስን ይዞ መገኘት በራሱ ኮትልኳል ወይም ጰንጥጧል ያሰኛል
  - ለምን እንደዛ ሊታሰብ ተቻለ ብሎ ነገሮችን በጥሞና መቃኘት ያስፈልጋል ፡፡ በአገራችን የህትመት ሥራ የተጀመረው በቅርብ ዘመን ነው ፡፡ ስለዚህም አባቶች ብራና እየደመጡ ፣ ቀለም እየበጠበጡ ፣ በእጃቸው እየጻፉ በነፍስ ወከፍ ማዳረስ እንደማይችሉ ሁላችንም የምናምነውና የምንቀበለው ሃቅ ነው ፡፡ እንዲህ ለፍተው የሚያዘጋጁአቸውን የሃይማኖት መጽሐፍት በሙሉ ለቤተ ክርስቲያን ያበረክታሉ ፡፡ ኋላ ላይ ደግሞ የጽሕፈት መሣሪያው ሥልጣኔ እያደገ ሲሄድና ሚሲዮኖች ወደ አገራችን ሲገቡ ፣ ነገሩ ተለዋወጠና በቤተ ክርስቲያንና በጥቂት ሊቃውንትና ምሁራን እጅ ይገኝ የነበረው መጽሐፍ በየግለሰቡ እጅ መታየት ጀመረ ፡፡ ይኸኛው ያልተለመደ አዲስ ባህል ስለነበረ ከመጤዎቹ ሃይማኖቶች ጋር ሊዛመድ የቻለ አነጋገር የፈጠረ ይመስለኛል ፡፡ አሁን ግን ያንን ዓይነት አመለካከት ያለው ሰው የለም ፡፡ አይ ይሄ ምክንያት አይሆንም የሚለኝ ካለ ፣ ችግሩን ለመረዳትና ለመጋራት ከአራቱ የወንጌል መጽሐፍት ፣ አንዱን ብቻ መርጦ ፣ እኔን ጨምሮ ለአንድ አሥር ሰው በእጅ እየጻፈ ያዳርሰንና ችግሩን በተግባር ይሞክረው ፡፡ እንዲያውም ጊዜው መልካም ነው ብራና ማዘጋጀት ፣ ቀለም መበጥበጥ አይጠይቅም ፤ ለሃይማኖቱ ፍቅር ብቻ እንጅ ፡፡ እስቲ እኔ አለሁ የሚለኝ ፡፡

  3.አንድም ሐዋርያ ሳይመጣ ያመንን ስለሆንን ያመኑ ብጹአን ናቸው የሚለው እኛን ይመለከታል ..
  - ይሄን ምን ይክዱታል ፤ ይሄ እኮ እውነተኛ ታሪካችን ነው ፡፡ በምንም ዓይነት ልንፍቀው ልንሠርዘው አንችልም ፡፡ እገሌ የሚባል መጥቷል ብሎ የታሪክ ማስረጃ ያስተማረበትን አካባቢ የሚጠቅስ ካለ ያቅርብልን ፡፡ አንዳንዶች ማቴዎስ ሳይመጣ እንዳልቀረ ይናገራሉ ፡፡ ያም እንኳ እውነት ቢሆን ፣ አሁንም ከአይሁድ በብዙ እንሻላለን ፡፡ አይሁድ እኮ ራሱ ጌታችንን እያዩ ፣ እየዳሰሱ ፣ የባረከውን እየበሉ ነው ሊያምኑና ሊቀበሉ ያልቻሉት ፡፡ እናም በእርግጠኝነት አሁንም ብፁዓን ነን ፡፡

  4.እውነተኛ ወንጌል በማስተማርና ሕዝቡን ከክርስቶስ ወንጌል ጋር በማስማማት እንዲኖር ለማድረግ እስከ ሞት ድረስ ከታገለው ከአባ እስጢፋኖስ በቀር ….
  - ለሃይማኖታቸውና ለእምነታቸው ስንት መስዋዕት የሆኑ አባቶችን ታሪክ በሙሉ ጨፍልቀው ፣ ለአንድ ሰው ሲጭኑት ፣ አባ ግርማን መጥራት ሊያስፈልግ ይመስለኛል ፡፡ በዚህ ሰው ስም የመጣብን ክፉ መንፈስ ሳይኖር አይቀርም ፤ ወይንም ከጀርባው የማናውቀው ስውር አጀንዳ አለ ፡፡ እስቲ ቅባት ካራና ተዋሕዶ በማለት ያለቀውንም ህዝብ ጨምረህ ጻፍልን ፡፡ የክርስቲያኖች ንጹህ ደም ነበር እኮ በከንቱ የፈሰሰው ፤ የወንጌል ትርጉም የፈጠረው መከራ ነው እኮ የነዚህን ሰዎች ሕይወት የቀጠፈው ፡፡ የኒህ ወገኖች ለወንጌል ቃል መሞት በአንተ ትርጉም መስዋዕትነት አይባል ይሆን ?

  5. ወንጌል ሥራው በግጻዌ ምድቡ በጥቅስ ደረጃ በቅዳሴ ከሚነበብ ውጭ ከተአምረ ማርያምና ከድርሳናት
  - ወንጌል ይሁን አይሁን ምእመኑ ትምህርቱን ላይረዳው የሚችልበት ምክንያት ከታች ተጠቅሷልና ስለ ትምህርቱ ከየት መጽሐፍ መጣ ማለት አልችልም ፡፡ ቢሆን ግን ተአምረ ማርያምም ሆነ ድርሳናት የሚናገሩት የወንጌልን ቃል ደባልቀው ነው ፡፡ በየትም ቢዞሩ መግቢያና መደምደሚያቸው ጌታችንን መስበክ ነው ፡፡

  6. አብያተ ክርስቲያናት በግእዝ ቀድሰው፤ በግእዝ አንብበው፤ ለዓለመ ዓለም ካሉ በኋላ እግዚኦ መኀረነ ክርስቶስ እንበል 12 ጊዜ ብለው ጣት ከማስቆጠር ባለፈ ….
  - ይሄ የማይታበል ሃቅ ነው ፡፡ ከሰሜን እስከ ደቡብ ፤ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ ምእመኑ ቢረዳውም ባይረዳውም ፣ ቤተ ክርስቲያን ስታገለግል የኖረችው በግዕዝ ቋንቋ ነበር ፡፡ ችግሩ መቀረፍ እንደሚገባው አምናለሁ ፤ አሁን አሁን መልካም ጅማሮ አለ ፤ በየቋንቋው ማስተማር ተጀምሯል ፡፡ እናንተን እንዲህ የሚያጽፋችሁ ምክንያት ግን ፣ ህዝቡ አልተረዳም በማለት ሳይሆን ፣ በግዕዝ የሚባለውን ጸሎትና ቅዳሴ ማነብነብ ስለማትችሉት ይመስለኛል ፡፡

  7. የዲቁናም ይሁን የቅስና ማእርግ የሚሰጠው ሥርዓተ ቅዳሴውንና ኩሳኩሱን ከመልክዓ መልክዑ ጋር መሸምደዱ እንጂ….
  - ትዕግሥት ነስቶኝ ፣ ችግራችሁን በግምት ስቀባዥር ፤ እራስህ ተናግረኸው አበቃህ ፡፡ አብረን እንድንዘምር ፣ በግዕዝ የሚባለው እንዲቀር ፣ በማመልከቻ ጠይቅ ፤ እኔም ከጐንህ ነኝ ፡፡

  ክፍል ሁለት ይቀጥላል
  ReplyDelete
 8. ክፍል ሁለት

  8. ስለታቦተ ጽዮን ትረካ፤ በሚለው ርዕስ የክብረ ነገሥትና (ወደ ኢትዮጵያ) የመጽሐፍ ዕዝራ ካልዕ (ወደ ባቢሎን) ቃላቸው ስለሚጋጭ እውነት ሊሆን አይችልም ፡፡
  *** አሁን ታቦተ ጽዮንን ከሸሸጉበት አውጥተው ቢያሳዩህ ለማክበርና ለመስገድ ነው ወይስ ለእሥራኤሎች ካልተመለሰ ብሎ ደግሞ ሌላ ጩኸት ለመጀመር አቅደህ እንዲህ የተቸገርከው ? ይኸ በተለያየ መልኩ የአፋልጉኝ አቤቱታ ፣ ለደግ ይሁን ለክፉ ሳይታወቅ ብዙ ከረመብን ፡፡ ፈረንጆቹ ብለው ብለው ሲያቅታቸው ፣ አሁን ደግሞ ----- የተጠናወታቸውን የቤት ልጆች አሰባስበው አሰማርተውብን እንዳይሆን እፈራለሁ ፡፡

  ወደ ጉዳዩ ስንመለስ ክብረ ነገሥት ከሞላ ጐደል ታሪክ የሚተርክ መጽሐፍ እንደ ሆነ እንረዳለን ፡፡ የጥንቶቹ ነገሥታት እምነት ፣ ከአይሁድ እምነት ጋር የተቆላለፈ በመሆኑ የቤተ እምነታችንን ታሪክም አደባልቋል ፡፡ የዕዝራ መጽሐፍ ደግሞ የእምነት መጽሐፍ ነው ፡፡ ስለዚህም ከእምነት ጋር የተዛመዱትን ጉዳዮች አስፍሯል ፡፡ ሁለቱንም ለማጣመር ዓለማዊውንና ሰማያዊውን ለማቆራኘት መሞከር ነው ፡፡ እንዲያው በደፈና ከማለፍ ሊያስኬደን ቢችል የሚከተለውን ገመትኩ ፡፡

  የሁለቱንም ታሪክ እውነት ሊያደርጋቸው የሚችል አንድ መንገድ ይታየኛል (የአእምሮ ጨዋታ ነው)፡፡ ይኸውም የንጉሥ ሰሎሞንንና የአይሁዳውያንን ቁጣ ለማብረድ ሲሉ የቤተ መቅደስ አገልጋዮች ታቦተ ጽዮንን እንደ ሙሴ ጠርበው በመተካት ፣ የጠፋው ታቦተ ጽዮን ይኸው ተገኘ ብለው ቢሆን ፤ ሁለቱም ታሪኮች እውነትነት ይኖራቸዋል ፡፡ የቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ መርማሪዎች እንዲህም እያሰቡ ቢፈትሹ መልካም ይመስለኛል ፡፡ ለአፋልጉኝ ጥያቄ ፍንጭ ቢሆን በማለት ነው እንጅ ሃቅ ነው አላልኩም ፡፡ እንዲያው ለምን እንዲህ ታስባለህ ለሚሉ ፤ የአይሁዳውያን የበኩር ልጆች ወደ ኢትዮጵያ ሲላኩ ፣ እንዴት ያለ ታቦተ ጽዮን እንኖራለን ብለዋል ፡፡ እኒህኛዎቹ እንዲህ መኖር አንችልም ካሉ ፣ እነዚያኛዎቹም ማለታቸው አይቀርምና መፍትሄ ሳያፈላልጉ አይቀርም በማለት ነው ፡፡ መቸም አዋቂዎች ይህን አውድማ አይቃኙትም እንጅ ፣ እንዲህ በየፊናችን ከሚያፈላስፉን አንድ መግለጫ ቢሰጡን እንማርበት ነበርም እላለሁ ፡፡

  9. ዲያብሎስ የወደቀው በትዕቢቱ አምላክ ለመሆን ስለፈለገ ነው ወይስ ለአዳም ስገድ ተብሎ እምቢ በማለቱ ነው?
  - መጽሐፍትን ተርጉመው የሚያስረዱ ሊቃውንት ስላሉ ጥያቄው ለነርሱ ቢቀርብ ምላሽ አያጣም ፡፡ ምክንያቱም ቀደም ሰባክያኑ የአንደምታ ትርጉም ተማሪዎች ስለሆኑ ወንጌልን እኛ ከምንረዳው ለየት ባለ መልኩ ይተረጉሙታል ፡፡ ለምሳሌም መጥምቁ ዮሐንስ በግዞት በነበረበት ሰዓት ፣ የምትመጣው መሲህ አንተ ነህ ወይ ብሎ መልዕክተኛ ሲልክ ፣ ጌታችን የምሠራውን አይታችሁ መስክሩለት በማለት የተላኩትን ስዎች አሰናበታቸው ፡፡ ኋላም ስለ መጥምቁ ሲናገር ከነቢያት እንደሚበልጥ ፣ ከሴቶች ከተወለዱት ሁሉ በርሱ የሚደርስበት እንደ ሌለ ይልና መንግሥተ ሰማያት በመግባት ግን …. ብሎ ይደመድማል ፡፡ የአንደምታ ትርጉሙን ላነበበ ግን ጌታ ያስተማረው እንዲህ እንዳልኩት ፍጥጥ ያለ አይደለም ፡፡ ቃሉን ከመልዕክቱና ከወንጌሉ ያስማሙታል ፡፡

  1ዐ. ለሰዎች በጥቁርና ቀይ ቀለም መጻፍ ያስተማረው አጋንንት ነው?
  - ጸሃፊው ከላይ ስለ ዲያብሎስ በጻፈው መልዕክቱ መጽሐፈ መቃብያንን ለመተቸት ሞክሯል ፡፡ ለእዚህኛው መግለጫ ደግሞ ምስክር አድርጐ የሚቆጥረው መጽሐፈ ሄኖክን ነው ፡፡ ጥርት ያለ አቋም አልያዘም ፡፡ አፖክሪፋ መጽሐፍትን አልቀበልም ከተባለ ፤ አስረጅ ከዛ ውስጥ መጥቀስም ሆነ ቃል መምረጥ ስህተት ነው ፡፡

  11. ዲያቆናት ጥርስ ማፋጨትና እሳቱ ወደማይጠፋ ቅጣት ይወርዳሉ የሚል
  ትምህርት ዉሸት ነው።
  - ይሄም ተከታዮችን ለመቀስቀስና የቡድን አባላትን ለማበራከት የተዜመ ይመስላል ፡፡ መጽሐፍን ለመተርጐም ምሳሌ አድርጎ መናገር ፤ ናቸው ወይም እንዲህ ይሆናሉ የሚል ፍቺ አይሰጥም ፡፡ ለዲያቆናት የሚሰጥ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ስለሆነ ፣ ለተማሪዎች በሚታያቸውና በሚገባቸው መልኩ ተመስሏል ይባላል እንጅ የመክሊት ሰብሳቢነት ሥራቸውም አይደለም ፡፡ ዶግማ ባለመሆኑ ምክንያት ፣ ምሳሌው ብዙዎችን የሚያስኮርፋቸው ቢሆን የሚመለከተው ክፍል ሊቀይረው የሚችል ይመስለኛል ፡፡

  ቃልህን ለወጥ አድርጌ እኔም ይቺን ልበል
  “ስህተት ካለብኝ ያለ እውቀት ነውና ፣ ስለሃይማኖት በማክረር ጌታን በምታወዱሱበት ምላስና ትናጋ ፤ ክፉ ቃል ከመሰንዘር እንድትቆጠቡና መልዕክቴን እንድትረዱልኝ እፈልጋለሁ”። የሰሞኑ የቃላት ዱላው በርክቷልና እስቲ ስለ ጌታ ብላችሁ ተለመኑ" ፡፡


  ReplyDelete
  Replies
  1. ጥሩ አድርገህ ለማድበስበስ ሞክረሃል፤ ነገር ራስህን ስትሸፍን ቃላቶችህ ቁምነገር ስለሌለባቸው እግርህን አጋልጦታል። ያም ማለት ምን ያህል እንደምታውቅ ያሳያል ማለት ነው። ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን ኦርቶዶክሳዊት ያሰኛት የቆመችበት ሃይማኖታዊ መሠረት እንጂ ያንተ ዓይነቱ ተረታ ተረቱን ለመከላከል ባደረጉት መፍጨርጨር አይደለም። ምስጢረ ሥላሴን እና ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ሥጋ የለበሰበትን ምስጢረ ሥጋዌ ከየትኛውም ሃኅማኖት በተሻለና በተብራራ መልኩ የምታምንና የምታሳምን መሆኗ ነው። ዳሩ ግን በብርሃኑ ትምህርቷ ውስጥ እውነቱን የሚጋርዱና ማን አሹልኮ እንዳስገባቸው የማይታወቁ የባልቴት መጻሕፍት ባንተ ዓይነቱ ፈሪሳዊ እንዳይነካ እየተጠበቀ ወደፊት ከመሄድ ታግዳ የገዛ ልጆቿን ጠብቃ ማቆየት አቅቷቷል። በግልሙትና አስተዳደርና መንፈሳዊ ውድቀት ውስጥ ተሰነጣጥቃ እየተንገዳገደች ትገኛለች። እርስዋ አምና ከተቀበለች ከ2000 ዘመን በኋላ ኢየሱስን ተቀበል የሚል ትውልድ ከጓዳዋ የተፈጠሩት የተቀበለችውን ለትውልድ ማስተላለፍ ባለመቻሏና በተረትና ገድላ ገድል ጊዜዋን በመግደልዋ ነው። የተቀበለችውን የወንጌል እውነት ትታ ንፍሮ የበላ፤ ጠላ የጠጣ፤ ዳቤ የቀመሰ፤ በላዔ ሰብእ፤ ምናምን ከማለትዋም በላይ ይኼንኑ ፈውስ የለሽ ትምህርት ለመከላከል መገኘትዋ አሳዛኝ ያደርገዋል። የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብትዳከምም አትወድቅም። ተረታ ተረቱ ቢሸፍናትም ጥንት የተቀበለችው እውነት ይገለጣል። ብትሰነጣጠቅም አትፈርስም። በአፋቸው የሚጮሁላትና ፍቅሯ ያቃጠላቸው የሚመስሉ ነገር ግን የከበባት ዘማና ስድ ትውልድ ያልፋል። ነገሮችን ሁሉ ማስረጀትና አዲስ ማድረግ የሚችለው እግዚአብሔር ራሱ ያድሳታል፤ ወደጥንት የተቀበለችው የወንጌል እውነት ትመለሳለች። ኢየሱስን ከተቀበልን 2000 ዘመን ያለፈን የኦርቶዶክሳዊቷ ልጆች ነን እንጂ ዛሬ ከማንም እጅ የምንቀበለው ኢየሱስ የለም። ነገር ግን የተቀበልነውን እውነት ከመግለጥ ወደኋላ አንልም።

   Delete
  2. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 12, 2013 at 1:23 PM

   AnonymousJanuary 12, 2013 2:04 AM

   Short and precise answer for this very cynical person who are defending Tert Tert to replace the holy bible.I also read his anti bible comment in English with Anonymous January 11, 2013 5:05 PM with out citation, I checked its Plagiarism. It was a rewrite with the number of websites.

   Truly speaking, I am very happy this days to see a true orthodox Christians living with the bible in stead of the tert tert. God bless you be in touch and we need your contribution.

   Take care!

   Delete
  3. ምእመን January 11, 2013 10:12 PM

   you are very loyal for your religion, I do appreciate that but at the same time, I advice you to compromise. you are knowledgeable to use reference for defending the wrong.This article is embedded with a lot references and evidences so don't put your fingers in the keyboard for non constructive comment just to oppose. See what kind of problems the church are facing.

   Thanks

   Delete
  4. ለAnonymous January 12, 2013 2:04 AM

   ስጽፍ በቁጥር ያስቀመጥኩት ለመተቸት እንዲያመቻችሁ ነበር ፡፡ እንዲያው ድፍን ያለ መያዣና መቋጫ የሌለው አስተያየት ብታስነብበኝም ፣ ምን ለማለት እንደፈለግህ እንናኳን አልተረዳሁም ፡፡ አሁን እግርህ ራቁት ነው ማለት ምን የሚሉት አስተያየት ነው ? የጻፍኩትን መቃወምህ ከሆነ ዘርዘር አድርገህ ይሄን በዚህ ምክንያት እያልክ አስተምረኝ ፡፡

   ሌላው ከጻፍከው መሃል "ኢየሱስን ከተቀበልን 2000 ዘመን ያለፈን የኦርቶዶክሳዊቷ ልጆች ነን እንጂ ዛሬ ከማንም እጅ የምንቀበለው ኢየሱስ የለም።" የሚል ቃል አነበብኩ ፡፡ እንዲህ ማለትህም ባልከፋ ነበር ፡፡ በተግባር ሥትሰሩ የምናየው ግን ተጻራሪውን ነው ፡፡ እኔ ኢየሱስን አምኛለሁ ስል ፤ በኪሳችሁ ይዛችሁት ትዞሩ ይመስል ፣ አይ ያኛው አይሠራም ዳግም ተቀበል ስለምትሉን መሰለኝ የሃሳብ ልዩነት የተፈጠረው ፡፡

   ለማንኛውም ስለ አስተያየትህ ሁሉ አመሰግናለሁ ፡፡ ጥሩ ሙከራ ነው

   Delete
  5. ውድ ምእመን፤ ለጥሩ ሙከራዬ አስተያየት የተሻለ መልስ መስጠት አልቻልክም።
   አባቱን አያውቅ፤ አያቱን ይናፍቅ መሆንህን አታውቅም! እውነቱ የቱ ነው የሚለው ጽሁፍ ላቀረባቸው ነጥቦች መልስ መስጠት ሲያቅትህ ልትሰግድ ነው? ሊቃውንቱ ይመልሱ፤ ሄኖክን መካድ፤ ምናምን ገለመሌ እያልክ ዙሪያ ጥምጥም ትዞራለህ። መመለስ የምትችል ከሆንክ፤ የጽሁፉ ጭብጥ ጨምቄ ላሳይህ፤
   1/ ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ የሚለው የማኅበረ ቅዱሳን መጽሐፍ ነው ትክክል ወይስ ክብረ ነገሥት? ክብረ ነገሥት ትክክል ነው ካልክ፤ የማኅበረ ቅዱሳን መጽሐፍ የቤተክርስቲያኒቱን መጽሐፍ የተጻረረ ነው ለምን አልተባለም?
   2/ታቦተ ጽዮን በንጉሥ ሰሎሞን ዘመን መጣች ከተባለ ከ300 ዓመት በኋላ በኢዮስያስ ዘመን በመቅደሱ ነበረች ያለውን ቃል ምን ትላለህ? በሴዴቅያስ ዘመንስ ወደባቢሎን ተማርካ ተወሰደች የሚለውን ያንተኑ መጽሐፈ መቃብያንን በምን ቃል ዝም በል ትለዋለህ?
   3/ ሰይጣን ከማእረጉ የወረደው ለአዳም አልሰግድም በማለቱ ነው ወይስ ራሱን አምላክ ለማድረግ ስለፈለገ ነው? ለአዳም አልሰግድም ስላለ ነው የሚል አስተምህሮ ብታገኝ ምን ትላለህ?
   ሌሎቹ ጥያቄዎች ይቆዩንና ብዙ ሸክም እንዳይሆንብህ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ስጥ! በእርግጥ አንተ መመለስ እንደማትችል እርግጥ ነው። ቢሆንም ሊመልሱልኝ ይችላሉ የምትችላቸውን ሁሉ ዞረህ ጠይቅና መልሱን አምጥተህ በዚህ ብሎግ ላይ አምድ ከፍተህ ለጠያቂዎች ሁሉ አፍ የሚያስዝ ጽሁፍ አቅርብ። መጽሐፉ «ለሚጠይቋችሁ መልስ መስጠት ትችሉ ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ» አይደለም እንዴ የሚለው?

   Delete
  6. ለየተሰቀለው
   ወንድሜ ራሱ ሌባ የሆነ ሰው ሌላውን ወገን በምንም ቢሉት አያምንም ፡፡ እንደ ጠቀስከው ሰው ያህል የቋንቋ ሊቅነት ቢኖረኝ አንተ በደንብ እንዲገባህ በእንግሊዝኛ በጻፍኩልህ ነበር ፡፡ እኔ በአኖኒመስ ስም ደግሞ ልሞክርልህ ስልህ በእንግሊዝኛ እጽፋለሁ ማለቴ አልነበረም ፡፡ በአኖኒመስ ስምም ቢሆን አማርኛዬን አልቀየርኳትም ፡፡ ምክንያቶቼ ደግሞ አንድም እንደ አንተና ሌሎች በእንግሊዝኛ የመጻፍ ክህሎቱ ስለሌለኝ ነው ፤ ሌላውም የማንበብ ዕድሉን ካገኘ ልትጠልፉ የፈለጋችሁት ብዙሃን በቀላሉ እንዲረዳኝ ስለምፈልግ ነው ፡፡

   ለማስታወስና ለመመስከር ያህል “በምእመን ስም የሚጻፈውን አላነብም” ብለህ አቋምህን ስላሳወቅኸኝና እኔም ቃል በገባሁት መሠረት በአኖኒመስ ስም “ሰውየው በሰበቡ ቤቱን አስመረቀን” ብየሃለሁ ፡፡

   ወንድሜ እምነትህ ሌላ ሆኖ ሳለ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነኝ እያልክ እየዋሸኸኝ ነውና ፤ በእርግጠኛ የተዋህዶ አማኝ ከሆንክ የምትከተለዋን ጥያቄ ሳትተነትንና ሳትዋሽ ፣ ቁጥር በማስቀመጥ ብቻ መልስልኝ ፡፡
   “ቅድስት ድንግል ማርያም ስንት ልጅ አላት ?”

   የምታነበውን ፣ የምታዳምጠውንና የምታጠናውን ሁሉ አይቼልሃለሁ ፡፡ እንኳንም በቶሎ ተዋወቅን ፡፡ የምጽፈው ሁሉ የተወላገደ የወንጌል ቃል የሆነብህ ውሎህ ከሌሎች ጋር ስለሆነ ነው ፡፡ እንዲያ ብትሆንም ወንድሜን አልጠላህምና ፡፡ ሰላም ሁንልኝ ፡፡

   ለሙሉ
   ወንድሜ/እህቴ ምክርህ/ሽ በመልካም ምክርና መልዕክት በመታጀቡ አመሰግናለሁ ፡፡ ነገር ግን የማነሳልህ/ሽ ጥያቄ
   1. እኔ ከማንና ከነማን መማር ይገባኛል ? የማንንስ መግለጫ እውነት ማለት አለብኝ ?
   2. እንደ ኦርቶዶክስ አማኝነቴ ደግሞ በየብሎጉ ከአባቶች አስተምህሮ ውጭ የተጻፈውን ሁሉ እውነትና ትክክል እያልኩ መቀበል ፣ ወይንስ ስለ ቤተ ክርስቲያኔና ሃይማኖቴ ሽንጤን ገትሬ መከራከር ይጠበቅብኛል ?
   3. የስህተት ትምህርት እንኳን ቢኖር ፣ ለማረም ፣ ትክክለኛው አካሄድ በብሎግ ላይ ለጥፎ ለመላው የዓለም ህዝብ ማስነበብ ነውን ?

   Delete
  7. ለ Mulu
   ወንድሜ/እህቴ/ ምክርህ/ሽ/ በመልካም አስተያየትና መልዕክት በመታጀቡ አመሰግናለሁ ፡፡ ነገር ግን የማነሳልህ/ሽ/ን ጥያቄዎች እንደ ዳኛ በንጹህ መንፈስ ሆነህ/ሽ/ ፣ ለየትኛውም ወገን ሳታዳላ/ዪ/ መልስ/ሽ/ልኝ

   1. እኔን እንደ አንድ ቀናዒ ሃይማኖተኛ ሰው ቆጥረህ/ሽ/ ፣ ከማንና ከነማን ሃይማኖትን መማር ይገባኛል ? የማንንስ መግለጫ እውነት ነው ብዬ መቀበል ይኖርብኛል ?

   2. እንደ ኦርቶዶክስ አማኝነቴ ፣ በየብሎጉ ከአባቶች አስተምህሮ ውጭ ወይም እየተወላገደ የተተረጐመና የተጻፈውን ሁሉ እውነትና ትክክል እያልኩ መቀበል ፣ ወይንስ ስለ ቤተ ክርስቲያኔና ሃይማኖቴ መከራከር ይጠበቅብኛል ? ማንኛውም የሃይመኖት ተከታይ ቢሆን ፣ ትክክለኟ አካሄዱ ምን መሆን ይገባዋል ? ለማለት ነው ፡፡

   3. መስተካከል የሚገባው የስህተት ትምህርት ቢኖር እንኳን ፣ ለማረምና ለማስተካከል ፣ ትክክለኛው አካሄድ በብሎግ ላይ ለጥፎ ለመላው የዓለም ህዝብ ማስነበብ ወይንስ ማስተካከልና ማሻሻል ወይም ማረም ለሚችለው ባለ ሥልጣን (ሲኖዶስ) በተደጋጋሚ አቤት ማለት ትክክለኛ የሚሆነው አሠራር ?

   4. ትምህርተ ሃይማኖትን ፣ አንዳንድ ብልጦችና ብልሆች በየሥፍራው ገልብጠውና ተርጉመው ስለጻፉት ብቻ ትክክልና ስህተት እያለ ለመፈረጅና ለመወሰን ፣ ችሎታና ዕውቀቱ ፣ የትምህርት ደረጃውም ይፈቅድለታል ብለህ/ሽ/ ትገምታ/ቻ/ለህ/ሽ/ ?

   5. ከመንገድ ላይ ያገኘሁትን የሃይማኖት መግለጫ ሁሉ በቃላቱ ማማርና መጣፈጥ የምከተል ቢሆን ፣ እስከ ዛሬ ስንቱ ቤት እሰነጣጠቅ ወይም እወጣ እገባ ይመስልሃ/ሻ/ል ? በክርስትና ስም እርስ በርስ የሚፎካከሩትን ብቻ ማለቴ አይደለም ፡፡

   እነዚህን ያቀረብኳቸውን ጥያቄዎች የጻፍኩት ዝም ብዬ አጥባቂ ኦርቶዶክስ በመሆኔ ወይም ምናልባትም ከተገኘ የተሸፈነ የቤተ ክርስቲያናችን ድክመትና ስህተት እንዳይገለጥ ወይም እንዳይስተካከል ለመሸፋፈን ፈልጌ አይደለም ፡፡ ዕውቀቴ እዚያ ድረስ ያደገ ስላልሆነ ፣ ያንን ማለት አልችልም ነበር ፡፡ ነገር ግን የምናነበው መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚያስተምረን ወይም ምሳሌነቱን ስለዘገበልን ብቻ ነው ፡፡

   ብዙዎች መጽሐፍ አዋቂዎች ከጳውሎስ የገላትያ መልዕክት እርግማኑን ብቻ ስለሚወዱት በተደጋጋሚ ይጠቅሱታል ፡፡ እኔ ደግሞ ከርግማኑ አለፍ ብዬ ለክርስቲያን ወገኖች የአሠራር ሥርዓት እንዲሆን ያካፈለውን ትምህርት ወይም ምሳሌነት እስከ ዛሬ አልታየ ወይም ትኩረት አልተሰጠው ቢሆን አቀርበዋለሁ ፡፡ ቃሉም ይኸው

   “ምናልባትም በከንቱ እንዳልሮጥ ወይም በከንቱ ሮጬ እንዳልሆን በአሕዛብ መካከል የምሰብከውን ወንጌል አስታወቅኋቸው፤ ዋኖች ግን መስለው ለሚታዩ ለብቻቸው አስታወቅኋቸው።” ገላ 2፡2 (ከሁለት ሺህ ዓመት በፊት እንኳን በግል ምክክር ይደረግ እንደነበረ ልብ ይሏል ፡፡ ምን እንደተመካከሩ ፣ ምን እንደተነጋገሩ ከእግዜር በቀር አንድም ሰው እስከ ዛሬ እንዲህ ተባባሉ ማለት አልቻለም ፡፡ ምሥጢረ ቤተ ክርስቲያን ይላሉ ይኸን ዓይነቱን አሠራርም ነው ፡፡ የትኛውንም ወገን ለሃሜትና ለትችት አልዳረገም)

   “ደግሞ የተሰጠኝን ጸጋ አውቀው፥ አዕማድ መስለው የሚታዩ ያዕቆብና ኬፋ ዮሐንስም እኛ ወደ አሕዛብ ፤ እነርሱም ወደ ተገረዙት ይሄዱ ዘንድ ለእኔና ለበርናባስ ቀኝ እጃቸውን ሰጡን፤” ገላ 2፡9 (ፍትሃዊና ገላጋይ ውሳኔም እንደሰጡት መመስከሩን ይገነዘቧል ፡፡ አሁንም ይህ የሚደረገው ክርክርና ውይይት በሲኖዶስ የተገደበ ቢሆንና ፣ በመጨረሻ የሚተላለፈው ውሳኔ ይፋ ቢደረግልን ሁሉም ተከታይ በቀላሉ ይቀበለዋል ፤ አንድነቱም እንደ ጠነከረ ይቀጥላል የሚል እምነት አለኝ)

   በወንጌልም እንዲህ ይለናል ፣ ወንድምህም ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው፤ ባይሰማህ ግን፥ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር አፍ ነገር ሁሉ እንዲጸና፥ ዳግመኛ አንድ ወይም ሁለት ከአንተ ጋር ውሰድ፤ እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ። ማቴ 18፡15-17

   በተጻፈው ላይ ያለህን ቅን አመለካከት በመጠባበቅ

   Delete
  8. ለ Anonymous January 12, 2013 2:04 AM

   ጥያቄዎቹን በጻፍካቸው ተራ ቁጥር መሠረት ሳላዛንፍ ለመመለስ ሞክሬአለሁ ፡፡
   1. ለአንደኛው ጥያቄህ መልሴ ማኀበረ ቅዱሳን ያሳተመውን መጽሐፍ ስለ አላገኘሁት አላነበብኩትም ፡፡ ባላነበብኩት መጽሐፍ ላይ አስተያየት ለመስጠት እቸገራለሁ ፡፡ በኢንተርኔት ተለቆ ከሆነ አድራሻ ጠቁመኝና አንብቤ በሦስት ቀን ውስጥ ጥያቄህን ልመልስልህ

   2. ይህን እውነታ የሚያስማማ ቃል ከመግለጫዬ ስለሠፈረ ፤ ሁሉንም እውን የሚያደርግ ዳግም ሌላ ግምት የለኝም ፡፡ አይ ግምትህ ትክክል አይደለም የምትለኝ ከሆነ በምን አረጋገጥህ እላለሁ ፡፡ ቢያንስ እሥራኤሎች ቤተ መዘክር ገብቶ ብዙ መፈተሽ የሚፈልግ ሥራ ነው ፡፡ ይኸን አረጋግጠህ እስካላስወገድህ ድረስ በሃሳብ ደረጀ ሊሠነዘር የሚችል ነው ፡፡

   3. የኛ መጽሐፍ ቅዱስ ገና አሁን ከግዕዝ ተተርጉሞ መውጣቱ ነው ፡፡ አሳታሚዎች ደግሞ የውጭ ሰዎች ናቸው ፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ራሷን ችላ አሳትማ አታውቅም ፡፡ ስለሆነም የትርጉምና የኀትመት ስህተቶች ከተገኙ በሂደት እያረመች ትሄዳለች ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም ሲጻፍ ያገጠመው ዕውነታ ይኸንኑ የመሰለ ነው ፡፡ ታሪክ ፈትሽ ፤ አሉ የማባሉት 15ዐዐ የጥንት ወንጌሎች አንዱ ከአንዱ አይመሳሰሉም ፡፡ ስለዚህም ለመተቸት አትሯሯጥ ፡፡

   ለአስረጅነቱ የሁለቱንም የሰማንያ አሃዱ መጽሐፍ ቅዱስ እተሞች ልዩነት እንድታነብና እንድታወዳድር ገልብጫቸዋለሁ ፡፡ በተረፈ አሁንም የምደግምልህ መጽሐፍትን የሚተረጉሙ ሊቃውንት ስላሏት ፣ ስለትርጉም ነገር እነርሱን ብትጠይቅ ማብራሪያ ይሰጡሃል ፡፡ ለመማር እግራቸው ሥራ መቀመጥ ብቻ ያስፈልግሃል ፡፡ እኔ ግን እንደ ተጻፈ ባነበውም አይረብሸኝም ፡፡ በአተረጓጐም የተበላሸ ካለ በሂደት የሚስተካከል ጊዜያዊ ሰው ሠራሽ ግድፈት ይሆናል ብዬ አልፈዋለሁ ፡፡

   “እግዚአብሔር ያይደለህ ደካማ ሰው ሆይ ፣ ለምን ትኮራለህ ፣ ዛሬ ሰው ሆነህ የምትታይ አንተ ነገ መሬት አመድ ነህ ፤ በመቃብርም ፈጽመህ ትል ትሆናለህ ፡፡ ያንተ መምህር አባታችን አዳምን ስላሳተ የሰውን ሁሉ ኃጢአት ፍዳ ወደ ራሱ የሚመልስ ዲያበሎስ ነውና ዳግመኛም ሲኦል ታገኝሃለች 4 ያንተንም ኃጢአት የሚሠሩ ሰዎችን ታገኛቸዋለች ፡፡ ክሣደ ልቡናውን በማጽናትና ራሱን በማኩራት ፈጣሪው ለፈጠረው ለአዳም መስገድን እምቢ እንዳለ ፡፡ አንተም መምርህ ፣ ዲያብሎስ እንዳዳረገ ለፈጣሪህ ለእግዚአብሔር መስገድ እምቢ ብለሃልና” ፡፡ 2ኛ መቃ 9፤1-4 ፤ ፲፱፻፹ እትም

   “እግዚአብሔር ያይደለህ አንተ ደካማ ሰው ሆይ! ለምን ትኰራለህ ? ዛሬ ሰው ነህ ፤ ነገም መሬትና ዐመድ ነህ ፤ በመቃብርህም ትልና ብስባሽ ትሆናለህ ፡፡ ዳግመኛም አንተንና የአንተን ሥራ የሚሠሩትን ሲኦል ትከተላቸዋለች ፤ የአንተ መምህር አባታችን አዳምን ስለ አሳተ የዐለምን ሁሉ ኀጢአት ወደ ራሱ የሚመልስ ሰብልያኖስ ነውና ፤ ራሱንም በማኩራትና ልቡናውን በማደንደን ለፈጣሪው ሥራ መስገድን እንቢ ብሏልና ፡፡ አንተም እንደ መምህርህ ለፈጣሪህ ለእግዚብሔር መስገድን እንቢ ብለሃል” ፡፡ መጽሐፈ መቃብያን ካልዕ 9፡1-4 ፤ ፳፻ ዕትም

   በሁለቱ ሺህ እትም ላይ አዳም የሚለው ቃል ለፈጣሪው ሥራ መስገድን በሚለው ተተክቷል ፡፡ ይህም ቢሆን ምን ማለት እንደሆነ የምሁራንን ትርጉም ይፈልጋል ፡፡

   ስለ ጥቁርና ቀይ ቀለም የተጻፈውም ልዩነቱን አስተውል
   “አራተኛውም ስሙ ፔንሙዕ ይባላል ለሰው ልጆችም የጣፈጠውንና የመረረውን ያስተማረ ይህ ነው ፡፡ የተሠወረ ጥበባቸውን ሁሉ አስተማራቸው ፣ ለሰዎችም በጥቁር ቀለም በወረቀት ቀይ መጽሐፍ መጻፍን አስተማራቸው ፡፡ እንደ መላእክት ንጹሐን ጻድቃን ሁነው ይኖሩ ዘንድ ነው እንጂ ሰው በእንዲህ ያለ ሥራ አልተፈጠረም ፡፡ በጥቊር ቀለምና በቀይ ቀለም ጽፈው ሃይማኖታቸውን ሊያጸኑ ሰው ለእንዲህ ያለ ሥራ አልተፈጠረም ነበርና ፡፡ ስለዚህ ነገር ከጥንት ጀምሮ እስከ ዘላለሙ እስከዚያችም ቀን ድረስ ብዙ ሰዎች ይስታሉ አለ” ፡፡ሄኖክ 19፡22-24 ፤ ፲፱፻፹ እትም

   አራተኛውም ስሙ ፔንሙዕ ነው ፤ ለሰው ልጆችም የመረረውንና የጣፈጠውን ያሳየ ይህ ነው ፡፡ የተሰወረ ጥበባቸውን ሁሉ አሳያቸው ፤ ለሰዎችም በጥቁር ቀለምና በወረቀት መጽሐፍ መጻፍን አስተማራቸው ፡፡ ስለዚህም ነገር ከጥንት ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ፣ እስከዚችም ቀን ድረስ ብዙ ሰዎች ይስታሉ ፡፡ እንደ መላእክት ጻድቃንና ንጹሓን ሆነው ይኖሩ ዘንድ ነው እንጂ ሰው ለእንደዚህ ያለ ሥራ አልተፈጠረም ነበርና ፣ በቀይ ቀለምና በጥቁር ቀለምም ሃይማኖታቸውን ሊያጸኑ ሰው ለእንዲህ ያለ ሥራ አልተወለደም ነበርና ፡፡ ፳፻ ዕትም

   በሁለቱ ሺህ ዕትም ጽፈው የሚል ቃል የለውም ፡፡ ስለዚህ በቀየ ቀለምና በጥቁር ቀለም ሃይማኖትን ማጥናት ማለት ተርጓሚ የሚፈልገ ገለጻ ነው ፡፡

   ስለ አስተያየትህ አመሰግናለሁ ፡፡ በሃሳብ ኰርኰም ስላደረግሁህ በግልጽ ተናገርህ ፡፡ ይኸን ዓይነት ሲሆን ለመነጋገር ያመቸናል ፡፡ ሰላም ሁንልኝ ፡፡

   Delete
  9. @mimimen, ere begeta endet yaleh liq neh ebakeh? I am always proude to have matured person like you in our chruch. I read all what you posted more than once. The way you argue and the content you write are so impressive for me. Kef bel new yemileh! Enezih behulet bilewa yemibeluten tewachew...ante gib berta ...we have a lot to learn from you. I wish if I could get you in private. Dingil tiketeleh!

   Delete
  10. ለ Anonymous January 14, 2013 at 3:35 AM
   መልካሙን ነገር ስለተመኘህልኝ እግዚብሔር ይባርክህ !!! አንተንም ቅድስት ድንግል ማርያም ትከተልህ !!!

   እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ስለ ፈቀደው ነው እንጅ የኔ መልስ መቀነባበሩ ፣ እኔ ቅስና የለኝ ዲቁና ፤ ዝም ብሎ በአንድ የተራ ምእመን ዕውቀት ነው የምገለገለው ፡፡ ማንበብን እወዳለሁ ፣ ከመጥፎውም ቢሆን ጥሩ ለማውጣት ትዕግሥቱ አለኝ ፡፡ እንዲሁ ስንት እየተባለብን አንድ ዓመት ከዚህ ብሎግ ጋር ለመሰንበት መቻሌ ምስክሬ ነው ፡፡ ባጋጣሚ ስለ ደብረ ማርቆስ ጥምቀት የጻፉትን አይቼ ተጠለፍኩ ፣ ይኸው እስከ አሁን በእሰጥ አገባ አለሁ ፡፡ ስምህን ከለመዱት በኋላ የሚሉህ ሲበዛብህ ፣ ያነበቡትም ሁሉ የአንተ ሲመስላቸው መንፈሳቸውን ለማረጋጋት መጠሪያህን ትቀይርና ትሞክራለህ ፡፡ አሁንም አንድ ወንድሜ ወደዚያው መንገድ እየመራኝ ነው ፡፡ ስምህን ከለመዱት በኋላ ፣ ሃሳብህን ሳይሆን ስምህን ለመቃወም የሚጽፉ አሉ ፡፡ ይሄን ደግሞ መጥፎ ስለት እለዋለሁ ፡፡ እርስ በርስ እንድንማማር አይረዳንም ፡፡ እኔንም ከማደርገው መግታት አይችሉም ፡፡ አባ ሰላማዎች ደስ የሚሉኝ ደግሞ ንፍጣም ብዬ ብሰድባቸው እንኳን ጨክነው ማውጣታቸው ነው ፡፡ ደስ አይልም የነሱስ እንደ እኔው ትዕግስተኛ መሆን ፡፡

   Delete
 9. ethiopia egeziabehare yebarkate

  ReplyDelete
 10. "ግብጾች ወርቁንና ብሩን ከጫንላቸው የቱንም የስህተት መንገድ ብንከተል ጉዳያቸው እንዳልነበር የሚያሳይ ነገር ነው።" It is true I knew them very well because I have been with them for long time. They don't care about your faith they care only about there income and business they are well organized Mafia groups they cover themselves by black galebya(kemis) and they grew up their bear for people eye attraction only. They do not fast even on Wednesday and Friday as they teach for us to keep it. They eat early in the morning. They are eating with out ceasing that is their aim.

  ReplyDelete
 11. ወይ እናንተ ሁል ጊዜ ስለእናንተ ሳስብ የሚገርመኝ ድፍረታቸሁ ነዉ::
  "... የሰማ እለት ያብዳል ነዉ ነገሩ" በቤተ ክርስቲያናችን ዉስጥ እነማን እንዳሉ ለማወቅና ተግቶ ቤትን ለመጠበቅ ካልሆነ በቀር ከእንክርዳድ መልካም የስንዴ ፍሬ ይገኛል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነዉ ::
  ለማንኛዉም
  አምላከ ቅዱሳን ዓይናቸሁን ይክፈትላቸሁ ከማለት በቀር ምን ይባላል????

  ReplyDelete
  Replies
  1. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 13, 2013 at 7:53 AM

   ምእመን
   አምላከ ቅዱሳን ዓይንህን ይክፈትልህ ከማለት በቀር ምን ይባላል?

   Delete
  2. ወንድሜ አገር ምድሩን በሙሉ ምእመን አደረግኸው እኮ ፡፡ ምን ይሻልሃል ? ይኸም ሰው እኔ አይደለሁም ፡፡ በስሙ መስተፋቅር እንኳን አላስደረግኩ ያንተ ፍቅር በዛብኝ ?
   ምን በደልኩህ ? እንዲህ እምባዬን እስከማፈሰው ድረስ የምታስቀኝ እባክህ ፡፡
   ምክር
   እመነኝ ፣ ከስሜ ውጭ በአኖኒመስ ከተዋወቅን እስከ አሁን ሦስት ጊዜ ብቻ ጽፌአለሁ ፤ ሁለቱ ለአንተ አይደለም ፡፡ አንደኛውን ያው ንስሐ ብትልልኝ አሳውቄሃለሁ ፡፡ ስለዚህ እዚህ ብሎግ ላየ የሚጽፈውን ሰው በሙሉ ምእመን ስትል አትክረም ፡፡

   Delete
  3. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 14, 2013 at 10:35 AM

   ወንድሜ አገር ምድሩን በሙሉ ምእመን አደረግኸው እኮ

   It is good to see all people to be follower of Jesus, unfortunately only few follow him, not you at this time.

   Delete
 12. ስለ መጽሐፈ መቃብያንና የቁርዓን ቃል ስምምነት

  ጸሐፊአችን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሆነውን መጽሐፈ መቃብያን ከቁርዓን አባባል ጋር እንደሚመሳሰል ማስረጃ አቅርቦ አስነብቦናል ፡፡ ከጸሐፊው የአገላለጽ ስሜት እንደገመትኩት ከሆነ ደግሞ ይኸ መጽሐፍ ከቁርዓን የተገለበጠ ወይም በከፊል የተወሰደ ለማለት የፈለገም መስሎኛል ፡፡ ክርስቲያን የሆነ ሰው እንዲህ ያለውን መረጃ ሲደርስበት ወይንም ሲኖረው ይኸ ምን ማለት ነው ? እንዴትስ ሊሆን ቻለ ? ለምንስ ሆነ ? ብሎ ትንሽ ራሱን ማስጨነቅ ይኖርበታል ፡፡ ይህን የቃል ስምምነት ስላገኘ ብቻ የመገላገል ያህል ዘርግፎልን ዞር አለ ፡፡

  ምናልባት አንዳንድ አንባቢ በመግለጫው እንዳይደነግጥ ወይንም በተባለው ግራ እንዳይጋባ በማሰብ ይህችን ማስታወሻ ልጽፍ ተገደድኩ ፡፡

  በዓለም ላይ ብዙ ተከታይ በማፍራት ከታወቁት ታላላቅ ሃይማኖቶች ሁለቱ ፣ ክርስትናና እስልምና ምንጫቸው የአይሁድ እምነት ስለሆነ እርስ በርሳቸው ከሞላ ጐደል በትምህርት ይጠላለፋሉ ወይም ይስማማሉ ፡፡ አንዳንዶች እንዲያውም የአይሁድ እምነት ፣ ክርስትናና እስልምና የአብርሃም እምነት ናቸው ብለው በአንድ ቃል ይጠቀልሏቸዋል ፡፡

  የክርስትና መጽሐፋችንም በብሉይ ኪዳን ስም የሚያስነብበን የአይሁድ እምነት የነበረውንና ከሞላ ጎደል የሆነውን ነው ፡፡ ጌታችንም እንደ ወገኖቹ የአይሁድ እምነት ተከታይ (ሉቃ 2፡43-46) ስለነበር ፣ ራሱን ለሕዝብ በይፋ እስከሚገልጽበት ድረስ ክርስትና ወይንም እስልምና የሚባል እምነት አልነበረም ፡፡ ለስም አጠራሩ ምስጋና ይግባውና ኢየሱስ ክርስቶስ በይፋ ወንጌል የማስተማር ተልዕኮውን ፈጽሞ በሞትና ትንሣዔ ሲደመድም ፣ ከሁለት ሺህ ዓመት በፊት የክርስትና ሃይማኖት ልደት ሆነች ፤ በሐዋርያት ስብስብም በአንጾኪያ ተመሠረተች (ሥራ 11፡26)፡፡ እንግዲህ የዚህን መነሻ ታሪክ ተከትሎ ነው የኢትዮጵያ ክርስትና ፊልጶስ ባጠመቀው ጃንደረባ የተጀመረውና ኋላም እነ አባ ሰላማ የወንጌል ትምህርቱን አስፋፉት የሚባለው ፡፡

  ቀደም በአይሁድ እምነት ልክ በአንድ አምላክ እያመነች መቆየቷ ፣ መጽሐፍ ቅዱስም ውስጥ ስሟ ከሌሎች አገሮች ይልቅ በብዛት ተጽፎ መገኘቱ ሁሉ ለምንጽፈውና ለታሪክ ምንጫችን እውነታነት አስረጅ ይሆናሉ ፡፡

  በዚሁ ድረ ገጽ “የኢትዮጵያ ኦርቶስዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክርስቲያን ታሪክ በአጭሩ በተሐድሶዎች እይታ”
  በሚል ርዕስ ቀርቦ ከነበር ጽሁፍ አሁን በቅርቡ ያነበብኩትንም ተመልከቱልኝ ፡፡

  1. በቋንቋ፣ በባህል፣ በታሪክና በመልካአ ምድር ከግብጽ ጋር ተቆራኝታ ለተገኘችው ለኑብያ ኢትዮጵያ ወንጌልን የሰበከላት ወንጌላዊው ፊልጶስ ነበር። በዚህች አገር ወንጌል በ34 ዓ.ም. ተሰበከ ቤተ ክርስቲያንም በ56 ዓ.ም.ተቋቋመች። በ1100 ዓ.ም. በሙስሊም ወራሪዎች ተደመሰሰች። በአሁንዋ ኢትዮጵያ የነበረች ቤተ ክርስቲያን ግን አልተደመሰሰችም።

  2 ሳባ ኢትዮጵያ የኛይቱ ፡- የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን ያስፋፋትና ወንጌልን የሰበከላት ግሪካዊው አባ ሰላማ ነው ዘመኑ ከ318-330 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ነው። በእርሱ የአገልግሎት ዘመንም መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ግእዝ ተተረጎመ ፤ ቤተክርስቲያንም በኢትዮጵያ መስፋፋት ጀመረች ..

  3. በመሐመድ አጎት በጃፋር መሪነት [600-800 ዓ.ም.] ከመሐመድ ዘመዶች 85 ያህሉ ሙስሊሞች በጥገኝነት ወደ ኢትዮጵያ ገቡ [በአርማህ ዘመን መሆኑ ነው] ፡፡ የእስልምና እምነትም በኢትዮጵያ በጥቂት አካባቢዎች ተጀመረ ፡፡

  ከዚህ በአጭሩ ከተጠቀሰው የታሪክ ቅደም ተከተል እንደምረዳው የመጽሐፍ መገለባበጥ ባህል ቢኖረን እንኳን የተገለበጠው አይሁድ ካጠፉት ወይንም ከሸሸጉት መጽሐፍ ይሆናል እንጅ ፣ የዘመን መለያየት ስላለ ከቁርዓን ሊሆን አይችልም ፡፡ እንዴት አንድ ሊሆኑ ቻሉ ለሚለው ጥያቄ ፣ የታሪክ አዋቂዎችና ተመራማሪዎች ሰፋ ያለ መልስ ቢሰጡበት ይመረጣል ፡፡ ቢሆንም ግን አሁን በቅርቡ የተገኘውን የቁፋሮ ውጤት እንኳን ምክንያት አድርገን ብንነሳ በድንበር አካባቢ ያሉ የአረብ አገሮች ከኢትዮጵያ አስተዳደር ጋር የታሪክ ትሥሥር (ሃይማኖትንም ይጨምራል) እንዳላቸውና ኢትዮጵያውያን በንግድና በሌላም ምክንያት ከነዚህም አገሮችም አልፈው እንደሄዱና እንደኖሩ አረጋግጧል ፡፡ እንዲህ ከተባለ ደግሞ ሰሞኑን ሰብአ ሰገል ለምን ኢትዮጵያውያኖች ናቸው ይባላል? ተብሎ የተጠየቀውን ፈተና ሁሉ ሊመልስልን ይችላል ማለት ነው ፡፡

  ስለ ችሮታው ሁሉ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቂቂቂቂቂ!
   መጀመሪያ መቃብያን ሰይጣን ከክብሩ የወደቀው ለአዳም አልሰግድም ስላለ ነው፤ ለሚለው መልስ አልሰጠህም። ቁርአን የመቃብያን ወንድም ሆኖ ያንኑ ሲመሰክር ሁለት ውሸታሞች ቢያደርጋቸው እንጂ ቀድሞ የዋሸው መቃብያንን ዘመኑ ብዙ ስለሆነ ከቁርአን የተሻለ አያደርገውም። ምን ትላለህ?

   Delete
  2. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 14, 2013 at 12:39 PM

   ምእመን

   who are you know? please! I can guess you are one of the top MK preachers.you are knowledge in both the old and new testaments and plus religious books concerning books. I don't have a fraction of the bible knowledge what you have, I only have faith the faith like my father Abraham had. I believe your knowledge is killing your faith and road to kingdom.

   Tell us your original real name, about me I am simple, nothing and original person.

   Also don't go around in order not to answer the question the person asked you. for me I don't worried about whether you answered it or not, my life book is only the holy bible.

   Delete
  3. ለAnonymous January 14, 2013 at 8:21 AM
   ደስታህን አልጠላሁትም ፡፡ ሳቅህ ሁሉ የልጄን ስለመሰለኝ እኔንም ሳላስበው አስቆኝ ምራቄ እስከሚተንነኝ ተጋራሁህ ፡፡ ለጠየከው ጥያቄ ከላይ በእኔ መታወቂያ ስም የተጻፈውን በሙሉ እያነበብክ ብትመጣ እዚህ እንደገና ግር አይልህም ነበር ፡፡ በሁለት ሺሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መጽሐፍ ቅዱስ ዕትም ለአዳም አልሰግድም የሚል ቃል የለውም ፡፡ አዳምን ከአእምሮህ አውጣው ፡፡ ሰይጣን አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ለዘላለም ይወድቃል ፤ ወደፊትም ሁሉ ይወድቃል ፡፡

   እስቲ አንተም ተጠየቅ ፤ ለመሆኑ ትንቢትን የምትረዳው አንተ በምን መልኩ ነው ፡፡ ወደፊት ይሆናል ብለህ የምትጠብቀውን ነው ወይንስ ያለፈን የተደመደመ ታሪክ ሁሉ?
   በተረፈ ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 14 ሙሉውን አንብብና ስለምን እንደሚናገር በምትችለው መጠን ተረዳው ፡፡ እኔ የትንቢት ተርጓሚ ስላልሆንኩ ፣ ጸጋውም ስላልተሰጠኝ እንዳላሳስትህ አልሞክረውም ፡፡

   ከላይ ያስቀመጥኩት የሁለት ሺሁን ግልባጭ መጨረሻው ላይ አንብበው ፡፡ ሌላ ማብራሪያ ከፈለግህ ግን ከላይ ጀምረህ ተመልከተው ፡፡ ሁሉንም አንብበህ የምትጠይቀኝ ካለ በምችለው ለማስተናገድ ፈቃደኛ ነኝ ፡፡ ሎጅክህ ደህና ነው ፤ ዓላማህ ለመማማር ከሆነ ግን በቁም ነገር መሃል ማሾፍን ተወው ፡፡ ምን ዓይነት ሰው እንደሆንክና እንደ ሆንኩ በአካል ሳንተዋወቅ በልጅነት ባህርያችን አንገላለጥ ፡፡ እንዲያ መሄዱ ማናችንንም አያስተምረንም ፡፡

   “እግዚአብሔር ያይደለህ አንተ ደካማ ሰው ሆይ! ለምን ትኰራለህ ? ዛሬ ሰው ነህ ፤ ነገም መሬትና ዐመድ ነህ ፤ በመቃብርህም ትልና ብስባሽ ትሆናለህ ፡፡ ዳግመኛም አንተንና የአንተን ሥራ የሚሠሩትን ሲኦል ትከተላቸዋለች ፤ የአንተ መምህር አባታችን አዳምን ስለ አሳተ የዐለምን ሁሉ ኀጢአት ወደ ራሱ የሚመልስ ሰብልያኖስ ነውና ፤ ራሱንም በማኩራትና ልቡናውን በማደንደን ለፈጣሪው ሥራ መስገድን እንቢ ብሏልና ፡፡ አንተም እንደ መምህርህ ለፈጣሪህ ለእግዚብሔር መስገድን እንቢ ብለሃል” ፡፡ መጽሐፈ መቃብያን ካልዕ 9፡1-4 ፤ ፳፻ ዕትም

   አክብረህ ስለጠየቅኸኝ አመሰግናለሁ ፡፡ ሰላም ሁንልኝ

   Delete
  4. ለየተሰቀለው
   የምጠቅም ሰው ስላልሆንኩ ማንነቴን ማወቅ አይረባህም ፡፡ ለሁላችንም የሚጠቅመን ምናልባት ተወያይተን ወደ አንድ ደረጃ ብንደርስ ነውና በዚሁ እንበርታ ፡፡

   ኢየሱስም ፤ ጸሐፊውን “በአእምሮ እንደ መለሰ አይቶ። አንተ ከእግዚአብሔር መንግሥት የራቅህ አይደለህም አለው።” ማር 12:34

   እንድታነብ የፈለኩት ሙሉ ታሪክ በማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 12፡28-34 ተጽፎ ይገኛል ፡፡ ኢየሱስ ሃይማኖትንና መጽሐፍ የሚያስተምሩንን መረዳትና ማወቅ የሚቃወም ቢሆን ፣ ይህን ተስፋ ለጸሐፊው ባልነገረውም ነበር ፡፡

   ችሎታው እያለህ ፣ ያለ እውቀት ከሆነ ፣ አማኝ የሆንከው ፣ ጊዜው የከፋ ነውና ጥሩ አይሆንም ፡፡ ነገ ደግሞ አንዱ ቆንጆ ምላሰኛ የሆነ ነገር እያስነበበ ይዞህ ወደ ሌላ እንደይነጉድ እፈራለሁ ፡፡ ይልቁኑ ያለችህን ትርፍ ሰዓት ሃይማኖትህን ለመረዳትና እውነትን ለማወቅ ተጠቀምባት ፤ ሰው በነገረህ ሳይሆን ፣ ከእግዚአብሔር ርዳታ ጋር በራስህ ወደ እውነቱ ለመድረስ ታገል ፤ መንፈስ ቅዱስ ስለሚያግዝህ በቶሎ ትመጣለህ ፡፡

   አማኝነቴ ሰው በሰበከኝና ባስነበበኝ ቢሆን ፣ እንደ ቀላዋጭ እስከ አሁን ስንቱ ቤት ገብቼ ከስንቱ በወጣሁ ነበር ፡፡ እግዚአብሔር ከእንደዛ መንገድ ስለጠበቀኝ ግን ፣ ይኸው እስከ ዛሬ ድረስ ከነድክመቴም ቢሆን ከተዋሕዶ እምነቴ ጋር ተጣብቄ እኖራለሁ ፡፡ ስለዛም ማወቄን አትንቀፈው ለማለት ፈልጌ ነው ፡፡ የምትታበይበት ዕውቀት ከሆነ ክፉ ነው ፡፡ የኔ ግን ለእንደዛ የዋለ አልመሰለኝም ፡፡ የሚነሰነስ ጭራም አልይዝም ፡፡

   Delete