Monday, January 14, 2013

ሰበር ዜና፦ ማንያዘዋል ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ እንዳይገባ በዐቃቤ መንበሩ ደብዳቤ መታገዱ ተሰማ

ጉዳዩ ወደ ተስፋዬ ውብሸትና እስክንድር ገ/ክርስቶስ ሳይዞር እንደማይቀር እየተነገረ ነው

የማቅ ቀኝ እጅ የሆነውና ማቅ በቤተ ክህነት ውስጥ የማይገባውን ከፍተኛ ቦታ እንዲያገኝ ትልቅ ሚና ሲጫወት የነበረው ማንያዘዋል ቤተክህነት ውስጥ እየፈጠረ ካለው ውስብስብ ችግር የተነሳ ወደዚያ እንዳይገባ መታገዱ ተሰማ፡፡ የታገደበት ምክንያት ለጊዜው ባይታወቅም ማቅ በፓትርያርክ ምርጫ ዙሪያ እያደረገ ባለው መጠነ ሰፊ ጣልቃ ገብነት ጋር ሳይያያዝ እንዳልቀረ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ማንያዘዋል የማቅ ድረገጾች ዋና የወሬ ምንጭ መሆኑ ሲታወቅ ባለፈው ግብጽ ሄዶ ሳለ ደጀሰላም የወሬ እጥረት አጋጥሟት አንደነበረ መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡ ማቅ ማን ያዘዋል ሙሉ ጊዜውን በምርጫው ላይ እንዲያደርግና የማቅን እጩ ጳጳስ ፓትርያርክ ለማድረግ እንዲሰራ በማሰብ ከቴዎሎጂ ምሩቃን ማህበር ገለል እንዲል ማድረጉን ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በማንያዘዋል የተጀመረው ይህ የደብዳቤ መጻፍ እርምጃ በአሁኑ ሰዓት ከማቅ ጎን በመቆም የማቅን አላማ ለማስፈጸም የሰራተኛ ህገ ወጥ ዝውውር በማድረግ ለማቅ ያልተመቹትን ሰዎች ከሞያቸውና ከትምህርታቸው ጋር ወደማይገናኝ ክፍል በማዛወርና በቦታቸው ለማቅና እርሱ ላጫቸው ጳጳሳት መመረጥ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ አቶዎችን በጠቅላይ ቤተ ክህነት ቁልፍ ቦታዎች ውስጥ በመሰግሰግ ለማቅ ያለውን ታማኝነት እያሳየ የሚገኘው ተስፋዬ ውብሸትና ባልደረባው እስክንድር ቀጣይ ደብዳቤ የሚጻፍባቸው እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡ ማንኛውም አይነት ዝውውር እንዳይደረግ መታገዱም ታውቋል፡፡ በዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር መረጃዎችን እየተከታተልን ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡   

13 comments:

 1. የትግራይ ጳጳሳት አንቀጽ 39ን ተጠቅመን የራሳችን ፓትርያርክ እንመርጣለን እያሉ ነው አሉ ። ይህን እንዴት ታዩት አላችሁ? ማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያላችሁን ውዝግብ አቁሙና ስለዚህ ሁኔታ ያላችሁን ሃሳብ ንገሩን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Kebede Bogale

   Ante malet wori lekakame politcagna nehe.

   Delete
  2. ማህበረ ቅዱሳን የተባለ የዝንጀሮ መንጋ ከቤተ ክርስቲያን ካልተወገደ የትግራይ ብቻ ሳይሆን እኛም የኦሮሚያና የደቡብ ህዝቦች የራሳችንን ፓትሪያርክ /አባት/ እንመርጣለን፡፡
   መብታችን ነው ፡፡

   Delete
  3. are u crazy? What do u mean? It is the Church in problem not a family or a single man. Do not you fear God?

   Delete
  4. AnonymousJanuary 14, 2013 at 9:13 PM

   ማህበረ ቅዱሳን የተባለ የዝንጀሮ መንጋ ከቤተ ክርስቲያን ካልተወገደ የትግራይ ብቻ ሳይሆን እኛም የኦሮሚያና የደቡብ ህዝቦች የራሳችንን ፓትሪያርክ /አባት/ እንመርጣለን፡፡
   መብታችን ነው ፡

   Bewnetu selemetaweraw neger menem atawkem! Endew letesatafinet yesafkew mehon alebet. Aweku beleh tsefehew kehone mechem betam aznelehalehu. Egziabher amlak ke chelema wede birhan endiyawetah tselote new!!!

   Delete
  5. AnonymousJanuary 15, 2013 at 12:14 PM
   AnonymousJanuary14,2013at9:13PM

   ማህበረ ቅዱሳን የተባለ የዝንጀሮ መንጋ ከቤተ ክርስቲያን ካልተወገደ የትግራይ ብቻ ሳይሆን እኛም የኦሮሚያና የደቡብ ህዝቦች የራሳችንን ፓትሪያርክ /አባት/እንመርጣለን፡፡መብታችንነው፡

   Bewnetu selemetaweraw neger menem atawkem! Endew letesatafinet yesafkew mehon alebet. Aweku beleh tsefehew kehone mechem betam aznelehalehu. Egziabher amlak ke chelema wede birhan endiyawetah tselote new!!!

   AnonymousJanuary 15, 2013 at 12:14 PM
   ስለ ጻፍኩት ነገር በጣም እርግጠኛ ነኝ ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ማህበር ናት ሌላ ማህበር አያስፈልገንም፡፡ ማህበረ ቅዱሳን/ አንድነት ፓርቲ/ በቤተ ክርስቲያኒቱ ጓዳ ተደብቆ እየበጠበጠን ነው ስለዚህ ማህበሩ መፍረስ አለበት፡፡
   ስለ ማ/ቅዱሳን ካላወቅክ ለማወቅ ጥረት አድርግ፡፡

   Delete

 2. ቀለለ
  ለእርሱማ እናተው ትበቃላችሁ። ዘረኝነት የእናንተ ጉዳይ ነው፤ አባ ሰላማ ከዘረኛ አስተሳሰብ በክርስቶስ ደም ተዋጁ ሰዎች የሚያዘጋጇት ብሎግ ትመስለኛለች፡፡ ስለዚህ ለአዲሱ ብሎጋችሁ ለሐራ ዘተዋህዶ ወይም ላረጀችዋ ደጀሰላም አስተያየቱን ብታካፍላቸው ሳይሻል አይቀርም፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. እርግጠኛ ነህ? አባ ሰላማን ዛሬ ይሆናል ማንበብ የጀመርከው እንጂ እንዲህ ለማለት አትደፍርም ነበር። አባ ሰላማማ ስለ ዘር አውርቶ መች ይጠግባል። ለምሳሌ የፅጌን የምንፍቅና መፅሃፎች ብታነብ ያለው ዘረኝነት በእጥፉ እዚህ ይገኛል።
   ለከበደ የዘሃበሻን በምርቃና የተፃፈ ፅሁፍ ማመንህ አስገራሚ ነው።

   Delete
  2. Men ergetegna yehonal "temeslegnalech" eko new yalew!! Selemayawkew neger be "meselegn" tibqena yekome meskin! Medhane alem aynun yabralet!

   Delete
 3. The only solution to fix the EOTC issue is to once and for all eliminate Mahibere Kidusan from the face of the earth. Mahibere Kidusan, aka Mahibere Seytan is disintegrating our church and holy fathers. Mahibere Kidusan is working on its hidden political agenda under the name of our holy church, very very sad. Believe or not, God will keep the church from the evil Mahibere Kidusan

  ReplyDelete
 4. አይ ማኔ አሁን የት ሄደህ ይሁን የምትልከሰከሰው?

  ReplyDelete
 5. እግዚኦ መሃረነJanuary 15, 2013 at 12:57 AM

  አባ ሰላማዎች አምላከ ቅዱሳን ከእናንተ ጋር ይሁን እና የብሎጋችሁ የዘወትር ተከታታይ ነኝ::
  እውነት ለመናገር ግን በአሁኑ ሰአት ትልቅ የቤተ ክርስቲያናችን ገጠመኝ ጉዳይ እያለ በዚህ ዙሪያ በመጻፍ፣ ሃሳቦችን በማፍለቅ እና በማንሸራሸር የተቻላችሁን መወጣት ሲገባችሁ ትልቁን እና ዋናውን ጉዳይ ወደ ጎን በማለት ማቅ ማቅ ማለታችሁን አልወደድኩላችሁም:: ስለ እናንተ ያለኝም አስተያየት እንዲሁ እየቀነሰ ነው::

  ReplyDelete
 6. Ase zerayokobe lege menew esume ende ayatu yebetekerstyan abatochen leysegedele asbo teneketobt yehonal. Yehe nefese geday leba metetena tenkwaye enkuwan ke betekrestian bete aganent enka megebat yelebetem.Keber Keber le abune Natnaeal.

  ReplyDelete