Thursday, January 17, 2013

የጉድ ሙዳዮች ሲኖዶስ የኢትዮጵያን ሕዝብ በሙሉ አሳዝኗል

የሁለቱ ሲኖዶሶች እርቅ የኢትዮጵያን ሁኔታ ይለውጣል ሰላም እና ልማት፤ መልካም አስተዳደር እርቅና ፍቅር ያመጣል የሚል ተስፋ ተጥሎበት ነበር። ቤተ ክርስቲያን አሁን ካለችበት ውስብስብ ችግር የመፈታት ተስፋ ይኖራታል ተብሎም ታስቦ ነበር። በተለይም ምዕመናን የዚህና የዚያኛው ከሚለው ክፍፍል የምናርፍበት ጊዜ መጣልን ብለው በተስፋ አድርገውት ነበር። ነገር ግን ተስፋው ባዶ፤ ብርሃኑም ጨለማ ሆኖ ተጠናቋል።
ድሮም የጉድ ሙዳዮች በሥጋ መንገድ ሲጓዙ ስናያቸው ከወዲሁ ውጤቱን አውቀነው ነበር። የእግዚአብሔርን ሥራ ይሠራሉ ብለን መጠበቅ ከተውን ረጅም ጊዜ ሆነን።  በመካከላቸው ያሉ ጤነኞች ብፁዓን አባቶች ከክፉው ጋር ተዋግተው ያሸንፉ እንደሆነ ብለን ትንሽ ተስፋ ነበረችን እንጂ ውጤቱን እናውቀው ነበር።
ጌታ በወንጌል "የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውስጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኩላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን? እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፣ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል፤ መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፤ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም‚ እንዳለ ማቴ 7፥15-18
ከመንፈሳዊ ሰው ፍቅር፣ ሰላም፣ ደስታ፣ ይቅርታ፣ የዋህነት፣ ደግነት፣ እራስን መግዛት የሚባሉ ፍሬዎች ይለቀማሉ፤ ከሥጋዊ ሰው ግን መልካም ሐሳብ ፈጽሞ አይገኝም። እንግዲህ ሕዝባችን ወደ ጌታ ቃል ዘወር ብሎ እግዚአብሔርን ከማዳመጥ ይልቅ በልዩነቱ ሲረጋገም እንዲኖር ዛሬ ተፈርዶበታል። እጅግ ያሳዝናል። ብፁእ አቡነ መርሐ ክርስቶስ ነቢይ ነበሩ ማለት ይቻላል፤ አቡነ ሳሙኤልና አቡነ አብርሃም ጵጵስና ሲሾሙ ጨርቃቸውን መቅደድ ነበር የቀራቸው ።ለረጅም ጊዜ ለቤተ ክርስቲያን ተሟግተው አረፉ። ይህ ያሁኑ ጊዜ ታይቷቸው ይሆን? ሲኖዶሱ በወሰነው መጥፎ ውሳኔ ኀዘናችን መራራ ነው።

3 comments:

 1. ድሮም የጉድ ሙዳዮች በሥጋ መንገድ ሲጓዙ ስናያቸው ከወዲሁ ውጤቱን አውቀነው ነበር። የእግዚአብሔርን ሥራ ይሠራሉ ብለን መጠበቅ ከተውን ረጅም ጊዜ ሆነን። በመካከላቸው ያሉ ጤነኞች ብፁዓን አባቶች ከክፉው ጋር ተዋግተው ያሸንፉ እንደሆነ ብለን ትንሽ ተስፋ ነበረችን እንጂ ውጤቱን እናውቀው ነበር።

  ReplyDelete
 2. የተሐድሶ ብሎጎች ተብለው በማቅና ደጋፊዎቹ የተሰየሙት ብሎጎች በሙሉ ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎች ጳጳሳት ቤተክርስቲያን ላይ የሚሰሩትን ደባ እየገለጹ፤ ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት የተነሱ መሆናቸውን በመረጃ አስደግፈው ሲጽፉ ምድረ የማቅ ቡችሎችና ጅል የቤተክርስቲያን ደጋፊዎች ሲቃወሟቸው ነበር። አሁን ግን እነዚያ የተሃድሶ ብሎጎች የተባሉት ሲጽፉ የቆዩት ነገር እውን ሲሆን እነሆ ታይቷል። ስለማቅ ሲጽፉ የቆዩትም ደግሞ ወደፊት የማቅ ገመና ሲገለጽ እንደሚታይ አልጠራጠርም። ያኔ ደግሞ የማቅ ደጋፊዎች ምን ሊሉ ይሆን?

  ReplyDelete
 3. ደርግ አቡነ ቴዎፍሎስን ከፓትርያርክነት ሲያወርድ
  በጊዜው ያሉ ጳጳሳት ደርግ ጋር ተባባሪዎች ነበሩ
  ደርግ አቡነ ቴዎፍሎስን ሲገል እንኵዋን በአደባባይ በቤተ ክርስቲን ፊት
  በግላቸው ተቃውሞ ወይም በግል ሃዘናቸውን የገለጹ አልነበሩም
  ደርግን አባሮ ስልጣን የያዘው TPLF በተራው የራሱ የሆነ የሚያዘው ፓትርያክ
  ሲፈልግ አራተኛውን ፓትርያክ አወረደ
  ይህን የማያውቅ ማናም የለም የዛሬዎቹ ያለብቃትና መንፈሳዊነት የጰጰሱ
  ይህን ይክዳሉ
  አራተኛውን ፓትርያክ በህመም ምክንያት ራሳቸውን አወረዱ እያሉ ዐይናቸው
  በጨው ታጥበው ይተርካሉ
  አራተኛውን ፓትርያክ አልወርድም አልታመምኩም ቢሉ
  TPLF በተራው ደርግ አቡነ ቴዎፍሎስን እንደገደለ እንደሚገላቸ ስለሚያውቁ ከአገር
  ወጡ
  ታመው ከስልጣን ወረዱ እያሉ በቤተ ክርስቲያን የሚዋሹ ከTPLF ጋር ተባብረው የሾሙት ፓትርያክ
  ታመው ሞቱ
  ታመዋል የተባሉት በሕይወት አሉ
  እነዚህ ሃሰተኛ ሳይገባቸ የጰጰሱ ቅዱስ ዳዊት እንዳለው
  መዝሙረ ዳዊት መዝሙር 2
  4 በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቃል፥ ጌታም ይሣለቅባቸዋል።
  5 በዚያን ጊዜ በቍጣው ይናገራቸዋል፥ በመዓቱም ያውካቸዋል።

  ReplyDelete