Friday, January 18, 2013

ሰበር ዜና፦ በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ የወቅቱን የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ አስመልክቶ ሰፋ ያለ መግለጫ አወጣ

በ4ኛው ፓትርያርክ በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሚመራውና በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ ከጥር 7-9 ቀን 2005 ዓ/ም በሎስ አንጀለስ ከተማ አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ አካሂዶ  ሰፋ ያለ መግለጫ አወጣ። መግለጫው አዲስ አበባ የሚገኘው ሲኖዶስ በቅርቡ ላወጣው መግለጫና የ 6ኛ ፓትርያርክ ሹመት መልስ ይሰጣል፤ የተወሰነውም የ 6ኛ ፓትርያርክ ሹመት ተገትቶ ለሰላምና ለአንድነት ቅድሚያ እንዲሰጥ ጥሪም ያስተላልፋል።

ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፦ መግለጫ6 comments:

 1. እንግዲህ እግዚአብሔር የሚሠራውን ብቻ እንጠብቅ ፤ ሰዎች እንኳንስ ያሰብነውንና የተመኘነውን የተናገርነውንም ሊያሳኩልን አልቻሉም ፡፡ ቢያንስ በውጭ ያለችዋ ቤተ ክርስቲያን ከሦስት መሆኗ ቀርቶ በአንድ የምትጠቃለልበት መንገድ እንኳን ቢፈለግ ለእኛ የሚሆን ትልቅ ካሣ ነው ፡፡ አሁን ኢትዮጵያ ካለው መከፈሉ ብቻ ሳይሆን ፣ በስደት ያለውም ቢሆን ራሱ አንድነት ማጣቱ ያሳስባል ፡፡ ያንን አንድነት ለመፍጠር ከባድ ርብርቦሽ ያስፈልጋል ፡፡ ልዩነቱ ከምን መነጨ ከሚል ጥያቄ በመነሣት መፍትሄ የሚሆኑትን በሙሉ መቃኘትና ለማዋሃድ መሥራቱ መልካም ይሆናል ፡፡ የዶግማ ልዩነት ሳይኖር ቤተ ክርስቲያን መከፈሏ ፣ ከመንፈሳዊነቷ ይልቅ ምድራዊነቷ ገዝፎ ወጥቷል ለማለት ያስደፍራል ፡፡ እግዚአብሔር ሊያስተምረን ያቀደው ይሆናልና በጸሎት መበርታቱና በእምነት መጽናቱ አማራጭ የማይገኝለት መፍትሄ ነው ፡፡
  እግዚብሔር ይህችን ቤተ ክርስቲያንና መንጋውን ይጠብቅ ፡፡ አሜን

  ReplyDelete
 2. ልክ ነው ብዙዎቻች እናውቃለን

  የአዲሳባው ጎረምሳ ጳጳሳት ነን ባዮች ቀጣፊዎች የሚታዘዙት
  መንፈስ ቅዱስን ሳይሆን ስልጣን የያዘውን TPLF ን ነው

  ደርግ አቡነ ቴዎፍሎስን ከፓትርያርክነት ሲያወርድ
  በጊዜው ያሉ ጳጳሳት ደርግ ጋር ተባባሪዎች ነበሩ
  ደርግ አቡነ ቴዎፍሎስን ሲገል እንኵዋን በአደባባይ በቤተ ክርስቲን ፊት
  በግላቸው ተቃውሞ ወይም በግል ሃዘናቸውን የገለጹ አልነበሩም
  ደርግን አባሮ ስልጣን የያዘው TPLF በተራው የራሱ የሆነ የሚያዘው ፓትርያክ
  ሲፈልግ አራተኛውን ፓትርያክ አወረደ
  ይህን የማያውቅ ማናም የለም የዛሬዎቹ ያለብቃትና መንፈሳዊነት የጰጰሱ
  ይህን ይክዳሉ
  አራተኛውን ፓትርያክ በህመም ምክንያት ራሳቸውን አወረዱ እያሉ ዐይናቸው
  በጨው ታጥበው ይተርካሉ
  አራተኛውን ፓትርያክ አልወርድም አልታመምኩም ቢሉ TPLF በተራው ደርግ አቡነ ቴዎፍሎስን እንደገደለ እንደሚገላቸ ስለሚያውቁ ከአገር ወጡ ታመው ከስልጣን ወረዱ እያሉ በቤተ ክርስቲያን የሚዋሹ ከTPLF ጋር ተባብረው የሾሙት ፓትርያክ ታመው ሞቱ
  ታመዋል የተባሉት በሕይወት አሉ

  እነዚህ ሃሰተኛ ሳይገባቸ የጰጰሱ
  ቅዱስ ዳዊት እንዳለው
  መዝሙረ ዳዊት መዝሙር 2
  4 በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቃል፥ ጌታም ይሣለቅባቸዋል።
  5 በዚያን ጊዜ በቍጣው ይናገራቸዋል፥ በመዓቱም ያውካቸዋል።

  ReplyDelete
 3. my brothers and sisters in Christ,
  I think our Lord Jesus Christ wants to clean up our church from these an unlawful and unfaithful leaders( bishops and archbishops. but let us do our job. we have to be united and we have to stand together against them. as you know, we are the church and we are also for the church and we have to protect our mother Church. From the Mafia young bishops of Addis Ababa, believe it or not , they do not have any poetical interest; except the desire of power and money. I do know them, they are thinking earthly thinks not heavenly. even they are against the Government. Remember, what they had done last year and before these young mafia and they had been straggling against their father the one who anointed them . Now i am asking you all my friends,we have to stand together against them. you know, we have a right to call peaceful demonstration by taking the right of the Constitution of Ethiopia. I think enough is enough.

  ReplyDelete
 4. I am really sad about their decision there. However I had some understanding about 18 bishops and archbishops strongly dis-agree the decision. Therefore, I was thinking the legal synod would give credit for those who tried to raise their voice.

  ReplyDelete