Sunday, January 20, 2013

ቃና ዘገሊላ የማን ክብር የተገለጠበት በዓል ነው?


ትናንት በጥምቀት በዓል አንዳንድ ወጣቶች በለበሷቸው ቲሸርቶች ላይ ጥምቀትን የተመለከቱ ጥቅሶች አንብቤአለሁ፡፡ የወንጌልን ቃል በሚታይ ቲሸርት ላይ ሳነብ እጅግ ደስ ብሎኛል፡፡ አንዱ ወንጌልን የምንሰብክበት መንገድ ይህ ነውና፡፡ አንዳንዶቹን ጥቅሶች ሳይ ግን በጣም «ሾክድ» አድርገውኛል፡፡ በተለይ የአምላክ ክብር ለማርያም ተሰጥቶ ስመለከት በጣም ነው የደነገጥኩት፡፡ ይህች ቤተ ክርስቲያን በቃ ሰው የላትም ማለት ነው? ስልም ቆዝሜያለሁ፡፡

አምላክ፣ ጌታ፣ ፈጣሪና የሕይወት ውሃ ምንጭ እርሱ እግዚአብሔር እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ ያለ እውቀት በሆነ ባዶ ሃይማኖታዊ ቅናት የተነሳሱ አንዳንድ ወጣቶች በዘንድሮው የጥምቀት በዓል በለበሱት ቲሸርት ላይ «ማርያም የሕይወት ውሃ ምንጭ ናት» የሚል ጽፈዋል፡፡ በድጋሚ በጣም «ሾክድ» የሚያደርግ ነው። እነዚህን መንፈሳዊ እውቀት የሌላቸው ባዶ ቀናተኞችና ከእግዚአብሔር ይልቅ ማርያምን የሚያመልኩ ወጣቶች «አቤቱ፥ የእስራኤል ተስፋ ሆይ፥ የሚተዉህ ሁሉ ያፍራሉ፤ ከአንተም የሚለዩ የሕይወትን ውኃ ምንጭ እግዚአብሔርን ትተዋልና በምድር ላይ ይጻፋሉ።» ኤር. 17፡13 ከማለት በቀር ምን ይባላል?

ለመሆኑ የዚህ በዓል ባለቤት ማነው? የቤተ ክርስቲያን ትምህርት እንደሚያስረዳው ጥምቀትና ቃና ዘገለላ የጌታ በዓላት ናቸው፡፡ ጥምቀት ከአበይት በዓላት አንዱ ሲሆን ቃና ዘገሊላ ደግሞ ከንኡሳን በዓላት መካከል ይመደባል፡፡ (የቤተክርስቲያን ታሪክ ከአባ ጎርጎርዮስ ገጽ 109 እና 115)፡፡ ሃይማኖተኛ ጽንፈኛነት የወለደው አዲሱ ትውልድ ሃይማኖቱን በመጽሐፍ ቅዱስና በቤተክርስቲያን ትምህርት ላይ ሳይሆን በስሜታዊነት ላይ ስለመሰረተ በቤተክርስቲያን ያልነበረና ከዚህ ቀደም ተሰምቶ የማያውቅ አዲስ ትምህርት እያስፋፋ ይገኛል፡፡ ተው የሚለው ስለጠፋም ሁሉ በመሰለው መንገድ እየተጓዘ ይገኛል፡፡ የእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና፣ ለእርሱና ለሥራው መታሰቢያነት የተወሰኑ በዓላትን ሁሉ ለሌሎች እየሰጠ ቤተክርስቲያናችንን የአምልኮ ጣኦት መናኸሪያ እያደረጋት ይገኛል፡፡ ሰው የእግዚአብሔርን ክብር ለሌላ ከሰጠ እኮ ጣኦት አምላኪ ነው፡፡

የቃና ዘገሊላ ተአምር እንዲታሰብበት ጥር 12 ቀን የበዓል ቀን ሆኖ ተሠርቷል፡፡ በዓሉ የጌታ በዓል ነው፡፡ ውሃውን ያለማንም ጣልቃ ገብነት ወደ ወይን የለወጠውም ብቻውን ተአምራትን የሚያደርገው ጌታ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በተለይ ቃና ዘገሊላ የጌታ በዓል መሆኑ እየተረሳና የማርያም በዓል እየሆነ መጥቷል፡፡ እኔም የዚህ በዓል ባለቤት ማነው? ብዬ እንድጠይቅ ያደረገኝ ይህ ነው።

በሰርጉ ላይ ታድማ የነበረችው እመቤታችን ማርያም በሰርጉ የታደመውን ልጇን ጌታ ኢየሱስን «የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም» ብላ በነገረችው ጊዜ ጌታ «አንቺ ሴት ካንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም» በማለት ነበር የመለሰላት፡፡ ሲጀመር የእርሷ ጥያቄ ምልጃ ነው ወይ? ምልጃ ነው ለማለት የሚያበቃ ነገር በጥያቄዋ ውስጥ አናይም፡፡ የልጇን ሁሉን ቻይነት አምና የሰነዘረችው ጥያቄ አድርገን ልንወስደው ግን እንችላለን፡፡ ከእርሷ ጥያቄ ይልቅ ጌታ ለጥያቄዋ ጌታ የሰጠው ምላሽ አስገራሚና የተለያዩ ጥያቄዎችን የሚያጭር ነው፡፡

በቅድሚያ እናቱን እናቴ በማለት ፋንታ «አንቺ ሴት» ብሎ በማክበር ቃል ግን ደግሞ የሩቅ ሰውን በሚያናግሩበት መንገድ መጥራቱ ያስገርማል፡፡ እርሱ የመጣው ለዓለም ሁሉ እንጂ በስጋ ዝምድና ለሚቀርባቸው እንዳልሆነ ያሳየበት አጋጣሚ ነው፡፡ ተመሳሳይ መልእክቶችን ያስተላለፈባቸው ሌሎች አጋጣሚዎችም አሉ።
«ባዩትም ጊዜ ተገረሙ፥ እናቱም። ልጄ ሆይ፥ ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ፥ አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን አለችው። እርሱም፦ ስለ ምን ፈለጋችሁኝ? በአባቴ ቤት እሆን ዘንድ እንዲገባኝ አላወቃችሁምን? አላቸው። እነርሱም የተናገራቸውን ነገር አላስተዋሉም።» ሉቃ. 2፡48-50

«ገናም ለሕዝቡ ሲናገር፥ እነሆ፥ እናቱና ወንድሞቹ ሊነጋገሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር። አንዱም። እነሆ፥ እናትህና ወንድሞችህ ሊነጋገሩህ ፈልገው በውጭ ቆመዋል አለው። እርሱ ግን ለነገረው መልሶ፦ እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው? አለው። እጁንም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዘርግቶ። እነሆ እናቴና ወንድሞቼ፤ በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነውና አለ።» ማቴ. 12፡46-50

ጌታ እንዲህ ያደረገበትን ምክንያት ያኔ እመቤታችን እንዳላስተዋለች ሁሉ (ሉቃስ 2፡50) ዛሬም ብዙዎቻችን አናስተውልም፡፡ ጌታ እናቱን አንቺ ሴት ያላት እንዲህና እንዲያ ለማለት ፈልጎ ነው ብለን ነገሩን በእኛ ፍላጎት መሰረት ለመንዳት እንፈልጋለን፡፡ ይህ ትክክል አይደለም፡፡ በሩቅ ሰው አጠራር እንዲሁም በአክብሮት ቃል መጥራቱ ግን እውነት ነው፡፡

«ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?» መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ የተባሉ ብዙዎች ወንዶች አሉ፡፡
«እርስዋም ኤልያስን፦ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? ኃጢአቴንስ ታሳስብ ዘንድ፥ ልጄንስ ትገድል ዘንድ ወደ እኔ መጥተሃልን? አለችው።» 1ነገ. 17፥18
«ኤልሳዕም የእስራኤልን ንጉሥ እኔ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? ወደ አባትህና ወደ እናትህ ነቢያት ሂድ አለው። የእስራኤልም ንጉሥ አይደለም፥ በሞዓብ እጅ ይጥላቸው ዘንድ እግዚአብሔር እነዚህን ሦስት ነገሥታት ጠርቶአል አለው።» 2ነገ 3፥13
«እርሱም፦ የይሁዳ ንጉሥ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? በምዋጋበት በሌላ ቤት ላይ ነው እንጂ በአንተ ላይ ዛሬ አልመጣሁም እግዚአብሔርም እንድቸኵል አዝዞኛል ከእኔ ጋር ያለው እግዚአብሔር እንዳያጠፋህ ይህን በእርሱ ላይ ከማድረግ ተመለስ ብሎ መልእክተኞችን ላከበት።» 2ዜና 35፥21
«በታላቅ ድምፅም እየጮኸ። የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? እንዳታሠቃየኝ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ አለ፤» ማር. 5፥7
«ኢየሱስንም ባየ ጊዜ ጮኾ በፊቱ ተደፋ በታላቅ ድምፅም። የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? እንዳትሣቀየኝ እለምንሃለሁ አለ።» ሉቃ. 8፥28  

ከሴቶች መካከል እንዲህ የተባለች ሴት ግን ድንግል ማርያም ናት፡፡ አረፍተ ነገሩ በሁሉም ጥቅሶች ውስጥ  ተመሳሳይ ሐሳብ ነው የሚያስተላልፈው፡፡ ለእመቤታችን የተሰጣትን ምላሽ ስንመለከት «ጥያቄሽን ላለመመለስ ከአንቺ ጋር ምንም ችግር የለብኝም» የሚል መልክት አለው፡፡ ለዚህ ምክንያቱ «ጊዜ ገና አልደረሰም» የሚል ነው፡፡ ይህም ጥያቄዋ በእርስዋ ጊዜ ተቀባይነት እንዳላገኘ ያስረዳል፡፡ ስለዚህ ከጌታ የተሰጣትን ምላሽ ተከትላ እርሷ «ለአገልጋዮቹ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ» የሚል መልእክት አስተላለፈች፡፡ ጌታም በራሱ ጊዜ ጋኖቹን ውሃ ሙሉአቸው ብሎ ውሃውን ወደ ወይን ጠጅ ለወጠ፡፡

በቅድሚያ ጌታ ወደ ሰርጉ ተጠርቶ የታደመ ቢሆንም በዚያ የተገኘው ክብሩን ለመግለጥ እንደ ነበር ግልጽ ነው፡፡ የሀዋርያው ዮሐንስ ትኩረት የሰርጉ ሁኔታና የማርያም ጥያቄ ወዘተርፈ ሳይሆን የጌታ ክብር መገለጥ ነው፡፡ በሰርጉ ታሪክ መጨረሻ ላይ የተላለፈውም ይኸው መልእክት ነው፡፡ ዛሬ ሰዎች በስሜት ተነድተው እንደሚሉት የማርያም አማላጅነት ተገለጠ አላለም፡፡ «ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።» ዮሐ. 2፡11፡፡ የዚህ ክፍል ዋና መልእክት የኢየሱስ ክብር ማለትም መሲሕነቱና ወልደ እግዚአብሔርነቱ መገለጡ ነው፡፡ ይህም በዮሐንስ ወንጌል ዘገባ መሰረት የመጀመሪያው ተአምር ተብሏል፡፡ ከዚህ ተአምር የተነሳ ደቀ መዛሙርቱ በእርሱ አምነዋል፡፡ ስለዚህ የውሃው ወደ ወይን መለወጥ ስለማርያም ምልጃ የሚናገር ሳይሆን የኢየሱስን ክብር መገለጥ የሚያበስር ነው፡፡ ይህ ክፍል ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የዮሐንስ ወንጌል የተጻፈበት አላማ ምን እንደሆነ ራሱ ዮሐንስ ይነግረናል፡፡ «ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤ ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል።» ዮሐ. 20፡30-31
ይሁን እንጂ የእግዚአብሔር ቃል ከሚናገረው አልፈው የሄዱና የራሳቸውን ሐሳብ የሚያራምዱ ሰዎች ያልተጻፈ ታሪክ በማንበብ ስተው እያሳቱ ይገኛሉ፡፡ የጌታ በዓል የሆነውን ቃና ዘገሊላን ለማርያም በመስጠት ተአምር ሰሪው ጌታ ሳይሆን ማርያም ጎልታ እንድትታይ እያደረጉ ነው፡፡ ወጣቶቹ ምን ያድርጉ ሊቃውንቱ ስህተቶችን በጊዜው ማረም ሲገባቸው የሐሰት ትምህርት ብዙ ደቀመዛሙርትን ስላፈራ ለስህተት ትምህርት ድጋፍ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡  ከዚህ ቀደም በአንድምታ ወንጌል ሊቃውንት ዘንድ በግእዝ ወንጌልም ላይ ያልተሰጠ ርእስ በአቡነ ጳውሎስ ዘመን በታተመው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ለዮሐንስ ወንጌል ምእራፍ 2 «ስለ እናቱ ምልጃ» የሚል ርእስ በመስጠት ይህ ሀሰት እንዲነግስ ተደርጓል፡፡ የዚህ ዳርዳርታው ቃና ዘገሊላ የማርያም በዓል ነው ወደሚል ጫፍ እየወሰደን ሳይሆን አይቀርም፡፡ ታዲያ ቃና ዘገሊላ የማን በዓል ነው?    
   
ከጸጋ ታደለ

72 comments:

 1. It is not fair to discount the role of Saint Mary in the miracle that Jesus did. She certainly interceded for that miracle to happen. Who asked Jesus to help the family that was facing big embarrassment? Please tell the truth, instead of distorting it. When He said "gezeye gena neew," He was referring to the day when He was going to give us the true Wine that gives eternal life.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ጥር 12 ቀን 2005 ዓ.ም
   “ጌትነቱን ገለጠ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ” እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የበዐላት አከባበር ቀመር ከበዓለ ልደት ፤ግዝረት፤ ጥምቀት ቀጥሎ ቃና ዘገሊላ ይከበራል፡፡ ምክንያቱም ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን አምላካችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ለማዳን ወደዚህ ዓለም በመጣበት ወቅት ልዩ ልዩ የሆኑ ድንቅ ተአምራት አድርጓል፡፡ ከእነዚህም የመጀመሪያው በቃና ዘገሊላ በሰርግ ቤት ተገኝቶ ያደረገው ተአምር ተጠቃሽ ነው፡፡

   ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ እንዲህ ጽፎታል፡፡ “በሦስተኛው ቀን በገሊላ ቃና ሠርግ ሆነ” ምን በሆነ በሦስተኛው ቀን የሚል ጥያቄ በሁላችንም እዕምሮ እንደሚመላለስ አያጠያይቅም፡፡ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማየ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ ጥር 11 ቀን ተጠምቆ ሳይውል ሳያድር ዕለቱን ገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ አርባ መዓልትና አርባ ሌሊት ጾሞ ፤ዲያብሎስን ድል ነስቶ፤ መዋዕለ ጾሙን ፈጽሞ ለእኛም ዲያብሎስን ደል የምንነሳበትን መንገድ አሳይቶን ከገዳመ ቆሮንቶስ ወጥቶ ደቀ መዛሙርቱን መረጠ፡፡ ከጥር ሃያ እስከ የካቲት ሃያ አርባ ቀን ይሆናል፡፡ መዋዕለ ጾሙን የካቲት ሃያ ፈጽሞ በወጣ በሦስተኛው ቀን ገሊላ አውራጃ ቃና በተባለች መንደር ሠርግ ሆነ፡፡ በዚህ ሠርግ ብዙ ሰዎች የታደሙ መሆኑን የወይን ጠጁ ማለቅ ያስረዳል፡፡ በእርግጥም የተጠሩት ሰዎች ብዙ ቢሆንም ብዙዎች መመገብ የሚችል አምላክ በሠርግ ቤት መጠራቱ ልዩ ያደርገዋል፡፡ በዚህ ሠርግ ከሠዎች በተጨማሪ ሦስት አካላት ተጠርተዋል፡፡

   1. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

   “ወሀለወት ህየ እሙ ለእግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ” የጌታ እናት ከዚያ ነበረች እንዲል እንዲያው ዝም ብሎ አይደለም፡፡ በደግ ሰው ልማድ ተጠርታ እንጂ እመቤታችን በማኅበራዊ ሕይወት የነበራትን ተሳትፎ እና በሰዎች ዘነድ የነበራትን ተዋቂነት ያመለክታል፡፡ በሌላ መልኩ በቤተ ዘመድ ልማድ ማንኛውም ዘመድ እንደተጠራው ሁሉ እርሷም በገሊላ በነበሩት ሰዎች ዘንድ ታላቅና ተዋቂ ስለበረች እና ቤተ ዘመድ በመሆኗ በዚህ ሠርግ ተጠርታ ነበር፡፡የተገኘችው የሰው ሰውኛው ይህ ቢሆንም በዚያ ሠርግ ቤት ማንም ሊሠራው የማይችል የሥራ ድርሻ ነበራት፡፡ይህ በሰዎች ዘንድ የማይታወቅ በእግዚአብሔርና በእርሷ መካከል ያለ አማላጅነት ነው፡፡ የጎደለውን መሙላት ለሚችል ውድ ልጇ የጎደለውን እንዲሞላ ማማለድ ነው ፡፡ እመቤታችን ከሰው ልጆች የተለየች ክብርት ቅድስት ንፅህት ልዩ በመሆኗ የምታውቀውም ምሥጢር ከሰው የተለየ ነው፡፡ “ወእሙሰ ተአቀብ ዘንተ ኩሎ ነገር ወትወድዮ ውስተ ልበ” ማርያም ግን ይህንን ሁሉ ትጠብቀው በልቧም ታኖረው ነበር ሉ.2፤19 ይህን ሁሉ ያለው ድንግል ማርያም አምላክን በመውለዷ ከሰው ልጆች የራቀ ምስጢር የተገለጠላት መሆኑን ያስረዳል፡፡ ይህንን ሁሉ ብሎ እንደ ሸማ ጠቅልሎ እንደ ወርቅ አንከብሎ የተናገረው የተገለጠላት ምስጢር በሰው አንደበት ተነግሮ የማያልቅ እንደሆነ ነው የሚገልጠው፡፡ ምክንያቱም አንድ ሁለት ብለን የምንቆጥረው አይደለምና መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እንደዚሁ “ፀጋን የተሞላሽ” በማለት የገለጠው ለእርሷ የተሰጠው ባለሟልነት ልዩ መሆኑን ለማስረገጥ ነበር፡፡ ከዚህ የተነሳ በሠርጉ ቤት የምትሰራውን ሥራ በውል ታውቅ ነበርና፡፡

   Delete
 2. ክርስቶስ የሕይዎት ውሀ ምንጭ ነው? ወይስ አይደለም ? እኔ ነው እላለሁ። ታድያ ክርስቶስ ሰውና አምላክ በተዋሕዶ አንድ ባኅርይ ነው ወይስ አይደለም ? እኔ ነው እላለሁ። ታድያ የሰውነቱ ምንጭ ከማን ተገኘ ? ''ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነብሷ ነብስን ነስቶ በሥጋዌ ተወለደ'' ብየ አምናለሁ። ታድያ አመክንዮ ክርስቶስን ሕይዎት ፥ እናቱን የሕይዎት ምንጭ ማለቱ ችግሩ ምንድን ነው ? እስቲ ለኔ ላንድ ምዕመን ይህን ጥያቄ መልሱ ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. እሄን ከማለቴ በፊት ልክ እንደርስዎ አስቤ ነበር እና በእውነቱ ሊያምንበት የሚያረጋግጥለትን ግልጽ እና ቀላል በሆነ መንገድ ነግረውታል። ያስቸገረ መስሎት ይጠቀስልኝ ማለቱ ግን አይቀርም እና ጥቅስ ብቻ ሳይሆን መጽሐፉን እንዲያነብ ደግሞ ቢመክሩት ይጸድቃሉ። አለበለዚያ አንድ ጥሩ ሰው ለሌላው በዋለው ውለታ እናቱጋ ሂዶ እርሱን የወለዱ እርሶ የተባረኩ ኖት በእርስዎም ችግሬ ተወገደ ብሎ አጥብቆ ቢያመስግንና ጥሩ ቀሚስ ቢያለብሳቸው፣ አጂሬው ደግሞ የእናትየዉን ቀሚስ ነጥቆ ውለታ የሠራው ልጆት ነው ብሎ ሙልጭ አድርጎ ሰድቦ ቀሚሱን ለልጃቸው ሊያለብስ ነው ማለት ነው። እሄ ነው ክህደት እና አለማመን የሚባለው።

   Delete
  2. Bible lai ke segawa seega ke nefesua nefes tebelo yetetsafewu yet bota newu Ato Kebede? Esti verse kale yengerun

   Delete
 3. ምንባቡ ሁለት ዋና ጉዳዮችን ማዕከል አድርጎ ያጠነጥናል ፡፡ አንደኛው ድንግል ማርያም ለምን የሕይወት ውኃ ምንጭ ተባለች የሚል ሲሆን ሌላው ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም አታማልድም የሚል መደምደሚያ ለመድረስ ብዙ ቦታ ረግጧል፡፡ ሁለቱንም ርዕሶች ጨፍልቀን እንመልከት ብንል ደግሞ በቅድስት ድንግል ማርያም ላይ የቀረበ የተቃውሞ አቤቱታ ሆኖ እናገኘዋለን ፡፡ በወጋችን የተባለውንም ስናክተው ደግሞ ፣ አባቶች ልጆችን ለምን አይቆጡም በሚል ሰበብ ፣ ለእመቤታችን የሚቀርበው ቅዳሴ ሁሉ መከለስ ፣ መቀየር ወይም መደምሰስ አለበት የሚል የማመልከቻ ግልባጭ ሆኖ እናገኘዋለን ፡፡

  1. በቅድሚያ የጌታችንን ሕይወትነት የሚገልጹ ኃይለ ቃሎችን እንመለከታለን
  - ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ ፤ ዮሐ 14:6
  - የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ ። ዮሐ 6:48
  - ኢየሱስም። ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ ፤ ዮሐ 11:25
  - በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች። ዮሐ1:4

  ከእነዚህ ኃይለ ቃሎች የምንረዳው ሕይወት እርሱ ራሱ ኢየሱስ እንደሆነ ነው ፡፡ ምክንያቱም ትንሣኤና ሕይወት ፣ መንገድና ሕይወት ፣ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ ብሏልና ፡፡ ይህን የምንቀበል ከሆነ ደግሞ በቀላል አመክንዮ ኢየሱስን የወለደች ቅድስት ድንግል ማርያም ፣ ለጌታችን በሥጋ መገኛነት ፈጣሪዋን አገልግላለችና ፤ ከርሷ በመገኘቱ ሳቢያ ምንጭ ብትባልለት መግለጫውን ወይም የወንጌልን መልዕክት አይቀይርም ፡፡

  ኢየሱስ === ሕይወት ሰጭ ፣ የሕይወት ውኃ ፣ ሕይወት
  ቅድስት ድንግል ማርያም --> ኢየሱስ ፤ ኢየሱስ ደግሞ --> ሕይወት ወይም የሕይወት ውኃ
  ስለዚህም ቅድስት ድንግል ማርያም --> የሕይወት ውኃ ምንጭ

  ቅድስት ድንግል ማርያም ኢየሱስን በሥጋ አካሉ አስገኘች ፤ ኢየሱስ ደግሞ ሕይወታችን ወይም የሕይወታችን ውኃና እንጀራ ነውና ፣ ቅድስት ድንግል ማርያም የሕይወት ውኃ ምንጩ መገኛው ናት ብትባል ስህተት ነው አያሰኝም ለማለት ፈልጌ ነው ፡፡

  ቅዳሴአችንም በማርያም ቅዳሴ ቁጥር 9 “ኦ ማርያም በእንተዝ ናፈቅረኪ ወናዐብየኪ እስመ ወለድኪ ለነ መብልዐ ጽድቅ ዘበአማን ወስቴ ሕይወት ዘበአማን”
  ትርጉም “ማርያም ሆይ ስለዚህ እንወድሻለን ከፍ ከፍም እናደርግሻለን ፤ እውነተኛ የጽድቅ መብልንና እውነተኛ የሕይወት መጠጥን ወልደሽልናልና”

  በቁጥር 93 ደግሞ “ኦ ጽዋዕ እንተ እምኔኪ ለእለ ይሰትዩ እምኔሁ በአሚን ዘያጐሥዕ ጥበበ ወይሁብ ሕይወተ”
  ትርጉም “ወዮ ከአንቺ የተገኘ ጽዋ በማመን ከርሱ ለሚጠጡ ሰዎች ጥበብን የሚገልጽ ሕይወትንም የሚሰጥ ነው” ይላል ፡፡

  2. የድንግል ማርያም አማላጅነትን በተመለከተ
  እንደ መጽሐፍ ቃል
  ቅድስት ድንግል ማርያም በመልአኩ ገብርኤል አማካኝነት ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ፣ ጌታ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው የተባለችና የተመሰከራላት ሴት ናት (ሉቃ 1፡28) ፡፡ ይኸ ሲባል ደግሞ አብ ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ሕይወቷን ይመሩላታል ፤ ከክፉ ሁሉ ይጠብቋታል ፣ ሁኔታዎችንና ሥውር ጉዳዮችን ይገልጹላታል ያሰኛል ፡፡ ለዚህ አስረጅ የሚሆነው ደግሞ ፣ ማንም ሰው ሳይነግራት ወይም ሳያሳስባት የወይን ጠጅ ማለቁን በራሷ ማወቋ ፤ እንዲሁም ደግሞ ከዛች ዕለት በፊት አንድም ተአምር አሳይቶ የማያውቀውን ልጅዋን ወዲህም ፈጣሪዋን ፣ ተአምር እንደሚያደርግ በመንፈስ ተገንዝባ ወይም ተረድታ የወይን ጠጅ አልቆባቸዋልና ብላ ርሱን መጠየቋ ነው ፡፡

  ባትጠይቀው ኖሮ ርሱ ራሱ በገዛ ፈቃዱ ያደርገው ነበር ወይ ? አዎ! ምንም ጥርጥር የለውም ፡፡ ምክንያቱም ጊዜዬ ሳይደርስ ማለቱ የወይን ጠጁ እንደሚያልቅባቸው ማወቁንና ድንቅ ሥራውን ሊያሳይ እንዳቀደ ወይም እንደተዘጋጀ ያመለክታልና ነው ፡፡

  ታድያ ስለምን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይህን የሰዎቹን ጭንቀት እንድትረዳ አደረጓት? ቢባል ከእርሱ አምላክነት ጋር የርሷም አማላጅነት እግረ መንገዱን እንዲገለጽ ስለተፈለገ ነው ፡፡ ሌላውም ማወቅ ያለብን ደግሞ የሰዎቹን ችግር በመንፈስ ተገንዝባ ፣ ዝም ብላ የእንግድነቷን ድርሻ ብቻ እንደ ሌሎች ታዳሚዎች መወጣት ስትችል ፣ አዛኝነቷም እንድናውቀው ስላስፈለገ ልጅዋን ጠየቀችው ተባለ ፡፡ እግዚአብሔር ጸጋን የሚያጎናጽፈን ቃለ አባይ ሲመጣ ልናሳፍርበት ፣ አጋንንት ሲቀርበን ልንገስጽበት ፣ አስፈላጊ በሆነበት ቦታና ሥፍራ ሁሉ በአግባቡ እንድንጠቀምበት ስለሆነ ፣ የተጎናጸፈችውን ጸጋ በተግባር አሳየች ያሰኛል ፡፡ ስለዚህም አዛኝቷ በጭንቃችንና በመከራችን ሁሉ ስሟን በእምነት ከጠራን ከአንድ ልጅዋ ታማልደናለች ፡፡ አሁንም ወደ ቅዳሴዋ ስንመለስ ፣ የሚጮኸው እንዲሁ ከልጅሽ አማልጂን ፣ ልጅሽን አሳስቢልን እየተባለ እንደሆነ እንመለከታለን ፡፡

  የማርያም ቅዳሴ ቁጥር 18 “ለእሉኒ ወለኲሎሙ ኦ መስተምሕርት አስተምህሪ ኀበ ወልድኪ ከመያዕርፍ ነፍሰ ኰሎሙ ጳጳሳት ወሊቃነጳጳሳት ወኤጲስ ቆጶሳት ቀሳውስት ወደያቆናት …” ፤
  ትርጉም ፡- “አማላጅቱ ሆይ እሊህንም ሁሉንም ከልጅሽ ዘንድ አማልጂ ፤ የጳጳሳትንና የሊቃነ ጳጳሳትን የኤጲስ ቆጶሳትንም ሁሉ ነፍስ ያሳርፍ ዘንድ የቀሳውስትንና የደያቆናትንም …”

  ቁጥር 165-171 ደግሞ “ድንግል አዘክሪ ኀበ መዘክር ዘኢረስእ ኲሎ ፡፡ አዘክሪ ድንግል ልደቶ እምኔኪ ዘተወልደ በቤተ ልሔም ወዛተጠብለለ በአዕርቅት ወአስተማወቅዎ እስትንፋሰ አድግ ወላህም በመዋዕለ ቊረ፡፡ አዘክሪ.…. ፡፡ አዘክሪ……፡፡”
  ትርጉም “ድንግል ሆይ ከሚያስብ ፣ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢ ፡፡ ድንግል ሆይ በቤተ ልሔም ካንቺ የተወለደውን መወለድ በጨርቅ የተጠቀለለውንም አድግና ላህም በብርድ ወራት እስትንፋስን ያሟሟቁትንም አሳስቢ ፡፡ ….. አሳስቢ ፡፡.…. አሳስቢ፡፡” በማለት ይቀጥላል

  ወንድማችን ጸጋ "የወንጌልን ቃል በሚታይ ቲሸርት ላይ ሳነብ እጅግ ደስ ብሎኛል፡፡" ስሜቱን የገለጸባቸው ልጆች ምናልባትም የወንጌልን ቃል በማያውቁ ሥርዓት አስከባሪዎች የተያዙትን ይሆናል ፡፡ ምክንያቱም "አንድ ጌታ ፣ አንድ ሃይማኖት ፣ አንዲት ጥምቀት ኤፌ 4፡5" የሚል ጽሁፍ የያዙትን ታሰሩ የሚል ንባብ አይቻለሁ ፡፡

  አባቶቻችን በሠሩት አዝኜ ፣ ከራሴ ጋር ብዙ ሰዓት ታግዬ ነው ይህችን ያቀረብኳት ፡፡ ዛሬ እንደ ወትሮው ብዙ የምለዋወጥበት አቅም የለኝም ፡፡ ከድብርት ገና በሥርዓቱ አልወጣሁም ፡፡ ምክንያቱም ወንጌልን ሥራዬ ብለው የያዙት አባቶች አርአያ መሆን ሲሳናቸው ፣ እኔስ ከምን እዳዬ ብዬ ነው ራሴን የማዞረው ብዬ አንድ ሁለት ቀን እርግፍ አድርጌ ወደ ዘመናዊ ሰዎች ልማድ ተመልሼ ነበር ፡፡ ንስሐ በማለት እግዚአብሔር እንዲረዳኝ በጸሎት አስቡኝ ፡፡ ክርስትና ፈተናም አለባት ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. እውነትም ምዕመን!!!!!!!!!

   Delete
  2. Miemen thanks I really appreciate what you always write. You are greateful for your balanced idea. Demo Tesfa atkuret. Betselotie asbihalehu.

   Delete
  3. @Miemen, from now on I would like to call you "melkam memehir". I always read what you write and it teaches me more details that I ever learned. Ene ezih bet "aba selama blog" minim guday yelegmn but to get other links I always open and pass by via this blog. But recently I am coming deliberately here to read your teachings and arguments. They are convincing and I like all. Egizer yibarkeh...aba selamawochin demo libona yisetachew because thye are always distroting facts and would like to change our church to prptestant (I guess). Sifelegu mariyamn, sifelgu melaktn ena kidisanin yisadebaly...but they would like to call themselves ortodox. Behulet bilewa yemibelu malet enzihn new. So pls we are learning a lot from you so bik eyalk astmren. Melkam memhir biyehalehu ena atitifa! Akibari ehitih negn!!

   Delete
 4. WONDME MNEW YIH AYNETU YEKINAT MENFES BIKERBIH LEMEHONU ANTE MANEHINA NEW HULEM YEKIDUSANEN KEBER EYAKALELK YEMIT TSFEW KIDUSANEN YAKEBERE KIDUS EGZIABHER SLEHONE KEBER LEMIGEBAW HULU KIBERINE SITU YALEW LEATE AYSERAM MALET NEW???

  ReplyDelete
 5. aba natneil said the following statement at janmeda አንድ አንድ ሰዎች ‹‹አንቺ ሴት ከኔ ምን አለሽ›› በማለት አዋርዷታል የሚሉት ጠላታችንን ሰይጣን እንዳያስተውሉ ልባቸውን ስለዘጋው እንጂ ወደው አይደለም፡፡ እንዲህማ ቢኾን ኑሮ ‹‹አባትኽንና እናትኽን አክብር›› ብሎ ሕግ ባልሠራም ነበር፡፡ አትሳቱ÷ እናቱንና አባቱን የሚያዋርድ፣ የሚያቃልል አምላክ የለንም፡፡ አንቺ ሴት ካንቺ ምን አለኝ ማለቱ ስድብ ሳይኾን ካንቺ ተወልጄ ሰው ኾኛለኁና አንቺ ጠይቀሽኝ የማላደርገው ምን አለ ማለቱ ነው፡፡ 9 ወር ከ5 ቀን የተሸከመችውን እናቱን ቀርቶ ለወዳጆቹ ቅዱሳን እንኳን ሰማይ እንዲለጉሙ፣ እሳት እንዲያወርዱ፣ ፀሐይ እንዲያቆሙ አድርጓል፡፡ 1ነገ. 17÷1፤ ኢያ. 10÷12፡፡ እነርሱ እንደሚሉት ቢኾንማ ኑሮ የሚላችኹን አድርጉ ከማለት ይልቅ ልጄ÷ በሰው መሀል አቃለልኽኝ፤ አዋረድኽኝ ባለች ነበር

  ReplyDelete
 6. Kebede Bogale Eyesus bichanew "yehiwpt minch", "yehiwot wiha minch" mebal yalebet le'Mariam gin ye'Eyesus Kiristos enat mebal bich yibekatal ersuam lela atifelgim. «ማርያም የሕይወት ውሃ ምንጭ ናት» ehe mebalu betam sihtetnew. Endigebah simetawi honeh sayhon kesbileh anbibew ena kuch bileh degimo aselasilew. Abba negn.

  ReplyDelete
 7. እውነት በሎጂክ አይደገፍም፡፡ የእግዚአብሔርንን እውነት እንደ እግዚአብሔር ቃል ብቻ መቀበል ያስፈልጋል፡፡ ክረስቶስ የህይወት ውሀ ምንጭ ነው፡፡ የሕይወት ውሃ ምንጭ የሆነው ደግሞ የዘላለም አምላክ ስለሆነ ነው፡፡ አደራህን ከበደ በዚህ አያያዝህ ከስላሴ አራተኛ ትሁነን ብለህ እንዳትጠይቅ ብቻ

  ReplyDelete
 8. for kebede
  ene eskmigebaghe derse embetachen mariyamenm getachen eysus kirstosenm yastwawken meshaf kidus new ena meshafu demo ye hiwot minch ande becha endhone yemskeral!! egizhabeher demo kenatgha amlak selhone ye sun kibr lelela lemanm endnset ayfelgem chgeru ezi ga yemslghal lene endmigebagh!!

  ReplyDelete
 9. ማርያም የሕይወት ውሃ ምንጭ ናት!!!!!!!!!!!!!!! <> aregeh....SHOKAKA!!!!

  ReplyDelete
 10. የረቡዕ ውዳሴ ማርያም እንዲህ ይላል
  “ኩሉ ትውልድ ያስተበፅዑኪ ወይሰግዱ ለዘተወልደ እምኔኪ ወያፀብይዎ”
  “ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑሻል ስግደት ግን ካንቺ ለተወለደው ነው፡፡ ከፍ ከፍም ያደርጉታል፡፡”
  ይህ የቅዱስ ኤፍሬም ድርሰት እንሚነግረን እመቤታችን ጌታችንን ስለወለደች ብቻ ለአምላክ የሚገባው ነገር ሁሉ ይገባታል ማለት አይደለም:: ምንጭ መነሻ ማለት ነው፡፡ እመቤታችን ክርስቶስ ለለበሰውም ስጋ ቢሆን መነሻ አይደለችም፡፡ የጥምቀት ዕለት ግን እመቤታችን የተባለችው ክረስቶስ ለለበሰው ስጋ ምንጭ ሳይሆን የህይወት ውሃ ምንጭ ነው፡፡ ለአቶ ከበደ በቅንንነት የምነግርዋት ስህተቱን እውነት ለማድረግ ከአውድ የወጣ ክርክር ማድረጎትን ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ክብር እና ብቸኛ መገለጫዎችን ለፍጡር እመቤታችንንም ጨምሮ ቢሆን መስጠት ከባድ ኑፋቄ ነው፡፡ እግዚአብሔር በክብሩ አይደራደርም፡፡ አቶ ጸጋ ታደለ ሂሳቸው ጠንካራ ቢሆንም እውነቱን ግን የሳተ አይደለም፡፡ ክርስቶስ ብቸኛው እና ተወዳዳሪ የሊለው የህይወት ውሃ ምንጭ ነው፡፡ በእርሱ ከሲኦል እስር ተፈትተናል፡፡ በእርሱ ከሞት ወደ ሕይወት ተመልሰናል፡፡ በእርሱ በበደላችንን ሙታን በነበርን ጊዜ የዘላላም ሕይወትን አግኝተናል፡፡ ይህ ነው የህይወት ውሀ ምንጭነት ትርጓሜ፡፡ እመቤታችንን የህይወት ዉሀ ምንጭ ብሎ መጥራት ታላቅ ኑፋቄ ነው፡፡ ለእመቤታችን የሚገባት ቅዱስ ኤፍሬም በረቡዕ ውዳሴ ማርያም ላይ የተናገረው ነው፡፡ “ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑሻል ስግደት ግን ካንቺ ለተወለደው ነው፡፡ ከፍ ከፍም ያደርጉታል፡፡”
  አዎን ስግደት ለክርሰቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው፡፡ የሕይወት ውሃ ምንጩ እርሱ ነውና
  በዮሐንስ ራዕይ ምዕርፍ 22 ላይ “መንፈሱና ሙሽራይቱም። ና ይላሉ። የሚሰማም። ና ይበል። የተጠማም ይምጣ፥ የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው ይውሰድ።” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የህይወት ዉሀ ምንጭ የሆነውን ክርስቶስን ነው፡፡
  ለእርሱ ከዓለም እስከ ዓለም ድረስ ክብር ይግባው፡፡ አሜን

  ReplyDelete
 11. ትንቢተ ኤርምያስ17፥13

  አቤቱ፥ የእስራኤል ተስፋ ሆይ፥ የሚተዉህ ሁሉ ያፍራሉ ከአንተም የሚለዩ የሕይወትን ውኃ ምንጭ እግዚአብሔርን ትተዋልና በምድር ላይ ይጻፋሉ።

  ReplyDelete
 12. ጸጋ
  በእውነት የእውነት ጌታ የሆነው እግዚአብሔር ይባርክህ

  ReplyDelete
 13. Who cares about what bible says? whether Lord Jesus gave honour to her or not, I totally love her,I respect her. That is all. When I compare my self with her, I am nothing.

  ReplyDelete
  Replies
  1. if u don't care about the bible. you are the son of devil.

   Delete
 14. Bible is written with persons, not by lord himself or angels. So persons can did mistakes when they record history. There are a lot of contradicting issue in bible.

  ReplyDelete
 15. እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው? አለው። ha ha ha . so lord himself violate the law that says respect your father & mother. we will follow him . Now I am going to say my mom & brothers እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው? What a fake scripture.

  ReplyDelete
  Replies
  1. why malaget with the word of God?? read ማቴ. 12፡48-50

   Delete
 16. Abba Selama, I do not know where you get your fallacious dogmatic conclusion. Your utter ignorance of the bible is manifested in every Article I read on your blog. What is wrong with the saying " ማርያም የሕይወት ውሃ ምንጭ ናት " ? Is our Holy Saviour Crist not the Living Water? የለበሰው ሥጋስ ከአብርሃም ዘር ፥ ከማርያም የተገኘ አይደለም እንዴ? ….. የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም። ዕብ. ፪፥ ፲፮ What about the dogmatic verse about a real believer, let alone St. Mary!?: በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል። John 7:38

  Please do not oppose for its own sake, and most importantly do not confuse people based only on your ignorance of the Truth!


  ReplyDelete
 17. 2. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠርቶ ነበር

  “ወፀውእዎ ለእግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ” ጌታ ኢየሱስንም ጠሩት” ዮሐ.2፤2 እናትን ጠርቶ ልጅን መተው ተገቢ አይደለምና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጠርተው ልጇም ጠርተውታል፡፡ ይህም ፍፁም ሰው መሆኑን ያስረዳል፡፡ ሰው ነውና እንደ ሰውነቱ ወደ ሰርግ ቤት ተጠራ፤አምላክ ነውና ጌትነቱን ገለጠ፡፡

  ከሚደሰቱት ጋር መደሰት ከሚያዝኑ ጋር ማዘን ተገቢ መሆን በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር አስተማረ፡፡ በቃና ዘገሊላ ከሠርግ ቤት እንደሄደ በአልአዛር ቤት ለለቅሶ መገኘቱን ልብ ይሏል፡፡ወደ ሠርግ ቤት የሄደው በደስታ ነበር፡፡ ቅዱስ ያሬድ እንደገለጠው “ሖረ ኢየሱስ በትፍስህት ውስተ ከብካብ እንዘ ይገብር ተአምረ ወመንክረ በውስተ አህዛብ፤ ኢየሱስ በአህዛብ ፊት ተአምራትንና ድንቆችን እያደረገ በደስታ ወደ ሠርግ ሄደ” ወደ አልአዛር ቤት ሲሄድ ግን “ጌታች ኢየሱስ ክርስቶስም እርሷ (ማርታ) ስታለቅስ ባየ ጊዜ በልቡ አዘነ፡፡በራሱም ታወከ(ራሱን ነቀነቀ፡-የሀዘን ነው) ጌታችን ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ ፡፡አይሁድም ምን ያህል ይወደው እንደነበር እዩ አሉ” ዮሐ.11÷33-38

  ከዚህ እንደ ምንመለከተው ከኀጢአት በቀር የሰውነትን ሥራ መሥራቱን የሰውን የተፈጥሮ ሕግ ምን ያህል እንደ ከበረ እና እንደፈጸመ ያሳያል በመደሰት እና በማዘን ፍጹም ሰው መሆኑን ሲያስረዳን ፍጹም አምላክ መሆኑን በሠርጉ ቤት ውኃውን የወይን ጠጅ በማድረግ በልቅሶ ቤትም ዓልዓዛርን ከአራት ቀናት በኋላ በማስነሣት አስረዳን፡፡ አምላክ ነኝ ከሠርግ ቤት አልሄድም ከልቅሶም ቤት አልገኝም አላለም በትሕትና ራሱን ዝቅ አድርጎ በሠርግ ቤት እንዲሁም የሚያዝኑትን ለማጽናት በልቅሶ ቤት በመገኘቱ ሁሉንም የሰውነት ሥራ አከናወነ፡፡ አምላክ ነው በሠርግ ቤት የጎደለውን ምሳ አምላክ ነውና የሞተውን አልዓዛርን መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱኝ ሳይል እንዲነሣ አደረገ፡፡

  በዚህ የሰርግ ቤት ባይገኝሰዎች ምን ያህል ሀፍረት ይሰማቸው ይሆን? የእርሱ እንዲሁም የእናቱ በሰርጉ ቤት መገኘት ለባለሰርጉና ለታዳሚዎች ሙላት ነበር እርሱ ባይኖር የሰርጉ ቤት የሃዘን ቤት ሊሆን እንደሚችል ምንም ጥርጥር የለውም በዚህ ሰርግ ቤት ተመላጅነት የአምላክ አማላጅነት ደግሞ የፍጡራን መሆኑን አስተምሯል፡፡
  “ወሶበ ሀልቀ ወይኖ ወይትቤሎ እሙ ወይንኬ አልቦሙ” ዮሐ.3÷3 “የወይን ጠጅ ባለቀባቸው ጊዜ እመቤታችን የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም” አለችው አማላጅነት የፍጡራን ገንዘብ ነው፡፡ እርሱ አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ÷ ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት” ከአንቺ ጋር ምን ጠብ አለኝ አንቺ ያልሽውን ልፈጽም አይደለም ሰው የሆንኩት አላት ጊዜ ገና አልደረሰም የሚለው ሥራውን ያለ ጊዜው አይሠራውምና ነው፡፡ ለእግዚአብሔር የሥራ ጊዜ አለው” እንዲል፡፡ መዝ.118÷126 በሌላ መልኩ በአምላክነቱ ማንም የማያዝዘው ግድ ይህን አድርግ ብሎ ማንም ሊያሰገድደው የሚችል የወደደውን የሚያደርግ ቢፈልግ የሚያዘገይ ሲፈልግ በዐይን ጥቅሻ በፈጠነ መልኩ መፈጸም የሚችል በራሱ ፈቃድ እንጂ በሰምች ፈቃድ የማይመራ መሆኑን ያስተምረናል፡፡

  “ፈቃድ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን” ማቴ.6÷ ብላችሁ ለምኑኝ ያለው ለዚህ ነው በሌላ መንገድ የወይን ጠጅ በሙሉ አላላቀም፡፡
  ያለውን ቢያበረክተው ተአምራቱን አናደቅም፥ ፈጽሞ ጭል ብሎ እስከሚያልቅ “ጊዜ ገና አልደረሰም” አለ፡፡ሰው ቢለምን ቢማልድ በእርሱ ፈቃድ ጊዜው ሲደርስ ነው የሚፈጸመው፡፡ምልጃው አልተስማም ተቀባይነት አላገኝም ማለት ግን አይደለም ተቀባይነት ያገኘ መሆኑ የሚታወቀው በመደረጉ ነው፡፡

  አማላጅ ያስፈለገው እርሱ የሚያውቀው ነገር ኖሮት በስምአ በለው ለመንገር አይደለም ለሰው ልጆች ያለው ፍቅር ይታወቅ ዘንድ እና የሰው ልጆችን ከችግር የሚያወጣበት መንገዱ ብዙ መሆኑን ለማስረዳት ነው እንጂ፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሚዜዎችን “ኩሎ ዘይቤለክሙ ግበሩ፤ያዘዛችሁን ሁሉ አድርጉ፡፡” ማለቷ “አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ” የሚለው የጌታችን መልስ “እሺታ ይሁንታን” የሚገልጽ መሆኑን ያስረዳል፡፡ “እሱም ውኃ ቅዱና ጋኖችን ምሏቸው” አለ፡፡ እነርሱም በታዘዙት መሠረት እመቤታችን ያላችሁን አድርጉ እንዳለቻቸው ውኃውን ቀድተው ጋኖችን ሞሏቸው፡፡ ውኃውንም ክብር ይግባውና በአምላካዊ ችሎታው ወደ ወይን ጠጅ ለወጠው፡፡ ለአሳዳሪውም ሰጠው አሳዳሪው የወይን ጠጅ የሆነውን ውኃ ቀምሶ አደነቀ ከወዴት እንደመጣ ግን አላወቀም ድንቅ በሆነ አምላክ ሥራ እንደተለወጠም አልተረዳም፡፡ ያን ምስጢር የሚያቀው ባለሰርጉ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ውኃውን የቀዱ ሰዎች ናቸውና፡፡

  ታዳሚዎችም “ሰው ሁሉ የተሻለውን ወይን አስቀድሞ ያቀርባል በኋላም ተራውን የወይን ጠጅ በኋላ ያቀርባል አንተስ መናኛውን ከፊት አስቀድመህ ያማረውን ከኋላ ታመጣለህን” ብለው አድንቀዋል፡፡ ድሮም የአምላክ ሥራ እንደዚያ ነው ብርሃን ከመፍጠሩ አስቀድሞ ጨለማን ፈጥሯል ከጨለማ ቀጥሎ “ብርሃን ይሁን” በማለት ብርሃንን ፈጥሯል፡፡ መጀመሪያ ብርሃን ተፈጥሮ ኋላ ጨለማ ቢፈጠር ይከብድ ነበርና መጀመሪያ 21 ፍጥረታት ፈጥሯል፡፡ በመጨረሻም በአርዓያውና በአምሳሉ የሥነ ፍጥረት የሆነውን የሰው ልጅ ፈጥሯል፡፡ ናትናኤልንም እንዲህ ብሎታል፡፡ “ከእንግዲህ ወዲህ ከዚህ የሚባልጥ ታያለህ” ማለቱ የእግዚብሔር ሥራ እየቆየ ውብ ያማረ መሆኑን ያመለክታል ሰው ግን ጥሩ ነው፡፡ ያለውን ያስቀድማል ያ ሲያልቅ የናቀውን ይፈልጋል፡፡ “የወደዱትን ቢያጡ ያጡትን ይቀላውጡ” እንዲሉ እግዚብሔር ልማዱ ነው፡፡ ተራውን ከፊት ታላቁን ከኋላ ማድረግ ለሰው መጀመሪያ የተሰጠው የሚያልፈው ዓለም ነው በኋላ የማያልፈው መንግሥተ ሰማያት ይሰጠዋል ሰው መጀመሪያ ይሞታል በመጨረሻ ትንሣኤ አለው፡፡ ሰው መጀመሪያ ሲወለድ ርቀቱን ነው፡፡ ኋላ ልብስ ያገኛል፡፡ ሁብታም ይሆናል፡፡ ሰው ወደዚህ ዓለም ሲመጣ ዓለምን የሚያገኛት የሚተዋወቃት በልቅሶ ነው፤ ኋላ ግን ይደሰታል በሀሳር በልቅሶ ወደመቃብር ይወርዳል፡፡ በደስታ “መቃብር ክፈቱልኛ፥ መግነዝ ፍቱልኝ” ሳይል ይነሣል ይህን የአምላክ ሥራ አድንቆ መቀበል እንጂ መቃወም አይችልም፡፡

  ReplyDelete
 18. 3. ቅዱሳን ሐዋርያት በዚህ ሠርግ ነበሩ

  “ወለአርዳኢሁ ውስተ ከብካብ” እንዲል፡፡ ዮሐ.2፥2 “ደቀመዛሙርቱንም ጠሯቸው” መምህርን ጠርቶ ደቀ መዝሙርን መተው ተገቢ አይደለምና፤ ደቀ መዛሙርቱ ከመምህራቸው ከክርስቶስ ጋር አብረው በሠርግ ቤት ተገኝተው በተደረገው ተአምር ጌትነቱን አምነዋል፡፡ ተአምራቱን ተመልክተዋል፣ ከዋለበት የሚውሉ፥ ከአደረበት የሚያድሩ፥ ተአምራት የማይከፈልባቸው፥ ይህን ዓለም ለማስተማር የተመረጡ ናቸውና፤ አየን ብለው እንጂ ሰማን ብለው አያስተምሩምና፡፡በጠቅላላው የእነርሱ በሰርጉ ቤት መገኘት የሚያስተምርና ካህናት የሌሉበት ሰርግ ሊደረግ እንደማይገባው ነው፡፡ በሰርግ ቤት የካህናት መገኘት እና ቡራኬ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ያስተምራል፡፡ በፍትሐ ነገሥት አን.24 የተገለጸውም ይህ ነው “ወማዕሰረ ተዋሰቦሶ ኢይትፌጸም ወኢይከውን ዘእንበለ በሀልዎተ ካህናት ወጸሎት ዘለዕሌሆሙ” የጋብቻ አንድነት ካህናት ቢኖሩ እንጂ ያለእነርሱ አይጸናም ጸሎት ቢያደርጉ እንጂ ያለ ጸሎት አይፈጸምም” እን. በቃና ዘገሊላው ሰርግ ጋብቻን በጥንተ ፍጥረት “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም ረዳት እንፍጠርለት” ዘፍ.2፥19 ያለ አምላክ የሐዲስ ኪዳን ጋብቻ በካህናት ቡራኬና ጸሎት መከናወን እንደሚገባው ሲያስተምረን ቅዱሳን ሐዋርያትን ይዞ ተገኝቷል፡፡ የቃና ዘገሊላ ሰርግ እና በሰርጉ ላይ የታዩ ተአምራት ምልጃዎች ሁሉ ሌላም ምሥጢር ያዘሉ ናቸው፡፡ እመቤታችን “የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም” ማለቷ “ወይን” በተባለው የክርስቶስ ደም ዓለም እንዲድን ያስረዳል፡፡ ደምህን አፍሰህ ሥጋህን ቆርሰህ አጽናቸው ማለቷ ሲሆን “ጊዜዪ ገና ነው” የሚለው የጌታ መልስ “ደሙ በዕለተ ዓርብ የሚፈስበት ጊዜ ገና መሆኑን ያስረዳል” ጥንቱን ዓለምን ለማዳን አይደለምን፣ ሰው የሆንኩት ሥጋ የለበስኩት ለዚህ ዓለምን ለማዳን አይደለምን ሲል ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ትልቅ ትምህርት ነው ፡፡
   ቃለ ሕይወት ያሰማልን
   ረጅም ዕድሜና ጸጋውን ያጐናጽፍልን ፡፡

   Delete
 19. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 21, 2013 at 9:58 AM

  AnonymousJanuary 20, 2013 at 3:54 PM
  Kebede BogaleJanuary 20, 2013 at 6:20 PM

  Both of you are nonsense and against ቅድስት ድንግል ማርያም. If you agree about the statement «ማርያም የሕይወት ውሃ ምንጭ ናት» , you must disagree with one and three of the Holy Trinity.

  You know what? Saint Mary mad at you because you insulted her by saying የሕይወት ውሃ ምንጭ ናት.Lord Jesus is the only የሕይወት ውሃ ምንጭ ናት.

  ReplyDelete
 20. ጌታ እሱ ብርሃን ሆኖ ሳለ እናንተ የአለም ብርሃን ናችሁ አለ ደቀ መዛሙርቱ እሱ አምላካዊ ብርሃን ሲሆን ደቀመዛሙርቱ ደግሞ የጸጋ ነው፡፡ ብርሃን ስለሆነ ብርሃን እንዲባሉ ፈቀደ፡፡ የሚበላውንና የሚጠጣውን ያፈራችልን ምክንያተ ድህነታችን ናት፡፡ እኛ እንድንበላ እንድንጠጣ የሰጠን ስጋና ደሙ ከስዋ የነሳው ነው፡፡ እመቤታችንን እኮ ለራሱ ያዘጋጃት እሱ ነው ፡፡ ሐዋርያቱንም እኔ መረጥሁዋችሁ እንጂ እናንተ አየደላችሁም ነው ያለው ፡፡ ዮሀ. 2፡1 የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች ይላል መጀመሪያ ይህም ማለት እመቤታችን ከደጋሹ ጋር ዝምድና ጉርብትና እንዳላት እንረዳለን እናትንም ጠርቶ ልጅን መተው የለምና ጌታንም ከነደቀበዛሙርቱ እንደነበረ ይናገራል ቀጥሎ፡፡ አንቺ ሴት ካንቺ ጋር ምን አለኝ ማለት እኮ እናትና አባትህን አክብር ላለ አምላክ ስድብ ተደርጎ የውርደት ንግግር ተደርጎ ከተወሰደ በናንተ ትርም እግዚአብሔርንም ተሳዳቢ አዋራጅ ማድረግ ነው፡፡ አንቺ ሴት ካንቺ ጋር ምን አለኝ ማለት እናቴ ስትሆኚ ስላንቺ የማልፈጽመው ነገር ምን አለ፡፡ አዳም እኮ ይቺ ስጋዋ ከስጋዬ አጥንትዋ ከአጥንቴ ነው ሴት ትባል ብሎ ሴት የሚለውን ትርጉም ያስረግጥልናል፡፡ ጌታም ስጋሽ ስጋዬ አጥንትሽ አጥንቴ ሲል ነው ከስዋ የነሳው ነውና፡፡ዘፍ. 2፡23፤ አዳምም አለ። ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል። ቅድስት ድንግል የሆነች እናታችን እኮ ብዙ ነገሮችን ታውቃለች ግን ከመግለጥ ይልቅ በልብዋ ታኖረው ነበር ይላል፡፡ሉቃ. 2፡51 ከእነርሱም ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ፥ ይታዘዝላቸውም ነበር። እናቱም ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ ትጠብቀው ነበር። ብዙ ጊዜ የእግዚአብሄርን ስራ ቅዱስ ዮሴፍ ከአይምሮ በላይ ስለሆነ ይቸገር ነበር፡፡ እመቤታችን ግን ከጽንሰት እስከ እርገት ያለውን ነገር በልብዋ ታኖረው ነበር ማለት ታውቃለች ግን ጌታ ደቀመዛሙርቱን ለማንም እንዳትናገሩ እያለ ሲነግራቸው እንደነበረ እስዋም ሳይነግራት በጸጋ በልብዋ ማኖር እንዳለባትና የሚሆነውን ሁሉ መጠበቅ ነበር፡፡ የዮሴፍን አለማስተዋል ሲገልጥ እስዋ በልብዋ ብታውቅም በእሱ ሃሳብ ሄደዋልና በአንድ ላይ ተናገረ ይህም ማለት በስቅለት ወቅት በግራ ያለው ጌታን ሲሳደብ በቀኝ ያለው ግን ምህረትን ለምኖዋል ነገር ግን ፡፡ሉቃ 23፡39-43፡፡ በማር. 15፡32 አይተን እናምን ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ ክርስቶስ አሁን ከመስቀል ይውረድ አሉ። ከእርሱም ጋር የተሰቀሉት ይነቅፉት ነበር። ብሎ ሁለቱም እንደነቀፉትና እንደሰደቡት ይናገራል ይህ የሚያጣላ ሆኖ አይደለም ወንበዴ በመሆናቸው ምህረት ለማኙን ከተሳዳቢው ደምሮታል፡፡ስለዚህ ድክመት የነበረው አለማወቅ አለማስተዋል የነበረው ከዮሴፍ እንጂ ከእመቤታችን አልነበረም፡፡ ጌታ እሱ ብርሃን ሆኖ ሳለ እናንተ የአለም ብርሃን ናችሁ አለ ደቀ መዛሙርቱ እሱ አምላካዊ ብርሃን ሲሆን ደቀመዛሙርቱ ደግሞ የጸጋ ነው፡፡ ብርሃን ስለሆነ ብርሃን እንዲባሉ ፈቀደ፡፡ የሚበላውንና የሚጠጣውን ያፈራችልን ምክንያተ ድህነታችን ናት፡፡ እኛ እንድንበላ እንድንጠጣ የሰጠን ስጋና ደሙ ከስዋ የነሳው ነው፡፡ እመቤታችንን እኮ ለራሱ ያዘጋጃት እሱ ነው ፡፡ ሐዋርያቱንም እኔ መረጥሁዋችሁ እንጂ እናንተ አየደላችሁም ነው ያለው ፡፡ ዮሀ. 2፡1 የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች ይላል መጀመሪያ ይህም ማለት እመቤታችን ከደጋሹ ጋር ዝምድና ጉርብትና እንዳላት እንረዳለን እናትንም ጠርቶ ልጅን መተው የለምና ጌታንም ከነደቀበዛሙርቱ እንደነበረ ይናገራል ቀጥሎ፡፡ አንቺ ሴት ካንቺ ጋር ምን አለኝ ማለት እኮ እናትና አባትህን አክብር ላለ አምላክ ስድብ ተደርጎ የውርደት ንግግር ተደርጎ ከተወሰደ በናንተ ትርም እግዚአብሔርንም ተሳዳቢ አዋራጅ ማድረግ ነው፡፡ አንቺ ሴት ካንቺ ጋር ምን አለኝ ማለት እናቴ ስትሆኚ ስላንቺ የማልፈጽመው ነገር ምን አለ፡፡ አዳም እኮ ይቺ ስጋዋ ከስጋዬ አጥንትዋ ከአጥንቴ ነው ሴት ትባል ብሎ ሴት የሚለውን ትርጉም ያስረግጥልናል፡፡ ጌታም ስጋሽ ስጋዬ አጥንትሽ አጥንቴ ሲል ነው ከስዋ የነሳው ነውና፡፡ዘፍ. 2፡23፤ አዳምም አለ። ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል። ቅድስት ድንግል የሆነች እናታችን እኮ ብዙ ነገሮችን ታውቃለች ግን ከመግለጥ ይልቅ በልብዋ ታኖረው ነበር ይላል፡፡ሉቃ. 2፡51 ከእነርሱም ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ፥ ይታዘዝላቸውም ነበር። እናቱም ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ ትጠብቀው ነበር። ብዙ ጊዜ የእግዚአብሄርን ስራ ቅዱስ ዮሴፍ ከአይምሮ በላይ ስለሆነ ይቸገር ነበር፡፡ እመቤታችን ግን ከጽንሰት እስከ እርገት ያለውን ነገር በልብዋ ታኖረው ነበር ማለት ታውቃለች ግን ጌታ ደቀመዛሙርቱን ለማንም እንዳትናገሩ እያለ ሲነግራቸው እንደነበረ እስዋም ሳይነግራት በጸጋ በልብዋ ማኖር እንዳለባትና የሚሆነውን ሁሉ መጠበቅ ነበር፡፡ የዮሴፍን አለማስተዋል ሲገልጥ እስዋ በልብዋ ብታውቅም በእሱ ሃሳብ ሄደዋልና በአንድ ላይ ተናገረ ይህም ማለት በስቅለት ወቅት በግራ ያለው ጌታን ሲሳደብ በቀኝ ያለው ግን ምህረትን ለምኖዋል ነገር ግን ፡፡ሉቃ 23፡39-43፡፡ በማር. 15፡32 አይተን እናምን ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ ክርስቶስ አሁን ከመስቀል ይውረድ አሉ። ከእርሱም ጋር የተሰቀሉት ይነቅፉት ነበር። ብሎ ሁለቱም እንደነቀፉትና እንደሰደቡት ይናገራል ይህ የሚያጣላ ሆኖ አይደለም ወንበዴ በመሆናቸው ምህረት ለማኙን ከተሳዳቢው ደምሮታል፡፡ስለዚህ ድክመት የነበረው አለማወቅ አለማስተዋል የነበረው ከዮሴፍ እንጂ ከእመቤታችን አልነበረም፡፡

  ReplyDelete
 21. ጸሐፍት ፈሪሳውያንና አይሁድ ካህናት ጌታ ተአምር እያደረገ ሕዝቡን ወደ ራሱ በማድረጉ ብሉይ የአባቶቻችን ስርዓት ይጠፋል በሚል ሊቃወሙት ፈልገው እሱን ከሰው ለመለየት ሲሉ የተጠቀሙበት መንገድ ቢኖር በጌታ ላይ አሉባልታ በህዝቡ መካከል ማስወራት ነበር፡፡ ሰውም አልሰማ ሲላቸውና ብዙ ህዝብ ሲከተለውና ከእግሩ ስር ሆነው ሲማሩ ቢቀኑ አሁንም ዮሴፍን ሄደው ልጅህ አበደ ብለው ቢነግሩት ድሮም ማስተዋሉ ስለሌለው እመቤታችንን ይዞ ከሚያስተምርበት ቦታ ጭንቅንቅ በመሆኑ መግባት ቢሳናቸው አይሁድ ካህናት ቆይ እንጥራላችሁ ብላው እንደምንም ገብተው እናትና አባትህ ይፈልጉሃል ባሉት ጊዜ እናቴስ ማን ናት አባቴስ ማን ነው በማለት እናቴና አባቴ የእግዚአብሄርን ፈቃድ የሚያደርጉ ናቸው ብሎ የልባቸውን ሃሳብ ስለሚያውቅ ትምህርቱን እንደማያቁዋርጥ ነገራቸው፡፡ ይህንን በማለቱ ትምህርቱ እንዳይቁዋረጥ የተጠቀመበት አነጋገር እንጂ እናት አባቱን ለማጣጣል የተጠቀመበት ቃል ነው፡፡
  ታዲያ አንተው እዛው ሰላማዊ ንግግር መሆኑን ተናገርክ እኮ ነቢዩ ኤልያስን ካንተ ጋር ምን አለኝ ያለችው ምን ጸብ ጥል አለን( እነዛን ለንጉሱ መልእክት ይዘው መጥተው ሊይዙት ሲሉ ከሰማይ እሳት ወርዳ እንድትበላቸው እንዳደረገ )ልጄን እንዲሞት የምታደርግብኝ ለማለት ፈልጋ ነው፡፡ ኤልሳእም እንደዚሁ በመካከላችን ጸብና ጥል የለም ሲል ነው፡፡ አጋንንቱም ቢሆን በሰዎች ላይ ፈተናዎችን እናመጣለን እናድራለን እናስታለን እንጂ ከአንተጋር መች ደርሰን እናውቃለን ምንስ ጸብ አለን ሲል ነው፡፡
  ጊዜዬ ገና አልደረሰም ማለቱ ይህ አከናውን የምትይኝ ምድራዊ ነው ነገር ግን ሰማያዊና የዘላለም ህይወትን የሚያገኙበትን እውነተኛውን መጠጥ የምሰጥበት ደሜን የማፈስበት ስጋዬን የምቆርስበት ቀኑ ገና እለተ አርብ አልደረሰም ሲላት ነው፡፡ እስዋም ንግግሩ ስለገባት የሚላችሁን አድርጉ አለቻቸው፡፡ በሁለተገኛ ደረጃ ገና የየጋኑ ሙጥጥ ብሎ አላለቀም አሁን ቢሆን ውስጥ ያለውን አበዛው ይሉኛል ስለዚህ የማበዛበት ጊዜ ጥቂት ይቀይ ሲላት ነው፡፡ እንኩዋን እመቤታችን ቅዱስ ጴጥሮስ እንኩዋን ሐናና ሰጲራ ገንዘባቸውን ደብቀው በመጡ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ተናግሮዋቸዋል፡፡ ስለዚህ መናፍቃን እባካችሁ እነሱ የጸጋ አምላክ ሲሆኑ እሱ ግን የባህርዩ ነው፡፡ ዘጸ 7፡1፤ እግዚአብሔርም ሙሴን አለው። እይ፥ እኔ ለፈርዖን አምላክ አድርጌሃለሁ፤ ወንድምህም አሮን ነቢይ ይሆንልሃል። ካለ አንተ ማን ነህ አይሆንም የምትል፡፡ ብርሃን ሲሆን ብርሃን ናችሁ ካለ እኛ ምን ቤት ነንና ነው ምቀኛ የምንሆነው፡፡ በቅዱሳን ክብር የሚቀና ዲያብሎስ ነው በዚህ ዘመን ደግሞ የ666 መንፈስ፡፡ ስለዚህ ልቦና ይስጣችሁ እንላለን፡፡
  ጸሐፍት ፈሪሳውያንና አይሁድ ካህናት ጌታ ተአምር እያደረገ ሕዝቡን ወደ ራሱ በማድረጉ ብሉይ የአባቶቻችን ስርዓት ይጠፋል በሚል ሊቃወሙት ፈልገው እሱን ከሰው ለመለየት ሲሉ የተጠቀሙበት መንገድ ቢኖር በጌታ ላይ አሉባልታ በህዝቡ መካከል ማስወራት ነበር፡፡ ሰውም አልሰማ ሲላቸውና ብዙ ህዝብ ሲከተለውና ከእግሩ ስር ሆነው ሲማሩ ቢቀኑ አሁንም ዮሴፍን ሄደው ልጅህ አበደ ብለው ቢነግሩት ድሮም ማስተዋሉ ስለሌለው እመቤታችንን ይዞ ከሚያስተምርበት ቦታ ጭንቅንቅ በመሆኑ መግባት ቢሳናቸው አይሁድ ካህናት ቆይ እንጥራላችሁ ብላው እንደምንም ገብተው እናትና አባትህ ይፈልጉሃል ባሉት ጊዜ እናቴስ ማን ናት አባቴስ ማን ነው በማለት እናቴና አባቴ የእግዚአብሄርን ፈቃድ የሚያደርጉ ናቸው ብሎ የልባቸውን ሃሳብ ስለሚያውቅ ትምህርቱን እንደማያቁዋርጥ ነገራቸው፡፡ ይህንን በማለቱ ትምህርቱ እንዳይቁዋረጥ የተጠቀመበት አነጋገር እንጂ እናት አባቱን ለማጣጣል የተጠቀመበት ቃል ነው፡፡
  ታዲያ አንተው እዛው ሰላማዊ ንግግር መሆኑን ተናገርክ እኮ ነቢዩ ኤልያስን ካንተ ጋር ምን አለኝ ያለችው ምን ጸብ ጥል አለን( እነዛን ለንጉሱ መልእክት ይዘው መጥተው ሊይዙት ሲሉ ከሰማይ እሳት ወርዳ እንድትበላቸው እንዳደረገ )ልጄን እንዲሞት የምታደርግብኝ ለማለት ፈልጋ ነው፡፡ ኤልሳእም እንደዚሁ በመካከላችን ጸብና ጥል የለም ሲል ነው፡፡ አጋንንቱም ቢሆን በሰዎች ላይ ፈተናዎችን እናመጣለን እናድራለን እናስታለን እንጂ ከአንተጋር መች ደርሰን እናውቃለን ምንስ ጸብ አለን ሲል ነው፡፡
  ጊዜዬ ገና አልደረሰም ማለቱ ይህ አከናውን የምትይኝ ምድራዊ ነው ነገር ግን ሰማያዊና የዘላለም ህይወትን የሚያገኙበትን እውነተኛውን መጠጥ የምሰጥበት ደሜን የማፈስበት ስጋዬን የምቆርስበት ቀኑ ገና እለተ አርብ አልደረሰም ሲላት ነው፡፡ እስዋም ንግግሩ ስለገባት የሚላችሁን አድርጉ አለቻቸው፡፡ በሁለተገኛ ደረጃ ገና የየጋኑ ሙጥጥ ብሎ አላለቀም አሁን ቢሆን ውስጥ ያለውን አበዛው ይሉኛል ስለዚህ የማበዛበት ጊዜ ጥቂት ይቀይ ሲላት ነው፡፡ እንኩዋን እመቤታችን ቅዱስ ጴጥሮስ እንኩዋን ሐናና ሰጲራ ገንዘባቸውን ደብቀው በመጡ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ተናግሮዋቸዋል፡፡ ስለዚህ መናፍቃን እባካችሁ እነሱ የጸጋ አምላክ ሲሆኑ እሱ ግን የባህርዩ ነው፡፡ ዘጸ 7፡1፤ እግዚአብሔርም ሙሴን አለው። እይ፥ እኔ ለፈርዖን አምላክ አድርጌሃለሁ፤ ወንድምህም አሮን ነቢይ ይሆንልሃል። ካለ አንተ ማን ነህ አይሆንም የምትል፡፡ ብርሃን ሲሆን ብርሃን ናችሁ ካለ እኛ ምን ቤት ነንና ነው ምቀኛ የምንሆነው፡፡ በቅዱሳን ክብር የሚቀና ዲያብሎስ ነው በዚህ ዘመን ደግሞ የ666 መንፈስ፡፡ ስለዚህ ልቦና ይስጣችሁ እንላለን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቃለ ሕይወት ያሰማልን

   Delete
 22. የአቶ ቦጋለ ልጅ
  ሎጂክህ በፋላሲ የተሞላ ነው፡፡ ይህ እውነት በአንተ ሎጂክ ሳይሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ነው የሚረጋገጠው መጽሐፍ ቅዱስ የሕይወት ውሃ ምንጭ ራሱ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ይናገራል። የተጻፈው ማርያም የሕይወት ውሃ ምንጭ አትባልም ነው። ትክክል ነው፡፡ አንተ ግን የሰውነቱ ምንጭ ናት አልክ፡፡ ትልቅ ክህደት፡፡ እርሷን የፈጠራት እኮ እርሱ ነው፡፡ ስለዚህ እርሷ እናቱ እንጂ ፈጣሪው ወይም ምንጩ አይደለችም፡፡ አንተ እናቴ ወለደችኝ ትላለህ ወይስ ፈጠረችኝ? እያልክ ያለኸው እኮ ማርያም ኢየሱስን ፈጠረችው ነው፡፡ ስለዚህ እባክህን ጣትህን አታፍታታብን

  ReplyDelete
  Replies
  1. የአቶ ሉተር ልጅ ፤ ክርስቶስ ወልደ አብ ወልደ ማርያም ይባላል ወይስ አይባልም ? ሁለት ልደት እንዳሉት ታምናለህ ወይስ አታምንም ? እግዚአብሔር ወልድ በቀዳማዊ ልደቱ ሥጋ ነበረውና ያን ሥጋ ይዞ ወደ ማኅፀነ ማርያም ገብቶ ነው 9 ወር ከ5 ቀን ቆይታ በኋል ተወለደ እንጅ ከማርያም የነሳው ሥጋና ነብስ የለም ነው የምትለው ? እኔ ግን የምለው እግዚአብሔር ወልድ ሥጋውን ከሥጋዋ ነብሱን ከነብሷ ነስቶ 2ኛ ልደት ስለተወለደ ፥ ለዳግማዊ ልደቱ ዘመን ስለተቆጠረለት ፥ የሕይዎታችን ምንጭ እርሱ በባኅርየ ሥጋዌው ከእመቤታችን መንጭቷል እላለሁ። ስለዚህ ፈጣሪ ከራሱ ፍጡር በሥጋ መንጭቷል ፥ ያችም ምንጭ ቅድስት ድንግል ማርያም ናት ብየ አምናለሁ ።

   Delete
  2. እየሱስ የህይወት ዉሃ ምንጭ ከሆነ.. እመቤታችን ደግሞ " የህይወት ዉሃ ምንጭ ምንጩ" ትሆናልቻ.... what a pervert people are..

   Delete
  3. ለKebede Bogale
   ወንድም ከበደ ቦጋለ ስለ እምነትህ መከራከርህና ለጠየቁህ ደግሞ መልስ መስጠትህ መልካም ነው ፡፡ እኔንም ደስ አሰኝቶኛል ፡፡ ዛሬም አንድ “እርስ በርሳችን ብንማማርና ሌሎችንም ከስህተት ብናተርፍ” በማለት የማነሳብህ ጥያቄ አለኝና እንደማትከፋብኝ እርግጠኛ ነኝ ፡፡

   ወልድ ወይም ቃል የሚባሉት ስሞች ከሥጋዌ በፊት የነበሩ የጌታችን መታወቂያዎቹ ናቸው ፡፡ ወልድ ለሚለው አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ብሏልና (ማቴ 28፡19 ፤ ራዕ 14፡1) ፤ ለቃል ደግሞ ዮሐንስ ወንጌል መጻፉን ሲጀምር “ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።” (ዮሐ 1፡1) በማለት ገልጾታልና ነው፡፡

   በሥጋ ከተገለጠ በኋላ ደግሞ የወልድ ወይም የቃል ስሙ ኢየሱስ ነው ፡፡ ይህን ስም የመረጠለት ራሱ ፈጣሪአችን (በገብርኤል በኩል) ነው ፡፡ (ማቴ 1፡21 ፤ ሉቃ 1፡31) ፡፡ ወልድ ስንልም ሆነ ቃል ፣ ከሦስቱ አካላት አንዱ የሆነውን ፣ እግዚአብሔርን ማለታችን ነው ፡፡ እግዚአብሔር (ሥላሴ) በሦስትነቱና አንድነቱ እንደሚኖር ብዙ ግዜ ተምረናል ፡፡ የስም ሦስትነታቸውም አብ ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ነው ፡፡ ይህ የአንድነትና የሦስትነት ትምህርትን በገሃዱ ዓለም በትክክል የሚነጻጸረውና የሚመሳሰለው ስለሌለና ፣ ለመረዳትም ሆነ ለማስረዳት ስለሚቸግር ፣ በእምነት ብቻ ሆነው ይረዱታልና ምስጢር ይሉታል ፡፡

   አሁን ከአባቶች ትምህርት ውስጥ በመለኰት ፣ በሥልጣን ፣ በአገዛዝ ፣ በፈቃድ አንድ የሆነውን አምላክ ሦስት አካላት እንደ አሉትም አውቀናል ፤ አምነናልም፡፡
   - ለአብ ፍጹም መልክ ፍጹም ገፅ ፍጹም አካል አለው።
   - ለወልድ ፍጹም መልክ ፍጹም ገፅ ፍጹም አካል አለው።
   - ለመንፈስ ቅዱስ ፍጹም መልክ ፍጹም ገፅ ፍጹም አካል አለው።

   ይኸ አካል የተባለው ግን መንፈሳዊ አካል ነው እንጅ ፣ የሚጨበጥ ፣ የሚዳሰስ ፣ በአምሳያ ካልሆነ በስተቀር የሚታይም አይደለም ፡፡ አዋሃደ የምንለውም ይኸን ልዩ አካሉን እንጅ የራሱን ሥጋና ነፍስ አቅርቦ አይደለም ፡፡ ኢየሱስንም ቢሆን በሥጋው ወይም በሚዳሰስ አካሉ ያወቅነው ከድንግል ማርያም በነሳው ሥጋና ነፍስ እንጅ እምቅድመ ዓለም በነበረው አካሉ አይደለም ፡፡ ይህንኑም ለማስረዳት ወልድን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወልድ ዋሕድ ብላ ትጠራለች ምክንያቱም ያለመለወጥና ያለመቀላቀል ቃል ሥጋ ኮነ ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ ስለሚለን ወንጌሉ (ዮሐ 1፡14)፡፡

   ታድያ በአንተ መግለጫ ውስጥ “እግዚአብሔር ወልድ ሥጋውን ከሥጋዋ ነብሱን ከነብሷ ነስቶ” የሚለው ከየት ይዞ የመጣውን ሥጋና ነፍስ ነው ያዋሃደው ? አዲስ አገላለጽ ስለሆነብኝ ነውና የተረዳኸው ወይም የተማርከው ወይም ያነበብከው ካለ ብታካፍለን በማለት ነው ፡፡ ወይም ልትገልጽ የፈለግኸውን አልተረዳሁ ከሆነም እጅግ በጣም ይቅርታ እንድታደርግልኝ ተንበርክኬአለሁ ፡፡

   አገላለጽህ ሥጋና ነፍስ ይዞ የመጣ ስላስመሰለው ነው ጥያቄ ያቀረብኩልህ ፡፡ ዓላማዬ እየተጋገዝን እንድንማር እንጅ ፣ እኔ የሃይማኖት ሊቅና ነገር አዋቂ ነኝ በማለት እንዳልሆን እንደምትረዳልኝ ዛሬም እገምታለሁ ፡፡ እኔም ሰዎች ሊወቅሱ ብለው ከጻፉት ነው እየተማርኩ ያለሁትና ቅር አትሰኝ ፡፡

   እግዚአብሔር ሰላሙንና ጸጋውን ያብዛልህ

   Delete
 23. Tenesh atafrem maryam ye hiwot mench nat setel. Why do not you read bible. Read and find the truth. Zem beleh be teret teret atemen. Be dersanua yetelekelekew hulu lek naw letel naw. Ye tenkola sera naw yehe.

  ReplyDelete
 24. መንፈሳዊ ሐተታውን ለሌሎች ባለሙያዎች በመተው፣ "ሾክድ" ለሚለው የእንግሊዝኛ ቃል የሚመጥን የአማርኛ ቃል ጠፍቶለት ይሆን ጸሐፊው ሁለት ጊዜ የተጠቀሙበት? የነገሩን ከባድነት ለማጉላት ከሆነ እንደ ፕሮፌሰር ሌስላው የእንግሊዝኛና አማርኛ መዝገበ ቃላት አተረጓጎም:

  shock አሰቀቀ፣ አስደነገጠ፣ አሽበረ፣ አሳፈረ፣ ተብሎ ሊተረጎም ይቻል ነበር፡፡

  ReplyDelete
 25. It is very sad to see articles and comments on this web site that look like coming from "religious sholars"who want to split hair . I am not saying all our (EOTC) religious teachings and interpretations are without both small and serious problems . Although I am just an ordinary follower of the Church, I strongly believe there must be some sort of appropriate step to make appropiate corrections or reform. And I sincerely believe this has to be dealt with in a very careful and wise manner,not just on all kinds of social media or web sites such as we continue to watch on this one. I want to believe that it is a kind of arrogancy and even ignorance to try to say everything on this kind of media instead of coming up with rational and genuine suggestions on how to deal with our tradtional/customary/cultural and etc. elements highly integrated in our religious doctrines and teachings for a long,long and long period of time. I am sorry to say but I have to say that if we continue just arguing and counter-arguing on all kinds of media , I am afraid that we are kinds of 'religious scholars" who perfectly fit to the saying, " Yeqes mist awoqish awoqish beluat metsahun atebech!"

  ReplyDelete
 26. ከበደ ቦጋለ ያቀረበውን አስተያየት የተቃረናችሁ አንባቢዎች የኔም ተቀራራቢ አስተያየት ስለሆነ ማለታችሁ ስለማይቀር ይህንንም አብራችሁ እንድትመዝኑት አቅርቤዋለሁ ፡፡ የሕይወት ውኃ ምንጭ የሚለውን ቃል እግዚአብሔር ከሚል ስም ጋር ተቆራኝቶ ስላገኛችሁት ፣ በመንፈሳዊ ቅናት በመሞላት ከሌላ ቃል ላይ መደረብ የለበትም የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሳችኋልና መጽሐፍ በተለያየ ገጽ ስለ ሕይወት ውኃ መገኛ የሚገልጸውን ምን አድርጋችሁ ትተረጉሙት ይሆን ?

  1. ኤርምያስ 17፡13 የሕይወት ውኃ ምንጭ እግዚአብሔር መሆኑን ይገልጻል ፡፡ ይኸም ማለት የሕይወት ውኃ ከእግዚአብሔር ይፈልቃል ወይም ይወጣል ማለት ነው ፡፡
  2. ዘካርያሰ 14፡8 ላይ የሕይወት ውኃ ከኢየሩሳሌም ይወጣል ፡፡
  3. ዮሐ 7፡38 ደግሞ በእኔ የሚያምን የሕይወት ውኃ ከሆዱ ይፈልቃል ይላል ፡፡

  ከዚህም በመነሳት ለተመሳሳይ የሕይወት ውኃ ለሚል ቃል ሦስት መገኛ ወይም ምንጭ ስላገኘን እግዚአብሔር የተባለው ከኢየሩሳሌም ወይም ከሆድ ጋር ተመሳሳይ ነው ማለታችሁ ይሆን ነው ? ለሕይወት ውኃ ምንጭነት ኢየሩሳሌምና ሆድ የሚሉት ቃላት መጽሐፍ ላይ በመገኘታቸው ተቀባይነት ካላቸው ፣ አምላክን በድንግልና አርግዛ የወለደችው እናቱ ፣ ርሱን በማስገኘቷ የሕይወት ውኃ ምንጭ መባሏ ምን ስህተት ያመጣል ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 22, 2013 at 8:12 AM

   ምእመን

   መጽሐፍ ቅዱስን ለማጣመም ማን ብሎክ!!!

   Delete
  2. ለየተሰቀለው
   ወንድሜን ካላስቆጣሁ ነገሮችን የማስተዋልና የማመዛዘን ትልቅ ችግር ያለብህ ሆኖ ይሰማኛል ፡፡ አንተና ቢጤዎችህ የሕይወት ውኃ ምንጭ (መገኛ) የሚለውን ቃል ከአምላክ መጠሪያ ጋር ተቆራኝቶ ስላገኛችሁት (ብቻ) ፣ ከእርሱ ስም በስተቀር ፣ ከሌላ ስም ጋር ሊገናኝ ወይም ሊያያዝ አይገባም የሚል የመከራከሪያ ሃሳብ ይዛችሁ ቀረባችሁ ፡፡ እኔ ደግሞ ቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ (በብሉይም በሐዲስም) ከሌላ ቃል ጋር መገናኘቱን ለማሳየት አመጣሁ ፡፡ እንግዲህ ስለ ድንግል ብለህ ፍረድ ፤ ምኑን ነው ? አጣመምክ ብለህ የምትወነጅለኝ ፡፡

   ልብ ብለህ አስተውለህ ከሆነ ከላይ ባሰፈርኩት መልዕክት ላይ ጌታችንና አምላካችን በባህርዩ የማይገባውን ፣ ከድንግል ማርያም መስዋዕት ሆኖ በቀረበበት በሥጋ ፣ በአጥንትና በደም በመወለዱ ምክንያት ፤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሕይወት ውኃ ምንጫችን ብትባል የወንጌልን ቃል አያፈርስም በማለት ለማስረዳት ሞክሬአለሁ ፡፡

   አይ ርሱ በሥጋና በደም ከርሷ አልተወለደም ብሎ መካድ አንድ ነገር ነው ፡፡ ወይም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ አምላካችን በተዋሕዶ እንደ እኛው ሰው ሆኖ ተወለደልን የሚለው ትምህርት ስህተት ነው የሚል ካለም ሌላው አማራጩ ነው ፡፡ እነዚህን ትምህርቶች እውነት ናቸው ብሎ በእምነት ለተቀበለ ሰው ግን ፣ እውነተኛ ቀና ልብ ካለው የእመቤታችን የሕይወት ውኃ ምንጭነትን ለመረዳት ምንም አያስቸግረውም ነበር እላለሁ፡፡ ምክንያቱም ዘወትር በየሰንበቱ የጌታን ተአማኒ ሥጋና ደሙን እየተቀበለ ዘለዓለማዊ ሕይወትን ያገኝበታልና ነው ፡፡

   ጌታችን ሲያስተምርም “ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።” ብሏልና ዮሐ 6፡54 ፡፡ በሌላው ቃሉም “ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ።” ዮሐ 6፡56 በማለት ቃል ገብቷል ፡፡

   ውኃው ከየት የመጣ ነው ? ካልከኝ በመስቀል ላይ ሆኖ ስለ እኛ ኃጢአት ከፈሰሰው ደም ጋር የታየው ነው ፡፡ ሌላውም ደግሞ ፣ ደም ሁልጊዜም ከውኃ ጋር ተዋሕዶ ስለሚገኝ ነው ፡፡ መጽሐፍ “ከጭፍሮች አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው፤ ወዲያውም ደምና ውኃ ወጣ።” ዮሐ 19፡34 ይላልና

   “ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና። እንካችሁ፥ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ። ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ። ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ (ለኃጢአት ይቅርታ የሚለው ትኩረት) የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።” ማቴ 26፡26-28 ፤ ሉቃ 22፡ 19-2ዐ ፤ ማር 14፡22-24 ብሏልና

   ወንድሜ አሁንስ የመጽሐፍ ቃል አለመጣመሙን ተረዳህልኝ ?

   Delete
  3. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 22, 2013 at 7:19 PM

   ምእመን

   ወንድሜን ካላስቆጣሁ ነገሮችን የማስተዋልና የማመዛዘን ትልቅ ችግር ያለብህ ሆኖ ይሰማኛል ፡፡ አንተና ቢጤዎችህ የሕይወት ውኃ ምንጭ (መገኛ) የሚለውን ቃል ከአምላክ መጠሪያ ጋር ተቆራኝቶ ስላገኛችሁት (ብቻ) ፣ ከእርሱ ስም በስተቀር ፣ ከሌላ ስም ጋር ሊገናኝ ወይም ሊያያዝ አይገባም የሚል የመከራከሪያ ሃሳብ ይዛችሁ ቀረባችሁ ፡፡

   I told you several times that I don't have a depth knowledge of bible as you have, but my attitude looking at Keraneow and Gologota with faith help me to be a christian and know about God. you don't have to misleading us by giving unappropriated references to discredit the blood of Lord Jesus. Stop your deception messages!

   I will not be mad at you, I only mad on the devil spirit who control your life.

   Delete
  4. I think the devil spirit that blocked your learning ability is with you. you blocked your self from learning and that is why you feel that what miemen writing is misleading. It is pure argument based on logic and facts. Awuko yetegna bikesekisut ayisemam new negeru...bible tebetibito bitigatim ayikebahim. Zim bilo begologota aminalehu that is enough malet for one chrestiyan dinkurena new!!

   Delete
  5. በየትኛውም የኛ ቤተ ክርስቲያን ቢሆን እንደምትለው ፣ ድንግል ማርያምን እያዋረዱ አያስተምሩም ፡፡ አንተ ግን የት ነው የምታስቀድሰው ? ወይስ ግዕዝ ስለሆነ እኔን አይመለከትም ብለሀ ነው ከመንጋው በጅምላ የምትቆጠረው ? ከላይ ያስቀመጥኩትን የቅድስት ማርያም ቅዳሴን መለስ በልና አንብበው ፡፡ አሁን አንተን ደስ እንዲልህ ብለው ያን የቅዳሴ ቃል ይሠርዙት ይመስልሃል ?

   የአንተንና የቢጤዎችህን መማሪያ ባላውቀውም ፣ ለእኛ አብ ወልድ መንፈሰ ቅዱስን እንድናመልክ ፤ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ስለ እኛ እንደሞተልንና ድኀነታችን በርሱ መስዋዕትነት እንደተገኘች ያስተምሩናል ፡፡ ጌታን የወለደች ቅድስት ድንግል ማርያምንም ስለ ንጽህናዋ ፣ ለእናትነት ፈቃደኛ ስለመሆኗ ፣ ፈጣሪያችንን ለማሳደግ በመንገላታቷ ምስጋናና የአማልጂኝ ጸሎት ይቀርብላታል ፡፡ ከዛ በተረፈ ደግሞ ለመላእክቱ ፣ ለጻድቃኑና ለቅዱሳኑ የአክብሮትና የተራዱን ልመና ይቀርባል ፡፡

   እንዲህ መማርና መጸለይ ክርስቶስን መክዳት ወይም በርሱ ላይ ማመጽ አይደለም ፡፡ ልብህ ሸፍቶ እየተቸገርክ ካልሆነ በስተቀር ፣ ትምህርቱ ከመጽሐፍ ቅዱስ የወጣ አይለም ፡፡ በትርጉም ያስፋፉታል እንጅ ፣ ያልሆነና የአምላክን ክብር የሚቀንስ ቃል አይቀላቀሉም ፡፡ የእኔ እውቀት በቋንቋየ ከሆነልኝ ብቻ ነው ፤ ሌሎች ሊቃውንትና መጽሐፍ አዋቂ አባቶች የጸሎታችን ተሳታፊ ስለሚሆኑ ግን ደፍሮ ስህተት የሚያስተምር አይኖርም ፡፡ ኀብረተሰቡም ቢሆን ያልተለመደ ትምህርት ሊያስተምሩት ቢሞክሩ እንኳን ፣ ጭነት ማራገፊያ ስላልሆነ እንደማይቀበላቸው በቅርቡ የታዘብኩት ገጠመኝ አለ ፡፡ ምናልባት ወደፊት በምክንያት ሃሳብ እንዲሰጥበት አቀርበው ይሆናል ፡፡

   "Stop your deception messages!" ለምትለው እነርሱም ትምህርታችንን እያወላገዱ ባይጽፉ እኔ አላስቸግርህም ነበር ፡፡ እኔን በየጊዜው ከምታወግዝ ችግሩ እንዲወገድ ምክንያቱን ማወቅና ማረም ቀላል ይመስለኛል ፡፡ ከዚህ ቀደም በብዙ ቦታዎች የመፍተሄ አቅጣጫ አስቀምጫለሁ ፡፡

   "I only mad on the devil spirit who control your life." እንዲያ መስሎ ከታየህና አቅሙ ካለህ እንደ ደም መላሻችን ግርማ ለማስለቀቅ በምታውቀው ብልሃት ሞክረው ፡፡ መቁጠሪያው ስላልደረሰህ ፣ የአንተን ደግሞ በዘንግ አድርገው ፡፡ እኔ ግን በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ራሴን የማማትብና የምቀድስ ስለሆንኩ ብትመኝልኝም ክፉው መንፈስ አይቀርበኝም ፡፡ በእኔ ላይ ኃይልና ሥልጣን ያለው በቀራንዮ መስቀል ላይ ደሙን ያፈሰሰልኝ ፣ ከምላሴ ሳይሆን በልቤ ላይ መሠረቱን ያኖረ አንድ ጌታ ብቻ ነው ፡፡

   በተረፈ ሃሳብ ስላጋራኸኝ ጌታ ይባርክህ!!! ሰላሙንም ያብዛልህ!!!
   ቅር እንዳይለኝ አትጥፋ ፡፡ ወደ በደል እንዳልመራህ የምትበሳጭ ሰው ከሆንክ ግን ከኔ ጋር አትግጠም ፡፡

   Delete
  6. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 23, 2013 at 7:57 AM

   ምእመን

   "I only mad on the devil spirit who control your life." እንዲያ መስሎ ከታየህና አቅሙ ካለህ እንደ ደም መላሻችን ግርማ ለማስለቀቅ በምታውቀው ብልሃት ሞክረው ፡፡ መቁጠሪያው ስላልደረሰህ ፣ የአንተን ደግሞ በዘንግ አድርገው ፡፡

   Ye ne deme melashe gene Kirstose new. Ken de ante anyentu be sitan menfese teseneso kadege ena Kemenore sew gare gizeyene matfafe alfelgem. Ante malete ye mesekelu telate nehe!

   Delete
  7. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 23, 2013 at 8:11 AM

   AnonymousJanuary 22, 2013 at 8:46 PM

   Zim bilo begologota aminalehu that is enough malet for one chrestiyan dinkurena new!!

   Answer For the above statement:
   Gologota sitan yeteshenfebet new, ante ke sitan kalhoneke bestkere end ምእመን , beza bota lay sitanen del yenesawen Geta Eysusine tamen neber.

   Delete
  8. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 23, 2013 at 8:50 AM

   ምእመን

   "እንዲያ መስሎ ከታየህና አቅሙ ካለህ እንደ ደም መላሻችን ግርማ ለማስለቀቅ በምታውቀው ብልሃት ሞክረው"
   You said the above statement, I am proudly saying the following:

   የጌታን ስም የሚጠራም ሁሉ ይድናል። የሐዋ ሥራ 2:21 እና እዩኤል 2:32
   የግርማን ስም የሚጠራ ሁሉ ይሞታል።

   Delete
  9. ለየተሰቀለው
   እንደ ሰው ማለትም እኔም እንደማደርገው ፣ የምታርመው ቢሆን ድክመትህን ላስነብብህ ፈለግሁ፡፡ እኔ አንድን ሃይማኖትን የተመለከተ ጽሁፍ ወይም ሃሳብ ሳገኝ ፣ ከቤተ ክርስቲያናችን ትምህርተ ሃይማኖት አኳያ (ለዛውም ጠንቅቄ ሁሉን አላውቀውም) ፈትሼ የሚያስኬደኝን ግንዛቤ ከወንጌል ቃል እያጣቀስኩ እሞግታለሁ ፡፡ የእኔ ቃል የማይሻር የእግዚብሔር ቃል ስላልሆነ ፣ ማንኛውም ሰው ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃልን እያመጣ ሊያርመኝ ፣ ሊያስተምረኝ ፣ ሊያስተካክለኝ አሁንም እንኳን ፈቃደኛ ነኝ ፡፡ በዛ መንገድ ካልቀረበልኝ ግን ፣ የኔው ሃሳብ ትክክል ነውና ጌታን ተቀበል ተብሎ ከየመንደሩ ለተነዳው መንጋ ፣ ያለ ዕውቀት ስለሆነ ቤተ ክርስቲያኑን የካዳት ፣ ሃቅን እንዲረዳ ለማስነበብ እሞክራለሁ ፡፡ እዚህ አካባቢ በሆነ ምክንያት የተለያየው ወገን መመላለሱ ስለማይቀር የደረስኩበትን እውነታ ለመግለጽ እታገላለሁ ፡፡ አንተም እውነት አለኝ የምትል ከሆነ አቅርበውና አሳምነኝ ፡፡ እኔ በደፈና አላምንም አላልኩም ፡፡ ግን እውነት ስለሌላችሁ ልታሳምኑኝ አትሞክሩም ፤ አትችሉምም ፡፡

   ጀሆቫዎችንና ወንጌላውያን ነን የሚሉትን ቢጤዎችህን በሬን እያንኳኩ እናስተምርህ ሲሉኝ ፣ እንዴት ተደርጎ በማለት በር አልጠረቅምባቸውም ፡፡ በሥርዓቱ እንዲያስተምሩኝ ወንበር አቅርቤ ዕድል እሰጣቸዋለሁ ፡፡ የሚሉትን በሙሉ አዳምጨ ካስጨረስኩ በኋላ የእኔን መግለጫ ፣ ማብራሪያና ጥያቄ ሲሰሙ ግን ሁለተኛ ድርሽ አይሉም ፡፡ አትምጡ ብያቸው ሳይሆን ፣ በራሳቸው ያለ መጽሐፍን የመረዳት ደካማነት ወይም የሃሰት ሐዋርያነት (ስለ እንጀራና ኑሮአቸው በማለት የሚደክሙ ስለሆኑ) ነው ፡፡ እንዲያውም በጊዜ እጥረት ምክንያት ራሴ ቀጠሮ አስይዤ የተለየኋቸው እንኳን ፣ ግፋ ቢል ከሁለት ጊዜ በኋላ ተመልሰው አይጎበኙኝም ፡፡

   አሁን አሁን ደግሞ ገና ሲጠይቁኝ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ መሆኔን ስገልጽላቸው ፣ አንዳንዶቹ ሌላ ጊዜ እንመጣለን በማለት በራሳቸው ፈቃድ ከበር መመለስ ጀምረዋል ፡፡ የነርሱም ይሻል ይመስለኛል ፤ ለምን ቢባል ፣ አሁን አንተ ከነርሱ የባሰ ነገር እያሳየኸኝ ስለሆነ ነው ፤ መልስ ስታጣ ወደ ዘለፋ ገብተሃል ፡፡ ጀርባዬ ለእንደዚህ ዓይነቱ ስልትም የገበረ ስለሆነ ደንዝዟልና በከንቱ አትድከም ፡፡ አደራህን የምለምነው ግን ከአንድ ሁለት ወር በኋላ ዛሬ የጻፍከውን ተመለስህ እንድታነበው ነው ፡፡ ትክክለኛ ክርስቲያን ከሆንክ በራስህ ሥራ ታፍራለህ ፡፡ ጤነኛ አእምሮ ካለህ ደግሞ ያስለቅስሃል ፡፡

   ቃልህ ፡- “Ken de ante anyentu be sitan menfese teseneso kadege ena Kemenore sew gare gizeyene matfafe alfelgem. Ante malete ye mesekelu telate nehe!”

   አየህ አይደል ክፉ መንፈስ እንዴት አድርጎ በሕይወትህ እንደሚጫወት ፡፡ አሁን ከየት ወገን የመጣ ትምህርት ነው ሰይጣንም በመንፈሱ የሰው እናትን እያስረገዘ ልጅ ያስወልዳል የሚለው ? ወይስ የመንፈስ ቅዱስን ክህሎት ለጌታህ ዲያብሎስም ልታጋራው ፈልገህ ይሆን ? እንደ እኔ ከሆነ የሰይጣን ማደሪያ ሆነሃልና ፣ ሄደህ የኪዳነ ምሕረትን ጠበል ለሰባት ቀን ተጠመቅ ፤ ያው እንደ ልማዱ አስጓርቶ ይለቅሃል ፡፡ እንዲህ ዓይነት ምስጢር ከተገለጸልህ ደግሞ ያለህ ሌላው አማራጭ ስድስተኛውን ወንጌል ጽፈህ ለብጤዎችህ ማስተማር ነው ፡፡ እኔን አንገት ለማስደፋት ብለህ ፣ እዚህ ብዙ ህዝብ በሚያነበው ላይ የጅል ቋንቋም አትጠቀም ፡፡

   እግዚአብሔር ሰላሙን ያብዛልህ !!! ምሕረቱንም ያውርድልህ ፡፡

   Delete
  10. @ ምእመን '' ኀብረተሰቡም ቢሆን ያልተለመደ ትምህርት ሊያስተምሩት ቢሞክሩ እንኳን ፣ ጭነት ማራገፊያ ስላልሆነ እንደማይቀበላቸው በቅርቡ የታዘብኩት ገጠመኝ አለ ፡፡''

   Brother, I expect more than this from you. This statments seems shallow. If I remember correctly, you once said the Ethiopian people in general need to be taught the gospel more because although we're one of the first Christian nations in the worlsld, we still haven't fully grasped the messege. Which I agree with. But the above statement seems to indicate the people are already knowledgeable enough to the point where they can sit down and critic the ''memhir'' that is humbly standing before them. If they hear something they don't like or some new teaching, they're ready to reject. Bro, then you're telling us they're all scholars which seems to contradict with your previous thought. Of course they will hear something new they haven't heard before. ''new'' doesn't mean wrong. Even throughout my short life, I have seen things that were considered alien to the orthodox faith become the norm now a days. So rejecting someting just because it's ''new'' might eventually make you in the back end of history so think about that

   Delete
  11. ሰላም Ewnt
   1. "If I remember correctly, you once said “the Ethiopian people in general need to be taught the gospel more”"
   እንዲህ ያልኩበትን አስተያየት ርዕስ ብታስታውሰኝና ባነበው ምክንያቴን አስረዳህ ነበር ፡፡ እንዲህ አንተ እንደ አሰፈርከው የተቀራረበ እንኳን ብዬ ቢሆን ፣ ስህተትነቱ አይታየኝም ፡፡ ምክንያቱም
   1. ክርስትና ጉዞ ነው ፡፡ ወንጌል ትንሽ መጽሐፍ ቢመስለንም ምሥጢሩን ለመረዳት ህይወትን ሙሉ እንኳን ቢሰጡት ስለማይጠናቀቅ ነው ፡፡ አራቴ አምስቴም አንብበኸው ስታበቃ ፣ ስትመለስ አዲስ ሆኖ ታገኘዋለህ ፡፡ ይኸ የወንጌል ጸባይ ነው ፡፡ ማስታወሻ ይዘህ ከዚህ እስከዚህ እንዲህ ይላል ብለህ የምትደመድመውና የምትዘጋው ዓይነት ትምህርት አይደለም ፡፡ ባነበብከው ቁጥር ዕውቀትህ እየጨመረ ይሄዳል ፤ ለማንበብም የሚያተጋህ ይኸው የማያበቃ እንቆቅልሹ ነው ፡፡

   2. የአገራችን ሕዝብ ማለትም ቀደምት አባቶቻችንና እናቶቻችን በእምነት ከማንኛችንም በላይ አድገዋል እንጅ ፣ በወንጌል ቃል ዕውቀት ብዙ የሚሉ ስላልሆኑ ማለት ይቻላል ፡፡ ሌላውም ምክንያት ደግሞ አብዛኛው አማኝ ማንበብና መጻፍ ስለማይችል ፣ ያለው የወንጌል መረጃ የቃል ዕውቀት ነው ፡፡ በቃል ያለ ደግሞ ይረሳልና ለማስታወስ በየጊዜው ማስተማር ያስፈልጋል ፡፡

   3. ኢትዮጵያ ቀደም የክርስትና አገር ተብላ ብትታወቅም ፣ የወንጌል ስብከት ሁሉንም ህዝቦቿን አላዳረሰም (የተሰራጨው በአብዛኛው በሰሜንና መሃል አገር ብቻ ነው)፡፡

   አሁን የሚደረገው ፍትጊያ ፣ በዋና ከተማዎችና ራሱን ክርስቲያን ብሎ ከሚጠራው ወገን ጋር ሆነ እንጅ ፣ ክርስትና ያልተሰበከለት የወገናችን ቁጥርማ ቢያንስ ዛሬም ከግማሽ በላይ ይሆናል ፡፡ ወደ ዳር አገር ሄዶ ፣ ሆቴል ሳይሆን መሬት እያደረ ፣ በመኪና ሳይሆን እንደ ሐዋርያቱ በእግር እየተጓዘ ኀብረተሰቡን የሚያስተምር ስላልተፈጠረላት ማለት ይቻላል ፡፡ አሁን የሚታየው ሽኩቻ ገበያን ለመቆጣጠር የሚደርግ ትግል ነው ፡፡ የመዝሙር ፣ የስብከት ካሴትና ሲዲ ፣ መጽሐፍ የመግዛት አቅም ያለውን ክርስቲያን ነኝ በሚለው ላይ ርብርቦሽ ነው ፡፡ እስቲ እንደ ደቀ መዛሙርቱና አርድዕቱ መኪና ከማይገባበት በእግር ፣ በበቅሎና በአህያ ለማስተማር የሚንቀሳቀስ ቡድን ይፈጠርና የሚደግፈው ይጥፋ ፡፡

   2. “ኀብረተሰቡም ቢሆን ያልተለመደ ትምህርት ሊያስተምሩት ቢሞክሩ እንኳን ፣ ጭነት ማራገፊያ ስላልሆነ እንደማይቀበላቸው”
   እኔ ታዘብኩ ያልኩትን እንዲህ በአጭሩ አልገልጸውም ፡፡ ይኸን ያልኩት በክርስትና እምነት የቆየው ኀብረተሰብ በቃልም ቢሆን ሥርዓቱንና ትምህርቱን ለምዷልና ፣ ሊቀይሩበት ቢሞክሩ አይቀበልም ማለቴ ነው ፡፡ አሁን ለምሳሌ አንተ ቤተ ክርስቲያን ስትገቡ ጫማ አታውልቁ ፣ ወይም አንድ እህትህን በወር አበባ ላይ እያለች ግቢና አስቀድሺ ፣ ምንም ችግር የለውም ብትላት አንዳቸውም አይቀበሉህም ፡፡ ትዝብቴም ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ በእምነት ያለውን ክርስቲያን የተመለከተ እንጅ ከውጭ በአሉባልታ የሚወራውንና የሚታየውን አይደለምና ጊዜ ስጠኝ ፡፡

   ሰላም ሁንልኝ

   Delete
  12. ምእመን lets invite you as always!lemn endemgabzh tawkaleh bewnet lebitkrstyan yaleh fkr des slemilegh new...almeslcheth hulie yasdenkeghal !!betselot alleyhm antem betselot asbegh..... 1. http://tewahdo.org/index.php?option=com_content&view=category&layout=blog&id=39&Itemid=86 2. http://antiglobalconspiracy.blogspot.com/ 3. 3.http://www.tesfayerobele.com/resources/default.aspx 4.http://www.youtube.com/watch?v=UwYQqime9nc 5.http://www.ethkogserv.org/....ykoyen hule gbza tebk endatselechbgn!!

   Delete
  13. @ምእመን
   Betam amesegenalw wendema, arif mels new yesetehegn. I would like to mention one thing. I have noticed even those that have attended church since their youth, haven't fully comprehended the orthodox faith. For most people, it's just a habit. They never ask questions, never question anything, we just like to follow what we are told and what our parents taught us. I think this is wrong. Faith is not a game. Our life after death depends on it.

   "በክርስትና እምነት የቆየው ኀብረተሰብ በቃልም ቢሆን ሥርዓቱንና ትምህርቱን ለምዷልና ፣ ሊቀይሩበት ቢሞክሩ አይቀበልም ማለቴ ነው ፡፡"
   Let me give you an example. In abune gorgorios' book "Ye ethiopia orthodox tewahido tarik" Abatachin talk about "tsega & kibat" faith that was very common in gojam and shewa part of ethiopia. The people from those part of ethiopia and the likwant at those places, rejected the teaching of "tewahedo". Imagine if they continued with that false teaching what kind of damage it would have for our church and the uncountable souls that would have been lost. Imagine if the people kept rejecting the teaching of "tewahido" because it's "new" to them. All I'm saying is, just because we think it's new, it doesn't mean it's wrong. Just because we think it's new, it doesn't mean it's actually new. Maybe it's new to us, but all along it was all there since the beginning. Give it a thought bro

   Delete
  14. ewnt ለአንተም ምስጋናዬ ትድረስህ
   እኔ ለማስረዳት የሞከርኩት የብዙሃኑን ህዝብ እምነትና አምልኮ ነው ፡፡ የተማሩና የተፈላሰፉትማ የራሳቸውን እምነትና እውነት ለማስረዳት ፣ ሊቅነታቸውንም ለማስከበር ፣ የማይፈነቅሉትና ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም ፡፡

   እንዳስቀመጥከው አዲስ የሆነ ትምህርት ሁሉ መጥፎ ነው የሚል እምነት እኔም የለኝም ፡፡ የወንጌል ትምህርት በግዕዝ ስለነበረ አማኝ የነበረው ወገናችን ምን እንደተማረ አልተገነዘበም ነበር ማለት ይቻላል እንጅ ላመነና ለተጠመቀው ህዝብ ወንጌል አዲስ ነው የሚል ፈሊጥና አገላለጽ ስህተት ነው ፡፡ በዚህ ዘመን አዲስ ሊባል የሚቻለው ለጆሮው የሚፈስለት ከግዕዝ የተለየ ፣ ሊረዳው በሚችል ቋንቋ መሆኑ ብቻ ነው ፡፡

   ቀድሞውንም የፈጠረው አምላክ እንዳለው ገብቶታል ፤ በጎ ምግባርና በሥርዓት መኖርም እንደሚገባው ያውቃል ፤ እምነቱን በምግባር መተርጎምና መኖር እንዳለበት አምኗል ፡፡ አሁንም ያንኑ አምልኮቱን በሚገባው ልሳን ተረድቶ እንዲቀጥል ማድረግ አዲስ ትምህርት እንደመጣ አድርጌ አልቆጥረውም ነበር ፡፡ ኩላሊትና ልብን የሚፈትሽ አምላክ የሚመዝነው እምነቱንና አምልኮቱን እንጅ በቋንቋ መረዳቱንና ስሜቱን ለፈጣሪው በቆንጆ ቃላት መግለጹ ፣ በነገር መራቀቁንም እንዳልሆነ አምናለሁ ፡፡

   በእኔ በኩል አዲስ ተብሎ የሚነቀፈው በማይረዳው ልሳን ቢሆንም ሲተላለፍለት የነበረውን ትምህርተ ሃይማኖት የሚንድበት ባዕድ ትምህርት ሲመጣ ነው ፡፡ አሁን ወንድማችን ጸጋ ያስነበበንን ረጋ ብለህ ተመልከተው ፡፡ ድንግል ማርያምን ልጅዋ ኢየሱስ ፣ እናቴ አይደለችም ብሏታል ፤ አነጋገሩ እንኳን አንቺ ሴት እያለ ነው ፤ ቅድስት ድንግል ማርያም አታማልደንም ፤ እንዲያ የሚል ቃል አልሰፈረም …….. የሚል ነው ፡፡ እንዲህ የሚለኝ አስተማሪ በጣም ችግር አለው ፡፡

   የመረዳት አቅሙ ካለን ወንጌል ላይ የሠፈረው እያንዳንዱ ቃልና ዓረፍተ ነገር (ይሰመርበት) የተጻፈው የቋንቋን ውበት ለማሳየትና ለማራቀቅ ሳይሆን በትክክል የሆነ መልእክትን ለማስተላለፍ ነው (የወንጌል ጥናት ማብቂያ የለውም የሚለውን ሃሳብ የምቀበለውም ስለዚህ ነው)፡፡ ስለምን ወይን አልቆባቸዋል ማለቷ ተገለጸልን ? ቃላት በመደርደር ወረቀትና ቀለም ለመጨረስ? አይደለም ፡፡

   ይህን የመሰሉትን መጤና በካይ ትምህርቶች ነው የምነቅፋቸው እንጅ ኢየሱስ ከድንግል ማርያም ተወለደ ፣ ለማስተማር ወጣ ወረደ ፣ መጨረሻም ስለ እኛ ኃጢአት መስዋዕት ሊሆን በመፍቀዱ በመስቀል ላይ ሞተ ፣ በሦስተኛው ቀን ተነሳ እያለ በርሱ እንድናምን የሚያስተምረንን ፣ የእግዚአብሔርን ፍቅር ገላጭ አስተማሪ በምንም መልኩ መሰናክል አልሆንበትም ፡፡ የቤተ ክርስቲያናችንን ትምህርት ሳይነቅፉ የሚጽፉ ፣ የሚሰብኩ ፣ የሚዘምሩ ወገኖች እንደ አሉ አውቃለሁ ፡፡ ነገር ግን ከነርሱ ጋር ምን ግዜም ቢሆን ግጥሚያ የለኝም ፡፡ መልካሙን መንገድ ተያይዘውታልና ፡፡ ካልነቀፈ የሚያሰተምር የማይመስለው መምህር ፣ ለአሠሪዎቹ እንደሚያገለግል እንጅ የወንጌል መልእክተኛ ነው ብዬ በበኩሌ አልቀበለውም ፡፡

   ሰላም ሁንልኝ

   Delete
  15. I think you somewhat misunderstood me. My discussion is not about language barrier (Geez). Although that was a problem in the past. What I'm saying is, in this generation the problem is rejecting anything we feel is wrong. We as a church should be open to criticism from others because eventually truth will outshine. But if we have the mentality of unlearned, uncompromising dictator, we will never grow as a church. If we still adhere to the common saying ''ke abatochachin weg ena seriat anenekanekim'', we're jeopardizing our life to come. Hey I believe we should follow the teachings of apostles. But we have to test everything if it's in line with apostles and the great church father that came after. Have you ever thought of the possibility, maybe Tsega is in line with the teachings of the church fathers and you might be wrong. Why are we quick to lable wrong any teaching we ''think'' is new? What if you're wrong? how do you dismiss all the proof provided? by the way, I think you are wrong in your assessment of this article. I believe in St. Mary's intersession and I believe she and all the saints pray for me because I'm a sinner. I don't see anywhere that says ''mariyam atamalidim''. he's pointing out the fact how the current generation distorted ''kana ze Gelila'' holiday. It's supposed to be one of our Lord's 9 minor holiday but we have changed the meaning. This is how I see it. But if Tsega doesn't believe in St. Mary's intersession, well that's a loss for him and it's unorthodox. But until then, I can't assume that's what he's trying to imply

   Delete
  16. ለ Anonymous January 23, 2013 at 3:27 PM

   እንድመለከት አድራሻ ያስቀመክልኝ ጋባዥ ወገኔን በጣም አመሰግንሃለሁ ፡፡
   http://antiglobalconspiracy.blogspot.com/ 3.

   http://www.tesfayerobele.com/resources/default.aspx
   እነዚህ ሁለቱን አላገኘኋቸውም ፡፡

   http://www.ethkogserv.org የሚለው ደግሞ ለየት ያለ ሃይማኖት ስለመሰለኝ ለዕውቀት ያህልም ቢሆን የሚያስረዳኝ ሰው እፈልጋለሁ ፡፡ በቀላሉ ለመመልከት በቀን መቁጠሪያ ላይ ያሰፈራቸውን መመልከቱ ይበቃል ፡፡ አሁን በቅርቡ አባቶች ስለወሰዱት ርምጃ አስመልክቶ ያወጣውን መግለጫ ተመልክቼው ትንሽ ግር ብሎኛል ፡፡ የተወጋገዘ አባት ፣ ሊባርክ ፣ ሊቀድስ ፣ ሌላ ቀርቶ አብሮ ሊጸልይ አይገባውም ይላል ፡፡ ውግዘቱ ሳይነሳ ምንም ዓይነት ሥልጣን ሊኖረው አይችልም የሚል አቋምም አለው ፡፡ ኮማንደር አሰፋ ሰይፉ የተባሉ ሰውም ቤተ ክርስቲያናችንን እናድን በማለት ያሰፈሩት ከንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ አቋም የተቀራራበ መልዕክት አለው ፡፡ ስለ ትምህርቱ የምታውቀው ካለ ትንሽ መግለጫ ብታክልበት ደስ ይለኛል ፡፡

   ስለሁሉም አመሰግናለሁ

   Delete
  17. ለ Ewnt
   ከቃልህ እነዚህን መርጫለሁ
   1. “We as a church should be open to criticism from others because eventually truth will outshine.”
   2. “If we still adhere to the common saying ''ke abatochachin weg ena seriat anenekanekim'', we're jeopardizing our life to come. ”
   3. “I believe we should follow the teachings of apostles.”
   4. “I don't see anywhere that says ''mariyam atamalidim''.

   መልሶቼን ከላይ ባሉት ቁጥሮች መሠረት አንብባቸው
   1. የዚህችን ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ለመተቸትማ የትኛውም የሃይማኖት ዘርፍ አላረፈም ፡፡ ነገር ግን ስለተቹኝ እያልኩ የምከተል ቢሆን መድረሻዬን መቁጠርና መጨረስ እንኳን አልችልም ነበር ፡፡ ወንጌልን መመርመርና ማስተማር ሥራቸውና ሕይወታቸው አድርገው የሚንቀሳቀሱ አባቶች በሲኖዶስ አሉና እነርሱ ከሚሉት ውጭ በእኔ ሚጢጢ እውቀት ይህ ነው ፣ ያ ነው ትክክሉ እያልኩ ከዘፈነልኝ ሁሉ ስነጉድ አልገኝም ፡፡

   2. ሃይማኖታችን የምርምር ውጤት አይደለችም ፡፡ ከአባቶች በትውፊትና በጽሁፍ ቅብብሎሽ የደረሰች ናት ፡፡ ይኸንን ወግና ሥርዓት በአእምሮ ብልሃት ተመርተን ካፈረስነው ፣ እምነታችን ጥበብ ወለድ ማለቴም የምርምራችን ግኝት ትሆንና ብልጥ ብቅ ባለ ቁጥር በአዳዲስ የፍልስፍና ቋንቋ ስናጋፍር ልንኖር ነው ማለት ይሆናል ፡፡ ሃይማኖት አንድ ናት የሚለውም ቃል ከንቱ ይባላል ፡፡

   3. የእኔም እምነት እንዳልከው ነው ፡፡ እኔ ግን የሐዋርያቱ ትምህርት ያለበትንና የሚለውን ለይቼ ስለማላውቅ ፣ አሁንም የቤተ ክርስቲያናችን አባቶች የሚያስተምሩኝን ከሐዋርያቱ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን ነው ፣ እውነት በማለት በሙሉ ልብ አምኜ የተቀበልኩት ፡፡

   ዝም ብለን ሐዋርያቱ ፣ ሐዋርያቱ ብለን እንደ ጸሎት ቃሉን እንደግማለን እንጅ ፣ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ከጌታ ትምህርትና መልሶች ውጭ የየትኛውም ሐዋርያ ትምህርት ቢሆን ተዘርዝሮ አልተጻፈም ፡፡ ጳውሎስ አደባባይ ላይ ምን እያለ እንዳስተማረ የሚያስነብበኝ አንድ ሰው እንኳን አላገኘሁም ፡፡ ሌሎቹም ቢያንስ በጌታ የተመረጡት አሥራ ሁለቱ (በይሁዳ ምትክ ጳውሎስን አክለህ) በዚህኛው አደባባይ በዛኛው ቤተ ክርስቲያን ወይም ጉባዔ እንዲህና እንዲያ አስተማሩ ተብለን እንኳን አናውቅም ፡፡

   ለግለሰቦችና ለጉባኤዎች የተጻጻፉትን (አንዳንዶቹም የማይገቡን ለምሳሌም የጳውሎስ የብራና መጽሐፍ ምንነት) ደብዳቤዎች ነው ትምህርት ብለን እያነበብን ያለነው ፡፡ እያንዳንዱ ሐዋርያ ከያዕቆብ (የዮሐንስ ወንድም) በቀር ቢያንስ አምስትና አሥር ዓመት ፣ ከዛም በላይ የግልጋሎት ዘመን አለው ፡፡ ታድያ እየተዘዋወሩ ያስተማሩት እስቲ ማስረጃ ሆኖ ይቅረብልንና እንማርበት ፡፡ በብዙ ቦታ ከሚያስተላልፉት መልዕክት እንዳየሁት ፣ ይህች የሐዋርያቱ የምትል ቋንቋ የሉተርን ትምህርት መጠቅለያ ሆና ነው ያገኘሁዋት ፡፡

   4. ቤተ ክርስቲያናችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነቷን የምትገልጸው በዚሁ ሠርግ ቤት ከፈጸመችው ተግባሯ ነው ፡፡ ይኸውም ጌታን የወይን ጠጅ አልቆባቸዋል ብሎ በማሳሰቧ ፡፡ ይህንን ማማለድ ይሉታል ፡፡ የጸጋ ቃልን ደግሞ ተመልከተውና ራስህ ፍረድ ፡፡

   ቃሉ ፡- “የቃና ዘገሊላ ተአምር እንዲታሰብበት ጥር 12 ቀን የበዓል ቀን ሆኖ ተሠርቷል፡፡ በዓሉ የጌታ በዓል ነው፡፡ ውሃውን ያለማንም ጣልቃ ገብነት ወደ ወይን የለወጠውም ብቻውን ተአምራትን የሚያደርገው ጌታ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በተለይ ቃና ዘገሊላ የጌታ በዓል መሆኑ እየተረሳና የማርያም በዓል እየሆነ መጥቷል፡፡ እኔም የዚህ በዓል ባለቤት ማነው? ብዬ እንድጠይቅ ያደረገኝ ይህ ነው።”

   “….ሲጀመር የእርሷ ጥያቄ ምልጃ ነው ወይ? ምልጃ ነው ለማለት የሚያበቃ ነገር በጥያቄዋ ውስጥ አናይም፡፡”

   “በቅድሚያ እናቱን እናቴ በማለት ፋንታ «አንቺ ሴት» ብሎ በማክበር ቃል ግን ደግሞ የሩቅ ሰውን በሚያናግሩበት መንገድ መጥራቱ ያስገርማል፡፡” በመቀጠልም የጻፈውን አንዳች ሳትወግን ሁሉንም አንብብ ፡፡ መላው እንዲሁ የጌታን እናት የሚያብጠለጥል ሐረግ ነው የምታገኘው ፡፡ ከእኔም የተሻለ ብዙ እንደሚያውቅ አውቃለሁ ፡፡ በሚጽፈው ግን አውቆ እያጠፋን ነው ያለው ፡፡

   አቋምህን ስለገለጽህልኝ አመሰግናለሁ
   ሰላም ሁንልኝ

   Delete
  18. ወንድም ጸጋ ካጠየቁት ቃል የተረዳሁትን ያህል ለማብራራት

   ጌታችን እመቤታችን ድንግል ማርያምን ስለምን አንቺ ሴት ብሎ ጠራት ?

   ጌታችን “አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት።” ብሎ (ዮሐ2፡4) የገለጻት ፣ ጾታዋን ለማስረዳት ወይንም እንደማያውቃት የሩቅ ባዕድ ሰው አድርጎ ስለተመለከታት ፤ አንዳንድ ወገኖች እንደሚገምቱትም ወላጅ እናቱን ለማዋረድ አይደለም ፡፡ ቢሉንም እንኳን አምላክነቱና ቅዱስነቱ ከነዚህ ሁሉ ገለጻዎችና አባባሎች ጋር አይጣጣሙም ፡፡ ይልቁንም ከአነጋገሩና ካስከተለው መግለጫ እናቱን ዘወትር የሚጠራበት ስም ይመስላል ፤ እኛ ታታዬ ፣ እምዬ ፣ የኔ ዓለም ወይም እናት ዓለም እንደምንለው የመሰለ ማለት፡፡

   ይኸንኑ ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ግዜ መጠሪያ አድርጎ የተጠቀመው የመጀመሪያው ሰው ፣ ማለትም አዳም ነው ፡፡ የአጥንቱ ክፋይና የሥጋው ቁራሽ ለሆነችው አካሉ ያወጣላት (ከበደል በፊት የነበረ) ስም ሴት የሚል ነው ፡፡ “አዳምም አለ። ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋዋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል።” (ዘፍ 2፡23) ይላል፡፡ ጌታችንም ከእመቤታችን ጋር በነበረው የሥጋ ፣ የደምና የአጥንት አንድነት (በተዋሕዶ) እንዲሁም ንጽህናዋንና ቅድስናዋን ስለሚያውቅ እንደቀዳማዊት የአዳም ባልደረባ አንቺ ሴት ብሏታል ፡፡

   ከበደልና እርግማን በኋላ ደግሞ ፣ አዳም ለሚስቱ ያወጣላት ሌላ ስም ሔዋን የሚል ነው ፡፡ ትርጓሜውም የሕያዋን ሁሉ እናት ማለት ነው (ዘፍ 3፡2ዐ)፡፡

   “ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ?” የሚለውን ገለጻ በአንደምታ ትርጓሜ ሲያስፋፉት አንድም እናቴን አይሆንም እልሽ ዘንድ ካንች ጋር ምን ጸብ አለኝ ፤ ከሠርግ ቤት ተጠርቼ መጥቼስ ውኃውን ጠጅ ላላደርግላቸው ነውን ማለቱ ነው ፡፡ አንድም ወኀውን ጠጅ አድርጌ የማጠጣቸው በኔ ፈቃድ ነው እንጅ በአንቺ ትእዛዝ ነውን ብሎ ለማጠየቅ (አምላክን በጸሎት ያሳስቡታል እንጅ አያዙትም ለማለት)፡፡

   “ጊዜዬ አልደረሰም” ማለቱም ፤ አንድም ሥራውን የሚሠራበት ቀንና ሰዓት አለውና ያንን ለማስገንዘብ ፤ አንድም ጠጁ ሙጥጥ ብሎ ባለማለቁ ፣ የነበረውን አበረከተውና ሰጣቸው እንዳይባል ፈልጐ ፤ አንድም ይሁዳ ከደቀ መዛሙርቱ መሃል ተለይቶ ወጥቶ ነበርና ፣ ከተአምራቱ ቢለየኝ ነው እንጂ በከህደት የገባሁበት እንዳይል ነው ፡፡ ሌላው ደግሞ አንድ ወንድም እንዳስረዱን ድኀነተ ዓለምን የሚመሰርትበትንና መስዋዕት የሚሆንበትን ሰዓት ለመናገር ነው ፡፡

   ጌታችን ስለምን “እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው?” አለ

   ማቴዎስ ፲፪ን ከላይ ጀምሮ ፣ የምዕራፉን ሙሉንባብ ብንከታተል ፣ ኢየሱስን የሚከታተሉ ሰዎች ማንነትን ለማወቅ እንችላለን ፡፡ እነርሱም ደቀ መዛሙርቱና ርሱን የሚሞግቱ ፈሪሳውያን ፣ በምኩራብ የተሰበሰቡ አይሁዶች ፣ እጁ የሰለለች ሰው ፣ እንዲፈውሳቸው የሚከተሉ በድውይና በሕማም የተጠቁ ሰዎች ፣ ጋኔን ያደረባቸውና ዕውሩ ሰው ናቸው ፡፡

   ፈሪሳውያን በሰንበት ቅጠል አይበጠስም ፤ እግር አይሰበሰብም ብለው የሚያምኑ ሰዎች ናቸው ፡፡ ከላይ በምዕራፉ መግቢያ ስለ ሰንበት መከበር ተከራክረውት በመልሱ ስለ አፈሩ ፣ ወጥተው እስከ መመካከር ደርሰዋል ፡፡ ከዚህም በላይ ደግሞ በዚህ ሰው ተአምራት ሰው ይሰበሰባል ፤ ወንጌልም ትሰፋለች ፤ ኦሪት ደግሞ ትጠፋለች በሚል ፍርሃት ስለተናወጡና ኋላም በተከታታይ ለህዝብና ለነርሱም በሚያሳየው የፈውስ ተአምራት በመቸገራቸው ፤ ስሙን ለማጥፋት በመፈለግ በብዔል ዜቡል አጋንንትን ያወጣል ብለው ወነጀሉት ፡፡ በዚህም ጌታችን የእፉኝት (መርዛማ እንስሳ) ልጆች በማለት ገሰጻቸው ፡፡ ይህን ያለበት ምክንያትም በህዝብ መሃል የሚናገሩት ኀብረተሰቡን በቀላሉ ሊቀበለው የሚችል የሃሰት ውንጀላ ስለሆነ ነው ፡፡

   ከዚህ በኋላ ደግሞ አንዳንዶች ፈሪሳውያን ሊያምኑት ፈልገው ይመስል ፣ ምልክት የሚሆን የበለጠ ተአምር እንዲያሳያቸው ጠየቁት ፡፡ ርሱ ግን ስለ ሞቱና ትንሣዔው በዮናስ የዓሣ አንባሪ ሆድ ውስጥ ታሪክ ምሳሌ አድርጎ ተናገረ ይለናል ፡፡

   አሁን በማጠቃለል ከዚህ ንባብ የምንረዳው ርሱን ለመቃወምና ሥራውን ለማስተጓጐል የሚከታተሉ ትጉሃን ብዙ ነበሩ ፡፡ ስለዚህም ደግሞ ወደዚህች ምድር የመጣበትን ምክንያት ለማስተማር በተጋበት ወቅት ፣ ምናልባትም ከተቃዋሚዎቹ አንዱ ሊሆን የሚችል ሰው (ከደቀ መዛሙርቱ ከሆነ ይሁዳ ፣ ወይም ከፈሪሳውያን አንዱ) ሥራውን እንዲያቋርጥና የሚከተሉትም ሰዎች እንዲበተኑ ፈልጎ “እነሆ፥ እናትህና ወንድሞችህ ሊነጋገሩህ ፈልገው በውጭ ቆመዋል” አለው።

   ጌታችንም ይህን የተንኰል ዕቅድና ዓላማ በመረዳቱ ፣ ሥራውን በምንም መልኩ እንደማያቋርጥ ለማስረዳትና ተስፋ ለማስቆረጥ ፤ “እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው?” አለው። እጁንም ደግሞ ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዘርግቶ ፤ “እነሆ እናቴና ወንድሞቼ ፤ በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነውና” አለ። ማቴ 12፡46-48 ፡፡

   የአንደምታ ተርጓሚዎችም ይህኑኑ ቃል ሲያፍታቱት አንድም በጊዜ ግብሯ ንጉሥና ንግሥት የሚገኙበትን ሰዓት ጠይቆ መምጣት ይገባታልና ሲል ነው ፡፡ አንድም ከአክብሮተ አብ ወእም ፣ አክብሮተ እግዚአብሔር እንዲበልጥ ለማጠየቅ ፤ አንድም ከጉባኤ መካከል መነሣት ይገባል ብለው አብነት ወይመ ምሳሌ እንዳያደርጉበት ነው ፡፡

   Delete
  19. @ምእመን You made it very clear you don't want any kind of criticism but want to live in a your own bubble. Which I respect but I don't agree with.It shows inferiority and lack of confidence in your belief. I expect this from our older generation but whether we like it or not, we'll have doubters; especially in this 21st century. The sooner we face the challenge, the better the outcome will be. I'm open to anyone who's willing to challenge my orthodox faith because our faith shall exceed any doubts. I don't have a blind faith. I strongly believe in faith with reason which leads to truth. My friend, you won't solve anything by run away from problems. It amazes me how we orthodox believers became so paranoid whenever anyone disagrees with anything we say. It shows from your previous comment. You've already presumingly labeled me "Lutheran" just because I don't follow your lead like a sheep even though I testified my belief. It's fruitless to argue ignorance. Maybe it's a misinterpretation of my comments due to language barrier; well in that case yekerta

   Good day

   Delete
  20. ለ ewnt
   1. You've already presumingly labeled me "Lutheran"
   በእዚህ አስተያየትህ ተሳስተሃል ፡፡ ሰዎች በሐዋርያት ስም ለማስተማር የሚፈልጉት የሉተርን የሃይማኖት ትምህርት ነው አልኩ እንጅ ፣ ስለ አንተ እምነት አንድም ቦታ ላይ አስመልክቼ አልጻፍኩም ፡፡ ብቻ ከዚህ ቃልህ ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም የሚሉትን እንዳይሆን ፈራሁ ፡፡ ሳልጠይቅህ የኦርቶዶክሰ አማኝ ነኝ ብለህ ስላልከኝ ፣ ቃልህን አምኜ አመለካከቴን አካፈልኩህ ፡፡ እንደ አባባልህ ቢሆን ለመወያየት ፣ ስለ ሃይማኖትህና እምነትህ ለመከራከር ፈቃድ አለኝ አልክ እንጅ ፣ በሚቀርቡልን ጽሁፎች ላይ ፣ አንድም ጊዜ አቋምክን አላስነበብከንም ፡፡ የማልክደው ከዚህ ቀደም ከኔ ጋር በነገረ ማርያም ላይ ተወያይተናል ፡፡ ያም ቢሆን አንተ በግብጾች መጽሐፍ ፣ እኔ ደግሞ የአገራችንን አባቶች መጽሐፍ ስለምናጣቅስ ፣ የኦርቶዶክሰ አማኞች ነን ብለን ራሳችንን ብንገልጽም በልዩነት ቀርተናል ፡፡ አሁን ደግሞ ለምሳሌ እንኳን እንዲጠቀስ በጸጋ ጽሁፍ ላይ ያለህን አቋም አላስነበብከንም ፡፡ እኔ ግን ያቀረበልን ሃሳብ ትክክል አለመሆኑን ማረጋገጫ እየጠቀስኩ ተከራከርኩ ፡፡ የአንተ ግን ያን በተመለከተ ሳይሆን ፣ ለእኔ የወዳጅ ምክር በመስጠት ላይ ያተኰረ መስሎኛል ፡፡

   2. It very clear you don't want any kind of criticism…. It shows inferiority and lack of confidence in your belief.
   ይኸንንም ካልተቀየምከኝ ሁለተኛው ስህተትህ ነው የምለው ፡፡ በችግር ምክንያት በተለያየ ስም ሆነ እንጅ ፣ ለአለፈው አንድ ዓመት የጻፍኳቸውን መለስ ብለህ ፈትሻቸው ፡፡ ምናልባትም ስለ እኔ ምንነት ያስረዱህ ይሆናል ፡፡ አደባባይ ወይም ሸንጐ ተቀምጠን በሥርዓቱ ተከራክረን ፍርድ እያስፈረድን አልቋጨነውም እንጅ ፣ ለእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያናችንን ትምህርት ለተመለከተ ጽሁፍ ሁሉ በመጽሐፍ ቅዱስ የተረጋገጠ መልስ ሰጥቼበታለሁ ፡፡ አሁንም እንኳን እያደረግሁ ያለሁት ምስክር ነው ፡፡ እናስ የመፍራትና በሃይማኖቴ ያለመተማመን ያልከው ምኑን ነው ? የተጻፈውን ሁሉ እሺ ፣ ልክ ነው እያልኩ ፣ እንደወረደ መቀበልን ነው ትክክል አቋም የምትልልኝ ?

   3. I'm open to anyone who's willing to challenge my orthodox faith
   ይኸንን አቋምህን እኔም እጋርሃለሁ ፡፡

   4. I strongly believe in faith with reason which leads to truth.
   ይኸኛውም ሦስተኛ ስህተትህ ነው ፤ ምክንያቱም ሃይማኖት በእምነት ሆነህ የምትቀበለው ነው እንጅ ፤ ምክንያት እየመረመርክና እያረጋገጥህ ንብረትህ የምታደርገው አይደለም ፡፡ በቀላሉ ከላይ የጠቀስኩትን ምሥጢረ ሥላሴ በየትኛውም ስልትና ሰው ሠራሽ ሂሳብ አታሳምነኝም ፡፡ ሌላውም ደግሞ ባይገጥምም የሆነ ምክንያት የማያቀርብልህ ፣ አስተያየት ሰጭ ያለመኖሩ ነው ፡፡ ሌሎች ቤተ እምነቶች የሚያነሱትን ጥያቄዎችና የሚያቀርቡትን ምክንያቶች ጠቅሼ ከማስተጋባላቸው ፣ ብወቀስበትም አንድ የራሴን የአእምሮ ጨዋታ ላቅርብልህ (እምነትህ ወይም ቤተ ክርስቲያን ያስተማረችህ ነው እንዳትለኝ አደራ)፡፡ እንቆቅልሽ መሥራትና መፍታት ደስ ስለሚለኝ ለጨዋታ እንዲሆነን ነው ፡፡

   የማወሳልህ ታሪክ በዘፍጥረት በመጀመሪያ ሦስት ምዕራፎች ውስጥ የቀረበ ነውና ቁጥርና ምዕራፍ አለመጠቀሱ ብዙ አያስቸግርህም ፡፡
   እግዚአብሔር ሰውን ከምድር አፈር በመልኩና ምሳሌው አድርጎ አበጀው ፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ። ከዛ በኋላም ፣ ብዙ ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ የየብስን ፣ የሰማይንና የባህርን እንስሶች ሁሉ ግዙአቸው በማለት ባረካቸው ።

   እግዚአብሔር አምላክም በምሥራቅ በዔድን ገነትን ተከለ ፤ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ የፈጠረውን ሰው ከዚያው አኖረው። ፡፡ በመቀጠል ደግሞ የሚከተለውን ትእዛዝ ሰጠው “ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህ።” አለው ፡፡ እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን ስለ አንድ ዛፍ መከልከል ቢናገርም ፣ ወረድ ብሎ ስለ ሁለተኛዋ የዛፍ ፍሬ ስለሚገልጽ ፤ በቁጥር እንዳይበላ የተከለከለው ከሁለት የዛፎች ፍሬ ነው ፡፡ አንደኛዋ ክፉንና መልካምን የምታስለይ (የበሏት) ስትሆን ፣ ሌላዋ ደግሞ ሰውን ሕያው አድርጋ የምታኖረዋ ናት ፡፡

   እንግዲህ በዚህ መመሪያ መሠረት የሰው ልጅ ባይሳሳት ኑሮ ምናልባትም እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ እኒያን ሁለት ፍሬዎች እንዳይወድቁ እየጠበቀ ፣ እየኮተኮተና እያረመ ከእንስሳቱና ከአራዊቱ ጋር እየተጋፋ ይኖር ነበር ማለት ነው ፡፡ እንደ ትእዛዙ ቢኖር ፣ ማሰብና መጨነቅ ፣ መራብና መጠማት ፣ መታመምና መሞት ፣ ቤት መሥራት ፣ ልብስ መልበስ ፣ መፈላሰፍም ሆነ መመራመር ….. አይኖርም ነበር ያሰኛል ፡፡

   የእባብና የሴቲቱ ውይይትን ደግሞ ልቀጥል ነውና አስተውልልኝ ፡፡
   ሴቲቱም ለእባቡ በገነት ካለው ከዛፍ ፍሬ እንበላለን ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ ፤ አትንኩትም ብሎናል አለችው ፡፡

   እባብም መልሶ ሲመክራት ፣ ሞትንስ አትሞቱም፤ ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው አላቸው ። በምክሩም ተመርተው ፣ አዳምና ሴት ከፍሬዎቹ በሉ የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ፥ ዕራቁታቸውንም እንደ ሆኑ አወቁ ፡፡ እያለ ታሪኩ ይቀጥላል ፡፡
   ክፍል ሁለት ይቀጥላል

   Delete
  21. ክእግዚአብሔር አምላክም እንደበደሉት ስለተረዳ የሚከተለውን ወሰነ ፡፡ ደግሞ አዳም ከሕይወት ዛፍ ወስዶ እንዳይበላ፥ ለዘላለምም ሕያው ሆኖ እንዳይኖር ፤ ከዔድን ገነት አስወጣው፥ የተገኘባትን መሬት ያርስ ዘንድ (ጥረህ ግረህ ብላ) አዘዘው። ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔድን ገነት ምሥራቅ አስቀመጠ። ይላል ፡፡

   ከዚህ መግለጫ በመነሳት የሚሰጠው መደምደሚያ፡-
   - ሰይጣን ሴትን እንደመከራት ከበሉ በኋላ ዓይኖቻቸው ተከፍተዋል ማስረጃ እራቁታቸውን መሆናቸውንም አወቁ ይላልና
   - በበላችሁ ቀን አትሞቱም እንዳላቸው ፣ አዳም የሞተው ከዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ ነው (ዘፍ 5፡5)
   - እንደ እግዚአብሔር መልካምንና ክፉን የምታውቁ ትሆናላችሁ ባላቸው መሠረት ፣ ሰዎች ጥበበኛና ተመራማሪ ፣ ክፉንና ደጉን የሚለዩ ሆነዋል (እግዚአብሔርም ይህንኑ መስክሯል 3፡22)
   - እንደ እግዚአብሔር ትሆናላችሁ ባላቸው መሠረት ፣ መንገዱ ረጅምና ውስብስብ ይሁን እንጅ የሰው ልጅ በጌታችን በኩል ለዙፋኑ በቅቷል (እግዚአብሔርም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ብሏልና 3፡22)
   - ስንፍና ይዞት ፣ ሳይበላ ስለዘገየ ወይም ሆዱ ጠግቦ ስላልቻለ አመለጠው እንጅ ፣ ቀደም ብሎ ከሁለቱም ፍሬዎች መብላት ቢችል ፣ ወይንም እግዚአብሔር ዝም ብሎ መንገዷን ሳያስጠብቅ ተራግሞ ተመልሶ ቢሆን ኖሮ ፣ አዳም ከሌላኛዋም ፍሬ በመብላት ለዘላለም ሕያው ይሆን ነበር ማለት ነው ፡፡ የሰይጣንም ምክር ሙሉ ለሙሉ እውነት ሊሆን ይችል ነበር ማለት ነው ፡፡

   ስለዚነህ ሁሉ ተጨባጭ ምክንያቶች ሰይጣን እውነተኛና ፣ ሰዎች አሁን ለደረሱበት ትልቅ ባለውለታ ነው የሚልህ ሰው ቢመጣ እንደ ቃልህ (faith with reason) ምን መልስ ትሰጠዋለህ ?

   5. you won't solve anything by run away from problems.
   ይህም ከላይ ስለገለጽኩልህ ፣ ለእኔ የጻፍከው አልመሰለኝም ፡፡ ምክንያቱም ለሚያነሱት ሁሉ መልስ ሰጠሁ እንጅ አንገት ደፍቼ ፣ ሸሽቼ አላውቅም ፡፡ ይህ እንዳያጋጥመኝ ዘወትር የማመልከው አምላክ ይረዳኛል ፤ አልተለየኝም ፡፡ ምንም ትምህርትና ዕውቀት የሌለውን ተራ ምእመን ከሊቃውንት ተራ አስገብቶ ይኸው ያታግለኛል ፡፡

   በቃላት አጠቃቀሜ ካስቀየምኩህ በጣም ይቅርታ ፤ ፈልጌው አይደለም
   ሰላም ሁንልኝ

   Delete
  22. @ምእመን ..It's pretty impressive to constantly write such a long essay to reply to each individual comment. Although I admire your passion to have the decency and patience to put your thoughts forward, I think you should make it short, sweet, and to the point. It's sometimes nerve wrecking for those of us who have to deal with it. Just my brotherly advice.

   With that being said, I'll reply as follows with same numerical order with your previous comment.

   1. The reason I think you're putting forward a preconceived opinion about my faith is because you previously said "በብዙ ቦታ ከሚያስተላልፉት መልዕክት እንዳየሁት ፣ ይህች የሐዋርያቱ የምትል ቋንቋ የሉተርን ትምህርት መጠቅለያ ሆና ነው ያገኘሁዋት ፡፡" why is there a need to write this unnecessary comment? Do you just like to throw words out hoping to hit a home run?

   2. Dude I'm just saying we as a church should embrace criticism because it will give us a chance to have a discussions and eventually lead a reasonable human being to decide which is true and which is false. It also diminishes our weak spots for heretics to attack us. I don't mean anything like a diatribe.

   3. "ይኸኛውም ሦስተኛ ስህተትህ ነው ፤ ምክንያቱም ሃይማኖት በእምነት ሆነህ የምትቀበለው ነው እንጅ ፤ ምክንያት እየመረመርክና እያረጋገጥህ ንብረትህ የምታደርገው አይደለም ፡፡"
   You twist and misinterpret everything I write. Maybe it's because you don't comprehend the English language very well. A lot of times you make valid points but it’s mostly meaningless because you make arguments based on something I didn't write. Mostly straw man arguments. There is a difference between reason and logic. The thought you put forward deals with LOGIC. There is a big difference between the two. Reason never goes against faith. But Logic and faith collide and intercept at some point. By the way, I have never read the genesis story as you put it. "በቁጥር እንዳይበላ የተከለከለው ከሁለት የዛፎች ፍሬ ነው ፡፡" what second tree are you talking about? Am I missing something?

   “የማልክደው ከዚህ ቀደም ከኔ ጋር በነገረ ማርያም ላይ ተወያይተናል ፡፡ ያም ቢሆን አንተ በግብጾች መጽሐፍ ፣ እኔ ደግሞ የአገራችንን አባቶች መጽሐፍ ስለምናጣቅስ ፣ የኦርቶዶክሰ አማኞች ነን ብለን ራሳችንን ብንገልጽም በልዩነት ቀርተናል” You actually came forward. You were the anonymous that kept saying “ ante ye gebsochin, ena degmo ye hagerachinin”. Sorry but that’s just lame. You quote aba heryaqos, yohanes afework, atnatiwos and you blame me for quoting “unethiopian” fathers. That was so double standard. Since when did aba heryaqos, yohanes afework, atnatiwos get Ethiopian passport? The churches these same fathers you mentioned all adhere to (Coptic, Constantinople) say the Holy Spirit sanctified the Virgin. Although this is off topic I had to put it since I know you now
   Delete
  23. ለewnt
   በትእዛዝህ መሠረት የተሰናዱ አጫጭር መልሶቼ ፡፡ ተራ ቁጥሩን የጠበቀ ነው ፡፡
   1. ሰዎች ሐዋርያት ሐዋርያት የሚሉትን ሰምተህ ፣ ዓላማቸውን ሳትረዳ ያስተጋባኸው ስለመሰለኝ እንድታውቅባቸው መረጃ ለማካፈል ስለፈለግሁ ነው ፡፡
   2. ሁለተኛው ተስተካክሎ ስለቀረበ ማለት የፈለግኸው ገብቶኛል ፡፡ ችግር የለኝም

   3. እንደናንተ በእንግሊዝኛ አራቅቄ መጻፍ ባልችልም ፣ አንብቤ መረዳት እችላለሁ ፡፡ እንደ አደግሁበት አማርኛ ግን ውብ የሚሆነልኝ የለም ፡፡ Reason አንድን ነገር እውነት ሊያደርግ የሚችል ምክንያት ፣ ለመከራከሪያና ለመከላከያ የሚቀርብ ሃሳብ ነው ፡፡ ከመዝገበ ቃላት ያገኘሁትን ላስቀምጥ ነበር ፣ እንዳይበዛብህ ፈራሁ ፡፡

   በተረፈ የዘፍጥረት የዛፎች ቁጥር በቤተ ክርስቲያን ትምህርት አንድ ዛፍ ተብለን ነው የምንማረው ፡፡ መጽሐፍም እንዲያ ይላል ዘፍ 3፡6፣ 3፡11፣ 3፡17 ፡፡ ለመደዴ አንባቢ ግን ሁለተኛዋን ዛፍ በዘፍጥረት 3፡22 ላይ ያገኛታል ፡፡ ምክንያቱም ከዛው ከገነት መሃል የነበረችና ሕይወት የምትሰጠዋ ርሷ ስለነበረች ነው፡፡ አዳም የበላው እንደተጠቀሰው ክፉንና መልካምን ከምታሳውቀው ብቻ ነው ፡፡

   ሰላም ሁንልኝ

   Delete
 27. ክርስቶስ ብቸኛው እና ተወዳዳሪ የሊለው የህይወት ውሃ ምንጭ ነው፡፡ በእርሱ ከሲኦል እስር ተፈትተናል፡፡ በእርሱ ከሞት ወደ ሕይወት ተመልሰናል፡፡ በእርሱ በበደላችንን ሙታን በነበርን ጊዜ የዘላላም ሕይወትን አግኝተናል፡፡ ይህ ነው የህይወት ውሀ ምንጭነት ትርጓሜ፡፡ እመቤታችንን የህይወት ዉሀ ምንጭ ብሎ መጥራት ታላቅ ኑፋቄ ነው፡፡ ለእመቤታችን የሚገባት ቅዱስ ኤፍሬም በረቡዕ ውዳሴ ማርያም ላይ የተናገረው ነው፡፡ “ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑሻል ስግደት ግን ካንቺ ለተወለደው ነው፡፡ ከፍ ከፍም ያደርጉታል፡፡”

  ReplyDelete
  Replies
  1. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 23, 2013 at 8:13 AM

   Geta yebarkehe

   Delete
 28. This is what I get POP Shinoda III book of Question & answer. I think every one can understand what
  Question
  I read that one of the Plymouth Brethren had made an
  attack which was very insulting, upon the title given to the Virgin Mary in the Agpia (the prayer book of the Coptic Church), of the 'gateway to life' or the 'gateway to heaven'.
  He based his argument on the fact that the Lord Christ is
  the only gate that leads to life,, according to what the Lord
  Christ said of Himself: "the gate for the sheep." (John 10:9-10). How should one reply to this?

  Answer:
  Calling the Lord Christ a 'gate' has one meaning, and
  calling St. Mary a 'gate' or 'gateway', has a different one.
  The Lord Christ gave us many of His own titles which have
  various meanings. For example He said: "you are the light of the world " yet He also said of Himself: "I am the light of the world " But He, of course, is the truest light of all, whilst the light that we have, is derived from His. In the same way, theVirgin being a 'gate' or 'gateway' does not prevent Christ's being the 'gate' for the sheep.
  The name 'gate' or 'gateway' has also been applied to the
  Church, to prayer, to faith, to preaching the gospel and to all spiritual means of reaching God.
  None of this, however, has detracted anything from Christ or His saving work. These titles, as we will see, are mentioned in the Bible, so they accord with the biblical truth which they defend.
  The first church in the world to be consecrated was called
  the 'gate of heaven'.
  Jacob, the Patriarch, said of the place in which he saw a ladder leading up to heaven from the earth: "How awesome is this place! This is none other than the house of God; this is the gate of heaven. " (Gen. 28:17), and he called that place 'Bethel'
  which means 'house of God'.
  Does the Church being the 'gate of heaven' prevent Christ from also being a gate, ie. a way in, or a way leading to heaven?
  The Church is a gate leading to Christ, and Christ is a gate leading to salvation and to the Father. The name is the same but the meaning is different.

  ReplyDelete
 29. PoP shinoda part II
  The Virgin Mary, however, can also be regarded as a
  gateway, because she connected Christ to us through the
  body, and she was referred to as a 'gate' in the Book of Ezekiel, where it says that the gate of the east has been
  shut, and "It is to remain shut because the Lord, the God of Israel, has entered through it. " (Ez. 44:3)
  Prayer, too, has been called a gateway to heaven, because
  heaven is opened by prayer.
  The Virgin Mary is not merely a gateway to heaven, but is
  in fact a kind of heaven herself.
  Heaven is, after all, the dwelling place of God, and the Virgin became a dwelling place for God when He grew within her womb for nine months. Thus she became a 'heaven' for Him.
  This is why the Church calls her the 'second heaven'. Because the Church has become a house of God, it too can be likened to heaven. Therefore we say in one of our prayers: When we stand in your holy temple (ie. in church), we consider ourselves to be standing in heaven.
  The Bible mentions that there are gates which lead to heaven.
  For example it says: " Blessed are those who do His
  commandments, that they may have the right to the tree of life, and may enter through the gates into the city." (Rev. 22:14)
  But does the existence of these gates prevent Christ from being a gate too?
  All spiritual means can be gateways, provided they connect
  us to Christ, who is the only gate which leads to salvation through His blood The Lord spoke of this matter when He said: "Because narrow is the gate and difficult is the way which leads to life, and there are few who find it." (Matt. 7:14)
  Do the Lord's words about the narrow gate prevent Him
  from being a gate too?
  " The letter kills but the Spirit gives life. " (1 Cor. 3:6) We
  must always remember to understand the words of the Lord,
  and prayers of the Church, for their spiritual and not simply their literal meaning, as "expressing spiritual truths in spiritual words. " (2 Cor. 2:13)
  Prayer and faith are both gates that can lead to God.
  Saul and Barnabas came to Antioch and called together the
  Church: " Now when they had come and gathered the church
  together, they reported all that God had done with them, and that He had opened the door of faith to the Gentiles. " (Acts
  14:27) It was this 'door of faith' that was their means to
  salvation, because it brought them into contact with Christ.
  Preaching can also be a gateway leading to salvation,
  because it leads to faith, and faith then leads to Christ.
  It was probably this gate which the Lord had in mind when He said to the angel of the church of Philadelphia "I know your works. See, I have set before you an open door, and no one can shut it; " (Rev. 3:8)So if prayer, faith, preaching the gospel, the Church and the
  Virgin Mary can all be gateways leading to Christ, then
  "Blessed are those who... may go through the gates into the city" which is of course, heaven. (Rev. 22:14)
  The Virgin Mary was the gate through which Christ came
  in order to save the world. Who was Christ?
  1. Christ was the Messiah, and He was Life, according to what He said of Himself: "I am the Resurrection and the life. " (John 11:25), and "I am the way, the truth and the life. " (John 14:6).
  So we can see how St. Mary can be called a 'gateway to
  life", by virtue of her being the very gate through which the Messiah - who is life, came into the world.
  2. Christ is also the Redeemer and 'our salvation'. We sing in the psalm: "The Lord is my strength and my song; And He has become my salvation. " (Ps. 118:14) So if Christ was and is a 'salvation' to the world, then there is nothing strange in our calling the gateway through which He came, that is the Virgin. Mary the 'gate of salvation'!

  ReplyDelete
 30. የቅዱስ ኤፍሬም ውዳሴ ማርያምን መከራከሪያ አድርጋችሁ ላቀረባችሁ ወገኖች በሙሉ ፡-

  የቅዱስ ኤፍሬም ውዳሴ ማርያም ጸሎትን ምንነት ሳታውቁ ወይንም ስለምን እንደተጻፈ የመልዕክቱን ዋና ዓላማ ሳትረዱ ፣ የርሱን መልእክትን በመጥቀስ ለመከራከር እየሞከራችሁ ነው ፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ውዳሴ ማርያምን የጻፈው ፣ ስሙ ራሱ እንደሚያመለክተን አምላካችንን ስለወለደችልንና ከአዳማዊው በደል ነጻ ለመውጣታችን ምክንያት ስለሆነች ለቅድስት ድንግል ማርያም ምስጋናዋን ለማቅረብ ነው ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በዋናነት አማላጅነቷንም ለማስተማር ነው ፡፡

  የአምላክ እናት ስለመሆኗ ሲገልጽ ፣ ማንም ሊነካው ፣ ሊታቀፈው የማይችለውንና የማይገባውን አምላኳን በማህጸኗ የማሳደሯ ታላቅ ምሥጢርነትን እየለፈፈ ልጅዋን እንድትለምንልን ይማጸናል ፡፡ ይኸውም ከመጀመሪያው የሰኞ ጸሎት አንስቶ በእያንዳንዱ አረፍተ ነገር ማብቂያ ፣ በየዕለቱ ባሰማውና በምናሰማው ጸሎት “ሰአሊ ለነ ቅድስት” ትርጉም “ቅድስት ሆይ ለምኝልን” እያለ ይወተውታል ፡፡ ለመከራከሪያ ተቆርጦ የተመረጠው ቃል ሙሉ አረፍተ ነገር ደግሞ ከዚህ ቀጥሎ ቀርቧል ፡፡

  የረቡዕ
  ኲሉ ትውልድ ያስተበፅዑኪ ዐቢያተ ለኪ ለባሕቲትኪ ኦ እግዝእትነ ወላዲተ አምላክ ፡፡ ተነበዩ ላዕሌኪ ዐቢያተ ወመንክራተ ኦ ሀገረ እግዚአብሔር እስመ ኮንኪ አንቲ ማኀደረ ለፍሡሐን ኲሎሙ ነገሥተ ምድር የሐውሩ በብርሃንኪ ወአሕዛብኒ በጸዳልኪ ኦ ማርያም ኲሉ ትውልድ ያስተበፅዑኪ ወይሰግዱ ለዘተወልደ እምኔኪ ወየዐብይዎ ፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት ፡፡

  ትርጉም ፡፡ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ ትውልድ ሁሉ አንችን ያመሰግኑሻል ፡፡ የእግዚአብሔር ሀገር (ከተማ) ሆይ ነቢያት ድንቅ ድንቅ ነገርን ተናገሩልሽ ደስ የተሰኙ የጻድቃን ማደሪያ ሆነሻልና የምድር ነገሥታት ሁሉ በብርሃንሽ ይሄዳሉ ፡፡ ሕዝቡም ሠራዊቶቻቸውም በብርሃንሽ ይሄዳሉ ፤ ማርያም ሆይ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑሻል ፡፡ ካንቺ ለተወለደውም ይሰግዱለታል ፤ ያገኑታልም ፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን ፡፡

  የሰኞ ፡
  ለምሳሌም "ጌታ ልቡ ያዘነና የተከዘ አዳምን ነፃ ያወጣውና ወደ ቀድሞ ቦታው ይመልሰው ዘንድ ወደደ ቅድስት ሆይ ለምኝልን" በማለት ይጀምርና ቅድስ ሆይ ለምኝልን ፤ ቅድስ ሆይ ለምኝልን እያለ በየአንቀጹ እንድታማልድ ይጠይቃል ፡፡

  የማክሰኞንም አለፍ አለፍ ብዬ ለመጥቀስ ያህል
  የመመኪያችን ዘውድ የድኀነታችን መጀመሪያ የንጽሕናችንም መሠረት እኛን ስለማዳን ሰው የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል በወለደችልን በድንግል ማርያም ተገኘልን ፤ ሰው ከሆነ በኋላም ፍጹም አምላክ ነው ፤ ስለዚህም በድንግልና ወለደችው ፡፡ ድንቅ የሆነ የመውለድዋ ችሎታ የማይመረመር ሊነገር የማይቻል ነው ፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን ፡፡

  በእርሱ ፈቃድ በአባቱ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ መጥቶ አዳነን ፡፡ በድንግልና ፍጽምት የሆንሽ ማርያም ሆይ የድንግልናሽ ምሥጋናና ክብር ታላቅ ነው ፡፡ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ቢሆን ባለሟልነትን አግኝተሻልና ያዕቆብ ከምድር እስከ ሰማይ ደርሳ የእግዚአብሔር መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ያያት መሰላል አንቺ ነሽ ፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን ፡፡

  ሙሴ በነገደ እሳት ሳትቃጠል ያያተ ዕፅ አንቺ ነሽ ፡፡ … ቅድስት ሆይ ለምኝልን

  …. የሕያዋን (የጻድቃን) ሁሉ እናታቸው ሆይ ደስ ይበልሽ ፡፡ ትለምኝልን ዘንድ ወደ አንቺ እናንጋጥጣለን ፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን ፡፡

  የድንግልን ገናንነቷን ሊናገሩት አይቻልም ፡፡ ጌታ መርጧታልና ፤ … እርሱ መጥቶ አደረባት ፡፡ … እርሱን በድንግልና ወለደችው ፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን

  እንደ ንጹሕ ጫፍ ሆንሽ የሃይማኖተ መገኛ ነሽ የቀናች የቅዱሳን አባቶቻችን ሃይማኖታቸው ነሽ ፡፡ … ቅድስት ሆይ ለምኝልን ፡፡

  ቃል እናቱ ንጽሕት ድንግል ሆይ ስለ አንቺ የሚነገረውን ነገር መናገር የሚቻለው ምን አንደበት ነው ፡፡ ኪሩቤል ለሚሸከሙት ንጉሥ ዙፋኑ (ማደሪያው) ሆንሽ የተከበርሽ ሆይ እናመሰግንሻለን ፡፡ … ስምሽን ለልጅ ልጅ እንጠራለን ፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን ፡፡

  ባጠቃላይ የዚህን አባት በየዕለት የሚያቀርበውን የሳምነቱን ጸሎት ስንመለከት ቅድስት ሆይ ለምኝልን የሚል ማሳረጊያ ቃል ያላስገባበት አንድም አንቀጽ አይገኝም ፡፡ ስለዚሀም እናንተው የመከራከሪያ ቃል የመረጣችሁበትን አንቀጽ እንኳን ቃሉን በሙሉ በእምነት ከተቀበላችሁ ፣ ሌላው ቢቀር በአማላጅነቷ ላይ ጥያቄ ማንሳት አይገባችሁም ነበር ለማለት ነው ፡፡ የአምልኮ ስግደት ፣ ከእርሷ ይልቅ በአምላክነቱ የሚገባው ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሆነ መከራከሪያ አጀንዳ ሆኖ አይቀርብምና እንስማማለን ፡፡

  ReplyDelete
 31. በአብዛኛው መጽሐፍ ቅዱስ በጣም ግልጽ በሆኑና ምንም ፍቺ በማይፈልጉ ምንባቦች የተሞላ ነው። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ለመረዳት ጥረት የሚጠይቁ ክፍሎች ደግሞ ያሉበት መሆኑ ግልጽ ነው። ይህ ማለት፥የእግዚአብሔርንን እውነት እንደ እግዚአብሔር ቃል ብቻ መቀበል ያስፈልጋል፡፡አዲስ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚቀጠልና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እኩያ ሥልጣን ያለው ቃል የለም፤ አይኖርምም።ግልጽ ያልሆነው ጥቅስ ወይም ክፍል ያንን ጉዳይ በተመለከተ ግልጽ ሆነው በተጻፉት ጥቅሶች መብራራት አለበት።አዲስ ኪዳን በብሉይ ሳይሆን ብሉይ ኪዳን በአዲስ ማብራሪያነት መፈታት አለበት።ታሪካዊ የሆኑት የማይደጋገሙ ክስተቶች ያንን በሚመለከቱ ትምህርታዊ በሆኑ ክፍሎች መፈታት አለባቸው።በጥቅሶች ሰንሰለት ተመሳሳይ ቃል በውስጣቸው ስለተገኘ ብቻ ተመሳሳይ አሳብ የሌላቸው ጥቅሶችና ምንባቦች ተደጋግፈው መቆም ሲያቅታቸው ተጣብቀው እንዲቆሙ መደረግ የለባቸውም።...http://www.ethiopianchurch.org/essay1/152-%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%8D%88%E1%89%B3%E1%89%B5-%E1%88%98%E1%88%AD%E1%88%86%E1%8B%8E%E1%89%BD.html

  ReplyDelete
 32. መጽሐፍ ቅዱስ ራሱን ይተረጉማል። በመጽሐፍ ቅዱስ አንድ ጥቅስ ወይም አንድ ክፍል ትርጉሙ ግልጽ ካልሆነ ወይም ጥያቄ የሚፈጥር ከሆነ በሌሎች ግልጽ በሆኑ፣ በማያሻሙ ጥቅሶችና ክፍሎች አንጻር መተርጎም አለበት። ይህም የሚሆነው የመጽሐፍ ቅዱስ ደራሲ አንድ አምላክ በመሆኑና በውስጡም የሚገኘው መንፈስና ሐሳብ አንድ ስለሆነ ቃሉ አንድነት እንጂ እርስ በርስ የመቃረን መንፈስ ስሌለው ነው። ቃሉን ወይም አረፍተ ነገሩን በቅደም ተከተሉና በአገባቡ መሠረት መተርጎም። አንድ ቃል ወይም ጥቅስ ከመተርጎም በፊት የሚቀድሙትንና የሚከተሉትን ጥቅሶችና አንቀጾች ማንበብና ይዞታቸውን ማወቅ ጥቅሱን ለመተርጎም አስፈላጊ ነው። አንዳንዴም በጥቅሶችና በአንቀጾች ሳንወሰን ምዕራፎችንና መጽሐፉን በሙሉ በማንበብ መገንዘብ አስፈላጊ ነው። አንድ ጥቅስ የሚቆመው ብቻውን ሳይሆን በቅደም ተከተል ካሉ ጥቅሶች፣ አንቀጾችና ምዕራፎች ጋር በሐሳብ ተገናኝቶ ስለሆነ አገባቡን በቅርብም በስፋትም መመርመር ያስፈልጋል። አዚህ ላይ ማስታወስ የሚገባን አሁን በመጽሐፍ ቅዱሳችን የምናየው የምዕራፍና የቁጥር ክፍፍል መጀመሪያ ሲጻፍ እንዳልነበረ ነው። ብሉይ ኪዳን በምዕራፍና በቁጥር የተከፈለው በ1445 ዓ.ም ሲሆን አዲስ ኪዳን ደግሞ የተከፈለው በ1551 ዓ.ም ነው። ስለዚህ ከጊዜ በኋላ በተደረገው በምዕራፍና በቁጥር ክፍፍል ሳንገደብ ሐሳቡን ለማግኘት የሚቀድመውንም የሚከተለውንም ማንበብ ያስፈልገናል።የቃሉን ወይም የአረፍተ ነገሩን የመጀመሪያ ትርጉም መገንዘብ። የቃላት ትርጉም አብዛኛውን ጊዜ ከዘመኑና ከአካባቢው ጋር የተገናኘ ነው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል መጀመሪያ በተነገረ ወይም በተጻፈ ጊዜ ለአድማጮቹና ለአንባቢያን ምን ትርጉም ሲሰጥ ነበረ ብሎ መጠየቅ አግባብ ያለው ነው። ስለዚህ የቃሉን ትርጉም በመረዳት ለራሳችን ያለውን መልእክት ከመውሰዳችን በፊት በተቻለ መጠን የተጻፈበትን ሁኔታና የመጀመሪያ ትርጉም ማወቅ አስፈላጊ ነው። ቃሉን ግልጽ በሆነ መሠረታዊ ትርጉሙ መረዳትና መተርጎም። ከላይ እንደገለጽነው የእግዚአብሔር ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ቃሉን ሲጽፉ ቋንቋቸውን ተጠቅመዋል፤ ቋንቋ ደግሞ የሰዋሰው ሕግና አገባብ አለው። ከዚህ የተነሣ አንድ ሰው የቃሉን ትርጓሜ ለማግኘት የተደበቀ ወይም የተሰወረ ነገር ከራሱ ሳይፈጥር በቀጥታ “ይህ የማነበው ቃል ምን ይላል?” ብሎ በመጠየቅ ግልጽ የሆነ ትርጓሜውን መውሰድ አለበት።

  ReplyDelete
 33. በቅድሚያ የእግዚአብሄር ቸርነት የእመቤታችን አማላጅነት የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት የጻድቃን ጸሎት አይለያችሁ።የምትሉት ሁሉ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከምታስተምረው ትምህርት እና ቤተክርስቲያናችን ከተቀበለችው እምነት ጋር በፍጹም የተቃረነ ነው።ስለዚህ ከወዴት ናችሁ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. የተሰቀለው ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ ነው !January 22, 2013 at 7:37 PM

   ስለዚህ ከወዴት ናችሁ?

   ከ ኢየሱስ ክርስቶስ!!!

   Delete